ታንዛንያ የምድብ መሪነቷን ያጠናከረችበት ድል አስመዘገበች


አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2017(ኢዜአ)፦ በስምንተኛው የአፍሪካ አገራት ሻምፒዮና(ቻን) የምድብ ሁለት መርሃ ግብር ታንዛንያ ሞሪታኒያን 1 ለ 0 አሸንፋለች።

ማምሻውን በቤንጃሚን ምካፓ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ተከላካዩ ሾማሪ ካፖምቤ በ89ኛው ደቂቃ የአሸናፊነቷን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ታንዛንያ በተጋጣሚዋ ላይ ብልጫ ወስዳ ተጫውታለች።

ውጤቱን ተከትሎ ታንዛንያ ነጥቧን ወደ ስድስት ከፍ በማድረግ የምድብ መሪነቷን አጠናክራለች። ሞሪታኒያ በአንድ ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዛለች።

በዚሁ ምድብ ቀን ላይ በተደረገ ጨዋታ ቡርኪናፋሶ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክን 4 ለ 2 አሸንፋለች።

በኬንያ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛንያ ጣምራ አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የቻን ውድድር ዛሬ አምስተኛ ቀኑን ይዟል።

ቻን በሀገር ውስጥ ሊግ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበት ውድድር ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም