ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በዓለም የንግድ ድርጅት የአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልዕክተኛ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 28/2017(ኢዜአ)፦ ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በዓለም የንግድ ድርጅት(ጄኔቫ) የአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልዕክተኛ ሆነው መሾማቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ለዚህ ቁልፍ ቦታ መምረጣቸውን ኢትዮጵያ እንደምታደንቅ ያስታወቀው ሚኒስቴሩ ይህም ህብረቱ ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ አፍሪካን በመወከል እየተወጣች ላለው ሚና የሰጠውን ትልቅ ዋጋ የሚያሳይ ነው ብሏል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ባላቸው የካበተ የአመራርነት ልምድ የተሰጣቸውን አዲስ ኃላፊነት በብቃት እንደሚወጡ ሙሉ እምነቱን ገልጿል።

ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) የኢፌዴሪ ግብርና ሚኒስቴርን ጨምሮ በተለያዩ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ መስራታቸውን በመግለጫው ተጠቅሷል

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም