የአረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት ያለውን አጋርነት እንደሚያጠናክር ገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
የአረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት ያለውን አጋርነት እንደሚያጠናክር ገለጸ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 19/ 2017 (ኢዜአ)፦ የአረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት (BADEA) ለአፍሪካ የልማት ስራዎች የሚያደርገውን ድጋፍና አጋርነት እንደሚቀጥል አስታወቀ።
የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሴኤ) ዋና ፀሐፊ ክላቨር ጋቴቴ ከአረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት (BADEA) ፕሬዝዳንት አብደላ አልሙሳይቤህ ጋር ተወያይተዋል።
ዋና ፀሐፊው ኢሴኤ እና የአረብ ባንክ ለረጅም ጊዜ የቆየ ወዳጅነት እንዳለው ገልጸው ይህን አጋርነቱን የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰራም ተናግረዋል።
በውይይቱ ላይ ባንኩ በአፍሪካ ልማት የሚያደርገውን ኢንቨስትመንት የማጠናከር ፍላጎት እንዳለው መገለጹን ኢዜአ ከኮሚሽኑ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የአረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት ፕሬዝዳንት አብደላ አልሙሳይቤህ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት እያደረጉ መሆኑም ይታወቃል።