ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
የአፍሪካ የለውጥ ብርሃን፤ የላቀ የዲፕሎማሲ ማዕከል- አዲስ አበባ 
Nov 2, 2026 30
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ የለውጥ ብርሃን፤ የላቀ የዲፕሎማሲ ማዕከል- አዲስ አበባ በሚፍታ ሽፈራ ከተማ የሰዎች የኑሮ ማዕከል፣ የታሪክና የባህል መገለጫ፣ የማኅበራዊ ግንኙነትና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መድረክ ነው። የከተማ ልማትም የሚለካው በነዋሪዎች የኑሮ ጥራት፣ በሚፈጥረው የኢኮኖሚ ዕድል፣ በሚጠብቀው ታሪካዊ ማንነትና በሚያጠናክረው ማኅበራዊ ትስስር ጭምር ነው። ይህንን እውነታ በተግባር እያሳዩ ካሉ ጥቂት የዓለም ከተሞች መካከል አዲስ አበባ አንዷ ናት። በቀደሙት ዓመታት አዲስ አበባ ከስሟ፣ ከታሪካዊ ክብሯና ከነዋሪዎቿ የኑሮ ፍላጎት ጋር የማይጣጣሙ በርካታ ችግሮች ይታዩባት ነበር። የአካባቢ ብክለት፣ የአረንጓዴ ስፍራ እጥረት፣ የወንዝ ዳርቻዎች መበከልና የመንገድ መጨናነቅ ከሚጠቀሱት ችግሮች መካከል ነበሩ። ከለውጡ በኋላ በገበታ ለሸገር የተጀመረውና በኋላም ወደ ገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ የተስፋፋው የልማት አቅጣጫ የከተማዋን ገጽታ ለመቀየር አዲስ መነሳሳት ፈጥሯል። የዚህ ለውጥ መሠረት ከመደመር እሳቤ ጋር ይገናኛል። መደመር የተለያዩ ሀብቶችን፣ አቅሞችን፣ ባህሎችንና ፍላጎቶችን በማቀናጀት ለጋራ ጥቅም ማዋል ነው። በዚህ እሳቤ ልማት የሰውን ክብር የሚያስጠብቅ፣ ሁሉንም የሚያሳትፍና ለጋራ ተጠቃሚነት የሚያበቃ ነው። በዚህ አቅጣጫ ከተከናወኑት የልማት ሥራዎች መካከል የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች ይጠቀሳሉ። የኮሪደር ልማት መንገዶችን ከማስፋትና ከማስዋብ ባለፈ፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶችን፣ የአረንጓዴ ስፍራዎችን፣ የመዝናኛ ማዕከላትንና የንግድ ቦታዎችን በአንድ ላይ ማቀናጀት የቻለ ነው ። ይህም የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የነዋሪዎችን፣የንግድ እንቅስቃሴና የማኅበራዊ ተግባቦት ዕድል አሳድጓል። በተመሳሳይ የወንዝ ዳርቻ ልማት የተፈጥሮ ሀብትን ከሕዝብ ጥቅም ጋር የሚያቀናጅ ግዙፍ የልማት ሥራ ነው። የተበከሉና በተለያዩ ችግሮች የተጎዱ የወንዝ ዳርቻዎችን ወደ አረንጓዴ መዝናኛ ስፍራዎች፣ የስፖርት ማዕከላት፣ የንግድና የቱሪዝም መዳረሻዎች የመቀየር ጥረት የአካባቢ ጥበቃንና የማኅበራዊ ጥቅምን አብሮ አስተሳስሯል። መዲናዋን እየቀየሩ ያሉ ሁለገብ የልማት ሥራዎች የመደመር የእይታ አድማስ በተግባር ያሳዩ ናቸው። የተለያየ አቅም፣ እውቀትና ሀብት በማቀናጀት የተከናወኑት እነዚህ ሥራዎች፤ የከተማዋን ነባር ባህላዊና ታሪካዊ እሴቶች ከዘመናዊ ግንባታ ጋር በማስማማት ዘላቂ የልማት ውጤት እንዲመዘገብ አስችለዋል። የዘመናዊ መሠረተ ልማቶች መዘርጋት፣ የትራፊክና የመንገድ መጨናነቅ መቃለል እንዲሁም የዲጂታልና የተቀናጁ አገልግሎቶች መስፋፋት የነዋሪዎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴና የኑሮ ዘይቤ ፈጣንና ቀልጣፋ አድርጎታል። የተዋቡ አረንጓዴ ስፍራዎች፣ የወንዝ ዳርቻ መዝናኛዎች፣ እና የታደሱ ታሪካዊ ቅርሶች አዲስ አበባን ዓለም አቀፍ ተደራሽነት ያላቸው የኮንፈረንስና የዕረፍት ጊዜ መዳረሻዎች አድርገዋታል። ይህም የቱሪዝም ፍሰቱን በእጅጉ በማሳደግ ለከተማዋ ኢኮኖሚ እጅግ አበረታች ፋይዳ እያስገኘ ይገኛል። አዲስ አበባ የብዙ ብሔር፣ ቋንቋ፣ ባህልና እምነት መገናኛ ናት። የከተማ ልማት ይህንን ብዝሃነት የሚያከብር፣ የተለያዩ ማኅበረሰቦችን የሚያገናኝና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያጠናክር በመሆኑ፤ መዲናዋ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በጋራ የሚገናኙባቸው ደማቅ መድረክ ሆናለች። የእነዚህ ሁሉ የልማት ጥረቶች ተጨባጭ ውጤት በዓለም አቀፍ መድረክም ታላቅ ዕውቅና እያገኘ ነው። አዲስ አበባ የዘንድሮውን የ2026 የዓለም ከተሞች ቀን “የሸንሃይ አዋርድ” (Shanghai Award) ሽልማት ማሸነፍ መቻሏ፤ በመዲናዋ የተተገበረው የሰው ተኮር ልማት እይታ፣ የአካባቢ ጥበቃ ጥረት እና የነዋሪዎች የኑሮ ጥራት መሻሻል ምን ያህል የላቀ ደረጃ ላይ እንደደረሰ የሚያረጋግጥ ትልቅ ታሪካዊ ማሳያ ነው። ይህ ሽልማት የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ይበልጥ እንዲቀጥሉ፣ አካታችነት እንዲጠናከር እና የነዋሪዎች ሁለገብ ተጠቃሚነት በዘላቂነት እንዲረጋገጥ የሚያደርግ ነው። አዲስ አበባ የተያያዘችው ሁለገብ የልማት እንቅስቃሴ የመላው አፍሪካ መዲናነቷን ክብር በላቀ ደረጃ የሚያጸና ነው። ይህም የአፍሪካውያንን ታሪካዊ ኩራት ከማደስ ባለፈ መዲናዋ የአህጉሪቱ የእድገትና የለውጥ ተምሳሌት ሆና እንድትቀጥል አስችሏታል። ይህ ፈጠራ የታከለበትና አካታች የልማት ጉዞ መዲናዋ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተጽዕኖ ፈጣሪነትና የከበረ የዲፕሎማቲክ ማዕከልነት ድርሻ በጽኑ መሠረት ላይ የጣለ ነው።
የኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ልማት ስኬቶች ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አርዓያ የሚሆኑ ናቸው
Nov 2, 2026 67
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ልማት ስኬቶች እና የምትከተላቸው አቅጣጫዎች ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አርዓያ የሚሆኑ ናቸው ሲሉ በኢትዮጵያ የዴንማርክ ኤምባሲ የኢነርጂ ዘርፍ አማካሪ ቶማስ ፍሉሪን ሶረንሰን ገለጹ። በኢትዮጵያ የዴንማርክ ኤምባሲ አማካሪ ቶማስ ፍሉሪን ሶረንሰን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ልማት የምትከተለው አቅጣጫ ትክክለኛ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በኃይል ልማት የምትወስዳቸው ውሳኔዎች ለሌሎች ሀገራት ማበረታቻ እንደሚሆኑ ገልፀው፣ በዘርፉ ያለው ዕድገት ለአፍሪካ ሀገራት ተሞክሮ እንደሚሆን አመልክተዋል። ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ምርት ጥሩ እድገት እያሳየች መሆኑን ጠቁመው፤ በዘርፉ የተያዙት እቅዶችና የልማት አቅጣጫዎች ጠንካራ መሆናቸውን አመልክተዋል። ዴንማርክ ከኢትዮጵያ ጋር በውሃና ኢነርጂ ዘርፎች የረጅም ጊዜ ጠንካራ ትብብር እንዳላትም ገልጸዋል። ትብብሩ የተቋማዊ አቅም ግንባታን፣ በተመሳሳይ ዘርፍ በሚሠሩ ተቋማት መካከል የልምድ ልውውጥንና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ያካተተ መሆኑን ጠቁመዋል። የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትም የሁለቱ ሀገራት ትብብር ማሳያ መሆኑን ጠቅሰው፤ ዴንማርክ በውሃና ኢነርጂ ዘርፎች የኢትዮጵያ ጠንካራ አጋር መሆኗን አስረድተዋል። በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ትብብር የግሉን ዘርፍ በማካተት የበለጠ ሊጠናከር እንደሚችልና ይህም ለሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች ጥቅም እንደሚያስገኝ አመልክተዋል። ዴንማርክ ኢትዮጵያ በኃይል ልማት ላይ ለምታከናውናቸው ተግባራት ድጋፏን እንደምታጠናከር ተናግረዋል።
በክልሉ ከ43 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የመስኖ ተቋማት ግንባታ ተጠናክሮ ቀጥሏል
Nov 2, 2026 57
ባህር ዳር ፤ ጥቅምት 23/2019(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ከ43 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 129 የሚሆኑ የነባርና አዳዲስ መስኖ ተቋማት ግንባታ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ። የመስኖ ልማቱ የገጸና ከርሰ ምድር ውሃን በአግባቡ በመጠቀም በመኸር ወቅት ከሚገኘው ሰብል ተጨማሪ ምርት ለማግኘት አስችሏል። በዚህም ስንዴን ጨምሮ ሌሎች ሰብሎችን፣ አትክልትና መሰል አዝርዕትን በብዛት በማምረት በምግብ እህል አቅርቦት ራስን ለመቻል በሚያስችል አግባብ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። በክልሉ ግብርና ቢሮ የመስኖ ድሬይኔጅ ግንባታና ክትትል ዳይሬክተር አቶ ጌትነት አያሌው ለኢዜአ እንደገለፁት፤ በመስኖ ልማት ለኢንዱስትሪዎች ግብዓትም ሆነ ለገበያ የሚሆን ምርት እየተመረተ ነው።   ባለፉት ዓመታት ዘመናዊ የመስኖ አውታሮችን በማስፋፋት በተሠራ ሥራም አርሶ አደሩ በተደራጀ አግባብ ወደ ልማቱ እንዲገባ መደረጉን ገልጸዋል። ይህንን አጠናክሮ ለማስቀጠልም በዚህ በጀት ዓመት 129 የሚደርሱ ነባርና አዳዲስ የመስኖ ተቋማትን ግንባታ ለማከናወን የሚያስችል ዝግጅት በማጠናቀቅ ወደ ሥራ መገባቱን አስታውቀዋል። የመስኖ ተቋማቱ 21 ሺህ ሄክታር መሬት የማልማት አቅም ያላቸው ሲሆን፣ ከ43 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን የልማቱ ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሆናቸውንም ተናግረዋል። ከእነዚህ አነስተኛና መካከለኛ ተቋማት መካከልም 65 የሚሆኑትን በዚህ ዓመት አጠናቆ ወደ ልማት ለማስገባት ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል። ለመስኖ ተቋማቱ ግንባታ 5 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዞ ወደ ሥራ መገባቱን ጠቅሰው፣ ማኅበረሰቡም ወሰን በማስከበር፣ በጉልበቱ፣ የግንባታ ቁሳቁስ በማቅረብና በገንዘቡ እያገዘ መሆኑን ተናግረዋል።   የዘመናዊ መስኖ ተቋማት ግንባታ ክልሉን በዘላቂነት ከዝናብ ጥገኝነት ከማላቀቅ ባለፈ፣ በምግብ ራስን ለመቻል የተያዘውን ግብ ለማሳካት በሚያስችል አግባብ በመንግሥት በኩል በትኩረት እየተከናወነ እንደሚገኝም አብራርተዋል። ባለፈው ዓመት 51 የመስኖ ተቋማትን በመገንባት ከ5 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘመናዊ መስኖ ማልማት መቻሉን ገልጸዋል። በክልሉ ከ2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ የመልማት አቅም እንዳለ አንስተው፣ ይህንኑ ወደ ልማት ለማስገባትም የዲዛይንና የጥናት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ጨምረው አስረድተዋል።
በክልሉ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚወሰዱ እርምጃዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ-አቶ ሃይሉ አዱኛ
Nov 2, 2026 72
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 23/2019(ኢዜአ)፦የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚወስዳቸውን እርምጃዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ ገለጹ። አቶ ሃይሉ በደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን፣በሽርካ ወረዳ፣በብርቦ ጮሌ ቀበሌ የተፈጸመውን የጽምዶ ቡድን ጥቃት አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፣መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥና የተጎዳውን ማኅበረሰብ መልሶ ለማቋቋም የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል። ሕዝቡ ያስመዘገባቸውን ድሎች በመጠበቅና በአንድነት ወደ ፊት መራመድ እንዳለበት ገልፀው፣ጥቃቱን የፈፀሙ እነዚህ ኃይሎች አዲስ የተጀመረውን የልማትና የለውጥ ሂደት ለማደናቀፍ በሽብር ተግባር በመሰማራት ራሳቸውን መከላከል በማይችሉ ንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል ብለዋል። በ2019 ዓ.ም.ጥቅምት 14 ቀን በሽርካ ወረዳ፣ በብርቦ ጮሌ ቀበሌ በተፈጸመው ጥቃት የንጹሐን ዜጎች ሕይወት መጥፋቱ፣የመንግሥትና የሕዝብ ንብረት መቃጠሉ፣እንዲሁም ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቤቶቻቸውና ከንብረቶቻቸው መፈናቀላቸው ተገልጿል። ጥቃቱን ተከትሎ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በተካሄዱ የጸጥታ ሥራዎች 73 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለው በምርመራ ላይ መሆናቸውን፣ እንዲሁም እነዚህ ኃይሎች እንቅስቃሴ የሚያደርጉባቸው የነበሩ ስድስት ቀበሌዎች ጸጥታቸው መረጋገጡን ገልጸዋል። መንግሥት በአንድ በኩል የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እርምጃ እየወሰደ፣ በሌላ በኩል ከመኖሪያ ቤቶቻቸውና ከንብረቶቻቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሰብዓዊ፣የምግብና የሕክምና ድጋፍ እያቀረበ መሆኑ ተገልጿል። በተጨማሪም ተፈናቃይ ዜጎችን ወደ መኖሪያ ቤቶቻቸውና ንብረቶቻቸው ለመመለስ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን መግለጫው ያመለክታል።
ባሮ - የጋምቤላ የውበት አክሊል!
Nov 2, 2026 53
ጋምቤላ ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ)፦ባሮ - የጋምቤላ የውበት አክሊል! በሙሉጌታ ዳምጤ (ኢዜአ-ጋምቤላ) ከኢትዮጵያ ከፍታማ ቦታዎች በመነሳት የጋምቤላ ከተማን መሀል ለመሀል አቆራርጦ ወደ ደቡብ ሱዳን በመሻገር የሶባት ወንዝ ተብሎ ከነጭ ዓባይ ጋር በመቀላቀል የመጨረሻ መዳረሻውን ሜድትራኒያን ያደርጋል። የባሮ ወንዝ የጋምቤላ ክልል ወሰን አካባቢ ሲደርስ ገባ እና ብርብራ በሚል የሚጠሩ ወንዞችን ጨምሮ ጉዞውን ወደ ሩቅ መዳረሻው ያደርጋል። የባሮ ወንዝ የብርብር እና የገባ ወንዞች ሲቀላቀሉት የውሃው ቀለም ቀላ ስለሚል ወንዞቹ የሚገናኙበት ቦታ "ባሮ ቀላ" የሚል ስያሜ አግኝቷል፤ ሀገር አቋራጩ የባሮ ወንዝ 306 ኪሎ ሜትር (190 ማይል) ርዝመት ይጓዛል። የጋምቤላ ክልልን የተፈጥሮ ውበት ከሰው ሕይወት፣ ከኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴና ከባህላዊ እሴቶች ጋር አስተሳስረው ከሚያቆዩ ታላላቅ የተፈጥሮ ሀብቶች መካከል የባሮ ወንዝ አንዱ ነው። ከነ ግርማ ሞገሱ የጋምቤላ ከተማን አቆራርጦ ሲያልፍ ለከተማዋ ድምቀት ነው ማለት ይቻላል። ባሮ በኢትዮጵያ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ብቸኛው ወንዝ ነው። የተፈጥሮ ውበት፣ የኢኮኖሚ አቅምና የሕዝብ ኑሮ ተሳስረው የሚታዩበት ታላቅ የሀገር ሃብትም እንደሆነ ይነገርለታል -ባሮ ወንዝ። የባሮ ወንዝ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1907 ዓ.ም ጀምሮ ወደብና የጉምሩክ ጣቢያ ተቋቁሞለት ከጋምቤላ ከተማ ወደ ወረዳዎችና ሱዳን ጠረፍ የውሃ የትራንስፓርት አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። በአሁኑ ወቅትም በዘመናዊ መልኩ ባይሆንም ወንዙ ወደሚያቋርጥባቸው ወረዳዎችና ደቡብ ሱዳን ጠረፍ ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። በአካባቢው ነዋሪዎች "ኦፔኞ" እየተባለ የሚጠራው ባሮ የጋምቤላ ተፈጥሯዊ መለያም፤ መድመቂያም ነው። የወንዙ ፍሰት፣ በወንዙ ዳርቻ የሚታየው አረንጓዴ ተፈጥሮና ከውኃው ጋር የተቆራኘው የነዋሪዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ሌላኛው ገጽታው ነው። በሞቃታማ የአየር ጸባይ ወቅት በወንዙ ዳርቻ ያሉ እጽዋቶች ብቻ ሳይሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎችም ሙቀቱን ለማስታገስ ወንዙን ስለሚጠቀሙበት አለኝታና ታዛቸው ነው ማለት ይቻላል። በባሮ ወንዝ ቁጥራቸው ከ51 እስከ 57 የሚደረሱ የዓሣ ዝርያዎች አሉ። በተለይም "ናይል ፐርች" በአካባቢው አጠራር "ጉር" የሚባለው ግዙፍ የዓሣ ዝርያ እስከ 100 ኪሎ ግራም ይመዝናል። እንዲሁም "ታይገር" ፣ "ስታር" ፣ "ካት" እና "ቀረሶና" የተባሉና ሌሎች የዓሣ ዝርያዎች በውስጡ የሚገኙ ሲሆን የአዞ እና ሌሎች የብዝሃ ሕይወት ሀብቶችም መኖሪያ ነው። በወንዙ ዙሪያ ያሉ የንግድ እንቅስቃሴዎች እና ከውኃው ጋር የተያያዙ ሌሎች ሥራዎች ለበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች የገቢ ምንጭ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ። የባሮ አዞዎች በሥነ-ምህዳሩ ውስጥ የራሳቸው ሚና ቢኖራቸውም ለሰው ሕይወት አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ። ስለሆነም በወንዙ ዳርቻ እንቅስቃሴ ሲደረግ ተገቢ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። በተለይም አዞ እንዳለ በሚታወቅባቸው ስፍራዎች ወደ ውኃው አለመግባትና የአካባቢውን ባለሙያዎች መመሪያ መከተል የግድ ይላል። የባሮ ወንዝ ለግብርና ልማት ሥራም ከፍተኛ አቅም ካላቸው የውኃ ሀብቶች መካከልም አንዱ ነው። በወንዙ ግራና ቀኝ ያለው ለም መሬት ለመስኖ ልማት እጅግ ጠቃሚ ነው። የአርሶ አደሮችን የምርት አቅም ለማሳደግ፣ የምግብ ዋስትናን ለማጠናከርና የገቢ ምንጭን ለማስፋት እያገዘም ነው ። የባሮ ወንዝ የልማት ዕድል ቢኖረውም ከወቅታዊ የውኃ መጠን መጨመር ጋር የተያያዙ ፈተናዎችም አሉት። በከፍተኛ የዝናብ ወቅት የወንዙ ውኃ ሞልቶ ሲፈስ በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎችን ከቄያቸው ያፈናቅላል። አንዳንዴም በወንዙ ዳርቻ የለሙ ሰብሎች ላይ ጉዳት በማድረስ ምርትን በመቀነስ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጫና ሊፈጥር ይችላል፤ ስለሆነም የጎርፍ ስጋትን ለመቀነስ በወንዙ የውኃ መጠን ላይ ክትትል በማድረግ በተጋላጭ አካባቢዎች የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓትን ማጠናከር ያስፈልጋል። እንዲሁም የወንዙን ዳርቻ እፅዋት መጠበቅና በጎርፍ ሊጎዱ በሚችሉ ቦታዎች ላይ የመሬት አጠቃቀምን በተቀናጀ አግባብ የመምራት አቅምን ማጎልበት አስፈላጊ ነው። የባሮ ወንዝ ለቱሪዝም፣ ለወንዝ ዳርቻ መዝናኛና ለአካባቢያዊ ባህል ተኮር ጉብኝቶች የሚያበረክተው አስተዋጽኦም ቀላል አይደለም። ጋምቤላን የሚጎበኙ ቱሪስቶች የአካባቢውን ተፈጥሮ፣ የወንዝ ዳርቻ ሕይወትና የጋምቤላን ባህላዊ እሴቶች በሚገባ ማወቅና መረዳት የሚችሉበት ሁኔታም ሰፊ ነው። ወንዙ የጋምቤላን የተፈጥሮ ውበት ከማሳየት ባለፈ የኑሮ መሠረት፣ የልማት አቅም፣ የቱሪዝም መስህብና የብዝኃ ሕይወት መገኛ ሆኖም እያገለገለ ነው። የባሮ ወንዝ የጋምቤላ የተፈጥሮ ውበት መገለጫ ነው። የሕዝቧ የኑሮ መጋመጃ እና የወደፊት የልማት ተስፋ መገለጫም በመሆኑ ይህን ሀብት በአግባቡ መጠበቅ ከራስ ባለፈ ለመጪው ትውልድ የተፈጥሮ ጸጋን እና የልማት ዕድልን ማስረከብም ይሆናል።
የሚታይ

ወርሃዊ ዜና መጽሔት
Nov 1, 2026 336
የአስተዳደር ጉዳዮች ይህ ወር በታሪካችን ውስጥ ታላቅ ምዕራፍ የተመዘገበበት ነው፤ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ መሠረት አዲሱ የመደመር መንግሥት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ ተመስርቷል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው አንደኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የካቢኔ አባላትን ሹመት በማጽደቅና የመንግሥት ኃላፊነት የላቀ ትጋት የሚጠይቅ መሆኑን በማጉላት ለሁለተኛው የሥራ ዘመናቸው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል። በተያያዘም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያዘጋጀውን የምክክር አጀንዳ ለፌደራል እና ለክልል አካላት በይፋ አስረክበዋል። ይህን ታላቅ ሀገራዊ ስትራቴጂ ከግብ ለማድረስና ሁለንተናዊ ዝግጁነትን ለማጎልበት ከፍተኛ የመንግሥት አመራር አካላት በአካል ብቃት፣ በሥነ-ምግባር እና በዲሲፕሊን የሚያንጽ የወታደራዊ ሳይንስ ሥልጠና በመውሰድ ላይ ይገኛሉ። ማኅበራዊ ጉዳዮች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለመላው ኢትዮጵያውያን የኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፤ በዓሉ ሰላምን፣ የገዳ ሥርዓትን የሥልጣኔ መሠረቶችና የጋራ ብልጽግናን የሚያጎላ መሆኑን ገልጸዋል። “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን!” በሚል መሪ ቃል በተከበረው 19ኛው የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን ላይም ሰንደቅ ዓላማው የሉዓላዊነታችን መገለጫ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። አያይዘውም የዓድዋን ታሪካዊ ቅርስ በማስታወስ ዜጎች ለሀገራዊ አንድነት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። በመጨረሻም በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከኢቢሲ ጋር በትግርኛ ቋንቋ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።   የፕሮጀክት ማስጀመሪያ፣ ጉብኝትና ምርቃት ጥቅምት ወር በሀገራዊ የኢንዱስትሪ፣ የመሠረተ ልማት እና የግብርና አቅም ግንባታ ረገድ ትልቅ እመርታ የታየበት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በዓመት 600 ቶን የማጣራት አቅም ያለውን ብሔራዊ የከበሩ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ መርቀዋል። በተጨማሪም ለሀገሪቱ የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የኢትዮጵያ ሚትሮሎጂ ኢንስቲትዩት የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶችን እና የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽንን ጎብኝተዋል።   በክልሎች እና በከተሞችም የልማት እንቅስቃሴዎች ተፋጥነዋል። በጎንደር 185 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ የመያዝ አቅም ያለውና ከ17 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የሚያለማው የመገጭ መስኖ ግድብ ተመርቋል፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በቆይታቸው የፋሲል ግቢንና የ«መሶብ» ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል። በአዲስ አበባ ደግሞ 351 ሄክታር መሬት ያረፈውና 10 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው የቀጨኔ–አምባሳደር–ጊዮን–ኢሬቻ–ባምቢስ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ተመርቋል።   በተያያዘም የነዳጅ ፍጆታን ለመቀነስ በሀገር ውስጥ ከነዳጅ ወደ የተፈጥሮ ጋዝ (CNG) የተቀየሩ የመጀመሪያዎቹ 26 የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች በይፋ ሥራ ጀምረዋል፤ ይህም የትራንስፖርት ወጪን በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንስና የሕዝብ የጉዞ ታሪፍን በግማሽ ያቃለለ ነው። ዲፕሎማሲ እና የሁለትዮሽ ግንኙነት በዲፕሎማሲው ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን መድረኮች ጠንካራ ተሳትፎ አድርገዋል። የመደመር መንግሥት ምሥረታን ተከትሎ የደቡብ አፍሪካውን ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ እና የናይጄሪያውን ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማን በይፋዊ የሥራ ጉብኝት ተቀብለዋል። በተጨማሪም ከሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንም ጃይሻንካር፣ ከእስራዔሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር ስትራቴጂካዊ ትብብሮችን ለማጠናከር የሚያስችሉ ውጤታማ ውይይቶችን አድርገዋል።   ቀጠናዊ ትስስርን ለማጠናከርም በኬንያው የ«ማሹጃ(የጀግኖች)» ቀን አከባበር ላይ ተገኝተዋል። በባሕር ዳር ከተማ በተካሄደው 12ተኛው የጣና ከፍተኛ የደህንነት ፎረም ከመጀመሩ አስቀድሞ ከኬንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ኪቱሬ ኪንዲኪ እና ከሞዛምቢኩ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ቻፖ ጋር ተወያይተዋል። በፎረሙ የመክፈቻ ንግግራቸውም አፍሪካውያን ሀገራት ውስጣዊ አቅማቸውን እንዲገነቡና በዓለም አቀፍ ሥርዓት ውስጥ አወንታዊ ዐሻራ እንዲያሳርፉ ጥሪ አቅርበዋል።   ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወሩን እንቅስቃሴያቸውን ያጠናቀቁት በሩሲያ ባደረጉት ይፋዊ ጉብኝት ነው። ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በንግድ፣ ጤና እና ኃይል ዙሪያ ተመካክረዋል። በ3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባዔ ላይም ዘመናዊ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ ለመገንባት ከሩሲያ ጋር እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። ከቀድሞ ስምምነቶች አንጻርም ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን አሥራ ሁለት Su-35 ተዋጊ ጄቶች እና አራት የS-400 የአየር መከላከያ ባትሪዎችን ተረክባለች።     በመጨረሻም የጠቅላይ ሚኒስትሩ «መደመር» መጽሐፍ የሩሲያኛ ዕትም በሞስኮ በይፋ መመረቁ የሀገሪቱ የፖለቲካና የአስተዳደር ፍልስፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ተደራሽነት ይበልጥ ያሰፋ ሆኗል። #PMOEthiopia #EthiopiaDelivers  
በመዲናዋ የሚከናወኑ ልማቶች ሰው ተኮር እና የማኅበራዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ናቸው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Nov 1, 2026 253
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 22/2019 (ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ ከተማ የሚከናወኑ ልማቶች ሰው ተኮር እና የነዋሪዎችን ማኅበራዊ ትስስር በማጠናከር ወደ ተሻለ የአኗኗር ዘይቤ የሚያሸጋግሩ መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለልማት ተነሺ አርሶ አደሮች የተገነባውን የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ የመኖሪያ መንደር መርቀው ለተጠቃሚዎች አስተላልፈዋል።   ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት አዲስ አበባን በጋራ፣ በትብብር እና በውጤታማነት እያለማን እንገኛለን ብለዋል። ይህም አዲስ አበባን በዓለም አቀፍ መድረክ እንድትሸለም እያስቻላት መሆኑን ተናግረዋል። እውቅናው የሁሉም ትብብር ውጤት መሆኑን አንስተው፣ የልማት ተነሺዎች ለልማት ተባባሪ መሆናቸው ለዚህ ውጤታማነት አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸዋል። አዲስ አበባን የማልማቱ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ከንቲባዋ፣ ዛሬም ለልማት ለተነሱ አርሶ አደሮች ዘመናዊ የሆነ የመኖሪያ ቤት ተገንብቶ መሰጠቱን ተናግረዋል። ልማት ማለት የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል፣ የኢኮኖሚ አቅሙን ማጠናከርና የነገ ተስፋውን ማለምለም ጭምር ነው ሲሉ ተናግረዋል።   መኖሪያ መንደሩ የነዋሪዎቹን ማኅበራዊ ትስስር በማጠናከር ወደ ተሻለ የአኗኗር ዘይቤ የሚያሸጋግርና ሰው ተኮር የአሠራር አቀራረብን የተከተለ ነው ብለዋል፡፡ ለአርሶ አደሮቹ የኑሮና የገቢ ምንጮቻቸውን የሚያሳድጉበትን ዕድል የሚፈጥሩ በርካታ አቅርቦቶችን ያካተተ መሆኑንም አብራርተዋል። የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አደፍርስ ኮራ በበኩላቸው፣ የተገነባው ቤት ነዋሪዎቹ የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ ለማስቻል ታስቦ በዘመናዊ መንገድ መገንባቱን አስታውቀዋል። የኢኮኖሚና ማህበራዊ አገልግሎቶችን በአንድ ላይ የሚያስተሳስሩ ዘርፈ ብዙ መሠረተ ልማቶች የያዘ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።   በመኖሪያ መንደሩ የቤት ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል ወ/ሮ ዘውድነሽ መስቀላ፣ የተሰጣቸው ቤት ከቀደመው የተሻለ፣ ዘመናዊ እና ውብ በመሆኑ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ኑሯቸውን በአግባቡ ለመምራት የሚያስችሉ መሠረተ ልማቶች እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ አገልግሎቶች በተሟሉበት መንደር በመግባታቸው መደሰታቸውን የገለጹት ደግሞ ሌላኛው የቤት ተጠቃሚ አብራሳ ዱመቻ ናቸው፡፡ በዚህም ለከተማ አስተዳደሩ ምስጋና አቅርበዋል።        
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርናን በማዘመን የተገኙ ውጤቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Nov 1, 2026 236
ሆሳዕና፤ ጥቅምት 22/2019 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርናን በማዘመን የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በተሰሩ ሥራዎች የተገኙ ውጤቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኡስማን ስሩር ገለጹ። በክልሉ ግብርና ቢሮ የምግብ ማጠናከሪያ ፕሮግራም እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን የተመለከተ የመስክ ምልከታና ውይይት አካሂዷል።   በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ስሩር በዚህ ወቅት እንዳሉት በክልሉ ግብርናን በማዘመን የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት ተመዝግቧል። በመደመር መንግሥት በግብርና ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን ይበልጥ በማሳደግ የአርሶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻልና ገበያን ለማረጋጋት በተከናወኑ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤት መገኘቱንም ገልጸዋል። በዚህም በክልሉ ግብርናን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ እሴት ጨምሮ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚነቱን የሚያረጋግጥ ማህበረሰብ እየተፈጠረ መጥቷል ብለዋል።   ለዚህም ባለቤትነታቸው የአርሶ አደር የሆኑ 27 የወተት፣ የማር፣ የእንሰት እና ቅመማ ቅመም ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎችን ወደ ሥራ የማስገባት ሥራ መከናወኑን በማሳያነት ጠቅሰዋል። በቀጣይም እነዚህን ውጤቶች አጠናክሮ ለማስቀጠል ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል። በቢሮው የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ማናጀር አቶ ከድር መሀመድ በበኩላቸው፣ ፕሮግራሙ የግብርና ቴክኖሎጂን ተግባራዊ በማድረግ ምርትና ምርታማነትን የማሳደግ ዋና ዓላማ እንዳለው ገልጸዋል። በበጀት ዓመቱም በክልሉ ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን በግብርናው ዘርፍ በመደገፍ ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ ግብ ተይዞ እየተሰራ መሆኑንም አመልክተዋል። በምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ሌራ ከተማ ነዋሪ አርሶ አደር ከማል ሀሰን፣ በተያዘው በጀት ዓመት በማር ማቀነባበር ሥራ በኢንተፕራይዝ ተደራጅተው ወደ ሥራ መግባታቸውን ተናግረዋል። በተሰማሩበት ዘርፍ ውጤታማ እንዲሆኑ በመንግሥት ምቹ ሁኔታ እንደተፈጠረላቸው ገልጸዋል። ከመደበኛ የግብርና ሥራቸው ጎን ለጎን ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኙ በመንግስት የተፈጠረላቸው ዕድል ነገን በተሻለ ተስፋ አሻግረው እንዲያዩ ያደረጋቸው መሆኑን ተናግረዋል። በመንግሥት የገንዘብ ብድርና የመስሪያ ቦታ ተመቻችቶላቸው በንብ ማነብ ዘርፍ በማህበር ተደራጅተው ወደሥራ እንደገቡ የገለጸው ደግሞ በሌራ ከተማ የፍረኮት የንብ ማነብ ማህበር ሰብሳቢ ወጣት ኡስማን መለሰ ነው። የማር ምርታቸውን በወረዳው ለሚገኝ የማር ማቀነባበሪያ ማዕከል በማቅረብ የተሻለ ገቢ እያገኙ መሆናቸውን ገልጾ፣ የመንግስት ድጋፍ ውጤታማ እያደረጋቸው መሆኑን ተናግረዋል። በመስክ ምልከታውና የውይይት መድረክ ላይ ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች፣ አርሶ አደሮች እና የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል።

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
በክልሉ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚወሰዱ እርምጃዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ-አቶ ሃይሉ አዱኛ
Nov 2, 2026 72
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 23/2019(ኢዜአ)፦የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚወስዳቸውን እርምጃዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ ገለጹ። አቶ ሃይሉ በደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን፣በሽርካ ወረዳ፣በብርቦ ጮሌ ቀበሌ የተፈጸመውን የጽምዶ ቡድን ጥቃት አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፣መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥና የተጎዳውን ማኅበረሰብ መልሶ ለማቋቋም የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል። ሕዝቡ ያስመዘገባቸውን ድሎች በመጠበቅና በአንድነት ወደ ፊት መራመድ እንዳለበት ገልፀው፣ጥቃቱን የፈፀሙ እነዚህ ኃይሎች አዲስ የተጀመረውን የልማትና የለውጥ ሂደት ለማደናቀፍ በሽብር ተግባር በመሰማራት ራሳቸውን መከላከል በማይችሉ ንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል ብለዋል። በ2019 ዓ.ም.ጥቅምት 14 ቀን በሽርካ ወረዳ፣ በብርቦ ጮሌ ቀበሌ በተፈጸመው ጥቃት የንጹሐን ዜጎች ሕይወት መጥፋቱ፣የመንግሥትና የሕዝብ ንብረት መቃጠሉ፣እንዲሁም ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቤቶቻቸውና ከንብረቶቻቸው መፈናቀላቸው ተገልጿል። ጥቃቱን ተከትሎ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በተካሄዱ የጸጥታ ሥራዎች 73 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለው በምርመራ ላይ መሆናቸውን፣ እንዲሁም እነዚህ ኃይሎች እንቅስቃሴ የሚያደርጉባቸው የነበሩ ስድስት ቀበሌዎች ጸጥታቸው መረጋገጡን ገልጸዋል። መንግሥት በአንድ በኩል የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እርምጃ እየወሰደ፣ በሌላ በኩል ከመኖሪያ ቤቶቻቸውና ከንብረቶቻቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሰብዓዊ፣የምግብና የሕክምና ድጋፍ እያቀረበ መሆኑ ተገልጿል። በተጨማሪም ተፈናቃይ ዜጎችን ወደ መኖሪያ ቤቶቻቸውና ንብረቶቻቸው ለመመለስ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን መግለጫው ያመለክታል።
ወርሃዊ ዜና መጽሔት
Nov 1, 2026 336
የአስተዳደር ጉዳዮች ይህ ወር በታሪካችን ውስጥ ታላቅ ምዕራፍ የተመዘገበበት ነው፤ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ መሠረት አዲሱ የመደመር መንግሥት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ ተመስርቷል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው አንደኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የካቢኔ አባላትን ሹመት በማጽደቅና የመንግሥት ኃላፊነት የላቀ ትጋት የሚጠይቅ መሆኑን በማጉላት ለሁለተኛው የሥራ ዘመናቸው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል። በተያያዘም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያዘጋጀውን የምክክር አጀንዳ ለፌደራል እና ለክልል አካላት በይፋ አስረክበዋል። ይህን ታላቅ ሀገራዊ ስትራቴጂ ከግብ ለማድረስና ሁለንተናዊ ዝግጁነትን ለማጎልበት ከፍተኛ የመንግሥት አመራር አካላት በአካል ብቃት፣ በሥነ-ምግባር እና በዲሲፕሊን የሚያንጽ የወታደራዊ ሳይንስ ሥልጠና በመውሰድ ላይ ይገኛሉ። ማኅበራዊ ጉዳዮች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለመላው ኢትዮጵያውያን የኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፤ በዓሉ ሰላምን፣ የገዳ ሥርዓትን የሥልጣኔ መሠረቶችና የጋራ ብልጽግናን የሚያጎላ መሆኑን ገልጸዋል። “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን!” በሚል መሪ ቃል በተከበረው 19ኛው የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን ላይም ሰንደቅ ዓላማው የሉዓላዊነታችን መገለጫ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። አያይዘውም የዓድዋን ታሪካዊ ቅርስ በማስታወስ ዜጎች ለሀገራዊ አንድነት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። በመጨረሻም በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከኢቢሲ ጋር በትግርኛ ቋንቋ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።   የፕሮጀክት ማስጀመሪያ፣ ጉብኝትና ምርቃት ጥቅምት ወር በሀገራዊ የኢንዱስትሪ፣ የመሠረተ ልማት እና የግብርና አቅም ግንባታ ረገድ ትልቅ እመርታ የታየበት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በዓመት 600 ቶን የማጣራት አቅም ያለውን ብሔራዊ የከበሩ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ መርቀዋል። በተጨማሪም ለሀገሪቱ የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የኢትዮጵያ ሚትሮሎጂ ኢንስቲትዩት የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶችን እና የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽንን ጎብኝተዋል።   በክልሎች እና በከተሞችም የልማት እንቅስቃሴዎች ተፋጥነዋል። በጎንደር 185 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ የመያዝ አቅም ያለውና ከ17 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የሚያለማው የመገጭ መስኖ ግድብ ተመርቋል፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በቆይታቸው የፋሲል ግቢንና የ«መሶብ» ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል። በአዲስ አበባ ደግሞ 351 ሄክታር መሬት ያረፈውና 10 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው የቀጨኔ–አምባሳደር–ጊዮን–ኢሬቻ–ባምቢስ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ተመርቋል።   በተያያዘም የነዳጅ ፍጆታን ለመቀነስ በሀገር ውስጥ ከነዳጅ ወደ የተፈጥሮ ጋዝ (CNG) የተቀየሩ የመጀመሪያዎቹ 26 የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች በይፋ ሥራ ጀምረዋል፤ ይህም የትራንስፖርት ወጪን በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንስና የሕዝብ የጉዞ ታሪፍን በግማሽ ያቃለለ ነው። ዲፕሎማሲ እና የሁለትዮሽ ግንኙነት በዲፕሎማሲው ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን መድረኮች ጠንካራ ተሳትፎ አድርገዋል። የመደመር መንግሥት ምሥረታን ተከትሎ የደቡብ አፍሪካውን ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ እና የናይጄሪያውን ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማን በይፋዊ የሥራ ጉብኝት ተቀብለዋል። በተጨማሪም ከሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንም ጃይሻንካር፣ ከእስራዔሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር ስትራቴጂካዊ ትብብሮችን ለማጠናከር የሚያስችሉ ውጤታማ ውይይቶችን አድርገዋል።   ቀጠናዊ ትስስርን ለማጠናከርም በኬንያው የ«ማሹጃ(የጀግኖች)» ቀን አከባበር ላይ ተገኝተዋል። በባሕር ዳር ከተማ በተካሄደው 12ተኛው የጣና ከፍተኛ የደህንነት ፎረም ከመጀመሩ አስቀድሞ ከኬንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ኪቱሬ ኪንዲኪ እና ከሞዛምቢኩ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ቻፖ ጋር ተወያይተዋል። በፎረሙ የመክፈቻ ንግግራቸውም አፍሪካውያን ሀገራት ውስጣዊ አቅማቸውን እንዲገነቡና በዓለም አቀፍ ሥርዓት ውስጥ አወንታዊ ዐሻራ እንዲያሳርፉ ጥሪ አቅርበዋል።   ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወሩን እንቅስቃሴያቸውን ያጠናቀቁት በሩሲያ ባደረጉት ይፋዊ ጉብኝት ነው። ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በንግድ፣ ጤና እና ኃይል ዙሪያ ተመካክረዋል። በ3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባዔ ላይም ዘመናዊ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ ለመገንባት ከሩሲያ ጋር እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። ከቀድሞ ስምምነቶች አንጻርም ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን አሥራ ሁለት Su-35 ተዋጊ ጄቶች እና አራት የS-400 የአየር መከላከያ ባትሪዎችን ተረክባለች።     በመጨረሻም የጠቅላይ ሚኒስትሩ «መደመር» መጽሐፍ የሩሲያኛ ዕትም በሞስኮ በይፋ መመረቁ የሀገሪቱ የፖለቲካና የአስተዳደር ፍልስፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ተደራሽነት ይበልጥ ያሰፋ ሆኗል። #PMOEthiopia #EthiopiaDelivers  
በክልሉ አመራሩ ከተለመደው አሰራር ወጥቶ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መስራት አለበት
Nov 1, 2026 252
ቦንጋ፤ ጥቅምት 22/2019 (ኢዜአ)፦በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አመራሩ ከተለመደው አሰራር በመውጣት የክልሉን ጸጋዎች በተደመረ አቅም ወደ ሃብት በመቀየር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንዳለበት ተገለጸ። በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅንጫፍ ጽህፈት ቤት የሩብ ዓመት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ዛሬ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል፡፡   የጽህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ በዚህ ጊዜ እንደገለጹት አመራሩ ከተለመደው አሰራር ወጥቶ በተደመረ አቅም የክልሉን ጸጋዎች ወደ ሃብት በመቀየር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ አለበት። ለዚህም የመደመር እሳቤን በመተግበር የሕዝቡን ሕይወት በተጨባጭ የሚቀይሩ የልማት ዕቅዶችንና ኢኒሼቲቮችን በብቃት በመተግበር መምራት ይጠበቅበታል ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በክልሉ ሁሉም ዞኖች ህዝብን በማወያየት ለተነሱ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ አቅጣጫዎች መቀመጣቸውን ገልጸዋል። ከህዝቡ የተነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በአግባቡ በመመለስ የሚጨበጥ ውጤት ማስመዝገብ ከአመራሩ ይጠበቃል ሲሉም አስገንዝበዋል። ባለፉት ጊዜያት የአመራሩን አቅም ለመገንባት የተሰሩ ሥራዎች የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ማሳደጉን የገለጹት የጽህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ተክሌ፣ የተጀመሩ ሁለንተናዊ የልማት ሥራዎችን በላቀ ብቃት እንዲያስቀጥልም ጠይቀዋል፡፡ በጽህፈት ቤቱ የስትራቴጂክ ሥራ አመራር ዘርፍ ሀላፊ አቶ አንተነህ አየለ የዴሞክራሲ ሥርአትን ለማጠናከር ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በጋራ የመስራት ባህል ይጠናከራል ብለዋል፡፡   የበጎ ፍቃድ አገልግሎትን በማጎልበት ለገዥ ትርክት ግንባታ ማዋልና እርስ በርስ የመረዳዳት ባህልን ማሳደግ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ አደረጃጀቶችን በማጠናከር የመንግስትና የፓርቲ ተግባራትን ማሳለጥ እና በየደረጃው የተነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መመለስ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሆኑ የገለጹት ደግሞ የጽህፈት ቤቱ የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አጥናፉ ሀይሌ ናቸው፡፡   የጽህፈት ቤቱ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ነጋ አበራም አመራሩ በትንሽ ውጤት ከመዘናጋት ተላቆ በቤተሰብ ደረጃ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ብዙ መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።   የፓርቲ የንቅናቄ አጀንዳዎችንና ተግባራትን አቀናጅቶ በመምራት የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል የሕዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።      
ከብሔራዊ ጥቅም ማስከበር እስከ ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪነት፡ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ስኬት
Nov 1, 2026 474
ጅማ፤ ጥቅምት 22/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በቀጣናዊና ዓለም መድረኮች እያሳየች ያለው ንቁ ተሳትፎና ዲፕሎማሲ መጠናከር የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ከማስከበር ባለፈ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተሰሚነት እያሳደገው መምጣቱን ምሁራን ገለጹ። ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ሰላም፣ ደህንነትና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ዙሪያ ታሪካዊና መሪ ሚና ያላት ሀገር ስትሆን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ያላትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት በከፍተኛ ደረጃ በማስፋት ላይ ትገኛለች። ሀገሪቱ የብሪክስ አባል በመሆን የተቀላቀለችበት ሂደት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የዲፕሎማሲ ክብደት ያደሰና በኢኮኖሚ፣ በንግድ እንዲሁም በኢንቨስትመንት ዘርፎች አዳዲስ የትብብር በሮችን የከፈተ ክስተት ሆኗል። በተለይም ደግሞ በሞስኮ በተካሄደው 3ኛው የአፍሪካ-ሩሲያ ጉባዔ ላይ ኢትዮጵያ ያደረገችው ንቁ ተሳትፎና የጎንዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶች ሀገሪቱ ከታላላቅ የዓለም ሀገራት ጋር ያላትን ስትራቴጂያዊ አጋርነት ማጠናከሯን ያሳያል። ይህ መድረክ ኢትዮጵያ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ፣ በኃይል ልማትና በምግብ ዋስትና ዙሪያ ብሔራዊ ጥቅሟን የሚያስክብሩ ስምምነቶችን እንድታመቻች እንዲሁም በቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ የራሷን የፀና አቋም እንድታንጸባርቅ ትልቅ እድል ፈጥሯል። እነዚህም ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲው ዘርፍ ያላት ተሰሚነትና ተጽዕኖ ፈጣሪነት ከቀደመው ጊዜ በላይ እንዲያንሰራራ ማድረጉን በርካታ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ምሁራን ይገልጻሉ። የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ውጭ ግንኙነት መምህሩ ኢዶሳ ደገፈ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መድረኮች ብሔራዊ ጥቅሟንና የጸና አቋሟን ያስጠበቀ የጋራ መፍትሔ የማፈላለግና የመደራደር አቅሟን በከፍተኛ ደረጃ እያጎለበተች ነው። መምህር ኢዶሳ አያይዘውም፤ ኢትዮጵያ የCOP32 ዓለም አቀፍ ጉባዔ አስተናጋጅ ሆና መመረጧንና ከመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት ጋር ያላትን የዲፕሎማሲ ትብብር ማጠናከሯን ለአብነት አንስተዋል። በተለይም ወደ ቀይ ባሕር የሚኖራትን ተደራሽነት ለማሳካት የምታደርገውን እንቅስቃሴ ጥንቃቄ የተሞላበት በጎ አካሄድ ነው ሲሉ ገልጸዋል። የጅማ ዩኒቨርሲቲ የሕግና አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር ደሊል አህመድ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ አቅምና በዓለም አቀፍ መድረኮች ያላት ተሳትፎ ከቀደመው ጊዜ በተሻለ ሁኔታ እየጎለበተ መምጣቱን ገልጸዋል። በተለይም የሀገሪቱን ሰላም፣ ደኅንነትና ሉዓላዊነት ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን በመመከት ረገድ ከሚወሰዱ እርምጃዎች ባሻገር፣ ስለ ሀገሪቱ እውነተኛ ሁኔታ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ግልጽ መረጃ በማድረስ የዲፕሎማሲ ሥራዎቿን ማጠናከሯ የተሻለ አቅም እየገነባች መምጣቷን የሚያመለክት መሆኑን አብራርተዋል። መምህሩ በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ3ኛው የአፍሪካ–ሩሲያ ጉባዔ ያደረጉት የነቃ ተሳትፎ የሀገሪቱ የውጭ ግንኙነት እየተስፋፋ መምጣቱን ከሚያመለክቱ ክስተቶች አንዱ አድርገው ጠቅሰዋል። እንደ መምህሩ ገለጻ፣ የጉባዔው አስፈላጊነት በአፍሪካና ሩሲያ መካከል ያለውን ትስስር ከማጠናከር ባለፈ፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድና በሰፊው ዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን የዲፕሎማሲ ሚና ለማሳደግ የሚያግዝ ነው። ይህም ሀገሪቱ ከአንድ ወገን ጋር ብቻ ተወስና ሳይሆን ከተለያዩ ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ግንኙነት ለመፍጠር የምትከተለውን የውጭ ግንኙነት አቅጣጫ የሚያሳይ መሆኑን አመልክተዋል። በመሆኑም ኢትዮጵያ በቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ያላት ተሳትፎ፣ ከተለያዩ ሀገራት ጋር እያሳደገች የመጣችው ግንኙነትና የራሷን አቋም በዓለም አቀፍ መድረኮች የማስገንዘብ አቅሟ እየጠነከረ መምጣቱን ገልጸዋል።  
የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ዓለም አቀፍ መርህን የተከተለ በመሆኑ ተቀባይነቱ እያደገ መጥቷል
Oct 31, 2026 624
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 21/2019 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በሰጥቶ መቀበልና በዓለም አቀፍ መርህ የተቃኘ በመሆኑ ተቀባይነቱ እያደገ መጥቷል ሲሉ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ያነጋገራቸው ምሁራን ገለጹ። የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ በሕግ፣ በኢኮኖሚያዊ ዕድገት ፍላጎት እና በመልከዓ ምድራዊ ቅርበት ላይ የተመሠረተ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑንም ምሁራኑ ተናግረዋል። ጠበቃና የሕግ አማካሪ አቶ ዮናስ ወልደየስ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ ፍላጎት የሌሎችን ሀገራት ሉዓላዊነት የሚጻረር ሳይሆን ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን የተከተለ ነው። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ፣ ግዙፍ የማዳበሪያ ፋብሪካ፣ የነዳጅ ማውጫ እና የኢነርጂ ተቋማት መገንባትን ጨምሮ ትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን መጀመሯን አንስተዋል። ይህም ተጨማሪ የባህር በር አማራጮችን ማግኘትን ሀገራዊ የህልውና እና የልማት ጥያቄ አድርጎታል ብለዋል። የኢትዮጵያ ጥያቄ ሕጋዊ፣ ታሪካዊ፣ መልከዓ ምድራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አመክንዮዎች ያሉት የማይቀለበስ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል። ግብጽ እና ሌሎች ሀገራት የዓባይ ወንዝን አጠቃቀም በተመለከተ ለትውልዶቻቸው በሚያስተምሩበት አግባብ ኢትዮጵያውያንም በባህር በር እና በውሃ ሀብታቸው ዙሪያ በሳይንሳዊ ማስረጃ የተደገፈ የጋራ ግንዛቤ እንዲኖራቸው መሥራት ከእኛ ይጠበቃል ብለዋል። ግብጽ የኢትዮጵያን ሕጋዊ መሠረት ያለው ጥያቄ በማዛባት ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ጭምር ለማሳሳት ሙከራ ማድረጓን ቀጥላለች ያሉት አቶ ዮናስ፤ መሰል እንቅስቃሴዎችን የመመከቱ ሥራ ሊጠናከር እንደሚገባ አመልክተዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደህንነት መምህርና ተመራማሪ ሙሉጌታ አየለ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሌሎች ሀገራት በሺዎች የሚቆጠሩ ማይሎችን አቋርጠው ቀይ ባህር ላይ ጥቅማቸውን እያስከበሩ፣ ከቀይ ባህር 60 ኪሎ ሜትር ብቻ የምትርቀው ኢትዮጵያ ከባህር እንድትርቅ መደረጉ በየትኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።   በቀይ ባህር ላይ ጥቅሞቿን ማስከበር የኢትዮጵያ የማይቀለበስ መብቷ ነው ሲሉም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ በሰጥቶ መቀበልና ዓለም አቀፍ መርህ የተቃኘ በመሆኑ ተቀባይነቱ እያደገ መጥቷል ያሉት ተመራማሪው፤ በብሔራዊ ጥቅም ዙሪያ በጋራ ከቆምን የማይሳካበት ምንም ምክንያት የለም ብለዋል። የቀይ ባህርና የኤደን ባህረ ሰላጤ መርከቦችን የሚያግቱ እና የወንጀል ድርጊቶችን የሚፈጽሙ የባህር ላይ ወንበዴዎች የሚስተዋሉበት ቀጣና መሆኑን አስታውሰው፤ የኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር መመለስ ለቀጣናው ሠላምና መረጋጋት ዓይነተኛ ሚና እንደሚጫወትም ጠቁመዋል። ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ከማሳለጥ አኳያም የኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር መመለስ ዘርፈ ብዙ ቀጣናዊ ፋይዳ እንዳለው አብራርተዋል።
የኢትዮጵያን ሥልጣኔ ለመገንባት እንችል ዘንድ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ አለብን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Oct 31, 2026 773
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 21/2019 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያን ሥልጣኔ ለመገንባት እንችል ዘንድ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ አለብን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። የመደመር መንግሥት አመራሮች በሁርሶ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ሥልጠና በመውሰድ ላይ ይገኛሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያን ሥልጣኔ ለመገንባት እንችል ዘንድ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ አለብን ብለዋል።   ሁለንተናዊ ብልጽግና ማለት ቁሳዊና መንፈሳዊ ብልጽግና፣ ባህላዊና ሞራላዊ ብልጽግና የተሸመኑበት ብልጽግና ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህ ደግሞ አመራሩ ሁለንተናዊ ዝግጁነት ያስፈልገዋል ሲሉም ገልጸዋል፡፡ በአካል የዳበረ፣ በሞራል የጠነከረ፣ በዕውቀት የተሳለ፣ በጥበብ የበሰለ እንዲሆን እንደሚጠበቅበት ገልጸው በተለይም በሀገር ፍቅር ስሜትና በሕዝብ ተቆርቋሪነት መንፈስ ግዴታዎቹን እንዲወጣ የሀገር አደራዋ ጥብቅ መሆኑንም ገልጸዋል። ወታደራዊ ሳይንስ፣ ልምድ እና ሕይወት የሰውን ልጅ ዓላማና ሰብእና በመቅረጽ ረገድ ተወዳዳሪ የለውም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰው ልጅ በአካልም፣ በመንፈስም፣ በሥነ ምግባርም፣ በአፈጻጸምም ዲሲፕሊናዊ እንዲሆን በማስቻል ለዘመናት ትውልድን ሲያዘጋጅ ኖሯል ብለዋል። ውጫዊና ውስጣዊ ማንነቱ የሠመሩለት ሰብእና በመቅረጽም ታላላቅ መሪዎችን አፍርቷል ብለዋል፡፡   ግዳጅን በብቃት መፈጸም፣ በዐርበኝነት መንፈስ አገልግሎት መስጠት፤ የሥራ ዲሲፕሊንን መቅረጽ፤ የጋራ ግብን በጋራ ማሳካት፤ ወትሮ ዝግጁነት፤ በተዋረድ አመራርን ማፍራት፤ ኃላፊነትና ተጠያቂነት፤ ከላይ እስከ ታች በመናበብ ዓላማን መፈጸም፣ እና የመሳሰሉት ከወታደራዊ ሳይንስና ልምድ ሊወሰዱ የሚችሉ ዕሴቶች ናቸው ብለዋል፡፡ የመደመር ሥልጣኔ ታላቁ ስትራቴጂን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል፣ ከወታደራዊ ሳይንስና ሕይወት የምንቀስማቸው ዕውቀቶች፣ ክሂሎቶች እና ልምዶች አሉን ሲሉም ገልጸዋል።   በተለይም ደግሞ በአንድ ሰዋሰው መግባባት፣ ሥነ ምኅዳርን በሚገባ መጠቀም፤ በተከታታይ ሕዝብን ለዓላማና ለተግባር ማነጽ፤ ለሕዝብ የገባነውን ቃል በሚገባ አከናውኖ መጨረስ፤ ከታች እስከ ላይ ያለውን መዋቅር ለሀገራዊ ዓላማ ማሣለጥ፤ ሀገርን በባለ አደራነት መምራት፤ ለምንምና ለማንም የማትበገር ጽኑ ሀገር መገንባት፤ ተተኪ ትውልድን ማፍራት እና የሀገርን ደኅንነት ምንጊዜም ማረጋገጥ የሚሉትን የስትራቴጂውን ሐሳቦች በተገቢው መንገድ ለመረዳትም ሆነ ለማስፈጸም ወታደራዊ ሥልጠናው የማይናቅ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡ ወታደሮች ዒላማ፤ ሲቪሎች ደግሞ ዓላማ አላቸው፡፡ የሁለቱም ግብ ድልን ማስመዝገብ ነው፡፡ ሁለቱን ዲሲፕሊኖች በማገናዘብ ዒላማውንም የሚመታ፤ ዓላማውንም የሚያሳካ ትውልድ እንፈጥራለን ብለዋል፡፡

ማህበራዊ
በመዲናዋ የሚከናወኑ ልማቶች ሰው ተኮር እና የማኅበራዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ናቸው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Nov 1, 2026 253
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 22/2019 (ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ ከተማ የሚከናወኑ ልማቶች ሰው ተኮር እና የነዋሪዎችን ማኅበራዊ ትስስር በማጠናከር ወደ ተሻለ የአኗኗር ዘይቤ የሚያሸጋግሩ መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለልማት ተነሺ አርሶ አደሮች የተገነባውን የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ የመኖሪያ መንደር መርቀው ለተጠቃሚዎች አስተላልፈዋል።   ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት አዲስ አበባን በጋራ፣ በትብብር እና በውጤታማነት እያለማን እንገኛለን ብለዋል። ይህም አዲስ አበባን በዓለም አቀፍ መድረክ እንድትሸለም እያስቻላት መሆኑን ተናግረዋል። እውቅናው የሁሉም ትብብር ውጤት መሆኑን አንስተው፣ የልማት ተነሺዎች ለልማት ተባባሪ መሆናቸው ለዚህ ውጤታማነት አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸዋል። አዲስ አበባን የማልማቱ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ከንቲባዋ፣ ዛሬም ለልማት ለተነሱ አርሶ አደሮች ዘመናዊ የሆነ የመኖሪያ ቤት ተገንብቶ መሰጠቱን ተናግረዋል። ልማት ማለት የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል፣ የኢኮኖሚ አቅሙን ማጠናከርና የነገ ተስፋውን ማለምለም ጭምር ነው ሲሉ ተናግረዋል።   መኖሪያ መንደሩ የነዋሪዎቹን ማኅበራዊ ትስስር በማጠናከር ወደ ተሻለ የአኗኗር ዘይቤ የሚያሸጋግርና ሰው ተኮር የአሠራር አቀራረብን የተከተለ ነው ብለዋል፡፡ ለአርሶ አደሮቹ የኑሮና የገቢ ምንጮቻቸውን የሚያሳድጉበትን ዕድል የሚፈጥሩ በርካታ አቅርቦቶችን ያካተተ መሆኑንም አብራርተዋል። የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አደፍርስ ኮራ በበኩላቸው፣ የተገነባው ቤት ነዋሪዎቹ የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ ለማስቻል ታስቦ በዘመናዊ መንገድ መገንባቱን አስታውቀዋል። የኢኮኖሚና ማህበራዊ አገልግሎቶችን በአንድ ላይ የሚያስተሳስሩ ዘርፈ ብዙ መሠረተ ልማቶች የያዘ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።   በመኖሪያ መንደሩ የቤት ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል ወ/ሮ ዘውድነሽ መስቀላ፣ የተሰጣቸው ቤት ከቀደመው የተሻለ፣ ዘመናዊ እና ውብ በመሆኑ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ኑሯቸውን በአግባቡ ለመምራት የሚያስችሉ መሠረተ ልማቶች እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ አገልግሎቶች በተሟሉበት መንደር በመግባታቸው መደሰታቸውን የገለጹት ደግሞ ሌላኛው የቤት ተጠቃሚ አብራሳ ዱመቻ ናቸው፡፡ በዚህም ለከተማ አስተዳደሩ ምስጋና አቅርበዋል።        
ልማት ሰውን ማዕከል ሲያደርግ፤ የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ መንደር ሌላኛው ማሳያ ነው
Nov 1, 2026 279
እውነተኛ ልማት የሚለካው የሰዎችን ሕይወት በምን ያህል ደረጃ እንደቀየረ በሚያሳየው ውጤት ነው፤ ይህም በከተማችን በተጨባጭ እየታየ ይገኛል። አዲስ አበባ ለልማት ፕሮጀክቶች መሬት ስታውል የዜጎቿን መብት፣ ጥቅምና የኑሮ ሁኔታ በማክበር ልማትን ከሰው ሕይወት ጋር አስተሳስራ እየሠራች ነው። የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ ነዋሪዎች መንደርም የዚህ አካሄድ ጉልህ ማሳያ ነው። የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ግንባታ ለሀገራዊ የቴክኖሎጂና ኢኮኖሚ ሽግግር ትልቅ አቅም የሚፈጥር ፕሮጀክት ቢሆንም፣ የልማቱ ተነሺዎች የነበራቸው የኑሮ ዘይቤና ማኅበራዊ ትስስር እንዳይጎዳ ልዩ ትኩረት ተደርጎለታል።   በዚህም 17 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ላይ የተገነባው የሹቡ ኤጀርሳ መንደር ለነዋሪዎች ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ከማቅረብ ባለፈ፣ የወተት ላም ማርቢያ ሼዶችን፣ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያን፣ የንግድ ሱቆችን፣ የምርት መሸጫ መጋዘንን፣ ወፍጮዎችንና ሌሎች አገልግሎቶችን አካቷል። ከዚህም በላይ የሕፃናት ማቆያና መጫወቻ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ እና የማኅበረሰብ መሰብሰቢያ አዳራሽ በማካተት የቤተሰብን ሕይወት በሁሉም ዘርፍ ለማሻሻል ተሠርቷል። የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት
በአምቦ ከተማ የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር የትምህርት ጥራትንና የተማሪዎችን ተሳትፎ እያሳደገ ነው
Nov 1, 2026 149
አምቦ፣ ጥቅምት 22/2019 (ኢዜአ)፡-በአምቦ ከተማ አስተዳደር የተተገበረው የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር ለትምህርት ጥራት መሻሻልና ለተማሪዎች የመማር ፍላጎት ማደግ አስተዋጽኦ ማድረጉን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ጫላ መገርሳ ለኢዜአ እንደለጹት በከተማው በ2014 ዓ.ም የተጀመረው የተማሪዎች ምገባ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና የተማሪዎችን የመማር ፍላጎት ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል።   ዘንድሮም መርሃ ግብሩን በማስቀጠል በ17 ቅድመ መደበኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ 13 ሺህ 970 ተማሪዎች የምገባ መርሀግብሩ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል። ለመርሀግብር 34 ሚሊዮን ብር በጀት መመደቡን አቶ ጫላ ገልጸው፣ ለዚህም የከተማዋ ቡሳ ጎኖፋና ህብረተሰቡ የላቀ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል። እስካሁንም 7 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸው፣ በምገባ መርሃግብሩ እየታየ ያለውን ውጤት ለማስቀጠል ህብረተሰቡ ድጋፉን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል። በበጀት ዓመቱ የተማሪዎችን ምገባ መርሀ ግብር ለማስፋፋትና የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ይበልጥ ትኩረት መሰጠቱን አመልክተው በተጨማሪ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻልና ግብዓት የሟሟላት ሥራዎችም በመከናወን ላይ ናቸው።   በከተማው የሰደን ሊባን 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ጫላ ቀነኒ በበኩላቸው እንዳሉት በትምህርት ቤቱ 2 ሺህ 134 ተማሪዎች በምገባ መርሀግብሩ ተጠቃሚ ሆነዋል። መርሀግብሩ በተለይ ወላጆቻቸው አቅም የሌላቸው ተማሪዎች ትምህርታቸውን ሳይቸገሩ በአግባቡ እንዲከታተሉና ውጤታማ እንዲሆኑ እያገዘ መሆኑን ጠቁመዋል። የተማሪዎች ምገባን ተከትሎ የደጋሚ ተማሪዎች ቁጥር እየቀነሰና የማለፍ ምጣኔ እየጨመረ መምጣቱን የገለጹት ርዕሰ መምህሩ፣ ትምህርት የሚያቋርጡ፣ የሚቀሩና የሚያረፍዱ ተማሪዎችም ቁጥር በእጅጉ ቀንሷል ብለዋል።   የተማሪዎች ምገባ የወላጆችን ጭንቀትና ወጪ ከመቀነስ ባለፈ ተማሪዎች ለትምህርታቸው ብቻ ሙሉ ትኩረት እንዲሰጡ አግዟል ያሉት ደግሞ የተማሪ ወላጅ አቶ ስለሺ ሚልኬሳ ናቸው። መርሀግብሩ በተለይ አቅም የሌላቸው የተማሪ ወላጆችን ችግርና ሀሳብ በማቃለል በኩል ከፍተኛ አስተዋጾ ማድረጉን የገለጹት አቶ ስለሺ፣ ብዙ ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ማገዙንም ተናግረዋል።   የትምህርት ቤቱ ተማሪ ኪሴ ደበሌ በበኩሏ የምገባ መርሀግብሩ የብዙ ወላጆችን የኑሮ ጫናን ማቃለሉን ጠቅሳ፤ እሷም ያለሀሳብ በትምህርቷ ላይ አተኩራ እንድትማር ያስቻላት መሆኑን ተናግራለች፡፡    
በአዳማ ከተማ አስተዳደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ለማስፋፋት ትኩረት ተሰጥቷል
Nov 1, 2026 197
አዳማ፤ ጥቅምት 22/2019 (ኢዜአ)፦ በአዳማ ከተማ አስተዳደር መሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን የከተማው የአንድ ማዕከል አገልግሎት አስታወቀ። በአዳማ ከተማ አስተዳደር ህብረተሰቡ ባለበት ሆኖ በበይነመረብ አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችለውን መሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት የማስፋፋት ስራ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ነው የከተማው የአንድ ማዕከል አገልግሎት አስተባባሪ አቶ መኩሪያ ድንቁ የገለጹት። በአሁኑ ወቅት በከተማውና በሶስት ክፍለ ከተሞች በተከፈቱ ማዕከላት የመሬት፣ የሙያ ፍቃድ፣ የገቢና የባንክ አገልግሎቶችን ጨምሮ 138 አገልግሎቶች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እየተሰጡ እንደሚገኙ አንስተዋል። በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከንግድ ፍቃድ (E-TRADE) ብቻ 37 ሺህ ተገልጋዮች ባሉበት ሆነው በበይነ መረብ ማስተናገድ መቻሉንም አንስተዋል። አገልግሎቱን በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተደራሽ ለማድረግ ህንፃዎች እየተገነቡ መሆኑን ገልጸው፤ እስከ ሁለተኛው መንፈቅ ዓመት ድረስ ሁሉንም ዓይነት አገልግሎቶች በበይነመረብ ለማቅረብና የተንቀሳቃሽ አገልግሎትንም ለመጀመር እየተሰራ ነው ብለዋል። ኢዜአ ያናገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ ማዕከሉ አገልግሎቶችን ባንድ ማዕከል በማቅረቡ እንግልትን፣ መመላለስንና ብልሹ አሰራሮችን ማስቀረቱን ገልጸዋል። ከአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች መካከል አቶ ጌዲዮን ማሬ የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ፍቃድ ለመጠየቅ ወደ ማእከሉ መምጣታቸውን ገልጸው፤ ካሁን በፊት የመንግሥት አገልግሎት ለማግኘት ከቢሮ ቢሮ መመላለስና ረጅም ጊዜ መቆየት የተለመደ ነበር ይላሉ። አሁን ግን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ይህንን የቀየረ እና ፈጣን፣ ቀልጣፋና ያለ ምንም እንግልት አገልግሎት በመስጠቱ ደስታ እንደተሰማቸው ተናግረዋል። ሌላኛዋ በማዕከሉ ያገኘናቸው ተገልጋይ ወይዘሮ ተስፉ ብሩ፤ የአንድ ማእከል አገልግሎት በጣም ፈጣንና ምንም ማጉላላት የሌለበት ሆኖ እንዳገኙት ጠቅሰዋል። የመጡበትን የወሳኝ ኩነት ጉዳይ በደቂቃዎች ውስጥ ጨርሰው መውጣታቸውን ገልጸው፤ በዚህም በእውነቱ እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። አገልግሎቱ የአሰራር ቅልጥፍናን ለማሳደግ፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲያጠናክር እንዲሁም የመልካም አስተዳደር መርሆዎችን በተቋማት ውስጥ በተግባር ለማስፈን ወሳኝ በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ተገልጋዮቹ ጠይቀዋል።
ኢኮኖሚ
የኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ልማት ስኬቶች ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አርዓያ የሚሆኑ ናቸው
Nov 2, 2026 67
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ልማት ስኬቶች እና የምትከተላቸው አቅጣጫዎች ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አርዓያ የሚሆኑ ናቸው ሲሉ በኢትዮጵያ የዴንማርክ ኤምባሲ የኢነርጂ ዘርፍ አማካሪ ቶማስ ፍሉሪን ሶረንሰን ገለጹ። በኢትዮጵያ የዴንማርክ ኤምባሲ አማካሪ ቶማስ ፍሉሪን ሶረንሰን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ልማት የምትከተለው አቅጣጫ ትክክለኛ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በኃይል ልማት የምትወስዳቸው ውሳኔዎች ለሌሎች ሀገራት ማበረታቻ እንደሚሆኑ ገልፀው፣ በዘርፉ ያለው ዕድገት ለአፍሪካ ሀገራት ተሞክሮ እንደሚሆን አመልክተዋል። ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ምርት ጥሩ እድገት እያሳየች መሆኑን ጠቁመው፤ በዘርፉ የተያዙት እቅዶችና የልማት አቅጣጫዎች ጠንካራ መሆናቸውን አመልክተዋል። ዴንማርክ ከኢትዮጵያ ጋር በውሃና ኢነርጂ ዘርፎች የረጅም ጊዜ ጠንካራ ትብብር እንዳላትም ገልጸዋል። ትብብሩ የተቋማዊ አቅም ግንባታን፣ በተመሳሳይ ዘርፍ በሚሠሩ ተቋማት መካከል የልምድ ልውውጥንና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ያካተተ መሆኑን ጠቁመዋል። የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትም የሁለቱ ሀገራት ትብብር ማሳያ መሆኑን ጠቅሰው፤ ዴንማርክ በውሃና ኢነርጂ ዘርፎች የኢትዮጵያ ጠንካራ አጋር መሆኗን አስረድተዋል። በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ትብብር የግሉን ዘርፍ በማካተት የበለጠ ሊጠናከር እንደሚችልና ይህም ለሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች ጥቅም እንደሚያስገኝ አመልክተዋል። ዴንማርክ ኢትዮጵያ በኃይል ልማት ላይ ለምታከናውናቸው ተግባራት ድጋፏን እንደምታጠናከር ተናግረዋል።
በክልሉ ከ43 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የመስኖ ተቋማት ግንባታ ተጠናክሮ ቀጥሏል
Nov 2, 2026 57
ባህር ዳር ፤ ጥቅምት 23/2019(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ከ43 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 129 የሚሆኑ የነባርና አዳዲስ መስኖ ተቋማት ግንባታ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ። የመስኖ ልማቱ የገጸና ከርሰ ምድር ውሃን በአግባቡ በመጠቀም በመኸር ወቅት ከሚገኘው ሰብል ተጨማሪ ምርት ለማግኘት አስችሏል። በዚህም ስንዴን ጨምሮ ሌሎች ሰብሎችን፣ አትክልትና መሰል አዝርዕትን በብዛት በማምረት በምግብ እህል አቅርቦት ራስን ለመቻል በሚያስችል አግባብ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። በክልሉ ግብርና ቢሮ የመስኖ ድሬይኔጅ ግንባታና ክትትል ዳይሬክተር አቶ ጌትነት አያሌው ለኢዜአ እንደገለፁት፤ በመስኖ ልማት ለኢንዱስትሪዎች ግብዓትም ሆነ ለገበያ የሚሆን ምርት እየተመረተ ነው።   ባለፉት ዓመታት ዘመናዊ የመስኖ አውታሮችን በማስፋፋት በተሠራ ሥራም አርሶ አደሩ በተደራጀ አግባብ ወደ ልማቱ እንዲገባ መደረጉን ገልጸዋል። ይህንን አጠናክሮ ለማስቀጠልም በዚህ በጀት ዓመት 129 የሚደርሱ ነባርና አዳዲስ የመስኖ ተቋማትን ግንባታ ለማከናወን የሚያስችል ዝግጅት በማጠናቀቅ ወደ ሥራ መገባቱን አስታውቀዋል። የመስኖ ተቋማቱ 21 ሺህ ሄክታር መሬት የማልማት አቅም ያላቸው ሲሆን፣ ከ43 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን የልማቱ ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሆናቸውንም ተናግረዋል። ከእነዚህ አነስተኛና መካከለኛ ተቋማት መካከልም 65 የሚሆኑትን በዚህ ዓመት አጠናቆ ወደ ልማት ለማስገባት ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል። ለመስኖ ተቋማቱ ግንባታ 5 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዞ ወደ ሥራ መገባቱን ጠቅሰው፣ ማኅበረሰቡም ወሰን በማስከበር፣ በጉልበቱ፣ የግንባታ ቁሳቁስ በማቅረብና በገንዘቡ እያገዘ መሆኑን ተናግረዋል።   የዘመናዊ መስኖ ተቋማት ግንባታ ክልሉን በዘላቂነት ከዝናብ ጥገኝነት ከማላቀቅ ባለፈ፣ በምግብ ራስን ለመቻል የተያዘውን ግብ ለማሳካት በሚያስችል አግባብ በመንግሥት በኩል በትኩረት እየተከናወነ እንደሚገኝም አብራርተዋል። ባለፈው ዓመት 51 የመስኖ ተቋማትን በመገንባት ከ5 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘመናዊ መስኖ ማልማት መቻሉን ገልጸዋል። በክልሉ ከ2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ የመልማት አቅም እንዳለ አንስተው፣ ይህንኑ ወደ ልማት ለማስገባትም የዲዛይንና የጥናት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ጨምረው አስረድተዋል።
በአዳማ ከተማ አስተዳደር በዘንድሮው የበጋ መስኖ ልማት 17 ሺህ ሄክታር መሬት ይለማል
Nov 2, 2026 75
አዳማ ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ)፦በአዳማ ከተማ አስተዳደር በምግብ ራስን ለመቻል በተያዘው አቅጣጫ በዘንድሮው የበጋ መስኖ ልማት 17 ሺህ ሄክታር መሬት የሚለማ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ግብርና ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። የኢትዮጵያ መንግሥት በምግብ ራስን ለመቻል እና የውጭ ምንዛሬን ለማዳን ከጀመራቸው አገራዊ የኢኮኖሚ ጥረቶች መካከል የበጋ መስኖ ልማት ዋነኛው ነው። በተለይም በአዋሽ ተፋሰስ እና በአካባቢው የሚገኙ በመስኖ የሚለሙ መሬቶችን አቅም በከፍተኛ ደረጃ የመጠቀም ስልት በመተግበር ላይ ይገኛል።   የአዳማ ከተማ አስተዳደርና የከተማ ዙሪያ አምራችም ክላስተሮች አትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ በስንዴና በሌሎች የብርዕ እና የጥራጥሬ ሰብሎች ምርታማነት ላይ ተጨባጭ ውጤት ሲያስመዘግቡ ቆይተዋል። የዘንድሮው የ17 ሺህ ሄክታር መሬት ልማት እቅድም የዚሁ አገራዊና ክልላዊ የምግብ ዋስትና ማረጋገጫ ጥረት አካል ነው። የከተማ አስተዳደሩ ግብርና ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ አለሙ ቂልጡ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ በዘንድሮው የበጋ መስኖ ልማት ትልቅ እቅድ ተነድፎ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ተገብቷል።   ለዚህም ባለፈው መኸር እርሻ ለምቶ ለአጨዳ የደረሰውን ሰብል ሙሉ በሙሉ በመሰብሰብ በበጋ መስኖ በአትክልትና ስንዴ ዘር ለመሸፈን በየደረጃው እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። በበጋ መስኖ ከሚለማው ውስጥ 10 ሺህ 200 ሄክታር የሚሆነው በስንዴ ምርጥ ዘር በኩታ ገጠም የሚለማ መሆኑን ጠቅሰው፤ ቀሪው መሬት ደግሞ የተለያዩ ገበያ ተኮር በሆኑ የአትክልት አይነቶች እንደሚሸፈን አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅት እቅዱን ለማሳካትና ስራውን ማሳለጥ የእርሻ ትራክተሮችን ጨምሮ በቂ የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሮች ለማቅረብ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል። ይህም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የጎላ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ጠቁመዋል። የበጋ መስኖ ልማቱ በወንጂ፣ በአዋሽ መልካሣና በሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ ከ20 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች እና ወጣቶች እንደሚሳተፉ አስረድተዋል። በአስተዳደሩ ያለው ምቹ የተፈጥሮ ፀጋ በተለይም አዋሽ ወንዝ ያለውን እምቅ አቅም በመጠቀም ዘመናዊና ባህላዊ መስኖ ልማቱን ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን አውስተዋል።   በዚህ ረገድ አስተዳደሩ አርሶ አደሮችን በቴክኖሎጂ እና በምርት ማሳደጊያ ግብአት በቅርበት በመደገፍ ምርታማነታቸውን ለማሳደግ እንደሚሰራ ጠቁመዋል። የበጋ መስኖ ልማት ተሳታፊ አርሶ አደሮችንም ቁጥር ለማሳደግ የውሃ መሳቢያ ሞተር አቅርቦት ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኃላፊው አረጋግጠዋል።
በአፋር ክልል የተፈጥሮ ሀብትን ወደ ልማት የመቀየር ሥራ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል- ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ
Nov 1, 2026 263
ሰመራ፣ ጥቅምት22/2019 (ኢዜአ):-በአፋር ክልል ያለውን የተፈጥሮ ሀብት ለይቶ ጥቅም ላይ ለማዋል የተጀመሩ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤት ማምጣታቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ አወል አርባ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በገቢ ረሱ ዞን ዱለሳ፣ በሃንሩካ እና ገለአሎ ወረዳዎች የተከናወኑ የመስኖ ልማት ሥራዎችን ዛሬ ተመልክተዋል። በዚህ ወቅት ርዕሰ መስተዳድር አወል እንደገለጹት በወረዳዎቹ እየተከናወኑ ያሉ የግብርና ልማት ሥራዎች የህብረተሰብ ተጠቃሚነትን የሚያሳድጉ ናቸው። ክልሉ ያለውን የተፈጥሮ ሀብት ለይቶ ጥቅም ላይ ለማዋል የተጀመሩ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆናቸውን ገልጸው፣ ዛሬ በወረዳዎቹ በመስኖ ልማት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ለዚህ ማሳያ ናቸው ብለዋል።   በወረዳዎቹ በመስኖ እየለሙ ካሉ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማቶች አርብቶ አደሩ ተጠቃሚነቱን እያሳደገ መምጣቱንም ተናግረዋል። እንደ አቶ አወል ገለጻ፣ በወረዳዎቹ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ተረክበው ወደሥራ የገቡ ባለሀብቶችም ለአካባቢው ነዋሪዎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ በጥጥና ሙዝ ልማት የግብርና ቴክኖሎጂዎችን እያሸጋገሩ ይገኛሉ። ክልሉ በተለይ በመስኖ ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚቻል የዛሬው የመስክ ምልከታ አንድ ማሳያ ነው ያሉት አቶ አወል፣ ይህም ቀደም ሲል በልማት የነበሩ አመላካከትና ትርክቶች እየተቀየሩ መምጣታቸውን ያሳያል ብለዋል።   በመደመር መንግስት በክልሉ ያለውን የተፈጥሮ ሀብት ለይቶ በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል የተጀመሩ ጥረቶች ውጤታማ በመሆናቸው ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉም አስታውቀዋል። በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአዋሽ ቤዝን አስተዳደር ጽህፈት ቤት ሀላፊ ኢንጂነር አደን አብዶ በበኩላቸው፣ "በገቢ ረሱ ዞን በተከናወኑ የጎርፍ መከላከል ሥራዎች አካባቢውን ከሥጋት ነፃ እና የልማት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል" ብለዋል። ለዚህም በዞኑ ዱለሳ፣ ሃንሩካና ገለአሎ ወረዳዎች 4 ሺህ 500 ሄክታር መሬትን ከጎርፍ አደጋ ነፃ በማድረግ ወደምርት ማስገባት መቻሉን አንስተዋል። በአሁኑ ወቅት በወረዳዎቹ ሙዝ፣ በቆሎ፣ ጥጥ፣ ሽንኩርትና ቲማቲም እየለማ መሆኑን ጠቁመው፣ በአካባቢው የውሃ ዕጥረት እንዳይከሰት ለአልሚዎቹ ውሃን በፍትሃዊነት የማከፋፈል ሥራ እየተሰራ ነው ብለዋል። የዱለሳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አሊ ደስታ በበኩላቸው እንደተናገሩት፣ በወረዳው በ1ሺህ 28 ሄክታር መሬት ላይ በቆሎ፣ ማሽላ፣ ሽንኩርት፣ ቲማቲምና ጥጥ እየለማ ይገኛል። አርብቶ አደሩ ማህበረሰብ በመስኖ ልማት ተሰማርቶ ውጤታማ መሆኑ ገቢውን በማሳደግ ተጠቃሚ እያደረገው መሆኑን ተናግረዋል። በገለአሎ ወረዳ በጥጥ እና ሙዝ ልማት የተሰማሩት ሁመድ ጅብሪል በበኩላቸው በመሰኖ ልማት ሥራ ተጠቃሚ በመሆናቸው ልማቱን እያስፋፉ መሆናቸውን ገልጸዋል። በዘንድሮው ዓመት ብቻ በ150 ሄክታር መሬት ላይ ሙዝ እንዲሁም በ600 ሄክታር መሬት ላይ ጥጥ እያለሙ መሆናቸውንና ለ630 ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን ተናግረዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የደብረ ብርሃን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ስራ አስጀመሩ
Nov 1, 2026 308
ደብረ ብርሃን፤ ጥቅምት 22/2019 (ኢዜአ)፦ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በደብረ ብርሃን ከተማ የተገነባውን ዘመናዊ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በይፋ መርቀው ስራ አስጀምረዋል። በማስጀመሪያ መርሃግብሩ የክልሉ፣ የዞንና የከተማው ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።   ማዕከሉ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ለህብረተሰቡ የሚያቀርባቸውን የተለያዩ አገልግሎቶች በአንድ ማእከል በማሰባሰብ፤ የህዝብን እንግልትና ውጣ ውረድ በዘላቂነት የሚያስቀር፣ ፈጣን፣ ጥራት ያለው እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል። በክልሉ ሕዝብን ከእንግልት ታድገው ዘመናዊ፣ ፈጣን እና ቀልጣፋ መስተንግዶ ለመስጠት የሚያስችሉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ተገንብተው ለሥራ እየበቁ ይገኛሉ።   ማዕከላቱ የተለያዩ መንግሥታዊ አገልግሎቶችን በአንድ ጥላ ሥር በማሰባሰብ የዜጎችን ጊዜና ጉልበት የሚቆጥቡና የአስተዳደር በደልን የሚያስቀር አዲስ ምዕራፍ እየከፈቱ መሆናቸው ታውቋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ ከሁዋዌ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኤሪክ ዩዋን ጋር ተወያዩ
Oct 31, 2026 197
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 21/2019 (ኢዜአ) ፦ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ የሁዋዌ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን በቅርቡ ሥራ ከጀመሩት ኤሪክ ዩዋን ጋር ተወያይተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በውይይታችን ወቅት መንግሥት የኢትዮጵያን የዲጂታል ጉዞ ለማስቀጠልና ለማፋጠን እየሠራቸው ያሉ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሥራዎች እጅግ አበረታች መሆናቸውን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸውልኛል ብለዋል።   ሁዋዌ የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይና ብሔራዊ የልማት ግቦቻችንን ለማሳካት በምናደርገው ጥረት ውስጥ፣ በተለይም በአይሲቲ መሠረተ ልማትና በግንኙነት ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ይገኛል ሲሉም ገልጸዋል። በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ጉዞም ከሁዋዌ ጋር በትብብር፣ በብሔራዊ ባለቤትነት፣ በዘላቂነት፣ በደኅንነትና በአካባቢያዊ እሴት ፈጠራ መርሆዎች ላይ ተመሥርተን በምንሠራባቸው የትብብር መስኮች ዙሪያ መክረናልም ብለዋል። የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታችን በእመርታ እየተጓዘ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ሁዋዌም ለዚህ ዕድገት የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ እና ያለንን የሥራ ግንኙነት አጠናክረን ለመቀጠል ተስማምተናል ሲሉም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ፍርድ ቤት ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ችሎት በተሞክሮነት የሚወሰድ ተምሳሌታዊ አሰራር ነው
Oct 29, 2026 672
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 19/2019 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ፍርድ ቤት ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ችሎት በተሞክሮነት የሚወሰድ ተምሳሌታዊ አሰራር መሆኑን የታንዛኒያ የካፒታል ገበያ ፍርድ ቤት ልዑካን ቡድን አባላት ገለጹ። ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብና ታላቅ ርዕይ ከትናንት ጥቅምት 18 ጀምሮ በአዲስ አበባ መካሄድ የጀመረው የኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ የካፒታል ገበያ ፍርድ ቤቶች የልምድ ልውውጥ መድረክ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል። የታንዛኒያ የካፒታል ገበያ ፍርድ ቤት ልዑካን ቡድን አባላትም የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደር ፍርድ ቤት፣ የኢትዮጵያ ስቶክ ገበያ እና የኢትዮጵያ ምርት ገበያን ጎብኝተዋል።   የታንዛኒያ የካፒታል ገበያ ፍርድ ቤት ሊቀመንበር ኔሚ ኪለካጄንጋ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደር ፍርድ ቤት በቴክኖሎጂ የታገዘ አስደናቂ ሥራ እየሠራ ነው። በተቋማቱ ጉብኝት ያገኙትን ልምድና ተሞክሮም በታንዛኒያ በመተግበር ዘመናዊና ስሉጥ አሠራር ሥርዓት ለመዘርጋት እንደሚያግዛቸው ገልጸዋል። በተለይም የሰው ሠራሽ አስተውሎት የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ልህቀት የፋይናንስ ዘርፍ የአቤቱታ ጉዳዮችን አፋጣኝና ግልጽ ምላሽ ለመስጠት እንደሚረዳ አስረድተዋል።   የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደር ፍርድ ቤት፣ የኢትዮጵያ ስቶክ ገበያ እና የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ አሠራርም ልምድና ተሞክሮ የቀሰሙበት መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አጠቃላይ የዲጂታል ሽግግርም አፍሪካውያንን ዘመናዊ የኢኮኖሚ ሥርዓት ለማሳለጥ በአርዓያነት የሚወሰድ አሠራር መሆኑን አብራርተዋል። በቀጣይም የአፍሪካን የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር በማሳለጥ መልኩ በታንዛኒያ ተግባራዊ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሠራ አንስተዋል።   የታንዛኒያ የካፒታል ገበያ ፍርድ ቤት የሕግ ባለሙያ ኤልያድ ኢ-መንደም በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት የቴክኖሎጂ ችሎት ተምሳሌታዊ ነው ብለዋል። ይህም ለፋይናንስ አለመግባባት ችሎቶች አፋጣኝ ምላሽ የሚሰጥና ታንዛኒያም በተሞክሮነት የምትቀስመው አርዓያነት ያለው ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።
የአፍሪካን የግብርና አቅም እውን ለማድረግ የሳይንስና ኢኖቬሽን ውጤቶችን ወደ ተግባር ማሸጋገር ይገባል
Oct 29, 2026 325
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 19 /2019 (ኢዜአ)፦ አፍሪካ የግብርና አቅሟን በአግባቡ ለመጠቀም እና የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ የግብርና ምርምር፣ የሳይንስ እና የኢኖቬሽን ውጤቶችን ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማሸጋገር እንደሚገባት የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት (FAO) ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ማውሪዚዮ ማርቲና ገለጹ። በአዲስ አበባ በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሽ ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ ሳይንስና ኢኖቬሽን ፎረም 2026 የማጠቃለያ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።   የፋኦ ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ማውሪዚዮ ማርቲና በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ የዘርፉን እድገት ለማረጋገጥ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ከምርምር ማዕከላት ጋር በየዕለቱ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል። በግብርናና በምግብ ሥርዓት ዘርፍ ኢንቨስትመንትን ለማደራጀትና ለማስፋፋት በትኩረት መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል። ዘርፉ የተለያዩ አቅሞችንና ሀብቶችን በተለየ መንገድ ማቀናጀትን እንደሚጠይቅ ገልጸው፣ በርካታ እድሎች ያሉት መሆኑንም አመላክተዋል። ፋኦ ተልእኮውን መሰረት በማድረግ በዩኒቨርሲቲዎች፣ በምርምር ተቋማትና በኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች መካከል እንደ ድልድይና አቅም ማስፈጸሚያ መሣሪያ ሆኖ እንደሚያገለግል ተናግረዋል። የእውቀት ልውውጥ የሚደረግባቸው ቀጣይነት ያላቸው መድረኮችን ማዘጋጀት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። በተጨማሪም የምርምር ውጤቶችን በፍጥነት ወደ ተግባርና ወደ ኢንቨስትመንት መቀየር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። እነዚህን እንቅስቃሴዎች በተቀናጀ አካሄድ ማስተዳደር ከተቻለ በዘርፉ የተቀመጡ ግቦችን ማሳካት እንደሚቻል ገልጸዋል። ገንዘብ አስፈላጊ ቢሆንም፣ የሰው ኃይል አቅምና ግልጽ የሆነ የአፈጻጸም መንገድ ከሌለ በቂ እንደማይሆን አስረድተዋል። በቂ ገንዘብ የተመደበላቸው አስፈላጊ ፕሮጀክቶች የታሰበውን ውጤት ሳያመጡ የቀሩት በገንዘብ እጥረት ሳይሆን በሰው ኃይል አቅም ማነስ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። በመሆኑም የፋይናንስና የሰው ኃይል አቅምን ውጤታማ በሆነ መንገድ ማቀናጀት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። አፍሪካ በርካታ እድሎች ያሏት አህጉር መሆኗን ጠቅሰው፣ ከዓለም ባንክና ከዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) ጋር በመተባበር አስፈላጊ ፕሮጀክቶች ተቀርጸው ወደ ሥራ መግባታቸውን አብራርተዋል። በመሆኑም በግብርናና በምግብ ሥርዓት ዘርፍ በጋራ መሥራትና የሙከራ ፕሮጀክቶችን ወደ ተቀናጀና ዘላቂ የሥራ አካሄድ መቀየር እንደሚገባ አሳስበዋል። ጥረቶች አንድ ጊዜ ብቻ ተከናወነው በሚያበቁ ፕሮጀክቶች ላይ ሳይወሰኑ፣ በቀጣይነት የሚሰፉና ዘላቂ ውጤት የሚያመጡ መሆን እንዳለባቸውም ተናግረዋል። የአፍሪካ ሳይንስና ኢኖቬሽን ፎረም ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽንን በመጠቀም በአፍሪካ የምግብና ግብርና ሥርዓት ውስጥ ያሉ ተደራራቢ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የተዘጋጀ አህጉራዊ መድረክ ነው። በተጨማሪም ፎረሙ ምርታማነትን በመጨመር፣ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን በማድረግ እና የግልና የመንግሥት ኢንቨስትመንቶችን በማሳደግ አህጉራዊ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ላይ ያተኮረ መሆኑንም አስገንዝበዋል።   በዓለም ባንክ የግብርና ዋና ኢኮኖሚስት እና የአፍሪካ የግብርና ልማት ፕሮግራም (CAADP) የልማት አጋሮች ማስተባበሪያ ቡድን ሊቀመንበር ሚዮ ታካዳ በበኩላቸው፣ የአለም ባንክ አግሪ ኮኔክት በተባለው ፕሮጀክቱ አማካይነት አርሶ አደሮችን እየደገፈ እንደሚገኝ ገልጸዋል ፕሮጀክቱ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ መካከል ትስስር በመፍጠር ከተለያዩ የልማት አጋሮች የሚሰጡ የተናጠል ድጋፎችን በማቀናጀት የጋራ አቅጣጫ እንዲኖር ማስቻሉን ተናግረዋል።   ለአርሶ አደሮች ፈጠራን ለማስፋፋት የሚያስችል የረጅም ጊዜ የፋይናንስ አቅርቦትን የሚያደናቅፉ ከአቅርቦትና ከፍላጎት ጎን የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን ፕሮግራም ኦፊሰር ዳንኤል ሂጊንስ ናቸው። ይህም የግሉ ዘርፍ በቀጣይነት ድጋፉን እንዲረከብና በረጅም ጊዜ ውስጥ ፋይናንስ ማድረጉን እንዲቀጥል የሚያበረታታ መሆኑን ጠቁመዋል።
ስፖርት
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኒውካስትል ዩናይትድ ከኤቨርተን ጋር ይጫወታል
Nov 2, 2026 100
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዘጠነኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ በኒውካስትል ዩናይትድ እና በኤቨርተን መካከል ዛሬ ይደረጋል። ጨዋታው ምሽት አምስት ላይ በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም ይካሄዳል። ባለሜዳው ኒውካስትል ዩናይትድ በ11 ነጥብ 12ተኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው ኤቨርተን በ10 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሁለቱ ክለቦች በሊጉ ሲገናኙ የአሁኑ ለ59ኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 58 ጨዋታዎች ኤቨርተን 24 ጊዜ ድል ሲቀናው ኒውካስትል ዩናይትድ በ21ዱ አሸንፏል። በቀሪ 13 ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል። ኤቨርተን በ58ቱ ጨዋታዎች ላይ 86 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ ኒውካስትል በበኩሉ 82 ጎሎችን ከመረብ ላይ አሳርፏል። ኒውካስትል ዩናይትድ በስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ክሪስታል ፓላስን 2 ለ 0 ያሸነፈ ሲሆን ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታል። ባለፉት ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ከድል የራቀው ኤቨርተን ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይፋለማል። ሁለቱ ቡድኖች ባለፈው ሳምንት በካራባኦ ካፕ ባደረጉት ጨዋታ ኤቨርተን ኒውካስትል ዩናይትድን 3 ለ 1 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜ ማለፉ የሚታወስ ነው። የ36 ዓመቱ ጆን ብሩክስ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት እንዲመሩ ተመድበዋል።
አካባቢ ጥበቃ
በኢትዮጵያና ጅቡቲ ኮሪደር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ መሙያ ኔትወርክ ለመዘርጋት የጋራ ኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈጸመ
Oct 31, 2026 364
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 21/2019 (ኢዜአ) ፦በኢትዮጵያና በጅቡቲ ኮሪደር ላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ መሙያ ኔትወርክ ለመዘርጋት ከሶስት የውጭ ኩባንያዎች ጋር የጋራ ኢንቨስትመንት ስምምነት መፈጸሙን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው እንደገለጹት፤ በአዲስ አበባ-ጅቡቲ የትራንስፖርት መስመር ላይ የኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጅ መሙያ አውታር ለመዘርጋት ከቻይና ሮድ ኤንድ ብሪጅ ኮርፖሬሽን፣ ከቤጂንግ ፎርኤቨር ቴክኖሎጂ ሊሚትድ እና ከሁዋዌ ቴክኖሎጂስ ጋር ስምምነት ተደረጓል። ይህ የትብብር ስምምነት ቀደም ሲል የኃይል ፍላጎትን በማጥናት፣ ጣቢያዎቹ የሚገነቡባቸውን አካባቢዎች በመለየት እንዲሁም የቴክኒክ ሞዴሎችን እና የጊዜ ሰሌዳዎችን በማውጣት ተግባራዊ ለማድረግ ያግዛል። ስምምነቱ በኮሪደሩ ላይ የተሽከርካሪ መሙያ ጣቢያዎችን በማቀናጀት ተደራሽነታቸውን ለማስፋት ያለመ እንደሆነም ተናግረዋል። በተጨማሪም ፕሮጀክቱ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር፣ የባለሙያዎች አቅም እንዲያድግ እና የሥራ ዕድል እንዲፈጠር ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። በዚህም አረንጓዴ የትራንስፖርት ሥርዓትን በማስተዋወቅ የነዳጅ ጥገኝነትንና ለነዳጅ ግዢ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ ለመቀነስ፣ የአየር ንብረት ብክለትን ለመከላከል እና የታዳሽ ኃይል አጠቃቀምን ለማሳደግ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል።
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ መሙያ ጣቢያዎች መስፋፋት የቢሾፍቱን የቱሪዝምና አረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ ያግዛል
Oct 31, 2026 346
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 21/2019 (ኢዜአ) ፦በቢሾፍቱ ከተማ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ መሙያ ጣቢያዎች መስፋፋት የቱሪዝምና አረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ እንዲያድግ ያግዛል ሲሉ የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ ገለጹ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቢሾፍቱ፣ ሞጆ፣ አዳማ፣ ባቱ እና ሀዋሳ እንዲሁም አዲስ አበባ አምስት ቦታዎች ያስገነባቸውን የኤሌክትሪክ ቻርጅ መሙያ ጣቢያዎች እያስመረቀ ይገኛል።   የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ፤ በቢሾፍቱ ከተማ የተገነቡ የኤሌክትሪክ ቻርጅ መሙያ ጣቢያዎች ምረቃ ወቅት ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት፤ ቢሾፍቱ ከአዲስ አበባ 47 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ፣ በተፈጥሮ ሀብቶቿና በሐይቆቿ የታወቀች የቱሪዝምና የኢኮኖሚ ማዕከል ናት። በከተማዋ የተቋቋሙት ጣቢያዎች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በቀላሉ ቻርጅ ለማድረግ የሚያስችሉ መሆናቸውን አውስተው፤ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ቢሾፍቱ የሚመጡ ተጓዦች በከተማዋ በምቾት ቆይታቸውን እንዲያደርጉ እንደሚያግዝ አመልክተዋል። የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን መጠቀም የነዳጅ ፍላጎትን ለማቃለል፣ የአየር ብክለትን ለመቀነስና አረንጓዴ ልማትን ለማጠናከር አስፈላጊ አማራጭ መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣይ በቢሾፍቱና በአካባቢው ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ቻርጅ መሙያ ጣቢያዎች ሲገነቡ ለፕሮጀክቶቹ የሚያስፈልጉ ቦታዎችን ከማዘጋጀት ጀምሮ እስከ ሥራ ማስጀመር ድረስ የከተማ አስተዳደሩ የሚጠበቅበትን ትብብር እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው በበኩላቸው፤ በስድስት ዋና ዋና ከተሞች የተገነቡ 11 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ፈጣን ቻርጅ መሙያ ጣቢያዎች በአንድ ጊዜ 96 ተሽከርካሪዎችን የመሙላት አቅም እንዳላቸው ገልጸዋል።   ተቋሙ በአንድ ጊዜ እስከ 150 ተሽከርካሪዎችን የኤሌክትሪክ ቻርጅ ለማድረግ የሚስችል አቅም መፍጠሩን ጠቅሰዋል። የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ መሙያ ጣቢያዎች መስፋፋት የንጹህ ኢነርጂ አጠቃቀምን ከማበረታታት ባለፈ የአየር ብክለትንና በነዳጅ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ እንደሚያግዝ ገልጸዋል። በቀጣይም በመቀሌ፣ በባህር ዳር፣ በጎንደር፣ በጅግጅጋ፣ በድሬዳዋ፣ በጅማ፣ በአርባ ምንጭና በሌሎች ከተሞች ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ቻርጅ መሙያ ጣቢያዎችን ለማስፋፋት ዕቅድ መያዙን ገልጸዋል።
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የቻርጅ መሙያ ጣቢያዎችን ተደራሽነት ለማስፋት እየተሰራ ነው - ኢንጂነር ጌቱ ገረመው
Oct 31, 2026 225
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 21/2019 (ኢዜአ) ፦በመላ ሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የቻርጅ መሙያ ጣቢያዎችን ተደራሽነት ለማስፋት ተቋሙ እየሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው ገለጹ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአዲስ አበባ በተለምዶ ሀጫሉ መንገድ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ያስገነባውን የኤሌክትሪክ ቻርጅ መሙያ ጣቢያ አስመርቋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ተቋሙ በአንድ ቀን 11 የቻርጅ መሙያ ጣቢያዎችን ማስመረቁ ለተቋሙ ልዩ ቀን ነው። በሀጫሉ መንገድ የተገነባው የቻርጅ መሙያ ማዕከል ከከተማው አስተዳደር ጋር በትብብር የተሠራ ሲሆን፣ በአንድ ጊዜ ወደ 12 የሚጠጉ ተሽከርካሪዎችን ቻርጅ የማድረግ አቅም እንዳለው ገልጸዋል። ማዕከሉ በአካባቢው ያለውን የቻርጅ መሙያ አገልግሎት ፍላጎት እንደሚያግዝ ገልጸው፤ ወደፊትም የማዕከሉን አቅም ለማስፋት ሰፊ ዕድል መኖሩን ጠቁመዋል።   በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የቻርጅ መሙያ ጣቢያዎችን በስፋት ለማስገንባት ተቋሙ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣዩ አንድ ዓመት የቻርጅ መሙያ ጣቢያዎችን ቁጥር ከአሁኑ በአምስት ዕጥፍ ለማሳደግ ዕቅድ መያዙንም ገልጸዋል። ከአዲስ አበባና አካባቢዋ ባሻገር ድሬዳዋ፣ መቐለ፣ ባሕር ዳር፣ አርባ ምንጭና ሌሎች የክልል ከተሞችንም በተለያዩ የሥራ ምዕራፎች የቻርጅ መሙያ አገልግሎቱን ለማዳረስ መታቀዱን አስረድተዋል። ተቋሙ የንጹሕ ኃይል አጠቃቀምን ለማስፋፋት ከሚያከናውናቸው ሥራዎች መካከል የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ማበረታታትና የቻርጅ መሙያ መሠረተ ልማትን ማስፋፋት አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።
በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ የተመዘገበው ስኬት ለቀጣናው የጋራ ተጠቃሚነት ትልቅ ሚና እያበረከተ ይገኛል
Oct 30, 2026 286
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 20/2019 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እና በተፋሰስ ልማት ያስመዘገበችው ስኬት ለቀጣናው የጋራ እድገትና ተጠቃሚነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ። የሦስተኛው የኢትዮጵያ የውሃና ኢነርጂ ሳምንት "ለውሃና ኢነርጂ ዋስትና የተጠበቀለት የወደፊት ሁኔታ ሳይንሳዊ መሠረት ያላቸውን ፖሊሲዎችና አጋርነቶችን ማሳደግ" በሚል መሪ ሐሳብ በተለያዩ መርሃ ግብሮች መካሄዱን ቀጥሏል።   በውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሚኒስትሩ አማካሪ ሚካኤል መሀሪ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የውኃ ሀብትን በተቀናጀ አስተዳደር ማልማት የውኃ፣ የምግብና የኢነርጂ ደህንነትን በአንድነት ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል። ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያላቸውን የውኃ ማከማቻና መሠረተ ልማቶች በማስፋፋት የመስኖ ልማትንና የኤሌክትሪክ ኃይል ምርትን በተቀናጀ መንገድ ማሳደግ እንደሚገባ አስረድተዋል። ኢትዮጵያ ወደ አባይ ወንዝ ሥርዓት ከሚገባው ውኃ ከ86 በመቶ በላይ የምታበረክት መሆኗን አንስተው፣ የውኃ ሀብቷን በአግባቡ ማልማትና መጠበቅ ለሀገር ውስጥ ልማት ብቻ ሳይሆን ለተፋሰሱ ሀገራት የጋራ ጥቅምም አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል። ኢትዮጵያ በአፈርና ውኃ ጥበቃ፣ በተፋሰስ ልማትና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ላይ እያከናወነች ያለችውን በርካታ ሥራዎች አንስተው፤ የላይኛው ተፋሰስ ሥነ-ምህዳርን መጠበቅ ለሀገር ውስጥ ልማት እንዲሁም ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት የጋራ ጥቅም ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም በወንዞች ድንበር ተሻጋሪ አስተዳደር ላይ በጋራ ጥቅምና በፍትሐዊ ተጠቃሚነት መርህ ላይ የተመሠረተ ትብብር ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በውኃና ኢነርጂ ዘርፎች የሚደረጉ ፖሊሲዎችና የልማት ውሳኔዎች በሳይንሳዊ ጥናትና በተጨባጭ መረጃ ላይ መመሥረት እንዳለባቸውም ተናግረዋል። በዘርፉ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶችን ማሳደግ፣ የአገር ውስጥ ተቋራጮችንና የግሉን ዘርፍ አቅም ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። የውኃ፣ የኢነርጂ፣ የምግብና የሥነ-ምህዳር ትስስርን በጋራ ማየት ለዘላቂ ልማት ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፣ የዘርፎቹ ጉዳይ ከቴክኒካዊ ውይይት ባለፈ ከሀገራዊ ህልውና፣ ብልጽግናና ሉዓላዊነት ጋር የተያያዘ መሆኑን አስገንዝበዋል። በውኃና ኢነርጂ ሳምንት በአረንጓዴ ኢነርጂ፣ በኤሌክትሪክ ተደራሽነት፣ ጤናንና አካባቢን የሚጠብቁ የማብሰያ ኃይል አማራጮችን በማስፋፋት፣ በተቀናጀ የውኃ ሀብት አስተዳደር፣ በንጽህናና በዲጂታል ፈጠራ ዙሪያ ውይይቶች መካሄዳቸውን ጠቁመዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ኢትዮጵያና ሩሲያ በረጅም ዘመናት ውስጥ በተገነባ ትብብር የተሳሰሩ ናቸው - ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን
Oct 29, 2026 884
ሞስኮ፤ ጥቅምት 19/2019(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ሩሲያ በረጅም ዘመናት ውስጥ በተገነባ ተምሳሌታዊ ትብብር የተሳሰሩ ሀገራት መሆናቸውን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በ3ኛው የአፍሪካ - ሩሲያ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ሞስኮ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋርም በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ተወያይተዋል።   ኢዜአ ከስፍራው እንደዘገበው በውይይቱ ላይ ፕሬዝዳንት ፑቲን የሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ከኢኮኖሚያዊ ትስስር ባሻገር በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያለውን ታሪካዊ ቅርበት አጉልቶ የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል። ይህ የጋራ የሞራል እሴት በብዙ ደረጃ ሕዝቦችን የሚያቀራርብ አስፈላጊ መሠረት መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ አስረድተው ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በብዙ የልማት መስኮች በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ በጋራ እንደሚሰሩ የገለጹት ፑቲን፣ በተመድ፣ በብሪክስ እና በሌሎችም ባለብዙ ወገን መድረኮች ውይይቶች መደረጋቸውን አንስተዋል። አፍሪካ በከፍተኛ የእድገት ጎዳና ላይ እንደምትገኝ የገለፁ ሲሆን የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ትብብር የአህጉሪቱን ተስፋ ሰጪ እድገት በጋራ ለማስቀጠል ማሳያ ነው ብለዋል። የአፍሪካ ሀገራት ሁለንተናዊ ብልፅግና ሊሳካ የሚችለውም ወቅቱ የሚጠይቀውን ቴክኖሎጂ በመታጠቅ ጭምር መሆኑን ገልጸው፣ በተለይም ሰው ሰራሽ አስተውሎት የሰው ልጅ የወደፊት እድገት ዋና መሠረት ከሚሆኑ ተስፋ ሰጪ ዘርፎች አንዱ ነው ብለውታል።   እንደሳቸው ገለጻ ዘርፉ እንዲያድግ የሂሳብና የሳይንስ ትምህርት ቤቶች፣ ማዕከላት ፣የሰው ኃይል እና የኃይል አቅርቦት መሠረተ ልማቶች ወሳኝ ናቸው። ሩሲያ በእነዚህ መስኮች ያላትን ዕምቅ አቅም ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለማጋራት ዝግጁ መሆኗንም አክለዋል። ፕሬዝዳንት ፑቲን ሩሲያ ከቀድሞ ሶቪየት ሕብረት ጀምሮ የአፍሪካ ሀገራትን የነፃነት ትግል በመደገፍ የተገነባ ታሪካዊ የትብብር መሠረት እንዳላት ጠቅሰዋል። አሁን ግን የሩሲያ እና የአፍሪካ ትብብር ወደፊት በማተኮር ኢኮኖሚያዊ እድገትን ሊያፋጥን ወደሚችል ምዕራፍ መሸጋገር እንዳለበትም አመልክተዋል። የ3ኛውን የሩሲያ - አፍሪካ ጉባዔ ውይይቶችን ተከትሎ ማጠቃለያ መግለጫዎች የሚጠበቁ ሲሆን ከ2027 እስከ 2029 የሚዘልቀው አዲስ የሩሲያ እና የአፍሪካ አጋርነት የትግበራ ዕቅድ እንደሚፀድቅም ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ ለዘላቂ ብልጽግናዋ እና ለሀገራዊ እድገቷ መሰረት በሆኑ ሶስት ቁልፍ ምሰሶዎች ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች ትገኛለች
Oct 29, 2026 703
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 19/2019 (ኢዜአ) ፦ኢትዮጵያ ለዘላቂ ብልጽግናዋ እና ለሀገራዊ እድገቷ መሰረት በሆኑ ሶስት ቁልፍ ምሰሶዎች ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች ትገኛለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፦በሞስኮ እየተካሄደ በሚገኘው 3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ በመገኘት መልዕክቴን ማስተላለፍ በመቻሌ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል ብለዋል።   በዚህ ታሪካዊ መድረክ የምናሳልፋቸው ውሳኔዎች ተጨባጭ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የጋራ ቁርጠኝነት እና ትብብር እጅግ አስፈላጊ ነው ሲሉም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለዘላቂ ብልጽግናዋ እና ለሀገራዊ እድገቷ መሰረት በሆኑ ሶስት ቁልፍ ምሰሶዎች ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች ትገኛለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነዚህም በምግብ ዋስትና እና ምርታማነት፣ በአስተማማኝ የኃይል አቅርቦት፣ እንዲሁም በክህሎት እና በዕውቀት ሽግግር ላይ የሚከናወኑ ተግባራት መሆናቸውን አብራርተዋል። የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ፣ በመከባበር እና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የጸና ታሪካዊ ወዳጅነት መሆኑንም አንስተዋል።   ይህንን ወዳጅነት ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ከሩሲያ ጋር በጋራ በመሆን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ ለመገንባት የሚያስችሉ ተግባራትን በቁርጠኝነት እያከናወንን እንገኛለን ብለዋል። ይህ ስትራቴጂካዊ ትብብር የኃይል አማራጮቻችንን ከማስፋት ባለፈ የሀገራችንን የብልጽግና ጉዞ በእጅጉ የሚያፋጥን እንዲሁም የሁለቱን ሀገራት ትስስር ከምንጊዜውም በላይ የሚያጠናክር ይሆናል ሲሉም ገልጸዋል።
የአፍሪካን የግብርና አቅም እውን ለማድረግ የሳይንስና ኢኖቬሽን ውጤቶችን ወደ ተግባር ማሸጋገር ይገባል
Oct 29, 2026 325
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 19 /2019 (ኢዜአ)፦ አፍሪካ የግብርና አቅሟን በአግባቡ ለመጠቀም እና የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ የግብርና ምርምር፣ የሳይንስ እና የኢኖቬሽን ውጤቶችን ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማሸጋገር እንደሚገባት የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት (FAO) ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ማውሪዚዮ ማርቲና ገለጹ። በአዲስ አበባ በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሽ ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ ሳይንስና ኢኖቬሽን ፎረም 2026 የማጠቃለያ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።   የፋኦ ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ማውሪዚዮ ማርቲና በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ የዘርፉን እድገት ለማረጋገጥ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ከምርምር ማዕከላት ጋር በየዕለቱ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል። በግብርናና በምግብ ሥርዓት ዘርፍ ኢንቨስትመንትን ለማደራጀትና ለማስፋፋት በትኩረት መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል። ዘርፉ የተለያዩ አቅሞችንና ሀብቶችን በተለየ መንገድ ማቀናጀትን እንደሚጠይቅ ገልጸው፣ በርካታ እድሎች ያሉት መሆኑንም አመላክተዋል። ፋኦ ተልእኮውን መሰረት በማድረግ በዩኒቨርሲቲዎች፣ በምርምር ተቋማትና በኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች መካከል እንደ ድልድይና አቅም ማስፈጸሚያ መሣሪያ ሆኖ እንደሚያገለግል ተናግረዋል። የእውቀት ልውውጥ የሚደረግባቸው ቀጣይነት ያላቸው መድረኮችን ማዘጋጀት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። በተጨማሪም የምርምር ውጤቶችን በፍጥነት ወደ ተግባርና ወደ ኢንቨስትመንት መቀየር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። እነዚህን እንቅስቃሴዎች በተቀናጀ አካሄድ ማስተዳደር ከተቻለ በዘርፉ የተቀመጡ ግቦችን ማሳካት እንደሚቻል ገልጸዋል። ገንዘብ አስፈላጊ ቢሆንም፣ የሰው ኃይል አቅምና ግልጽ የሆነ የአፈጻጸም መንገድ ከሌለ በቂ እንደማይሆን አስረድተዋል። በቂ ገንዘብ የተመደበላቸው አስፈላጊ ፕሮጀክቶች የታሰበውን ውጤት ሳያመጡ የቀሩት በገንዘብ እጥረት ሳይሆን በሰው ኃይል አቅም ማነስ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። በመሆኑም የፋይናንስና የሰው ኃይል አቅምን ውጤታማ በሆነ መንገድ ማቀናጀት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። አፍሪካ በርካታ እድሎች ያሏት አህጉር መሆኗን ጠቅሰው፣ ከዓለም ባንክና ከዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) ጋር በመተባበር አስፈላጊ ፕሮጀክቶች ተቀርጸው ወደ ሥራ መግባታቸውን አብራርተዋል። በመሆኑም በግብርናና በምግብ ሥርዓት ዘርፍ በጋራ መሥራትና የሙከራ ፕሮጀክቶችን ወደ ተቀናጀና ዘላቂ የሥራ አካሄድ መቀየር እንደሚገባ አሳስበዋል። ጥረቶች አንድ ጊዜ ብቻ ተከናወነው በሚያበቁ ፕሮጀክቶች ላይ ሳይወሰኑ፣ በቀጣይነት የሚሰፉና ዘላቂ ውጤት የሚያመጡ መሆን እንዳለባቸውም ተናግረዋል። የአፍሪካ ሳይንስና ኢኖቬሽን ፎረም ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽንን በመጠቀም በአፍሪካ የምግብና ግብርና ሥርዓት ውስጥ ያሉ ተደራራቢ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የተዘጋጀ አህጉራዊ መድረክ ነው። በተጨማሪም ፎረሙ ምርታማነትን በመጨመር፣ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን በማድረግ እና የግልና የመንግሥት ኢንቨስትመንቶችን በማሳደግ አህጉራዊ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ላይ ያተኮረ መሆኑንም አስገንዝበዋል።   በዓለም ባንክ የግብርና ዋና ኢኮኖሚስት እና የአፍሪካ የግብርና ልማት ፕሮግራም (CAADP) የልማት አጋሮች ማስተባበሪያ ቡድን ሊቀመንበር ሚዮ ታካዳ በበኩላቸው፣ የአለም ባንክ አግሪ ኮኔክት በተባለው ፕሮጀክቱ አማካይነት አርሶ አደሮችን እየደገፈ እንደሚገኝ ገልጸዋል ፕሮጀክቱ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ መካከል ትስስር በመፍጠር ከተለያዩ የልማት አጋሮች የሚሰጡ የተናጠል ድጋፎችን በማቀናጀት የጋራ አቅጣጫ እንዲኖር ማስቻሉን ተናግረዋል።   ለአርሶ አደሮች ፈጠራን ለማስፋፋት የሚያስችል የረጅም ጊዜ የፋይናንስ አቅርቦትን የሚያደናቅፉ ከአቅርቦትና ከፍላጎት ጎን የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን ፕሮግራም ኦፊሰር ዳንኤል ሂጊንስ ናቸው። ይህም የግሉ ዘርፍ በቀጣይነት ድጋፉን እንዲረከብና በረጅም ጊዜ ውስጥ ፋይናንስ ማድረጉን እንዲቀጥል የሚያበረታታ መሆኑን ጠቁመዋል።
ብሪክስ ከአፍሪካ ጋር ያለውን የኢንዱስትሪ ትብብር ለማጠናከር አዳዲስ አሰራሮችን ይፋ አደረገ
Oct 29, 2026 184
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 19 /2019 (ኢዜአ)፦ ብሪክስ ከአፍሪካ ጋር ያለውን የኢንዱስትሪ ትብብር ለማጠናከር አዳዲስ አሰራሮችን ይፋ አድርጓል። ይህ የተገለጸው በሞስኮ በተካሄደው በሶስተኛው የሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ “የብሪክስ መድረክ ለሩሲያ-አፍሪካ የንግድ ትብብር እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ነው። የሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ማክሲም ረሼትኒኮቭ፣ ብሪክስ ለአፍሪካ ሀገራት ክፍት የሆነ ገበያ ከመሆኑም በላይ የቴክኖሎጂ፣ የኢንዱስትሪ ምርቶች እና የኢንቨስትመንት አቅርቦት ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ ገልጸዋል። እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ እየተዘጋጁ ካሉ አዳዲስ አሰራሮች መካከል የልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ማህበር እና የእህል የንግድ ልውውጥ (Grain Exchange) ይገኙበታል። በተጨማሪም የአባል ሀገራቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴሮች የኢንዱስትሪ ዲጂታላይዜሽን እና የቴክኖሎጂ ትብብር ማዕቀፍ እንዲዘረጋ ሀሳብ ማቅረባቸውን የቲቪ ብሪክስ ዘገባ ያመለክታል። ረሼትኒኮቭ አክለውም፣ ብሪክስ አሁን ላይ ትብብሩን ከፖለቲካዊ ውይይት ባለፈ ወደ ተጨባጭ ውጤት የሚቀይሩ ፕሮግራሞችን እያዘጋጀ እንደሚገኝና የመንግስታት እንቅፋቶችን በማስወገድ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጠይቀዋል። የንግዱ ማህበረሰብ ለአሰራሮች ውጤታማነት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት አመልክተዋል። በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት እና ሩሲያ መካከል የኢንዱስትሪ ትብብር ዞን መፈጠሩ ለሁለቱ ወገኖች ትስስር መጠናከር የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት በስብሰባው ላይ ተመላክቷል። በብሪክስ ማዕቀፍ ውስጥ በመሰረተ ልማት፣ በትራንስፖርት፣ በሎጂስቲክስ፣ በኃይል እና በሳይበር ደህንነት ዘርፎች ውጤት የሚያመጡ ፕሮጀክቶችን በጋራ መተግበር እንደሚገባ ተመላክቷል። የብሪክስ (BRICS) አባል ሀገራት ነጻ የሆነ የክፍያ ስርዓት የመዘርጋት፣ ኢንቨስትመንትን የሚስቡ አሰራሮችን የመፍጠር እና የኢንዱስትሪ ትብብራቸውን የማስፋት ስራ እያከናወኑ እንደሚገኝም እንዲሁ። የስብሰባው መሪና የሩሲያ ሳይንስ አካዳሚ የአፍሪካ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ኢሪና አብራሞቫ በአሁኑ ወቅት ከ37 ሺህ በላይ የአፍሪካ ተማሪዎች በሩሲያ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ እንደሆኑ መግለጻቸውን የቲቪ ብሪክስ መረጃ ያመለክታል።
ሐተታዎች
የአፍሪካ የለውጥ ብርሃን፤ የላቀ የዲፕሎማሲ ማዕከል- አዲስ አበባ 
Nov 2, 2026 30
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ የለውጥ ብርሃን፤ የላቀ የዲፕሎማሲ ማዕከል- አዲስ አበባ በሚፍታ ሽፈራ ከተማ የሰዎች የኑሮ ማዕከል፣ የታሪክና የባህል መገለጫ፣ የማኅበራዊ ግንኙነትና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መድረክ ነው። የከተማ ልማትም የሚለካው በነዋሪዎች የኑሮ ጥራት፣ በሚፈጥረው የኢኮኖሚ ዕድል፣ በሚጠብቀው ታሪካዊ ማንነትና በሚያጠናክረው ማኅበራዊ ትስስር ጭምር ነው። ይህንን እውነታ በተግባር እያሳዩ ካሉ ጥቂት የዓለም ከተሞች መካከል አዲስ አበባ አንዷ ናት። በቀደሙት ዓመታት አዲስ አበባ ከስሟ፣ ከታሪካዊ ክብሯና ከነዋሪዎቿ የኑሮ ፍላጎት ጋር የማይጣጣሙ በርካታ ችግሮች ይታዩባት ነበር። የአካባቢ ብክለት፣ የአረንጓዴ ስፍራ እጥረት፣ የወንዝ ዳርቻዎች መበከልና የመንገድ መጨናነቅ ከሚጠቀሱት ችግሮች መካከል ነበሩ። ከለውጡ በኋላ በገበታ ለሸገር የተጀመረውና በኋላም ወደ ገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ የተስፋፋው የልማት አቅጣጫ የከተማዋን ገጽታ ለመቀየር አዲስ መነሳሳት ፈጥሯል። የዚህ ለውጥ መሠረት ከመደመር እሳቤ ጋር ይገናኛል። መደመር የተለያዩ ሀብቶችን፣ አቅሞችን፣ ባህሎችንና ፍላጎቶችን በማቀናጀት ለጋራ ጥቅም ማዋል ነው። በዚህ እሳቤ ልማት የሰውን ክብር የሚያስጠብቅ፣ ሁሉንም የሚያሳትፍና ለጋራ ተጠቃሚነት የሚያበቃ ነው። በዚህ አቅጣጫ ከተከናወኑት የልማት ሥራዎች መካከል የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች ይጠቀሳሉ። የኮሪደር ልማት መንገዶችን ከማስፋትና ከማስዋብ ባለፈ፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶችን፣ የአረንጓዴ ስፍራዎችን፣ የመዝናኛ ማዕከላትንና የንግድ ቦታዎችን በአንድ ላይ ማቀናጀት የቻለ ነው ። ይህም የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የነዋሪዎችን፣የንግድ እንቅስቃሴና የማኅበራዊ ተግባቦት ዕድል አሳድጓል። በተመሳሳይ የወንዝ ዳርቻ ልማት የተፈጥሮ ሀብትን ከሕዝብ ጥቅም ጋር የሚያቀናጅ ግዙፍ የልማት ሥራ ነው። የተበከሉና በተለያዩ ችግሮች የተጎዱ የወንዝ ዳርቻዎችን ወደ አረንጓዴ መዝናኛ ስፍራዎች፣ የስፖርት ማዕከላት፣ የንግድና የቱሪዝም መዳረሻዎች የመቀየር ጥረት የአካባቢ ጥበቃንና የማኅበራዊ ጥቅምን አብሮ አስተሳስሯል። መዲናዋን እየቀየሩ ያሉ ሁለገብ የልማት ሥራዎች የመደመር የእይታ አድማስ በተግባር ያሳዩ ናቸው። የተለያየ አቅም፣ እውቀትና ሀብት በማቀናጀት የተከናወኑት እነዚህ ሥራዎች፤ የከተማዋን ነባር ባህላዊና ታሪካዊ እሴቶች ከዘመናዊ ግንባታ ጋር በማስማማት ዘላቂ የልማት ውጤት እንዲመዘገብ አስችለዋል። የዘመናዊ መሠረተ ልማቶች መዘርጋት፣ የትራፊክና የመንገድ መጨናነቅ መቃለል እንዲሁም የዲጂታልና የተቀናጁ አገልግሎቶች መስፋፋት የነዋሪዎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴና የኑሮ ዘይቤ ፈጣንና ቀልጣፋ አድርጎታል። የተዋቡ አረንጓዴ ስፍራዎች፣ የወንዝ ዳርቻ መዝናኛዎች፣ እና የታደሱ ታሪካዊ ቅርሶች አዲስ አበባን ዓለም አቀፍ ተደራሽነት ያላቸው የኮንፈረንስና የዕረፍት ጊዜ መዳረሻዎች አድርገዋታል። ይህም የቱሪዝም ፍሰቱን በእጅጉ በማሳደግ ለከተማዋ ኢኮኖሚ እጅግ አበረታች ፋይዳ እያስገኘ ይገኛል። አዲስ አበባ የብዙ ብሔር፣ ቋንቋ፣ ባህልና እምነት መገናኛ ናት። የከተማ ልማት ይህንን ብዝሃነት የሚያከብር፣ የተለያዩ ማኅበረሰቦችን የሚያገናኝና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያጠናክር በመሆኑ፤ መዲናዋ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በጋራ የሚገናኙባቸው ደማቅ መድረክ ሆናለች። የእነዚህ ሁሉ የልማት ጥረቶች ተጨባጭ ውጤት በዓለም አቀፍ መድረክም ታላቅ ዕውቅና እያገኘ ነው። አዲስ አበባ የዘንድሮውን የ2026 የዓለም ከተሞች ቀን “የሸንሃይ አዋርድ” (Shanghai Award) ሽልማት ማሸነፍ መቻሏ፤ በመዲናዋ የተተገበረው የሰው ተኮር ልማት እይታ፣ የአካባቢ ጥበቃ ጥረት እና የነዋሪዎች የኑሮ ጥራት መሻሻል ምን ያህል የላቀ ደረጃ ላይ እንደደረሰ የሚያረጋግጥ ትልቅ ታሪካዊ ማሳያ ነው። ይህ ሽልማት የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ይበልጥ እንዲቀጥሉ፣ አካታችነት እንዲጠናከር እና የነዋሪዎች ሁለገብ ተጠቃሚነት በዘላቂነት እንዲረጋገጥ የሚያደርግ ነው። አዲስ አበባ የተያያዘችው ሁለገብ የልማት እንቅስቃሴ የመላው አፍሪካ መዲናነቷን ክብር በላቀ ደረጃ የሚያጸና ነው። ይህም የአፍሪካውያንን ታሪካዊ ኩራት ከማደስ ባለፈ መዲናዋ የአህጉሪቱ የእድገትና የለውጥ ተምሳሌት ሆና እንድትቀጥል አስችሏታል። ይህ ፈጠራ የታከለበትና አካታች የልማት ጉዞ መዲናዋ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተጽዕኖ ፈጣሪነትና የከበረ የዲፕሎማቲክ ማዕከልነት ድርሻ በጽኑ መሠረት ላይ የጣለ ነው።
ከውበት ባሻገር
Oct 29, 2026 228
ከተሞች የሕዝብ መኖሪያ ብቻ ሳይሆኑ የኢኮኖሚ እድገት፣ የማኅበራዊ ትስስር፣ የፈጠራና የቴክኖሎጂ ማዕከላት ናቸው። የከተሞች ልማትና ዘመናዊ አሰራር የአንድን አገር ህዝብ የኑሮ ደረጃ፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴና የወደፊት የልማት አቅጣጫ የሚወስን ነው። በመሆኑም የከተሞች ልማት ከውበት ባሻገር የዜጎችን የኑሮ ደረጃ የማሻሻልና ዘላቂ ልማትን የማረጋገጥ ጉዳይ ሆኖ ይወሰዳል። በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ የከተማ ልማት መሰረታዊ ለውጥ፣ እድገትና ማንሰራራት የታየበት መሆኑን መናገር ይቻላል። ከአፍሪካ መዲና እና የዓለም የዲፕሎማቶች ማእከል ከሆነችው አዲስ አበባ የጀመረው የኮሪደር ልማት ሌሎች ከተሞችንም አዳርሷል። የከተሞች የኮሪደር ልማት ከጅግጅጋ እስከ ወለጋ፣ ከሀረር እስከ ባህር ዳርና ጎንደር፣ ከሰመራ እስከ ጋምቤላ፣ ከሀዋሳ እስከ አሶሳ፣ ከጅማ እስከ አዳማና ነቀምት፣ በአርባ ምንጭ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሆሳእና እና ሌሎችም ከተሞች ተስፋፍቷል። የከተሞቹ ልማት በተቀናጀ የከተማ ፕላን የሚመራ የወንዝ ዳር ልማትን ጨምሮ የእግረኛና የሳይክል መንገዶች፣ የአረንጓዴ ስፍራዎች፣ የመዝናኛ ቦታዎችና የስፖርት ማዘውተሪያዎችን በማካተት እየተከናወነ ይገኛል። ከትራንስፖርት፣ ከውሃና ፍሳሽ አገልግሎት፣ ከመብራት፣ ከቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መሰረተ ልማቶች ጋር ተሰናስሎ እየተገነባ ነው። በመሆኑም የስማርት ከተሞች ግንባታ ለነዋሪዎች አገልግሎት አሰጣጥ መሳለጥ ብሎም ወንጀልን ለመከላከል አስችሏል። የከተማ ወንዞችን በማልማት፣ አረንጓዴ ስፍራዎችን በማስፋፋትና ለእግረኞችና ለሳይክል ተጠቃሚዎች ምቹ መንገዶችን በመገንባት የተሻለ ህይወት እንዲመሩና እንዲኖሩ እየተደረገ ነው። በልማቱ የአካል ጉዳተኞች፣ የአረጋውያን፣ የሕፃናትና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ወገኖችን ማእከል ያደረገ ሰው ተኮር ብሮጀክት መሆኑም ይታወቃል። የከተማና የገጠር ኮሪደር ልማትን በማሰናሰል በምርት አቅርቦት፣ በገበያ ትስስር፣ በትራንስፖርትና ሌሎችም አገልግሎቶች የተገናኙ እንዲሆኑ እየተደረገም ይገኛል። የከተሞችና የገጠር ልማት ትስስሩም የኢኮኖሚ እድገትን፣ እኩልነትንና የጋራ ተጠቃሚነትን፣ የአካባቢ ጥበቃንና ሌሎችንም መሰረት ያደረገ መሆኑም ይታወቃል። በመሆኑም የኢትዮጵያ የከተማ ልማት ከውበትና ምቾትም የተሻገረ ሀገር የመገንባት ስትራቴጂ ስለመሆኑ መናገር ይቻላል። የ2026 ዓለም አቀፍ የከተሞች ቀን “Regenerating the City: Adequate Housing for All” “ከተሞችን ማደስ፤ የተሟላ መኖሪያ ቤት ለሁሉም” በሚል መሪ ሃሳብ የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም በመላው ዓለም ይከበራል። የክብረ በዓሉ መልእክትም የከተሞችን የወደፊት አቅጣጫ ከሰው ልጆች ደህንነት፣ ከአካባቢ ጥበቃ፣ ከኢኮኖሚያዊ እድገትና ከሁሉን አቀፍ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ጋር በማስተሳሰር ነው። ከዚህ አንፃር የኢትዮጵያ የከተማ ልማት ከማደስና ዘመናዊ አድርጎ ከመስራት ባሻገር የዜጎችን ህይወት የመለወጥ ዓላማን የሰነቀ መሆኑ ይታወቃል።  
የመኸር በረከት፤ የምግብ ሉዓላዊነት መሰረት
Oct 29, 2026 235
ኢትዮጵያ በአራቱ ወቅቶች የተሸለመች፣ በእርሻና በተፈጥሮ በረከት የተባረከች ምድር ናት። ከእነዚህ ወቅቶች መካከል ደግሞ "መኸር" ለአርሶ አደሩና ለአጠቃላይ ሕዝቡ ልዩ ትርጉም ያለው፣ የድካም ውጤት የሚታይበትና የተስፋ ፍሬ የሚለቀምበት ወርቃማ ወቅት ነው። የመኸር በረከት፤ የምግብ ሉዓላዊነት መሰረት ስለመሆኑ መናገር ይቻላል። የአረንጓዴው የመስክ ገጽታ ወደ ቢጫና ወርቃማ ቀለም በሚቀየርበት በዚህ ጊዜ፣ የኢትዮጵያ ገበሬዎች የደስታ፣ የሥራና የምስጋና መንፈስ ይላበሳሉ። የዛሬው የመኸር ወቅት ከቀደሙት ዓመታት የተለየ ትርጉምና ሀገራዊ ተልእኮ ይዞ መጥቷል። ይህ ወቅት የምግብ እጥረትና ጥገኝነትን በማስወገድ፣ የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥና የሀገርን ክብርን የመመለስ አዲስ የታሪክ ምእራፍ መነሻ ሆኗል። የመኸር ወቅት ሲጠባ ከሰማይ የሚወርደው የክረምት ደመና አልፎ አየሩ መለስ ይላል፤ ፀሐይ በደማቅ ብርሃኗ መስኩን ታበራለች። ክረምቱን ሙሉ በዝናብና በጭቃ ውስጥ ደክሞ፣ ዘርቶና አለስልሶ ያሳደገው አርሶ አደር የድካሙን ፍሬ ለማየት አይኖቹ ወደ ማሳው ያማትራሉ። በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች የመኸር አዝመራ የሥራ ወቅትን ብቻ ሳይሆን የማህበረሰባዊ ትስስርን ያመለክታል። በማለዳ ከወፎች ጫጫታ ጋር የሚነቃው አርሶ አደር ማገዶውንና ማጨጃውን ይዞ ይሰማራል። በአብዛኛው ወንዶች በማጨድ፤ ሴቶችና ህፃናት ደግሞ የታጨደውን ሰብል በስርዓት በማሰርና በመከመር ይተባበራሉ። ይህ የመደመር፣ የህብረትና የደቦ አሰራር የኢትዮጵያውያን የወል ጥበብና የመረዳዳት እሴት መግለጫ ነው። በመኸር ወቅት ትልቁ ፈተና እና ትኩረት ሰብልን ወቅቱን ጠብቆና በጥንቃቄ መሰብሰብ ነው። የመኸር አዝመራ በሰዓቱ ካልተሰበሰበ ያልተጠበቀ ዝናብ መና ሊያስቀረው ይችላል። በመሆኑም አርሶ አደሮች ጊዜ ሳይሰጡ አዝመራቸውን በፍጥነትና በብቃት ለመሰብሰብ ሌሊትና ቀን ይሰራሉ። አዝመራን ያለብክነት መሰብሰብ የምርት ጥራትን ጠብቆ ወደ ጎተራና ወደ ገበያ ለማድረስ ወሳኝ ነው። የሰብል ምርት ከማጨድ እስከ ጎተራ ገቢ እስከሚሆን ድረስ የሚደረግ የጥራትና የፅዳት ጥንቃቄ፣ በድካም የተገኘውን ምርት ከብልሽትና ከብክነት ይከላከላል። ይህም የአርሶ አደሩን የብዙ ወራት ላብና ሀገራዊ ሀብትን ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም ያስችላል። በመሆኑም አሁን ላይ በዘመናዊ ማሽነሪዎች (ኮምባይነር ሃርቨስተር) ሰብልን የመሰብሰብ ልምድ እያደገ በመሄዱ ሲታጨድም ይሁን ሲወቃ ብክነትን ማስቀረት አስችሏል። በኢትዮጵያ ግብርና ልማት አዲስ የታሪክ ምእራፍ የከፈተው የስንዴ ልማትና ምርታማነት መሆኑ ይታወቃል። የበጋ መስኖን ጨምሮ በመደበኛ ወቅቶች ስንዴን በስፋት በማምረት ከሀገር ውስጥ ፍጆታ አልፎ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ተችሏል። በዚህም ምርታማነትን የማሳደግና ከተረጅነት የመውጣት ጥረት ስኬታማ እየሆነ ይገኛል። የስንዴ ምርት መጠን ከፍተኛ ማንሰራራት በማሳየቱ የዜጎች የምግብ ዋስትና መሰረት ከመሆን አልፎ የጎረቤት አገራትም ሲሳይ ሆኗል። በመሆኑም ኢትዮጵያን የምስራቅ አፍሪካ የእህል ጎተራ የማድረግ ርዕይ እውን እያደረገ ይገኛል። ለዘመናት "የረሃብና የእርዳታ እጅ ዘርጊ" ተደርጋ ትታይ የነበረችው ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ አምርታ በምግብ ፍጆታ ራሷን የምትመግብ መሆኑን በተግባር እያሳየች ትገኛለች። በምግብ ራስን መቻል ማለት የሀገርን ነፃነትና ክብር ማስከበር ነው። በእርዳታ እህል ላይ የነበረውን ጥገኝነት በማስቀረት ሀገራዊ ሰብዓዊ ክብርና ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል። የታጨደው ሰብል ተወቅቶ ወደ ጎተራ ሲገባ፤ ከአርሶ አደሩ አልፎ በከተሞች የምርት አቅርቦት ሲበራከት የገበያ መረጋጋትና የምግብ ዋስትና መሰረት እየተጠናከረ ይሄዳል። ለዚህም ነው የመኸር በረከት፤ የምግብ ሉዓላዊነት መሰረት የሚሆነው። የምርት ማደግና ሰብልን ያለብክነት መሰብሰብ ቀጥታ ወደ የቤተሰብ ብልጽግና ይተረጎማል። አርሶ አደሩ ምርቱን ለራሱ ከተጠቀመ በኋላ ትርፉን ለገበያ በማቅረብ፡ ቤተሰቡን ያስተዳድራል፣ የልጆቹን ትምህርትና ጤና ያሟላል። የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን፣ ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶችንና የንግድ ኢንቨስትመንቶችን ለመስራት የሚያስችል የኢኮኖሚ አቅም ይፈጥራል። ገጠሩ ክፍል ከዕለት ጉርስ ፍለጋ ወጥቶ ወደ ሀብት ፈጣሪነትና ወደ አጠቃላይ ብልጽግና ይሸጋገራል። በመሆኑም የመኸር ወቅት የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ፅናት፣ የላብና የህብረት ጥረታቸው በውጤት የሚደመደምበት ወርቃማ ጊዜ ነው።  
አዋሽና ትሩፋቱ
Oct 29, 2026 236
አዋሽ ሀገሩን ተሻግሮ ላያልፍ መሃላ የፈፀመ ይመስላል። አዋሽ ሀገር ወዳድ፣ የሀገር ቤት ወንዝ፣ አልሚ እና ጠቃሚ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። የአዋሽ ወንዝ ለኢትዮጵያ ከውሃ ሀብት እስከ መስኖ ግብርና፣ ከኢንዱስትሪ እስከ አረንጓዴ ልማት የሚያገለግል የሀገር ባለውለታ ነው። አዋሽ የግብርና ምርት ማሳደጊያ፣ የኢንዱስትሪ መደገፊያ፣ የሰዎች ኑሮ መሠረትና የኢትዮጵያ የልማት አቅም ማሳያ መሆኑ ይታወቃል። በተለይም የዝናብ እጥረት ለሚገጥማቸው አካባቢዎች የመስኖ ልማትን በማስፋፋት፣ የምግብ ምርትን ለማሳደግና የአካባቢውን ኢኮኖሚ በማነቃቃት ረገድ የማይተካ ሚናውን እየተወጣ ይገኛል።     በግምት 1 ሺህ250 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የአዋሽ ወንዝ የውሃ ሀብቱ በአንድ አካባቢ ብቻ የተገደበ አይደለም። ከከፍተኛ ቦታዎች እስከ ደረቅና ከፊል ደረቅ የስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች በመዝለቅ ፈላጊዎቹን ያገለግላል። የውሃና የኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያመለክተው የአዋሽ ተፋሰስን ስፋት ወደ 110 ሺህ ካሬ ኪሎ ሜትር፣ አማካይ ዓመታዊ የውሃ ምርቱን ደግሞ 4 ነጥብ 9 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ያደርሰዋል።   የአዋሽ ወንዝ በተለይም የአፋርና የተፋሰሱ ዝቅተኛ አካባቢዎች በመስኖ ለሰብል ልማት፣ ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት እንዲሁም ለእንስሳት መኖ ምርት ያገለግላል። በወንዙ ተፋሰስ ከተገነቡት የመስኖ ፕሮጀክቶች መካከል የወንጂ፣ የመተሃራ፣ የቀሰምና የተንዳሆ መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ይጠቀሳሉ። እነዚህ ፕሮጀክቶች የግብርና ምርትን ከዝናብ ጥገኝነት ለማላቀቅ፣ በዓመት በተለያዩ ወቅቶች በማምረት ከችግርና ድህነት ለመውጣት እያገዙ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ የስንዴ ምርትን በመስኖ በማልማት የምግብ ዋስትናዋን ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት አዋሽ አለኝታነቱን አሳይቶ እየተሰራበት ነው። በተጨማሪም ለስኳር ልማት፣ ለጥጥ፣ ለአትክልትና ለፍራፍሬ ምርት የአዋሽ ውለታ ከፍተኛ ነው። የአዋሽ ተፋሰስ ከግብርና ባሻገር ለኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ እድገት ወሳኝ ስፍራ ነው። በተፋሰሱ የሚገኙ የኢንዱስትሪ ተቋማት፣ የማምረቻ ዘርፎች፣ የስኳር ፋብሪካዎችና የከተማ ልማት ስራዎች አቅርቦት ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። እዎ እርግጥ ነው አዋሽ ውለታው ብዙ ነው፤ በታማኝነቱ የሚታወቅ ሀገር ወዳድ ወንዝ ነው። የወንዙ ተጠቃሚዎችም የከተማ ነዋሪዎችና ገበሬዎች ብቻ አይደሉም። በተለይ በወንዙ የታችኛው ተፋሰስ የሚኖሩ አርብቶ አደሮች ለእንስሳት፣ ለግጦሽ መሬትና ለኑሯቸው መሰረት ሆኖ ዘመናትን እያገለገለ ይገኛል። በመሆኑም የአዋሽ ጉዳይ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የአርብቶ አደሮች የኑሮ መሰረት ነው። ለተፈጥሮ ሃብትና ለዱር እንስሳት ጥበቃ፣ ለቱሪዝምና ለምርምር ጭምር አገልጋይ መሆኑንም መናገር ይቻላል። የአዋሽ ወንዝ ትልቅ የልማት አቅም ቢኖረውም፣ ይህን ሀብት በዘላቂነት ለመጠቀም መፍትሔ የሚሹ ተግዳሮቶችም አልጠፉም። ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ የከተማ ነዋሪዎችና አርብቶ አደሮች በተመሳሳይ የውሃ ሀብት ላይ ጥገኛ ስለሆኑ በድርቅ ወቅት የውሃ ክፍፍል ውስብስብ ይሆናል። ሌላው ደግሞ የአየር ንብረት ለውጥና የዝናብ መዛባት ሲከሰት የወንዙን ፍሰት ስለሚዛባ የድርቅና የጎርፍ አደጋ ሊያጋጥም ይችላል። እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ደግሞ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር፣ የጎርፍ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓትን ማጠናከር፣ የተፋሰስ ጥበቃ፣ የውሃ ቆጣቢ ቴክኖሎጂና የሕዝብ ተሳትፎ ወሳኝ ስለመሆኑ ይመከራል። የአዋሽ ወንዝን አቅም በሙሉ ለመጠቀም የሚያስፈልገው የውሃ ፕሮጀክቶችን መገንባት ብቻ አይደለም። የተገነቡትን መሠረተ ልማቶች በብቃት ማስተዳደር፣ የውሃ ብክነትን መቀነስ፣ የመስኖ መሬቶችን በተሻለ ቴክኖሎጂ ማልማትና የወንዙን የተፈጥሮ ሥርዓት መጠበቅም ያስፈልጋል። በተመሳሳይ የወንዙ የታችኛው ተፋሰስ ለሚገኙ ማህበረሰቦችና ለተፈጥሮ ሥነ-ምህዳር የሚያስፈልገው የውሃ መጠን መጠበቅ አለበት። የውሃ ሀብት ለአንድ የኢኮኖሚ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም በሚጠቅም መልኩ መመራት ይገባዋል።
ትንታኔዎች
ጦርነትን የማስቀረት ጥበብ (ዲተረንስ)
Oct 29, 2026 334
ጥቅምት 19/2019 (ኢዜአ) ፦ ጦርነትን የማስቀረት ጥበብ (ዲተረንስ) ጦርነትን በማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ጦርነቱ ሳይጀመር በማስቀረት የሚገኝ ድል ከሁሉ የላቀ ነው። ጥንታዊው የቻይና ጦር ስትራቴጂስት ሱን ዙ "ዘ አርት ኦፍ ዋር" በተሰኘው መጽሐፉ፣ ትልቁ የጦር ጥበብ ጠላትን ሳይዋጉ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደሆነ ጽፏል። በዚህም መፅሐፉ መቶ ጦርነትን አሸንፎ መገኘት የላቀ ጥበብ አይደለም፤ ምክንያቱም ድል መንሳት በራሱ የሰው ሕይወትና የአገር ሀብትን ያስከፍላልና። ይህ ሃሳብ በዘመናዊው የደህንነት ጥናት ጦርነትን የማስቀረት ጥበብ ወይም "ዲተረንስ" ተብሎ ይጠራል። የትርጉሙ ጭብጥም ጠላት ጥቃት ከመሞከር እንዲታቀብ የሚያደርግ እምነትን መፍጠር ነው። ጦርነትን የማስቀረት ጥበብ መሠረታዊ አመክንዮ ማንኛውም ወገን ጦርነት የሚጀምረው ከጦርነቱ የሚያገኘው ጥቅም ከሚከፍለው ዋጋ እንደሚበልጥ ሲያስብ ነው። ስለዚህ አንድ አገር የጥቃትን ዋጋ በበቂ ሁኔታ ካናረ፣ ጠላት ሒሳቡን ሲሰራ ጦርነት ኪሳራ ሆኖ ይታየዋል። ሮማዊው ወታደራዊ ጸሐፊ ቬጌቲየስ ከ1 ሺህ 600 ዓመታት በፊት በጻፈው መፅሓፍ የከተበው ታዋቂ አባባል ይህንኑ ይገልጻል። "ሰላምን የሚሻት ቢኖር ለጦርነት ይዘጋጅ" ይላል። ይህም በተለያዩ አስረጂ ጉዳዮች ሊዳሰስ ይችላል፤ የመጀመሪያው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ነው። የአየር መከላከያ፣ የመድፍና የሚሳይል አቅም፣ የታጠቁ ኃይሎችና የአየር ኃይል ብቃትን ይመለከታል። ሁለተኛው የሰለጠነ ወታደር ነው፤ ምክንያቱም መሳሪያ በብቁ እጅ ካልተያዘ ክብደት እንጂ ጉልበት አይሆንምና። ተከታታይ ስልጠና፣ ዲሲፕሊንና የዕዝ ሰንሰለት ያለው ሠራዊት ለጠላት ከሚታየው ቁጥር በላይ ግምትን ይፈጥራል። ሦስተኛው በቴክኖሎጂ የታገዘ የውጊያ ብቃት ነው፤ ይኸውም ስለላና የስለላ ድሮኖች፣ ሳይበር፣ የመገናኛና የመረጃ ሥርዓት እንዲሁም ትክክለኛ ኢላማን የመምታት አቅምን ያካትታል። በዘመናችን ጦርነት የሚወሰነው በመረጃ የበላይነት ጭምር ነው፤ ምክንያቱም ጠላቱን አስቀድሞ የሚያይ ወገን ሁልጊዜም አንድ እርምጃን ቀድሟል። ሌላኛው ደግሞ ብዙ ጊዜ የሚዘነጋው ተዓማኒነት ነው። አሜሪካዊው የስትራቴጂ ምሁር ቶማስ ሼሊንግ “Arms and Influence” በተሰኘው መጽሐፉ እንደሚያስረዳው፣ ጦርነትን የማስቀረት ጥበብ ወይም "ዲተረንስ" የሚሰራው አቅሙ ብቻ ሳይሆን ያንን አቅም የመጠቀም ፍላጎትና ቁርጠኝነት ጭምር ለጠላት ግልጽ ሲሆን ነው። ምስጢር ሆኖ የተቀመጠ ወይም በማሳየት ያልተረጋገጠ አቅም ጠላትን ሁለቴ ደጋግሞ እንዲያስብ ሊያደርገው አይችልም። ለዚህም ነው ወታደራዊ ልምምዶች፣ ሰልፎችና ግልጽ የመከላከያ ፖሊሲዎች የጥበቡ አካል የሆኑት። የቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን ልምድም ይህን ያሳያል፤ ሁለቱ ልዕለ ኃያላን አሜሪካና የቀድሞዋ ሶቪዬት ህብረት የጋራ ጥፋት የሚያስከትል የኒውክሌር አቅም ስለነበራቸው በቀጥታ ከመዋጋት ተቆጥበው በቃላት ጦርነት ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ አድርጓቸዋል። ኢትዮጵያም ለዚህ ጉልህ ታሪካዊ ምሳሌ አላት። በ1888 ዓ.ም. በዓድዋ አፄ ምኒልክ ከየአቅጣጫው የተሰበሰበውን ሕዝብ በአንድ ዓላማ አሰልፈው፣ እቴጌ ጣይቱንና ሌሎች የጦር መሪዎችን አስተባብረው ጣሊያንን በሚወስን ሁኔታ ድል አድርገዋል። ድሉ ከውጊያ ሜዳ ባሻገር ዲፕሎማሲያዊ ውጤትም ነበረው፤ በዚያው ዓመት በተፈረመው የአዲስ አበባ ውል ጣሊያን የኢትዮጵያን ነጻነት እንድታውቅ ተገደደች። ለሌሎች የአውሮፓ ኃያላንም ኢትዮጵያን መውረር ከባድ ዋጋ እንደሚያስከፍል ጠንካራ መልዕክት በመሆን ሌላ ጦርነትን ለማስቀረት አገለገለ። ይህ ጦርነትን የማስቀረት ጥበብ በተግባር የተፈተነ አቅሙ ታይቷል፣ ቁርጠኝነቱም ተረጋግጧል። አሁን ላይም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባህር አካባቢ ባላት ስትራቴጂያዊ አቀማመጥ ምክንያት ለውስጣዊና ለውጫዊ ጫናዎች ተጋላጭ ሀገር ናት። ሀገሪቷ የምትገኝበት መልክዓ ምድር በተለያዩ ግጭቶች የሚታወቅ ብቻም ሳይሆን የተለያዩ ኃያላን አገራት ጦር የሚገኝበት ቀጣና ነው። ይህንን ከግምት ባስገባ መልኩ የኢትዮጵያ መንግስት የመከላከያ ሠራዊቱን በማዘመን ረገድ ተጨባጭ እርምጃዎችን ወስዷል እየወሰደም ይገኛል። ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት አከባበር በዓል ላይ አየር ኃይሉን በማዘመን በ2030 ከአራተኛ ትውልድ ወደ አምስተኛ ለማሻገር እንደሚሰራ መናገራቸው ይታወሳል። አየር ኃይሉ አሁን ካለበት በዕጥፍ የማሳደግ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑንም አስረግጠው ተናግረዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር በራሱ ጠላት በኢትዮጵያ ላይ ጥቃትን ከመፈፀሙ በፊት ሁለቴና ሦስቴ እንዲያስብበት የሚያደርግ መሆኑን ማንሳቱ ግድ ይላል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ከቃል በላይ ለመሆኑ ማሳያ የሚሆነው ደግሞ አየር ኃይሉ ከዚህ ቀደም ከታጠቃቸው ዘመናዊ የውጊያ አውሮፕላኖች በተጨማሪ ኢትዮጵያ ትናንት 12 የሱ-35 4ኛ++ ትውልድ የጦር ጄቶችን ከሩሲያ ተረክባለች። በዚህም ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓለም ላይ በርካታ ሀገራት በሰላሙ ጊዜ አስፈላጊውን ዝግጅት ባለማድረጋቸው ምክንያት ችግር ሲፈጠር ለአደጋ ሲጋለጡ እንደሚታይ ጠቁመው፤ የኢትዮጵያን የአየር ክልል ላለማስደፈር በቂ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ የተረከበቻቸው የሱ-35 ኤርክራፍቶች በዓለም ላይ ካሉ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መካከል ግንባር ቀደም ናቸው። መሳሪያዎቹ ከአየር ወደ አየር እንዲሁም ከአየር ወደ ምድር ውጊያ የማካሄድ ከፍተኛ አቅም ያላቸውና በተግባር የተፈተኑ መሆናቸውን ገልጸዋል። በተለይም ከየትኛውም አቅጣጫ የሚቃጡ የክሩዝ ሚሳኤል ጥቃቶችን እስከ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት የመለየት (Detect) እና የማክሸፍ (Intercept) ብቃት እንዳላቸው አስረድተዋል። ይህንን የቴክኖሎጂ አቅም መገንባት ለሀገር ህልውና ወሳኝ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ቀደም ሲል የነበሩት የሱ-30 እና የአሁኖቹ የሱ-35 ተዋጊ ጄቶች የኢትዮጵያን የአየር ክልል በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚያስችሉ መሆናቸውን ተናግረዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የሱ-35 4ኛ++ ትውልድ የጦር ጄት ባለቤት ከሆኑ በጣት የሚቆጠሩ አገራት መካከል አትዮጵያ አንዷ መሆኗ ደግሞ ከራሷ ሉአላዊትንም ባለፈ ለአህጉሩ እና ለቀጣናው ሰላም መጠበቅ ወሳኝ ሚና ይኖራታል ማለት ነው። ምክንያቱም የሱ-35 4ኛ++ ትውልድ የጦር ጄት በዓለም ላይ እጅግ ከፍተኛ የአየር ላይ እንቅስቃሴ ማድረግ የሚችል ዘመናዊ ተዋጊ ጀት ነው። የጀቱ ሞተሮች አቅጣጫቸውን መቀየር የሚችሉ (3D Thrust Vectoring Nozzles) በመሆናቸው አየር ላይ ባልተለመዱ ማዕዘኖች እና ፍጥነቶች እንዲንቀሳቀስ ያስችሉታል። የሩሲያ አየር ኃይል ከሚጠቀማቸው እጅግ ዘመናዊ እና አደገኛ የጦር ጄቶች መካከል አንዱ ነው። የዚህ ጀት መገለጫ እጅግ ዘመናዊና ተዋጊ በመባል የሚታወቅ ሲሆን የ5ኛ ትውልድ ቴክኖሎጂ የተቀላቀለበት ስለመሆኑም ይነገራል። በሰአት 2 ሺህ 400 ኪ.ሜ የመብረርና ያለተጨማሪ የነዳጅ ታንከርም 3 ሺህ 600 ኪሎ ሜትር መብረር የሚችለው ተዋጊ ጀት በአንድ ጊዜ እስከ 30 ኢላማዎችን የመከታተል እና 8ቱን በአንድ ጊዜ የመምታት አቅም አለው። ራዳሩን ሳያበራ (ምንም ዓይነት የራዳር ሞገድ ሳይለቅ) በኢንፍራሬድ/ካሜራ (IRST) አማካኝነት ጠላትን በድብቅ እስከ 80 ኪ.ሜ ርቀት ድረስ መከታተል ይችላል። የጠላት ራዳሮችን እና ሚሳይሎችን በመረበሽ (Jamming) ጄቱን ካልተጠበቀ ጥቃት ይከላከላል። የሩሲያ አየር ኃይል ከሚጠቀማቸው እጅግ ዘመናዊ እና አደገኛ የጦር ጄቶች መካከል አንዱ ነው። የዚህ ጀት መገለጫ እጅግ ዘመናዊና ተዋጊ በመባል የሚታወቅ ሲሆን የ5ኛ ትውልድ ቴክኖሎጂ የተቀላቀለበት ስለመሆኑም ይነገራል። ለዚህም ነው በሩሲያ በተደረገው የጦር ጀቶቹ ርክክብ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሀገራችንን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የምናደርገው ሁለንተናዊ ጥረት ዛሬ ሌላ አዲስ ምዕራፍ ላይ ደርሷል ያሉት። ኢትዮጵያ በመከላከያ ኃይል እያደረገች ያለው ዝግጁነት ጥቃትን ቀድሞ ማስቀረት የሚያስችላትን አቅም የገነባች መሆኑንም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የየብስ፣ የአየርና የባህር ኃይሎች በሳተላይትና በዲጂታል የመገናኛ መረቦች እንዲተሳሰሩና እንደገና እንዲደራጁ መደረጉም ጠላት ሁለቴ እንዲያስብ የሚያደርግ ነው። ቴክኖሎጂን የሚጠቀም ብቁና ጠንካራ ሠራዊት የስለላ፣ የትክክለኛ ጥቃትና የፈጣን ምላሽ አቅምን ስለሚጨምር የአየር ክልልን የመጠበቅ ችሎታን ያሳድጋል። ይህ ሁሉ አንድ ላይ ሲታይ ኢትዮጵያን በቀላሉ ለማጥቃት እንደማይቻል የሚያስተላልፈው መልዕክት የጎላ ነው። እውነተኛ ድል ጥይት ሳይተኮስ በሚገኝ ሰላም ይረጋገጣል!!! የሚባለውስ ለዚህ አይደል!
የኢትዮጵያ ጽኑ ሉዓላዊነትና የቀጣናው ዋስትና- ዘመናዊ ጄቶች የታጠቀው አየር ኃይል
Oct 29, 2026 285
በለይኩን አሰፋ ትልቅ ሕዝብ፣ትልቅ ሀገርና ታላቅ ራዕይ ሰማይ ወሰን የሌለው የተፈጥሮ ስፋት ቢሆንም፣ ለአንድ ሀገር ግን የሉዓላዊነት፣ የደኅንነትና የብሔራዊ ጥቅም አካል ነው። በዚህ ሰማይ ላይ የሀገርን ክብር ለመጠበቅ፣ የሕዝብን ደኅንነት ለማረጋገጥና የውጭ ስጋቶችን ለመከላከል የቆመው የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሀገሪቱ የመከላከያ ሥርዓት ወሳኝ አካል ነው። አንድ ሀገር ሉዓላዊነቷን በምድር ላይ ብቻ አትጠብቅም። የአየር ጠፈሯን መጠበቅ፣ ከድንበሯ በላይ የሚንቀሳቀሱ ስጋቶችን መከታተልና ለሀገራዊ ደኅንነት የሚያስፈልገውን የአየር የበላይነት ማረጋገጥ የዘመናዊ መከላከያ አቅም ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው። በዚህ የብሔራዊ ደኅንነት ምሰሶ ውስጥ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የራሱ የሆነ ታሪክ፣ የተለየ ተልዕኮና የረጅም ዘመን የአገልግሎት ልምድ አለው። ከታሪካዊ አመሠራረቱ ጀምሮ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከአውሮፕላኖችና ከወታደራዊ መሣሪያዎች የበለጠ ትርጉም ይዞ ቆይቷል። ከጀግንነት፣ ከሙያዊ ብቃትና ከሀገር ፍቅር መርህ ጋር የተያያዘ ተቋም ሆኖ በተለያዩ ዘመናት የሀገሪቱን የአየር ደኅንነት ለማስጠበቅ ተልዕኮውን ተወጥቷል። የዚህ ተቋም ታሪክ የሚዘከረው በተከናወኑ ዘመቻዎች ብቻ ሳይሆን፣ ለሀገር ጥቅም በተከፈሉ መሥዋዕትነቶች፣ በተገነባው ሙያዊ ልምድና ከትውልድ ወደ ትውልድ በተላለፈው የአገልግሎት መንፈስ ጭምር ነው። ዛሬ የዓለም ወታደራዊ አሠራር በፍጥነት እየተለወጠ ባለበት ወቅት፣ የአየር ኃይል አቅም በአውሮፕላኖች ብዛት ብቻ አይለካም። የራዳርና የክትትል ሥርዓቶች፣ የመረጃ ልውውጥ፣ የአየር መከላከያ፣ የሰው ኃይል ሥልጠና፣ የጥገናና የቴክኒክ ብቃት እንዲሁም የተቀናጀ የውጊያ አሠራር የአቅሙ ወሳኝ መለኪያዎች ሆነዋል። ታዲያ የኢትዮጵያ አየር ኃይልም በየጊዜው ከሚለዋወጡት ዓለም አቀፍ የጂኦፖለቲካ እና የቴክኖሎጂ እድገቶች ጋር አብሮ በመጓዝ አሁን ላይ ሰፊና ጥልቅ የሆነ የዘመናዊነት ሽግግር እያደረገ ይገኛል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከተካሄደው ሀገራዊ የሪፎርም ሂደት፣ ለአየር ኃይሉ መሰረታዊ የላቀ ጥንካሬ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል። የመደመር መንግሥት ለአየር ኃይሉ መጠናከር እያበረከተ ያለው የቴክኖሎጂ፣ የመሰረተ ልማት እና የሰለጠነ የሰው ኃይል ግንባታ ድጋፍ ተቋሙን በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ተፅዕኖ ፈጣሪ እና ዘመናዊ የጦር ኃይል አድርጎታል። የአየር ኃይሉ የዘመናዊነት ጉዞ ዋነኛው መገለጫ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን መታጠቁ ነው። ተቋሙ ወቅታዊ የጦርነት ስልቶችን መሠረት ያደረጉ ዘመናዊ ሲስተም የታጠቁ ድሮኖችን በስፋት በመጠቀም ረገድ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። ይህም የቅድመ-ማስጠንቀቂያ እና ተፈላጊውን ኢላማ የመምታት አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎታል። ከዚህም በተጨማሪ ነባር የውጊያ አውሮፕላኖችን እና ሄሊኮፕተሮችን ማዘመን ብቻ ሳይሆን፣ አዳዲስ የላቁ የውጊያ አውሮፕላኖችን መታጠቁ የአየር ክልል የበላይነቱን እንዲያረጋግጥ አስችሎታል። ከእነዚህም መካከል ኢትዮጵያ ዛሬ ከሩሲያ የተረከበችው የመጀመሪያዎቹን አስራ ሁለት የሱ-35 4ኛ++ ትውልድ የጦር ጄቶች (Su-35 4++ Generation) ተጠቃሽ ናቸው። ይህም የኢትየጵያን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚደረገው ሁለንተናዊ ጥረት ሌላ ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ መድረሱን የሚያረጋግጥ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት በሩሲያ ተገኝተው የጦር ጄቶችን በተረከቡበት ወቅት ኢትዮጵያ በመከላከያ ኃይሏ እያደረገች ያለው ዝግጁነት ጥቃትን ቀድሞ ማስቀረት የሚያስችላትን አቅም በከፍተኛ ሁኔታ እያላበሳት ይገኛል ብለዋል። እነዚህን እጅግ ዘመናዊ የጦር ጄቶች በመታጠቅ ብቻ ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚ መሆን ችላለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይህንን ስኬት አስመልክተው ሲናገሩም፦ "ይህ ታሪካዊ ስኬት የሀገራችንን ሉዓላዊነት ይበልጥ የሚያጠናክር ሲሆን፣ ወደፊትም የጋራ ደህንነታችንን እና ቀጣናዊ መረጋጋትን ለማረጋገጥ የምናደርገውን ጉዞ በልበ ሙሉነት እንድንቀጥል ትልቅ አቅም ይሆነናል።" ብለዋል። በዚህ ድንቅ ዕምርታ የታጀበው የአየር ኃይላችን ዝግጁነት፣ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ከማስጠበቅ ባለፈ ለቀጣናው ሰላም ትልቅ ዋስትና የሚሰጥ መሆኑን ይህ ታሪካዊ ቀን በግልጽ አሳይቷል። ይህ ሀገራችንን የሰማይ ላይ ጥበቃ (Air Defense) ከመቼውም ጊዜ በላይ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ ትልቅ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው። ሱ-35 በአየር ላይ የሚደረጉ ውጊያዎችን በመቆጣጠር፣ የጠላት አውሮፕላኖችን እና ሚሳኤሎችን በረጅም ርቀት ላይ የማወቅ፣ የራዳር ሥርዓቶችን የማደናቀፍ እና የማስወገድ ከፍተኛ ብቃት ያለው ሲሆን፤ አየር ኃይሉ ቀደም ሲል ከታጠቃቸው Su-30፣ Su-27 እና ዘመናዊ ተዋጊ ጄቶች ጋር የተቀናጀ የሰማይ ጥበቃ መረብ ለመፍጠር ያስችላል። የማንኛውም አየር ኃይል ጥንካሬ መሠረቱ የቴክኖሎጂው ጥራት ብቻ ሳይሆን የሰው ኃይሉ ብቃት ነው። ለዚህም ስኬት አጋዥ እንዲሆን የበረራ ባለሙያዎችን፣ የቴክኒክ እና የምህንድስና ባለሙያዎችን የሚያሰለጥንበት አካዳሚ በዘመናዊ የበረራ ልምምድ መሳሪያዎች (Flight Simulators) እና ላቦራቶሪዎች እንዲደራጅ ተደርጓል። ፓይለቶች እና የጥገና ባለሙያዎች ወቅታዊውን ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ እና የስልት ደረጃ ጠብቀው እንዲሰለጥኑ በመደረጉ በከፍተኛ ደረጃ ፕሮፌሽናል የሆነ የሰው ኃይል መገንባት ተችሏል። ዛሬ ወደ ዘመናዊ አሰራር የሚደረገው ሽግግር የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን እና የሎጂስቲክስ ቅልጥፍናንም ያካተተ ነው። ቢሾፍቱን ጨምሮ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚገኙ የአየር ኃይል ጣቢያዎች በዘመናዊ መገናኛዎች፣ የበረራ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች እና የደህንነት ሥርዓቶች እንዲደራጁ ተደርገዋል። የመረጃ ልውውጥን እና የዕዝ ሥራዎችን በዲጂታል መንገድ የሚያቀናጁ የቴክኖሎጂ ሥርዓቶችንም መዘርጋት ተችሏል። ከዚህ ባሻገርም ኢትዮጵያ በኤሮስፔስ እና በመከላከያ ቴክኖሎጂ ዘርፍ በሀገር ውስጥ የሰው አልባ አውሮፕላኖች ማምረት እና መገጣጠም መጀመሯ ትልቅ ታሪካዊ ምዕራፍ ነው። እንደ ኤሮ ዓባይ (Aero Abay) እና ስካይ ዊን (Sky Win Aeronautics) ያሉ የድሮን ማምረቻ ፋብሪካዎች እውን መሆን ሀገሪቷ ከውጭ ጥገኝነት ወጥታ የራሷን የቴክኖሎጂ አቅም እንድትገነባ መንገድ ከፍቷል። ፋብሪካዎቹ በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች የሚመሩ በመሆናቸው ለከፍተኛ የቴክኖሎጂ ሽግግር ትልቅ መደላደል የፈጠሩ ሲሆን፤ ለስለላ፣ መረጃ ለመሰብሰብ፣ ተፈላጊውን ዒላማ ነጥሎ ውጤታማ እርምጃ ለመውሰድ እንዲሁም ለስልታዊ ወታደራዊ አገልግሎቶች የሚውሉ ድሮኖችን በማምረት ላይ ናቸው። እነዚህ የሀገር ውስጥ ውጤቶች የውጭ ምንዛሬን ከማዳን ባለፈ በዘመናዊ ግብርና፣ በሜጋ ፕሮጀክቶች ጂኦስፓሻል ክትትል፣ በተፈጥሮ አደጋዎች የጉዳት መጠን ዳሰሳ እና በአስቸኳይ የህክምና ቁሳቁሶች ማድረስ ላይ ከፍተኛ ሲቪል አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ አየር ኃይል ጥንካሬ የአገራችንን ሉዓላዊነት ከማረጋገጥ ባለፈ ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ትልቅ ዋስትና ነው። ሱ-35 አውሮፕላኖች እና ዘመናዊ የአየር መከላከያ ሥርዓቶች መታጠቁ የታላቁ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሀገራዊ የኢኮኖሚ፣ የኃይል እና የሎጂስቲክስ ማዕከላትን ከአየር ላይ ስጋቶች በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ ያስችላል። በወታደራዊ ስትራቴጂ ውስጥ ጥንካሬን ማሳየት ራሱ ግጭቶችን የመከላከል ትልቅ ሚና እንዳለው ሁሉ፣ ኢትዮጵያ የላቀ የአየር የበላይነት አቅም መገንባቷ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ሊነሱ የሚችሉ ስጋቶችን በቅድሚያ ለመከላከል የማይደፈር አቅም ይሆናሉ። ይህ ጠንካራ የመከላከል አቅም መኖሩ ኢትዮጵያ በቀጣናው የደህንነት እንቅስቃሴዎች ላይ የሰላም እና የመረጋጋት አምባሳደር ሆና እንድትቀጥል የሚያስችላት ሲሆን፤ በሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ወቅትም አስፈላጊውን የአየር ክልል ጥበቃ እና ደህንነት ለመስጠት ከፍተኛ ዝግጁነትን ፈጥሯል። የኢትዮጵያ አየር ኃይል እያደረገ ያለው የዘመናዊነት ሽግግር የታሪክ አደራውን ከነገው የቴክኖሎጂ እድገት ጋር ያጣመረ ነው። በሰው ኃይል ልማት፣ በሀገር ውስጥ የድሮን ማምረቻዎች፣ በዘመናዊ የሱ-35 የውጊያ አውሮፕላኖች ትጥቅ እና ቀልጣፋ የአሰራር ሥርዓት ላይ የተደረጉት ተጨባጭ ለውጦች ተቋሙን በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ካሉ ጠንካራ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ የአየር ኃይሎች አንዱ አድርገውታል። ይህ ጉዞ የኢትዮጵያን ሰማይ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ እና ለአካባቢው ቀጣና ዘላቂ ሰላም፣ መረጋጋት እና የደህንነት ዋስትና የሚሰጥ ስትራቴጂካዊ ምሽግ ሆኗል።      
የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ፍኖት፦ የአዲሱ ትውልድ የክህሎት ማበልጸጊያ መንገድ
Oct 28, 2026 342
በሀሪ መልስ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብና ታላቅ ርዕይ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የዓለም አቀፍ የበላይነትና የኢኮኖሚ ጥንካሬ በመረጃ፣ በቴክኖሎጂና በፈጠራ አቅም እየሆነ መጥቷል። ኢትዮጵያም ይህንን የዓለም አቀፍ እውነታ በመገንዘብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎትን ወደሚያሳልጥ የላቀ የዲጂታል ምዕራፍ ተሸጋግራለች። በዚህ ሀገራዊ የሽግግር ጉዞ ውስጥ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎትና የጀማሪ ፈጠራ ስራ (Startups) የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ዋና ሞተር በመሆን ግንባር ቀደም ስፍራ እየያዙ ነው። በኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ሂደትም በቴክኖሎጂ ስነ-ምህዳር ውስጥ አዲስ የስራ ባህልና የፈጠራ ምህዳር ፈጥሯል። የፖሊሲ ስትራቴጂዎች፣ የሕግ ማዕቀፎችና የመሰረተ ልማት አውታሮች ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የቴክኖሎጂና የፈጠራ ማዕከል የማድረግ ታላቅ ተስፋን የሰነቁ ናቸው። ኢትዮጵያ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ አፈጻጸም የቀመረችውን ልምድና ተሞክሮ ወደ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ በማሸጋገር የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ወደ ላቀ ደረጃ የሚሸጋግር ትልቅ ምዕራፍ ውስጥ ገብታለች። የስትራቴጂው መሰረታዊ ዋና ዓላማም የመንግሥት አገልግሎቶችን በዲጂታል አማራጭ ማቅረብ፣ የሕዝብ አገልግሎቶችን ቀልጣፋ ማድረግ እና የፋይናንስ አካታችነትን ማረጋገጥ ነው። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የታለመለትን ግብ አሳክቷል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂም የኢትዮጵያን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በማሳለጥ በስኬታማ የትግበራ ምዕራፍ እየተጓዘ ይገኛል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂም ተደራሽነትን በማስፋት፣ ለዜጎች እኩል ዕድል በመፍጠር እንዲሁም በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን በማጎልበት ቁልፍና መሰረታዊ ውጤት ማስገኘቱን ቀጥሏል። እነዚህ ትልሞችም የሕዝብ ዲጂታል መሰረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ስፍራ እየተሰጣቸው መጥቷል። ይህም ሰው ተኮር የዲጂታል ቴክኖሎጂ ምኅዳር በመፍጠር የዜጎችን ኑሮ ወደ ትልቅ አቅም እያስፈነጠረ ይገኛል። በዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂክ ፍኖተ ካርታ የሚከናወኑ ሥራዎችም የመደመር መንግሥት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስኬቶችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ መሆናቸውን ያመላክታል። «ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የታለመለትን ግብ አሳክቶ ተጠናቋል። በዛሬው ዕለትም ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በይፋ አስጀምረናል። ተደራሽነትን ማስፋት፣ ለዜጎች እኩል ዕድል መፍጠር እንዲሁም በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት የስትራቴጂው ቁልፍ መሠረታዊ ትልሞች ናቸው። እነዚህ ትልሞች እንዲሳኩም በተለይ የሕዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ሥራ የሚከናወን ሲሆን ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም ይፈጥራል። በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ሥራዎች የመደመር መንግሥት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ ናቸው።» — ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ የዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓትም በተለያዩ የግብይትና የመተግበሪያ አማራጮች እየተሳለጠ ነው። የቴሌብርና የኦንላይን የክፍያ ሥርዓቶችም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በማሳለጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ እያስገኙ ነው። አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችም ያለ ማስያዣ ብድር በማግኘት የልማት ስራዎቻቸውን ወደ ላቀ የዕድገት ምኅዳር የሚያስፈነጥሩበትን አዲስ ዕድል ተፈጥሯል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ መረጃ ማዕከላት ግንባታና የክላውድ ኮምፒውቲንግ መሰረተ ልማት ዝርጋታም የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን የሚመጥን አቅም ገንብቷል። የኢንተርኔት ተደራሽነትን የማስፋት ተግባርም የመረጃ ሉዓላዊነትና የሳይበር ደህንነትን የማረጋገጥ አካል ናቸው። እነዚህም የኢትዮጵያን ቁልፍ የመሰረተ ልማት ተቋማትና የመረጃዎች ደህንነትን እንዲጠበቁ እያስቻለ ነው። ኢትዮጵያ በቅርቡ ይፋ ያደረገችው በአፍሪካ የመጀመሪያው ሁሉን አቀፍ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፖሊሲና ስትራቴጂም ታሪካዊ እርምጃ ሆኖ ተመዝግቧል። ይህ ፖሊሲና ስትራቴጂም በቴክኖሎጂ ዘርፍ በዕውቀትና ክህሎት የበለጸገ ስልጡን የሰው ሃይል በመገንባትና የመረጃ ሉዓላዊነትን በማስጠበቅ ለስታርትአፖች ምቹ የፈጠራ ማዕቀፍ መፍጠር አስችሏል። «በኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ያየሁት ነገር፤ ሰው የጠራ ርዕይ ካለው፣ በከፍተኛ ዲሲፕሊን የሚሰራ ከሆነ አንድን ነገር ባየው ልክ ማሳካት እንደሚችል፤ ኢትዮጵያ ብቃት ያላት ሀገር እንደሆነች ነው።» — ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በሰው ሰራሽ አስተውሎት የምርምር፣ ልማትና የፖሊሲ አፈጻጸም ዋና መሪ አካል ሆኖ እየሰራ ይገኛል። ይህም የቴክኖሎጂ ፈጠራና ክህሎት ዝንባሌ ያላቸው ወጣቶችና ዜጎች ክህሎታቸውን በማበልጸግ ወደ ተግባር የሚገልጡበትን ወሳኝ ዕድል ፈጥሯል። የአዲስ አበባ የቦሌ አትላስ ኮሪደር የንግድ ጀማሪ ፈጠራ ስራ (Startups)፣ የኢትዮጵያ አይሲቲ ቪሌጅ ሮቦቲክስና ከፍተኛ ምርምር፤ የፈጠራ ማዕከላት የኢትዮጵያ ተስፋ ወደ ተጨባጭ ተግባር እየተቀየረ መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው። ይህም በግብርና ዘርፍ የሰብል በሽታን በምስል በመለየት፣ በጤና የሕክምና ምስሎችን በመተንተን እና በፋይናንስ ዘርፍ ደግሞ በርካታ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መፍትሔን መተግበር የሚያስችል ዕድል መፈጠሩን ያመላክታል። ኢትዮጵያ የመደመር አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲን በማቋቋም አህጉራዊ የዲጂታል ልማት ማዕከል የሚያደርጋትን ወሳኝ መንገድ ተልማለች። ዩኒቨርሲቲውም በዓለም አቀፍ ደረጃ ሙሉ በሙሉ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና በላቁ የኮምፒውቲንግ ሳይንሶች ብቻ ከተመደቡ ጥቂት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል የሚመደብ ነው። ሥርዓተ-ትምህርቱ ከወረቀት ላይ ትምህርት ይልቅ በተግባራዊ አፕሊኬሽኖች፣ በማሽን ለርኒንግ፣ በሮቦቲክስ፣ በዳታ ማይኒንግ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ምርምር ላይ ያተኮረ ይሆናል። በኢትዮጵያ የሚሰሩ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መፍትሔዎች ሀገራዊ እና አካባቢያዊ ችግሮችን መፍትሔ በመስጠት ላይ የተመሰረቱ ናቸው። ከነዚህም መካከል በአማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ትግርኛ እና ሌሎች የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች የትርጉም፣ የድምፅና የጽሑፍ ማቀናበሪያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መሳሪያዎች ይገኙበታል። እነዚህ በሀገር በቀል ድርጅቶች የሚለሙ የቴክኖሎጂ አማራጮችም ከዓለም አቀፍ አፕሊኬሽኖች የተሻለ የቋንቋ ትክክለኛነት በማረጋገጥ ላይ ናቸው። የአምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ስልጠና ተነሳሽነትም በሶስት ዓመታት ውስጥ አምስት ሚሊዮን ወጣቶችን በፕሮግራሚንግ፣ በዳታ አናሊቲክስ፣ በአንድሮይድ ዴቨሎፕመንት እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መሰረታዊ ክህሎት እንዲጨብጡ አድርጓል። ተነሳሽነቱም የዲጂታል ፈጠራና ምርምርን በማጎልበት የቴክኖሎጂ ክህሎት ያላቸው ወጣቶችን ማፍራት እያስቻለ ነው። የስታርትአፕ አዋጅ (Startup Proclamation No. 1396/2025) መጽደቁ ለጀማሪ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ትልቅ ምዕራፍ ከፍቷል። የአሰራር ሥርዓቱም በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አማካኝነት ስታርትአፖችና የሥነ-ምህዳር ደጋፊዎች በአንድ ቦታ እንዲመዘገቡና ሕጋዊ የምስክር ወረቀት እንዲያገኙ ያስችላል። አዋጁም የስታርትአፕ ግራንት (Grants)፣ የብሔራዊ ክሬዲት ጋራንቲ ፈንድ (Credit Guarantee Fund) እና የገንዘብ ፈንድ (Fund of Funds) አሰራሮች በመዘርጋት የቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎት ዝንባሌን ወደ ተግባር መቀየር የሚያስችል ዕድል ፈጥሯል። የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና የስታርትአፕ ስነ-ምህዳር እርስ በእርስ የተቀናጁና አንዱ ለሌላው ማፋጠኛ መሳሪያነት የተዋቀሩ ናቸው። የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ለAI ሞዴሎች ስልጠና አስፈላጊውን የኮምፒውቲንግ አቅም ያቀርባሉ። የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂዎች ለስታርትአፖች አዲስ ምርትና አገልግሎት ፈጥረው ለገበያ እንዲያቀርቡ መንገድ እየከፈቱ ነው። ስታርትአፖች ደግሞ የፈጠሯቸው የዲጂታል አገልግሎቶች የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ግቦችን በማሳለጥ ላይ ናቸው። ኢትዮጵያ ከፖሊሲ ቀረፃ ወደ ተጨባጭ የልማት ስነ-ምህዳር ግንባታ ሽግግር በአፍሪካ ደረጃ የቴክኖሎጂ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ማዕከል የማድረግ ታላቅ ዕድል ከፍቷል። ይህ ታላቅ ርዕይ ሙሉ በሙሉ እውን እንዲሆንም የፖሊሲ ማዕቀፎችን፣ የተቋማት ጥረትን እና የወጣቶችን የፈጠራ አቅም በተቀናጀ መልኩ ወደ ላቀ ደረጃ የማሸጋገር ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል። ይህንን ዘላቂ ስኬት ለማረጋገጥም ስትራቴጂክ ትልሞችን በተቀመጠላቸው መርሃ ግብር መተግበር ወሳኝ ነው። የቴሌኮም፣ የብሮድባንድና የዳታ ማዕከላት ተደራሽነትን በማስፋፋት ለሀገር ውስጥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) አልሚዎች እና ስታርትአፖች በዝቅተኛ ወጪ የሚጠቀሙበት ምቹ የመሰረተ-ልማት ምህዳር መፍጠር ያስፈልጋል። በጸደቀው የስታርትአፕ አዋጅ የተመላከቱትን የብሔራዊ ክሬዲት ጋራንቲ ፈንድ እና የገንዘብ ፈንድ አሰራሮችን በመተግበርና የቬንቸር ካፒታል ኢንቨስትመንቶችን በማበረታታት የጀማሪ ስራዎችን የፋይናንስ እጥረት መቅረፍ ይገባል። በተጨማሪም፣ ከአምስት ሚሊዮን ኮደርስ እና ከሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ የሚወጡ ሰልጣኞችን በቀጥታ ወደ ስራ የሚቀይሩ የኢንኩቤሽን ማዕከላትን ማብዛትና በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ የSTEM ክህሎቶችን ማጠናከር ወሳኝ ነው። በዩኒቨርሲቲዎች፣ በምርምር ተቋማት እና በንግዱ ማህበረሰብ መካከል ያለውን ቅንጅት በማጠናከር የመንግስት ተቋማት የሀገር ውስጥ ስታርትአፖች ምርቶችን ቅድሚያ ሰጥተው እንዲገዙ ማበረታታት፣ የመረጃ ሉዓላዊነትን፣ የሳይበር ደህንነትን እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ስነ-ምግባር ደንቦችን በጥብቅ ማስከበር ያስፈልጋል።
የመደመር መንግስት የማይጠናቀቅ ፕሮጀክት አይጀምርም!
Oct 24, 2026 361
ጥቅምት 14/2019 (ኢዜአ):- የመደመር መንግስት የማይጠናቀቅ ፕሮጀክት አይጀምርም! የአንድ ሀገር የልማት ጉዞ የሚለካው በታቀዱ ፕሮጀክቶች ሳይሆን፤ በተያዘላቸው ጊዜ ተገንብንተው ተጠናቀው ለሀገር በሚኖራቸው ፋይዳ እና በሕዝብ ሕይወት ላይ በሚያመጡት ተጨባጭ ውጤት ነው። የልማት ፕሮጀክቶች የሀገርን ኢኮኖሚ ከማሳደግ ባለፈ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ የማሻሻል፣ የሥራ ዕድሎችን የመፍጠር፣ የምርታማነት አቅምን የማሳደግና ለቀጣይ ትውልድ የተሻለች ሀገር የማስረከብ አላማ የሰነቁ ናቸው። በመሆኑም የመደመር መንግስት እነዚህን መሰረታዊ መርሆዎች በማንገብ ለሀገር ልማት፣ እድገትና ማንሰራራት በትጋትና በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል። የመደመር መንግስት የማይጠናቀቅ ፕሮጀክት አይጀምርም፤ የዚህ መርህ ውጤት ማሳያዎችም ባለፉት ስምንት ዓመታት የተከናወኑና የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ማሳያ ናቸው።   የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በተለያዩ የፋይናንስ፣ የቴክኒክና የዲፕሎማሲ ፈተናዎች ውስጥ አልፎ በመደመር መንግስት ጽናትና በህዝቡ ድጋፍ ተጠናቆ ለአገልግሎት በቅቷል። የግድቡ ግንባታ መጠናቀቅ የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨት ባለፈ ለኢንዱስትሪ ዕድገት፣ ለኢኮኖሚ መስፋፋት፣ ለቀጣናዊ የልማት ትስስርና የጋራ ተጠቃሚነት ትርጉሙ የላቀ መሆኑ ይታወቃል። ኢትዮጵያዊያን ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ገንብቶ የማጠናቀቅ አቅምና ችሎታ ስለመኖሩ ተግባራዊ ምላሽ የሰጠና የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ድል መሆኑንም መናገር ይቻላል። በዚህ ግዙፍ ፕሮጀክት ግንባታ የመደመር መንግስት ብቃትና ቁርጠኝነት በተለይም ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመሪነት አቅም የታየበት ነው። የመደመር መንግስት ቀደም ሲል የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ፣ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በተቀመጠላቸው ጊዜ አጠናቆ ለአገልግሎት በማብቃት አዲስ የስራ ባህልና የመፈፀም አቅም አካብቷል። በተለያዩ ምክንያቶች ግንባታው ተጓትቶ የቆየው የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ለዚህ ጥሩ ማሳያ መሆን ይችላል። በመሆኑም የመገጭ ፕሮጀክትን አጠናቆ ለስኬት በማብቃት የመደመር መንግስት የመፈፀም አቅሙን አሳይቷል። የመገጭ የመስኖ ፕሮጀክቶች የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማጠናከርና የገበሬዎችን ገቢ ለማሳደግ እንዲሁም ለመጠጥ ውሃ የሚያገለግል ሰው ተኮር ፕሮጀክት በመሆኑ ግንባታው መጠናቀቁ ትልቅ ትርጉም አለው።   የዚህ ስራ ማሳያና መገለጫነቱ ተቋርጠው የነበሩና የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በሃላፊነትና በተጠያቂነት መርህ የማጠናቀቅ ጠንካራ አቋም መኖሩን ነው። በመሆኑም የመደመር መንግስት ከረጅም ዓመታት በፊት ተጀምረው የነበሩና አቅዶ የጀመራቸውን ፕሮጀክቶች በጥራትና በብቃት ማጠናቀቅ የሚችል መሆኑን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል። ፕሮጀክቶችን መጀመር፣ ግንባታቸውን መከታተል፣ በተቀመጠው ጊዜ አጠናቆ ለአገልግሎት ማብቃት የመደመር መንግስት ግልጽ አቋም ነው። የፕሮጀክት አፈጻጸም ብቃት በተያዘለት ጊዜ፣ በተመደበለት በጀት፣ በተጠበቀው ጥራትና በሚያመጣው የልማት ጥቅም የሚለካ መሆኑ ይታወቃል። የዕቅድ ጥራት፣ የበጀት አጠቃቀም፣ የግዥና ኮንትራት አስተዳደር፣ የባለሙያዎች ብቃት፣ የግንባታ ጥራትና የቁጥጥር ሥርዓትም እንዲሁ። በእነዚህ ሁሉ መስፈርቶች የመደመር መንግስት በፕሮጀክት አፈፃፀም የተሳካለትና እየተሳካለት መሆኑን መናገር ይቻላል። የከተሞች የኮሪደር ልማት፣ የቅርሶች እድሳት፣ የዘመናዊ ሪዞርት ግንባታዎችን በጥራትና በፍጥነት በማከናወን ለአገልግሎት አብቅቷል። ሌሎች ተጀምረው የተጠናቀቁና በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችም በርካታ ናቸው። ከዚህ አንፃር የማዳበሪያ ፋብሪካና የቢሾፍቱ ኤርፖርት ግንባታ የመስራት አቅም ተጨማሪ ማሳያዎች እና የሀገር እድገት መሰረቶች ናቸው።   የማዳበሪያ ፋብሪካ መገንባት የግብርና ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ በማዳበሪያ አቅርቦት ላይ የነበረውን የውጭ ገበያ ጥገኝነት ለመቀነስና የውጭ ምንዛሬ ወጪን ለማስቀረት የሚያስችል ነው። የአገር ውስጥ የኢንዱስትሪ አቅምን ለማሳደግም የሚያግዝ ይሆናል። በሌላ በኩል የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ፕሮጀክት ግንባታ የኢትዮጵያን የአቪዬሽን ዘርፍ እድገትና ማንሰራራት የሚያስቀጥል ታላቅ ፕሮጀክት ነው። የመደመር መንግስት የፕሮጀክት አፈጻጸም አቅም ይበልጥ ሲጠናከርና ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት የሚበቁ ፕሮጀክቶች ቁጥር ሲጨምር የዜጎች ተጠቃሚነት ብሎም የሀገር እድገትና ማንሰራራት እየተጠናከረ ይሄዳል።
ልዩ ዘገባዎች
ከዓባይ እስከ ቀይ ባሕር 
Oct 9, 2026 939
ነጋሪ መጽሔት የዓባይ ውሃ አጠቃቀምና የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት በስፋት ተንትናለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በመደመር መንግሥት ምሥረታ ላይ፣ “የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ያለ ባሕር በር እውን ሊሆን አይችልም” በማለት ሀገሪቱ የባሕር መዳረሻ እንድታገኝ በትጋት እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል። ይህ ጥረት በሰላማዊ ውይይት፣ በጋራ ተጠቃሚነትና በ“ሰጥቶ መቀበል” መርሕ እንደሚመራ በማስገንዘብ፣ ጉዳዩን ከአፍሪካ ቀንድ፣ ከቀይ ባሕርና ከመካከለኛው ምሥራቅ እየተለወጡ ካሉ የጂኦፖለቲካና የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ጋር አያይዘው አቅርበዋል። መጽሔቷም በመስከረም 2019 ዓ.ም. እትሟ “የኢትዮጵያ የትንሳኤ መንገድ፡ ከዓባይ እስከ ቀይ ባሕር ፖለቲካ የዘለቀው ፍጥጫ” በሚል ርዕስ ባቀረበችው ትንታኔ፣ የውሃ ሀብት፣ የባሕር መዳረሻ፣ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮችና የቀጣናዊ ደኅንነት ጉዳዮች በሀገራት መካከል ባለው የኃይል አሰላለፍ ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ ዳስሳለች። እንደ መጽሔቷ ትንታኔ፣ ዓባይና ቀይ ባሕር በተፈጥሮ የተለያዩ የውሃ አካላት ቢሆኑም፣ በዘመናዊው የጂኦፖለቲካ ስሌት ውስጥ በውሃ አጠቃቀም፣ በኢኮኖሚያዊ ጥቅም፣ በባሕር መዳረሻና በደኅንነት ጉዳዮች የተሳሰሩ ናቸው። የዓባይ ወንዝ ለኢትዮጵያና ለተፋሰሱ ሀገራት ለኃይልና የልማት ጥቅም ሲኖረው፣ ቀይ ባሕር ደግሞ አፍሪካን፣ እስያንና አውሮፓን የሚያገናኝ ወሳኝ የዓለም አቀፍ የንግድና የባሕር መተላለፊያ ነው። በተለይም የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ የዓባይ ውሃን በፍትሐዊነትና በጋራ ተጠቃሚነት የማስተዳደር ጥያቄና የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት በቀጣናው የፖለቲካና የደኅንነት ስሌቶች ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ መጽሔቷ በስፋት ተንትናለች። የ1929 እና የ1959 የውሃ ስምምነቶች የላይኛውን ተፋሰስ ሀገራትን ጥቅም በበቂ ሁኔታ እንዳልተካተቱ በመግለጽ፣ የወንዙ ውሃ አጠቃቀም በፍትሐዊነት፣ በትብብርና በጋራ ጥቅም ላይ በተመሠረተ ማዕቀፍ መመራት እንዳለበት አመልክታለች። ኢትዮጵያ በ1993 ዓ.ም በኋላ የባሕር በር መዳረሻዋን ማጣቷን ተከትሎ፣ ጉዳዩ ከኢኮኖሚያዊ ጥቅም ባለፈ ከብሔራዊ ደኅንነትና ከረጅም ጊዜ የልማት ፍላጎት ጋር እንደተያያዘ መጽሔቷ አትታለች። የባሕር በር መዳረሻ ማግኘት የንግድ ወጪን ለመቀነስ፣ የወደብ አማራጮችን ለማስፋትና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለመደገፍ ወሳኝ መሆኑንም አብራርታለች። በሌላ በኩል፣ ቀይ ባሕር ከእስያ፣ ከአፍሪካና ከአውሮፓ የንግድ መስመሮችን የሚያገናኝ ስትራቴጂካዊ የባሕር መተላለፊያ በመሆኑ፣ በአካባቢው ያለው የደኅንነት ሁኔታ ከአካባቢያዊ ግንኙነቶች ባለፈ ዓለም አቀፋዊ የንግድ ፍሰትን ይነካል። መጽሔቷ የቀይ ባሕር የጂኦፖለቲካ አስፈላጊነት ከስዊዝ ቦይና ከባብ-ኤል መንደብ የባሕር መተላለፊያ ጋር በማያያዝ የዳሰሰች ሲሆን፣ በአካባቢው የሚካሄዱ የኃይል ፉክክሮች የንግድና የደኅንነት ስጋቶችን እንደሚያባብሱ ተንትናለች። መጽሔቷ በትንታኔዋ የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት ከቀጣናው ሀገራት የፖለቲካ አቋሞች ጋር በማያያዝ የተለያዩ ትንታኔዎችን አቅርባለች። ሆኖም እነዚህ በመጽሔቷ የቀረቡ የፖለቲካ ትንታኔዎች ሲሆኑ፣ የተጠቀሱ አቋሞችንና ክሶችን ከተረጋገጡ እውነታዎች መለየት ያስፈልጋል። መጽሔቷ በዓባይ ውሃ አጠቃቀምና በባሕር መዳረሻ ጉዳይ ዙሪያ የሚነሱ አለመግባባቶች በግጭት ሳይሆን በውይይት፣ በድርድርና በጋራ ተጠቃሚነት መርሕ መፍትሔ ማግኘት እንዳለባቸው አጉልታለች። የውሃ ሀብትን በፍትሐዊነት ማስተዳደርና የባሕር መዳረሻ ጉዳይን በሰላማዊ ስምምነት መፍታት ለቀጣናዊ መረጋጋት፣ ለኢኮኖሚ ትብብርና ለዘላቂ ልማት ወሳኝ መሆናቸውን በትንታኔዋ አመልክታለች። የመጽሔቱ ሊንክ https://www.ena.et/web/negari/w/negari_9696604
ከአዲሱ መንግስት ምን ይጠበቃል?
Oct 5, 2026 877
ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት በሀገሪቷ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን የማስቀጠል፤ በተለይም የተጀመሩ ግዙፍ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችን ለስኬት ማብቃት ትልቁ የቤት ስራ ነው የሚሆነው። በከተሞች እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማትና የስማርት ሲቲ ግንባታ፣ የዲጂታል አገልግሎቶችን የማስፋት፣ የአረንጓዴ አሻራ ልማትን ማስቀጠል ሌላኛው ሀገራዊ ሃላፊነት ነው የሚሆነው። የኢትዮጵያ ልማት በከተሞች ጋር ብቻ የሚወሰን ባለመሆኑ በገጠር አካባቢዎች የተጀመሩ የገጠር ትራንስፎርሜሽን የልማት ስራዎችንም ማስቀጠል የግድ ይላል። የገጠር ትራንስፎርሜሽን ዋነኛ ዓላማም የገጠሩን ህዝብ አኗኗር ማዘመን፣ የመሠረተ ልማትና የመሰረታዊ አገልግሎት ተደራሽነትን ማሻሻል፣ የገጠር ኢኮኖሚን ማጠናከርና የገጠር ነዋሪዎችን ከዘመናዊ የምርትና የገበያ ሥርዓት ጋር ማስተሳሰር መሆን አለበት። ኢትዮጵያ በተፈጥሮ፣ በታሪክ፣ በባህልና በሃይማኖት የበለፀገች ሀገር በመሆኗ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መፍጠር፣ ያሉትን የመጠበቅና የማልማት እንዲሁም ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ሀብቶችን መጠበቅ፣ የቱሪስት ቆይታን ማራዘምና ከቱሪዝም ጋር የተሳሰሩ የስራ እድሎችን የማስፋት ጉዳይ የአዲሱ መንግስት ዋነኛ ትኩረት ሆኖ ይቀጥላል። በግብርናው ዘርፍም በምርትና ምርታማነት፣ በመስኖ ልማት፣ በስንዴ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በቡና፣ በሆርቲካልቸርና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች የተጀመሩ ስራዎች በዘላቂነት እንዲቀጥሉ ማድረግ ይጠበቃል። ከምርት መጨመር ባሻገር የግብርና ምርቶችን ማቀነባበር፣ የገበያ ትስስርን ማሻሻል፣ የማከማቻና የመጓጓዣ ስርዓትን ማዘመን እና የአርሶ አደሩን ገቢ የማሳደግ ጉዳይ ትኩረት ይፈልጋል። የምርትና ምርታማነት መጨመር በመጨረሻም ከውጭ የሚገቡ የምግብ ምርቶችን በመተካት፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ አቅም በማሳደግ ከተረጅነት ለመውጣት የሚደረገውን ጥረት ማሳካት ይጠበቅበታል። የማዕድን ልማት፣ ዲጂታላይዜሽንና የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ጉዳይም ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ይሆናል። የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የምርትና የገበያ አቅርቦትን ማሳደግ፣ የአቅርቦት ሰንሰለትን ማሻሻል፣ ህገወጥ የገበያ አሰራሮችን መቆጣጠርና የዜጎችን የመግዛት አቅም ማሻሻል ይጠበቃል። የኑሮ ውድነት ችግር በአንድ መፍትሄ የሚፈታ ባለመሆኑ የገቢ፣ የምርት፣ የገበያና የፋይናንስ ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መልኩ ማስኬድ ያስፈልጋል።
የአካታች ሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት
Oct 5, 2026 659
መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):- አዲሱ የመንግስት ምስረታ - አካታች የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ በምክር ቤት አብላጫ መቀመጫ ያገኘው ብልጽግና ፓርቲ መንግስት የመመስረት ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ በዛሬው እለት ይሄው የሚከናወን ይሆናል። በፓርላማው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መቀመጫ ያገኙ በመሆኑ የፖለቲካ ክርክሮችና የሃሳብ ብዝሃነት የሚስተናገዱበት እንደሚሆንም ይጠበቃል። በኢትዮጵያ አካታችና አሳታፊ የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ያኖረው አዲሱ የመንግስት ምስረታ ሂደት የክልሎች ተጠናቆ በዛሬው እለት የፌዴራል መንግስት ምስረታ እውን ይሆናል። ባለፉት ዓመታት የተመዘገበው የአካታችነት ስኬት የመንግሥት ከፍተኛ የአመራር እርከኖች፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤትና የፍትህ ተቋማት አመራሮች ላይ የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮችን፣ የሴቶችንና የወጣቶችን ፍትሃዊ ስብጥር በተግባር ማሳየት ያስቻለ ነው። ከባለፉት አምስት አመታት ተሞክሮ በመነሳትም የዘንድሮው ምርጫ በብዙ መስፈርቶች ዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊ እና አካታች መሆኑን በተግባር ያሳየና የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት ያኖረ ሆኗል። በተቋማዊ አካታችነትና ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር በተወሰዱ እርምጃዎችም ጉልህ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ሁሉንም የፖለቲካና የኅብረተሰብ ክፍሎች ያቀፈው ሀገራዊ የምክክር ሂደት በሀገሪቷ የቆዩ ልዩነቶችን በምክክር ለመፍታት አዲስ ምእራፍ የከፈተ ሆኗል። ከዚህ ጎን ለጎን የጽንሰ-ሐሳብ፣ የቋንቋና የባህል ስብጥሮችን ያከበሩ የትምህርትና የባህል ፖሊሲዎች መተግበራቸው፣ ዜጎች በቋንቋቸው የመማርና አገልግሎት የማግኘት መብታቸው እንዲሰፋ በማድረግ ረገድም ትልቅ ስኬት ታይቷል። በመሆኑም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አብላጫ ድምፅ ያገኘው የብልፅግና ፓርቲ የሚያቋቁመው አዲሱ መንግስት በቀጣይ ሁለንተናዊ አካታችነትን በማረጋገጥ ረገድ ብዙ እንደሚሰራ ይጠበቃል። ገዢው ፓርቲ መወዳደር የሚችልባቸውን አካባቢዎች በመተው ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እድሉን መስጠቱ በምክር ቤቱ የተለያዩ ድምፆች እንዲስተጋቡ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ሆኗል። በመሆኑም ጠቅላላ ምርጫው የፖለቲካ ተሳታፊነትንና ውክልናን በማስፋት ረገድ ጉልህ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነበር ማለት ይቻላል። በተጨማሪም በውሳኔ ሰጪነትና በፖለቲካ ውድድር ውስጥ የሴቶች፣ የወጣቶችና የልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ እንዲያድግ በመደረጉ ህዝባዊ ወካይነት ያለው የምርጫ ሂደትን ለማከናወን አስችሏል። ምርጫ አስተዳደሩንና አሰራሩን አሳታፊና ፍትሃዊ በማድረግ ረገድ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል የታዩት እርምጃዎች ሌላው የአካታችነት ማሳያዎች ናቸው። የድምፅ መስጫ ጣቢያዎችን ተዳራሽ ማድረግ፣ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሆኑ የምርጫ ግብዓቶችን ማዘጋጀት እና በምርጫ ታዛቢነት የሲቪክ ማህበራትን፣ የሀገር ውስጥና የውጪ ምርጫ ታዛቢዎችን ማሳተፍ ተችሏል። ይህም የህብረተሰቡ ልዩ ልዩ ክፍሎች ያለምንም ገደብ የመምረጥ መብታቸውን እንዲጠቀሙና በሂደቱ ላይ ያላቸው እምነት እንዲጎለብት አድርጓል። በመሆኑም በዛሬው እለት የሚመሰረተው መንግሥት ልዩ ልዩ የፖለቲካና የማህበረሰብ ክፍሎችን ድምፅ በማስተናገድና ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር ጠንካራ የሀገረ መንግስት ግንባታ መሰረት የሚያኖር እንደሚሆን ይጠበቃል።
የመደመር መንግሥት-የብሔራዊ ጥቅም ዘብ
Oct 5, 2026 664
ኢትዮጵያ ዛሬ አዲስ መንግሥት ትመሠርታለች።ይህ መንግሥት የዛሬውን ትውልድ ብቻ ሳይሆን፤የመጪውንም ትውልድ ፍላጎት በጽኑ መሠረት ላይ የሚያቆም ሥራ የሚሠራ ነው። አዲሱ መንግሥት ትልቅ የሕዝብ አደራ የሚቀበልና የነገዋን ኢትዮጵያ በከፍታ ላይ የሚያስቀምጥ እንደሚሆን እሙን ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ እጅግ ውስብስብ የሆኑ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ፈተናዎች አልፋ ዛሬ አዲስ የምዕራፍ ላይ ትገኛለች። አዲሱ መንግስት ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን፣ ሉዓላዊነቷን እና የሕዝቦቿን የጋራ እድገት ለማረጋገጥ ባደረገችው ያላሰለሰ ጥረት ውስጥ ቀጣይ ጉዞዋን በተሻለ መልኩ የሚያስቀጥል መንግሥት ይሆናል። ይህ ታሪካዊ ጉዞ በቀላሉ የተገኘ አልነበረም። ሕዝቡ የወደፊት ዕጣ ፈንታውን በቃላት ሳይሆን በተግባር ለመወሰን፣ መብቱን በድምፁ በመጠቀም ታሪካዊ አደራውን ለመወጣት ውስብስብ ፈተናዎችን አልፏል። በፈተና ውስጥ አልፎ የሰጠው ድምፅ ተራ የምርጫ ሂደት ሳይሆን፤ የሀገርን ሕልውና የማስከበር፣የብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ እና ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር የማስረከብ ጽኑ ፍላጎት መግለጫ ነበር። ዛሬ የሚመሠረተው አዲስ መንግሥት የዚሁ የሕዝብ አደራና የጽናት ውጤት ነው።ይህ የመደመር መንግሥት የሀገሪቱን ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ እና ቀጣናዊ ጥቅሞች ያስከብራል፤ የኢትዮጵያን የሉዓላዊ ድንበር እና የወደፊት ሕልውና በጠንካራ ዲፕሎማሲና በውስጥ አንድነት ይጠብቃል። የዛሬዎቹን አጣዳፊ ጥያቄዎች ለመመለስ ብቻ ሳይሆን፣ መጪው ትውልድ የሚተማመንባት፣ በኢኮኖሚ የበለጸገች እና ብሔራዊ ጥቅሟን የምታስጠብቅ ሀገር መንግስት ይመሰርታል። ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን በሁለት ውኃዎች ላይ አድርጋ በጽናት እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች። የአባይን ውኃ ለሁለንተናዊ እድገቷ መጠቀም ጀምራለች፤ ሕዳሴንም ጨርሳ የማድረግ አቅሟን አረጋግጣለች።ይህ ጉዞ ቀላል አልነበረም፤ሀገሪቱ በውስጥና በውጭ በርካታ ፈተናዎችን፣ ተፅዕኖዎችንና ጫናዎችን አልፋ ነው እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰችው። ዛሬ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን የበለጠ የሚያስከብርላትን የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ አንሥታ ጉዳዩን ዓለም አቀፍ አጀንዳ አድርጋዋለች። የመደመር መንግሥት ኢትዮጵያ ኢ-ፍትሐዊና ባልተገባ መልኩ ያጣችውን የባሕር በሯን እንድታገኝ በትክክለኛው መንገድ ይጓዛል፤ ግቡንም ያሳካል። ዛሬ የሚመሠረተው አዲስ መንግሥት ለነገዋ ኢትዮጵያ ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መደላደል የሚፈጥር ነው፤ የሀገሪቱን የባሕር በር ፍላጎት፣የዓባይ ወንዝ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት፣የውስጥ ደኅንነትና የኢኮኖሚ ነፃነት አፅንኦት ሰጥቶ ማስጠበቅ ነው።ልዩነቶችን በማቀናጀትና አቅሞችን በመደመር የሀገርን ሕልውና አስተማማኝ ማድረግም ሌላው ከመደመር መንግስት የሚጠበቅ ነው። ከምንም በላይ ኢትዮጵያ የበርካታ ዘመናት ታሪካዊ ጠላቶቿንና ተላላኪዎቻቸውን እኩይ ሴራ ትበጣጥሳለች።የውስጥና የውጭ ጫናዎችን በህዝቦቿ ጽናት፣የአንድነት መንፈስና የማይናወጥ ሀገራዊ ወኔ እያሸነፈች ትቀጥላለች።ለነፃነቷና ሉዓላዊነቷ ሳትበገር በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ወደ ላቀ የልማት፣ የብልፅግናና የዕድገት ከፍታ ወደ ፊት መገስገሷን ትቀጥላለች። ዛሬ የሚመሰረተው አዲሱ የመደመር መንግሥትም የሕዝቡን ተስፋና እምነት ወደ መሬት በማውረድ፣የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም አክብሮና አስከብሮ ለመጪው ትውልድ የምትመችና በጽኑ መሠረት ላይ የተገነባች ሀገርን የማስረከብ ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 110053
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 83129
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 60712
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 58333
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 41279
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 41249
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 40630
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 39136
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 110053
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 83129
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 60712
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 58333
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
ባሮ - የጋምቤላ የውበት አክሊል!
Nov 2, 2026 55
ጋምቤላ ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ)፦ባሮ - የጋምቤላ የውበት አክሊል! በሙሉጌታ ዳምጤ (ኢዜአ-ጋምቤላ) ከኢትዮጵያ ከፍታማ ቦታዎች በመነሳት የጋምቤላ ከተማን መሀል ለመሀል አቆራርጦ ወደ ደቡብ ሱዳን በመሻገር የሶባት ወንዝ ተብሎ ከነጭ ዓባይ ጋር በመቀላቀል የመጨረሻ መዳረሻውን ሜድትራኒያን ያደርጋል። የባሮ ወንዝ የጋምቤላ ክልል ወሰን አካባቢ ሲደርስ ገባ እና ብርብራ በሚል የሚጠሩ ወንዞችን ጨምሮ ጉዞውን ወደ ሩቅ መዳረሻው ያደርጋል። የባሮ ወንዝ የብርብር እና የገባ ወንዞች ሲቀላቀሉት የውሃው ቀለም ቀላ ስለሚል ወንዞቹ የሚገናኙበት ቦታ "ባሮ ቀላ" የሚል ስያሜ አግኝቷል፤ ሀገር አቋራጩ የባሮ ወንዝ 306 ኪሎ ሜትር (190 ማይል) ርዝመት ይጓዛል። የጋምቤላ ክልልን የተፈጥሮ ውበት ከሰው ሕይወት፣ ከኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴና ከባህላዊ እሴቶች ጋር አስተሳስረው ከሚያቆዩ ታላላቅ የተፈጥሮ ሀብቶች መካከል የባሮ ወንዝ አንዱ ነው። ከነ ግርማ ሞገሱ የጋምቤላ ከተማን አቆራርጦ ሲያልፍ ለከተማዋ ድምቀት ነው ማለት ይቻላል። ባሮ በኢትዮጵያ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ብቸኛው ወንዝ ነው። የተፈጥሮ ውበት፣ የኢኮኖሚ አቅምና የሕዝብ ኑሮ ተሳስረው የሚታዩበት ታላቅ የሀገር ሃብትም እንደሆነ ይነገርለታል -ባሮ ወንዝ። የባሮ ወንዝ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1907 ዓ.ም ጀምሮ ወደብና የጉምሩክ ጣቢያ ተቋቁሞለት ከጋምቤላ ከተማ ወደ ወረዳዎችና ሱዳን ጠረፍ የውሃ የትራንስፓርት አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። በአሁኑ ወቅትም በዘመናዊ መልኩ ባይሆንም ወንዙ ወደሚያቋርጥባቸው ወረዳዎችና ደቡብ ሱዳን ጠረፍ ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። በአካባቢው ነዋሪዎች "ኦፔኞ" እየተባለ የሚጠራው ባሮ የጋምቤላ ተፈጥሯዊ መለያም፤ መድመቂያም ነው። የወንዙ ፍሰት፣ በወንዙ ዳርቻ የሚታየው አረንጓዴ ተፈጥሮና ከውኃው ጋር የተቆራኘው የነዋሪዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ሌላኛው ገጽታው ነው። በሞቃታማ የአየር ጸባይ ወቅት በወንዙ ዳርቻ ያሉ እጽዋቶች ብቻ ሳይሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎችም ሙቀቱን ለማስታገስ ወንዙን ስለሚጠቀሙበት አለኝታና ታዛቸው ነው ማለት ይቻላል። በባሮ ወንዝ ቁጥራቸው ከ51 እስከ 57 የሚደረሱ የዓሣ ዝርያዎች አሉ። በተለይም "ናይል ፐርች" በአካባቢው አጠራር "ጉር" የሚባለው ግዙፍ የዓሣ ዝርያ እስከ 100 ኪሎ ግራም ይመዝናል። እንዲሁም "ታይገር" ፣ "ስታር" ፣ "ካት" እና "ቀረሶና" የተባሉና ሌሎች የዓሣ ዝርያዎች በውስጡ የሚገኙ ሲሆን የአዞ እና ሌሎች የብዝሃ ሕይወት ሀብቶችም መኖሪያ ነው። በወንዙ ዙሪያ ያሉ የንግድ እንቅስቃሴዎች እና ከውኃው ጋር የተያያዙ ሌሎች ሥራዎች ለበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች የገቢ ምንጭ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ። የባሮ አዞዎች በሥነ-ምህዳሩ ውስጥ የራሳቸው ሚና ቢኖራቸውም ለሰው ሕይወት አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ። ስለሆነም በወንዙ ዳርቻ እንቅስቃሴ ሲደረግ ተገቢ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። በተለይም አዞ እንዳለ በሚታወቅባቸው ስፍራዎች ወደ ውኃው አለመግባትና የአካባቢውን ባለሙያዎች መመሪያ መከተል የግድ ይላል። የባሮ ወንዝ ለግብርና ልማት ሥራም ከፍተኛ አቅም ካላቸው የውኃ ሀብቶች መካከልም አንዱ ነው። በወንዙ ግራና ቀኝ ያለው ለም መሬት ለመስኖ ልማት እጅግ ጠቃሚ ነው። የአርሶ አደሮችን የምርት አቅም ለማሳደግ፣ የምግብ ዋስትናን ለማጠናከርና የገቢ ምንጭን ለማስፋት እያገዘም ነው ። የባሮ ወንዝ የልማት ዕድል ቢኖረውም ከወቅታዊ የውኃ መጠን መጨመር ጋር የተያያዙ ፈተናዎችም አሉት። በከፍተኛ የዝናብ ወቅት የወንዙ ውኃ ሞልቶ ሲፈስ በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎችን ከቄያቸው ያፈናቅላል። አንዳንዴም በወንዙ ዳርቻ የለሙ ሰብሎች ላይ ጉዳት በማድረስ ምርትን በመቀነስ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጫና ሊፈጥር ይችላል፤ ስለሆነም የጎርፍ ስጋትን ለመቀነስ በወንዙ የውኃ መጠን ላይ ክትትል በማድረግ በተጋላጭ አካባቢዎች የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓትን ማጠናከር ያስፈልጋል። እንዲሁም የወንዙን ዳርቻ እፅዋት መጠበቅና በጎርፍ ሊጎዱ በሚችሉ ቦታዎች ላይ የመሬት አጠቃቀምን በተቀናጀ አግባብ የመምራት አቅምን ማጎልበት አስፈላጊ ነው። የባሮ ወንዝ ለቱሪዝም፣ ለወንዝ ዳርቻ መዝናኛና ለአካባቢያዊ ባህል ተኮር ጉብኝቶች የሚያበረክተው አስተዋጽኦም ቀላል አይደለም። ጋምቤላን የሚጎበኙ ቱሪስቶች የአካባቢውን ተፈጥሮ፣ የወንዝ ዳርቻ ሕይወትና የጋምቤላን ባህላዊ እሴቶች በሚገባ ማወቅና መረዳት የሚችሉበት ሁኔታም ሰፊ ነው። ወንዙ የጋምቤላን የተፈጥሮ ውበት ከማሳየት ባለፈ የኑሮ መሠረት፣ የልማት አቅም፣ የቱሪዝም መስህብና የብዝኃ ሕይወት መገኛ ሆኖም እያገለገለ ነው። የባሮ ወንዝ የጋምቤላ የተፈጥሮ ውበት መገለጫ ነው። የሕዝቧ የኑሮ መጋመጃ እና የወደፊት የልማት ተስፋ መገለጫም በመሆኑ ይህን ሀብት በአግባቡ መጠበቅ ከራስ ባለፈ ለመጪው ትውልድ የተፈጥሮ ጸጋን እና የልማት ዕድልን ማስረከብም ይሆናል።
የተፈጥሮ ገጸ በረከት የሞላበት አስደናቂ ምድር
Oct 31, 2026 292
ጋምቤላ ፤ ጥቅምት 21/2019 (ኢዜአ) ፦ የተፈጥሮ ገጸ በረከት የሞላበት አስደናቂ ምድር በሙሉጌታ ዳምጤ ከአዲስ አበባ በ700 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ በተፈጥሮ ሃብት የታደለ፣ መልማት የሚችል ሰፊ ምድር ያለው፣ ለአትክልትና ፍራፍሬ፣ ለዓሳ ሀብት ልማት ብሎም ለኢንቨስትመንት ምቹና ተመራጭ አካባቢ ነው። እዚህ ክልል መጥቶ ምን ጠፍቶ! ከባሮ ወንዝ ዓሳ አጥምዶ፣ በቆሎ፣ ሩዝ፣ ጥጥ፣ ሰሊጥ እና ማሾ አምርቶ በአረንጓዴው ስፍራ ተዝናንቶ የሚኖርበት ነው። በባሮ ወንዝ ፍሰት፣ በደኖች የነፋስ ሽውታና ውበት፣ በዱር እንስሳት፣ የሕዝቡ ባህላዊ እሴት የክልሉ የብዝሃነት ምልክቶች ናቸው። የወንዞች በረከት፣ የደኖች ጥላና የሕዝቦች አንድነት የተዋሃዱበት ጋምቤላ ክልል የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ውበትና የልማት ተስፋ ማሳያ መሆኑን መናገር ይቻላል። የጋምቤላ ልዩ የተፈጥሮ ሃብት፣ የእድገትና የማንሰራራት መሰረት የሚሆን የሀገር ሃብት የሚገኝበት መሆኑም ይታወቃል። በመሆኑም የክልሉ የብዝሃ ህይወት ሃብት በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ፣ የትምህርትና የባህል ድርጅት /ዩኒስኮ/ በባዮስፌር ሪዘርቭነት የተመዘገቡ የተፈጥሮ ደን ሃብት ባለቤት እንዲሆን አስችሎታል።   የተፈጥሮ ገጸ በረከት የሞላበት አስደናቂው ምድር ጋምቤላ፤ በማጃንግና አኙዋሃ ዞኖች የሚገኙ ጥብቅ የተፈጥሮ የደን ሃብቶቹ በ’’ዩኒስኮ በባዮስፌር ሪዘርቭነት’’ የተመዘገቡ ናቸው። እነዚሁ በባዮስፌር ሪዘርቭነት የተመዘገቡት የተፈጥሮ ጥብቅ ደኖች በውስጣቸው በርካታ የዕፅዋት፣ የእንስሳት፣ የውሃና ሌሎች የብዝሃ ህይወት ሀብቶችን አቅፈው ይዘዋል። ጥብቅ የተፈጥሮ ደኖቹ የአካባቢውን ስነ-ምህዳርና የአየር ንብርት ለውጥ ከመጠበቅ ባለፈ ለቱሪዝም ኢንዱስትሪው ትልቅ አቅም ናቸው። እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2017 በዩኒስኮ በባዮስፌር ሪዘርቭ የተመዘገበው የማጃንግ ጥብቅ የተፈጥሮ የደን ሃብት በቡሬ ሐይቅ፣ በጀይና በዋኪ ፏፏቴዎች፣ በጊሎ ወንዝና በሌሎችም የብዝሃ ህይወት ሃብቶች ያጌጠ ነው። ከክልሉና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት መልካ ኢትዮጵያ የተሰኘ ግብር ሰናይ ድርጀት ባካሄደው ጥናት መሰረት በጥብቅ ደኑ ውስጥ ከ550 በላይ የዕፅዋት፣ 33 የአጥቢ እንስሳት፣ 130 የአዋፋትና ሌሎችም የብዝሃ ህይወት ሃብቶች አሉት።   በ2025 በዩኒስኮ የተመዘገበው የአኙዋሃ ባዮስፌር ሪዘርቭ የተፈጥሮ የደን ሃብት በመካከሉ የጊሎና የአሌሮ ወንዞች አቋርጠውት ያልፋሉ፤ በሰሜና ምዕራብ አቅጣጫ ጠርዝ በባሮ ወንዝ፤ በምስራቅና በደቡብ አቅጣጫ ጠርዝ ደግሞ በአኮቦ ወንዝ ታቅፏል። የተፈጥሮ የደን ሀብቱ ባለው ሜዳማና አረንጓዴያማ መልካ ምድራዊ ገጽታው በመሃሉና በጠርዞቹ ላይ የሚያልፉት ወንዞች ማራኪና ልዩ የውበት ገጽታዎችን አላብሰውታል። ጥብቅ የደን ሃብቱ ከጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ ጋር የተሳሰረ በመሆኑ የብዝሃ ህይወት ሀብቱ ስብጥር ከፍተኛ ነው። የደን ሃብቱ ውስጡ ከ1 ሺህ በላይ የዕጽዋት፣ 69 የአጥቢ እንሰሳት፣ 327 የአዕዋፋትና በተጠቀሱት ትላላቅ ወንዞች ከ113 በላይ የዓሳ ዝርያዎች ያሉት መሆኑ በጥናቱ ተረጋግጧል። በባዮስፌር ሪዘርቭነት የተመገቡት ጥብቅ የተፈጥሮ የደን ሃብቶች የአካባቢውን ስነ-ምህዳርና የአየር ንብረት ሚዛን በማስጠበቅ ረገድ የጎላ አበርክቶ አላቸው።   በባዮስፌር ሪዘርቭነት የተመዘገቡትን ሁለቱን ጥበቅ የተፈጥሮ ደን ሃብቶች ጨምሮ በርካታ የቱሪዝም መስህቦች በክልሉ እንደሚገኙ የገለጹት በክልሉ ቱሪዝም ቢሮ የቱሪዝም መስህቦች መዳረሻና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ ደርባቸው ሸዋለም ናቸው። በተለይም በተፈጥሮ የደን ሃብቶቹ ውስጥ የሚገኙት ፏፋቴዎች፣ ሐይቆች፣ ወንዞች፣ አጥቢ እንስሳቶች፣ የአዕዋፍ ዝርያዎችና ሌሎችም የብዝሃ ህይወት ሃብቶች ለቱሪዝም ኢንዲስትሪው ትልቅ አቅም መሆናቸውን አንስተዋል።   በክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ የደን ዘርፍ ባለሙያው አቶ ፓል ኛክ፤ በክልሉ የግብርና ልማትን በማሳለጥ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ጠንካራ መሰረት መኖሩን ይናገራሉ። በኢትዮጵያ ሁሉም አካባቢዎች ያሉ እምቅ ሃብቶችን በተደመረ አቅም በአግባቡ በማልማት ጥቅም ላይ ማዋል ከተቻለ እድገትና ማንሰራራቷን እውን ማድረግ ይቻላል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም