አርእስተ ዜና
መንግስት የትይዩ የውጭ ምንዛሬ ለማስፋት እየሰሩ ባሉ ህገ ወጥ ድርጅቶች ላይ ጠንካራ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን ይቀጥላል- አቶ ማሞ ምህረቱ
Aug 6, 2025 98
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2017(ኢዜአ)፦ መንግስት ከገበያ ባፈነገጠ ሁኔታ የትይዩ የውጭ ምንዛሬ እንዲስፋፋ በሚሰሩ ህገ-ወጥ ድርጅቶች ላይ ጠንካራ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ገለጹ። በህገ-ወጥ ድርጊቱ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች እንደ አስፈላጊነቱ ለህዝብ ይፋ ይደረጋሉም ብለዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ወቅታዊ የውጭ ምንዛሪ ገበያን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል። አቶ ማሞ ባንኩ በመደበኛነት እያካሄደ ያለውን የውጭ ምንዛሬ ጨረታውን ለመቀጠል መወሰኑንም ገልጸዋል። ባለፈው ዓመት የብሔራዊ የውጭ ምንዛሬ መጠባበቂያ ክምችት በሶስት እጥፍ መጨመሩ እና ይህ መልካም ውጤት በተያዘው በጀት መቀጠሉ እንዲሁም የባንኩ የውጭ ምንዛሬ ፍሰት እና ግኝት ከተጠበቀው በላይ ማደጉ ጨረታው እንዲቀጥል ምክንያት መሆናቸውን አመልክተዋል። ከውጭ ምንዛሬ ገቢው ከፊሉ ለባንኮች መቅረቡ ባንኮች ያላቸውን የውጭ ምንዛሬ ከማሳደግ ባሻገር ዋጋ እና የውጭ ምንዛሬ የማረጋጋት ስራን ለማሳካት እንደሚያግዝ ተናግረዋል። ትናንት በተደረገው የ150 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ 28 ባንኮች በጨረታው መሳተፋቸውን ገልጸው ሁሉም ባንኮች የሚፈልጉትን የውጭ ምንዛሬ ማግኘታቸውንና አንድ ዶላር 138 ብር መሸጡን ጠቁመዋል። ባንኮቹ በጨረታው ያገኙትን ጨምሮ የራሳቸውን ገቢ በመጨመር በቂ የውጭ ምንዛሬ እንደሚያቀርቡ ይጠበቃልም ነው ያሉት። የንግዱ ማህበረሰብ እና የግሉ ዘርፍ ባንኮች በሚያቀርቡትን የውጭ ምንዛሬ እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል። በሌላ በኩል አብዛኞቹ የንግድ ማህበረሰብ አባላት በመደበኛ እና ህጋዊ የውጭ ምንዛሬ ስርዓት ውስጥ የሚሳተፉ ቢሆንም አንዳንዶች በትይዩ የውጭ ምንዛሬ ገበያ ውስጥ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ነው የባንኩ ገዥ ያመለከቱት። በህገ ወጥ ድርጊቱ ላይ የሚሳተፉ የንግዱ ማህበረሰቦች ወደ መደበኛ ስርዓቱ እንዲመለሱ ያሳሰቡ ሲሆን ከድርጊታቸው በማይቆጠቡት ላይ ሀብታቸውን እስከ መውረስ የሚደርስ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቀዋል። ባንኮች ከውጭ ምንዛሬ አቅርቦት ጋር በተገናኘ በንግዱ ማህበረሰብ አባላት ይቀርብባቸው የነበሩ አብዛኞቹ ቅሬታዎች መፈታተቸውን የገለጹት አቶ ማሞ ቀሪ ተግዳሮቶች መፍትሄ እንዲያገኙ እየሰሩ ይገኛል ነው ያሉት። ብሄራዊ ባንክ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ስርዓት ተአማኒነት ሆን ብለው ለመሸርሸር እና የገበያ ዋጋ መዛባትን በማለም እየሰሩ ያሉ በውጭ የሚገኙ ህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሬ አዘዋዋሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን እንደሚቀጥልም አስገንዝበዋል። ባንኩ እንደ አስፈላጊነቱ በዚህ ህገ ወጥ ተግባር ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን ስም ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል። ተቀማጭነታቸውን በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ዱባይ ያደረጉ ከገበያ ባፈነገጠ ሁኔታ የትይዩ ገበያውን ለማስፋት በሚሰሩ ህገወጥ ድርጅቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድም አብራርተዋል። አሳሳች መረጃን ከማሰራጭት ጋር በተያያዘም ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ነቀፌታ አቅርቧል የሚለው መረጃ መሰረተ ቢስ እና ከእውነት የራቀ መሆኑን ነው ያብራሩት። አይኤምኤፍ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ያለው አጠቃላይ እይታ እጅግ አዎንታዊ ነው ያሉት አቶ ማሞ የሚያወጣቸው መረጃዎች እና ሪፖርቶች ይሄን የሚያመላክቱ ናቸው ብለዋል። በውጭ ምንዛሬ ስርዓት እና አጠቃላይ የኢኮኖሚ ሪፎርሙ የተገኙ አዎንዊ ውጤቶች ኢትዮጵያ በትክክለኛ የእድገት ጎዳና ላይ እንደምትገኝ ያሳያሉ ነው ያሉት። በአዲሱ በጀት መጀመሪያ ላይ የታየው አበረታች የውጭ ምንዛሬ ክምችት እድገት በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። አቶ ማሞ ማህበረሰቡ ከሀሰተኛ መረጃዎች እና አሳሳች አሉባልታዎች ራሱን በመጠበቅ መደበኛ የንግድ እንቅስቃሴውን ያለ ምንም ስጋት እንዲያከናውን ጥሪ አቅርበዋል።
ታታሪውን የካሜራ ባለሙያ የዘከረው የስነ-ጽሁፍ ምሽት
Aug 6, 2025 56
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በየወሩ በቋሚነት የሚከናወን ተቋማዊ የስነ ጽሁፍ ምሽት አስጀምሯል። መድረኩ በዛሬው መርሃ ግብሩም ‘’ታታሪነትን ማወደስ” በሚል መሪ ሃሳብ በቅርቡ በድንገተኛ አደጋ ሕይወቱ ያለፈውን የካሜራ ባለሙያ ብዙዓየሁ ብርሃኑን ዘክሯል። በዛሬው የስነ-ጽሁፍ መድረክ የተቋሙ ሰራተኞች በግጥም፣ በወግ እንዲሁም አጫጭር ልብ ወለዶች ታታሪውን የካሜራ ባለሙያ ብዙዓየሁ ብርሃኑን ዘክረዋል።   በመድረኩ የተገኙት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሰይፈ ደርቤ ወርሃዊ የስነ-ጽሁፍ ምሽቱ ተቋማዊ የእርስ በርስ መቀራረብን በማጠናከር ጠንካራ የስራ ባህል ለማጎልበት እንደሚያግዝ ጠቁመዋል። የስነ ጽሁፍ አቅም እያላቸው ዕድሉን ያላገኙ ሰራተኞች ያላቸውን ተሰጥኦ የሚገልጡበት መድረክ እንደሚሆንም ገልጸዋል። የመጀመሪያው መድረክ በሙያውም ሆነ በባህሪው ምስጉንና ታታሪ የነበረውን ብዙዓሁ ብርሃኑን በመዘከር መካሄዱንም አድንቀዋል።   ብዙዓየሁ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት በነበረው የስራ ስምሪት በሙያው የተመሰከረለትና ለሀገር ታላላቅ ስራዎችን ያበረከተ ባለሙያ እንደነበርም አንስተዋል። ታታሪነትን ማወደስ በስራቸው ምስጉን ሰራተኞችን ለመፍጠር ሚናው የጎላ መሆኑን አንስተው፤ ከዚህ አኳያ መድረኩ የብዙአየሁ ጠንካራ የስራ ክህሎት በሌሎች ሰራተኞች መነሳሳትን እንደሚፈጥር ገልጸዋል።   በመድረኩ የሚቀርቡ የስነ ጽሁፍ ስራዎችም ተመርጠው በአንድ መድብል እንዲታተሙ ጥረት እንደሚደረግም ጠቁመዋል። ቀጣዩ የስነ-ጽሁፍ መድረክም በመጪው ነሐሴ ወር መጨረሻ የሚከናወን ይሆናል።
የባህር ዳር ከተማ የኮሪደር ልማት መንግስት ለሰው ተኮር ልማት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው
Aug 6, 2025 63
ባህር ዳር፤ ሐምሌ 30/2017(ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት መንግስት ለሰው ተኮር ልማት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ሲሉ የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ መንገሻ ፈንታው(ዶ/ር) ገለጹ። የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ፣ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ የአማራ ስቴት ዩኒቨርሲቲ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አመራሮችና ሠራተኞች የከተማዋን የመሰረተ ልማት እንቅስቃሴ ዛሬ ጎብኝተዋል። የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታው(ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንደገለጹት መንግስት ከተሞችን ለማዘመንና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ መሰረተ ልማቶችን በስፋት እየገነባ ነው። በባህር ዳር ከተማ ግንባታው እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማትም ከተማዋ ያላትን የተፈጥሮ ጸጋ ለነዋሪዎቿና ለጎብኚዎች የገለጠ መሆኑን ገልጸዋል።   ልማቱ መንግስት ለሰው ተኮር ልማት ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር በማረጋገጥ አርአያነት ያለው ተግባር መሆኑንም ተናግረዋል። የኮሪደር ልማቱ ባህር ዳር ከተማ የቱሪስትና የኢንቨስትመንት መዳረሻነቷን በማሳደግ የህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል። በመሆኑም የኮሙኒኬሽንና የመገናኛ ብዙሃን በከተማዋ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን በአግባቡ በማስተዋወቅ የከተማዋን ገጽታ ከመገንባት ባለፈ የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኚዎችን ለመሳብ በትኩረት እንዲሰሩ አሳስበዋል። የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አስሜ ብርሌ በበኩላቸው የከተማዋን የልማት ሥራዎች ለማስተዋወቅ የተጀመረው ሥራ ቀጣይነት ባለው መልኩ ይከናወናል ብለዋል። ይህም በከተማዋ ስለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ህብረተሰቡ በስፋት ግንዛቤ እንዲኖረው ከማድረግ ባለፈ በቀጣይ ለከተማዋ ልማት የሚያደርገውን ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚያስችል አስረድተዋል። በከተማዋ ግንባታው እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት የከተማ አስተዳደሩ ችግሮችን ተቋቁሞ ልማትን ለማፋጠን ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል። ከኮሪደር ልማቱ በተጨማሪ የባህር ዳር ከተማን የቱሪስት ማዕከል ማድረግ የሚያስችሉ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ምክትል ከንቲባው ጨምረው ገልጸዋል።
በምስራቅ ወለጋ ዞን ቢሎ ቦሼ ወረዳ ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ከ39 በላይ ፕሮጀክቶች ተመረቁ
Aug 6, 2025 58
ጊምቢ፤ ሀምሌ 30/ 2017 (ኢዜአ) ፡-በምስራቅ ወለጋ ዞን ቢሎ ቦሼ ወረዳ ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ከ39 በላይ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቁ። በፕሮጀክቶቹ የምርቃ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት በብልፅግና ፓርቲ የምስራቅ ወለጋ ዞን ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍቃዱ ገመዳ፤ በሁሉም አካባቢዎች ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።   የህዝብን የልማትና የተጠቃሚነት ጥያቄዎች መንግስት በሂደት ምላሽ እየሰጠ መሆኑን አንስተው በቢሎ ቦሼ ወረዳ የተከናወነውም ይሄው መሆኑን ተናግረዋል። በወረዳው ከ109 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የትምህርት ቤትና የመንገድ ግንባታ፣ የመጠጥ ውሃእና የመስኖ ፕሮጀክቶች እና ሌሎችንም ጨምሮ በድምሩ ከ39 በላይ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት በቅተዋል ብለዋል።   በዞኑ የልማት ስራዎች በልዩ ትኩረት መከናወናቸውንና በመከናወን ላይ የሚገኙ እንዳሉም ጠቅሰው ሰላምን አስቀድመን ልማትን አጠናክረን ለሀገራዊ ብፅግና ስኬት እንሰራለን ሲሉ አረጋግጠዋል። የቢሎ ቦሼ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ በየነ ሞረዳ፤ የወረዳው ህዝብ ለልማት ባለው ቁርጠኝነትና በሚያደርገው ተሳትፎ በመታገዝ አስተዳደሩ ስኬታማ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በወረዳው ለተከናወኑት ፕሮጀክቶች ወጪ በማድረግ የመንግስት ሚና ከፍተኛ መሆኑን አስታውሰው የህብረተሰቡ እና የተለያዩ ተቋማትም እገዛ እንዳለበት አንስተዋል።   ከቢሎ ቦሼ ወረዳ ነዋሪዎች መካከል አቶ አብዱልቃዲር ኡስማን እና ወይዘሮ አስናቁ ተካልኝ፤ ፕሮጀክቶቹ በጥራትና በፍጥነት ተጠናቀው ለአገልግሎት በመብቃታቸው ተደስተናል ብለዋል። የተመረቁት የልማት ፕሮጀክቶች ከዚህ በፊት በአካባቢው ይስተዋሉ የነበሩ የአገልግሎት ችግሮችን የፈቱ ስለመሆናቸውም አንስተዋል። በመሆኑም ለልማቱ መሳካት የመንግስት አካላት፣ ተቋማትና ሌሎችም ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል።
የሚታይ

የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የባህር መተላለፊያ የማግኘት መብታቸው ሊከበር ይገባል- ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር)
Aug 6, 2025 146
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2017(ኢዜአ)፦ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ያልተቋረጠ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር መተላለፊያ የማግኘት መብታቸው ሊከበር እንደሚገባ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር) ገለጹ። ሶስተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የባህር በር የሌላቸው በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት ኮንፍረንስ በተርኪሚኒስታን እየተካሄደ ይገኛል። የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር) በኮንፍረንሱ ባደረጉት ንግግር የባህር በር የሌላቸው በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት ቀጥተኛ የባህር በር መተላለፊያ አለማግኘት፣ ከፍተኛ የትራስፖርት ወጪ እና መሰረተ ልማቶች በበቂ ሁኔታ አለመሟላትን ጨምሮ በሌሎች መሰረታዊ ችግሮች እየተፈተኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል። የጂኦ ፖለቲካ ውጥረቶች፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ከፍተኛ የእዳ ጫና ችግሩ ይበልጥ እንዲባባስ ምክንያት መሆናቸውን አመልክተዋል። ኢትዮጵያ የመሬትን 50 በመቶ እና የዓለምን 60 በመቶ የውቅያኖስ ስፍራ የሚሸፍኑት ዓለም አቀፍ የውሃ ሀብቶች የሁሉንም ሀገራት ብልጽግና የማረጋገጥ ትልም እንደሚያሳኩ በጽኑ ታምናለች ብለዋል። የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ያልተቋረጠ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር በር መተላለፊያ የማግኘት መብታቸው ሊከበር እንደሚገባም ነው ሚኒስትሩ የገለጹት። ይህም ከትራንዚት ባለፈ የሀገራት ሁሉን አቀፍ መብት መሆኑን በውል መረዳት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። የሀገራቱ ፍላጎት በማሪታይም የኢኮኖሚ እድሎች ተጠቃሚ መሆን፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የማሪታይም ደህንነት መጠበቅ ጭምር እንደሆነም ገልጸዋል።   የባህር በር መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦች ሙሉ ለሙሉ ሊተገበሩ እንደሚገባ ጠቅሰው ይህም ዘላቂ እና የጋራ ልማትን ለማምጣትና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ቁልፍ መሆኑን አመልክተዋል። ኢትዮጵያ ከዚህ ኮንፍረንስ የባህር በር ማግኘት ላይ የእይታ ለውጥና ዓለም ለጉዳዩ ያለው ቁርጠኝነት ዳግም ይታደስበታል ብላ እንደምትጠብቅ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የሀብት ማሰባሰብ እና አዳዲስ የመፍትሄ ሀሳቦች የሚያመጡ ውጤታማ ትብብሮችን መፍጠር እንደምትፈልግም አብራርተዋል። በአዋዛ የድርጊት መርሃ ግብር(Awaza Programme of Action) አማካኝነት በማደግ ላይ የሚገኙ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የባህር በር የማግኘት መብታቸውን እውን ማድረግ በሚቻልበባቸው አማራጮች ላይ ሙያዊ ምክረ ሀሳቦችን የሚያቀርብ ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን መቋቋሙን እንደምታደንቅ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ያሉበት መልክዐ ምድራዊ አቀማመጥ መሰናክል ሳይሆንባቸው እኩል የማሪታይም መብታቸው መረጋገጥ አለበት የሚለው ጉዳይ ላይ መሰረታዊ የእሳቤ ለውጥ መምጣት እንዳለበት ታምናለች ብለዋል። ቀጣናዊ ትስስር ከማጠናከር እና ንግድን ከማሳለጥ አኳያም ድንበር ተሻጋሪ ትስስሮችን የሚያጎለብቱ መሰረተ ልማቶች ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ይገባል ነው ያሉት። በዚህ ረገድም የልማት አጋሮች በተለይም በአፍሪካ የንግድ መሰናክሎችን የሚያቃልሉና የገበያ ተደራሽነትን የሚያሰፉ ፕሮጀክቶች ላይ የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል። በመሰረት ልማት ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በዲጂታል ትስስር ላይ ያለው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አቅርቦት ማደግ እንዳለበት ተናግረዋል። በማደግ ላይ የሚገኙ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ልዩ የሆነ ችግራቸው እንዲፈታ እና ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ የሚያስችል ሙሉ አቅማቸውን እንዲጠቀሙ ሁሉን አቀፍና ዘላቂ ትብብር እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል። በአዋዛ የድርጊት መርሃ ግብር(Awaza Programme of Action) የማሪታይም አስተዳደር አስመልክቶ የተቀመጡ ሀሳቦች ሁሉም ሀገራት እኩል የማሪታይም መብቶች ተጠቃሚ የመሆን፣ የአካባቢ ጥበቃ መብቶች እና የውሃ ሀብቶችን በጋራ የመጠቀም መብታቸው መጠበቅ ጋር መጣጣም አለበት ብለዋል። የባህር በር የማግኘት መብት ላይ የሚሰሩ ተቋማት ሀገራትን በእኩልነት እንዲያስተናግዱም ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ የአዋዛ የድርጊት መርሃ ግብርን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ማዕቀፎች እንዲተገበሩ በቁርጠኝነት ትሰራለች ያሉት ሚኒስትሩ ሌሎች ሀገሮችም ለማዕቀፎቹ ተፈጻሚነት አብክረው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል። ሁለተኛ ቀኑን በየያዘው ሶስተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የባህር በር የሌላቸው በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት ኮንፍረንስ እስከ ነሐሴ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል።
በመዲናዋ 44ሺህ 45 ሜትር ኪዩብ የኮንሶ እርከን ተሰርቷል - ባለስልጣኑ
Aug 6, 2025 82
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2017(ኢዜአ)፦ በመዲናዋ በተጠናቀቀው በጀት አመት 44ሺህ 45 ሜትር ኪዩብ የኮንሶ እርከን መሰራቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ። ባለስልጣኑ በ2017 በጀት አመት የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ዲዳ ድሪባ እንደገለጹት የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚችልና ስነምህዳሯ የተጠበቀ ከተማ ለማድረግ በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል።   የኮንሶ ሀገር በቀል እውቀትን በመጠቀም የአፈርና የውሃ እቀባዎች መሰራቱን አንስተው ለቱሪስት መስህብነትም ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። በባህላዊው የእርከን ስራው ከ600 በላይ የሚሆኑ ሰዎች መሳተፋቸውን ገልጸው፤ በዚህም 44ሺህ 45 ሜትር ኪዩብ የኮንሶ እርከን ተሰርቷል ብለዋል። ከእንጦጦ ወንዝ እስከ ራስ መኮንን ድልድይ በወንዙ ግራና ቀኝ አካባቢዎች፣ የቀበና ወንዝ፣ በአዲስ ኮንቬንሽን ማዕከል፣ በጎሮና ሌሎች አካባቢዎች የእርከን ስራዎቹ መከናወናቸውን ጠቅሰዋል። በወንዞች ዳርቻ የአፈር መከላትን ለመከላከልና ጎርፍን መቀነስ የሚያስችል በኮንሶ ባህላዊ አሰራር የጋብዮን ግንብ 7ሺህ 786 ሜትር ኪዩብ መገንባቱንም አክለዋል። እንደ ዋና ስራ አስኪያጁ ገለጻ በተፋሰስ ልማትና የወንዞች ዳርቻም ከቀበና እና እንጦጦ ወንዞች እስከ ፒኮክ አካባቢ ድረስ የወንዝ ዳርቻ ልማት ተከናውኗል። 438 ሄክታር የተጎዱ ቦታዎች ተለይተው የዝናብ ማቆሪያ፣ የድንጋይና የአፈር ክትር ስራዎች ተከናውነዋል ሲሉም ገልጸዋል።   በመዲናዋ የሚገኙ ወንዞችን በማጽዳት ብክለትን የመከላካል፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲኖራቸው የሚያስችሉ ስራዎች በስፋት እየተሰሩ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል። የወንዞች ልማትና ብክለትን ለመከላከል የወጣው ደንብ ላይ ለተለያዩ አካላት ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች መሰራታቸውንም ዋና ስራ አስኪያጁ አስታውቀዋል። ወንዞችን በበከሉ አካላት ላይ ከ2ሸህ እስከ 1 ሚሊየን ብር የሚደርስ የቅጣት እርምጃ መወሰዱንም ተናግረዋል።
የባህር በር የሌላቸው ታዳጊ ሀገራት በዓለም የኢኮኖሚ ሥርዓት ላይ ፍትሐዊ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ እያደረጋቸው ይገኛል
Aug 6, 2025 81
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2017(ኢዜአ)፦ በርካታ ታዳጊ ሀገራት የባህር በር አልባ መሆናቸው በዓለም የኢኮኖሚ ሥርዓት ላይ ፍትሐዊ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ እያደረጋቸው እንደሚገኝ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፈትሂ ማህዲ(ዶ/ር) ገለጹ። 3ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የባሕር በር የሌላቸው በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት ጉባኤ በተርክመኒስታን አዋዛ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።   በጉባኤው እየተሳተፉ የሚገኙት ዶክተር ፈትሂ ማህዲ ለኢዜአ በሰጡት ማብራሪያ÷ ኢትዮጵያን ጨምሮ የባህር በር የሌላቸው ታዳጊ ሀገራት ጥቅምና ፍላጎታቸውን ማስከበር የሚያስችል ተሳትፎ እያደረጉ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር) የሚመራ የኢትዮጵያ ልዑክም የሀገርን ጥቅምና ፍላጎት ማስገንዘብ የሚያስችል የነቃ ተሳትፎ እያደረገ ነው ብለዋል። ከጉባኤው በተጓዳኝ በተካሄዱ የወጣቶች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና የሕዝብ ተወካዮች የቅድመ ጉባኤ ፎረሞች ላይ የኢትዮጵያ ተወካዮች ንቁ ተሳትፎ ማድረጋቸውን አስረድተዋል። በሕዝብ ተወካዮች ቅድመ ጉባዔ የፓናል ውይይትም ’’የባሕር በር መዳረሻ የሌላቸው ታዳጊ ሀገራትን ተጠቃሚ የሚያደርግ የንግድ ሥርዓት ማቋቋምና ማጠናከር” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ጽሁፍ ማቅረባቸውን አስታውቀዋል። በጽሁፋቸውም ኢትዮጵያ የባሕር በር የሌላት መሆኑ በወጪና ገቢ ምርት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዋ ላይ ቀጥተኛ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን ማስገንዘብ እንደተቻለ አብራርተዋል። በተለይም የኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት አለመሆን የወጪና ገቢ ምርት እንቅስቃሴና የምርቶች ዋጋ ላይ ጫና እያስከተለ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም ኢትዮጵያ የባሕር በር መዳረሻ ሳይኖራት በመቆየቷ ሁለንተናዊ ዕድገቷንና ብልጽግናዋን ለማረጋገጥ በምታደርገው ጉዞ ትልቅ እንቅፋት መፍጠሩን አስረድተዋል። የባህር በር የሌላቸው ታዳጊ ሀገራት በዓለም አቀፍ የንግድ ሥርዓት ላይም ፍትሕዊና እኩል ተጠቃሚ መሆን አለመቻላቸውን ለተሳታፊ ሀገራትና ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማስገንዘብ ተችሏል ብለዋል። ይህም ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገታቸውን እንዳያፋጥኑ እንዲሁም ከባህር ለሚነሱ የደህንነት ስጋቶች ተጋላጭ እንዲሆኑ እያደረገ እንደሚገኝ አንስተዋል።   በዚህም የባሕር በር የሌላቸው ታዳጊ ሀገራት ሕግ አውጪዎች ጉዳዩን ታሳቢ ያደረገ ስራ መስራት እንዳለባቸው ምክክር መደረጉን ጨምረው ተናግረዋል። በተለይም ቀጣናዊ ትስስርን የሚፈጥሩ የወደብና የመንገድ መሠረተ ልማት ትስስሮችን የሚያሳልጥ የበጀትና ተያያዥ የድጋፍና ክትትል ስራ መስራት እንደሚገባ በመድረኩ አፅንኦት መሰጠቱን ጠቅሰዋል። የባህር በር ያላቸው ሀገራትም ለፍትሕዊ የንግድ ስርዓት መጠናከርና የባህር በር የሌላቸው ሀገራትን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ገልጸዋል። በኮንፍረንሱ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ፣ እስያ፣ አውሮፓ እና ደቡብ አሜሪካ የሚገኙ 32 ሀገራት እየተሳተፉ ሲሆን፤ ከተሳታፊዎቹ ሀገራት መካከልም 16ቱ ከአፍሪካ ናቸው። ሶስተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የባህር በር የሌላቸው በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት ኮንፍረንስ እስከ ነሐሴ 2 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል።
ኢትዮጵያና ተርኪሚኒስታን ኢ-ፍትሃዊ የሆኑ የባህር በር ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት እንደሚሰሩ ገለጹ
Aug 6, 2025 87
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ተርኪሚኒስታን በባህር በር ምክንያት የሚከሰቱ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት እንዲሁም ቀጣናዊ ውህደትንና ንግድን ለማጠናከር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። ሦስተኛው የተባበሩት መንግሥታት ባህር በር የሌላቸው በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ጉባኤ (UNLLDC3) "በአጋርነት ለውጥ ማምጣት" በሚል መሪ ሀሳብ በተርኪሚኒስታን አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል። ከጉባኤው በተጓዳኝ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ከተርኪሚኒስታኑ የንግድና የውጭ ኢኮኖሚ ግንኙነት ሚኒስትር ናዛር ሃልናዛሮቪች አጋሃኖቭ ተወያይተዋል።   ሁለቱ ሀገራት ኢ-ፍትሃዊ የሆነውን የባህር በር ተግዳሮት በጋራ ለመፍታት የመከሩ ሲሆን፤ ለንግድና ኢኮኖሚ እድገት መፋጠን አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ቀልጣፋና አነስተኛ ወጪ ያላቸውን የትራንስፖርት መፍትሄዎች ለመፍጠር ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል። ሚኒስትሮቹ ከፍተኛ የትራንስፖርት ወጪ፣ በጎረቤት ሀገራት ወደቦች ላይ ሙሉ ጥገኝነት እና የንግድ መስመሮችን የሚያውኩ የጂኦ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ስጋቶችን ጨምሮ የተለያዩ ተግዳሮቶችን አንስተዋል። ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) የባህር በር አለመኖር ለረጅም ጊዜ የሀገራትን ልማት የሚያደናቅፍ መልክዐ ምድራዊ ተግዳሮት መሆኑን ጠቅሰው ይህንን ተግዳሮት ወደ መልካም አጋጣሚ ለመቀየር የዚህ ዓለም አቀፍ መድረክ ታላቅ ሚና እንደሚጫወት ያላቸውን እምነት ገልፀዋል። ናዛር ሃልናዛሮቪች አጋሃኖቭ በበኩላቸው ቀጣናዊ ውህደት የባህር በር አልባ ሀገራትን እምቅ አቅም ለማውጣት ቁልፍ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። መፍትሔው ሀገራቱ በቀጣናቸው ውስጥ ያልተቋረጠ የሸቀጦች፣ የአገልግሎቶችና የሃሳቦች ፍሰት በሚፈጥር የግንኙነት መስመር መዘርጋት መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም ተርኪሚኒስታን ይህንን እውን ለማድረግ የሚያስችሉ መሰረተ ልማቶችን ለመገንባትና አስፈላጊ ስምምነቶችን ለመፈጸም ቁርጠኛ ናት ብለዋል። ኢትዮጵያን በዚህ ጥረት ውስጥ እንደ ዋና አጋር እንደሚመለከቱ እና ሀገራቸው የመካከለኛው እስያ መግቢያ በር እንደሆነች ሁሉ ኢትዮጵያም የአፍሪካ መግቢያ በር መሆኗን ጠቅሰዋል። ሚኒስትሮቹ በጉባኤው ለሀገራቱ ቁልፍ መፍትሔዎች እንደሚቀርቡ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። ኢትዮጵያና ተርኪሚኒስታን አጋርነታቸውን ለማስፋትና በባህላዊ የንግድ መስመሮች ላይ ያላቸውን ጥገኝነት ለመቀነስ እንዲሁም የተቀላጠፈ አሠራር ላይ የተመሠረተ አዲስ የንግድ አጋርነትን ለመመስረት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ኢዜአ ከስፍራው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።  

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የባህር መተላለፊያ የማግኘት መብታቸው ሊከበር ይገባል- ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር)
Aug 6, 2025 146
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2017(ኢዜአ)፦ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ያልተቋረጠ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር መተላለፊያ የማግኘት መብታቸው ሊከበር እንደሚገባ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር) ገለጹ። ሶስተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የባህር በር የሌላቸው በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት ኮንፍረንስ በተርኪሚኒስታን እየተካሄደ ይገኛል። የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር) በኮንፍረንሱ ባደረጉት ንግግር የባህር በር የሌላቸው በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት ቀጥተኛ የባህር በር መተላለፊያ አለማግኘት፣ ከፍተኛ የትራስፖርት ወጪ እና መሰረተ ልማቶች በበቂ ሁኔታ አለመሟላትን ጨምሮ በሌሎች መሰረታዊ ችግሮች እየተፈተኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል። የጂኦ ፖለቲካ ውጥረቶች፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ከፍተኛ የእዳ ጫና ችግሩ ይበልጥ እንዲባባስ ምክንያት መሆናቸውን አመልክተዋል። ኢትዮጵያ የመሬትን 50 በመቶ እና የዓለምን 60 በመቶ የውቅያኖስ ስፍራ የሚሸፍኑት ዓለም አቀፍ የውሃ ሀብቶች የሁሉንም ሀገራት ብልጽግና የማረጋገጥ ትልም እንደሚያሳኩ በጽኑ ታምናለች ብለዋል። የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ያልተቋረጠ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር በር መተላለፊያ የማግኘት መብታቸው ሊከበር እንደሚገባም ነው ሚኒስትሩ የገለጹት። ይህም ከትራንዚት ባለፈ የሀገራት ሁሉን አቀፍ መብት መሆኑን በውል መረዳት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። የሀገራቱ ፍላጎት በማሪታይም የኢኮኖሚ እድሎች ተጠቃሚ መሆን፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የማሪታይም ደህንነት መጠበቅ ጭምር እንደሆነም ገልጸዋል።   የባህር በር መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦች ሙሉ ለሙሉ ሊተገበሩ እንደሚገባ ጠቅሰው ይህም ዘላቂ እና የጋራ ልማትን ለማምጣትና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ቁልፍ መሆኑን አመልክተዋል። ኢትዮጵያ ከዚህ ኮንፍረንስ የባህር በር ማግኘት ላይ የእይታ ለውጥና ዓለም ለጉዳዩ ያለው ቁርጠኝነት ዳግም ይታደስበታል ብላ እንደምትጠብቅ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የሀብት ማሰባሰብ እና አዳዲስ የመፍትሄ ሀሳቦች የሚያመጡ ውጤታማ ትብብሮችን መፍጠር እንደምትፈልግም አብራርተዋል። በአዋዛ የድርጊት መርሃ ግብር(Awaza Programme of Action) አማካኝነት በማደግ ላይ የሚገኙ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የባህር በር የማግኘት መብታቸውን እውን ማድረግ በሚቻልበባቸው አማራጮች ላይ ሙያዊ ምክረ ሀሳቦችን የሚያቀርብ ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን መቋቋሙን እንደምታደንቅ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ያሉበት መልክዐ ምድራዊ አቀማመጥ መሰናክል ሳይሆንባቸው እኩል የማሪታይም መብታቸው መረጋገጥ አለበት የሚለው ጉዳይ ላይ መሰረታዊ የእሳቤ ለውጥ መምጣት እንዳለበት ታምናለች ብለዋል። ቀጣናዊ ትስስር ከማጠናከር እና ንግድን ከማሳለጥ አኳያም ድንበር ተሻጋሪ ትስስሮችን የሚያጎለብቱ መሰረተ ልማቶች ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ይገባል ነው ያሉት። በዚህ ረገድም የልማት አጋሮች በተለይም በአፍሪካ የንግድ መሰናክሎችን የሚያቃልሉና የገበያ ተደራሽነትን የሚያሰፉ ፕሮጀክቶች ላይ የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል። በመሰረት ልማት ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በዲጂታል ትስስር ላይ ያለው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አቅርቦት ማደግ እንዳለበት ተናግረዋል። በማደግ ላይ የሚገኙ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ልዩ የሆነ ችግራቸው እንዲፈታ እና ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ የሚያስችል ሙሉ አቅማቸውን እንዲጠቀሙ ሁሉን አቀፍና ዘላቂ ትብብር እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል። በአዋዛ የድርጊት መርሃ ግብር(Awaza Programme of Action) የማሪታይም አስተዳደር አስመልክቶ የተቀመጡ ሀሳቦች ሁሉም ሀገራት እኩል የማሪታይም መብቶች ተጠቃሚ የመሆን፣ የአካባቢ ጥበቃ መብቶች እና የውሃ ሀብቶችን በጋራ የመጠቀም መብታቸው መጠበቅ ጋር መጣጣም አለበት ብለዋል። የባህር በር የማግኘት መብት ላይ የሚሰሩ ተቋማት ሀገራትን በእኩልነት እንዲያስተናግዱም ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ የአዋዛ የድርጊት መርሃ ግብርን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ማዕቀፎች እንዲተገበሩ በቁርጠኝነት ትሰራለች ያሉት ሚኒስትሩ ሌሎች ሀገሮችም ለማዕቀፎቹ ተፈጻሚነት አብክረው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል። ሁለተኛ ቀኑን በየያዘው ሶስተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የባህር በር የሌላቸው በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት ኮንፍረንስ እስከ ነሐሴ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል።
ለህዝብ ተጠቃሚነት የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን ለማስቀጠል የድጋፍና ቁጥጥር ሥራችንን እናጠናክራለን-የክልሉ ምክር ቤት አባላት
Aug 6, 2025 82
ወልቂጤ፤ሐምሌ 30/2017( (ኢዜአ) )፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለህዝብ ተጠቃሚነት የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን ለማስቀጠል የድጋፍና ቁጥጥር ሥራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ምክር ቤት አባላት ገለጹ። በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት ከተገኘው ልምድ በመነሳት በበጀት ዓመቱ የተሻሉ የልማት ተግባራት እንዲከናወኑ ከምክር ቤት ጉባኤ ባለፈ በመስክ ምልከታ ድጋፍና ቁጥጥር በማድረግ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እንደሚወጡም ተናግረዋል። የምክር ቤቱ አባላት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በክልሉ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በፖለቲካዊና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ውጤታማ ሥራዎች እንደተከናወኑ በመስክ ምልከታ ጭምር ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ የምክር ቤት አባላት መካከል አቶ ጌታሁን ነጋሽ፣ የህዝብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች በከተማና በገጠር መከናወናቸውን ተናግረዋል።   ህብረተሰቡ የፍትህ፣ የመልካም አስተዳደርና የልማት ተጠቃሚነቱ እንዲረጋገጥ ምክር ቤቱ የሚጠበቅበትን ለመወጣት ሲሰራ መቆየቱንም አስታውሰዋል። በበጀት ዓመቱ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በከተሞች እና በገጠር የተጀመሩ የኮሪደር ልማት፣ የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች፣ ተዘዋዋሪ ችሎት እንዲሁም ባህላዊ ፍርድ ቤቶች የበለጠ እንዲጠናከሩ የድጋፍ፣ ክትትል እና ቁጥጥር ስራቸውን እንደሚያጠናክሩም ተናግረዋል። አቶ ግዛቸው ዋሌሬ የተባሉ ሌላው የምክር ቤት አባል እንዳሉት፣ በአሁኑ ወቅት በክልሉ የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደምክር ቤት አባል የበኩላቸውን ለመወጣት ተዘጋጅተዋል።   ክልሉ ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆነውም በተለያዩ ዘርፎች ውጤቶች መመዝገባቸውን አስታውሰው፣ ቀሪ የህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ እንዲያገኙ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ገልጸዋል። በተለይ አስፈጻሚ ተቋማት የህዝብ ጥያቄን ለመመለስ የሚያናውኗቸውን ተግባራትን አፈጻጸም የመከታተልና የመደገፍ ሚናቸውን በአግባቡ እንደሚወጡ ነው ያረጋገጡት። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በመስኖ ልማት፣በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ በትምህርት፣ በጤናና ሌሎች ዘርፎች በተከናወኑ ስራዎች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ውጤቶች ተመዝግበዋል ሲሉም አቶ ግዛቸው ተናግረዋል። በአስፈጻሚ አካላት የህዝብ ጥያቄዎችን ለመፍታት በሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ ድጋፍና ክትትላቸውን እንደሚያጠናክሩ የገለጹት ደግሞ ሌላኛዋ የምክር ቤቱ አባል ወይዘሮ አሌይካ ሽኩር ናቸው።   በተለይ ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ተጠቃሚ ለማድረግ የሚከናወኑ ተግባራት በቀጣይም ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እንደምክር ቤት አባል በመስክ ጭምር በማረጋገጥ ሀላፊነታቸውን እንደሚወጡም ገልጸዋል። ግብርናን ለማሳደግ በመስኖ ልማት የተመዘገበው ውጤት ቀጣይነት እንዲኖረውና በትምህርት ለትውልድ ኢኒሼቲቭ የተጀመሩ ውጤታማ ሥራዎችን ለማጠናከር እንደሚሰራም አመልክተዋል። ሌላኛው ምክር ቤት አባል ሀጂ ገራድ ድልታታ በበኩላቸው፥ በክልሉ በሚከናወኑ የልማት ስራዎች አርሶ አደሩ የልፋቱን ውጤት እንዲያስገኙ በገበያ ትስስር የተጀመሩ ጥረቶችን ለማጠናከር እንሰራለን ብለዋል።   በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የመስክ ምልከታ ባደረጉበት ወቅት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ የተለያዩ የልማት ሥራዎች እንደተከናወኑ በተጨባጭ ማየታቸውንም ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የጀርመን እና የግብፅ አምባሳደሮች አሰናበቱ
Aug 5, 2025 123
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 29/2017 (ኢዜአ)፡-የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ጄንስ ሃኔፌልድን እና የግብፅ አምባሳደር ሞሀመድ ኦማር ጋድን አሰናበቱ። ፕሬዚዳንት ታዬ አምባሳደሮቹ በነበራቸው ቆይታ አገሮቹ ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ እየጎለበተ እንዲመጣ ላደረጉት አስተዋፅኦ አመስግነዋል።   ተሰናባች አምባሳደሮቹ በበኩላቸው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ኢትዮጵያ በአፍሪካ ካላት ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ እና ፋይዳ አኳያ፤ የአገሮቻቸውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በቆይታቸው አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ ተናግረዋል። ከተሰናባች አምባሳደሮቹ ጋር የተደረገውን ውይይት የተከታተሉት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ዘሪሁን አበበ እንደገለጹት፤ኢትዮጵያ ከጀርመን እና ግብፅ ጋር ያላትን ታሪካዊ ግንኙነት ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኗን አብራርተዋል።   በተለይም ደግሞ ፕሬዚዳንት ታዬ የስራ ጊዜያቸውን ካጠናቀቁት የግብጽ አምባሳደር ጋር ያደረጉትን ውይይት ያወሱት አምባሳደር ዘሪሁን፤ፕሬዚዳንቱ አምባሳደር ጋድን ለአራት ዓመት በአዲስ አበባ ላደረጉት አገልግሎት አመስግነዋል። የኢትዮጵያ እና የግብፅ ግንኙነት እጅግ ታሪካዊ የሚባል እና በተፈጥሮ የተሳሰረ መሆኑን አውስተው፤ይህንን ታሳቢ ያደረገ ግንኙነት መፍጠር እንዲሁም ግንኙነቱ ከፍ እንዲል ማስቻል የሚጠበቅ ሀላፊነት ነው ሲሉ አጽንኦት መስጠታቸው ተጠቁሟል። የኢትዮጵያ እና የግብጽ በአፍሪካ አህጉር ካላቸው ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ እና ተፈጥሯዊ ትስስር አኳያ ትብብራቸውን መመዘን እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል። በተለይም ደግሞ ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር ያላትን ታሪካዊ ግንኙነት መሰረት በማድረግ እና አገሮቹ በዓባይ ወንዝ አማካኝነት በተፈጥሮ የተቆራኙ መሆናቸውን አጽንኦት የሰጡት ፕሬዚዳንት ታዬ፤ ይህ የተፈጥሮ ሀብት በፍትሐዊነት ጥቅም ላይ እንዲውል የኢትዮጵያ የፀና አቋም እንደሆነ ማስረዳታቸውን ገልጸዋል። ይህንን በተመለከተ ሁለቱ አገሮች በመካከላቸው ሌላ ወገን ሳይጋብዙ ተመካክረው ማናቸውንም የልዩነት መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን ማቃለል ይችላሉ ሲሉም ተናግረዋል። ላለፉት አራት ዓመታት በአዲስ አበባ የግብፅ አምባሳደር ሆኜ ማገልገሌን እንደ ትልቅ እድል ነው የምቆጥረው ያሉት ደግሞ ተሰናባቹ በኢትዮጵያ የግብፅ አምባሳደር ሞሀመድ ኦማር ጋድ ናቸው።   ግብፅ እና ኢትዮጵያ በአፍሪካ የጎላ ጠቀሜታ ያላቸው አገሮች መሆናቸውን እና ዘመን ተሻጋሪ የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዳለቸው የጠቀሱት አምባሳደሩ፤ የሚገጥሟቸውን ልዩነቶች በውይይት እየፈቱ እንደሚሄዱ እምነታቸውን ገልጸዋል። በሌላ በኩል የጀርመን አምባሳደር ጄንስ ሃኔፌልድ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ እና ጀርመን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት 120ኛ ዓመቱን አስቆጥሯል ብለዋል።   አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ልዩ ስፍራ እንደምትሰጠው የገለጹት አምባሳደር ሃኔፌልድ፤ የሁለቱ አገሮች ግንኙነት በሁሉም ዘርፍ ከፍተኛ ዕምርታ እንዳሳየ አብራርተዋል። ከፕሬዚዳንት ታዬ ጋር በነበራቸው ቆይታም በአገራቸው መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማጎልበት በሚያስችሉ ቀጣይ የትብብር መስኮች ላይ መወያየታቸውን አምባሳደሩ አውስተዋል።
በህገ መንግስት አጣሪ ጉዳዮች ባሉ ክርክሮች የሚነሱ ነጥቦችን መሰረት አድርጎ ምርምሮችን ማካሄድ ጠቀሜታቸው የጎላ ነው
Aug 5, 2025 112
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2017(ኢዜአ)፦በህገ መንግስት አጣሪ ጉዳዮች ባሉ ክርክሮች የሚነሱ ነጥቦችን መሰረት አድርጎ የሚካሄዱ ምርምሮች የህብረተሰቡን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያስችሉ በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረት ገለጹ። የህገ-መንግስት አጣሪ ጉባኤ ጽህፈት ቤት እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል በተለያዩ ጉዳዮች በጋራ ለመስራት በተስማሙበት ወቅት እንደተገለጸው፤ ምርምሮች ለህገ መንግስታዊነትና ለህግ አስተምህሮ የሚኖራቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረት በዚሁ ወቅት፤ በህገ መንግስት አጣሪ ጉዳዮች ባሉ ክርክሮች የሚነሱ ነጥቦችን መሰረት አድርጎ የሚካሄዱ ምርምሮች ተጽዕኖ ከመፍጠራቸውም በላይ የህብረተሰቡን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ይሆናሉ። የህገ መንግስት አጣሪ ጉባኤ ጽህፈት ቤት በህገ-መንግስት ጉዳዮች ላይ በሚሰጥ ውሳኔ ላይ ምክረ ሃሳብ እና ውሳኔ የሚሰጥ ትልቅ ሃላፊነት ያለበት አካል መሆኑን የገለጹት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ፤ በተቋሙ የሚሰጡ ውሳኔዎች የሚኖራቸው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን አመልክተዋል። እነዚህን ለመወሰን የሚያስችል አቅም መፍጠር እንደሚያስፈልግ አንስተው፤ ይህም ለህገ መንግስት እና ለህግ አስተምህሮ የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት ባለፉት ዓመታት በፍትህ ስርዓቱ ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎችን እያፈራ ይገኛል።   ትምህርት ቤቱ የፍትህ ስርዓቱና የህግ ማዕቀፉ እንዲዘምን በርካታ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን አንስተዋል። የህገ-መንግስት አጣሪ ጉባኤ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ደሳለኝ ወይሳ እንደተናገሩት፤ ተቋሙ ጥራት ተደራሽ እና ቀልጣፋ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል የጥናትና ምርምር ስራዎች ያከናውናል፡፡   በተቋሙ ጥናትና ምርምር የሚፈልጉ ፈርጀ ብዙ ጉዳዮች መኖራቸውን ጠቁመው፤ እነዚህ መዝገቦች ላይ ውሳኔ ለመስጠት ከዩንቨርሲቲው ጋር የተደረገው ስምምነቱ ትልቅ ሚና አለው፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ክፍል ተጠባባቂ ዲን ፕሮፌሰር ሙራዱ አብዶ እንደገለጹት፤ ዩኒቨርሲቲው ወደ ተቋሙ መምህራንን የማሰማራት እንዲሁም በጥናትና ምርምር ስራ የመሳተፍ ተግባር ያከናውናል።   ተቋሙ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ተግባር ተኮር ትምህርት እንዲያገኙ እገዛ እንደሚያደርግም ፕሮፌሰር ሙራድ አስታውቀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሰኔ እና በሐምሌ ወር 2017 ዓ.ም ያከናወኗቸው ቁልፍ ተግባራት
Aug 2, 2025 207
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሰኔ እና በሐምሌ ወር 2017 ዓ.ም ቁልፍ የሆኑ ብሔራዊ የፖሊሲ ትግበራን፣ የኢኮኖሚ ሪፎርምን፣ ቀጠናዊ እና ዓለማቀፋዊ ስትራቴጂካዊ ዲፕሎማሲን በሚያሳልጥ መልኩ ተከታታይ ተግባራት አከናውነዋል። በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሀገር ውስጥ ካከናወኗቸው ተግባራት መካከል፤ የ2017 የዕቅድ አፈጻጸምን አስመልክቶ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ሰፊ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡበት ይጠቀሳል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ17ኛው BRICS የመሪዎች ጉባኤ ላይ በመሳተፍ፣ ከዓለም መሪዎች ጋር ባደረጉት የላቀ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የኢትዮጵያ ስም ከፍ እንዲል አድርገዋል። ሌላው የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ የታየበት ሁነት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሁለተኛው የምግብ ስርዓት ጉባኤ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ በጋራ ያዘጋጀችው ትልቅ አለማቀፍ ጉባኤ ነበር። እነዚህ የከፍተኛ ደረጃ ተሳትፎዎች(High-level engagements) ሀገራዊ ልማትን ለማፋጠን እና ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ያላትን ሚና በከፍተኛ ሁኔታ ለማጎልበት ያለመ አመራር እንደተሰጠ ያረጋግጣል።   በሰኔ ወር መጨረሻ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመንግስትን የ2017 የዕቅድ አፈጻጸምን አስመልክቶ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ሰፊ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ማበራሪያቸው ኢትዮጵያ እያከናወነች ባለቸው ጥልቅ የኢኮኖሚ ሪፎርም እና የምጣኔ ሀብታዊ ማሻሻያዎች፤ እንዲሁም በሂደቱ እየተመዘገቡ ስለሚገኙ ስኬቶች እና ተግዳሮቶች በሰፊው አስረድትዋል። ለአብነትም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን በተመለከተ ማበራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ወደ ማክሮ ኢኮኖሚ ያስገቡን ጉዳዮች አንዱ የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቶች ናቸው፤ በስራ አጥነት፣ በዋጋ ግሽበት፣ በወጪና ገቢ ንግድ ሚዛን መጓደል ሊገለፅ የሚችል ነው ብለዋል። ሁለተኛው ለግሉ ዘርፍ የስራ አካባቢው ምቹ አልነበረም። ሶስተኛው ምርታማነት ነው። በግብርናም በኢንዱስትሪም ምርታማነታችን ውስን ነበር። ይህም በርካታ ተግዳሮቶች እነዲስተናገዱ አድርጓል። አራተኛው ተወዳዳሪ የኢኮኖሚ ሁኔታን አልፈጠርንም ብለዋል።   እነዚህን ጉዳዮች ጨክነን በመፍታት የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቱን መፍታት እንችላለን ብለን ነው ወደ ተግባር የገባነው ሲሉ ነው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጠቆሙት። እንደ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ መንግስት ባደረገው ውጤታማ የሪፎርም ስራዎች እና በተደረገው ሁሉን አቀፍ ርብርብ፤ በ2017 በጀት ዓመት በወሳኝ የልማት ዘርፎች ማለትም በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በአገልግሎት፣ በፋይናንስ፣ በውጭ ንግድ እና ሌሎችም አበረታች ስኬቶች ስለመመዝገባቸው ለምክር ቤት አባላቱ አብራርተዋል። በዚሁ ማብራሪያቸው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰላምና ጸጥታን በተመለከተ ግልጽ ማብራሪያ ያቀረቡ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሰላምና የጸጥታ ችግር ዋነኛው መንስኤ የተሳሳተ የፖለቲካ አመለካከት እንደሆነ አስረድተዋል። ኢትዮጵያ በጎረቤት ሀገራት ዘንድ የምትከተለውን የዲፕሎማሲ አና አሁናዊ እንቅስቃሴ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሲያብራሩ ደግሞ፤ ሀገሪቱ ከጎረቤቶቿ ውጭ ህልውና የላትም ብለዋል። በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ዓመታት ከየትኛውም የጎረቤት ጋር ግጭት ውስጥ እንዳልገባች በመግለጽ፤ ሀገራቸው በቀጣናው ሰላማዊ ግንኙነት ያላትን ቁርጠኝነት አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በሌላ በኩል ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ17ኛው የብሪክስ ጉባኤ ለመሳተፍ ወደ ሪዮዲጀኔሮ ባቀኑበት ወቅት፣ ከጉባኤው አስቀድሞ ከብራዚል ፕሬዝደንት ሉዊዝ ኢናቺዮ ሉላ ደ ሲልቫ ጋር ተገናኝተን በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል። የሁለቱ መሪዎች ውይይትም በቅርብ እያደገ የመጣውን የሀገራት ግንኙነት የበለጠ በማጠናከር ረገድ አንድ ርምጃ ወደፊት የወሰደ ነበር። በተለያዩ ዘርፎች የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትስስሮቻቸውን የበለጠ ለማጠናከር መሪዎቹ ተስማምተዋል።   በተመሳሳይ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር 55 ዓመታትን ባስቆጠረው የኢትዮ-ቻይና ግንኙነት ላይ ውይይት አድርገዋል። ግንኙነታቸው በሁኔታዎች ሁሉ እንደማይቀያየር አጋሮች (all weather strategic partners) ባለፉት ሰባት ዓመታት ትብብራችን ጉልህ ፍሬዎችን አፍርቷል። ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን እና አይሲቲን ባካተቱ ቁልፍ የኢኮኖሚ ዓምዶች ላይ የሀገራቱ ትኩረት እንዳለ ሆኖ ሌሎች የትብብር መስኮችን ለማጠናከርና እንደ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ ሎጂስቲክስ እና ንጹሕ የኃይል ምንጮች ልማት ላይ ያላቸወን ዕምቅ ዐቅም ለመመልከትም መሪዎቹ ችለዋል። በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሪዮ ዲ ጄኒሮ በተካሄደው 17ኛው የብሪክስ ጉባኤ የሰላም፣ የፀጥታ እና አለምአቀፍ አመራር መድረክ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ስኬታማ ትብብርን ለማስቻል አፀፋዊ መተማመንን የሚያሳድጉ ዓለምአቀፍ ተቋማት የመኖርን አጣዳፊነት አንስተዋል። ዓለምአቀፍ የገንዘብ ተቋማት የጋራ ደኅንነትን እና ሁሉን አካታች ብልጽግናን ለማምጣት ይረዳ ዘንድ የውሳኔ አሰጣጥ መዋቅራቸው ምሉዕነት ባለው መልክ የሚሻሻልበትን ሁኔታም አፅንኦት ሰጥተው አንስተዋል።   ኢትዮጵያ በይፋ ወደ ብሪክስ የተቀላቀለችው በ2015 ዓ.ም ሲሆን ኢኮኖሚያዊ ወዳጅነት ብቻ ሳይሆን ፍትኃዊ የሆነ፣ እኩልነት የሚሰፍንበት ብዝኃ ዋልታዊ አለምን ለመፍጠር ከሚተጉ ሀገራት ጋር በእኩል ደረጃ የተሰለፈችበት ስብስብ ነው። እንደ ብሪክስ አባልነቷ ኢትዮጵያ እነዚህ ጥረቶች እንዲሳኩ በተለይም በአለምአቀፍ ውሳኔ ሰጪ መድረኮች ለአዳዲስ ገበያዎች እና በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት ሰፋ ያለ ውክልና በሚገኝበት ሁኔታ ላይ በንቃት አስተዋፅኦ ታደርጋለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የብሪክስን እያደገ የመጣ ተፅዕኖ ሲገልጹም የሚከተለውን ብለዋል። ”ብሪክስ ከጠንካራ አዲስ ሀሳብ ተነስቶ ለአለምአቀፍ ለውጥ የሚሰራ ብርቱ ኃይል ወደመሆን ተሸጋግሯል። አዳዲስ አባላት በመጨመራቸውም የጋራ ድምፃችን የበለጠ ይጠናከራል። የጋራ አላማችን የበለጠ ይጠራል። አቅማችንም ይሰፋል።” ኢትዮጵያ በ2017 የሥራ ዘመን ትርጉም ያለው እና ለመጪው የ2018 የቀጠለ የእድገት ጉዞ ጠንካራ መሠረት የሚሆን እድገት ፈጽማለች። በዚህ መነሻነትም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላትን በመሰብሰብ ለመጪው ዓመት ለትግበራ የተዘጋጀውን የ2018 የተሟላ የሁሉም ዘርፎች እቅድ እና ሀገራዊውን የልማት እቅድን ገምግመዋል። እንዲሁም በሐምሌ ወር ኢትዮጵያ ለሶስት ቀናት በአዲስ አበባ በስኬት የተከናወነውን ሁለተኛውን የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ በጋራ ማዘጋጀቷን ተከትሎ፣ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተለተለያዩ ሀገራት መሪዎችን እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ሀላፊዎችን ተቀብለው አነጋግረዋል። በዚህም (የጣሊያኗን ሪፐብሊክ) ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒን ጨምሮ (የኬንያውን ሪፐብሊክ) ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶን፣ (የሶማሊያውን) ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ እና (የኮሞሮስ ህብረት) ፕሬዝዳንትን አዛሊ አሱማኒ በመቀበል በሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።   በተጨማሪም ከዚሁ ጉባኤ ቀደም ብሎ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ፀሐፊ የሆኑትን አሚና መሃመድን እና ሌሎች የዓለም አቀፍ ተቋማት ሃላፊዎችን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። በዚሁ ውይይት በመላው አፍሪካ እና በተቀረውም አለም ዘላቂ፣ አካታች እና በተለያዩ ፈተናዎች የማይበገር የምግብ ሥርዓት አስፈላጊነትን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል። በውይይቱ ኢትዮጵያ በተቀናጁ ፖሊሲዎቿ፣ ለአየር ንብረት ጥበቃ ምላሽ ሰጪ በሆነ የግብርና ሥራዋ ብሎም በምግብ ዋስትና እና ለሁሉም የተመጣጠነ ምግብ በማቅረብ ማኅበረሰብ መር ዘዴዎቿ የምግብ ሥርዓትን ለማሻሻል ባላት ፅኑ አቋም እና ተግባር መቀጠሏን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስምረውበታል።   በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሁለተኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው እንደገለጹት በገጠር መሠረተ ልማት እና በሥነ-ምግብ ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶችን ለማጎልበት ተገማች የሆነ የኮንሴሽናል ፋይናንሺንግ አስፈላጊነትን አጽንኦት ሰጥተዋል።   በዚሁ የመክፈቻ ንግግራቸው ኢትዮጵያ በምግብ ስርዓት ሽግግር ያደረገችውን ስኬታማ ጉዞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያብራሩ ሲሆን፤ በሀገር ውስጥ የምርት እድገት ላይ ኢንቨስትመንትን በማሳደግ፣ ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት በመቀነስ እና ለትውልዱ በቀጣይ ፈተናዎች የማይበገር ስርዓትን እውን በማደረግ ሂደት አመርቂ ውጤት መገኘቱን ጠቁመዋል። በወቅቱም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተባበሩት መንግስታት የምግብ ስርዓቶች ጉባዔን አስመልክቶ ለክብር እንግዶች በብሔራዊ ቤተ መንግሥት እራት ግብዣ አሰናደተዋለ።   በጥቅሉ በሰኔ እና ሐምሌ ወር 2017 ዓ.ም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፍተኛ የሆነ ሀገራዊ የፖሊሲ ግምገማዎች እንዲደረጉ፣ ጉልህ የሆኑ አለም አቀፍ ስብሰባዎች እንዲከናወኑ እና በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎ እንዲፈጠር በሳል አመራር የሰጠበት ነው። ሁሉም ተግባራት የኢትዮጵያን ዕድገት እውን ለማድረግ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለትን ስትራቴጂካዊ አስፈላጊነት ለማጉላት የታለሙ ስኬታማ ክንውኖች ነበሩ።
በሲዳማ ክልል ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Aug 1, 2025 150
ሀዋሳ፤ ሃምሌ 25/2017(ኢዜአ)፦ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በሲዳማ ክልል የተከናወኑ ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ስራዎች በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥሉ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ። በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የ2017 ክልል አቀፍ የአባላት ማጠቃለያ የውይይት መድረክ በሀዋሳ ተካሂዷል፡፡   በመድረኩ ላይ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፤ በበጀት አመቱ የክልሉን የመልማት አቅም በመለየት ድህነትን መቀነስ የሚያስችሉ የተለያዩ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል። በተለይም የእንስሳት ልማት፣ የማህበራዊ አገልግሎት፣ የቱሪዝም ልማት፣ የሌማት ትሩፋት፣ የኮሪደር ልማት፣ የስንዴ ልማት፣ የፍራፍሬና ሌሎችም የግብርና ልማት ስራዎች ተጨባጭ ውጤት የተመዘገበባቸው መሆኑን አብራርተዋል። የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የተቀረጹ 6 ኢንሼቲቮችና 68 ፓኬጆች ከክልሉም ባለፈ እንደ ሀገር የህዝብን የልማት ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ጥሩ ማሳያዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። በቀጣይም የተገኙ ውጤቶችን በማስፋት፣ ጉድለቶችን በመሙላትና የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ከዳር በማድረስ ለሀገራዊ የብልፅግና ስኬት በጋራ መትጋት ይገባናል ሲሉ አስገንዝበዋል።   በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አብረሃም ማርሻሎ በፓርቲው ጉባኤ የሰላም ግንባታና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች አጽንኦት መሰጠቱን አንስተው የክልሉ የኢንቨስትመንትና ቱሪዝም አቅም ማሳደግ ላይ ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል፡፡ በመልካም አስተዳደር ዘርፉ ከነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ጋር በተያያዘ የሚነሳውን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ለመቅረፍ በተወሰደ እርምጃ መሻሻል መኖሩን ጠቅሰው በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ በቀጣይም የሃሳብ ብዝሃነትን በማክበርና የልማት አንድነትን በማጠናከር በተለይም በመልካም አስተዳደር ረገድ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት የመፍታትና የማስተካከል ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል። በመድረኩ በ2017 እቅድ አፈጻጸምና በቀጣይ እቅድ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አደረጃጀቶችም እውቅና ተሰጥቷል፡፡
በትግራይ ክልል የምክክር ሂደት ለመጀመር የሚያስችል ውይይት ተካሔደ
Aug 1, 2025 214
መቀሌ፤ ሀምሌ 25/2017(ኢዜአ)፦ በትግራይ ክልል የምክክር ሂደት ለመጀመርና ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የሚያስችል ውይይት ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር አድርገናል ሲሉ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ተናገሩ፡፡ በኢትዮጵያ የቆዩ ችግሮችን በምክክር ለመፍታት ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ በክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ከዝግጅት ምእራፍ አንስቶ በሂደት የምክክር ምእራፍ ላይ ይገኛል። የእስከ አሁኑ ሂደትም አሳታፊ በሆነ መልኩ የተከናወነ መሆኑንና በስኬታማነት መቀጠሉን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል። የምክክር ኮሚሽኑ የጀመረውን ስኬታማ ጉዞ በመቀጠልና ተሞክሮዎችን በመቀመር በትግራይ ክልልም ለመጀመር እንቅስቃሴ ጀምሯል። በዚሁ ጉዳይ ላይ በክልሉ የተጀመረው እንስቅስቃሴ ምን ይመስላል? በማለት ኢዜአ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያን አነጋግሯል። ኮሚሽነሩም በማብራሪያቸው የምንም ነገር መፍትሄው ምክክር መሆኑን አንስተው ለኢትዮጵያ አሁን ላይ ከምንም በላይ ምክክር ያስፈልጋታል፤ ይህንንም በነፃነትና አሳታፊ በሆነ መልኩ ቀጥለንበታል ሲሉ ተናግረዋል። ከትግራይ ክልል በስተቀር በሌሎች ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች አሳታፊና አካታች የሆነ አጀንዳ የማሰባሰብና የልየታ ስራ በተሳካ መልኩ መካሄዱን አስታውሰው በትግራይ ክልልም በተመሳሳይ መልኩ ለማካሄድ እንቅስቃሴ መጀመሩን አረጋግጠዋል ። በመሆኑም በትግራይ ክልል የምክክር ሂደት ለመጀመርና ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የሚያስችል ውይይት ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እና ሌሎች አካላት ጋር አድርገናል ብለዋል። በውይይታቸውም ለሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብና ሌሎች ስራዎች አጋዥ የሚሆኑ ገንቢ የውይይት ጊዜ እንደነበራቸው ያስታወሱት ዋና ኮሚሽነሩ ለስኬታማነቱ እገዛና ትብብራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም አረጋግጠዋል። የምክክሩ ሂደት በሌሎች አካባቢዎች በነፃነትና አሳታፊ በሆነ መልኩ መካሄዱን ገልፀው በትግራይ ክልልም በተመሳሳይ መልኩ የሚካሄድ በመሆኑ ሁሉም አካላት ተሳታፊ እንዲሆኑ ዋና ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ዋና ሀገራዊ ችግሮችን በምክክር በመፍታት ህብረ-ብሄራዊ አንድነትን ለማጥበቅና ጠንካራ ሀገረ-መንግስት ለመገንባት የሚያስችል በታሪክ አጋጣሚ የተገኘ እድል መሆኑም ይታወቃል።

ማህበራዊ
ታታሪውን የካሜራ ባለሙያ የዘከረው የስነ-ጽሁፍ ምሽት
Aug 6, 2025 56
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በየወሩ በቋሚነት የሚከናወን ተቋማዊ የስነ ጽሁፍ ምሽት አስጀምሯል። መድረኩ በዛሬው መርሃ ግብሩም ‘’ታታሪነትን ማወደስ” በሚል መሪ ሃሳብ በቅርቡ በድንገተኛ አደጋ ሕይወቱ ያለፈውን የካሜራ ባለሙያ ብዙዓየሁ ብርሃኑን ዘክሯል። በዛሬው የስነ-ጽሁፍ መድረክ የተቋሙ ሰራተኞች በግጥም፣ በወግ እንዲሁም አጫጭር ልብ ወለዶች ታታሪውን የካሜራ ባለሙያ ብዙዓየሁ ብርሃኑን ዘክረዋል።   በመድረኩ የተገኙት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሰይፈ ደርቤ ወርሃዊ የስነ-ጽሁፍ ምሽቱ ተቋማዊ የእርስ በርስ መቀራረብን በማጠናከር ጠንካራ የስራ ባህል ለማጎልበት እንደሚያግዝ ጠቁመዋል። የስነ ጽሁፍ አቅም እያላቸው ዕድሉን ያላገኙ ሰራተኞች ያላቸውን ተሰጥኦ የሚገልጡበት መድረክ እንደሚሆንም ገልጸዋል። የመጀመሪያው መድረክ በሙያውም ሆነ በባህሪው ምስጉንና ታታሪ የነበረውን ብዙዓሁ ብርሃኑን በመዘከር መካሄዱንም አድንቀዋል።   ብዙዓየሁ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት በነበረው የስራ ስምሪት በሙያው የተመሰከረለትና ለሀገር ታላላቅ ስራዎችን ያበረከተ ባለሙያ እንደነበርም አንስተዋል። ታታሪነትን ማወደስ በስራቸው ምስጉን ሰራተኞችን ለመፍጠር ሚናው የጎላ መሆኑን አንስተው፤ ከዚህ አኳያ መድረኩ የብዙአየሁ ጠንካራ የስራ ክህሎት በሌሎች ሰራተኞች መነሳሳትን እንደሚፈጥር ገልጸዋል።   በመድረኩ የሚቀርቡ የስነ ጽሁፍ ስራዎችም ተመርጠው በአንድ መድብል እንዲታተሙ ጥረት እንደሚደረግም ጠቁመዋል። ቀጣዩ የስነ-ጽሁፍ መድረክም በመጪው ነሐሴ ወር መጨረሻ የሚከናወን ይሆናል።
ህገ-ወጥ የሰዎች ፍልሰትን ለመከላከል የሥራ አማራጮችን ማስፋትና ህጋዊ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን ማጠናከር ይገባል
Aug 6, 2025 93
ባህር ዳር፤ ሐምሌ 30/2017(ኢዜአ)፦ ህገ-ወጥ የሰዎች ፍልሰትን ለመከላከል የሀገር ውስጥ የሥራ አማራጮችን ማስፋትና የውጭ ሀገራት ህጋዊ የሥራ ስምሪትን ማጠናከር እንደሚባ ተመላከተ። በአማራ ክልል ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀልን ለመከላከል ያለመ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል። በክልሉ በሰው የመነገድ፣ በህገወጥ መንገድ ሰዎችን ድንበር የማሻገርና ተዛማጅ ወንጀሎችን መከላከል የሚያስችልና የተለያዩ ተቋማትን ያካተተ የትብብር ጥምረት ተቋቁሞ ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል። ጥምረቱ የክልሉን ስራና ስልጠና፣ ፖሊስና ፍትህ ቢሮን ጨምሮ ሌሎች ተቋማትን በማካተት ወንጀሉን መከላከል የሚያስችሉ የግንዛቤና የሥራ እድል ፈጠራ እንዲሁም ተጋላጮችን ወደ ቤተሰቦቻቸው የመመለስ ተግባራትን በማከናወን ላይ ነው።   የክልሉ ስራና ስልጠና ቢሮ የስራ ስምሪትና የስራ ገበያ መረጃ ዳይሬክተር ጌታሰው መንጌ እንደገለጹት በ2017 በጀት ዓመት ዜጎች በሃገር ውስጥ የሥራ አማራጮችና በውጭ ሃገራት የሥራ ስምሪት ተጠቃሚ መሆን የሚያስችሉ ተግባራት ተከናውነዋል። በዚህም ለውጭ ሃገራት የሥራ ስምሪት ተገቢ ስልጠና በመስጠትና በሙያ ብቃት ተወዳዳሪ እንደሆኑ በማድረግ 87ሺህ 900 ዜጎች ወደ ተለያዩ ሃገራት በህጋዊ መንገድ ተልከዋል ብልዋል። በሃገር ውስጥ ከ1 አንድ 1 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የመስሪያ ቦታ በማመቻቸትና የመንቀሳቀሻ ብድር በመስጠት የስራ እድል መፈጠሩን አንስተዋል። ከዚህም በላይ በህገወጥ መንገድ ዜጎችን ድንበር ለማሻገር የሞክሩ ደላሎች እና ከ6 ሺህ በላይ ዜጎችን በህብረተሰቡ ጥቆማና በፀጥታ አካላት ክትትል ተይዘው ወደ ቤተሰቦቻቸው የመቀላቀል ሥራ መሰራቱንም አመልክተዋል። የተሰራው ሥራ ከችግሩ ስፋት አንፃር በቂ እንዳልሆነ ገልጸው፣ ቅንጅታዊ ስራን በማጎልበት የሃገር ውስጥ የስራ እድል ፈጠራና የውጭ ሃገራት የሥራ ስምሪት ተግባሩ እንዲጠናከር ይበልጥ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።   የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወንዳቸው ሰራው በበኩላቸው በሰዎች የመነገድና በህገወጥ መንገድ ሰዎችን የማሻገር ወንጀል በህግ የተከለከለና ለቅጣት የሚዳርግ ተግባር ነው። በዚህም ወንጀሉን ለመከላከል ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ጥምረት ተዋቅሮ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው፣ በተግባሩ ሲሳተፉ የተገኙ ደላሎችን በህግ እንዲጠየቁ በማድረግ እስከ 21 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ ተደርጓል ብለዋል። ይህን አጠናክሮ ከማስቀጠል ጎን ለጎን በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ይበልጥ አተኩሮ መስራት ይገባል ነው ያሉት።   ዜጎች በህገወጥ መንገድ ወደ ተለያዩ የውጭ ሃገራት ሄደው ለመስራት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለከፍተኛ ጉዳት እየተጋለጡ ነው ያሉት ደግሞ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ ብርሃኑ ጎሽም ናቸው። በርካታ ዜጎች በደላሎች ተታለው ባህር አቋርጠው ለመውጣት በሚያደርጉት ህገወጥ እንቅስቃሴ ህይወት እስከማጣት የደረሱበት አጋጣሚ እንዳለም አስታውሰዋል። ችግሩን ለመከላከል በክልሉ የተቋቋመው ጥምረት እየሰራ ቢሆንም በቅንጅት መጓደል ምክንያት የሚፈለገውን ያህል ውጤት እየተገኘ እንዳልሆነም አመልክተዋል። በቀጣይ በዚህ የወንጀል ድርጊት የሚሳተፉ ደላሎች ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገር ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር የሃገር ውስጥ እና ህጋዊ የውጭ ሃገራት የሥራ ስምሪት ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በመድረኩ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ የጥምረቱ አባላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ የህክምና አገልግሎት ለበሽታ ቅድመ መከላከል ስራዎች ትኩረት ተሰጥቷል - ጤና ሚኒስቴር
Aug 6, 2025 75
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2017(ኢዜአ)፦ በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ የህክምና አገልግሎት ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን መከላከል እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በምርመራ በመለየት ለቅድመ መከላከል ስራዎች ትኩረት መሰጠቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ጋር በመሆን የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የጤና ምርመራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሂዷል።   አገልግሎቱ "በጎ ፈቃደኝነት ለጤናማ ማህበረሰብ" በሚል መሪ ሀሳብ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የጤና ምክር፣ ምርመራና ህክምና የሚሰጥበት ነው። የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በጤናው ዘርፍ በርካታ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ተከናውነዋል። በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ የህክምና አገልግሎት ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን መከላከል ላይ በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።   እንዲሁም ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በተመለከተ ምርመራ በማድረግ የመለየትና የቅድመ መከላከል ስራዎች ይከናወናሉ ነው ያሉት። የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ላይ መገናኛ ብዙኃን እያበረከቱት ያለው አስተዋፅኦ የሚበረታታ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፥ በየዓመቱ እያደገ የመጣውን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ጠቁመዋል።   የአዲስ አበባ የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽነር ይመር ከበደ በበኩላቸው ሆስፒታሉ ለሚሰጠው የበጎ ፈቃድ የህክምና አገልግሎት ኮሚሽኑ አስፈላጊውን ትብብር ያደርጋል ብለዋል። የኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሙሉቀን ተስፋዬ፥ አገልግሎቱ የጤና ባለሙያዎች በጎነትን በተግባር የሚያሳዩበት ነው ብለዋል።   ሆስፒታሉ ላለፉት ሶስት ዓመታት ከፍለው መታከም ለማይችሉ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች የክረምት በጎ ፈቃድ የህክምና አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን ጠቅሰው፥ ዘንድሮም ይህንኑ ሚናውን አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት። በበጎ ፈቃድ የህክምና አገልግሎት ተሳታፊ የሆኑት ዶክተር የትናየት በቀለ እና ዶክተር ነብዩ ዛራ፥ ከፍለው መታከም ለማይችሉ የማህበረሰብ ክፍሎች በሚሰጠው ነፃ የህክምና አገልግሎት በመሳተፋቸው የህሊና እርካታ እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል።   ከበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ተጠቃሚዎች መካከል ሊቀ ትጉሃን ያሬድ አበበ የአይን ምርመራ ለማድረግ መምጣታቸውንና በሀኪሞቹ ምክር ሙሉ የጤና ምርመራ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። መንግስት ከፍለው መታከም ለማይችሉ ዜጎች ነፃ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረጉ የሚበረታታና ተስፋ ሰጪ ጅማሮ ነው ብለዋል።   ወይዘሮ እታገኝ ትርፌ በበኩላቸው በጤና ባለሙያዎቹ ልጃቸው ነጻ የተለያዩ የጤና ምርመራዎች እንደተደረገለት ገልፀዋል። የበጎ ፈቃድ የህክምና አገልግሎቱ በህክምና ወጪ ምክንያት ሳይታከሙ በየቤቱ ላሉ ሰዎች ትልቅ እፎይታ የፈጠረ መሆኑን የገለጹት ደግሞ አቶ ግርማ አለማየሁ ናቸው።    
የአካባቢያቸውን ሰላም ለማጠናከር የበኩላቸውን እንደሚወጡ የወልዲያ ከተማ የሀገር ሽማግሌዎች ገለጹ
Aug 6, 2025 62
ወልዲያ ሐምሌ 30/2017(ኢዜአ):-ከአባቶቻችን በወረስነው የሽምግልና ባህልና ወግ መሰረት የአካባቢያችንን ሰላም ለማጠናከር የድርሻችንን እንወጣለን ሲሉ የወልዲያ ከተማ የሀገር ሽማግሌዎች ገለጹ። የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሃይማኖት አባቶችና ከእድር አመራሮች ጋር በከተማዋ ሰላምን በዘላቂነት ማስፈን በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ዛሬ መክሯል።   በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የሀገር ሽማግሌዎች እንዳሉት በተለያዩ ጊዜያት በተከሰቱ ግጭቶችና የሰላም እጦቶች ምክንያት የሰው ህይወት ሲጠፋና ንብረት ሲወድም ቆይቷል። ከሀገር ሽማግሌዎች መካከል ሐጅ አሊጋዝ አስረስ እንዳሉት ችግሮችንና ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ተነጋግሮ በመፍታት ትኩረትን ሙሉ ለሙሉ ወደ ልማት መዞር ይገባል። በአካባቢያችን በሰላም እጦት በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ሲደርስ የነበረን ጉዳት ለማስቆም እንደ ሀገር ሽማግሌ የበኩላችንን እንወጣለን ሲሉም አረጋግጠዋል። ሁላችንም ችግሮችን ተረባርበን በመፍታት ለሰላም ቅድሚያ ሰጥተን መስራት አለብን ያሉት የሀገር ሽማግሌው፣ "ከአባቶቻችን በወረስነው ባህልና ወግ መሰረት በጫካ ያሉ ወንድሞቻችን ወደሰላማዊ ኑሮ እንዲመለሱ የድርሻዬን እወጣለሁ" ብለዋል። "ከተማችን ትልማ፣ አገራችንም ትደግ ብለን የምናስብ ከሆነ ለአካባቢያችን ዘላቂ ሰላም የምንቆጥበው ጉልበትና ጊዜ ሊኖር አይገባም" ያሉት ደግሞ አቶ አሰፋ ደስታ የተባሉ የሀገር ሽማግሌ ናቸው። በወንድማማቾች መካከል መጠፋፋት እንዲቆም፣ ሰላም እንዲሰፍን፣ ልማት እንዲፋጠንና ህብረተሰቡም በነጻነት መንቀሳቀስ እንዲችል ለዘላቂ ሰላም በትጋት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። መንግስት እስከዛሬ ያሳየውን ሆደ ሠፊነት አጠናክሮ እንዲቀጥል የጠየቁት የሀገር ሽማግሌው፣ በጫካ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ታጣቂዎች ለሀገርና ለህዝብ ሲሉ ወደ ሠላማዊ ህይወት እንዲመለሱ ለማድረግ ተግተው እንደሚሰሩ ገልጸዋል።   የወልዲያ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ በበኩላቸው እንደገለጹት የከተማዋን ሰላም በዘላቂነት ማረጋገጥ የሚቻለው ሁሉም ለሰላም መስፈን በቁርጠኝነት ሲሰራ ነው። በዚህም በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎች ከማህበረሰቡ የተሰወሩ ባለመሆናቸው በቤተሰብ፣ በጎረቤትና በእድር በመምከር ወደ ሠላማዊ ህይወት እንዲመለሱ ማድረግ ከሀገር ሽማግሌዎች ይጠበቃል ብለዋል። ባለፉት ሁለት ዓመታት በሰላም እጦት በሰውና በንብረት ላይ ሲደርስ የነበረን ጉዳት በማስቀረት አካባቢውን የዘላቂ ሰላም፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ የሀገር ሽማግሌዎች የጀመራችሁትን የሰላም ጥረት አጠናክራችሁ ልትቀጥሉ ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል። በመድረኩ ማጠናቀቂያ ላይ የወልዲያ ከተማን የወከሉና 21 አባላት ያሉት የሰላም አፈላላጊ የአገር ሽማግሌዎች ተመርጠዋል።    
ኢኮኖሚ
መንግስት የትይዩ የውጭ ምንዛሬ ለማስፋት እየሰሩ ባሉ ህገ ወጥ ድርጅቶች ላይ ጠንካራ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን ይቀጥላል- አቶ ማሞ ምህረቱ
Aug 6, 2025 98
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2017(ኢዜአ)፦ መንግስት ከገበያ ባፈነገጠ ሁኔታ የትይዩ የውጭ ምንዛሬ እንዲስፋፋ በሚሰሩ ህገ-ወጥ ድርጅቶች ላይ ጠንካራ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ገለጹ። በህገ-ወጥ ድርጊቱ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች እንደ አስፈላጊነቱ ለህዝብ ይፋ ይደረጋሉም ብለዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ወቅታዊ የውጭ ምንዛሪ ገበያን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል። አቶ ማሞ ባንኩ በመደበኛነት እያካሄደ ያለውን የውጭ ምንዛሬ ጨረታውን ለመቀጠል መወሰኑንም ገልጸዋል። ባለፈው ዓመት የብሔራዊ የውጭ ምንዛሬ መጠባበቂያ ክምችት በሶስት እጥፍ መጨመሩ እና ይህ መልካም ውጤት በተያዘው በጀት መቀጠሉ እንዲሁም የባንኩ የውጭ ምንዛሬ ፍሰት እና ግኝት ከተጠበቀው በላይ ማደጉ ጨረታው እንዲቀጥል ምክንያት መሆናቸውን አመልክተዋል። ከውጭ ምንዛሬ ገቢው ከፊሉ ለባንኮች መቅረቡ ባንኮች ያላቸውን የውጭ ምንዛሬ ከማሳደግ ባሻገር ዋጋ እና የውጭ ምንዛሬ የማረጋጋት ስራን ለማሳካት እንደሚያግዝ ተናግረዋል። ትናንት በተደረገው የ150 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ 28 ባንኮች በጨረታው መሳተፋቸውን ገልጸው ሁሉም ባንኮች የሚፈልጉትን የውጭ ምንዛሬ ማግኘታቸውንና አንድ ዶላር 138 ብር መሸጡን ጠቁመዋል። ባንኮቹ በጨረታው ያገኙትን ጨምሮ የራሳቸውን ገቢ በመጨመር በቂ የውጭ ምንዛሬ እንደሚያቀርቡ ይጠበቃልም ነው ያሉት። የንግዱ ማህበረሰብ እና የግሉ ዘርፍ ባንኮች በሚያቀርቡትን የውጭ ምንዛሬ እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል። በሌላ በኩል አብዛኞቹ የንግድ ማህበረሰብ አባላት በመደበኛ እና ህጋዊ የውጭ ምንዛሬ ስርዓት ውስጥ የሚሳተፉ ቢሆንም አንዳንዶች በትይዩ የውጭ ምንዛሬ ገበያ ውስጥ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ነው የባንኩ ገዥ ያመለከቱት። በህገ ወጥ ድርጊቱ ላይ የሚሳተፉ የንግዱ ማህበረሰቦች ወደ መደበኛ ስርዓቱ እንዲመለሱ ያሳሰቡ ሲሆን ከድርጊታቸው በማይቆጠቡት ላይ ሀብታቸውን እስከ መውረስ የሚደርስ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቀዋል። ባንኮች ከውጭ ምንዛሬ አቅርቦት ጋር በተገናኘ በንግዱ ማህበረሰብ አባላት ይቀርብባቸው የነበሩ አብዛኞቹ ቅሬታዎች መፈታተቸውን የገለጹት አቶ ማሞ ቀሪ ተግዳሮቶች መፍትሄ እንዲያገኙ እየሰሩ ይገኛል ነው ያሉት። ብሄራዊ ባንክ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ስርዓት ተአማኒነት ሆን ብለው ለመሸርሸር እና የገበያ ዋጋ መዛባትን በማለም እየሰሩ ያሉ በውጭ የሚገኙ ህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሬ አዘዋዋሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን እንደሚቀጥልም አስገንዝበዋል። ባንኩ እንደ አስፈላጊነቱ በዚህ ህገ ወጥ ተግባር ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን ስም ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል። ተቀማጭነታቸውን በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ዱባይ ያደረጉ ከገበያ ባፈነገጠ ሁኔታ የትይዩ ገበያውን ለማስፋት በሚሰሩ ህገወጥ ድርጅቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድም አብራርተዋል። አሳሳች መረጃን ከማሰራጭት ጋር በተያያዘም ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ነቀፌታ አቅርቧል የሚለው መረጃ መሰረተ ቢስ እና ከእውነት የራቀ መሆኑን ነው ያብራሩት። አይኤምኤፍ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ያለው አጠቃላይ እይታ እጅግ አዎንታዊ ነው ያሉት አቶ ማሞ የሚያወጣቸው መረጃዎች እና ሪፖርቶች ይሄን የሚያመላክቱ ናቸው ብለዋል። በውጭ ምንዛሬ ስርዓት እና አጠቃላይ የኢኮኖሚ ሪፎርሙ የተገኙ አዎንዊ ውጤቶች ኢትዮጵያ በትክክለኛ የእድገት ጎዳና ላይ እንደምትገኝ ያሳያሉ ነው ያሉት። በአዲሱ በጀት መጀመሪያ ላይ የታየው አበረታች የውጭ ምንዛሬ ክምችት እድገት በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። አቶ ማሞ ማህበረሰቡ ከሀሰተኛ መረጃዎች እና አሳሳች አሉባልታዎች ራሱን በመጠበቅ መደበኛ የንግድ እንቅስቃሴውን ያለ ምንም ስጋት እንዲያከናውን ጥሪ አቅርበዋል።
የባህር ዳር ከተማ የኮሪደር ልማት መንግስት ለሰው ተኮር ልማት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው
Aug 6, 2025 63
ባህር ዳር፤ ሐምሌ 30/2017(ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት መንግስት ለሰው ተኮር ልማት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ሲሉ የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ መንገሻ ፈንታው(ዶ/ር) ገለጹ። የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ፣ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ የአማራ ስቴት ዩኒቨርሲቲ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አመራሮችና ሠራተኞች የከተማዋን የመሰረተ ልማት እንቅስቃሴ ዛሬ ጎብኝተዋል። የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታው(ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንደገለጹት መንግስት ከተሞችን ለማዘመንና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ መሰረተ ልማቶችን በስፋት እየገነባ ነው። በባህር ዳር ከተማ ግንባታው እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማትም ከተማዋ ያላትን የተፈጥሮ ጸጋ ለነዋሪዎቿና ለጎብኚዎች የገለጠ መሆኑን ገልጸዋል።   ልማቱ መንግስት ለሰው ተኮር ልማት ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር በማረጋገጥ አርአያነት ያለው ተግባር መሆኑንም ተናግረዋል። የኮሪደር ልማቱ ባህር ዳር ከተማ የቱሪስትና የኢንቨስትመንት መዳረሻነቷን በማሳደግ የህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል። በመሆኑም የኮሙኒኬሽንና የመገናኛ ብዙሃን በከተማዋ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን በአግባቡ በማስተዋወቅ የከተማዋን ገጽታ ከመገንባት ባለፈ የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኚዎችን ለመሳብ በትኩረት እንዲሰሩ አሳስበዋል። የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አስሜ ብርሌ በበኩላቸው የከተማዋን የልማት ሥራዎች ለማስተዋወቅ የተጀመረው ሥራ ቀጣይነት ባለው መልኩ ይከናወናል ብለዋል። ይህም በከተማዋ ስለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ህብረተሰቡ በስፋት ግንዛቤ እንዲኖረው ከማድረግ ባለፈ በቀጣይ ለከተማዋ ልማት የሚያደርገውን ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚያስችል አስረድተዋል። በከተማዋ ግንባታው እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት የከተማ አስተዳደሩ ችግሮችን ተቋቁሞ ልማትን ለማፋጠን ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል። ከኮሪደር ልማቱ በተጨማሪ የባህር ዳር ከተማን የቱሪስት ማዕከል ማድረግ የሚያስችሉ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ምክትል ከንቲባው ጨምረው ገልጸዋል።
በምስራቅ ወለጋ ዞን ቢሎ ቦሼ ወረዳ ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ከ39 በላይ ፕሮጀክቶች ተመረቁ
Aug 6, 2025 58
ጊምቢ፤ ሀምሌ 30/ 2017 (ኢዜአ) ፡-በምስራቅ ወለጋ ዞን ቢሎ ቦሼ ወረዳ ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ከ39 በላይ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቁ። በፕሮጀክቶቹ የምርቃ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት በብልፅግና ፓርቲ የምስራቅ ወለጋ ዞን ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍቃዱ ገመዳ፤ በሁሉም አካባቢዎች ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።   የህዝብን የልማትና የተጠቃሚነት ጥያቄዎች መንግስት በሂደት ምላሽ እየሰጠ መሆኑን አንስተው በቢሎ ቦሼ ወረዳ የተከናወነውም ይሄው መሆኑን ተናግረዋል። በወረዳው ከ109 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የትምህርት ቤትና የመንገድ ግንባታ፣ የመጠጥ ውሃእና የመስኖ ፕሮጀክቶች እና ሌሎችንም ጨምሮ በድምሩ ከ39 በላይ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት በቅተዋል ብለዋል።   በዞኑ የልማት ስራዎች በልዩ ትኩረት መከናወናቸውንና በመከናወን ላይ የሚገኙ እንዳሉም ጠቅሰው ሰላምን አስቀድመን ልማትን አጠናክረን ለሀገራዊ ብፅግና ስኬት እንሰራለን ሲሉ አረጋግጠዋል። የቢሎ ቦሼ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ በየነ ሞረዳ፤ የወረዳው ህዝብ ለልማት ባለው ቁርጠኝነትና በሚያደርገው ተሳትፎ በመታገዝ አስተዳደሩ ስኬታማ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በወረዳው ለተከናወኑት ፕሮጀክቶች ወጪ በማድረግ የመንግስት ሚና ከፍተኛ መሆኑን አስታውሰው የህብረተሰቡ እና የተለያዩ ተቋማትም እገዛ እንዳለበት አንስተዋል።   ከቢሎ ቦሼ ወረዳ ነዋሪዎች መካከል አቶ አብዱልቃዲር ኡስማን እና ወይዘሮ አስናቁ ተካልኝ፤ ፕሮጀክቶቹ በጥራትና በፍጥነት ተጠናቀው ለአገልግሎት በመብቃታቸው ተደስተናል ብለዋል። የተመረቁት የልማት ፕሮጀክቶች ከዚህ በፊት በአካባቢው ይስተዋሉ የነበሩ የአገልግሎት ችግሮችን የፈቱ ስለመሆናቸውም አንስተዋል። በመሆኑም ለልማቱ መሳካት የመንግስት አካላት፣ ተቋማትና ሌሎችም ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል።
በምሥራቅ ጎጃም ዞን ከ77 ሺህ በላይ የሀይል አማራጮች ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ሆነዋል
Aug 6, 2025 99
ደብረ ማርቆስ ፤ ሐምሌ 30/2017 (ኢዜአ) ፡- በምሥራቅ ጎጃም ዞን በ2017 የበጀት ዓመት ከ77 ሺህ በላይ የሀይል አማራጮችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ማድረጉን የዞኑ ውሃና ኢነርጂ መምሪያ ገለጸ። ቀደም ባሉት ዓመታትም ከ900 ሺህ በላይ የሀይል አማራጮች ተደራሽ ማድረግ መቻሉ ተመልክቷል። የመምሪያው ሃላፊ አቶ ፍሬው ካሴ ፤ በዞኑ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ60ሺህ በላይ የሀይል አማራጮችን ለማከፋፈል ታቅዶ ከ77ሺህ 500 በላይ ማሰራጨት መቻሉን ለኢዜአ ተናግረዋል። ክንውኑም ከታቀደው በላይ እንደሆነ አመልክተው፤ በገጠር የሚኖረውን ማሕበረሰብ የሀይል ተጠቃሚ ለማድረግ ከተሰራጩት ውስጥ ከ32 ሺህ በላይ በጸሃይ የሚሰሩ፣ 45 ሺህ 406 በላይ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃና 177 በ የባዮ ጋዝ አማራጭ እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል። በዚህም ከ200ሺህ በላይ የማሕበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስታውቀዋል። የሀይል አማራጮችን ተደራሽ ለማድረግም በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም በሕብረተሰቡ የጉልበት ተሳትፎ ጨምሮ ከ15ሚሊየን ብር በላይ አስተዋጽኦ መደረጉን አስረድተዋል። በተለይም ከባዮ ጋዝ ሀይል ግንባታው የሚወጣው "ባዮ ሳለሪ " የተበላው ተረፈ ምርት እንደ ተፈጥሮ ማዳበሪያ በማገልግል የአርሶ አደሮቹን ምርታማነት ለማሳደግ ማገዙን ተናግረዋል። ከተጠቃሚዎች መካከል በጎዛምን ወረዳ የጥጃን ቀበሌ አርሶአደር ሞላልኝ ክብረት በሰጡት አስተያየት፤ በዚህ ዓመት ባዮጋዝ በመገንባት ለመብራትና ለምግብ ማብሰያነት እየተጠቀሙበት መሆኑን ገልጸዋል።   ከዚህ በፊት ለመብራትና ለምግብ ማብሰያነት ናፍጣ በመግዛትና ከደን ዛፎችን በመቁረጥ ይጠቀሙ እንደነበር አውስተው፤ ይህም በጭስ ምክንያት ቤተሰባቸው ለዓይን ህመም ተጋላጭ ሆነው እንደቆዩ አውስተዋል። አሁን የባዮ ጋዝ በመጠቀማቸው ችግሩ ከመፍታቱም በላይ ተረፈ ምርቱን በማዳበሪያነት በመጠቀማቸው ለአፈር ማዳበሪያ ግዥ ያወጡት የነበረውን ወጪ መቀነስ እንዳስቻላቸው ተናግረዋል። በአዋበል ወረዳ የወጀል ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ ዘውዲቱ ጥላሁን በበኩላቸው፤ በፊት የእንጨት ማገዶ በመጠቀም ምግብ በሚያበስሉበት ወቅት ለጭስ በመጋለጣቸው ሕመም ገጥሟቸው እንደነበር አስታውሰዋል። በዚህ ዓመት ዘመናዊ ምድጃዎችን በመጠቀም ጤናቸውን መጠበቅ መቻላቸውን ተናግረዋል። ከውሃና ኢነርጂ መምሪያው የተገኘው መረጃ እንደሚመለክተው፤ በምሥራቅ ጎጃም ዞን ባለፉት ዓመታት ከ900 ሺህ በላይ የሀይል አማራጮች ለሕብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ተችሏል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የዲጂታል ቴክኖሎጂ እውቀትና የፈጠራ አቅማችንን ለማዳበር እያገዘን ነው
Aug 6, 2025 58
ዲላ፤ ሐምሌ 30/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የዲጂታል ቴክኖሎጂ እውቀትና የፈጠራ አቅማቸውን ለማዳበር እያገዛቸው መሆኑን በዲላ ከተማ የኢትዮ ኮደርስ ሰልጣኞች ገለጹ። በከተማ አስተዳደሩ ከ3ሺህ 500 በላይ ዜጎች የሚሳተፉበት የክረምት ወራት የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ማስጀመሪያ መድረክ ዛሬ ተካሂዷል።   ከከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ሠራተኞች መካከል አቶ ሚካኤል ተሰማ ለኢዜአ እንደገለጹት ቀደም ሲል በወሰዱት የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ እውቀት መጨበጣቸውን ገልጸዋል። ይህም የመንግስት ሥራቸውን በቴክኖሎጂ ታግዘው ለማከናወን ዕድል ከመፍጠሩና የዲጂታል ክህሎታቸውን ከማዳበር በሻገር ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንዳስቻላቸው ተናግረዋል።   በፋንዳሜንታል ፕሮግራምና በሰው ሰራሽ አስተውሎት የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ወስዳ ማጠናቀቋንና በዚህም የፈጠራ አቅሟን ማሳደጓን የተናገረችው ደግሞ ተማሪ መልካም አስራት ናት። ለዚህም ቃላትን፣ ተንቀሳቃሽ ምስልና ፎቶዎችን ያካተተ የቋንቋ መማሪያ ሶፍት ዌር ማበልጸጓን ጠቅሳለች። ሶፍት ዌሩ ጀማሪ ሕጻናትን ሳቢ በሆነ መንገድ የአካባቢና ዓለም አቀፍ ቋንቋዎችን በቀላሉ እንዲማሩ የሚረዳ መተግበሪያ መሆኑንም ገልጻለች። የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የፈጠራ አቅሟን ከማጎልበት በተጨማሪ ለቀለም ትምህርቷ እና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዓለምን ለመረዳት እያገዛት መሆኑን ተናግራለች።   የዲላ ከተማ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ ኢሣያስ ተፈራ በበኩላቸው በከተማው ባለፈው ዓመት 1ሺህ 951 ሰዎች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ወስደዋል ብለዋል። በተያዘው የክረምት ወራትም 3ሺህ 502 ዜጎችን ለማሰልጠን ዝግጅት መደረጉን አንስተው፣ በስልጠናው የኔትወርክ መሰረተ ልማት ውስንነት እንደይገጥም ስድስት ማዕከላት መደራጀታቸውን ገልጸዋል። በስልጠናው ወጣቶች፣ የመንግስት ሠራተኞችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጎን ለጎን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በመውሰድ ራሳቸውን እንዲያበቁ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።   የከተማው ነዋሪዎች በስልጠናው የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ መፋጠን የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው ያነሱት ደግሞ የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መስፍን ደምሴ(ዶ/ር) ናቸው። በተለይ የኮደረስ ስልጠና ዲጂታል እውቀታቸውንና ክህሎታቸውን በማሳደግ የሀገር ውስጥና የውጪ ሥራ እድል ተጠቃሚነታቸውን እንደሚያሰፋ ገልጸዋል።   በመሆኑም ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ በኮዲንግ ስልጠና አቅሙንና ክህሎቱን በመሳዳግ ለዲጂታል ዓለም ብቁ ዜጋ ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዝ አስገንዝበዋል። በመድረኩ የክረምት ወራት የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናን ከማስጀመር በተጨማሪ ቀደም ሲል ስልጠናቸውን ወስደው ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት ተበርክቷል።
በክልሉ መናኸሪያዎች የተጀመረው የ"ኤሌክትሮኒክስ " ክፍያ የአሰራር ስርዓት ለተጓዦች ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ ነው
Aug 5, 2025 92
ባሕርዳር፤ሐምሌ 29/2017 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል የተሽከርካሪ መናኸሪያዎች የተጀመረው የኤሌክትሮኒክስ ( የኢ-ትኬት) ክፍያ የአሰራር ስርዓት ለተጓዦች ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ ተገለጸ። የክልሉ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ባለስልጣን አመራሮች በቀድሞ የባሕርዳር የተሽከርካሪ መናኸሪያ የተተገበረውን የመንገደኞች ኤሌክትሮኒክስ የትኬት ክፍያ ስርዓት ተመልክተዋል።   ‎በዚህ ወቅት ‎የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘውዱ ማለድ እንደገለጹት፤ በመናኸሪያዎች ውስጥ ከዚህ በፊት ጫኝ እና አውራጅ እንዲሁም ህገ ወጥ አሽከርካሪዎች በተጓዦች ላይ እንግልትና ጫና ሲያደርሱ ቆይተዋል።   ተጓዡን ለአላስፈላጊ ብዝበዛ ጭምር ሲዳርግ የቆየውን ይህንን ኋላ ቀር አሰራር ለማስወገድ በ2016 ዓ.ም በስድስት መናኸሪያዎች ውስጥ የኤሌክትሮኒክስ(የኢ-ትኬት) ክፍያ ስርዓት እንደተጀመረ አውስተዋል። በእነዚህ የተገኘውን መልካም ተሞክሮ በመጠቀምና በማስፋት አሁን ላይ በ32 መናኸሪያዎች የኤሌክትሮኒክስ (የኢ-ትኬት) ክፍያ ስርዓት ተዘርግቶ መተግበር መቻሉን አስታውቀዋል።   ይህም ለተጓዦች ‎ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ሕብረተሰቡ በሚታወቅ ተሽከርካሪ እና የታሪፍ ክፍያ ወደ ፈለገው አካባቢ በነጻነት የሚጓዝበት አሰራር ጭምር መሆኑን ገልጸዋል። ‎ስርዓቱ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርግና ትርፍ ለመጫን የሚሞክር አሽከርካሪ ካለ ትኬቱ ላይ በሚገኘው ስልክ ቁጥር በመደወል ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል። ‎ይህም ተገልጋዮች በተደጋጋሚ ሲያነሱት የቆየውን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በዘላቂነት ለመመለስ ባለስልጣኑ በልዩ ትኩረት በመስራቱ የተገኘ ውጤት መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል። ‎በክልሉ 252 የተሽከርካሪ መናኸሪያዎች እንደሚገኙ ያወሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ በ2018 በጀት ዓመት በሁሉም መናኸሪያዎች የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አሰራር ስርዓት ተዘርግቶ ለመተግበር እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ‎በባሕርዳር የተሽከርካሪ መናኸሪያ ‎ኢዜአ ያነጋገራት ተጓዥ ወጣት ሶስና ደሳለኝ በሰጠችው አስተያየት ፤ የኢ-ትኬት ስርዓቱ የተሳፋሪዎችን መብት ያስከበረና አላስፈላጊ ግፊያን ማስቀረት የቻለ ነው ብላለች።   ‎ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር በየመንገዱ ትርፍ እየተጫነና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ተሳፋሪው እንዲከፍል እየተደረገ እንደነበር አስታውሳ፤ አሁን ላይ ችግሩ በመቃለሉ የሚያስደስት መሆኑን ገልጻለች።
የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የተሻለ የዲጂታል እውቀትና ክህሎት እንዲኖረን ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል
Aug 5, 2025 137
‎ወልቂጤ፤ ሐምሌ 29/2017 (ኢዜአ):- የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የተሻለ የዲጂታል እውቀትና ክህሎት እንዲኖረን ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ሲሉ በወልቂጤ ከተማ ስልጠናውን እየወሰዱ ያሉ ተማሪዎች ተናገሩ። ‎‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በበኩሉ በክረምት ወራት በእረፍት ላይ ያሉ ተማሪዎች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና እንዲወስዱ ሁኔታዎች ተመቻችተው ወደ ተግባር መገባቱን አስታውቋል።   ስልጠናውን እየተከታተሉ ካሉ ተማሪዎች መካከል በከተማው ያበሩስ ትምህርት ቤት 12ኛ ክፍል ተማሪ ኤሰትን ሲሳይ እየወሰዱት ያለው ስልጠና ዲጂታል እውቀትና ክህሎትን ለመጨበጥ እንዳስቻላቸው ተናግሯል። መንግስት ስልጠናውን በነጻ ማመቻቸቱንና እሱም ተጠቃሚ መሆኑን ገልጾ፣ በተለይ ወጣቱ ትውልድ ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር አብሮ እንዲጓዝ ታስቦ ስልጠናው በመንግስት በመመቻቸቱ አመስግኗል። ‎በስልጠናው እያገኘ ያለው ዲጂታል እውቀት በቀጣይነት ከመደበኛ ትምህርቱ ጎን ለጎን በቴክኖሎጂ ራሱን እያሳደገ ለመምጣት መነሳሳት እንደፈጠረበት ተናግሯል።   ‎በወልቂጤ ከተማ ጃይካ ትምህርት ቤት የዘጠነኛ ከፍል ተማሪዋ ሃሮት ኪዳኔ፤ የኮደርስ ስልጠና የክረምት የእረፍት ጊዜዋን ባልተገባ ቦታ እንዳታሳልፍ ያገዛት መሆኗን ገልጻለች። ‎ስልጠናው ለቴክኖሎጂ ያላትን ቅርበት እያሳደገላት መሆኑን ጠቁማ፣ ዘመኑ ዲጂታል በመሆኑ በቴክኖሎጂ እውቀት ብቁ ሆና ለመገኘትና ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ የስልጠናው ጠቀሜታ የጎላ ነው ብላለች። መደበኛ ትምህርት ቤቶች ዝግ በመሆናቸው ወጣቶች የእረፍት ጊዜያቸውን የኮደርስ ስልጠና በመውሰድ ራሳቸውን ለማብቃት እንዲጠቀሙበትም መክራለች። ‎ወጣቶች ጊዜው የሚጠይቀውን የቴክኖሎጂ እውቅት በመጨበጥ ብቁና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ስልጠናው በተለያዩ የዞኑ ተቋማት እየተሰጠ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የጉራጌ ዞን ሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያ ሃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ ናቸው።   ‎እንደእሳቸው ገለጻ በዞኑ ከፍተኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የስልጠና ማዕከላት ተዘጋጅተው ወደ ተግባር ተገብቷል። በአሁኑ ወቅትም ከ9 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናቸውን እየተከታተሉ መሆኑን ተናግረዋል። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ስልጠናውን የወሰዱ ተማሪዎች መካከል አንዳንዶቹ ድረ ገጽ እስከማልማት መድረሳቸውንም ገልጸዋል። ‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ሃላፊ እና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ ልማትና እና አስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ አቶ ከበደ ሻሜቦ እንዳሉት የኮደርስ ስልጠና በንቃት እየተሰጠ ነው።   በዲጂታል እውቀት የጎለበተ ዜጋ ለመፍጠር የተያዘውን ሀገራዊ ራዕይ ለማሳካት የሚያስችል ስራ ትኩረት ተሰጥቶ እየተከናወነ መሆኑንም ጠቁመዋል። ‎የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የሰልጣኞችን የቴክኖሎጂ እውቀት በማጎልበት የፈጠራ አቅም እና ተወዳዳሪነታቸውን እያሳደገው መሆኑንም አቶ ከበደ አስታውቀዋል። እንደ እሳቸው ገለጻ ‎በክልሉ በተያዘው የክረምት ወቅት ከ50 ሺህ በላይ ተማሪዎች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የአፍሪካ ድምጽ ለመሆን የጀመራቸው እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Aug 4, 2025 130
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 28/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የአፍሪካ ድምጽ ለመሆን የጀመራቸው እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አሳሰቡ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የኢትዮጵያን አቋም ላለፉት ከ82 ዓመታት በላይ በማይናወጥ መልኩ ለዓለም ያስተጋባውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ)ን ዛሬ መጎብኘታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።   ኢዜአ ዛሬ ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግሯል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ታሪካዊ ዐሻራውን በአዲስ እሳቤ እያዳበረ ለስራ ምቹ የሆነ ከባቢን፣ ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ፣ ዘመናዊ ስቱዲዮዎችን በመገንባት የመጪው ዘመን ቀንዲል ሆኖ ለማገልገል በብዝኃ ቋንቋ ከኢትዮጵያ አልፎ አፍሪካን ለዓለም ለማሳየት የያዘው ግብ የሚደነቅ ነው ብለዋል። የሚዲያ ተቋሙ ሀገራዊ ጥቅሞችን እያስጠበቀ፣ የባህልና የቱሪዝም ሀብቶችን እያስተዋወቀ፣ መልካም ገፅታን ለዓለም እያሳየ ለመቀጠል በሰው ኃይልና በሚዲያ ቴክኖሎጂ ራሱን እያደራጀ መሆኑ ይበል የሚያሰኝ ጅምር እንደሆነም አመልክተዋል። በተለይ በውጭ ቋንቋዎች(Pulse of Africa) የአፍሪካ ድምጽ ለመሆን የጀመራቸው እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አሳስበዋል። የአፍሪካን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ራሳችን ተልመን፣ ራሳችን ሰርተን፣ ራሳችን ጽፈን፣ ራሳችን ለዓለም የምንናገረውና የምናሳየው መሆን ይኖርበታልም ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልክታቸው።   ለዚህ ደግሞ መንግስት ተቋሙ የጀመራቸውን ሀገራዊና አህጉራዊ የለውጥ አራማጅ ግቦች ለማሳካት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተናግረዋል። ኢዜአ ከዜና ባለፈ የህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ማፅኛ፣ አፍሪካውያን በራሳቸው አስተሳሰብ የራሳቸውን ታሪክ እንዲናገሩ ዋነኛ የትርክት ማሰራጫ መሰረተ ልማት ሆኖ እንዲቀጥል አደራ ብለዋል።   ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢዜአ ለጀመረው የለውጥ ስራ በትጋት ለሰሩና ለተባበሩ አካላት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ስፖርት
ቡርኪናፋሶ በቻን ውድድር የመጀመሪያ ድሏን አስመዘገበች
Aug 6, 2025 53
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2017(ኢዜአ)፦ በስምንተኛው የአፍሪካ አገራት ሻምፒዮና(ቻን) የምድብ ሁለት ጨዋታ ቡርኪናፋሶ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክን 4 ለ 2 ረታለች። በቤንጃሚን ምካፓ ስታዲየም ዛሬ በተካሄደው መርሃ ግብር ፓፑስ ናስር ኡታራ እና አብዱል ከሪም ባጉአን በጨዋታ፣ አብዱል አባስ ጉይሮ እና ፓትሪክ ማሎ በፍጹም ቅጣት የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ሲድኒ ቺፎርት ቺቢንዳ እና አንጌ ዙማራ ለማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ቺቢንዳ ሀገሩ በቻን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ባደረገችው ጨዋታ የመጀመሪያውን ጎል በማስቆጠር ታሪክ ሰርቷል። በጨዋታው ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በኳስ ቁጥጥር ብልጫ ብትወስድም ቡርኪናፋሶ ለግብ የቀረቡ እድሎችን በመፍጠር የተሻለች ነበረች። ውጤቱን ተከትሎ ቡርኪናፋሶ የመጀመሪያ ሶስት ነጥቧን በማግኘት በምድቡ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች። ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻው አምስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። በዚሁ ምድብ ሞሪታኒያ ከታንዛንያ ምሽት 2 ሰዓት በቤንጃሚን ምካፓ ስታዲየም ይጫወታሉ።
የቻን የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳሉ 
Aug 6, 2025 72
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2017(ኢዜአ)፦ በኬንያ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛንያ ጣምራ አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው ስምንተኛው የአፍሪካ አገራት ሻምፒዮና(ቻን) ዛሬ አምስተኛ ቀኑን ይዟል። ሀገራት ከዛሬ አንስቶ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። በምድብ ሁለት ቡርኪናፋሶ ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ቤንጃሚን ምካፓ ብሄራዊ ስታዲየም ይጫወታሉ። በቻን ውድድር ለአራተኛ ጊዜ የተሳተፈችው ቡርኪናፋሶ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ ባልተጠበቀ ሁኔታ በታንዛንያ 2 ለ 0 ተሸንፋ መጥፎ ጅማሮ አድርጋለች። በውድድሩ የመጀመሪያ ተሳትፎዋን ያደረገችው ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ካሜሮንን በመጨረሻው ዙር ማጣሪያ ጥላ በሻምፒዮናው ላይ መሳተፏ ማንም ያልጠበቀው ውጤት ነበር። ሁለቱ ሀገራት ከዚህ ቀደም አራት ጊዜ ተገናኝተው ቡርኪናፋሶ ሶስት ጊዜ ስታሸንፍ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ አንድ ጊዜ አሸንፋለች። ሁሉም ጨዋታዎች በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የተደረጉ ናቸው። መርሃ ግብሩ ቡርኪናፋሶ የመጀመሪያ ድሏን ለማስመዝገብ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ደግሞ በመጀመሪያዋ ጨዋታዋ ድል ለማስመዝገብ የሚያደርጉት መሆኑ ተጠባቂ ያደርገዋል። በዚሁ ምድብ ምሽት 2 ሰዓት ላይ ሞሪታኒያ ከታንዛንያ በቤንጃሚን ምካፓ ብሄራዊ ስታዲየም ይጫወታሉ። ሞሪታኒያ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ ከማዳጋስካር ጋር ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይታለች። ከጣምራ አዘጋጆቹ አንዷ የሆነችው ታንዛንያ ቡርኪናፋሶን 2 ለ 0 በማሸነፍ በድል ጀምራለች። ሁለቱ ሀገራት እርስ በእርሳቸው ሲገናኙ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ታንዛንያ ካሸነፈች ወደ ሩብ ፍጻሜ የመግባት እድሏን የበለጠ ታሰፋለች። በአንጻሩ ሞሪታኒያ በውድድሩ ለመቆየት ማሸነፍ ይጠበቅባታል። በስምንተኛው የቻን ውድድር 19 ሀገራት በአራት ምድብ ተከፋፍለው ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛል።
የወቅቱ የቻን አሸናፊ ሴኔጋል ክብሯን የማስጠበቅ ጉዞዋን በድል ጀምራለች
Aug 5, 2025 75
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2017(ኢዜአ)፦ በስምንተኛው የአፍሪካ አገራት ሻምፒዮና(ቻን) በምድብ አራት በተደረገ ጨዋታ ሴኔጋል ናይጄሪያን 1 ለ 0 አሸንፋለች። ማምሻውን በዛንዚባር አማኒ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ክርስቲያን ጎሚስ በ75ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል። ውጤቱን ተከትሎ የወቅቱ የዋንጫ ባለቤት ሴኔጋል ምድቡን በሶስት ነጥብ መምራት ጀምራለች። ናይጄሪያ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛለች። በዚሁ ምድብ ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ኮንጎ ብራዛቪል እና ሱዳን አንድ አቻ ተለያይተዋል። ታንዛንያ፣ ኬንያ እና ዩጋንዳ በጣምራ ያዘጋጁት ውድድር ዛሬ አራተኛ ቀኑን ይዟል። በሻምፒዮናው ላይ 19 ሀገራት በአራት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛል። ውድድሩ እስከ ነሐሴ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል። በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን የሚያነሳ ሀገር የ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት እንደሚያገኝ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አስታውቋል። አጠቃላይ ለውድድሩ ተሳታፊ ሀገራት የ10 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን ይህም አልጄሪያ ላይ ከተካሄደው ሰባተኛው የቻን ውድድር የ32 በመቶ ብልጫ አለው። ታንዛንያ፣ ኬንያ እና ዩጋንዳ እ.አ.አ በ2027 የሚካሄደው 36ኛውን የአፍሪካ ዋንጫም በጋራ ያዘጋጀሉ። የቻን ውድድር ለሀገራቱ የአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት የሚያገለግል ነው ተብሏል። እ.አ.አ በ2009 የተጀመረው ቻን በአገር ውስጥ ሊግ የሚገኙ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበት ውድድር ነው። ይህም ሀገር በቀል ተጫዋቾች የሚያገኙትን የጨዋታ እድል መጨመር ያለመ ነው። ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሞሮኮ በተመሳሳይ ሁለት ጊዜ ዋንጫውን ሲያነሱ ቱኒዚያ፣ ሊቢያ እና ሴኔጋል ቀሪ አሸናፊ ሀገራት ናቸው።
አካባቢ ጥበቃ
በመዲናዋ 44ሺህ 45 ሜትር ኪዩብ የኮንሶ እርከን ተሰርቷል - ባለስልጣኑ
Aug 6, 2025 82
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2017(ኢዜአ)፦ በመዲናዋ በተጠናቀቀው በጀት አመት 44ሺህ 45 ሜትር ኪዩብ የኮንሶ እርከን መሰራቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ። ባለስልጣኑ በ2017 በጀት አመት የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ዲዳ ድሪባ እንደገለጹት የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚችልና ስነምህዳሯ የተጠበቀ ከተማ ለማድረግ በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል።   የኮንሶ ሀገር በቀል እውቀትን በመጠቀም የአፈርና የውሃ እቀባዎች መሰራቱን አንስተው ለቱሪስት መስህብነትም ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። በባህላዊው የእርከን ስራው ከ600 በላይ የሚሆኑ ሰዎች መሳተፋቸውን ገልጸው፤ በዚህም 44ሺህ 45 ሜትር ኪዩብ የኮንሶ እርከን ተሰርቷል ብለዋል። ከእንጦጦ ወንዝ እስከ ራስ መኮንን ድልድይ በወንዙ ግራና ቀኝ አካባቢዎች፣ የቀበና ወንዝ፣ በአዲስ ኮንቬንሽን ማዕከል፣ በጎሮና ሌሎች አካባቢዎች የእርከን ስራዎቹ መከናወናቸውን ጠቅሰዋል። በወንዞች ዳርቻ የአፈር መከላትን ለመከላከልና ጎርፍን መቀነስ የሚያስችል በኮንሶ ባህላዊ አሰራር የጋብዮን ግንብ 7ሺህ 786 ሜትር ኪዩብ መገንባቱንም አክለዋል። እንደ ዋና ስራ አስኪያጁ ገለጻ በተፋሰስ ልማትና የወንዞች ዳርቻም ከቀበና እና እንጦጦ ወንዞች እስከ ፒኮክ አካባቢ ድረስ የወንዝ ዳርቻ ልማት ተከናውኗል። 438 ሄክታር የተጎዱ ቦታዎች ተለይተው የዝናብ ማቆሪያ፣ የድንጋይና የአፈር ክትር ስራዎች ተከናውነዋል ሲሉም ገልጸዋል።   በመዲናዋ የሚገኙ ወንዞችን በማጽዳት ብክለትን የመከላካል፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲኖራቸው የሚያስችሉ ስራዎች በስፋት እየተሰሩ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል። የወንዞች ልማትና ብክለትን ለመከላከል የወጣው ደንብ ላይ ለተለያዩ አካላት ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች መሰራታቸውንም ዋና ስራ አስኪያጁ አስታውቀዋል። ወንዞችን በበከሉ አካላት ላይ ከ2ሸህ እስከ 1 ሚሊየን ብር የሚደርስ የቅጣት እርምጃ መወሰዱንም ተናግረዋል።
የደንብ ጥሰት የፈጸሙ ከ3 ሺህ 200 በላይ ተቋማት እርምጃ ተወስዶባቸዋል
Aug 6, 2025 83
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2017(ኢዜአ)፦ የአየር እና የድምጽ ብክለት ህግን የተላለፉ ከ3 ሺህ 200 በላይ ተቋማት እርምጃ እንደተወሰደባቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ። ባለስልጣኑ በ2017 በጀት አመት የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ድሪባ እንደገለጹት በተጠናቀቀው በጀት አመት በከተማው የአካባቢ ፣ የድምፅና ፍሳሽ ብክለት እንዲሁም የአማቂ ጋዝ ልቀትን ለመቀነሰ የሚያስችሉ የቁጥጥር ስራዎች ተከናውነዋል፡፡ በዚህም በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ14 ሺህ 800 ተቋማት በላይ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች መከናወኑን አንስተዋል፡፡ ተቋማቱ በአካባቢ ላይ የድምጽና የአየር ንብረት ብክለት እንዳያስከትሉ ሙያዊ ድጋፍና ክትትል መደረጉን የገለጹት ስራ አስኪያጁ፤ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶአቸው ያላስተካከሉት ላይ እርምጃ መወሰዱንም ነው የተናገሩት። የደንብ ጥሰት በፈጸሙ 3 ሺህ 249 ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን ጠቅሰው በዚህም የተለያዩ ፋብሪካዎች፣ የምሸት ጭፈራ ቤቶችና ሌሎች ተቋማት እንደሚገኙበት ገልጸዋል። በተወሰደው ህጋዊ እርምጃም ለ3 ሺህ 66 ተቋማቱ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ሲሆን 183 ተቋማት ደግሞ እንዲታሸጉ መደረጉን አስታውቀዋል። በወንዝና ወንዝ ዳርቻ ላይ ብክለት ባደረሱ ተቋማት ላይ ከ120 ሚሊየን ብር በላይ ቅጣት መጣሉንም አክለዋል።
በምዕራብ ወለጋ ዞን ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ስራዎች ዘርፈ ብዙ ጥቅም እየሰጡ ነው
Aug 6, 2025 68
ጊምቢ፤ሀምሌ፤30/2017 (ኢዜአ) በምዕራብ ወለጋ ዞን ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ስራዎች ዘርፈ ብዙ ጥቅም እየሰጡ መሆኑን ኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተናገሩ። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የተራቆቱ አካባቢዎችን አረንጓዴ የማልበስና የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን የመከላከል አላማ ሰንቆ ባለፉት ሰባት ዓመታት እየተከናወነ ነው። በኢትዮጵያ መሰረታዊ ለውጥ የማምጣትና ከችግር የመውጫ አንዱ መንገድ ተደርጎ የተወሰደው ይኸው መርሃ ግብር በተደራጀና በተጠናከረ መልኩ ቀጥሏል። በዚህም መሰረት ዘንድሮ "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ሀሳብ በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል እቅድ ተይዞ 714 ነጥብ 7 ሚሊዮን በማሳካት አዲስ ታሪክ ማስመዝገብ ተችሏል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እንደ ሀገር ስኬት እየተመዘገበበት ጥቅሙም እየተገለጠ መምጣቱን በርካቶች ምስክርነታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ። በምዕራብ ወለጋ ዞንም የኢዜአ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ስራዎች ዘርፈ ብዙ ጥቅም እየሰጡ መሆኑን አረጋግጠዋል። ከዞኑ ነዋሪዎች መካከል አቶ ኤሊያስ ለሚ፣ አቶ ባልይና ተርፋ እና አቶ ጸጋዬ ተሰማ የአረንጓዴ አሻራ ልማት መርሐግብር በጋራ ሰርተን በጋራ የምንጠቀምበት ሃብት መሆኑን በተግባር እያረጋገጥን ነው ብለዋል።   በለውጡ ዓመታት በተከናወኑ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት እንዲሁም የቡና ልማት ተጨባጭ ውጤት የታየበት መሆኑን አንስተዋል።   ለአካባቢ ጥበቃና እንስሳት የመኖ አገልግሎት እንዲሁም ሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች አሻራው በጉልህ መታየቱን ገልጸው ልማቱን አጠናክረን እንቀጥላልን ሲሉ አረጋግጠዋል።   በምዕራብ ወለጋ ዞን ግብርና ጽህፈት ቤት የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ቡድን መሪ አቶ ፍቅሩ ብርሃኑ፤ የአረንጓዴ አሻራ ልማቱ ጥቅም በተግባር እየታየና ተጠቃሚዎችም ምስክርነታቸውን እየሰጡ መሆኑን አንስተዋል። በለውጡ ዓመታት በብዙ መልኩ ጥቅም የሚሰጡ ችግኞች ተተክለው ለውጤትም መብቃታቸውን ገልጸው በዞኑ ዘንድሮ ከ6 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ችግኞች መሸፈኑን አረጋግጠዋል።   የልማት ስራው በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥል መሆኑን ጠቁመው ችግኞችን በመንከባከብ ለፍሬ ማብቃት ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል።
በአየር ንብረት ጉባኤው አፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ በግንባር ቀደምነት እየሰራች መሆኗን ለዓለም ታሳያለች
Aug 6, 2025 96
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2017(ኢዜአ)፦ ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ አፍሪካውያን ድምጻቸውን በጋራ ከማሰማት ባለፈ ለአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ በግንባር ቀደምነት እየሰሩ መሆኑን ለዓለም የሚያሳዩበት መሆኑን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ገለጸ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር ሁለተኛውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባዔ እንደምታስተናግድ መግለጻቸው ይታወሳል። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መኮንን ዝግጅቱን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ፥ ጉባኤው ከጳጉሜን 3 እስከ 5/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን ቅድመ ጉባኤው ደግሞ ከነሐሴ 30 ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 2 ይከናወናል ብለዋል። "ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት መፍትሔዎችን ማፋጠን የአፍሪካን የማይበገር እና አረንጓዴ ልማት በፋይናንስ መደገፍ" በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄደው ጉባኤው አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የመሪነት ሚናዋን እንድትወጣ የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል። አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ተጎጅነቷን ከሚያንጸባርቅ ትርክት በመሻገር የመፍትሄ አካል ሆና በግንባር ቀደምነት እየሰራች እንደምትገኝ የምታሳይበት ነው ብለዋል። አፍሪካውያን የጋራ አቋማቸውን የሚያንጸባርቁበት ጉባኤ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፥ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጡ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉበት አመላክተዋል። ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት እያከናወነቻቸው የሚገኙ መሪ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎችን በጉባኤው በተሞክሮነት እንደምታቀርብም አንስተዋል። በጉባኤው የበርካታ ሀገራት መሪዎችን ጨምሮ ከ20 ሺህ እስከ 25 ሺህ ሰዎች እንደሚሳተፉ ገልጸው፥ ለዚህም ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የአፍሪካ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እየወሰዱት ያለውን እርምጃ የሚያሳዩ ፓቪሊዮኖች መዘጋጀታቸውን ጠቅሰው፥ በርካታ የጎንዮሽ ውይይቶች እንደሚኖሩም ጠቁመዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ የአንድ ሀገር የመልማት እና የማደግ ፍላጎት ሊገደብ አይገባም - አንቶኒዮ ጉቴሬዝ
Aug 5, 2025 102
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 28/2017(ኢዜአ)፦መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ የአንድን ሀገር የመልማት እና የማደግ መብት በፍጹም መወሰን የለበትም ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ። ሶስተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የባህር በር የሌላቸው በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት ኮንፍረንስ ዛሬ በተርኪሚኒስታን መካሄድ ጀምሯል።   በኮንፍረንሱ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ፣እስያ፣አውሮፓ እና ደቡብ አሜሪካ የሚገኙ 32 ሀገራት ተሳታፊ ሆነዋል። ከተሳታፊዎቹ ሀገራት መካከል 16 ከአፍሪካ ናቸው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በኮንፍረንሱ ላይ ባደረጉት ንግግር የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ያሉባቸውን የልማት፣የኢኮኖሚ እና የእድገት ፈተናዎችን አንስተዋል። በማደግ ላይ የሚገኙ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የመልማት አቅማቸው ባሉበት መልክዐ ምድራዊ ስፍራ ምክንያት ሊገደብ እንደማይገባ አመልክተዋል። ዋና ፀሐፊው የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የዓለምን ሰባት በመቶ ህዝብ የያዙ ቢሆንም በዓለም ኢኮኖሚና ንግድ ውስጥ ያላቸው ድርሻ ከአንድ ፐርሰንት ጥቂት ሻገር ያለ መሆኑን ገልጸው ይህ ትልቅ ኢ-ፍትሃዊነት ነው ሲሉ ተናግረዋል። በተጨማሪም ሀገራቱ ለአየር ንብረት ለውጥ ያላቸው ድርሻ ዝቅተኛ ቢሆንም የጉዳቱ ዋንኛ ሰለባ መሆናቸውን አንስተዋል። የዓለም ማህበረሰብ ሀገራቱ በዓለም ኢኮኖሚ እና የንግድ ስርዓት ውስጥ ያላቸው ድርሻ እንዲያድግ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።   የባህር በር የሌላቸው ሀገራት በዓለም የንግድ እሴት ሰንሰለት ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ እንዲጨምር የሚያስችል መዋቅራዊ ለውጥ ያሻል ያሉት ዋና ፀሐፊው፥ ይህም ሀገራት ጥሬ ምርቶችን ከመላክ ከፍተኛ እሴት ያለው ምርት ወደ ማምረት እንዲሸጋገሩ ያደርጋል ነው ያሉት። የባለብዙ ወገን የልማት ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት አነስተኛ ወለድ ያለው የፋይናንስ አቅርቦት ለሀገራት ተደራሽ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ከትስስር ጋር በተያያዘ የሚገጥማቸውን የመሰረተ ልማት እና መዋቅራዊ ችግሮች መፍታት እንደሚገባ አመልክተዋል። ለዚህም ድንበር ተሻጋሪ አሰራሮችን ማቅለል፣የተለያዩ የመመዘኛ ደረጃዎችን ማጣጣም እንዲሁም የተሳለጠ ንግድና ትራንዚት እንዲኖር የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎችን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ነው ያነሱት። ጉቴሬዝ በመሰረተ ልማት መጠነ ሰፊ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ይገባል ያሉ ሲሆን የባህር በር የሌላቸው በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት የማይበገር የትራንስፖርት መተላለፊያ መስመር፣ ድንበር ተሻጋሪ የእርስ በእርስ የኢነርጂ ትስስር፣ ሰፊ የአየር ትስስር እና በቴክኖሎጂ የታገዙ የሎጅስቲክስ አውታሮች እንደሚያስፈልጋቸው አስገንዝበዋል። ሀገራቱ ያለባቸውን የመልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ እክሎች ምላሽ ለመስጠት ፍትሃዊ የዲጂታል አገልግሎት ተደራሽነትን ማስፈን እንዳለባቸው አሳስበዋል።   ኮንፈረንሱ ላይ ኢትዮጵያ እና የባህር በር የሌላቸው ሌሎች ሀገራት በዓለም የንግድ ስርዓት ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ በትስስር፣ በፍትሃዊ የዲጂታል አገልግሎት ተደራሽነት እና ዓለም አቀፍ ትብብር እንዲያድግ ግፊት እንደሚያደርጉ ተመላክቷል። ሶስተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የባህር በር የሌላቸው በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት ኮንፍረንስ እስከ ነሐሴ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል።
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኤርትራ በአፋር ህዝብ ላይ እየፈጸመች ያለውን ግፍ የተሞላበት የዘር ማጥፋት ዘመቻ ሊያስቆም ይገባል -  የአፋር ቀይ ባህር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት 
Jul 22, 2025 457
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 15/ 2017 (ኢዜአ)፦ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኤርትራ በአፋር ህዝብ ላይ እየፈጸመች ያለውን ግፍ የተሞላበት የዘር ማጥፋት ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲያስቆም የአፋር ቀይ ባህር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ጥሪ አቀረበ። በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራው በዳንካሊያ ክልል የሚገኙ የአፋር ህዝቦች የተቀናጀ የዘር ሽብር ዘመቻ መክፈቱን አመልክቷል። ድርጅቱ ኤርትራ በአፋር ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለው ያልተቋረጠ የጭካኔ ተግባር የዓለምን አስቸኳይ ትኩረት ይሻል በሚል መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫው የኤርትራ መንግስት መጠነ ሰፊ ግድያዎች፣ በግዳጅ ለውትድርና መመልመል፣ አስገድዶ መሰወር፣ ማሰቃየት እና ሆን ብሎ የአፋር ማህበረሰቦችን ማፈናቀል ጨምሮ የተለያዩ ግፎችን እየፈጸመ መሆኑን አመልክቷል። ድርጅቱ ኤርትራ የምትፈጽማቸው ድርጊቶች በመንግስት ደረጃ የተቀነባበረ የባህል እና የዘር ማጥፋት ዘመቻ አካል ነው ሲል ገልጿል።   እየፈጸሙ ያሉ በደሎች የአንድ ጊዜ ብቻ ክስተቶች አይደለም ይልቁንም በተጠና ፖሊሲ አፋርን ከኤርትራ ለማጥፋት በመንግስት እየተፈጸመ ያለ ተግባር ነው ብሏል። ድርጅቱ ጉዳዩን አስመልክቶ በግንቦት ወር 2017 ዓ.ም ለአፍሪካ የሰብዓዊና የህዝብ መብቶች ኮሚሽን በይፋ አቤቱታ ማቅረቡን ገልጾ በአፍሪካ ቻርተር የተቀመጡ 25 የመብት ጥሰቶችን መፈጸማቸውን አመልክቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) እና ለዔሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት በኤርትራ መንግስት ባለስልጣናት እና ተቋማት ማዕቀብ እንዲጥሉ ጥሪ አቅርቧል። ተቋማቱ ዓለም አቀፍ የሕግ እርምጃ እንዲወስዱ እና የአፋር ህዝብ የፍትህ፣ የመጠበቅ እና በራሱ የመወሰን መብት እውቅና እንዲሰጡ ጠይቋል። ኤርትራ በአፋር ህዝብ ላይ እየፈጸመች ያለው ግፍ እና በደል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለልተኛ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች እና በሰብዓዊ መብት ተቋማት በሰፊው በማስረጃ ተሰንዶ ያለ ጉዳይ መሆኑን አመልክቷል። በኤርትራ መንግስት ላይ እርምጃ ካልተወሰደ የዜጎች ህይወት መቀጠፉን እንደሚቀጥል እና ሊቀለበስ የማይችል የባህል ውድመት እንደሚፈጥር ድርጅቱ አስጠንቅቋል።
በህንድ የአውሮፕላን አደጋ የ204 ዜጎች ህይወት አልፏል- የሕንድ ፖሊስ
Jun 12, 2025 1525
አዲስ አበባ፤ሰኔ 5/2017 (ኢዜአ)፦በህንድ የአውሮፕላን አደጋ የ204 ዜጎች ህይወት ማለፉን የሀገሪቷ ፖሊስ አስታወቀ። በሕንድ 242 መንገደኞችን ይዞ በህንድ ሰሜን ምዕራባዊ ክፍል አህመዳባድ ከተማ ከሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ለንደን ጋትዊክ ለማምራት በተነሳበት ቅፅበት በአካባቢው በሚገኝ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ማረፊያ ላይ ተከስክሷል። በቦይንግ 787-8 ድሪምላይነር አውሮፕላን ውስጥ 169 ህንዳውያን፣ 53 የብሪታኒያ ዜጎች፣ 7 ፖርቹጋላዊ እና አንድ ካናዳዊ ነበሩ።   በአደጋው የተረፈ ሰው ለማግኘት የሚቻልበት እድል እጅጉን የጠበበ ነው ሲል የአህመዳባድ ፖሊስ ኃላፊ ለአሶሲዬትድ ፕሬስ ገልጾ ነበር። ይሁንና ማምሻውን በወጣ መረጃ የ40 ዓመት የህንድ እና ብሪታኒያዊ ጥምር ዜግነት ያለው ቪሽዋሽ ኩማር ራሜሽ ከአደጋው መትረፉ ተጠቁሟል። እስከ አሁን የ204 ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል። የአውሮፕላኑ አካል የህክምና ባለሙያዎች ማረፊያ ላይ ወድቆ ቢያንስ አምስት የህክምና ተማሪዎች መሞታቸውን እና 50 ገደማ የሚሆኑት መጎዳታቸው ተገልጿል። የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት የሀዘን መግለጫ መልዕክት አደጋው ቃል ከሚገልጸው በላይ ልብ የሚሰብር ነው ሲሉ ገልጸዋል። በአደጋው ለተጎዱ በሙሉ ልባዊ ሀዘናቸውን በመግለጽ መጽናናትን ተመኝተዋል።
ሐተታዎች
የኢትዮጵያ አረንጓዴ ማዕበል
Aug 1, 2025 173
ኢትዮጵያ የአሸናፊዎች ሀገር ናት። ትጋት፣ አይበገሬነት እና ጽናትን የማንነት ካባቸው አድርገው የለበሱ ዜጎቿ ፊታቸው ካለው ችግር ይልቅ የነገን መጻኢ ብሩህ ተስፋ እያዩ በአንድነት በመጓዝ በስኬት ላይ ስኬት በድል ላይ ሌላ ድል በገድል ላይ አዲስ ገድል እያስመዘገቡ ኖረዋል። አሁንም በዚህ ብርቱ የድል አድራጊነት መንፈስ ቀጥለዋል። ለማሳያነት አትሌቲክስን እንመልከት። ከኢትዮጵያ የተለያዩ መልክዐ ምድሮች የፈለቁ አትሌቶች ድል ከማስመዝገብ ባለፈ መልካም ገጽታዋን ገንብተዋል። ባንዲራዋ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ አድርገዋል። ስሟን አስጠርተዋል። ኢትዮጵያ የጀግኖች ሀገር ናት የሚለውን እሳቤ ከንግግር ባለፈ በተግባር አሳይተዋል። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከድላቸው ጀርባ አንድ ትልቅ ኃይል አለ የቡድን ስራ ይባላል። አትሌቶች ከግል ክብራቸው ይልቅ ሀገርን በማስቀደም በቡድን ስራ የሚያስመዘግቡት ድል “አረንጓዴው ጎርፍ” (Green Wave) የሚል ታዋቂ ስያሜ አሰጥቷቸዋል። አረንጓዴው ጎርፍ ኢትዮጵያውያንን በደስታ ጮቤ አስረግጧል ሀሴት እንዲሰማቸው አድርጓል። ይህ የአረንጓዴ ማዕበል መንፈስ ከአትሌቲክስ መሮጫ መም እና ሜዳ ወደ ደኖች፣ ኮረብታዎች እና እርሻ ስፍራዎች ሰተት ብሎ ገብቷል። በአረንጓዴ አሻራ አማካኝነት። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው አረንጓዴ አሻራ ሰባተኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል። ትናንት በአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ 700 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ 714 ነጥብ 7 ሚሊዮን ችግኝ በመትከል አዲስ ታሪክ ተሰርቷል። በዚህ አኩሪ ስራ ላይ 29 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዜጎች መሳተፋቸውን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። አትሌቶች በመሮጫ ስፍራው የብሄራዊ አይበገሬነት እና ክብር ምልክት ሲሆኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በነቂስ ወጥቶ ችግኝ በመትከል የደን መልሶ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራ አሸናፊ ሆነዋል። ሚሊዮኖች ችግኝ ሲተክሉ ልክ እንደ አትሌቶቹ አንድነት፣ ጽናት እና አላማን በቁርጠኝነት ማሳካትን አሳይተዋል። አፍሪካን ኒውስ የትናንቱን የአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ አስመልክቶ በሰራው ዘገባ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት እና ደንን ለመጠበቅ አረንጓዴ ማዕበል ሆነው ችግኝ ተክለዋል ሲል አድናቆቱን አስፍሯል። ዘገባው ኢትዮጵያውያን ያሳዩትን አንድነት እና ህብረት አሞካሽቷል። ለመሆኑ ኢትዮጵያውያን ለምን በነቂስ ወጥተው ችግኝ ይተክላሉ? ለሚለው ጥያቄ ከፊት ለፊት የሚመጣው ምላሽ ችግኝ መትከል ለከባቢ አየር ጥብቃ አንገብጋቢ አጀንዳ ከዛ ሲያልፍም ማህበራዊ እና የኢኮኖሚ ፈተናዎችን ለመፍታት ቁልፍ ነው ብለው በጽኑ ስለሚያምኑ ነው። ማህበረሰባዊ መሰረት በያዘው አረንጓዴ አሻራ ዜጎች በመትመም ለችግኝ ተከላ የሚወጡት በጉዳዩ ላይ የባለቤትነትና የኃላፊነት ስሜት ስለሚሰማቸው ነው። አረንጓዴ አሻራ በርካታ ትሩፋቶችና በረከቶች ያሉት ነው። የኦክስጅን አቅርቦት ጨምሯል፣ የአየር ንብረት ሚዛንን ጠብቋል አልፎም የተራቆተ መሬት መልሶ ወደ ነበረበት እንዲመለስ እያደረገ ይገኛል። ደኖች የአፈር ለምነትን በማሻሻልና ውሃን አቅቦ በመያዝ የምግብ ምርታማነት እንዲያድግ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ። ከዚህ አንጻር አረንጓዴ አሻራ ያለው ሚና ግዙፍ ነው። ምርታማ የሆነ መሬት ሲሰፋ እና ስነምህዳሮች ከጉዳታቸው ታክመው ነባር ይዞታቸውን ሲይዙ ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነቷን የማረጋገጥ፣ አይበገሬ አረንጓዴ ኢኮኖሚ የመገንባትና አካባቢን የመጠበቅ ህልሟን ያሳካል። አረንጓዴ አሻራ ከአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም የተሻገረ ትርጉም ያለው ነው የአንድነት እና የብሄራዊ ክብር መገለጫም ሆኗል። ኢትዮጵያውያን ለአንድ አላማ ከቆሙና ከተባበሩ ከስኬት ማማ ለመድረስ የሚያግዳቸው ነገር እንደሌለ በግልጽ አሳይቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ትናንት በአንድ ጀንበር የ700 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ በሰጡት አስተያየት አረንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያ ትላልቅ ዕቅዶችን አቅዳ ህዝቧን አስተባብራ ማሳካት እንደምትችል ለዓለም ያሳየችበት ትልቅ ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል። በተለይም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በነቂስ ወጥተው መሳተፋቸው የሀገርን የጋራ ራዕይ ለማሳካት ያላቸውን ፍላጎትና ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንደሆነም ተናግረዋል። ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ከሀገር ያለፈ ቀጣናዊ አንድምታ አለው። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን ለጎረቤት ሀገራት በስጦታ በማበርከት ለቀጣናዊ ትስስርና ትብብር ያላትን ቁርጠኝነት ከፖሊሲ ትኩረት ባለፈ በተግባር አሳይታበታለች። ኢትዮጵያ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን መትከሏ የቀጣናው ፈተና የሆነውን ድርቅን በመከላከል፣ ጎርፍን በመቀነስ እና ስነ ምህዳር እንዲያገግም በማድረግ ትልቅ ሚና ይጫወታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ማስጀመሪያ ላይ ለተገኙት የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ካሺም ሼቲማ የአራት ሺህ ችግኞች ስጦታ ማበርከታቸው የሚታወስ ሲሆን በምላሹም ናይጄሪያ ለኢትዮጵያ 2 ሺህ የካሽው ችግኝ እና 100 ሺህ ዘር በሥጦታ አበርክታለች። ይህ አረንጓዴ አሻራ የፓን አፍሪካን የአጋርነት መንፈስ አዲስ መገለጫ እና ጉዳዩ የአፍሪካ አጀንዳ እየሆነ መምጣቱን አመላካች ሲሆን አፍሪካውያን በአካባቢ ጥበቃ ዘላቂ ትብብር መፍጠር እንዳለባቸውም የሚያስገነዝብ ነው። እዛው አፍሪካ ላይ ስንቆይ አረንጓዴ አሻራ ከአፍሪካ ህብረት ትልቁ ማዕቀፍ አጀንዳ 2063 ጋር የሚጎዳኙ ጉዳዮች አሉት። አጀንዳ 2063 የበለጸገች እና አረንጓዴ አፍሪካን እውን ሆኖ የማየት ህልምን ያነገበ ነው። በደን መልሶ ልማት እና ዘላቂ ግብርና ስራ የመሪነት ሚና እየተወጣች የምትገኛው ኢትዮጵያ ከአጀንዳ 2063 ቁልፍ ግቦች መካከል ለስነ ምህዳር መልሶ ማገገም፣ ሁሉን አቀፍ ልማት እና ቀጣናዊ ትብብር ቀጥተኛ አስተዋጽኦ እያደረገች ትገኛለች። የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ አጀንዳ 2063 በእሳቤ ደረጃ ሊያሳካቸው ያሰባቸውን ጉዳዮች በተግባር የገለጠ ተምሳሌት ነው ማለት ይቻላል። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ስኬት የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ከፍታ ጨምሯል። በቅርቡ በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ በአዲስ አበባ በተካሄደው ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ ስርዓት ጉባኤ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ያከናወነቻቸውን ስራዎች ለዓለም በስፋት አስተዋውቃለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ40 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃንና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ገንቢ ሚና እየተወጣች እንደምትገኝ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በዚህ ግዙፍ ዓለም አቀፍ ሁነት የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ አጀንዳዎች ያጎላች ሲሆን በአረንጓዴ አሻራ ሀገር በቀል ኢኒሼቲቭ በትብብር እና ፈጠራ በታከለባቸው የመፍትሄ አማራጮች ዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ግቦች ማሳካት እንደሚቻልም አሳይታለች። የጉባኤው ተሳታፊዎችም በአረንጓዴ አሻራ ላይ መርሃ ግብሮች ላይ በመሳተፍ ችግኝ ተክለዋል። ይህ አረንጓዴ ዲፕሎማሲ በተግባር ፍንትው ብሎ የታየበት ነው። አረንጓዴ አሻራ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የከባቢ አየር መራቆትን ለማስቀረት ስራዎች ዓለም አቀፍ ተምሳሌት የሚሆን ነው። ኢኒሼቲቩ እንደ ኢትዮጵያ ያለች በማደግ ላይ የምትገኝ ሀገር በራዕይ እና በተግባር በመምራት ሌሎች ሀገራት የህዝብ ኃይልን ተጠቅመው አካባቢያቸውን እንዲጠብቁ ያነሳሳል። አረንጓዴ አሻራ መንግስት እና ህዝብ እጅና ጓንት ሆነው መጻኢው ጊዜ ብሩህ የሆነና አረንጓዴ የለበሰች ሀገር ለመፍጠር ቆርጠው ከተነሱ የማይሳካ ነገር እንደሌለም አመላካች ነው። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ የእስከ አሁን ቆይታ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን ተክላለች። አረንጓዴ አሻራ ቀጣይነት ያለው እና የረጅም ጊዜ ብሄራዊ ተልዕኮ እና ግብ ነው። አሳይቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አረንጓዴ አሻራ የኢትዮጵያ የታሪክ አሻራ አካል ይሆናል ያሉት ሀሳብም የፕሮጀክቱን ዘላቂነት እና ቆይታ በግልጽ የሚያመላክት ነው። ኢትዮጵያ ትናንት በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን ችግኝ ለምትካል አቅዳ 714 ነጥብ 7 ሚሊዮን ችግኞች በመትከል ከእቅድ በላይ አሳክታለች። በ2018 ዓ.ም በአረንጓዴ አሻራ የተተከሉ ችግኞችን ብዛት 50 ቢሊዮን የማድረስ እቅድ ከእቅድ በላይ በላቀ ሁኔታ እንደሚሳካ ሳይታለም የተፈታ እውነት ነው። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ አማካኝነት ትላልቅ ህልሞቿን፣ እቅዶቿ እና ራዕዮቿን ማሳካት እንደምትችል በግልጽ አሳይታለች። በአየር ንብረት ለውጥ የተግባር ምላሽ በመስጠት፣ የተፈጥሮ ጠበቃ በመሆን እና ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ ጉዞ ዘላቂ መሪነቷን እያሳየች ትገኛለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በተቀረው ዓለም የአረንጓዴ ትራንስፎርሜሽን አሸናፊ እና ቁንጮ ሆና መቀጠሏ አይቀሬ ነው። ለግዙፍ ሀገራዊ አላማ በሚሊዮኖች ደረጃ የሚተመው አረንጓዴ ማዕበልም ይህን ግብ የሚያሳካ ትልቅ ሀብት እና አቅም ሆኖ ይቀጥላል።
የህንድ የፈጠራ ማዕከል - ባንጋሎሩ
Jul 2, 2025 1112
ቤተልሄም ባህሩ(ኢዜአ) የዴልሂና አግራ ቆይታችንን ጨርሰን ወደ ቀጣይ መዳረሻችን ባንጋሎሩ ከተማ ልንጓዝ ስንሰናዳ አብዛኛው የጋዜጠኛ ልዑክ ያሳሰበው እንደሰም የምታቀልጠውን የአግራ ፀሀይና ሙቀት በባንጋሎሩም ታገኘን ይሆን? የሚለው ነበር። ሆኖም ከዴልሂ ኢንድራ ጋንዲ አየር ማረፊያ ተነስተን ለሶስት ሰዓት ከተቃረበ በረራ በኋላ ያገኘናት ባንጋሎሩ የተለየች ሆነን አገኘናት። ባንጋሎሩ ቀዝቀዝ ባለ አየር ነበር እንግዶቿን የተቀበለችን። በዕለቱ ከክፍሎቻችን ወጥተን በጋራ ወደአየር ማረፊያ የሚወስደንን ትራንስፖርት ስንጠባበቅ ከጋዜጠኛ ቡድኑ ስድስት አባላት ከአጠገባችን እንዳልነበሩ አስተዋልን። የት ጋር እንደተነጣጠልን አላስታውስም። በዚህ ምክንያት ግን የእለቱ ጉዟችን ተሰርዞ ከተማዋን ለማየት ስንዘዋወር የማውቀው ዓይነት እንጂ የተለየ ሙቀት አላስተናገድኩም። የ13 ወር ፀጋ በመባል የምትታወቀው አገሬ ኢትዮጵያ ከዳሎል እስከ ራስ ዳሽን ባላት የመልከዓ ምድር አቀማመጥና ልዩ ልዩ የአየር ጠባይ ሙቀቱንም፣ ቅዝቃዜውንም ማወቃችን እንደዚህ ለአለ አጋጣሚ መልካም ስሜት ይፈጥራል። በተወሰነ ደረጃ በህንድ ያጋጠመኝ የአየር ባህሪ ከአገሬ ጋር ቢመሳሰልብኝ የፈጣሪንና የተፈጥሮን ስራ አጃኢብ ብዬ እንዳልፍ አድርጎኛል። ባንጋሎሩ ከተማ የቴክኖሎጂና ፈጠራ ማዕከል በመሆኗ የህንድ ሲልከን ቫሊ በመባል ትታወቃለች። ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ስፍራዎችም ከመገለጫዎቿ መካከል ናቸው። የጠፈር ጠበብቶቹ - ባንጋሎሩ ደርሰን በመጀመሪያ ያየነው ዓለም በስፔስ ሳይንስ እየሰራች ያለችውና እያስመዘገበችው የምትገኘው ውጤት ማሳያ የሆነውን የህንድ ስፔስ ምርምር ድርጅትን ነው። ተቋሙ የህንድ መንግስት የስፔስ ዲፓርትመንት አካል ሲሆን፤ ዶክተር ቪክራም ሳራብሃይ በተሰኙ ባለራዕይ በ1962 የተወጠነና አሁን ላይ በዘርፉ ተገዳዳሪ መሆን የቻለ ነው። የተቋሙ ዓላማ የስፔስ ቴክኖሎጂዎችን በማልማትና በመተግበር ለተለያዩ አገራዊ ጥቅሞች ማዋል መሆኑን ተከትሎ የሳተላይት ማምጠቂያ መሳሪያዎችን የማምረት ስራን ጨምሮ ከአገሩ አልፎ ለሌሎች አገራትም በዘርፉ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። የተደረገልን ገለፃ አብዛኛውን ጋዜጠኛ ያስደመመ ነበር ከገለፃ በኋላ በጋዜጠኞች የተነሳው ሃሳብም ህንድ በስፔስ ዘርፍ ያላት ልምድና ያከናወነችው ተግባር በቀጣይም ልትሰራ የወጠነቻቸው ሃሳቦች የአገሪቱን መዳረሻ የተለሙ በአገራቸው እንዲተገበር የሚናፍቁት መሆኑን ነው። ተቋሙ በዘርፉ ለተሰማሩ ኢትዮጵያዊያን የአቅም ግንባታ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንና በቀጣይም ትብብሩን የሚያጠናክር መሆኑን ከተደረገልን ገለፃ ተገንዝበናል።   በሳይንስ፣ ኢንጂነሪንግና አስተዳደር ምሁራንን በማስተማር እያበረከተ ያለው የህንድ የሳይንስ ኢንስቲትዩት በባንጋሎሩ ከጎበኘናቸው መካከል የሚጠቀስ ነው። ኢንስቲትዩቱ ከአፍሪካ የተውጣጡ ተማሪዎችን የሚያስተምርና ከተቋማት ጋርም በዘርፉ የሚሰራ ሲሆን፤ በኢትዮጵያም ከጅማ፣ በተግባር ለመቀየር ሲታትሩ የስታርት አፖችን የምርት ውጤቶቻቸውን ሲፈትሹና ሲሞክሩ ተመልክቻለሁ። በኢትዮጵያም አሁን ላይ ለስታርት አፖች በተሰጠው ትኩረትና በተፈጠረው ምቹ ስነ ምህዳር የፈጠራ ውጤቶች እያደጉና እየተበራከቱ መሆናቸው የሚታወቅ ነው። እንደ አዳማና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ተቋማት የተማሪዎችን ፈጠራ ወደ ውጤት ለመቀየር እየተጉ መሆኑና የስታርት አፕ ኤግዚቢሽንና የሰመር ቡት ካምፖች ፈጠራን ምን ያህል እያበራከቱ መሆናቸው በጉብኝቱ ወቅት ወደ አዕምሮዬ የመጣ የአገሬው ህዝብ በውጤት የታጀበ ጥረት ነው።   ከአራት አስርት ዓመታት በላይ በባዩቴክኖሎጂ ዘርፍ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ የሚገኘው ባዮኮንም ከባላንጎሩ የጉብኝት መዳረሻችን መካከል የሆነና አስፈላጊ መድሀኒቶችን የሚያመርትና በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች አቅም ግንባታ ላይም እየሰራ ያለ ነው። ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ አገራት የአቅም ግንባታ ስልጠናው ተጠቃሚ ናቸው። ከ120 በላይ በሆኑ አገራት ለስኳርና ካንሰር ህመም የሚያገለገሉ መድሀኒቶችን በማምረትና በማሰራጨት ለህሙማን ፈውስና ለጤናው ዘርፍ ስርዓት አስተዋፅኦ እያበረከተም ይገኛል። የተቋሙ ላቦራቶሪና ዘመኑን የዋጀና ደረጃውን የጠበቀ ማምረቻ ፋብሪካን መጎብኘቴ አለም በፋርማሲዩቲካልስ ዘርፍ ያለችበትን ሁኔታ የሚያሳይ ነው። የባንጋሎሩ ቤተመንግስት - ይህን ቤተ መንግስት ማስቃኘቴን ከመጀመሬ በፊት በስፍራው ካስገረመኝ ነገር ላወጋችሁ ወደድኩ። ቤተ መንግስቱን ለመጎብኘት ያቀናነው በእለተ ሰኞ ነበር። ሆኖም ምድረ ግቢውን ቃኝተን ስለህንፃው ሰምተን ከመመለስ ውጪ ወደ ውስጥ አልዘለቅንም። ለምን? ለሚለው ምላሹ በዚህ ስፍራ "ሰኞ የእረፍት ቀን ናት" ነው። እንዴት ካላችሁ ቤተ መንግስቱ ቅዳሜና እሁድ በበርካታ ሰዎች የሚጎበኝ መሆኑን ተከትሎ በስፍራው ለሚሰሩ ሰራተኞች የእረፍት ቀናቸው ሰኞ በመሆኑ ነው። የቤተ መንግስቱ ምድረ ግቢ ሰፊና ልምላሜ የተላበሰ ሲሆን፤ የሚያምርና ለዓይን የሚስብ ኪነ ህንፃ ያለው ነው። አሰራሩና ውጥኑም እንደሚከተለው ነው። በዎዲየር ስርወ መንግስት ንጉስ ቻማራጃ ዋዲያር ወደ እንግሊዝ ባደረጉት ጉዞ በለንደን ዊንሶር ግንብ ይደነቃል። ተደንቆም አልቀረ የባንጋሎሩ ቤተ መንግስትን በተመሳሳይ ሁኔታ ይገነባል። ይህ ቤተ መንግስት በተወሰነ መልኩ የመካከለኛው ዘመን የኖርማንሲና የእንግሊዝ ግንቦችን ይመስላል።   ቪድሃና ሶውዳ የካራንታካ ህግ አውጪ አካል መናገሻ በጉብኝታችን ያየነው ሌላው መዳረሻ ስፍራችን ነው። የህግ አውጪና የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የያዘው ይህ ህንፃ ህንድ ነፃነቷን ካገኘች በኋላ በራሷ መሀንዲስ የሰራችው የመጀመሪያው ህንፃ መሆኑ ተገልፆልናል። የህንፃ ግንባታ ጥበብ ማሳያ፣ የፖለቲካ መናገሻ እንዲሁም የባህል ማሳያ ተደርጎም ይወሰዳል።   እንደአጠቃላይ በቆይታዬ የተመለከትኩት የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ማበረታቻ እንዲሁም የአረንጓዴ ልማት ስራ ኢትዮጵያ እያከናወነች ካለው የኮሪደር ልማትና ስታርት አፕን የማበረታታት ብሎም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስነ ምህዳር ምቹነት ስራዎች ጋር ተመሳሳይነት ያለው መሆኑን ነው። በህንድና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት ዘመናትን የተሻገረ፤ ለሁለት ሺህ ዓመታት የዘለቀ መሆኑን የታሪክ መዛግብት ያሳያል። የህንድና ኢትዮጵያ ግንኙነት በአክሱም ስርወ መንግስት ኢትዮጵያና ህንድ በአዱሊስ ወደብ በኩል የንግድ ልውውጥ ሲያደርጉ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። በወቅቱ ኢትዮጵያ ቅመማ ቅመምና ሐርን ከህንድ ትገበይ ነበር። ህንድ ደግሞ ወርቅና የዝሆን ጥርስን ከኢትዮጵያ ትሸምት ነበር። ህንድ ከንግድ ልውውጥ ባሻገር በኢትዮጵያ ኪነ ህንፃ ግንባታ ላይ አሻራዋን አኑራለች። በኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፍም ትልቅ አበርክቶ ያላት አገር ናት። ህንድ ነፃነቷን ካገኘችበት እኤአ 1948 አንስቶ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት ኢትዮጵያና ህንድ ሌላው የሚያመሳስላቸው ነገር ሆኖ ያገኘሁት የአምራች ዘርፉን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እያከናወኑ ያሉት ንቅናቄ ነው። ህንድ እ.አ.አ ከ2014 ጀምሮ የአምራች ዘርፉን ለማበረታታት "ሜድ ኢን ኢንዲያ" በሚል ለአስር ዓመት የተገበረችውና በርካታ ለውጥ የተመዘገበበት ንቅናቄ በኢትዮጵያ ከ2014ዓ.ም ጀምሮ እየተተገበረ ካለውና የሃገር በቀል ምርቶች እና አምራቾችን ማጠናከር፣ የኢንዱስትሪያል ማህበረሰብ ግንባታን ማሳደግ ፣ ምቹ የቢዝነስ ከባቢ መፍጠር እና የጥናት እና ምርምር ችግር ፈቺነትን ማሳደግን ዓላማ ካደረገው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ጋር የተመሳሰለ ነው። ንቅናቄ በኢትዮጵያ መተግበሩ ዓመታዊ የዘርፍ ዕድገት፣ የማምረት አቅም አጠቃቀምና ገቢ ምርት በመተካት በኩል ጉልህ ሚና እየተወጣ መሆኑም ይታወቃል። በህንድ ተዘዋውሬ በተመለከትካቸው ከተማዎች ባሉ ጎዳናዎች ከታዘብኩት ነገር ሰዎች ከሱቅ ለሚገበያዩት ነገር ሳይቀር በዲጂታል መንገድ ክፍያ መፈፀማቸውን ነው። በባጃጅና በሞተር የትራንስፖርት አገልግሎት ለማግኘትም ጭምር ሞባይሉን በመጠቀም “ይህ ቦታ የት ነው?” ሳይል ያሻዎት ስፍራ መድረስም ሌላው ትዝብቴ ነው። ይህ ነገር በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ትኩረት አግኝተው እየተሰራባቸው ካሉት የዲጂታል ክፍያና ዲጂታል ክህሎት ማሳደጊያ መርሃ ግብር ጋር የሚመሳሰል ሆኖ አግኝቼዋለሁ። በቆይታችን ልክ እንደአትሌቶቻችን ሁሉ በዓለም አደባባይ የኢትዮጵያን ስም ከፍ አድርጎ የሚያስነሳውን ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዝናና ክብር ለማስተዋል ችያለሁ። ፀጉረ ልውጥ መሆናችንን የተገነዘቡ በገበያ ማዕከላት የሚያገኙን እንዲሁም በምንጎበኛቸው ተቋማት የምንተዋወቃቸው ህንዳውያን "ከየት ናችሁ?" ብለው ሲጠይቁ፤ ለእኔና አንድ ከሌላ መገናኛ ብዙሃን የሄድን "ከኢትዮጵያዊ" ስንል የሚከተልልን ምላሽ "አሃ የኢትዮጵያ አየር መንገድ" የሚል ነው። ይህም አየር መንገዱ ስሙ ከኢትዮጵያ ተሰናስሎ የሚጠራ የአገሪቷ መታወቂያ ተቋም መሆኑን ያስገነዘበኝ ነው። ከህንዳውያን ጋር ብቻ ሳይሆን አብረን ከተጓዝን ጋዜጠኞች አንዱ "የኢትዮጵያ አየር መንገድ የእናንተ የብቻ ሳይሆን እኛንም እንደራሳችን ሆኖ እያገለገለን ያለ የጋራ አየር መንገዳችን ነው" ሲል ነው የገለፀው። ይሄ ለእኔ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገር ኩራት ብቻ ሳይሆን መለያ ምልክትም ጭምር መሆኑን የተረዳሁበት አጋጣሚ ነው። በቀናት ቆይታዬ በእንግዳ አክባሪነታቸውና በለገሱን ፍቅርና እንክብካቤ ከአገሬ የራቅኩ ያህል ሳይሰማኝ ብቸኝነትን ሳላስተናግድ እንደውም እየናፈኳቸው እንድመለስ ላደረጉኝ ህንዳውያን በከበረ ሰላምታ ላመሰግን እወዳለሁ።
ውበትና ትጋት በህንድ
Jun 27, 2025 854
በቤተልሄም ባህሩ (ኢዜአ) በልጅነቴ እያየሁ ያደግኳቸው አብዛኛዎቹ ፊልሞች የህንድ ናቸው። ይህ ደግሞ ከአገራችን አርቲስቶች በላይ የህንድ የፊልም ተዋንያኑን ስም ለመለየት አስችሎኛል። የህፃንነት ዘመኔን የሚያስታውሱኝን ፊልሞች ከትዝታ ማህደሬ እያወጣሁ ከመተረክ በስተቀር ህንድን የማይበት አጋጣሚ ይኖራል ብዬ አስቤ አላውቅም። እነዚያን በህንድ ፊልም የማደንቃቸውን የምደመምባቸውን የህንዳውያንን ሶስት ከተሞች ለመጎብኘት ከተመረጡ ከሰሜንና ምስራቅ አፍሪካ የተውጣጡ ጋዜጠኞች መካከል መሆን ድንገቴ ሆነብኝ። እኔም ብቻ ሳይሆን አብዛኛዎቹ የጋዜጠኞች ልዑካን ህንድ ከልጅነት ትዝታቸው ጋር የተሳሰረ አንዳች ነገር አለው። ህንድ በፊልሞቿ የሚያቋት ስለመሆኑ ጉብኝቱን ተከትሎ በተካሄደው በዶርሻን የቴሌቪዥን ጣቢያ ውይይት ላይ ሲያነሱ ሰምቻለሁ። በዓለም ላይ በህዝብ ብዛቷ ቀዳሚዋ ህንድ የብዝሃ ባህል፣ ቋንቋና ሃይማኖት አገር ናት። በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኪነ ጥበብ ስራዎቿ በዓለም ላይ ትታወቃለች። ለጉብኝት ከተጋበዙት የጋዜጠኞች ቡድን መካከል አባል ሆኜ በዴልሂ፣ አግራና ባንጋሎሩ ከተሞች በተጓዝንባቸው ስፍራዎች ሁሉ የታዘብኩት ህንዳዊያን በስራና ትጋት ላይ መሆናቸውን ነው። ሁሉም ነገውን ለማሳመር የራሱን ድርሻ ለማኖር፤ ለሀገሩ እድገትና ልማት አሻራውን ለማኖር እንደሚታትር መረዳት ይቻላል።   ባረፍንበት ሆቴል ያሉ ሰራተኞች፣ በገበያ ስፍራ የምናገኛቸው ሰዎች እንዲሁም በጎበኘናቸው ስፍራዎች ያሉ ሰዎች ሁሉ ለሀገራቸው እድገትና ልማት ብሎም ነጋቸውን ለማሳመር የራሳቸውን ድርሻ ለማኖር ይታትራሉ። አብሬ ከነበርኳቸው ጋዜጠኞች ጋር ስናወጋ የምናነሳው በከተማዋ በተጓዝንባቸው ጎዳናዎች የምናየው የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ በየተቋማት የሚታትሩ ሰራተኞች እንዲሁም በንግድ የተሰማሩ ሰዎች ደፋ ቀና ማለት ለአገር የሚያደርጉትን ልፋት ነው። አንድ ቀን በጋራ ሆነን ወደገበያ ስፍራ ስናቀና በፍጥነት የሚደርሱ ምግቦች ተመግበው ለመሄድ የሚፋጠኑ ህንዳውያንን ያየ የጋዜጠኛ ቡድኑ አባል መሰል ልምድና ጊዜ አጠቃቀም በአፍሪካም ሊለመድ የሚገባውና የአህጉራችንን የስራ ባህልና እድገት የሚያረጋግጥ መሆኑን የገለጸበት ሁኔታ ለአገሬው ህዝብ ታታሪነት እንደማሳያ አድርጌ ላነሳው ወደድኩ። በሄድንባቸው አካባቢዎች ሁሉ አዲስ ሰው ሲያዩ ለማገዝ አና ስለነገሮች ለማስረዳት የሚፈጥኑ ዜጎችን ተመልክቻለሁ። በተጓዝኩባቸው ከተማዎች ያየኋቸውን ስፍራዎች ከማስታወሻዬ እየነቀስኩ ለእናንተ ላካፍል ወደድኩ። በቅድሚያ ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የስድስት ሰዓት ተኩል በረራ በማድረግ የመጀመሪያ መዳረሻ ያደረግናትን ዴልሂን እንቃኛለን። ዴልሂ- ታሪካዊ ህንፃዎችን ከአዲሶቹ ጋር አጣምራ የያዘች ጥንታዊ ስልጣኔን ከዘመናዊው ጋር አዋህዳ የምታንፀባርቅ ከተማ ናት። በከተማዋ በተዘዋወርንባቸው ስፍራዎች ሁሉ ከጎዳናዎቿ እስከ ህንፃዎቿ ምድረ ግቢ ድረስ በእፅዋት የተሞላችና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትኩረት የሰጠች መሆኗን በግልፅ ያሳየች ከተማ ናት። በዴልሂ ብቻም ሳይሆን በተዘዋወርንባቸው በሶስቱም ከተሞች ጎዳና ስንጓዝ ያየናቸው ግዙፍ ዛፎች ትናንት አገሪቷ ለእፅዋት የሰጠችው ትኩረት ዛሬ ላይ ፍሬ አፍርቶ አስተዋልኩ። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ባለፉት ዓመታት እየተከናወነ ያለው ተግባር እንዲሁም በኮሪደር ልማት ከተሞችን ፅዱና አረንጓዴ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት አሁን ላይ ካመጡት ለውጥ ባለፈ ለወደፊት የሚኖራቸውንም መዳረሻ አሻግሬ ለማየት አስችሎኛል። አሰላሳዮቹ - በዴልሂ ቆይታችን በመጀመሪያ ያቀናነው ጥናቶችን በመስራትና ውይይቶችን በማድረግ በኩል አበርክቶ እያደረገ ያለውን ኦብዘርቨር ሪሰርች ፋውንዴሽን የተሰኘ አሰላሳይና ሃሳብ አመንጪዎች ቡድን (ቲንክ ታንክ ግሩፕ) ነው። ተቋሙ በአገር ውስጥ ባሉ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ በማተኮር የመስራት ተልዕኮን አንግቦ የተነሳ ቢሆንም አሁን ላይ ከኢኮኖሚና እድገት ባለፈ በኢነርጂ፣ አካባቢ፣ በደህንነትና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑና ለውሳኔ የሚጠቅሙ ሃሳቦችን በማመንጨት የአገሪቷን ህዝብና መንግስት እያገዘ ይገኛል። ከተቋሙ አባላት ጋር ባደረግነው ቆይታ ለራስ ችግር የራስ መፍትሄ ማምጣት ተገቢ ስለመሆኑ በአጽንኦት አንስተዋል። የአፍሪካ አገራት ትብብር የአህጉሪቷን ልዕልና ለማረጋገጥ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑም ተነስቷል። የአሰላሳይና ሃሳብ አመንጪዎች ቡድን አባላቱ ጋር ያደረግነውን ቆይታ ጨርሰን በቀጣይ ያመራነው በህንድ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ባሉ አገራት ጭምር በባቡር መንገድ መሰረተ ልማት ላይ አሻራ እያኖረ ወዳለው ራይትስ ወደተሰኘው ተቋም ነው። የህንድ የባቡር መንገድ የቴክኒካልና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት (Rail India Technical and Economic Service) የተሰኘው ይህ ተቋም ላለፉት 51 ዓመታት በባቡር መንገድ ጠበብቶች አማካኝነት በህንድና በመላው ዓለም ባሉ 62 አገራት በዘርፉ ሲሰራ ቆይቷል።   የእጅ ጥበብ ገበያ - ቀጣይ መዳረሻችን ደግሞ ዲል ሃት ኢና የተሰኘው የባህላዊ አልባሳትና ጌጣጌጦች እንዲሁም የቤት ማስዋቢያዎች መገኛ ወደ ሆነው ገበያ ነው። ገበያው ባይገበዩበትም ዞረው እንዲቃኙ የሚያስገድድ አንዳች ድምቀትን የተላበሰ መሆኑን ባደረኩት ቆይታ አስተውያለሁ። የንግድ ማህበር የሆነው የህንድ ኢንዱስትሪ ኮንፌዴሬሽን (ሲአይ አይ) በዴልሂ ቆይታችን ካየናቸው ተቋማት መካከል የሚጠቀስ ነው። ተቋሙ የንግድ፣ ፖለቲካ፣ የትምህርትና የሲቪል ማህበረሰብ አመራር አባላትን በጋራ በማሰለፍ ዓለም አቀፍና የኢንዱስትሪ አጀንዳዎችን እንዲቀርፁ የሚሰራ ነው። አደጋን የሚቋቋም መሰረተ ልማት ጥምረት (CDRI) በነበረን ቆይታ ጥምረቱ ከአገራት፣ ከተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎችና መርሃግብሮች፣ ከፋይናንስና የግል ተቋማት ጋር በመተባበር የአየር ንብረትና የአደጋ ስጋትን የሚቋቋም መሰረተ ልማት አስተዳደር ላይ እየሰራ መሆኑን ተገንዝበናል። ጥምረቱ የአደጋ ምላሽና መልሶ ማቋቋም፣ በተቋማትና ህብረተሰብ አቅም ግንባታ ድጋፍ ላይ ይሰራል። ጥምረቱ 46 አባል አገራትና ስምንት አጋር ድርጅቶች ያሉበት ሲሆን፤ አገራትና ዓለም አቀፍ አካላትን በማስተባበር የገንዘብና ቴክኒክ ድጋፍ የሚያደርግ የጥናትና ፈጠራዎች ውጤቶች እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን የሚጋሩበትም ነው።   የህንድ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዴልሂ(IIT Delhi) ሌላው የጉብኝት መዳረሻችን ነበር። ኢንስቲትዩቱ በኢንጂነሪንግና ሳይንስ ጨምሮ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በርካታ ሰዎችን አስተምሮ ያስመረቀ ሲሆን፤ የተለያዩ ሳይንቲስቶች፣ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችና ስራ ፈጣሪዎችን ማፍራት የቻለ ተቋም መሆኑን መገንዘብ ችለናል። ብሄራዊ ሙዝየም - በኒው ዴልሂ የሚገኘው የህንድ ብሄራዊ ሙዚየም በአገሪቱ ያለ ትልቁ ሙዚየም ሲሆን፤ በጉብኝታችን ወቅት ለዘመናት የቆየች ቅሪተ አካልን ጨምሮ፣ የተለያዩ የጥበብ ውጤቶችና የታሪክ አሻራ ማሳያ ስራዎችን ቀርበው ይጎበኙበታል። በዴልሂ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተደረገልን የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባባልና ውይይት ህንድና አፍሪካ የጠነከረ ቁርኝት ያላቸውና በንግድ አጋርነትት በቀዳሚነት የሚጠቀሱ መሆኑ ተመላክቷል። በተደረገልን ገለፃ ህንድና የአፍሪካ የንግድ መጠን 100 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ነው።   ህንድ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፣ ፋርማሲዩቲካል ፣ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪዎች ፣ ማዕድን እና የባንክ ዘርፎችን ያላት የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ወደ 75 ቢሊዮን ዶላር ገደማ መድረሱም ተገልጿል። ኢትዮጵያም ከህንድ ጋር ለዘመናት የዘለቀ ወዳጅነት ያላትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷም ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ መሆኑ ተነስቷል። ሁለቱ አገራት ያላቸው ግንኙነት በንግድና ኢንቨስትመንት ላይ ያተኮረ ብቻ ሳይሆን በባህል ትስስር ጭምርም የተጋመደ መሆኑ ተመላክቷል። ለወደፊቱም ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአህጉሪቱ ካሉ አገራት ጋር የምታደርገው ትብብርና ወዳጅነት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑም ተነስቷል። አግራ- የህንድ ታሪክ፣ ባህልና ኪነ ህንፃ መገለጫ በሆነችው አግራ ተገኝተን የጎበኘነው ህንድ ስትነሳ ስሙ ተያይዞ የሚነሳውን ታጅ መሃልን ነው። ታጅ መሃል በእምነ በረድ የተሰራ ውብ ኪነ ህንፃ ሲሆን፤ ንጉስ ሻህ ጃሃን ከሌሎች ሚስቶቹ ሁሉ አስበልጦ ለሚወዳት ሚስቱ ሙምታዝ መሀል ክብር ሲል የገነባው ድንቅ የእጅ ስራ ውጤት ነው። ታጅ መሃልን ስንጎበኝ የነበረው ሙቀት ሀይለኛ ቢሆንም ላባችን እየተንቆረቆረ ንጉሱ ለፋርስ ልዕልቷ ሚስቱ የነበረውን ፍቅር በተመለከተ በአስጎብኚያችን የሚሰጠንን ማብራሪያ ስናደምጥና የፍቅር ሃያልነትን ስናደንቅ ነበር። በዴልሂ ከጉብኝታችን ባሻገር በኢንዲያን ጌትና በገበያ ቦታዎች እንዲሁም በከተማዋ ጎዳናዎች ተዘዋውረን የህዝቡን ፍቅርና ተባባሪነት አይተናል። በተለይ ቦታ የጠፋን መሄድ ያሰብንበት ቦታ እንዳለ የሚያመላክት ፍንጭ በግርታችን ያስተዋሉ ከመሰላቸው "እዚህ መሄድ ፈልገህ ነው ይህን እዚህ ማግኘት ትችላለህ" የሚል ጥቁምታ በመስጠት እንግዳ ተቀባይነትና ሰው አክባሪነታቸውን ይገልፁልሃል። በዴልሂና አግራ የነበረንን ጉብኝትና ትዝታ እያሰላሰልን ቀጣይ መዳረሻ ያደረግናት ባንጋሎሩ ከተማን ነው። ባንጋሎሩ ቀጣይ ትረካችን ይሆናል።    
ስራዋን በውጤታማነት በማስቀጠል ለሌሎች ወጣቶችም መትረፍ የቻለችው ወጣት
May 22, 2025 1371
ብርሃኑ ፍቃዱ - ከሰቆጣ ኢዜአ በ2013 ዓ.ም የልብስ ስፌት ስራ የጀመረችው ወጣት ማህደር አስማረ፤ ነዋሪቷ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ሰቆጣ ከተማ ነው። ስራዋን በውጤታማነት የቀጠለችው ወጣት ከአንድ የልብስ ስፌት መኪና ተነስታ ወደ ሶስት የልብስ ስፌት መኪና የደረሰች ሲሆን ካፒታሏንም ከዓመት ዓመት በማሳደግ ላይ ትገኛለች። ስራዋን ለመጀመርም ባጠራቀመችው አነስተኛ ገንዘብ ቤት ተከራይታ ነበር። ከልብስ ስፌት መኪናው በተጨማሪ የሌዘርና የጥልፍ ማሽኖችን በማስመጣት የፋሽንና ዲዛይን ስራና ማሰልጠኛ ማዕከል በመክፈት ለሌሎች ወጣቶች መትረፍ የቻለችበትን አቅም ገንብታለች።   የማሰልጠኛ ማዕከሉን ለመክፈት እስከ 500 ሺህ ብር ወጪ ማድረጓን የገለፀችው ወጣት ማህደር፤ 30 ተማሪዎችን ተቀብላ አጫጭር ስልጠና ለመስጠት የምዝገባና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አጠናቃለች። "ውጤታማ ለመሆን ጠንክሮ ከመስራት ውጪ ሴትነቴም ሆነ ሌላ ምንም የሚያግደኝ ነገር የለም" የምትለው ወጣት ማህደር ፤ የፋሽንና ዲዛይን ማሰልጠኛ ማዕከልን ከማስፋት ባለፈ በቀጣይ የጨርቃ ጨርቅ ማምረቻ ፋብሪካ ለመገንባት አቅዳ እየሰራች መሆኑን ገልፃለች። ወጣት መሰረት ጌታቸው በማህደር የልብስ ስፌትና የፋሽንና ዲዛይን ማሰልጠኛ ማዕከል ከባለፈው ዓመት ጀምሮ የስራ እድል ተጠቃሚ ሆናለች።   ከድርጅቱ በቂ የልብስ ስፌት ሙያ፣ ልምድና እውቀት መቅሰሟንና ለዚህም ማህደር እውቀቷንና ልምዷን ሳትሰስት በማከፈሏ ብቁ ሰራተኛ እንድትሆን አድርጋታለች ። የማሰልጠኛ ማዕከሉ በከተማዋ መከፈቱ በተለይም ሴቶችና ወጣቶችን በዘርፉ ሰልጥነው የሙያ ባለቤት በመሆን ሰርተው የሚለወጡበት እድል የከፈተ ነው በማለት ትገልጻለች። ከወጣት ማህደር ጊዜን በአግባቡ መጠቀምና ጠንክሮ መስራትንና ቁርጠኝነትን ትምህርት ወስጃለሁ ያለችው ወጣት መሰረት ፤ በልብስ ስፌት ዘርፍ ላይም ውጤታማ ለመሆን እየተጋች መሆኑን ትናግራለች። የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ስራና ስልጠና መምሪያ ሃላፊ ዲያቆን ኪዳነ ማርያም ገብረህይወት፤ ወጣቶች የአካባቢያቸውን ፀጋ ለይተው ከተንቀሳቀሱ ውጤታማ እንደሚሆኑ ወጣት ማህደር ትልቅ አርአያ ናት ይላሉ።   ለአብነትም እንደ ወጣት ማህደር ያሉ ታታሪ ወጣቶችን በስፋት ለማፍራት በስራ እድል ፈጠራ ላይ በማተኮር እየተሰራ እንደሚገኝ ያስረዳሉ። የወጣቷን አርአያነት ለማስፋት በቀጣይ የብድር፣ የመስሪያና መሸጫ ቦታና ሌሎች ድጋፎችን በማድረግ እንደሚያበረታቱ አረጋግጠዋል። ወጣቶች በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ውጤታማ እንዲሆኑ ድጋፍና ክትትል በማድረግ በባለፉት ወራት ለ11 ሺህ ሰዎች የስራ እድሉ ተጠቃሚ መሆናቸውንም አውስተዋል።      
ትንታኔዎች
የባሕር  በር የሌላቸው ሀገራት አንገብጋቢው ጉዳይ
Aug 6, 2025 46
የባህር በር ጉዳይ በሀገራት ዘንድ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ግዙፍ ኢኮኖሚና ሰፊ ህዝብ ላላቸው ሀገራት ሕልውና ጉዳይ ሆኗል። በቱርክሜኒስታን አዋዛ ከተማ ሶስተኛው ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራት ጉባዔ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም በጉባኤው መክፈቻ ላይ ቁልፍ መልዕክት አስተላለፈዋል። ዋና ፀሐፊው ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በተለይም መልኩ እየተለዋወጠ ባለው ዓለም፤ በአየር ንብረት ለውጥና መሰል ተጽዕኖዎች ሳቢያ መልከ ብዙ ፈተና እንደተደቀነባቸው ገልጸዋል። በተለይ ለአንዳንዶቹ ህልውናቸውን እየተፈታተነ ስለመሆኑም አጽንኦት ሰጥተዋል። የዋና ጸሐፊው ንግግርም ፦ ዛሬ ከዚህ የተሰባሰብነው ለማንክደው አንድ ዕውነት ነው። መልክዓ ምድር መዳረሻን መወሰን የለበትም። ነገር ግን በአፍሪካ፣ በኤዥያ፣ በላቲን አሜሪካና በአፍውሮፓ 32 ሀገራት ባህር በር ስለሌላቸው የማደግ ዕድላቸው ተገድቧል፤ ኢ-ፍትሃዊነትንም አስፍቷል። ሀገራችሁ አያሌ ተግዳሮቶች ተጋርጦባቸዋል። ዕድገታቸው እንዲወሰን፣ በከፍተኛ የወጪ ንግድ ትራንስፖርት እንዲበዘበዙና በዓለም ገበያ ተደራሽ እንዳይሆኑ ፈተና ገጥሟቸዋል። በርካቶች በጥሬ ዕቃ ኤክስፖርት እንዲወሰኑ፣ ለተለዋዋጭ ዓለም አቀፍ ገበያ እንዲጋለጡ ብሎም በጠባብ ኢኮኖሚያዊ መሰረት እንዲታጠሩ አድርጓቸዋል። በሌላ በኩል የዕዳ ጫና ለመልከ ብዙና ዘላቂነት ላለው ችግር ዳረጓቸዋል። አንድ ሶስተኛው የዓለማችን ባህር በር አለባ ሀገራትም ለደህንነት እንዲጋለጡና የግጭት አዙሪት ችግር እንዲገጥማቸው ተገደዋል። ምንም እንኳን 7 በመቶው የዓላማችን ህዝብ ድርሻ ቢይዙም በዓለም ኢኮኖሚ አንድ በመቶ ብቻ ድርሻ ይዘዋል። ይህም ምንጊዜም ኢ-ፍትሃዊነትና መገለል ሁነኛ ማሳያ ነው። ይህ የኢ-ፍትሃዊነት መልክ ዘላለማዊ መሆን የለበትም። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በዓለም የፋይናንስና የንግድ መዋቅር ውስጥ ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ ናቸው። በበይነ-ዓለም ትስስር በገሀድ በሚታይበት የዛሬው የዓለም መልክ ስርዓታዊ መድሎና መገለል በይፋ የደረሰባቸው ሀገራት ናቸው። ይህም በብዙ ምክንያቶችም የቅኝ ግዛት አሻራ ምልክት ነው። በቅርብ ጊዜ ትውስታዎች እንኳን ከኮቪድ 19 እስከ አየር ንብረት ለውጥ ቀውሶች፣ ከአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል እስከ ግጭት እንዲሁም በጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች ሳቢያ ባህር በር የሌላቸው ሀገራት ዘላቂ የልማት ግቦችን ዕውን ለማድረግ ተቸግረዋል። ይህ ጉባኤ ችግሮችን ከማንሳት ባሻግር መፍትሄዎች ላይ ማተኮር አለበት። የቀጣይ ዘመን የእድገት መሻት ጉዞን መቀየስ ብሎም ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራትን የማልማት ዕድሎች በጋራ መግለጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምክር ይገባል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም በዚህ ረገድ ከሀገራቱ ጎን የቆመ ነው። በቀጣይ አስርት ዓመታት በትብብር መሰራት ካለባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ መዋቅራዊ ሽግግርን ማሳለጥ እና ኢኮኖሚያዊ ስብጥርን ማብዛት ላይ መተኮር ይገባል። ምክንያቱም እነዚህ ሀገራት በሰው ሃይል እና በተፈጥሮ ሀብት የታደሉ ቢሆንም በፋይናንስ እጥረትና በገበያ እጦት ይህን አቅም ተጠቅመው መልማት አልቻሉም። ወሳኝ የሆኑ እሴት ጨማሪ ኢንዱስትሪዎችን መገንባት፣ ሀገር ውስጥ ፈጠራዎችን ማጎልበት እንዲሁም ለቀጣናው ለትውልድ ትሩፋት የሚያቋድስ አካታች ልማትን ዕውን ማድረግ ይሻል። የሀገራቱን የገበያና የመልክዓ ምድር ተግዳሮቶችን ለማቅለል አንዱ መፍትሄ የዲጂታላይዜሸን ሽግግር ነው። በዲጂታል ምህዳር ተደራሽነት ለማቅለልም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ስራዎች መጠንከር አለባቸው። የግል ዘርፉን ማጠናከርም ኢ-ፍትሃዊነትና ተደራሸነትን ችግርን ለማቅለል ያግዛል። ሀገራቱ በቋንቋ፣ በባህልና በጥበብ በጥልቅ የተቆራኙ ናቸው። በሀገራቱ መካከል ያለው የተቆራረጠ ሎጂስቲክስ፣ ያልተሳለጠ የድንበር ግብይት፣ የተሟላ መሰረተ ልማት አለመኖር በዓለም ገበያ ተወዳደሪና ተደራሽ ለመሆን አልቻሉም። በመሆኑም ድንበር ዘለል የሆኑ ትስስሮችን ማሳለጥ በተለይም ሀገራትን የሚያስተሳሰሩ ኮሪደሮችን መገንባት፣ የጭነት ሎጂስቲክስን ማሳለጥ፣ የሃይል እና የአየር ትራንስፖርት ትስስርን መጨመር ያስፈልጋል። ይህን መንገድ በመከተል በቀጣናውና በዓለም ገበያ መግባት ብሎም ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወደ እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን ማቅረብ መሸጋገር ይቻላል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የንግድ ግብይት መልክን መለወጥ፣ የትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተቃኘ አካሄድ መከተል ይገባል። ዓለም አቀፍ የባለብዙ ወገን የፋይናንስ ተቋማትም የበይነ ሀገራት የድንበር ላይ ትስስርና የጋራ ልማት ላይ ተገቢውን የኢንቨስትመነት ልማት ፋይናንስ ማቅረብ ይገባቸዋል። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በቀጣናው ደረጃ ከተሰባሰቡ ልማትን ዕውን ማድረግ ያስችላልና። ባህር በር አልባ ሀገራት ምንም እንኳን ከዓለማችን ሀገራት የበካይ ጋዝ ልቀታቸው ለከ3 በመቶ ያነሱ ቢሆነም የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ገፈት ቀማሾች ግን እንርሱ ናቸው። ከሰሃራ በርሃ መስፋፋት እስከ በረዶ የሚቀልጥባቸው ተራራማ ሀገራት፣ የኤስያ ሀገራት አስቸጋሪ የአየር ጸባይ ለውጥ፣ በከባድ ዝናብና አውሎንፋስ የሚመቱ የላቲን አሜሪካ ሀገራት ለዚህ ማሳያ ናቸው። የአየር ንብረት ለውጥ ባህር በር አልባ ሀገራትን እየበላቸው ነው። የአየር ንብረት ለውጥና ባህር በር አልባነት ተዳምሮ ዕድገታቸውን እንዲወሰን ለአንዳንዶቹም በህልውናቸው ላይ አደጋ ደቅኗል። በተባበሰው የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ሳቢያ በአንድ አዳር በሚደርስ የመሰረተ ልማት ውድመት የሀገራት ዓለም አቀፍ ንግድ ተሳትፎ አደጋ ውስጥ ይወድቃል። በመሆኑም ቃል የተገቡ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መቋቋሚያ ፋየናንስ መተግበር፣ ተዕጽኖ የሚቋቋም መሰረተ ልማት መዘርጋት ይሻል” በማለት ነበር መልዕክታቸውን ያስተላለፉት። በአረንጓዴ ልማት፣ በፋይናንስ ማሰባሰብ፣ በብድር አቅርቦት እና ወለድ አያያዝና ትግበራ ጉዳይም ልብ መባል ያለበትን ጉዳይ ጠቅሰዋል። ባህር በር አልባ ሀገራት በጋራ ነጋቸውን ለማሳመርና ፈተናዎቻቸውን ለመሻገር በትብብር እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ጥያቄዋን በይፋ ከገለጸች ውላ አድራለች፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የባህር በር ጥያቄ የህልውና ጉዳይ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሽግግር ለምን አስፈለጋት?
Jul 19, 2025 662
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቲኒዮ ጉቴሬዝ አነሳሽነት እ.አ.አ 2021 የተመድ የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በኒው ዮርክ በበይነ መረብ አማራጭ ተካሄዷል። “የህዝቦች ጉባኤ” እና “የመፍትሄ ጉባኤ” የሚሉ ስያሜዎች የተሰጠው ጉባኤ ላይ ከ193 ሀገራት የተወጣጡ ከ51 ሺህ በላይ ሰዎች ተሳትፈውበታል። በምግብ ስርዓት ላይ የተዘጋጀ ይህ ታሪካዊ ጉባኤ ዓለም አቀፍ ሁነት ዋንኛ ግቡ የነበረው የተመድ አባል ሀገራት የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን እንዲያመጡ እና ስርዓተ ምግብን ከዘላቂ ልማት ግቦች በተለይም ከግብ ሁለት ረሃብን ማጥፋት ጋር ማስተሳሰር ነው። ጉባኤው በአምስት ዓበይት የትኩረት ነጥቦች ላይ ያተኮረ ነበር።   ለሁሉም ዜጋ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ ተደራሽ ማድረግ፣ ከብክነት ወደ ዘላቂ የምግብ አጠቃቀም መሸጋገር፣ ተፈጥሮን ያማከለ የምግብ ምርማነትን ማሳደግ፣ እኩልነትን መሰረት ያደረገ የአኗኗር ሁኔታን ማጠናከር እና ለአደጋዎችና ጫናዎች የማይበገር ጠንካራ የምግብ ስርዓት መገንባት ጉባኤው የተወያየባቸው ጉዳዮች ናቸው። ጉባኤው በወቅቱ አባል ሀገራት ሁሉን አቀፍ የምግብ ስርዓትን በመፍጠር የዘላቂ ልማት ግቦችን እንዲያሳኩ ጥሪ አቅርቧል። የተመድ የዓለም የምግብ ደህንነት ኮሚቴ የምግብ እና የስነ ምግብ ከፍተኛ የባለሙያዎች ፓናል የስርዓተ ምግብ አካሄድ ከባቢ አየር፣ ዜጎች፣ ግብአቶች፣ ሂደቶች፣ መሰረተ ልማቶችና ተቋማትን ጨምሮ ሁሉንም ተዋንያን ያሳተፈ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል።   ስርዓተ ምግብ ምርት፣ ማቀነባበር፣ ስርጭት፣ ማዘጋጀት፣ መመገብ እና የተረፈ ምግብ አወጋገድን አቅፎ የያዘ እና ይህም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ከባቢ አየር ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ ያለው ነው። የባለሙያዎች ፓናሉ የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን ዜጎች፣ ምድር፣ ብልጽግና፣ ሰላም እና አጋርነት ላይ ያውጠነጠነ መሆኑን ይገልጻል። ፓናሉ ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት በምግብ ስርዓት ላይ ለውጥ ያመጣል ያላቸውን ስድስት ሀልዮታዊ ማዕቀፎችን ቀርጿል። ህይወት ያላቸው እና የቁስ አካላት ባህርያት፣ ከባቢ አየር የመጀመሪያው ነው። በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ቴክኖሎጂ፣ ኢኖቬሽንና መሰረተ ልማት ሲሆን ኢኮኖሚ እና ገበያ ሶስተኛውን ስፍራ ይይዛል። ፖለቲካ እና ተቋማዊ ሁኔታ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ጉዳዮች እንዲሁም የስነ ሕዝብ ውቃሬ ሌሎች የምግብ ስርዓት ለውጥ አምጪ ምክንያቶች እንደሆኑ ተቀምጧል። ስድስቱ የምግብ ለውጥ አሳላጭ ሁኔታዎች ተፈጻሚ እና ውጤታማ የሚያደርጉ አራት ቁልፍ መስኮች እንዳሉም የባለሙያዎች ፓናሉ ያስቀምጣል። የምግብ ምርታማነትን የሚያሳድጉ ስርዓቶችን መደገፍ፣ የምግብ አቅርቦት ሰንሰለትን ማጠናከር፣ የዜጎችን የምግብ አጠቃቀም ባህሪያት ላይ ለውጥ ማምጣት እና የተመጣጠኑ ንጥረ ምግቦችን ብዝሃነት ማስፋት ቁልፍ የትኩረት ጉዳዮች ናቸው።   የተቀመጡትን ማዕቀፎች፣ ለውጥን የመፍጠሪያ መንገዶች እና አስቻይ ሁኔታዎች ከፖሊሲ እና ሁሉን አቀፍ አስተዳደር ጋር በማቆራኘት የምግብ ስርዓት ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚገቡ ባለሙያዎቹ ምክረ ሀሳባቸውን ያቀርባሉ። የኢትዮጵያ የስርዓት ምግብ ራዕይ (EFS) መነሾም በስርዓተ ምግብ ጉባኤው እ.አ.አ በ2030 መሳካት አለባቸው ብሎ ያስቀመጣቸውን የስርዓተ ምግብ ግቦች እውን ለማድረግ ያሉ ፈተናዎች እና እድሎች ናቸው። እ.አ.አ በ2024 የወጣው የኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሁሉን አቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ በጉባኤው የተቀመጡ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት እና የጉባኤውን ምክረ ሀሳቦች ለመተግበር ቁርጠኛ እንደሆነች ይገልጻል። የኢትዮጵያ መንግስት እ.አ.አ ዲሴምበር 2020 የኢትዮጵያ ስርዓተ ምግብ የአሰራር ሂደት ይፋ ያደረገ ሲሆን ሂደቱ እ.አ.አ ጃንዋሪ 2021 ተጀምሯል። የስርዓተ ምግብ ማዕቀፉ የኢትዮጵያን የስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ራዕይን በግልጽ ያስቀመጠ ነበር። በወቅቱ ሂደቱን ለማስጀመር የቀድሞ የግብርና ሚኒስትር ኡመር ሁሴን እና የቀድሞ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የመሯቸው የከፍተኛ ደረጃ ምክክሮች የተደረጉ ሲሆን ሰነዶችም ተቀርጸዋል። በስርዓት ምግብ ላይ ሁለት ብሄራዊ ምክክሮች የተደረጉ ሲሆን ምክክሮችን ተከትሎ የኢትዮጵያ ስርዓተ ምግብ ሂደት ይፋ ሆኗል። ምክክሮቹ የኢትዮጵያ ምግብ ስርዓት አሁናዊ ሁኔታ አና መጻኢ ሁኔታዎች፣ የኢትዮጵያን የምግብ ስርዓት የመለወጥ ጉዞ በሚል ርዕስ የተካሄዱ ናቸው። የስርዓተ ምግብ ሂደት ቀረጻው ላይ መንግስት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የሲቪክ ማህረሰቦች፣ የምርምር ተቋማት፣ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ተቋማት ያሉባቸው ከ120 በላይ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። ይፋ የሆነውም የስርዓተ ምግብ ሂደት ሰነድ እ.አ.አ በ2021 በጣልያን ሮም በአካል ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ ላይ ቀርቦ አዎንታዊ ምላሾችን አግኝቷል። የስርዓተ ምግብ ሂደት ማዕቀፉ ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ፣ ከ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ እንዲሁም ከሌሎች የፖሊሲ እና አሰራሮች ጋር የተጋመደ ነው። የኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሁሉን አቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ለውጥ እና ሽግግር ያስፈለገባቸውን ምክንያቶች ያስቀምጣል። የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ተደራሽነት በሚፈለገው ደረጃ ማረጋገጥ አለመቻል፣ ፈጣን የህዝብ እድገት፣ የክትመት መጠን መስፋፋት፣ የከባቢ አየር ጉዳት እና የአየር ንብረት ለውጥ፣ እኩል ያልሆነ የዜጎች አኗኗር፣ ደካማ የምግብ ስርዓት መሰረት፣ ግብርናን ለኢኮኖሚ ያለውን ድርሻ ማሳደግ እና የምግብ ስርዓትን ከብሄራዊና ዓለም አቀፍ ግቦችን ጋር ማሰናሰን ማስፈለጉ የስርዓተ ምግብ ለውጡ መሰረታዊ ለውጥ መነሻ ናቸው። ኢትዮጵያ በስርዓተ ምግብ ሽግግር ውስጥ ስንዴን ጨምሮ በተለያዩ ሰብሎች ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ፣ የንጥረ ነገሮችን ብዝሃነት በማስፋት፣ የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ተደራሽነትን በማሳደግ እና የግብርና ማቀነባበሪዎችን ቁጥር በመጨመር አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግባለች። በዚህም በዜጎች ጤና እና ገቢ እድገት ላይ ለውጦች መምጣታቸውን ሪፖርቱ ያሳያል። ብሄራዊ የምግብ ስርዓት ማዕቀፎች፣ በምክክሮች የዘርፉ ተዋንያን የማሳተፍ ሁኔታ እያደገ መምጣት፣ በምግብ ስርዓቱ በሰባቱ ስትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ስር ለውጥ አምጪ ተብለው የተቀመጡ 24 መፍትሄዎች እና ተቋማዊ አቅም ግንባታ ሌሎች የታዩ አበረታች ለውጦች ናቸው። ሰባቱ ስትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብን ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ፣ ጤናማ የአመጋገብ ሁኔታን መፍጠር፣ አሰራሮች እና ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መንገድ መተግበር፣ በምግብ ስርዓቱ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና አሰራሮችን መተግበር፣ የገበያ ተደራሽነት ማስፋት እና መረጃ አሰጣጥን ማጠናከር፣ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ህብረተሰብ ክፍሎችን መጠበቅ እና የማይበገር አቅም መገንባት እንዲሁም መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋት፣ ዘላቂነት ያለው የከተሜነት እድገትን መፍጠር እና ክህሎት ልማት ላይ ያተኮሩ ናቸው።   ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን በሚፈለገው መጠን ተደራሽ አለማድረግ፣ ደካማ የምግብ ደህንነት መሰረተ ልማት፣ የግብርና ሜካናይዜሽን አለመስፋፋት፣ የከባቢ አየር ጉዳቶች፣ የቅንጅታዊ አሰራር ላይ ያሉ ክፍቶች እና የዜጎች የአኗኗር ሁኔታ ለይ ለውጦች ቢኖሩም አመርቂ አለመሆን፣ የፋይናንስ ውስንነት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ ቴክኖሎጂዎች ተደራሽነት በምግብ ስርዓቱ ዋና ፈተናዎች ተብለው የተቀመጡ ናቸው። የምግብ ስርዓትን አስተዳደርን እና የባለድርሻ አካላት ቅንጅትን ማጠናከር፣ የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ መዋቅሮችን መዘርጋት፣ የመንግስት እና የግል አጋርነትን ማጠናከር፣ አቅምን መገንባት እና የምግብ ስርዓት አጀንዳ ዘላቂነት ባለው እና በተቀናጀ ሁኔታ ለማህበረሰቡ ማስገንዘብ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተብለው ከተለዩ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ። የገበያ ትስስርን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ እቅዶች እና ስትራቴጂዎችን ማቀናጀት እንዲሁም ወጣቶች፣ ሴቶች እና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጨምሮ የስርዓተ ምግብ ትግበራው ሁሉን አካታችነት የበለጠ ማረጋገጥ ቀጣይ የቤት ስራ ተብለው የተያዙ ናቸው። በአጠቃላይ የስርዓተ ምግብ ማዕቀፉን በየጊዜው በመፈተሽ እና የሁኔታዎችን ተለዋዋጭነት ከግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ የአስተዳደር መዋቅርን በማሻሻል እ.አ.አ በ2030 የተያዙ ግቦችን ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራ ሁሉን አቀፍ ሪፖርቱ ያመለክታል። በአዲስ አበባ ከሐምሌ 20 እስከ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በስርዓተ ምግብ ላይ እያከናወነች ያለውን ስራ ለዓለም የማሳወቅ ስራ ታከናውናለች። በስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ያላትን ተሞክሮዎች በዋናው ጉባኤ እና በጎንዮሽ ሁነቶች ላይ ታቀርባለች። የጉባኤው ተሳታፊዎችም የኢትዮጵያን የስርዓተ ምግብ የተግባር ስራዎች እና ውጤቶች በመስክ ምልከታቸው ይቃኛሉ።
የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ አሻራ ያረፈበት የኢትዮ-ታንዛንያ ወዳጅነት
Dec 17, 2024 3862
የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። የታንዛንያ የውጭ ጉዳይ እና ምሥራቅ አፍሪካ ትብብር ሚኒስትር አምባሳደር ማሕሙድ ታቢት ኮምቦ በስብስባው ላይ ለመሳተፍ ትናንት አዲስ አበባ ገብተዋል። ስብስባው የኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የሁለትዮሽ ትስስር እና የጋራ ትብብር የማጠናከር ዓላማ የያዘ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት በየካቲት ወር 2016 ዓ.ም ከታንዛንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከነበሩት ጃንዋሪ ማካምባ ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት የኮሚሽኑን ስብስባ ለማካሄድ ከስምምነት መድረሳቸው አይዘነጋም። የኢትዮጵያና ታንዛንያ የሁለትዮሽ ወዳጅነት በቅርበት ለመረዳት የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄን ማየት ግድ ይላል። የመላው ጥቁር ሕዝቦች ንቅናቄ የሆነው ፓን አፍሪካኒዝም ጅማሮ በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። የፓን አፍሪካኒዝም መሰረት የሆነችው ኢትዮጵያ የንቅናቄው ፋና ወጊ በመሆን ወሳኝ ሚና ተጫውታለች።   የፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር አብረው በመቆም ትግል ሲያደርጉ ከነበሩት አገራት መካከል ታንዛንያ ትገኝበታለች። በፓን አፍሪካኒዝም ትግል ውስጥ ስማቸው በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ መሪዎች መካከል ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ እና የታንዛንያው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጁሊዬስ ኔሬሬ ተጠቃሽ ናቸው። መሪዎቹ ለአፍሪካ አገራት ከቅኝ አገዛዝ መውጣት ትልቅ ሚና በመጫወት ሕያው አሻራቸውን አሳርፈዋል። የኢትዮጵያና ታንዛንያ የሁለትዮሽ ግንኙነት በእነዚህ መሪዎች ጊዜ የተጀመረ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። አገራቱ በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጣር ግንቦት 25 ቀን 1963 የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (በአሁኑ መጠሪያው የአፍሪካ ኅብረት) መቋቋሙ ሲበሰር መስራች አባል አገራት ነበሩ። ኢትዮጵያና ታንዛንያ በየአገራቱ ኤምባሲያቸውን በይፋ በመክፈት የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናክር እየሰሩ ይገኛሉ። አገራቱ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማጠናከር የሚያስችላቸው በርካታ አቅሞች አሉ። ኢትዮጵያ እና ታንዛንያ ባላቸው የቁም እንሥሳት ኃብት ከአፍሪካ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ አገራት ናቸው። ሁለቱ አገራት በሚያደርጓቸው የጋራ ምክክሮች ይሄን ሰፊ ኃብት በመጠቀም የንግድ እና ኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከር እንደሚገባ በተደጋጋሚ ጊዜ ያነሳሉ። ግብርና፣ የሰብል ምርት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ እና አቪዬሽን ከሁለቱ አገራት የትብብር መስኮች መካከል በዋናነት ይጠቀሳሉ። የኢትዮጵያ አቪዬሽን አካዳሚ በርካታ ታንዛንያውያን ፓይለቶች እና ኢንጂነሮችን አሰልጥኖ አስመርቋል። አቪዬሽንም የሁለቱ አገራት ቁልፍ የትብብር መስክ በሚል ይነሳል።   ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በየካቲት ወር 2016 ዓ.ም በታንዛንያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከታንዛንያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሁሉ ሀሰን ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። አገራቱ በወቅቱ በባህልና ኪነ-ጥበብ፣ በግብርና እንዲሁም በኤሌክትሪክ ኃይል ንግድ ላይ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቶቹ የሁለቱ አገራት ትብብር ይበልጥ ለማጠናክር ትልቅ ፋይዳ አላቸው። የዛሬው የኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባም የስምምነቶችን አፈፃጸም በመገምገም ትግበራውን ማፋጠን የሚያስችል አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።   ከሰሞኑ የምሥራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት አካል የሆነው ከኬንያ ወደ ታንዛንያ የተዘረጋው የኤሌክትሪክ መስመር የሙከራ የኃይል አቅርቦት መጀመሩ ይታወቃል። የቀጣናው ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ (ሃይዌይ) ፕሮጀክት የመጀመሪያው የኃይል ትስስር ኢትዮጵያና ኬንያን ያስተሳሰረ መሆኑ ይታወሳል። የፕሮጀክቱ ሁለተኛ ክፍል ደግሞ ከኬንያ ወደ ታንዛኒያ የተዘረጋ ሲሆን የኤሌክትሪክ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ተጠናቆ የሙከራ ኃይል አቅርቦት መጀመሩን የውኃና ኢኒርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ይህ ቀጣናዊ የኃይል ትስስር በተመጣጣኝ ዋጋ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት በማረጋገጥ በሀገራት መካካል ትብብርን እና የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው። የኃይል አቅርቦት መጀመሩ ከኢትዮጵያ እና ታንዛንያ አልፎ በቀጣናው ያለውን ትስስር ለማፋጠን ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይታመናል። ሁለቱ አገራት በቅርቡ ወደ ትግብራ ምዕራፍ የገባው የናይል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን በአገራቸው ፓርላማ ማጽደቃቸው ይታወቃል። ስምምነቱ በናይል ተፋስስ የውኃ ኃብትን ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ በሆነ መልኩ በበጋራ ለመጠቀም የሚያስችል ነው። አገራቱም በውኃ ኃብት ያላቸውን ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክር ነው። የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ ያስተሳሰራቸው ኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ትብብራቸውን ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ማሸጋግር የሚያስችሉ ሰፊ እድሎች ከፊታቸው ይጠብቃቸዋል።    
ከተለምዷዊ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር የተሻገረው የኢትዮ-አልጄሪያ ወዳጅነት 
Dec 16, 2024 3268
የኢትዮ-አልጄሪያ ግንኙነት ታሪካዊ ነው፡፡ታሪካዊነቱ በዘመንም፣ በጸና ወዳጅነትም ይለካል።ትናንት ማምሻውን የሀገሪቷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ የሀገሪቷን ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔን መልክዕት ይዘው አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል። ዛሬ ማለዳ ደግሞ ሚኒስትሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱም ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን የፀና ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናግረዋል። የፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔን መልዕክትም ተቀብለዋል። ​ ጉብኝቱን አስመልክቶ የሰሜን አፍሪካዊቷ አልጄሪያ እና የኢትዮጵያን ወዳጅነት የትመጣ እና ሂደት በወፍ በረር እንቃኝ። የኢትዮ-አልጀሪያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሰባት አስርት ዓመታትን ተሻግሯል። ሁለቱ ሀገራት ከመደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር የተሻገረ ወንድማማችነትና ወዳጅነት መስርተዋል። የፈረንሳይ ቅኝ ተገዥ የነበረችው አልጄሪያ በአውሮፓዊያኑ 1960ዎቹ መባቻ ነጻነቷን ለመቀዳጀት ትንቅንቅ ላይ በነበረችበት ዘመን ኢትዮጵያ አጋርነቷን አሳይታለች። ይህን ደግሞ በኢትዮጵያ የአልጄሪያ አምባሳደር የነበሩት ኤልሃምዲ ሳላህ ‘አልጀሪያ የኢትዮጵያን ውለታ አትረሳውም’ ሲሉ በአውሮፓውያኑ 2022 ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀው ነበር። ​​​ አልጀሪያ በ1962(በአውሮፓዊያኑ) ነበር ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ነጻነቷን ያረጋገጠችው። ከዚህ ዘመን ጀምሮ ሁለቱ ሀገራት ወዳጅነታቸውን መሰረቱ። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንዲመሰረት እና የፓን አፍሪካኒዝም እንዲያብብ ንቅናቄ አድርገዋል። በ1960ዎቹ መጨረሻም ይፋዊ ዲፕሎማሲ ግንኙነታቸውን በይፋ ጀመሩ። አልጄሪያ የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት(የአሁኑ የአፍሪካ ሕብረት) መገኛ በሆነችው ኢትዮጵያ ኤምባሲዋን በ1976(እ.ኤ.አ) ከፈተች። ኢትዮጵያም በ2016 ኤምባሲዋን በአልጀርስ ከፍታለች። ሁለቱ ሀገራት በአውሮፓዊያኑ 2014 በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ንግድ፣ ባህል እና በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር የሚያስችል የጋራ ኮሚቴ ፈጥረዋል። ሁለቱ ሀገራት በንግድ፣ ኢንቨስትመንት ጥበቃ እና ማስተዋወቅ እንዲሁም ተደራራቢ ታክስ ማስቀረትን ጨምሮ ከ20 በላይ የትብብር መስኮች በጋራ መስራት ስምምነት ተፈራርመዋል። ከሁለትዮሽ ባሻገርም ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ የትብበር መስኮች ያላቸውን ትብብር የማጠናከር ፍላጎት አላቸው። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት በመስከረም ወር 2017 ዓ.ም በኒውዮርክ በተካሄደው 79ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን ከአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር መወያየታቸው ይታወቃል። በዚሁ ውይይት ኢትዮጵያ እና አልጄሪያ በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን አልፎም በዓለም የሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል። አምስተኛውን የኢትዮ-አልጄሪያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ በቅርብ ጊዜ ለማከናወን የተጀመረውን ዝግጅት ለማፋጠን ተስማማተዋል። ​​​ አልጄሪያ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና የጸጥታ ምክር ቤት ከአውሮፓዊያኑ ጃንዋሪ 2024 አንስቶ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና በመስራት ላይ ትገኛለች። ይህም ሁለቱ ሀገራት በባለብዝሃ ወገን የዲፕሎማሲ መድረክ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ የሚያጎለብት ነው። አልጄሪያ በአውሮፓዊያኑ በ2021 የአረብ ሊግ ሊቀመንበር በነበረችበት ወቅት ተቋሙ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የተዛባ አረዳድ ለማስተካከል እና ሚዛናዊ እይታ እንዲኖረው ጥረት አድርጋለች። የኢትዮ-አልጄሪያ የሁለትዮሽ ትብብር የሚያጠናክሩ የጉብኝት ልውውጦች እና ውይይቶች እያደጉ መጥተዋል። ​​​ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም በአልጄሪያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል። በወቅቱም ከአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔ ጋር ተወያይተው ነበር።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኢትዮ-አልጄሪያ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ታሪካዊ በሁለትዮሽ ትብብር ይበልጥ ማጠናከር የሚቻለባቸው ዘርፎች እንዳሉ ገልጸው ነበር። ​​​ ከዚህ ጊዜ ጀምሮም በሀገራቱ መካከል የጉብኝት ልውውጦች እና ውይይቶች እየጨመሩ መጥተዋል። ለአብነትም በአውሮፓዊያኑ በ2021 የያኔው የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራምታኔ ላማምራ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገው ነበር፤ የሁለትዮሽ ትብብር ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውም አይዘነጋም። ​​​ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ደግሞ በሩሲያ ሶቺ በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ከተካሄደው የመጀመሪያው የአፍሪካ-ሩሲያ የትብብር ፎረም የሚኒስትሮች ስብስባ ጎን ለጎን ከአልጄሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ ጋር መክረዋል። በውይይታቸውም የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያስጠብቁ ቀጣናዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር። እናም ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ የትብብር መስኮች ግንኙነታቸውን ማጎልበት ቀጥለዋል። በአልጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር መሀመድ ዋሬ በቅርቡ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብዱልመጂድ ቴቡኔ ሲያቀርቡ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና የፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴን ልባዊ ሰላምታ እና የወዳጅነት መልዕክት ለፕሬዝዳንቱ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው። ዛሬ ደግሞ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የሚገኙት የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ የፕሬዝዳንት አብደልመጂድ ቴቡኔን መልዕክት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አድርሰዋል። የሚኒስትር አሕመድ አታፍ ጉብኝት ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው እና የኢትዮ-አልጀሪያ ሁለትዮሽ ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት አካል ስለመሆኑ የአልጄሪያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ጋርም ተወያይተዋል። በውይይቱ በሁለትዮሽ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው አገራቱ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትስስር በማጠናከር እና አዳዲስ የትብብር አድማሶችን በመፈለግ አጋነታቸውን ለማጎልበት እንደሚሰሩ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ እና አልጄሪያ የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብስባን በቅርቡ ለማድረግ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። ​ እናም ኢትዮጵያና አልጄሪያ ከተለምዷዊ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር የተሻገረ ነው። ሁሉን አቀፍ በሆኑ የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ባደረጉ ትብብር መስኮች እየተወዳጁ ነው። የስትራቴጂካዊ አጋርነት ደረጃ እየጎለበተ ይመስላል። የአገራቱ መጻዒ የትብብር ጊዜ ብሩህ እና ፍሬያማ እንደሚሆን አያጠራጥርም።
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 3332
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 2740
  ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
የአርሶ አደሮችን ጓሮና ኑሮ የለወጡ ቁጥሮች- “30-40-30”
Nov 15, 2024 4236
ለዛሬው ትውልድ ምግብ፣ ለመጪው ትውልድ ደግሞ ቅርስና ውርስ የሚሆን ሃብት የሰነቀው የ"30-40-30" ኢኒሼቲቭ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አርሶ አደሮች መንደር ተገኝቶ ስለ ’30-40-30’ አሃዞች አርሶ አደሮችን የሚጠይቅ ካለ የቁጥሮችን ትርጓሜና ስሌት በቅጡ መረዳት ይችላል። እነዚህ ቁጥሮች በገጠራማው የክልሉ አካባቢዎች አባውራዎች ዘንድ ሕይወትም፣ አስተሳስብም ለውጠዋልና። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኅላፊ አቶ ዑስማን ሱሩር የ’30-40-30’ ኢኒሼቲቭ የተጠነሰሰው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭን በመመርኮዝ ስለመሆኑ ያስታውሳሉ። እነዚህ ቁጥሮች የተራ አሃዝ ስያሜ ሳይሆኑ በክልሉ ግብርና ወደ እመርታ ለማስፈንጠር የተቀየሱና ትውልድ ተሻጋሪ ዓላማ የሰነቁ ናቸው። በ2014 ዓ.ም ጀምሮ እያንዳንዱ የክልሉ አርሶ አደር በሶስት ዓመታት ውስጥ ቢያንስ 100 የፍራፍሬ ዛፎች አልምቶ እንዲጠቀም መሰረት የሆኑም ናቸው። በኢኒሼቲቩ የለሙ ፍራፍሬዎች የአርሶ አደሩን ኑሮ ማሻሻል ያለሙ፣ 'ለዛሬው ትውልድ ምግብ፣ ለመጪው ትውልድ ደግሞ ቅርስና ውርስ ናቸው' ይላሉ። የምግብና ስነ-ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ ገቢ ምንጭ ማድረግ፣ ስራ ዕድል መፍጠር፣ ገበያ ማረጋጋት፣ ለኤክስፖርትና ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት ማቅረብን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ዓላማዎችም አሏቸው። በእያንዳንዱ አባውራ ጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲለማና ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል የተወጠነ ነው። በዚህም በ'30-40-30'ን እያንዳንዱ አባወራ ጓሮውን እንደየአካባቢው ስነ-ምህዳር በሙዝ፣ በፓፓያ፣ በማንጎ፣ በቡና፣ በአቮካዶና በሌሎች ፍራፍሬ ችግኞች እንዲያለማ ተደርጓል። 'ያልተሄደበትን መንገድ በመሄዳችን በትግበራ ሂደቱ ፈተናዎች ነበሩ' የሚሉት ሃላፊው፤ ዛሬ ላይ ግን የ30-40-30 ኢኒሼቲቭ ፍሬ የቀመሱትን ሁሉ አስተሳስብ ለውጧል ይላሉ። ኢኒሼቲቩ ባልተለመዱ አካባቢዎች የፍራፍሬ መንደሮች የተፈጠሩበት፣ የአርሶ አደሩ ኑሮና ጓሮ የተለወጠበት፣ የይቻላል አስተሳስብ የተፈጠረበት እንደሆነ ይናገራሉ። በክልሉ የ30-40-30 ኢኒሼቲቭ በመተግበር ከሴፍቲኔት የተላቀቁና ኑሯቸውን ያሻሻሉ አረሶ አደሮች ለዚህ ምስክር ናቸው። በስልጤ ዞን ውልባረግ ወረዳ ቶዴ ጠመዳ ነዋሪዎች አቶ ሀምዛ አሊዬ እና ባለቤታቸው አናጃ ኢሳ በሴፍትኔት ታቅፈው ሲረዱ የቆዩ ሲሆን በ30-40-30 ጓሯቸውን በቡና በማልማታቸው ዛሬ ገቢም፣ ምግብም ችለዋል። በ500 የቡና ችግኝ ድጋፍ ጀምረው በየዓመቱ እያሳደጉ ዛሬ ላይ ቡናቸውን ለቅመው በመሸጥ ገቢ ማመንጨትና ነሯቸውን መደጎም ችለዋል። ጓሯቸውን በማልማታቸውም ከሴፍትኔት መላቀቅ ብቻ ሳይሆን ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ያላቸው ማህበራዊ ህይወት እንዲሻሻል ስለማድረጉም ገልጽው፤ በቀጣይነትም ሌሎች ፍራፍሬዎችን ለማልማት ተዘጋጅተዋል። በውልባረግ ወረዳ ቢላዋንጃ ባቢሶ ቀበሌ ነዋሪው አቶ ኢክማላ መሀመድ እና ልጃቸው መካ ኢክማላ ደግሞ አካባቢውን ያልተለመደ የሙዝ መንደር በማድረግ ኑሯቸውን እንዳሻሻሉ ይናገራሉ። የ30-40-30 ንቅናቄ ሲጀመር በአካባቢው "ሙዝ አይለማም" በሚል የተሳሳተ እሳቤ ቅር እያላቸው ችግኞችን ወስደው የተከሉ ቢኖሩም በርካቶች በእምቢታ ጸንተው እንደነበር አስታውሰዋል። በሂደት ውጤቱ ሲታይ ግን የልማቱ ተሳታፊዎች በዝተው በውጤትና የስኬት መንገድ ላይ መቀጠላቸውን ተናግረዋል። ከሳዑዲ አረቢያ የ10 ዓመታት የስደት ቆይታ በኋላ የተመለሰው ልጃቸው መካ ኢክማላ የስደት አስከፊነትን በማንሳት ተፈጥሮ በሰጠችን ጸጋ ሳንጠቀም በመቆየታችን ይቆጨናለ ይላል። የ30-40-30 ንቅናቄም ወጣቶች ከስደት ይልቅ በጓሯቸው ሰርተው መለወጥ እንደሚችሉ ዐይን የገለጠ እና የአስተሳሰብ ለውጥም ያመጣ ስለመሆኑ ይናገራል።     በሀድያ ዞን ሻሸጎ ወረዳ ዶዕሻ ጎላ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ይቴቦ ሽጉጤ፤ ኢኒሼቲቩን በመጠቀም ከሌሎች አርሶ አደሮች ጋር የሙዝ መንደር መስርተዋል።   የክላስተር ሙዝ መንደራቸው በሶስት ዓመታት ውስጥ የቤተሰባቸው ኑሮ እንዲሻሻል ያደረገና በቀላሉ ጸጋን ተጠቅሞ መለወጥ እንደሚቻል ያረጋገጠ ስለመሆኑም ገልጸዋል። የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሙበራ ከማል፤ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚል ንቅናቄ በርካቶች በተለይም በፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ልማት ተሳትፈው ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል። በአካባቢ ያሉ ጸጋዎችን በመለየት የቡና፣ የሙዝና የአቮካዶ ክላስተር በማልማት ከፍጆታ አልፈው ለማዕከላዊ ገበያ እየቀረቡ ስለመሆኑም ይናገራሉ። በሀድያ ዞን የሻሸጎ ወረዳ ግብርና ፅህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር ወንዱ መለሰ፤ የ30-40-30 የፍራፍሬ ልማት ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱን ተናግረዋል። በሙዝ ክላስተር አርሶ አደሮች በትብብር ሰርተው እንዲለወጡ ያስቻለ መሆኑን ገልጸው፤ አርሶ አደሮችም ውጤቱን በማየት ወደተጨማሪ ልማት እየገቡ ይገኛሉ ብለዋል። የ30-40-30 ኢኒሼቲቩ 'ጥረት ካለ ስኬት እንዳለ ማሳየት የተቻለበት እና የግብርናው ዘርፍ አንኳር መሰሶዎችን ዕውን ለማድረግ ተስፋ ሰጭ ውጤት የተገኘበት መሆኑን አቶ ዑስማን ይገልጻሉ። በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የግብዓት ፍላጎት በመጨመሩ ተደራሽነቱን ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል። የ30 40 30 የፍራፍሬ ልማት ፕሮጀክት አንድ አርሶ ወይም አርብቶ አደር በመጀመሪያ ዓመት 30፣ በሁለተኛው ዓመት 40 እና በሶስተኛ ዓመት 30 የፍራፍሬ ችግኞችን በመትከል ተጠቃሚ የሚሆንበት መርሃ ግብር መሆኑ ይታወቃል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 49616
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 46123
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 28504
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 25880
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 24031
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 22119
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 22072
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 21691
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 49616
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 46123
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 28504
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 25880
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
በደን ውስጥ ያረፈ አረንጓዴ አሻራ ምግብ እና ገንዘብ የሆነባት - ቤንች ሸኮ ዞን!
Aug 1, 2025 671
(በቀደሰ ተክሌ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ውስጥ የሚገኘው የቤንች ሸኮ ዞን አረንጓዴና የምድር ገነት ከሚባሉ አካባቢዎች አንዱ ነው። ይህ አካባቢ በተፈጥሮ የተቸረው ሰፊ የደን ሽፋን ያለው ሲሆን ደኑ ክብሩን ጠብቆ ከዘመን ዘመን የመሸጋገሩ ምሥጢር ደግሞ በአካባቢው ብሔረሰቦች ዛፍ መቁረጥን እንደ ነውር የማየት ባህል መሆኑ ነው። በአካባቢው ዛፍ መቁረጥ ነውር ነው። ደፍሮ ያለአግባብ ቆርጦ ዛፍን ከቦታው የሚያጠፋ በአካባቢው ሽማግሌዎች ይረገማል። በዞኑ ዛፍን ቀርቶ ከዛፉ ጋር ተያይዞ የወጣን ሐረግ እንኳ በዘፈቀደ መቁረጥ አይፈቀድም። ለቤት መሥሪያና ሌሎች አገልግሎቶች ለመጠቀም ሲፈለግ እንኳን ጥቅጥቅ ያለ ደን እንዳይሳሳ አለፍ አለፍ ብሎ በጥንቃቄ የመቁረጥ ተሞክሮ አላቸው።   ለቤንች ሸኮ ዞን ነዋሪዎች በቤታቸው ቅርበት ላይ ዛፍ መትከል ቅንጦት ሳይሆን እንደ መሠረታዊ የኑሮ ዘዬ ተደርጎ ይቆጠራል። በአረንጓዴ ልምላሜ ያልተከበበ ቤት የሰነፍ ቤት ነው። ከዛፎቹ አንዱ ቢቆርጥ እንኳ ሌላ ከስር ይተካል እንጂ እንዲሁ አይተውም። የአካባቢውን ልምላሜና አረንጓዴ ገጽታን ጠብቆ ያቆየው ይህ ባህል የቤንች ሸኮዎች ከጥንት ጀምሮ ዛሬም ድረስ የሚጠቀሙበት በጎ እሴታቸው ነው። በፍቅር የሚማግ ንጹህ አየር እና ኩልል ያሉ ምንጮች፣ ፏፏቴዎችና ክረምት ከበጋ የማይደርቁ ወንዞች ሕያው ምስክርና ሌላው የአካባቢው ድምቀቶች ናቸው። የቤንች ሸኮ ዞን ለምለም የተፈጥሮ ደን፤ ደን ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ ምንጭም ጭምር ነው። መኖሪያ ቤቶችን የከበቡ ዛፎች የማንጎ፣ የብርቱካን፣ የፓፓያ፣ የአቮካዶ፣ የሙዝ፣ የእንሰት አሊያም ሌላ ለምግብነት የሚውሉ ናቸው።   እምቅ የሆነው የተፈጥሮ ደን ደግሞ በውስጡ ቡና፣ ኮረሪማ፣ ጥምዝ እና ሌሎችንም ቅመማ ቅመሞችን ያቀፈ ነው። ይህ እምቅ የኢኮኖሚ አቅም ለአካባቢው ማኅበረሰብ አለኝታም ሆኑ እያገለገለ ይገኛል። ለዚህም የአካባቢው ነዋሪዎች ብዙ ጊዜ "ደን ሕይወታችን ነው" ሲሉ ይደመጣሉ። አዎ ደን ሕይወት ነው፣ ደን እስትንፋስ ነው፣ ደን ምግብና ውሃም ጭምር ነው። ትናንት የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የተከናወነበት የሸኮ ወረዳ "አሞራ ገደል" የተባለ ድንቅ ተፈጥሯዊ ገጽታ አለው። አሞራ ገደል ጥቅጥቅ ባሉ ዕድሜ ጠገብ ዛፎች ከመከበቡ ባሻገር ከስር ወንዝ እያለፈ ከላይ ተሽከርካሪ የሚያልፍበትን በተለምዶ "የእግዜር ድልድይ" እየተባለ የሚጠራውን ግዙፍ ድልድይንም በውስጡ ይዟል። አረንጓዴ ካባ የደረበው ጋራ ሸንተረሩ ለዓይን የሚማርክ መስህብ ስፍራም ጭምር ነው። የደኑ ጫፍ ከ20 የሚበልጡ ፍል ውሃዎችን በአንድ ሰብስቦ በመያዙ በየእለቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከደዌያቸው ለመፈወስ ሲሉ ወደስፍራው ይመጣሉ።   ታዲያ በዚህ ደን ተከበው የሚኖሩ የአካባቢው አርሶ አደሮች ችግኝ ከመትከል አልቦዘኑም። ባላቸው ከመኩራራት ይልቅ ትርጉም ባለው መልኩ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወኑ ነው። ዛሬም በትጋት ችግኝ እየተከሉ ነው፤ ነገም ይቀጥላሉ። በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከፍራፍሬ ባሻገር የነገን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በማሰብ የቁንዶ በርበሬ ቅመም ለማልማት በማቀድ የግራቪላ ዛፍ ተከላ ላይ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ ነው። ይህ እሳቤ ደን ውስጥ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ የሚያደርጋቸውን ችግኝ እንዲተክሉ እያደረጋቸው ነው። በደኑ ዙሪያ ያሉ ገላጣ ሜዳዎች በችግኝ እየተሞሉ ነው። የአርሶ አደሩ ማሳም በፍራፍሬ ተንበሽብሿል። በተለይ አካባቢው ለፍራፍሬ ምርት ያለው ተስማሚነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ ስለሚያደርጋቸው በራሳቸው በቅለው በማደግ ላይ ያሉ የደን ዛፎችን አንስተው በፍራፍሬ ይተካሉ። ይህ ወቅቱ የሚጠይቀው ብልህነት የተሞላበት የልማት አርበኝነት ነው፤ የአካባቢውን ስነ ምህዳር እየጠበቁ በኢኮኖሚ የመበልጸግ ትልም ያለው ጉዞ ማሳያም ነው። በዚህም የቤንች ሸኮ ዞን ባለፉት ዓመታት በተተከሉ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ሥራ በፍራፍሬ ዘርፍ ሰፊ ውጤት ከተመዘገበባቸው የክልሉ አካባቢዎች የሚጠቀስ ነው። ለአብነትም በደቡብ ቤንች ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የጃንቹ ተራራ "የአረንጓዴ አሻራ ልማት ያከበረው ተራራ" መሆን ችሏል።   ስፍራው ምንም እንኳ ፍጹም ገላጣ ባይሆንም ለእርሻ ሥራ የማይመች በመሆኑን ለዘመናት ጾሙን አድሯል። የአረንጓዴ አሻራ ልማት ከተጀመረ ወዲህ ሙሉ በመሉ የሙዝ ችግኝ ተተክሎበት ዛሬ ላይ የሙዝ ፍሬ የሚሰበሰብበት የኢኮኖሚ ማዕከል ሆኗል ማለት ይቻላል። ይህ ተሞክሮም የበርካቶችን ወኔ ቀስቅሶ በአረንጓዴ አሻራ ልማት ሥራ ላይ በራስ ተነሳሽነት እንዲዘምቱ ምክንያት ሆኗል። ክረምትን ብቻ ሳይጠብቁ የበልግ ወራትንም መደበኛ የችግኝ ተከላ ወቅት አድርገው ቡናን ጨምሮ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ችግኞችን አርሶ አደሮቹ በማሳቸው በስፋት ይተክላሉ። በቤንች ሸኮ ዞን በደን ውስጥ ያረፈ አረንጓዴ አሻራ ዛሬ ምግብ ነው፤ ገንዘብም ነው። የዛሬ ሦስት ዓመት በዚሁ የአረንጓዴ አሻራ ያለሙት የሙዝ ችግኝ ለፍሬ መድረሱን ከተናገሩ አርሶ አደሮች መካከል የሸኮ ወረዳ ነዋሪው ሁሴን እንድሮ ተጠቃሽ ናቸው።   ሙዝ ብቻ ሳይሆን የተከሉት የግራቪላ ችግኞች አድገው ከሥራቸው የተተከለው የቁንዶ በርበሬ ቅመም ተስፋ ሰጪ ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል። ከሁለት ዓመታት ወዲህ በአካባቢው የፍራፍሬ ምርት መጨመሩን የተናገሩት ደግሞ ወይዘሮ ምሳዬ መሐመድ ናቸው። ዋጋውም የተረጋጋ፣ አቅርቦቱም ከፍ ያለ መሆኑን አንስተዋል። ለዚህ ደግሞ የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ትልቅ ሚና እንደተጫወተ ነው የገለጹት። ይህን መነሻ ሆኗቸው እርሳቸውም ችግኝ በመትከል አሻራቸውን በማሳረፍ ላይ ናቸው። የቤንች ሸኮ ዞን ደን፣ አካባቢ ጥበቃና ኅብረት ሥራ መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ጉብላ እንደሚሉት በዞኑ ችግኝ የሚተከለው ገላጣ ቦታዎችን በመፈለግ ብቻ ሳይሆን ከጥቅጥቅ ደኖች ውጭ ያሉ የባህር ዛፍና ተጨማሪ ጥቅም የሌላቸውን ዛፎች በማንሳት ጭምር ነው። ለአብነትም የባህር ዛፍ ደንን አንስተው በቦታው የተተከለው ሙዝ የአፈር ለምነትን ከመጠበቅ ባሻገር ፍሬ በመስጠት የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና እያረጋገጠ ነው። በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ30 ሚሊዮን በላይ የፍራፍሬ ችግኞችን በመትከል የማሳ ሽፋኑን ለማሳደግ ታልሞ እየተሠራ መሆኑንም ጠቅሰዋል። አቶ መስፍን እንዳሉት ከአምስት ዓመታት በፊት በዞኑ የነበረው 29 ሺህ ሄክታር የፍራፍሬ ማሳ ዛሬ ላይ ወደ 100 ሺህ ሄክታር ማሳ አድጓል። ይህም በየቀኑ በርካታ ተሽከርካሪዎች ከዞኑ ወደ ማዕከላዊ ገበያ የፍራፍሬ ምርት ጭነው እንዲወጡ እያስቻለ ነው። በዚህም ተጨባጭ ውጤት የአርሶ አደሩ ኑሮ እና የዞኑ ኢኮኖሚ እያደገ መምጣቱን አቶ መስፍን ይገልጻሉ።   የቤንች ሸኮዎችን ተሞክሮ ያነሳንበት ዋና ዓላማ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከአካባቢ ጥበቃ እና ደን ልማት ያለፈ አንድምታ እንዳለው ለማሳየት ነው። ደን አለን ብለው በመኩራራት ያልተቀመጡ የቤንች ሸኮ እጆች ዛሬ የልማት ትሩፋታቸውን እየለቀሙ ነው። በመትከል መመገብ፣ በመትከል ሀብትን ማካበት፣ በመትከል ከድኅነት ወደ ራስን መቻል ማንሠራራት እንደሚቻል የእነሱ ልምድ ለብዙዎች ተሞክሮ ይሆናል። ሰላም!
ለለውጥና ስኬት የሚታትሩ እጆች
Jul 28, 2025 218
(በማሙሽ ጋረደው) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ የሚኖረው ወጣት ሀብታሙ ደስታ፤ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አጠናቆ ወደ ከፍተኛ ትምህርት በመግባት የመጀመሪያ ዲግሪውን በቢዝነስ ማኔጅመንት ተመርቋል። ሀብታሙ ከተመረቀበት ሙያ ባሻገር በአካባቢው መልካም እድሎችን በማጥናት ሰርቶ ለመለወጥና አግኝቶ ለማደግ ወሰነ። በዚህም መሰረት የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ከሚያመርት አንድ የግል ድርጅት ውስጥ በመቀጠር ስራ ጀመረ። በድርጅቱ ውስጥ እየሰራ እና የሙያ ክህሎቱን እያሳደገ በሙያው የላቀ ብቃት እያካበተ መምጣቱን ያስታውሳል። በዚህም መሰረት ከሰባት ዓመት በፊት ከጓደኞቹ ጋር በመደራጀት በ70 ሺህ ብር መነሻ ካፒታል በተመሳሳይ የእንጨት ስራ ጀመረ። በ70 ሺህ ብር የተጀመረው ስራም አሁን ላይ ካፒታሉ 10 ሚሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን ከ40 ለሚልቁ ወጣቶችም የስራ እድል የፈጠረ ሆኗል። በሀገራችን የተለያዩ እድሎችና የስራ አማራጮች አሉ የሚለው ሀብታሙ፤ አንዳንዶች ስደትን የመጨረሻ አማራጭ ከማድረግ ይልቅ በየአካባቢያቸው ሰርቶ የመለወጥ እድል መኖሩን ማየት አለባቸው ሲል ተናግሯል። በአካባቢው ሰርቶ መለወጥ የሚያስችሉ በርካታ ዕድሎች መኖራቸውን አንስቶ እርሱ የተሰማራበት የእንጨት ስራ ሁነኛ ማሳያ መሆኑንም ጠቅሷል። የሀብታሙ ለለውጥና ስኬት የሚታትሩ እጆች ዛሬ ላይ ከራሱ አልፎ ለሌሎች የስራ ዕድል መፍጠር አስችለዋል። ለመለወጥ ቁርጠኝነትና ጠንክሮ መስራት የግድ መሆኑን የሚናገረው ወጣቱ ተስፈኛ "ያለጥረት የሚገኝ ስኬት የለም" ሲልም ተናግሯል። የሚያመርቷቸው የቤትና የቢሮ ዕቃዎች በብዙዎች ዘንድ ተፈላጊ መሆናቸውን አንስቶ የራሱ እና የጓደኞቹ እንዲሁም የሌሎች የኑሮ ሁኔታ እየተቀየረ መሆኑን ገልጿል። በተለይም ወጣቶች በአካባቢያችን ያሉንን በርካታ አማራጮች ለይተን የማየትና የመጠቀም ውስንነቶቻችንን ማረም ከቻልን ከራሳችን አልፈን ለሌሎች መትረፍ የምንችልበት ምህዳር ተፈጥሯል፡፡'' ብሏል። በከምባታ ዞን አዲሎ ዙሪያ ወረዳ ጆሬ ቀበሌ የሚኖሩት ሞዴል አርሶ አደር ሰለሞን ወልዴ፤ የጤና እክል ገጥሟቸውም ቢሆን እየታገሉ ከመስራትና ማምረት አልቦዘኑም። የህይወት መንገድ ብዙ ውጣ ውረድ የሚጠይቅ በመሆኑ ባለመስነፍና ተስፋ ባለመቁረጥ መስራት ይገባል የሚል እምነት አላቸው። በመሆኑም የእርሻ ስራ እና የዶሮ እርባታን ጭምር በማቀናጀት ከራሳቸውና ቤተሰባቸው የምግብ ዋስትና አልፈው ለሌሎችም የሚተርፍ ስራ እያከናወኑ ይገኛሉ። በመሆኑም በተለይ እምቅ ችሎታና ያልደከመ ጉልበት ያላቸው በመሆኑ በተለያዩ የልማት መስኮች መልፋት፣ መስራትና ውጤት ማምጣት እንዳለባቸው ይመክራሉ። የኢትዮጵያ አየር ለመኖር የተመቸ፤ ለማምረት ተስማሚ በመሆኑ እድሉን ተጠቅሞ በቀላሉ ማደግና መለወጥ የሚቻል መሆኑን አንስተዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሙስጠፋ ኢሳ፤ በክልሉ ያለውን እምቅ ኃብት በማልማትና በማምረት ከተረጂነት ወደ አምራችነት ለመሸጋገር ሰፊ ጥረት እየተደረገ ስለመሆኑ ተናግረዋል።በመሆኑም በተለይም ወጣቶች የመስራትና የፈጠራ ችሎታቸውን ተጠቅመው የሀገር ልማትና እድገት መሪ ተሰላፊ እንዲሆኑ ጠይቀዋል። በክልሉ የስራ ዕድል የፈጠሩና የውጭ ምንዛሪ ወጪን የቀነሱ ኢንተርፕራይዞች መፈጠራቸውን አንስተው በመንግስት የብድር አቅርቦት፣ የግንዛቤና የህይወት ክህሎት ስልጠናን በመስጠት እገዛ የሚደረግ መሆኑንም አረጋግጠዋል። በክልሉ በ2017 በጀት ዓመት በግብርናና በኢንዱስትሪ ዘርፍ ብቻ ከ370 ሺህ ለሚልቁ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን አስታውሰው በተያዘው በጀት ዓመት ደግሞ ለ400 ሺህ ሰዎች ስራ ለመፍጠር ታቅዷል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም