አርእስተ ዜና
ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ስራዎች ስኬታማነት ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን
Apr 28, 2024 8
ድሬዳዋ/ አዳማ/ ሀዋሳ/ አርባምንጭ ፤ ሚያዚያ 20 /2016(ኢዜአ) ፡- የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ስራዎች ስኬታማነት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ገለጹ። ኮሚሽኑ እስካሁን ባለው ሂደት መሠረታዊና የህዝብ ተሳትፎ ባማከለ የተሳታፊዎች ልየታና መረጣ በ10 ክልሎችና በሁለቱ ከተማ መስተዳድሮች እንዳገባደደ ቀደም ብሎ ተገልጿል። የተሳታፊዎች መረጣ በተካሄደባቸው ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ውስጥ ሰሞኑን አጀንዳ የማሰባሰብ ተግባር እንደሚጀመር ተመልክቷል። ኮሚሽኑ ቅድመ ዝግጅቶች ሲያደርግባቸው ከቆዩት ከተሞች መካካል አሶሳ፣ ድሬዳዋ ፣ አዳማ ፣ ሀዋሳና ወላይታ ሶዶ ከተሞች ይገኙበታል። በእነዚህ ከተሞች በኮሚሽኑ የስራ ሂደቶች ላይ ተሳትፎ የነበራቸውና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት እንዳመለከቱት፤ የምክክር ኮሚሽኑ በእስካሁኑ ሂደት ከታች ጀምሮ ተሳታፊዎች እየለየ መምጣቱ አሳታፊነቱንና ተአማኒነቱን የሚያሳይ መሆኑን ተገንዝበዋል። የድሬዳዋ ነዋሪ አቶ ደረጀ ጉተማ ፤ ኮሚሽኑ በመላው አገሪቱ ዘላቂ ሰላምና መሰራታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት እንዲፈጠር እየሰራ እንደሚገኝ ግንዛቤ እንዳላቸው አመልክተዋል። የምክክር ኮሚሽኑ የሚያከናውናቸው ተግባራት በአገሪቱ ዘላቂ ሰላም በማስፈን የበለፀገች አገር ለትውልድ ለማስተላለፍ እንዲቻል እያመቻቸ መሆኑ የሚበረታታ ነው ብለዋል። አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ተልዕኮ ስኬታማ እንዲሆን የድርሻቸው እንደሚወጡ አቶ ደረጀ ተናግረዋል። ​​​ለኮሚሽኑ ተልዕኮ መሳካት ዜጎች በሙሉ የድርሻችንን ኃላፊነት መወጣት ይገባናል ብለዋል። የአዳማ ከተማ የአገር ሽማግሌዎች ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ፈይሳ መገርሳ በበኩላቸው፤ በኮሚሽኑ በተለያዩ ጊዜ በተዘጋጁ መድረኮች ላይ በመሳተፍ የምክክሩ ዓላማ ላይ በቂ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልጸዋል። በምክክር ሂደቱ ሁሉም የአገር ጉዳይ ያገባናል የሚሉት አካላት መሳተፍ አለባቸው ያሉት አቶ ፈይሳ፤ ከሴቶች፣ ወጣቶች፣ ከአገር ሽማግሌዎችና ከሃይማኖት አባቶች ከተወከሉት አካላት ጋር መድረኮች ላይ በመሳተፍ ሀሳቦችንና ግብዓቶችን ማከላቸውን አውስተዋል። ለምክክር ኮሚሽኑ ስራ መሳካት አስፈላጊው ድጋፍ ማድረጋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል። በሚኖሩበት ሃዋሳና የሲዳማ ክልል የተለያዩ አካባቢዎችም የተጣላን በማስታረቅና በማስማማት የሽምግልና ሃላፊነታቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ የገለጹት ደግሞ የሀዋሳ ከተማ የነዋሪ የሆኑት የሲዳማ ክልል የአገር ሽማግሌ መጋቢ ጢሞቲዎስ በራሳ ናቸው። የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለአገሪቱ ሰላምናአንድነት መጠበቅ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው አመልክተው፤ የቆዩ ችግሮቻችን በመነጋገርና በመመካከር የሚፈቱ ናቸው ብለዋል። ለዚህም ከሚሽኑ እያመቻቸ ያለው ተግባር አበረታችና የሚደግፍ መሆኑን ተናግረዋል። ለምክክር ኮሚሽኑ ውጤታማነት እያንዳንዱ ዜጋ ለአገርና ለህዝብ አንድነት የሚያግዙ ሃሳቦች ማመንጨት እንዳለበትም አመልክተዋል፡፡ ለዚህም የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገልጸው፤ ሲንከባለል የመጣው የኢትዮጵያ ችግር መቋጫ የሚያገኘው በአገራዊ ምክክር ነው ብለዋል፡፡ የወላይታ ሶዶ ነዋሪ ወይዘሮ ብሩክ ባልቻ ፤ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከታች ጀምሮ ተሳታፊዎች እየለየ መምጣቱ አሳታፊነቱንና ተአማኒነቱን የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል። መወያየት ለሁሉ ችግር መፍትሄ መሆኑን አመልክተው፤ በዚህም ባሳለፍናቸው ጊዜያት የተፈጠሩ ችግሮች እልባት ለመስጠት ዕድሉን መጠቀም ይገባናል ሲሉም ተናግረዋል። አሁን ላይ አገራችን በልማት ጎዳና ላይ ትገኛለች ያሉት ወይዘሮ ብሩክ ፤ ይህን በዘላቂ ሰላም ብልጽግናዋን ለማረጋገጥ ምክክሩ ወሳኝ መሆኑንና ለኮሚሽኑ ስራ መሳካት የበኩላቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። ይህ ስራ ከግብ እንዲደርስ ሀሳብ ከመስጠት ጀምሮ ሁሉም ዜጋ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለበትም አመልክተዋል    
ከተማን ውብና ፅዱ በማድረግ ምቹ የመኖሪያ አካባቢ ለመፍጠር የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Apr 28, 2024 24
ሠመራ፤ ሚያዚያ 20 /2016(ኢዜአ)፦ ከተማን ውብና ፅዱ በማድረግ ምቹ የመኖሪያ አካባቢ ለመፍጠር የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉ የሠመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አብዱ ሙሳ ተናገሩ። እንደ አገር የተጀመረው የአካባቢ ጽዳትና ውበት ዘመቻ በአፋር ክልል ደረጃ ባለፈው ሳምንት መጀመሩን ተከትሎ የከተማ አስተዳድሮችና ወረዳዎችም ዘመቻውን እየተገበሩት ይገኛሉ። "ብክለት ይብቃ-ሁሉም ይንቃ" በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ያለው የአካባቢ ብክለትን የማስወገድ ንቅናቄ መድረክ በክልሉ እስከ መስከረም 30 ቀን 2017ዓ.ም የሚቆይ እንደሆነም ተገልጿል። ዘመቻውን በሠመራ ሎጊያ ከተማ ያስጀመሩት ከንቲባ አብዱ ይህን የንቅናቄ ዘመቻ በተከታታይነት የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል። የመንግስት ተቋማት ሆቴሎችና የግል ተቋማት በጽዳት ዘመቻው ተሳታፊዎች መሆናቸውን የገለፁት ከንቲባው፤ ከተማችንን ውብ፣ ፅዱ እና ለነዋሪዎች ምቹ የመኖሪያ ሥፍራ የመፍጠሩ ስራ ዘላቂና የዘወትር ትኩረታችን ነው ብለዋል። በዚሁ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የክልሉ ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ሃላፊ ኢንጂነር ገቡ መሐመድ በበኩላቸው በአገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን መርሃ ግብር ማከናወን መጀመራቸውን ገልፀዋል። ምክትል ሃላፊው አክለውም ስራዎቻችንን በብቃት ልንፈፅም የምንችለው ከብክለት ፅዱ የሆነ አካባቢ መፍጠር ሲቻል ነው ብለዋል። በጽዳት ሥራው ተሳታፊ ከሆኑት የሠመራ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ አምቢያ አብዱ በበኩላቸው የከተማችንን ውበት ንፁህ በማድረግ እንግዶች ወደ አካባቢያችን በመጡ ጊዜ የሚረኩበት እና በጥሩ የሚመለከቱት መሆን ይኖርበታል ብለዋል። ሰለሆነም ለከተማዋ መደረግ ያለበትን ህብረተሰብን ከማስተባበር ጨምሮ ፅዱ እና ከብክለት ነፃ የማድረግ ስራ ላይ በግንባር ቀደምትነት እሳተፋለሁ ብለዋል።    
ከ500 ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ተመርቶ ለአርሶ አደሩ እየተሰራጨ ነው- የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ
Apr 28, 2024 41
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2016(ኢዜአ)፦ የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ከ500 ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ተመርቶ ለአርሶ አደሩ እየተሰራጨ መሆኑን አስታወቀ። ኢንተርፕራይዙ ምርታማነታቸው ከፍተኛ የሆኑና በሽታን መቋቋም የሚችሉ ከ20 በላይ የሰብል ዓይነቶች ምርጥ ዘር እያመረተ መሆኑን ገልጿል። የኢንተርፕራይዙ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ጫላ አበበ ለኢዜአ እንዳሉት ኢንተርፕራይዙ በክልሉ ከ80 በመቶ በላይ እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ ከ60 በመቶ በላይ ምርጥ ዘር ያቀርባል። ኢንተርፕራይዙ በኩታ ገጠም በተደራጁት አርሶ አደሮች፣ ባለሀብቶችና በራሱ የዘር ብዜት እርሻዎች በዚህ ዓመት ከ500 ሺህ በላይ ኩንታል የተመረተ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 300 ሺህ ኩንታል ንጹህ ምርጥ ዘር ለስርጭት መዘጋጀቱን ገልጸዋል። እስካሁንም ከ60 ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን ተናግረዋል። ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ከሚያስችሉ ውስጥ ምርጥ ዘር በስፋት ለአርሶ አደሩ እንዲደርስ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም ኢንተርፕራይዙ በራሱ በሚያለማቸው በባሌ፣አርሲ እና በምዕራብ ወለጋ በሚገኙ 13 እርሻዎች ላይ እንደ አካባቢው ስርዓተ ምህዳር ተስማሚነት ምርጥ ዘር እየተባዛ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም ምርታማነታቸው ከፍተኛ የሆኑና በሽታን መቋቋም የሚችሉ የስንዴ፣ ገብስ፣ በቆሎ፣ ሩዝ፣ ጤፍን ጨምሮ ከ20 በላይ የሰብል ዓይነት ምርጥ ዘሮችን በማባዛት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።  
የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ይካሄዳል
Apr 28, 2024 48
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20 /2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ይካሄዳል:: የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና መካከል ዛሬ ይደረጋል። የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ከቀኑ 9 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይከናወናል። ሀዋሳ ከተማ በሩብ ፍጻሜው አርባ ምንጭ ከተማን 2 ለ 0 እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና ፋሲል ከነማን 4 ለ 1 በማሸነፍ ለግማሽ ፍጻሜው ማለፋቸው ይታወቃል።   በአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ የሚመራው ሀዋሳ ከተማ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎች ቤንች ማጂ ቡና እና መቻልን አሸንፏል። ክለቡ በኢትዮጵያ ዋንጫ እስከ አሁን ባደረጋቸው 3 ጨዋታዎች 7 ግቦችን ከመረብ ሲያሳርፍ 1 ጎል አስተናግዷል። ተጋጣሚው ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ በዚህ ውድድር አስቀድሞ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ወልዲያ እና ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማን ማሸነፉ ይታወቃል።   በአሰልጣኝ ነጻነት ክብሬ የሚመሩት ቡናማዎቹ በውድድሩ ባደረጓቸው 3 ጨዋታዎች 10 ጎሎችን ሲያስቆጥሩ የተቆጠረባቸው 1 ግብ ብቻ ነው። የሁለቱ ክለቦች አሸናፊ ከወላይታ ድቻ በፍጻሜው የሚገናኝ ይሆናል። በኢትዮጵያ ዋንጫ ትናንት በተደረገው የመጀመሪያ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ኢትዮጵያ መድንን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለፍጻሜ ማለፉ ይታወቃል።   የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ በቀጣዩ ዓመት በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን ወክሎ ይሳተፋል።  
ስራ ከድህነት የምንወጣበትና የአሸናፊነት ታሪካችንን በደማቁ የምናጽፍበት መሳሪያችን ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Apr 27, 2024 105
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2016(ኢዜአ)፦ ስራ ከድህነት የምንወጣበትና ደማቁን የአሸናፊነት ታሪካችንን በደማቁ የምናጽፍበት መሳሪያችን ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡ ይህን እውን ለማድረግ ደግሞ ሰላም ቁልፉ መንገድ ነው ሲሉም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል። በአጭር ጊዜ ወደ ስራ የተመለሰው የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክም ሆነ ሌሎች የክልሉ የልማት ስራዎችን ለማጠናከር ሰላም ወሳኝ ነው ብለዋል።   በህልውና ጦርነቱ የኢንዱስትሪ መንደሮቿን ጨምሮ የከፋ ጉዳት የደረሰባት የኮምቦልቻ ከተማ በተገኘው ሰላም ወደ ቀደመ ድምቀቷ መመለሷን ዛሬ ተመልክተናል ሲሉም ገልጸዋል። በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ የጎበኘናቸው አምራች ድርጅቶች ከክልሉ አልፎ ለሀገር እድገት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያላቸውን ምርቶች በሙሉ አቅም እና ጥራት እያመረቱ እንደሆነ አይተናል ብለዋል።   ምርቶቹ በከፍተኛ ጥራት ተመርተው ወደ ውጭ የሚላኩ ናቸው ያሉት አቶ ተመስገን በቀጣይ የሀገር ውስጥ ገበያውን እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል ሲሉም ጠቁመዋል፡፡ መንግስትም ለሀገር ውስጥ ምርት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። በሌላ በኩል ጥያቄዎችን ከሰላም ውጭ በመሳሪያ ለማስፈጸም የሚንቀሳቀስ ሃይል ወደ ውይይትና ምክክር እንዲመለስ ከፌዴራል መንግስትም ሆነ ከክልሉ የቀረበውን ጥሪ እንዲጠቀም በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እወዳለሁ ብለዋል። ከሰላም እና ከውይይት ውጭ በጠመንጃ ጥያቄን ለማስመለስ የሚደረግ ሙከራ የክልሉን ልማት ወደ ኋላ የሚመልስ፣ የማይሳካና አክሳሪ በመሆኑ ይህን ለማስቆም የፌዴራልም ሆነ የክልሉ መንግስት ህግና ስርዓትን ለማስከበር የጀመረውን ስራ ይቀጥላል ሲሉም አስታውቀዋል።
የሚታይ

በአዲስ አበባ ኢንዱስትሪዎች የሚገጥሟቸውን የአሰራር ማነቆዎች በመቅረፍ  የማምረት አቅማቸውን  ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Apr 27, 2024 66
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2016(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የሚገጥሟቸውን የአሰራር ማነቆዎች በመቅረፍ የማምረት አቅማቸውን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ሲካሔድ የቆየው ከተማ አቀፍ "የኢትዮጵያ ታምርት፤ እኛም እንሸምት" ንቅናቄ በዛሬው እለት ተጠናቋል፡፡ በማጠናቀቂያ መርሃ ግብሩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡   የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ በመዲናዋ በርካታ አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች በስራ ላይ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ኢንዱስትሪዎች በስራ እድል ፈጠራ፣ በውጭ ምንዛሬ ግኝት እና በኤክስፖርት ዘርፍ ጉልህ ሚና እያበረከቱ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለአንድ አገር ኢኮኖሚ ሽግግር ወሳኝ ሚና እንዳለው የተናገሩት ከንቲባዋ፤ ከዚህ አኳያ በአዲስ አበባ በአስር ዓመቱ የልማት እቅድ በተለይ የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለኢኮኖሚያዊ እድገት ያለውን ድርሻ ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ አምራች ኢንዱስትሪው የሚገጥመውን የአሰራር ማነቆ መፍታት ደግሞ ትኩረት ከተሰጠባቸው ጉዳዮች መካከል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ከዚህ አኳያ ባለፉት ሶስት ዓመታት 162 የመስሪያ ቦታዎች ለኢንዱስትሪዎች እንዲሰጡ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡ በውሃ፣ መብራት፣ መንገድና መሰል መሰረተ ልማቶች ላይ ይገጥማቸው የነበረውን ችግር ለማቃለል በተሰራ ስራ ትርጉም ያለው ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን አመላክተዋል፡፡ ከተማ አስተዳደሩ የኢንዱስትሪዎችን አቅም ለማሳደግ የአገር ውስጥ ምርቶችን መጠቀም መጀመሩን የጠቆሙት ከንተባዋ፤ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡   የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ በበኩላቸው፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በከተማ አስተዳደሩ ስር በሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ተመርተው ወደ ውጪ ከተላኩ የተለያዩ ምርቶች ከ667 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ ገቢ ምርቶችን በአገር ውስጥ መተካት መቻሉንም እንዲሁ፡፡ በመርሃ ግብሩ የተሻለ ካፒታል በማስመዝገብ የደረጃ ሽግግር ላደረጉ ኢንዱስትሪዎች እውቅና ተሰጥቷል፡፡ የደረጃ ሽግግር ካደረጉት መካከል ወጣት እየሩስዓለም መለሰ እና ወጣት ናስር የኑስ መንግስት ባመቻቸላቸው የመስሪያ ቦታና የብድር አቅርቦት ለደረጃ ሽግግር መብቃታቸውን ገልጸዋል፡                            
የብዝኃ ማንነት ባህላዊ ኃብቶቻችንን በመጠበቅ በሕዝቦች መካከል ትስስርና የወል ትርክት ለመገንባት እየተሰራ ነው- አቶ ቀጀላ መርዳሳ
Apr 27, 2024 64
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2016(ኢዜአ)፦ያሉንን የብዝኃ ማንነት ኃብቶችን በመጠበቅ በሕዝቦች መካከል ትስስርና የወል ትርክትን ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ ቀጀላ መርዳሳ ገለጹ። የፊቼ ጫምባላላ በዓል የማጠቃለያ መርሃ-ግብር በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ ተካሂዷል። የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ ቀጀላ መርዳሳ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ፊቼ ጫምባላላ ለሀገር ግንባታና ለማኅበረሰብ ትስስር ሚናው የጎላ መሆኑን አንስተዋል፡፡   የብዝኃ ማንነት ባህላዊ ኃብቶችን በማልማትና በማስተዋወቅ በሕዝቦች መካከል ትስስርንና የወል ትርክቶችን ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። ከዚህ አኳያ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችን ባህላዊ እሴቶች ለማልማት በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በዘመናት ቅብብሎሽ ዛሬ ላይ የደረሰው የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ ከሲዳማ ሕዝብ አልፎ የሀገርና የዓለም ኃብት እንዲሆን ከፍተኛ ሥራ መከናወኑን ገልፀዋል።   የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲዳማ ባህል ማዕከል የሚገነባበት ቦታ በመስጠትም አዲስ አበባ የሁሉም ቤት መሆኗን በተግባር ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡ ይህን የዓለም ቅርስ የሆነ አኩሪ በዓል በመጠበቅ ትውልዱ በአግባቡ እንዲረዳው ማድረግ እንደሚገባም አመላክተዋል።   የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ቡዜና አልከድር፤ አዲስ አበባ ብዝኃነትን በማስተናገድ ፈጣን ልማትን በማረጋገጥ ለኑሮና ለሥራ የምትመች ከተማ መሆኗን በተግባር እያረጋገጠች ነው ብለዋል፡፡ ፍቼ ጫምባላላ የአብሮነት በዓል በመሆኑ ለሕብረ-ብሔራዊ እህትማማችነትና ወንድማማችነት እንዲሁም ለጠንካራ ሀገረ-መንግሥት ግንባታ ለማዋል ሁሉም የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።   ፊቼ ጫምባላላ እና መሰል ባህላዊ ፌስቲቫሎችን በቱሪዝም መስህብነት በማስተዋወቅ ጥቅም ላይ በማዋል ተወዳዳሪ የቱሪዝም መዳረሻዎች በመፍጠር ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይገባል ያሉት ደግሞ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ ናቸው። የቱሪዝም ሚኒስቴርም ፊቼ ጫምባላላን ጨምሮ የሲዳማ ክልል የቱሪዝም ኃብቶች እንዲጠበቁ፣ እንዲለሙና እንዲተዋወቁ ለማድረግ ከክልሉ መንግሥት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በበዓሉ ላይ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የፌዴራል የሥራ ኃላፊዎች፣ የሲዳማ ክልልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የሲዳማ ተወላጆችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ፊቼ ጫምባላላ የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ከማይዳሰሱ ቅርሶች ምድብ የሰው ልጆች ወካይ ቅርስ ሆኖ ኅዳር 18 ቀን 2008 ዓ.ም የዓለም ኃብት ሆኖ ተመዝግቧል።  
ማስታወቂያ
ኢዜአ
Feb 7, 2023 18044
ኢዜአ
ፖለቲካ
ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ስራዎች ስኬታማነት ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን
Apr 28, 2024 8
ድሬዳዋ/ አዳማ/ ሀዋሳ/ አርባምንጭ ፤ ሚያዚያ 20 /2016(ኢዜአ) ፡- የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ስራዎች ስኬታማነት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ገለጹ። ኮሚሽኑ እስካሁን ባለው ሂደት መሠረታዊና የህዝብ ተሳትፎ ባማከለ የተሳታፊዎች ልየታና መረጣ በ10 ክልሎችና በሁለቱ ከተማ መስተዳድሮች እንዳገባደደ ቀደም ብሎ ተገልጿል። የተሳታፊዎች መረጣ በተካሄደባቸው ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ውስጥ ሰሞኑን አጀንዳ የማሰባሰብ ተግባር እንደሚጀመር ተመልክቷል። ኮሚሽኑ ቅድመ ዝግጅቶች ሲያደርግባቸው ከቆዩት ከተሞች መካካል አሶሳ፣ ድሬዳዋ ፣ አዳማ ፣ ሀዋሳና ወላይታ ሶዶ ከተሞች ይገኙበታል። በእነዚህ ከተሞች በኮሚሽኑ የስራ ሂደቶች ላይ ተሳትፎ የነበራቸውና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት እንዳመለከቱት፤ የምክክር ኮሚሽኑ በእስካሁኑ ሂደት ከታች ጀምሮ ተሳታፊዎች እየለየ መምጣቱ አሳታፊነቱንና ተአማኒነቱን የሚያሳይ መሆኑን ተገንዝበዋል። የድሬዳዋ ነዋሪ አቶ ደረጀ ጉተማ ፤ ኮሚሽኑ በመላው አገሪቱ ዘላቂ ሰላምና መሰራታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት እንዲፈጠር እየሰራ እንደሚገኝ ግንዛቤ እንዳላቸው አመልክተዋል። የምክክር ኮሚሽኑ የሚያከናውናቸው ተግባራት በአገሪቱ ዘላቂ ሰላም በማስፈን የበለፀገች አገር ለትውልድ ለማስተላለፍ እንዲቻል እያመቻቸ መሆኑ የሚበረታታ ነው ብለዋል። አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ተልዕኮ ስኬታማ እንዲሆን የድርሻቸው እንደሚወጡ አቶ ደረጀ ተናግረዋል። ​​​ለኮሚሽኑ ተልዕኮ መሳካት ዜጎች በሙሉ የድርሻችንን ኃላፊነት መወጣት ይገባናል ብለዋል። የአዳማ ከተማ የአገር ሽማግሌዎች ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ፈይሳ መገርሳ በበኩላቸው፤ በኮሚሽኑ በተለያዩ ጊዜ በተዘጋጁ መድረኮች ላይ በመሳተፍ የምክክሩ ዓላማ ላይ በቂ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልጸዋል። በምክክር ሂደቱ ሁሉም የአገር ጉዳይ ያገባናል የሚሉት አካላት መሳተፍ አለባቸው ያሉት አቶ ፈይሳ፤ ከሴቶች፣ ወጣቶች፣ ከአገር ሽማግሌዎችና ከሃይማኖት አባቶች ከተወከሉት አካላት ጋር መድረኮች ላይ በመሳተፍ ሀሳቦችንና ግብዓቶችን ማከላቸውን አውስተዋል። ለምክክር ኮሚሽኑ ስራ መሳካት አስፈላጊው ድጋፍ ማድረጋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል። በሚኖሩበት ሃዋሳና የሲዳማ ክልል የተለያዩ አካባቢዎችም የተጣላን በማስታረቅና በማስማማት የሽምግልና ሃላፊነታቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ የገለጹት ደግሞ የሀዋሳ ከተማ የነዋሪ የሆኑት የሲዳማ ክልል የአገር ሽማግሌ መጋቢ ጢሞቲዎስ በራሳ ናቸው። የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለአገሪቱ ሰላምናአንድነት መጠበቅ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው አመልክተው፤ የቆዩ ችግሮቻችን በመነጋገርና በመመካከር የሚፈቱ ናቸው ብለዋል። ለዚህም ከሚሽኑ እያመቻቸ ያለው ተግባር አበረታችና የሚደግፍ መሆኑን ተናግረዋል። ለምክክር ኮሚሽኑ ውጤታማነት እያንዳንዱ ዜጋ ለአገርና ለህዝብ አንድነት የሚያግዙ ሃሳቦች ማመንጨት እንዳለበትም አመልክተዋል፡፡ ለዚህም የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገልጸው፤ ሲንከባለል የመጣው የኢትዮጵያ ችግር መቋጫ የሚያገኘው በአገራዊ ምክክር ነው ብለዋል፡፡ የወላይታ ሶዶ ነዋሪ ወይዘሮ ብሩክ ባልቻ ፤ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከታች ጀምሮ ተሳታፊዎች እየለየ መምጣቱ አሳታፊነቱንና ተአማኒነቱን የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል። መወያየት ለሁሉ ችግር መፍትሄ መሆኑን አመልክተው፤ በዚህም ባሳለፍናቸው ጊዜያት የተፈጠሩ ችግሮች እልባት ለመስጠት ዕድሉን መጠቀም ይገባናል ሲሉም ተናግረዋል። አሁን ላይ አገራችን በልማት ጎዳና ላይ ትገኛለች ያሉት ወይዘሮ ብሩክ ፤ ይህን በዘላቂ ሰላም ብልጽግናዋን ለማረጋገጥ ምክክሩ ወሳኝ መሆኑንና ለኮሚሽኑ ስራ መሳካት የበኩላቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። ይህ ስራ ከግብ እንዲደርስ ሀሳብ ከመስጠት ጀምሮ ሁሉም ዜጋ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለበትም አመልክተዋል    
የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
Apr 27, 2024 69
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2016 (ኢዜአ)፡- የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። መስተዳድር ምክር ቤቱ በዋናነትም ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ለኢንቨስትመንት የተዘጋጁ መሬቶችን እንዲሁም በመልሶ ማልማት ከጁገል ዙሪያ ለተነሱ የገበያ ቦታዎች የተዘጋጁ መሬቶችን እና በሸዋበር ታይዋን ተብሎ በሚጠራው የገበያ ስፍራ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ አግባብነት ላላቸው አካላት የተዘጋጁ የመሬት ጥያቄ ላይ በስፋት ተወያይቶ አጽድቋል። ለኢንቨስተሮች የመሬት ምደባ የተደረገላቸው በሚሰማሩበት የልማት መስክም ፋይዳ ያላቸውና ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስለመሆናቸው ተጠቁሟል።   መስተዳድር ምክር ቤቱም የተሰጠው መሬት ለተፈለገው ልማት እንዲውል በአፋጣኝ ወደ ስራ እንዲገቡ አቅጣጫ ማስቀመጡን ከሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል። መስተዳድር ምክር ቤቱ ከዚህ በተጨማሪም በሌሎች አጀንዳዎች ዙሪያ ውይይት በማካሄድ ውሳኔ አሳልፏል።
የኢትዮጵያ የዓለም የዲፕሎማሲ ስብት ማዕከልነት እየጨመረ መጥቷል
Apr 27, 2024 94
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የዓለም የዲፕሎማሲ ስብት ማዕከልነት እየጨመረ መምጣቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ተናገሩ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 44ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና ሰጥቷል። በመርሃ ግብሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ስብሰባው "ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ የትምህርት ስርዓቶች በመገንባት በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ፣ የሕይወት ዘመን ጥራትና አግባብነት ያለው የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት" በሚል መሪ ሃሳብ መካሄዱ ይታወሳል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ኢትዮጵያ የዓለም የዲፕሎማሲ ስብት ማዕከልነቷ እየጨመረ መጥቷል። የሀገሪቱ የገጽታ ግንባታ ላይ በተሰራ ስራና ቀደም ሲል በነበራት አኩሪ ታሪክ በዓለም የዲፕሎማሲ ስብት ማዕከልነቷ እያደገ መጥቷል ነው ያሉት። ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ነጻነትና አንድነት ላበረከተችው አስተዋጽኦ የአፍሪካ መዲና ለመሆን በቅታለች።   የቀደሙ የኢትዮጵያ መሪዎች በሰሩት ጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራ የሕብረቱ መቀመጫ አዲስ አበባ ሊሆን ችሏል ብለዋል። የተወሰኑ ሀገራት በተለያዩ ጊዜያት የሕብረቱን መቀመጫ ወደ ሌላ ሀገር ለማዛወር ያደረጉት ጥረት በኢትዮጵያ መሪዎች ጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራ ሳይሳካ መቅረቱን አስታውሰዋል።   በ37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጉባኤው በስኬት እንዲጠናቀቅና የኢትዮጵያ ከፍታ እንዲጨምር ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይም የበለጠ በቅንጅት በመስራት እንግዳ ተቀባይነታችንን ለዓለም እያስመሰከርን መቀጠል አለብን ብለዋል።   የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በዚሁ ጊዜ፤ 37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 44ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በከፍተኛ ቅንጅት በስኬት መጠናቀቁን አስታውሰዋል። በሕብረቱ ስብሰባ ከ8 ሺህ በላይ እንግዶች ተሳትፈው በሰላም ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውንም ገልጸዋል። ለዚህም የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ የጸጥታ አካላት፣ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ስብሰባው በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ተናግረዋል።    
ሴቶች በሀገራዊ ምክክር ሂደት የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል -ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
Apr 27, 2024 91
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 19/2016(ኢዜአ)፡- ሴቶች በሀገራዊ ምክክር ሂደት የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የሀገረ መንግስት ግንባታው ውጤታማ እንዲሆን ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አስታወቁ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሴቶችን ተሳትፎ ለማጉላት "አገራዊ ምክክር ለአንቺ፤ ስለኢትዮጵያ በአንቺ፤ ኢትዮጵያ እየመከረች ነው" በሚል መሪ ሀሳብ የምክክር መድረክ በማካሄድ ላይ ይገኛል። ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ አካታች ሀገራዊ ምክክር ማካሔድ ብሔራዊ መግባባትን የመፍጠር እና ተቀራርቦ የመስራት ባህልን ለማጎልበት ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል። በብሔራዊ ምክክር ያለፉ አገራት በጦርነት ከሚገኝ ጊዜያዊ መፍትሔ ይልቅ ለንግግርና ምክክር ቅድሚያ በመስጠታቸው ዘላቂ ሰላምን በመፍጠር የተሻለ ኢኮኖሚ እየገነቡ እንደሚገኙ ተናግረዋል።   በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘው ሀገራዊ ምክክር የተሻለ ሀገር ለመገንባት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ስላለው ሴቶች ገንቢ ተሳትፏቸውን ለማበርከት መዘጋጀት እንደሚኖርባቸው አስገንዝብዋል። በኢትዮጵያ በሚፈጠሩ አለመግባባቶች እና የሃሳብ ልዩነቶች ሴቶች ግንባር ቀደም የጉዳት ሰለባ መሆናቸውን አንስተዋል። ለዚህም በሀገረ መንግስት ግንባታ የሴቶች ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ በሀገራዊ ምክክር ሂደት ላይ ወሳኝ ተሳትፏቸውን ማጉላት እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል። ስልታዊ መፍትሔን በማበጀት ረገድ ሴቶች የተሰጣቸው ተፈጥሯዊ ፀጋ የላቀ በመሆኑ ምክክሩ ላይ የሚያደርጉት ተሳትፎ ቀላል የሚባል እንዳልሆነም አብራርተዋል። በሀገራዊ ምክክሩ ላይ የሴቶች ድምፅ ትልቅ ቦታ እንደሚሰጠው በማመን በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ያሉ ሴቶች የነቃ ተሳትፎ ሊያደርጉ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።  
በዕቅድ መመራት ካልቻልን ለህዝቡ የገባነውን ቃል ማሳካት አንችልም - አቶ ሽመልስ አብዲሳ
Apr 27, 2024 86
አዳማ፤ ሚያዝያ 19/2016(ኢዜአ)፦በዕቅድ መመራት ካልቻልን ለህዝቡ የገባነውን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ቃል አናሳካም ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ። በክልል ያለፉት ዘጠኝ ወራት የመንግሥትና የፓርቲ የስራ አፈፃፀም ክንውንና የ2017 ዓ.ም መነሻ ዕቅድ ላይ ያተኮረ ግምገማ በአዳማ አባገዳ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ይገኛል ። በመድረኩ ላይም አቶ ሽመልስ እንደገለጹት በዕቅድ መመራት ካልተቻለ ለህዝቡ የተገባውን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ስራዎችን ማሳካት አይቻልም ብለዋል። እቅዱ የሚሳካው በተሰጠው አቅጣጫ በአግባቡ ሲተገበር መሆኑን ገልጸው ከዚህ አኳያ የተሰጠ አቅጣጫ ቆጥሮ በመቀበል ያለመተግበር ክፍተቶች እንዳሉም ጠቁመዋል። የልማት፤ የሰላም፣ የአገልግሎትና መልካም አስተዳደር ውጤቶች የምዘና ዝንባሌ በትንሽ ድሎች መዘናጋት እየፈጠረ ነው ያሉት አቶ ሽመልስ ከዚህ አስተሳሰብና ተግባር መውጣት አለብን ሲሉም አሳስበዋል። የ2017 ዓ.ም ዕቅድም በዚህ መልኩ መፈፀም እንደማይቻል ገልጸው መድረኩ አመራሩ የእቅዱን ማስፈፀሚያ ስልቶች በሚገባ ወደ መሬት ለማውረድ የሚያስችል አቅጣጫ የሚቀመጥበት መሆኑንም ተናግረዋል።   በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ በበኩላቸው መድረኩ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለህዝቡ የተገባውን ቃል እውን ከማድረግ አኳያ የታዩ ጥንካሬና ድክመቶችን በመለየት ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም በየአካባቢው የሚገኙትን አቅሞችና አማራጮች በመለየት ለዕቅዱ ውጤታማነት የምንጠቀምበት ነው ሲሉም አስረድተዋል። ፓርቲው ለህዝቡ የገባውን ቃል ከማሳካት፣ ጽንፈኝነትን ከመታገልና አስተማማኝ ሰላም ከማስፈን እንዲሁም የተዛቡ አመለካከቶችን ከማረም ጀምሮ ጠንካራ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የሚሰራበት መሆኑንም አስረድተዋል።   ጠንካራ ድርጅታዊ ቁመና መፍጠር ውስጣዊ ትግላችንን ማጠናከር ነው ያሉት አቶ ፍቃዱ ሰላምን ማስፈን ፣ልማትና መልካም አስተዳደርን ማረጋገጥና አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል የሚፈትሽበት ነው ብለዋል። መድረኩ ያለፉት ዘጠኝ ወራት የመንግስትና የፓርቲ ስራ ክንውን፣ ጠንካራና ደካማ ጎኖች እንዲሁም የ2017 ዓ.ም የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ማስፈፀሚያ የመነሻ ዕቅድ ቀርቦ ምክክር ይካሄድበታል ተብሏል።
የአማራ ክልል ከፍተኛ ልዑክ በዋሽንግተን ዲሲ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች ጋር ምክክር አደረገ
Apr 27, 2024 105
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2016 (ኢዜአ)፡- ወደ ሰሜን አሜሪካ የሥራ ጉዞ ያደረገው የአማራ ክልል ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በዋሽንግተን ዲሲ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ አምባሳደር እና ዲፕሎማቶች ጋር ምክክር አደረገ። ልዑኩ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች በመዘዋወር ከኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ ከልዩ ልዩ ኩባንያዎች፣ ከዩኒቨርስቲዎች እንዲሁም ከተለያዩ ተቋማትና አካላት ጋር ውይይት እና ምክክር አድርጓል። በዋሽንግተን ዲሲ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር የተደረገው ውይይት ደግሞ መንግሥትና ኤምባሲው ማከናወን ስለሚገባቸው ቀጣይ ሥራዎች ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተገልጿል።   በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ እና ዲፕሎማቶች ከልዑካን ቡድኑ ጋር ባደረጉት ምክክር፥ የተሠራው ሥራ ውጤታማ እንደነበር ገልጸው፤ በቀጣይም ከዚህ የተሻለ ውጤት ማስገኘት የሚያስችሉ ሥራዎችን ለመሥራት እንደ መነሻ ሆኖ ያገለግላል ብለዋል። በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ እና በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ ኅላፊ ዶክተር አህመዲን መሐመድ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ሪፎርም እንዲሁም ወቅታዊ የሀገሪቱን እና የክልሉን ሁኔታ በተመለከተ ለዲፕሎማቶች መረጃ እና ማብራሪያ ሰጥዋል። የልዑካን ቡድኑ በአሜሪካ በነበረው ቆይታ ለኢትዮጵያ ጠቃሚ የሆኑ ተግባራትን ማከናወኑን አውስተው በቀጣይ ከዚህ ጉዞ የተገኙት ተሞክሮዎች ተቀምረው ከትውልደ- ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያን ጋር የሚደረጉ ውይይቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ መናገራውን ከዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና ተሰጠ
Apr 26, 2024 92
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 18/2016(ኢዜአ)፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 44ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈፃሚ የምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና ሰጠ። በመርሃ ግብሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አጽቀሥላሴ፣የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርቱካን አያኖ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ስብሰባው"ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ የትምህርት ስርዓቶች በመገንባት በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ፣የሕይወት ዘመን ጥራትና አግባብነት ያለው የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት“ በሚል መሪ ሃሳብ መካሄዱ ይታወሳል።   የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርቱካን አያኖ በዚሁ ጊዜ ፤37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 44ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈፃሚ የምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በከፍተኛ ቅንጅት በስኬት መጠናቀቁን አስታውሰዋል ። በሕብረቱ ስብሰባ ከ8 ሺህ በላይ እንግዶች ተሳትፈው በሰላም ወደ አገራቸው መመለሳቸውን ገልጸዋል። ለዚህም የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ፣የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣የጸጥታ አካላት ፣የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ስብሰባው በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ተናግረዋል። ይህም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች ለማስከበር የሚያስችሉ የተለያዩ ስራዎች እንዲከናወኑ ማድረግ አስችሏል ብለዋል።  
በተቋማት የሚታዩ ብልሹ አሰራርና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ በሚዲያ ተቋማቱ ቅርንጫፎች የተጀመሩ የይዘት ሥራዎች መጠናከር አለባቸው
Apr 26, 2024 120
አዳማ፤ሚያዝያ 18/2016(ኢዜአ)፡- በተቋማት የሚታዩ ብልሹ አሰራርና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ በሚዲያ ተቋማቱ ቅርንጫፎች የተጀመሩ የይዘት ሥራዎች መጠናከር እንዳለባቸው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና የአመራር አባላት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አዳማ ቅርንጫፍና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን አዳማ ማሰራጫ ጣቢያን ጎብኝተዋል። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ እውነቱ አለነ በዚህ ወቅት እንደገለፁት አዳማ ከአዲስ አበባ ቀጥላ ሁለተኛዋ የቱሪዝምና ኮንፈረንስ ከተማ መሆኗን ጠቅሰዋል። በሚዲያ ተቋማቱ ቅርንጫፎች እየተከናወኑ ያሉት ኩነቶችና የፕሮጀክት ስራዎች የዋናው መስሪያ ቤትን ጫና ከመቀነሳቸው በተጓዳኝ ለህብረተሰቡም የቀረቡ ናቸው ብለዋል። በተለይም የዴሞክራሲ ተቋማት በምልከታና በዳሰሳ ጥናት የሚያገኙትን ግኝቶች ከኩነት ባለፈ የፕሮጀክት ስራዎችን በመስራት ረገድ የቅርንጫፎቹ ሙያተኞች እያከናወኑ ያሉትን አበረታች ተግባር አጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል። የዞኖችና የከተማ አስተዳደሮችን ብልሹ አሰራርና የመልካም አስተዳደር እጦት ችግሮችን ከመፍታት አንጻር እየተሰሩ ያሉ የይዘት ስራዎች በቀጣይም ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ነው ያሉት። ቅርንጫፎቹ ከዋናው መስሪያ ቤት ጋር በቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ያላቸው ትስስር፣ የዜና ቅብብሎሽና ቅንጅታዊ ስራ ይበልጥ መጠናከር ይገባዋል ብለዋል። የቋሚ ኮሚቴው አባልና የሚዲያ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ አቡኔ ዓለም በበኩላቸው የኢዜአ አዳማ ቅርንጫፍ ከቢሮ አደረጃጀት ጀምሮ ጥሩ ይዘት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ቅርንጫፉ ከዕለታዊ ኩነቶች ባለፈ በከተማዋ በሚካሄዱ ሀገራዊና ክልላዊ መድረኮች የሀገሪቷን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ስኬቶች፣ ውስንነቶችና የቀጣይ ትኩረትን መሰረት ያደረጉ የፕሮጀክትና የዕቅድ ሥራዎች ማከናወኑን በጥሩ ጎን ተመልክተናል ብለዋል። በተለይም በአዳማ የሚካሄዱ ሀገራዊና ክልላዊ ሥራዎች ቅርንጫፉ የሚሸፍናቸውና ከዋናው መስሪያ ቤት የጊዜ፣ የትራንስፖርትና የወጪ ጫናዎችን የቀነሰ መሆኑን ገልጸዋል። ቅርንጫፉ በአካባቢው ካሉ ሌሎች ሚዲያዎች ጋር ያለውን ትስስር ማጠናከር አለበት ያሉት ወይዘሮ አቡኔ፤ በዙሪያው ባሉ አካባቢዎችም ተንቀሳቅሶ ሽፋን መስጠት እንዳለበት አሳስበዋል። የቋሚ ኮሚቴው አባላትና የአመራር አካላቱ በተመሳሳይ የኢቲቪ የአዳማ ቅርንጫፍ የማሰራጫ ጣቢያን የተመለከቱ ሲሆን ጣቢያው ጥራትና ተደራሽነት ላይ በትኩረት መስራት እንዳለበት አመልክተዋል።    

ማህበራዊ
በምስራቅ ኢትዮጵያ ለሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ዲጂታል የመማር ማስተማር ስራን የሚያሳልጥ ስቱዲዮ ተመርቆ ለአገልግሎት በቃ
Apr 27, 2024 65
ድሬዳዋ፤ ሚያዚያ 19/2016(ኢዜአ)፦ በምስራቅ ኢትዮጵያ ለሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ዲጂታል የመማር ማስተማር ሥራን ለማሳለጥ የሚያስችልና በ25 ሚሊዮን ብር የተገነባ ዲጂታል ስቱዲዮ ዛሬ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የተገነባውን ዲጂታል ስቱዲዮውን መርቀው ሥራ ያስጀመሩት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ኡባህ አደምና ዲጂታል የመማር ማስተማር ሥራውን እየደገፉ ያሉት የአጋር ተቋማት አመራር አባላት ናቸው። በምረቃው ላይ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ኡባህ አደም ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዲጂታል የመማር ማስተማር ሥራን ለመጀመርና ስኬታማ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው። በዩኒቨርሲቲውም ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በ25 ሚሊዮን ብር ዲጂታል ስቱዲዮ እንደተገነባ ገልጸዋል። በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየተከናወኑ የሚገኙ ዲጂታል የመማር ማስተማር ስራዎችን በተቀናጀ መንገድ ማሳካት ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግም ያግዛል ሲሉ ገልጸዋል። ዶክተር ኡባህ እንዳሉት፤ በዩኒቨርሲቲው ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት በጀመረው ዲጂታል ስቱዲዮ የሚጠቀሙት በምስራቅ የአገሪቱ ክፍል ያሉት የድሬዳዋ፣ የሐረማያ፣ የኦዳቡልቱም፣ የጅግጅጋ እና የቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲዎች ናቸው። በዩኒቨርሲቲው እስካሁን ሁለት የትምህርት ዓይነቶችን በሙከራ ደረጃ በ"ኦን ላይን" ማስተማር እንደተጀመረ የገለጹት ዶክተር ኡባህ፣ ለመምህራን በተለያዩ የዲጂታል ትምህርት ቀረፃዎች ላይ ስልጠና ተሰጥቶ ለመማሪያ የሚሆኑ ማንዋሎች ማዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። ዲጂታል የመማር ማስተማር መርሃ ግብርን ዕውን ለማድረግ የሚከናወኑ ተግባራት የሚመሩት በትምህርት ሚኒስቴር መሆኑም ተመላክቷል። የዩኒቨርሲቲው የዘርፉ አመራር አባላት ዲጂታል የመማር ማስተማር ሥራውን በተሟላ መንገድ ማስጀመር በሚቻልበት መንገድ ላይ ዛሬ መክረዋል።        
የብዝኃ ማንነት ባህላዊ ኃብቶቻችንን በመጠበቅ በሕዝቦች መካከል ትስስርና የወል ትርክት ለመገንባት እየተሰራ ነው- አቶ ቀጀላ መርዳሳ
Apr 27, 2024 64
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2016(ኢዜአ)፦ያሉንን የብዝኃ ማንነት ኃብቶችን በመጠበቅ በሕዝቦች መካከል ትስስርና የወል ትርክትን ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ ቀጀላ መርዳሳ ገለጹ። የፊቼ ጫምባላላ በዓል የማጠቃለያ መርሃ-ግብር በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ ተካሂዷል። የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ ቀጀላ መርዳሳ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ፊቼ ጫምባላላ ለሀገር ግንባታና ለማኅበረሰብ ትስስር ሚናው የጎላ መሆኑን አንስተዋል፡፡   የብዝኃ ማንነት ባህላዊ ኃብቶችን በማልማትና በማስተዋወቅ በሕዝቦች መካከል ትስስርንና የወል ትርክቶችን ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። ከዚህ አኳያ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችን ባህላዊ እሴቶች ለማልማት በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በዘመናት ቅብብሎሽ ዛሬ ላይ የደረሰው የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ ከሲዳማ ሕዝብ አልፎ የሀገርና የዓለም ኃብት እንዲሆን ከፍተኛ ሥራ መከናወኑን ገልፀዋል።   የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲዳማ ባህል ማዕከል የሚገነባበት ቦታ በመስጠትም አዲስ አበባ የሁሉም ቤት መሆኗን በተግባር ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡ ይህን የዓለም ቅርስ የሆነ አኩሪ በዓል በመጠበቅ ትውልዱ በአግባቡ እንዲረዳው ማድረግ እንደሚገባም አመላክተዋል።   የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ቡዜና አልከድር፤ አዲስ አበባ ብዝኃነትን በማስተናገድ ፈጣን ልማትን በማረጋገጥ ለኑሮና ለሥራ የምትመች ከተማ መሆኗን በተግባር እያረጋገጠች ነው ብለዋል፡፡ ፍቼ ጫምባላላ የአብሮነት በዓል በመሆኑ ለሕብረ-ብሔራዊ እህትማማችነትና ወንድማማችነት እንዲሁም ለጠንካራ ሀገረ-መንግሥት ግንባታ ለማዋል ሁሉም የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።   ፊቼ ጫምባላላ እና መሰል ባህላዊ ፌስቲቫሎችን በቱሪዝም መስህብነት በማስተዋወቅ ጥቅም ላይ በማዋል ተወዳዳሪ የቱሪዝም መዳረሻዎች በመፍጠር ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይገባል ያሉት ደግሞ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ ናቸው። የቱሪዝም ሚኒስቴርም ፊቼ ጫምባላላን ጨምሮ የሲዳማ ክልል የቱሪዝም ኃብቶች እንዲጠበቁ፣ እንዲለሙና እንዲተዋወቁ ለማድረግ ከክልሉ መንግሥት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በበዓሉ ላይ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የፌዴራል የሥራ ኃላፊዎች፣ የሲዳማ ክልልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የሲዳማ ተወላጆችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ፊቼ ጫምባላላ የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ከማይዳሰሱ ቅርሶች ምድብ የሰው ልጆች ወካይ ቅርስ ሆኖ ኅዳር 18 ቀን 2008 ዓ.ም የዓለም ኃብት ሆኖ ተመዝግቧል።  
በመዲናዋ የግሉ ዘርፍ በመኖሪያ ቤት ልማት በስፋት እንዲሳተፍ ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ 
Apr 27, 2024 65
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2016(ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የግሉ ዘርፍ በመኖሪያ ቤት ልማት በስፋት እንዲሳተፍ ምቹ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በግሉ ዘርፍ እና የመንግሥት አጋርነት የቤቶች ልማት መርሐ-ግብር አማካኝነት በጊፍት ሪል ስቴት የሚገነቡ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታን አስጀምረዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት የመጀመሪያ ምዕራፍ ከ14 እስከ 22 ወለል ያላቸው 4 ሺህ መኖሪያ ቤቶች እንደሚገነቡ ተናግረዋል፡፡ ከተማ አስተዳደሩ በመዲናዋ የመኖሪያ ቤት እጥረትን ለመቅረፍ በርካታ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ጠቅሰው፤ ካለው የፍላጎት አኳያ ግን አሁንም የሚቀሩ ስራዎች መኖራችውን ጠቅሰዋል፡፡ ይህን የፍላጎትና የአቅርቦት አለመጣጣም ለማጥበብ ከመንግስት ባሻገር የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ አሁን ላይ የግሉ ዘርፍ በመኖሪያ ቤት ልማት በስፋት እንዲሳተፍ ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል ነው ያሉት፡፡ በዚህ ረገድ በመንግስትና በግሉ ዘርፍ አጋርነት የሚገነቡ ቤቶችን ለአብነት አንስተዋል፡፡ ይህ ትብብር ወደ ፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡ በመንግስት እና በግል አጋርነት መርሃ ግብር ከጊፍት ሪል እስቴት ጋር የተጀመረው የ4 ሺህ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል። ከጊፍት ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ገብረየሱስ ኢጋታ በበኩላቸው፤ ጊፍት ሪል ስቴት ባለው የካበተ ልምድ አንጻር ፕሮጀክቱን በተያዘለት ጊዜና ጥራት ለማጠናቀቅ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡    
አስቸኳይ እርዳታ ለሚሹ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል-የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን 
Apr 27, 2024 91
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2016(ኢዜአ)፦ አስቸኳይ እርዳታ ለሚሹ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) ገለጹ። የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) በተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወነ ያለውን የሰብአዊ ድጋፍና ተደራሽነትን በተመለከተ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በሰው ሠራሽና የተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ በተጠናከረ መልኩ እየቀረበ መሆኑንም ገልፀዋል። የሰብአዊ ድጋፉ በየሩብ ዓመቱ እንደሚሰራጭ ጠቅሰው ከጥር እስከ መጋቢት ድረስ ለ6 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዜጎች ድጋፍ ሲደረግ መቆየቱን ጠቁመዋል። አሁን ባለንበት ወቅትም ከሚያዝያ አንስቶ እስከ ሰኔ ከስምንት ሚሊዮን በላይ ዜጎች የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽ የማድረጉ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ድጋፉ በመንግስትና በአጋር አካላት ትብብር እንደሚከናወንም እንዲሁ። በአጠቃላይ ከሚያዚያ እስከ ሰኔ ላለው ድጋፍ 11 ቢሊዮን ብር አካባቢ ወጭ የሚጠይቅ ሲሆን 5 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ ድጋፍ በመንግስት ይሸፈናል ነው ያሉት፡፡ ቀሪው በለጋሽ አካላት እንደሚሸፈንም ነው የተናገሩት፡፡ የመንግስት ዋነኛ ትኩረት አደጋን ቀድሞ መከላከል መሆኑን የተናገሩት ኮሚሽነሩ ለዚህም የተጋላጭነት ልየታ የአደጋ ስጋት ፕሮፋይል ጥናት መሰራቱን ጠቁመዋል። በሀገሪቱ ከሚገኙ ወረዳዎች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በዚህ ጥናት መሸፈናቸውን ተናግረዋል።  
ኢኮኖሚ
ከ500 ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ተመርቶ ለአርሶ አደሩ እየተሰራጨ ነው- የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ
Apr 28, 2024 41
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2016(ኢዜአ)፦ የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ከ500 ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ተመርቶ ለአርሶ አደሩ እየተሰራጨ መሆኑን አስታወቀ። ኢንተርፕራይዙ ምርታማነታቸው ከፍተኛ የሆኑና በሽታን መቋቋም የሚችሉ ከ20 በላይ የሰብል ዓይነቶች ምርጥ ዘር እያመረተ መሆኑን ገልጿል። የኢንተርፕራይዙ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ጫላ አበበ ለኢዜአ እንዳሉት ኢንተርፕራይዙ በክልሉ ከ80 በመቶ በላይ እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ ከ60 በመቶ በላይ ምርጥ ዘር ያቀርባል። ኢንተርፕራይዙ በኩታ ገጠም በተደራጁት አርሶ አደሮች፣ ባለሀብቶችና በራሱ የዘር ብዜት እርሻዎች በዚህ ዓመት ከ500 ሺህ በላይ ኩንታል የተመረተ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 300 ሺህ ኩንታል ንጹህ ምርጥ ዘር ለስርጭት መዘጋጀቱን ገልጸዋል። እስካሁንም ከ60 ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን ተናግረዋል። ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ከሚያስችሉ ውስጥ ምርጥ ዘር በስፋት ለአርሶ አደሩ እንዲደርስ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም ኢንተርፕራይዙ በራሱ በሚያለማቸው በባሌ፣አርሲ እና በምዕራብ ወለጋ በሚገኙ 13 እርሻዎች ላይ እንደ አካባቢው ስርዓተ ምህዳር ተስማሚነት ምርጥ ዘር እየተባዛ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም ምርታማነታቸው ከፍተኛ የሆኑና በሽታን መቋቋም የሚችሉ የስንዴ፣ ገብስ፣ በቆሎ፣ ሩዝ፣ ጤፍን ጨምሮ ከ20 በላይ የሰብል ዓይነት ምርጥ ዘሮችን በማባዛት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።  
ስራ ከድህነት የምንወጣበትና የአሸናፊነት ታሪካችንን በደማቁ የምናጽፍበት መሳሪያችን ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Apr 27, 2024 105
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2016(ኢዜአ)፦ ስራ ከድህነት የምንወጣበትና ደማቁን የአሸናፊነት ታሪካችንን በደማቁ የምናጽፍበት መሳሪያችን ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡ ይህን እውን ለማድረግ ደግሞ ሰላም ቁልፉ መንገድ ነው ሲሉም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል። በአጭር ጊዜ ወደ ስራ የተመለሰው የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክም ሆነ ሌሎች የክልሉ የልማት ስራዎችን ለማጠናከር ሰላም ወሳኝ ነው ብለዋል።   በህልውና ጦርነቱ የኢንዱስትሪ መንደሮቿን ጨምሮ የከፋ ጉዳት የደረሰባት የኮምቦልቻ ከተማ በተገኘው ሰላም ወደ ቀደመ ድምቀቷ መመለሷን ዛሬ ተመልክተናል ሲሉም ገልጸዋል። በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ የጎበኘናቸው አምራች ድርጅቶች ከክልሉ አልፎ ለሀገር እድገት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያላቸውን ምርቶች በሙሉ አቅም እና ጥራት እያመረቱ እንደሆነ አይተናል ብለዋል።   ምርቶቹ በከፍተኛ ጥራት ተመርተው ወደ ውጭ የሚላኩ ናቸው ያሉት አቶ ተመስገን በቀጣይ የሀገር ውስጥ ገበያውን እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል ሲሉም ጠቁመዋል፡፡ መንግስትም ለሀገር ውስጥ ምርት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። በሌላ በኩል ጥያቄዎችን ከሰላም ውጭ በመሳሪያ ለማስፈጸም የሚንቀሳቀስ ሃይል ወደ ውይይትና ምክክር እንዲመለስ ከፌዴራል መንግስትም ሆነ ከክልሉ የቀረበውን ጥሪ እንዲጠቀም በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እወዳለሁ ብለዋል። ከሰላም እና ከውይይት ውጭ በጠመንጃ ጥያቄን ለማስመለስ የሚደረግ ሙከራ የክልሉን ልማት ወደ ኋላ የሚመልስ፣ የማይሳካና አክሳሪ በመሆኑ ይህን ለማስቆም የፌዴራልም ሆነ የክልሉ መንግስት ህግና ስርዓትን ለማስከበር የጀመረውን ስራ ይቀጥላል ሲሉም አስታውቀዋል።
ስታርት አፖችን በተደራጀ  አግባብ ለመደገፍ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ-- ሙፍሪያት ካሚል 
Apr 27, 2024 56
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2016(ኢዜአ)፦ ስታርት አፖችን በተደራጀ አግባብ ለመደገፍ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፍሪያት ከሚል ገለጹ። ለሦስት ሳምንታት በሳይንስ ሙዚየም ሲካሄድ የቆየው የስታርት አፕ ኢትዮጵያ አውደ ርዕይ ተጠናቋል፡፡ በማጠቃለያ መርሃ -ግብሩ ላይ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ባይሳ በዳዳ እና ሌሎችም የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። በአውደ ርዕዩ አዳዲስ በቴክኖሎጂ የታገዙ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ወጣቶች ተሞክሯቸውን በስፋት ለሌሎች ያጋሩበት ፣ጀማሪ ስታርት አፖችን በማስተዋወቅ የተሻለ የፈጠራ ስራዎች እንዲዳብሩ ለማስቻል ምቹ ምህዳር የተፈጠረበት መርሃ ግብር እንደነበር በመድረኩ ተገልጿል። የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ መንግስት ለስታርት አፖች ምቹ ምህዳር ለመፍጠር ሰፊ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም ዘጠኝ የሚደርሱ የአሰራር ማሻሻያ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰው፤ ማሻሻያዎቹ የፋይናስ አቅርቦትን ጨምሮ ለስታርት አፖች የተቀላጠፈ አሰራርን ገቢራዊ የሚያደርጉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ለተደረጉ ማሻሻዎች ተግባራዊነት ቀጣይነት ያለው ክትትል እንደሚደረግም ነው ያነሱት፡፡ አውደ ርእይ ከማዘጋጀት ባሻገር ስታርት አፖችን በተደራጀ አግባብ ለመደገፍ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም እንዲሁ፡፡ ​​​ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ (ዶ/ር) ባይሳ በዳዳ በበኩላቸው፤ አውደ ርእዩ በተለይ ጀማሪ ስታርት አፖች ሃሳባቸውን ለማስተዋወቅ እድል ያገኙበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ ከለውጡ በፊት እንደ ሀገር 50 ስታርታፖች ብቻ የነበሩ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታው በአሁኑ ወቅት ከ900 በላይ ስታርት አፖች መፈጠራቸውን ገልጸዋል። በአውደ ርዕይው ስራዎቻቸውን ለውድድር ያቀረቡ እና ከአንድ እስከ ሦስት የወጡ ስታርት አፖችን እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በአውደ ርዕዩ 300 የሚደርሱ ስታርት አፖች ለእይታ የበቁበት፤ የተለያዩ ትልልቅ የውይይት መድረኮች የተካሄዱበት፤ ዘጠኝ የሚደርሱ የፖሊሲ የሪፎርም አቅጣጫዎች የተቀመጡበት መሆኑ ተገልጿል። በአውደ ርእዩ በግብርና ፣ጤና፣ በኢንዳስትሪ፣በኢነርጂና ሌሎችም ዘርፎች ችግር ፈቺ የሆኑ የፈጠራ ሃሳቦችና ምርቶች ለእይታ የበቁበት ሲሆን ይህም ውጤታማ የስራ ፈጣሪነትን ለመተግበር ምቹ ምህዳር የፈጠረ መሆኑን ተገልጿል። በአውደ ርዕይው የተሳተፉ የስታርት አፕ ስራዎችን ከ16 ሺህ በላይ ሰዎች ጎብኝተውታል።  
በክልሉ የግብርና ሜካናይዜሽን ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሩ ለማድረስ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ
Apr 27, 2024 66
ባህር ዳር፤ ሚያዝያ 19/2016(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል የሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ የግብርና ሜካናይዜሽን ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ መጠናከር ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ። የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የአማራ ክልል ግብርና ሜካናይዜሽን ፎረም በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል። የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አጀበ ስንሻው በወቅቱ እንዳሉት፣ የሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ ዘመናዊ የግብርና ሜካናይዜሽንን አስፋፍቶ መጠቀም ተገቢ ነው። በክልሉ የግብርና ሜካናይዜሽን አቅርቦት እየተሻሻለ ቢሆንም፤ በሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ የተቀናጀ ጥረት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። ኋላ ቀር የእርሻ መሳሪያዎችን በመጠቀም በሚፈለገው ልክ የሰብል ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንደማይቻል ጠቁመዋል። ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በብዛትና በጥራት መጠቀም እንደሚገባም አመልክተዋል። ፎረሙ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በጋራ ተወያይቶ በመፍታት ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ባለድርሻ አካላት ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል። በክልሉ ከሚታረሰው 5 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት 42 በመቶ የሚሆነው ለግብርና ሜካናይዜሽን እርሻ የተመቸ ቢሆንም እስካሁን ማረስ የተቻለው 14 በመቶ ብቻ ነው። መንግስት ለድርጅቶች ብድር አመቻችቶ የእርሻ ትራክተሮችና ኮምባይነሮችን ወደ ክልሉ እንዲያስገቡ እያደረገ መሆኑን ገልጸው፣ ይህም የክልሉን የግብርና እንቅስቃሴ እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።   የቲዜድ ቢዝነስና ኢንቨስትመንት ካምፓኒ ዋና ሥራ አስኪያጅና የክልሎች ግብርና ሜካናይዜሽን ፎረም አስተባባሪ አቶ ቴዎድሮስ ዘውዱ በበኩላቸው፤ እንደ ሀገር በግብርና ሜካናይዜሽን ላይ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት በሲዳማ፣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ፎረሞች መቋቋማቸውን ገልጸዋል። ፎረሞቹ በዘርፉ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ወሳኝ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ የሚስተዋሉ የሰለጠነ የሰው ሀይል፣ የቴክኖሎጂ አቅርቦት፣ የፋይናንስና መሰል ችግሮችን ለማቃለል ያግዛሉ ብለዋል።   ድርጅቱ ከማጭድ ጀምሮ እስከ ትራክተር በማቅረብ የድርሻውን እየተወጣ ነው ያሉት ደግሞ የአምባሰል ንግድ ሥራዎች ድርጅት የክልሉና የእህት ኩባንያ አቅርቦት ቡድን መሪ ወይዘሮ ፀሐይ ተስፋዬ ናቸው። ድርጅቱ እስካሁን ድረስ ከ220 በላይ የእርሻ ትራክተሮችን አስገብቶ ማሰራጨቱን ጠቅሰው፤ ከ30 በላይ ኮምባይነሮችም ወደ ክልሉ እንዲገቡ መደረጉን አስታውቀዋል። በመድረኩ ላይ ከክልሉ ግብርና ቢሮ፣ ከምርምር ማዕከላት፣ ከህብረት ሥራ ማህበራት፣ ከቴክኖሎጂ አቅራቢ ድርጅቶች፣ ከባንኮች፣ ከዩኒየኖች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በሳይንስ ሙዚየም ሲካሄድ የቆየው የስታርትአፕ ኢትዮጵያ አውደ ርዕይ ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ተካሄደ
Apr 27, 2024 54
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2016(ኢዜአ)፦ ለሦስት ሳምንታት በሳይንስ ሙዚየም ሲካሄድ የቆየው የስታርትአፕ ኢትዮጵያ አውደ ርዕይ ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡ በማጠቃለያ መርሃ-ግብሩ ላይ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ (ዶ/ር) ባይሳ በዳዳ እና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። በአውደ ርዕዩ በቴክኖሎጂ የታገዙ አዳዲስ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ወጣቶች ተሞክሯቸውን በስፋት ለሌሎች ያጋሩበት፣ ጀማሪ ስታርትአፖችን በማስተዋወቅ የተሻለ የፈጠራ ስራዎች እንዲዳብሩ ለማስቻል ምቹ ምህደር የተፈጠረበት መርሃ ግብር እንደነበር በመድረኩ ተገልጿል። በአውደ ርዕዩ ስራዎቻቸውን ለውድድር ያቀረቡ እና ከአንድ እስከ ሦስት የወጡ ስታርትአፖችን እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በአውደ ርዕዩ 300 የሚደርሱ ስታርታአፖች ለእይታ የበቁበት፤ የተለያዩ የውይይት መድረኮች የተካሄዱበት፤ ዘጠኝ የሚደርሱ የፖሊሲ የሪፎርም አቅጣጫዎች የተቀመጡበት መሆኑ ተገልጿል። በአውደ ርእዩ በግብርና፣ በጤና፣ በኢንዳስትሪ፣ በኢነርጂና ሌሎች ዘርፎች ችግር ፈቺ የሆኑ የፈጠራ ሃሳቦችና ምርቶች ለእይታ የበቁበት ሲሆን ይህም ውጤታማ የስራ ፈጣሪነትን ለመተግበር ምቹ ምህዳር የፈጠረ መሆኑ ተገልጿል። የስራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፍሪያት ከሚል በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፣ ዛሬ ተሸላሚ የሆኑት የስታርትአፖች የተፈጠረላቸውን ምቹ እድል ተጠቅመው የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግቡ አስገንዝበዋል፡፡ በአውደ ርዕይው የተሳተፉ የስታርትአፕ ስራዎችን ከ16 ሺህ በላይ ሰዎች ጎብኝተውታል።
የመንግስት ተቋማትን የዲጂታል አቅም በማጎልበት ለዜጎች ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆን በትኩረት ሊሰራ ይገባል
Apr 27, 2024 77
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2016(ኢዜአ)፦ የመንግስት ተቋማትን የዲጂታል አቅም በማጎልበት ለዜጎች ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆን በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን ገለጸ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት በፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስተባባሪነት የተቋቋመው የፌዴራል ሱፐርቪዥን ቡድን የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን የስራ እንቅስቃሴ ተመልክቷል። ቡድኑ የአይ ሲ ቲ ፓርክ፣ የቡራዩ ልዩ ተሰጥኦ ማበልጸጊያ ማዕከልና የኢ-ሰርቪስ አገልግሎት የኮቪድና የሌሎች ተላላፊ በሽታዎች የመድሃኒት ምርምር የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ሱፐርቪዥን አካሂደዋል። የሱፐርቪዥን አስተባባሪ ተገኔ ኃይሉ በዚሁ ወቅት ስታርትአፖችን በአይሲቲ ፓርክ በማስገባት የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራው እንዲጎለብት እየተከናወነ ያለው ስራ የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ልዩ ተሠጥኦ ያላቸው ተዳጊዎች ክህሎት ለማጎልበት የተሰጠውን ትኩረት አድንቀው፤ ከዚህ አኳያ በተለይ የቡራዩ ልዩ ተሰጥኦ ማበልጸጊያ ማዕከል በተሟላ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጥ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ እስካሁን ባለው ሂደትም አገልግሎታቸውን በዲጂታል ስርዓት(ኢ-ሰርቪስ) ተደራሽ ማድረግ ከሚጠበቅባቸው 64 ተቋማት ውስጥ 25 ብቻ እየሠጡ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል። ከዚህ አኳያ የመንግስት ተቋማትን የዲጂታል አቅም በማጎልበት ለዜጎች ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆን በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም ነው ያነሱት፡፡ አገልግሎታቸውን በዲጂታል ስርዓት ተደራሽ ለማድረግ እየሰሩ ያሉ ተቋማትን ማገዝና መደገፍ እንደሚገባም እንዲሁ፡፡   የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፤ በቡራዩ ማዕከል ልዩ ተሠጥኦ ያላቸውን ወጣቶች አቅም በማጎልበት ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። እንደ ሀገር የቡራዩ ማዕከል በቂ ባለመሆኑ የሳይንስ ካፌዎችንና መሰል ስራዎችን በማስፋት የታዳጊዎችን ተሰጥኦ ለማጎልበት ስራዎች መጀመራቸውንም አንስተዋል፡፡ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም ጭምር የታዳጊዎችን ተሰጥኦ ለማበልጸግ በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑ ጠቁመዋል፡፡ የመንግስት ተቋማት ዲጂታል አገልግሎት ተደራሽ ከማድረግ አንጻር ቅንጅታዊ አሰራርን የተከተለ ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል ስትራቴጂ መዘጋጀቱን ነው ያብራሩት፡፡   የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር) በበኩላቸው 10 ሺህ ለሚሆኑ ባለ ተሰጥኦ ወጣቶች በቡራዩ የተሠጥኦ ማበልጸጊያ ማእከል ስልጠና እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ስልጠናው ከተያዩ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር በመቀናጀት እንደሚሰጥም ገልጸዋል፡፡        
በኢትዮጵያ አለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን የሚያረጋግጡ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ስራዎችን የሚያጎለብቱ የአሰራር ማሻሻያዎች እየተደረጉ ነው
Apr 26, 2024 85
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 18/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችሉ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ስራዎችን የሚያጎለብቱ የአሰራር ማሻሻያዎችን እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን አስታወቀ። በኢትዮጵያ ጠንካራ ብሔራዊ የአዕምሯዊ ንብረት አስተዳደርን መገንባት የሚያስችሉ የአዋጅ ማሻሻያዎች እየተከናወኑ መሆኑም ተገልጿል። የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን በአለም ለ24ኛ በኢትዮጵያ ለ22ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የአዕምሯዊ ንብረት ቀን በሳይንስ ሙዚየም አክብሯል። ቀኑ ''አዕምሯዊ ንብረት ለዘላቂ ልማት መጪው ጊዜያችንን በኢኖቬሽንና ፈጠራ መገንባት'' በሚል መሪ ሃሳብ በፈጠራ ስራዎች አውደ ርዕይና በፓናል ውይይት ነው የተከበረው። የፈጠራ አውደ ርዕዩን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ(ዶ/ር)፣ የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ ኤርሚያስ የማነብርሃን (ዶ/ር) እንዲሁም የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወልዱ ይመስል ከፍተውታል። በዚህ ወቅት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ(ዶ/ር) እንዳሉት ኢትዮጵያ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት በቁርጠኝነት እየሰራች ሲሆን በአንዳንድ ዘርፎች የተሻሉ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ከዚህ ቀደም የፈጠራ ስራ ባለቤቶች ሃሳባቸውን ወደ ተግባር ለመቀየር የሚገድቧቸው የህግ ማዕቀፍና ፋይናንስን የመሳሰሉ ችግሮች እንደነበሩ አንስተዋል። ይህም የፈጠራ ስራዎች እንዳይበራከቱና ዘርፉ ለኢኮኖሚው የሚጠበቅበትን አስተዋፅኦ እንዳያበረክት ተግዳሮት ሆኖ መቆየቱን ተናግረዋል። አሁን ላይ በአገሪቱ ለፈጠራ ስራ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የህግ ማዕቀፍ ከማሻሻያ ጀምሮ ለስታርት አፖች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልፀዋል። መንግስት ስታርት አፖች ለሀገሪቱ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ሞተር ሆነው እንዲዘልቁ ብሎም ፈጠራና አዳዲስ ግኝቶች የሚያፈልቅባቸው የጥራት ማዕከል እንዲሆኑ በትጋት እየሰራ ይገኛል ነው ያሉት። የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወልዱ ይመስል መንግስት ጠንካራ ብሄራዊ የአዕምሯዊ ንብረት አስተዳደር ለመገንባት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።   በፍጥነት በሚለዋወጥ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሁኔታ በመኖሩ ቀጣይነት ያለው የለውጥ ስራ ማከናወን ይጠይቃል ነው ያሉት። ባለስልጣኑ ይህን በመገንዘብ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የስትራቴጂና የህግ ማዕቀፍ ማሻሻያዎችና ተቋማዊ ሪፎርም እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል ። ዋና ዳይሬክተሩ በአሁኑ ወቅት ሶስት አዋጆችን የማሻሻል እንዲሁም ሁለት አዳዲስ አዋጆችን እየተረቀቁ መሆኑን ተናግረዋል። ዘርፉ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ሽግግር ለማምጣት የሚያስችል ቢሆንም እስካሁን ባለው ሁኔታ ብዙ እንዳልተሰራበት ነው የገለፁት። አሁን ላይ በስታርት አፕ ዙሪያ የተጀመረው ስራ የህብረተሰብ ችግር የሚፈቱ የፈጠራ ሃሳቦች ተግባር ላይ እንዲውሉ ያግዛል ብለዋል። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣናና የአለም ንግድ ድርጅት አባልነትን ስትቀላቀል ተወዳዳሪ ሆና እንድትቀጥል የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ስራዎች መበራከት አለባቸው ብለዋል። ባለስልጣኑ የሚሰራባቸውን ህጎች ከዘመኑ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ደረጃ ጋር ተመጣጣኝ ለማድረግ የአሰራር ማሻሻያ እያደረገ መሆኑንም አስረድተዋል። በአውደርዕዩ የፈጠራ ስራቸውን ይዘው የቀረቡ የፈጠራ ባለቤቶች በበኩላቸው የአዕምሯዊ ንብረት ከፈጠራ ባለቤቱ ባሻገር ለአገር ኢኮኖሚ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።   መጸዳጃ ቤትን በንፅህና ለመጠበቅ የሚያስችልና ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻን መለየት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ይዘው የቀረቡት በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰበ ጤና አጠባበቅ መምህር ዶክተር ግዛቸው አብደታ እንዳሉት የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ለአገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ ሚና አለው።   መምህር በሌለበት ጊዜ ማስተማር የምትችል ሮቦት ይዞ የቀረበው ወጣት በረከት ጌቱ በበኩሉ የፈጠራ ባለቤትነት መብት መሰጠቱ የፈጠራ ባለቤትነት ደህንነትን ከማስጠበቅ ባሻገር ስራን በማሻሻል አገርን ለመደገፍ ያግዛል ብሏል።  
ቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭ በኢትዮጵያ ስራ መጀመሩ ስታርትአፖችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የተያዘው ቁርጠኝነት ያግዛል
Apr 26, 2024 90
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 18/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭ ስራ መጀመሩ ስታርት አፕንና የስራ ፈጠራ እንዲጎለብት ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ ተናገሩ። በአፍሪካ የስራ ፈጠራና ስታርትአፕን የሚደግፈው ቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭ በኢትዮጵያ በትላንትናው እለት ስራውን በይፋ ጀምሯል። ኢኒሼቲቩ በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም አነሳሽነት በአፍሪካ በተለይ ኢንቨስትመንትን፣ ስራ ፈጠራንና ስታርት አፕን ለመደገፍ የሚሰራ ነው። በኢንሼቲቩ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ፣ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ብሩክ ታዬ፣ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ ቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭ በሀገራችን መጀመሩ የስራ ፈጠራና ስታርትአፕን እንዲጎለብት ትልቅ አቅም የሚፈጥር እንደሆነ ገልጸዋል። ኢንሼቲቩ በአፍሪካውያን መካከል ያለውን የኢኖቬሽን ስነ-ምህዳርን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል። በቀጣይም የዜጎችን የፈጠራ አቅም ለማጎልበት እና ዲጂታልን የመጠቀም ባህል ለማጎልበት ሚኒስቴሩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ገልፀል። የስራ ፈጠራና ስታርት አፕን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ አላማ ይዞ እየሰራ የሚገኘውን የቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭን ከግብ ለማድረስ ከአጋር ድርጅቶች ጋር የጀመራቸውን የጋራ ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ሚኒስትሩ አክለዋል። የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ብሩክ ታዬ በበኩላቸው ኢኒሸቲቩ ስታርትአፖች በጋራ ሆነው በዘርፉ ላይ በመስራት ለውጥ እንዲያመጡ አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል። መንግስት በሀገሪቱ ስራ ፈጠራን ለማበረታታት ብሎም የቲምቡክቱ ኢንሼቲቭን ወደ ተግባር ለመቀየር ፖሊሲዎችን ከማዘጋጀት ጨምር ሌሎች በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።   የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተጠሪ ዶክተር ሳሙኤል ዶ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የዲጂታል ዘመንን ለመገንባት የምታደርገው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል። ኢንሺቲቩ አፍሪካውያን በጋራ እንዲሰሩ ያግዛል ብለዋል።    
ስፖርት
የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ይካሄዳል
Apr 28, 2024 48
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20 /2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ይካሄዳል:: የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና መካከል ዛሬ ይደረጋል። የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ከቀኑ 9 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይከናወናል። ሀዋሳ ከተማ በሩብ ፍጻሜው አርባ ምንጭ ከተማን 2 ለ 0 እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና ፋሲል ከነማን 4 ለ 1 በማሸነፍ ለግማሽ ፍጻሜው ማለፋቸው ይታወቃል።   በአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ የሚመራው ሀዋሳ ከተማ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎች ቤንች ማጂ ቡና እና መቻልን አሸንፏል። ክለቡ በኢትዮጵያ ዋንጫ እስከ አሁን ባደረጋቸው 3 ጨዋታዎች 7 ግቦችን ከመረብ ሲያሳርፍ 1 ጎል አስተናግዷል። ተጋጣሚው ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ በዚህ ውድድር አስቀድሞ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ወልዲያ እና ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማን ማሸነፉ ይታወቃል።   በአሰልጣኝ ነጻነት ክብሬ የሚመሩት ቡናማዎቹ በውድድሩ ባደረጓቸው 3 ጨዋታዎች 10 ጎሎችን ሲያስቆጥሩ የተቆጠረባቸው 1 ግብ ብቻ ነው። የሁለቱ ክለቦች አሸናፊ ከወላይታ ድቻ በፍጻሜው የሚገናኝ ይሆናል። በኢትዮጵያ ዋንጫ ትናንት በተደረገው የመጀመሪያ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ኢትዮጵያ መድንን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለፍጻሜ ማለፉ ይታወቃል።   የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ በቀጣዩ ዓመት በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን ወክሎ ይሳተፋል።  
የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ ይካሄዳሉ 
Apr 27, 2024 75
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 19/2016(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋሉ። የመጀመሪያው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በወላይታ ድቻ እና ኢትዮጵያ መድን መካከል ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ይከናወናል። በሩብ ፍጻሜው ወላይታ ድቻ ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 1 እንዲሁም ኢትዮጵያ መድን አዳማ ከተማን 3 ለ 1 በማሸነፍ ለግማሽ ፍጻሜ ጨዋታው ቀርበዋል። ወላይታ ድቻ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር ደሴ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕናን ማሸነፉ ይታወቃል። ክለቡ በኢትዮጵያ ዋንጫ ባደረጋቸው 3 ጨዋታዎች 10 ግቦችን ሲያስቆጥር 4 ግቦችን አስተናግዷል። ተጋጣሚው ኢትዮጵያ መድን በበኩሉ በውድድሩ የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎች ድሬዳዋ ከተማ እና አርሲ ነገሌን አሸንፏል። ኢትዮጵያ መድን እስከ አሁን በኢትዮጵያ ዋንጫ ባደረጋቸው 3 ጨዋታዎች 7 ጎሎችን ከመረብ ጋር ሲያገናኝ 3 ግቦችን አስተናግዷል። በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ወላይታ ድቻ በ28 ነጥብ 11ኛ፤ ኢትዮጵያ መድን በ22 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በሌላኛው የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ መርሐ ግብር ነገ ሀዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም እንደሚደረግ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የፍጻሜው ጨዋታ የሚደረግበት ቀንና ቦታ በቀጣይ ይፋ እንደሚሆንም ፌዴሬሽኑ ገልጿል። የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ በቀጣዩ ዓመት በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን ወክሎ ይሳተፋል። የኢትዮጵያ ዋንጫ በኮቪድ-19 ወረርሽኝና በተለያዩ ምክንያቶች ላለፉት አራት ዓመታት ሳይካሄድ የቆየ ሲሆን በዚህም ምክንያት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ የሚያጠናቅቀው ቡድን ኢትዮጵያን ወክሎ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሲሳተፍ ቆይቷል።        
አካባቢ ጥበቃ
ከተማን ውብና ፅዱ በማድረግ ምቹ የመኖሪያ አካባቢ ለመፍጠር የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Apr 28, 2024 24
ሠመራ፤ ሚያዚያ 20 /2016(ኢዜአ)፦ ከተማን ውብና ፅዱ በማድረግ ምቹ የመኖሪያ አካባቢ ለመፍጠር የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉ የሠመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አብዱ ሙሳ ተናገሩ። እንደ አገር የተጀመረው የአካባቢ ጽዳትና ውበት ዘመቻ በአፋር ክልል ደረጃ ባለፈው ሳምንት መጀመሩን ተከትሎ የከተማ አስተዳድሮችና ወረዳዎችም ዘመቻውን እየተገበሩት ይገኛሉ። "ብክለት ይብቃ-ሁሉም ይንቃ" በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ያለው የአካባቢ ብክለትን የማስወገድ ንቅናቄ መድረክ በክልሉ እስከ መስከረም 30 ቀን 2017ዓ.ም የሚቆይ እንደሆነም ተገልጿል። ዘመቻውን በሠመራ ሎጊያ ከተማ ያስጀመሩት ከንቲባ አብዱ ይህን የንቅናቄ ዘመቻ በተከታታይነት የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል። የመንግስት ተቋማት ሆቴሎችና የግል ተቋማት በጽዳት ዘመቻው ተሳታፊዎች መሆናቸውን የገለፁት ከንቲባው፤ ከተማችንን ውብ፣ ፅዱ እና ለነዋሪዎች ምቹ የመኖሪያ ሥፍራ የመፍጠሩ ስራ ዘላቂና የዘወትር ትኩረታችን ነው ብለዋል። በዚሁ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የክልሉ ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ሃላፊ ኢንጂነር ገቡ መሐመድ በበኩላቸው በአገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን መርሃ ግብር ማከናወን መጀመራቸውን ገልፀዋል። ምክትል ሃላፊው አክለውም ስራዎቻችንን በብቃት ልንፈፅም የምንችለው ከብክለት ፅዱ የሆነ አካባቢ መፍጠር ሲቻል ነው ብለዋል። በጽዳት ሥራው ተሳታፊ ከሆኑት የሠመራ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ አምቢያ አብዱ በበኩላቸው የከተማችንን ውበት ንፁህ በማድረግ እንግዶች ወደ አካባቢያችን በመጡ ጊዜ የሚረኩበት እና በጥሩ የሚመለከቱት መሆን ይኖርበታል ብለዋል። ሰለሆነም ለከተማዋ መደረግ ያለበትን ህብረተሰብን ከማስተባበር ጨምሮ ፅዱ እና ከብክለት ነፃ የማድረግ ስራ ላይ በግንባር ቀደምትነት እሳተፋለሁ ብለዋል።    
በዘንድሮው ዓመት ለሚካሔደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 7 ነጥብ 3 ቢሊዮን ችግኞች ተዘጋጅተዋል
Apr 26, 2024 101
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 18/2016(ኢዜአ)፡- በዘንድሮው ዓመት ለሚካሔደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 7 ነጥብ 3 ቢሊዮን ችግኞች መዘጋጀታቸውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ብሔራዊ ዐቢይ ኮሚቴ ገለፀ። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ብሔራዊ ዐቢይ ኮሚቴ የችግኞችን የጽድቀት መጠንና የዘንድሮ ዓመት ዝግጅቶችን አስመልክቶ በኦሮሚያ ክልል የምስራቅ ሸዋ ዞን አዳኣ ወረዳ ጉብኝት አድርጓል። ከጉብኝቱ ቀጥሎ በቢሾፍቱ ከተማ የ2016/17 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ ዝግጅትና የቀጣይ የስራ አቅጣጫን አስመልክቶ የምክክር መድረክ አካሂዷል።   የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ብሔራዊ ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ(ዶ/ር)፤ ጉብኝቱ የተመዘገቡ ስኬቶችን በመገምገም የቀጣይ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ስኬት ለማጠናከር ነው ብለዋል። በ2015/16 ዓ.ም በጀት አመት በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን የደንና የፍራፍሬ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ችግኞች መተከላቸውን አስታውሰዋል። በሁለት ዙር በተካሄደ የዳሰሳ ጥናትም የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ የጽድቀት መጠናቸውን 90 ከመቶ ማድረስ እንደተቻለ አስታውቀዋል። ለዚህም በኦሮሚያ ምስራቅ ሸዋ ዞን አዳኣ ወረዳ በተደረገው የመስክ ምልከታ በተሰራ የአፈርና ውሃ ጥበቃ የችግኝ ተከላ ስራ ተራቁቶ የቆየን አካባቢ በደን መሸፈን መቻሉም አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል። በአረንጓዴ አሻራ በለሙ የተፋሰስ ይዞታዎች ላይ በእንስሳት ማድለብና በንብ ማነብ መስኮች የሕብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ ለማሳደግ መቻሉን ጠቅሰዋል። በ2016/17 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በዕቅድ ከተያዘው የ6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ውስጥ ከዕቅድ በላይ 7 ነጥብ 3 መዘጋጀቱን አስታውሰዋል። በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለሚተከሉ ችግኞችም 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር መሬት ለተከላ ቦታ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።   የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ብሔራዊ ዐቢይ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ እና የውሃና ኢነርርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር)፥ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተራቆቱ አካባቢዎችን እንዲያገግሙ በማድረግ ለአፈርና ውሃ ጥበቃ ተጨባጭ ውጤት ማምጣቱን ገልጸዋል። መርሃ ግብሩም በግብርና ምርታማነት በማሳደግ ለዜጎች በስራ ዕድል ፈጠራና በሥነ-ምግብ ስርዓት መሻሻል አዎንታዊ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም ቀጣይነት ያለው የውሃ ፍሰት በመፍጠር ለመስኖ ምርታማነት፣ ለግድቦች የውሃ ደህንነት እና ለንጹህ የምንጭ ውሃ ዕድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል። የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኤሊያስ ከድር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የዜጎችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ተጨባጭ ውጤት አስመዝግቧል ብለዋል። በዘንድሮው መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያሳድጉ የፍራፍሬ እና የደን ችግኞችን ለተከላ ዝግጁ ማድረግ እንደተቻለ ገልጸዋል። በመጪው ክረምት በሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዜጎች የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ለአካባቢ ጥበቃና ለግብርና ምርታማነት አዎንታዊ ሚና መጫወት እንደሚኖርባቸውም በዚሁ ወቅት ተጠቅሷል።
በደቡብ ኢትዮጵያና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች በተያዘው ዓመት ከ713 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ይተከላሉ
Apr 26, 2024 100
ቦንጋና ዲላ፤ሚያዚያ 18/2016 (ኢዜአ)፦በደቡብ ኢትዮጵያና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከ713 ሚሊዮን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት ተደርጎ ወደተግባር መገባቱ ተገለጸ። የየክልሎቹ ግብርና ቢሮዎች ከደን አካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቁጥጥር ቢሮዎች ጋር በመተባበር የቅድመ ዝግጅት ሥራ እያከናወኑ መሆኑም ተመላክቷል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ሀይለማሪያም ተስፋዬ ለኢዜአ እንዳሉት በክልሉ ከበልግ ወቅት ጀምሮ ከ372 ሚሊዮን በላይ የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተከላ ይካሄዳል።   አስካሁንም ከአካባቢ ጥበቃ ጋር በመቀናጀት ችግኝ የማዘጋጀት ሥራ መጠናቀቁን ገልጸው የበልግ ወቅት የችግኝ ተከላ መርሀግብር ተከላ መጀመሩን አስረድተዋል። "ከሚተከሉት ችግኞች መካከል 32 ሚሊዮን ቡና እንዲሁም 27 ነጥብ 9 ሚሊዮኑ የፍራፍሬ ችግኞች መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ ሃይለማርያም፣ ችግኞቹን በተያዘው የበልግ ወቅት ተክሎ ለማጠናቀቅ በርብርብ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ቀሪዎቹን ችግኞች በክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሚተከሉ መሆናቸውንም አመልክተዋል። በክልሉ በየዓመቱ የሚከናወኑ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ሥራዎች የውሃ አቅምን በመጨመርና የመሬት ለምነትን በማጎልበት ለግብርና ልማቱ ውጤታማነት አስተዋጾ ማድረጋቸውን ሃላፊው ተናግረዋል። ህብረተሰቡም በችግኝ ተከላ ሲያደርገው የነበረውን ተሳትፎ በቀጣይም አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የተፈጥሮ ሀብት፣ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ውብሸት ዘነበ በክልሉ ለአርንጓዴ ልማት ሥራ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።   በተያዘው ዓመትም በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ከ341 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን ተናግረዋል። ከእዚህ ውስጥ ከ149 ሚሊዮን በላይ ችግኞች በተያዘው የበልግ ወቅት እንደሚተከሉ ጠቁመው፣ ቀሪ 192 ሚሊዮን ችግኞች በክረምት ወራት ይተከላሉ ብለዋል። ችግኞቹ ከክልሉ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቁጥጥር ቢሮ ጋር በመተባበር መዘጋጀታቸውን የገለጹት ኃላፊው፣ የአረንጓዴ ልማት ሥራው በተቀናጀ መንገድ ይከናወናል ብለዋል። ባለፉት ዓመታት በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተተከሉ ችግኞች የክልሉን የደን ሽፋን እያሳደጉት መሆኑንም ጠቅሰዋል። አቶ ውብሸት እንዳሉት የአረንጓዴ ልማት ሥራው የደን ሽፋኑን ከማሳደግ ባለፈ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ሥራዎችን በእጅጉ እያገዘ ነው። በመሆኑም ህብረተሰቡ የተተከሉ ችግኞች እንዲጸድቁ ተገቢውን ጥበቃና ክብካቤ ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል። ባለው ዓመት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በክልሉ ከ288 ሚሊዮን በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን የጽድቀት መጠናቸውም 86 በመቶ መሆኑን የቢሮው መረጃ ያሳያል።    
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የቆላማ ስርአተ ምህዳር የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ ፕሮጀክት እየተገበረ ነው
Apr 25, 2024 124
መቀሌ ፤ሚያዚያ 17/2016 (ኢዜአ)፦ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች 120 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የቆላማ ስርአተ ምህዳር የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ ፕሮጀክት እየተገበረ መሆኑን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ። ፕሮጀክቱን በትግራይ ክልል ለማስጀመር በተዘጋጀ የትውውቅ መድረክ ላይ እንደተመለከተው፣ ፕሮጀክቱ በቆላማ የሀገሪቱ አካባቢዎች 120 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው። በባለስልጣኑ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ደሳለኝ ሙሉጌታ እንደገለጹት የቆላማ ስርአተ ምህዳር የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ ፕሮጀክት በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች እየተተገበረ ይገኛል። በፕሮጀክቱም በዋነኛነት በከፍተኛ ሁኔታ እየተጎዳ ያለው የአካባቢ ስነምህዳር እንዲያገግም ለማድረግ የሚያግዙ ሥራዎች በመከናወን ላይ ናቸው። በተለይ በቆላማ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች የአፈር መከላትን ለመከላከል የደን ልማት ጥበቃ ሥራን ጨምሮ በተለያዩ የገቢ ማስገኛ የሥራ እድሎች እንዲሰማሩ መደረጉን ገልጸዋል። ከእዚህ በተጨማሪ ለአየር ንብረት ለውጥ መሻሻል የበኩላቸውን እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን ነው አቶ ደሳለኝ ያስረዱት። በዚህም ነዋሪዎች የአየር ንብረትን በማይጎዱ የልማት ሥራዎች እንዲሰማሩና እንደ ሶላር ያሉ የሃይል አማራጮችን የመጠቀም ባህላቸው እንዲጎለብት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። መንግስት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ጋር በመተባበር ካለፋት ሦስት ዓመታት ጀምሮ ፕሮጀክቱን እየተገበረ ይገኛል ያሉት አስተባባሪው፣ ፕሮጀክቱ በትግራይ ክልል በተለያዩ ምክንያቶች ሳይተገበር ቢቆይም አሁን ወደስራ እየገባ መሆኑን ገልጸዋል። ፕሮጀክቱን በሁለት የትግራይ ወረዳዎች በሚገኙ አራት የገጠር ቀበሌዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ለማስጀመር መታቀዱንና የዛሬው መድረክም ፕሮጀክቱን ለማስተዋወቅ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።   በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የአየር ንብረት ለውጥና የአካባቢ ባለስልጣን ሀላፊ አቶ ፀጋይ ገብረማሪያም በበኩላቸው እንዳሉት፣ ፕሮጀክቱ በትግራይ ዘግይቶ ቢጀመረም በህዝቡ የተደራጀ ተሳትፎ ለማሳካት ጠንክረን እንሰራልን በለዋል። ፕሮጀክቱን ለማስተዋወቅ በተዘጋጀ መድረክ ላይ ከሁለቱ ወረዳዎች እና ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎችም ፕሮጀክቱን በተፋጠነ መልኩ ተግባራዊ በማድረግ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።  
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል- አንቶኒዮ ጉተሬዝ
Apr 15, 2024 1182
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- አለም ተጨማሪ ጦርነት እንድታስተናግድ እድል ባለመፍጠር በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አሳሰቡ። ኢራን እስራኤል ከሳምንታት በፊት ሶርያ በሚገኘው ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ጥቃት አድርሳብኛለች በሚል ባሳላፍነው ቅዳሜ ሌሊት መጠነ ሰፊ ጥቃት መሰንዘሯ በተለያዩ የዓለም መገናኛ ብዙሃን መዘገቡ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ በቀጣናውና በአለም ሀገራት የተፈጠረውን ከፍተኛ ውጥረት ለማርገብ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የጸጥታ ምክር ቤቱን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል። በስብሰባውም አለም ተጨማሪ ጦርነት የምታስተናግድበት ምንም አይነት አቅም ስለሌለ ሀገራት በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። ችግሩ በቸልታ የሚታይ ከሆነ አስከፊ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል መናገራቸውን ያስነበበው ፍራንስ 24 የጸጥታው ምክር ቤት አባላት ሁኔታውን በአስቸኳይና ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ሊያስቆሙት እንደሚገባ ማሳሰባቸውንም ዘግቧል።
በሞዛምቢክ በደረሰ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ
Apr 8, 2024 2097
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2016(ኢዜአ)፦በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል የባህር ዳርቻ በተከሰተ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ። በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው ናምፑላ ግዛት 130 የሚሆኑ ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ መስጠሟን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ነዋሪዎቹ በግዛቷ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ በመሸሽ ወደ ሌላ አካበቢ ለመሄድ በጀልባ በተሳፈሩበት ወቅት አደጋው እንደተከሰተ የገለጹት ባለስልጣናቱ ጀልባዋ መሸከም ከምትችለው የሰው መጠን በላይ በመጫኗ አደጋው እንደደረሰ አመልክተዋል። በዚህም ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይታቸው እንዳለፈ ማረጋገጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። በአሁኑ ወቅት አምስት ሰዎችን ከአደጋው በሕይወት ማትረፍ እንደተቻለ ያመለከተው ዘገባው ተጨማሪ ሰዎችን ለማዳን ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስነብቧል። የናምፑላ ግዛት ባለፈው አመት በሞዛምቢክ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ ክፉኛ ከተጎዱ አካባቢዎች መካከል አንዷ መሆኗም በዘገባው ተመላክቷል።
የአየር ንብረት ለውጥና መዘዙ
Apr 5, 2024 1390
በዓለማችን ላይ እየተስተዋለ ያለው የአየር ንብረት ለውጥ የተወሳሰበ ችግር እያስከተለ ከመሆኑ በተጨማሪ በስነምህዳር ላይ እያደረሰ ያለው አደጋ ሊቀለበስ ወደ ማይችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑን ሞደርን ዲፕሎማሲ ድረገጽ አስነበበ። ድረ ገጹ በዓለማችን በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የአየር ንብረት ለውጥ በሚያስከትለው ድርቅ፣ ጎርፍ እና ተዛማጅ በሆኑ ክስተቶች ምክንያት ቀያቸውን ጥለው ለመሰደድ እንደሚገደዱ አስነብቧል። የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በይነመንግስታት ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው አሁን ላይ ያለው የዓለማችን የሙቀት መጠን ወደ 1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴሊሺየስ እየተጠጋ በመምጣቱ በስነምህዳር፣ በከባቢ አየር እና በአካባቢ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እየተስተዋለ መሆኑን ገልጿል። የአየር ንብረት ለውጥ ለዘላቂ ልማት እንቅፋት በመሆን ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ክስተቶች የሚፈጥራቸውን ችግሮች በማባባስ ለሰዎች መፈናቀልና የህይወት መጎሳቆል እያደረሰ ይገኛል። እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 በማዕከላዊ አሜሪካ እና ደቡባዊ ሜክሲኮ የተከሰተው ሃሪኬን ኤታ የተባለው የአየር ንብረት ለውጥ ክስተት ያስከተለው የሰብል ውድመትና የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ የደረሰው አደጋ ከባለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ውስጥ እጅግ የከፋ አደጋ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። በዚህም በጎርፍ፣ በመሬት መንሸራተትና በሰብል ውድመት ምክንያት ከ1 መቶ 20 ሺህ በላይ ሰዎችን ከሞቀ መኖሪያቸው ተፈናቅለው እርዳታ ጠባቂ እንዳደረጋቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽንን መረጃ ዋቢ አድርጎ አትቷል። የአየር ንብረት ለውጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን የጠቆመው ድረ ገጹ በቀጣይ ተመሳሳይ ችግሮች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉም አመልክቷል። በአውሮፓውያኑ 2022 ወደ 32 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተፈናቀሉ ሲሆን፤ ይህ አሃዝ በ2008 ከተከሰተው በ41 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ዘገባው አመልክቷል። ይህም የዓለማችን የሙቀት መጠን እየጨመረ መምጣቱን እንጂ ምንም ዓይነት የመቀነስ አዝማሚያ ያላሳየ መሆኑን ያመለከተው ዘገባው በቺሊ፣ ካናዳ፣ ዛምቢያ፣ ሞዛምቢክ፣ ሜክሲኮ፣ ኢክዋዶር፣ ሊቢያ እና በሌሎችም አገራት ሃሪኬን በተሰኘው የአየር ለውጥ፣ በሰደድ እሳት፣ በጎርፍ እና በድርቅ ምክንያት ለባለፉት በርካታ ወራት መፈናቀልን እንዳስከተለ ተገልጻል። የአለም ባንክን የትንበያ መረጃ ዋቢ ያደረገው ድረ ገጹ በአውሮፓውያኑ 2050 ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ 216 ሚሊዮን ሰዎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ተመላክቷል። ድረገጹ ይሄ ክስተት የሚያስከትላቸው ችግሮች እንዳይቀጥሉ መቆጣጠር ካስፈለገ ዘላቂ ልማት ላይ ያተኮሩ ግንዛቤን የሚያሳድጉ ትምህርቶች፣ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ እውነተኛ ውይይቶች እና ተፈጥሮን መሰረት ያደረጉ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ በማሳሰብ መሪዎች የሚጠበቅባቸውን ሊተገብሩ ይገባል ሲል ምክሩን አስቀምጧል።  
ሐተታዎች
ነገረ - አስተውሎት
Apr 24, 2024 139
ሰው በሀሳብ ከሕይወታዊያን ፍጥረት ይለያል። ከፍጥረቱ ጀምሮ ኑሮውን ቀላል ለማድረግ አስቧል። ሀሳቡም መላ ፈጥሯል። ድንጋይ አፋጭቶ እሳትን አንድዷል። እንስሳትን አላምዶ፣ ሰብልን አባዝቶ፣ መጠለያውን ቀልሶ… ኑረቱን አሳልጧል። ዕለታዊ ተግባሩን ለማቃለል በቁስ ላይ ተመራምሮ አጋዥ ቁስ ፈጥሯል። በሂደትም የኢንዱስትሪን አብዮት አፈንድቷል። በ18ኛው ክፍለ ዘመን በባተው የኢንዱስትሪ አብዮት ዓለም አዲስ ክስተት አስተናግዳለች። ፋብሪካዎች፣ መኪናና አውሮፕላን፣ የእንፋሎትና የኤሌክትሪክ ኃይልና የኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂዎች ተፈብርከው ምርትና ምርታማነት ጨምሯል። ከተሜነት አብቧል። የዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ አውቶሜሽን፣ ሮቦቲክስና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች በሰው ተፈጥረዋል። ሳይንስን ለመፍትሔ-እንከን አውሏል። ቴክኖሎጂን ለሁለንተናዊ ሕይወት ማቃለያ ተጠቅሟል። ጊዜ፣ ጉልበትና ሀሳብን ከፈጠራ ጋር አዋዶ ኑሮና ሕይወት አቅልሏል። ኮምፒዩተር ፈበረከ፤ ኢንተርኔትን ፈጠረ፣ ዓለምን አስተሳሰረ። የተዓምር ዘመን ሆነ። ሰው እያስተዋለ... እያስተዋለ… በረቀቀ ጥበብና ግኝት ዛሬ ከዘመነ-አስተውሎት ደረሰ። ሰው ሰራሽ አስተውሎት!! የዘመኑ ቴክኖሎጂ ልህቀት ደረጃ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ) እንደሆነ ይጠቀሳል። ዳሩ የቴክኖሎጂው እምርታ የዘመን ክስተት ሳይሆን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በፊት ጀምሮ እርሾ ሲያቦካ እንደነበር የዘርፉ ምሁራን ይጠቅሳሉ። ዋረን ማክኩሎች እና ዋልተር ፒትስ ለዛሬው ሰው ሰራሽ አስተውሎት እርሾ የሆነ በነርቭ አውታረ መረብ የሚታገዝ ሒሳባዊ ሞዴል የፈጠሩት በ1943 ዓ.ም ነበር። በ1950 ዓ.ም ደግሞ አለን ተርኒግ እንደ ሰው ማሰብ የሚችል ማሽን ፈለሰፈ። በተመሳሳይ በ1960ዎቹ አጠቃላይ ችግር ፈቺ፣ ሎጂክ ቴዎሪስትና መሰል የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፕሮግራሞች በልፅገዋል። በ1950 ዓ.ም ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ራሱን ችሎ እንዲጠና ተወሰነ። ለውስብስብ ችግሮች አይነተኛ መፍትሄ መሆኑ ታመነበት። በ1970 እና 80ዎቹ የዘርፉ ሊቃውንት የሰውን ልጅ የመወሰን አቅም የሚተካ የኮምፒውተር ፕሮግራም ለማበልጸግ ጥረት አድርገዋል። በ1990ዎቹ ምርምሮቹ መቀዛቀዝ ጀምረው ነበር። በ21ኛው ክፍለ ዘመን ዳግም አንሰራርቷል። ስልተ ቀመርን (algorithm) የሚረዱ ማሽኖች ስራ ላይ ውለዋል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት የጥናት ዘርፍ የሰውን ስራና ሃሳብ በኮምፒዩተር መራሽ ቁሶች መተካት ነው። የሰው ልጅ ፍጥረት የሆኑ ማሽኖች መገንዘብ፣ መማርና ችግሮችን እንዲቀርፉ ማስቻልም ነው። ማሽኖች በሰው ልጅ ምትክ አካባቢን ማመዛዘን፣ መማር፣ ማቀድና መፍጠር፣ መተንተንና እንከኖችን ማምከን እንዲችሉ ማድረግ ነው። የሰውን የማሰብ ኅይል በኮምፒዩተር አዳብሮ በሰውኛ ጥበብ ሕይወትን ማቅለል ነው። አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሰው ልጅ ያሉትን የስሜት ህዋሳት ክህሎቶች ለማሽኖች በማስተማር ሰዎች ነገሮችን በቀላሉ እንዲያገኙና እንዲተገብሩ ማስቻል ነው። በዚህም የኮምፒውተር ሊቃውንት ስልተ ቀመር ወይም አልጎሪዝምና አስበው የሚሰሩ ማሽኖች ወደ ስራ እያስገቡ ነው። ለአብነትም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ጥበብ ቤት የሚያጸዱ ሮቦቶች፣ አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪዎች፣ ሰው አልባ ጦር መሳሪያዎች፣ የደህነንት ጥበቃ ካሜራዎች፣… በልጽገው ስራ ላይ ውለዋል። በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ የተጀመረው ይህ ቴክኖሎጂ ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተስፋም ስጋትም ይዞ መምጣቱ ይነገራል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት ዛሬ ላይ በሁሉም መስክ ገቢራዊ እየተደረገ ነው። በትምህርት፣ በኢንዱስትሪ፣ በጤና፣ በደህንነት፣ በግብርና ዘርፎች ምርትና አገልግሎትን ለማቀላጠፍና ለመጨመር ቁልፍ አማራጭ ተደርጓል። ቴክኖሎጂው ከዓለም ገበያ ከ350 ቢሊዮን ዶላር በላይ ድርሻ አለው። አፍሪካም እያደገ የመጣውን ዓለም አቀፍ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ገበያ 10 በመቶ ድርሻ መያዝ ከቻለች እኤአ 2030 አሁን ያለው አህጉራዊ ጥቅል ምርቷ (ጂዲፒ) 50 በመቶ ይጨምራል። ኢትዮጵያ ከአራት ዓመታት በፊት ዘርፉን የሚመራ ተቋም መስርታለች፤ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን። ኢንስቲትዩቱ ኢትዮጵያን በአፍሪካ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ምህዳር ተጠቃሽ ሀገር ለማድረግ አበክሮ እየሰራ ነው። በቅርቡ የተመረቀው “አስተውሎት” የተሰኘ ፊልም ደግሞ ለዚህ ሁነኛ ማሳያ ነው። ሰው ሰራሽ አስተውሎት በሰው ልጅ የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ የማይገባበት ሕይወት እንደሌለ ፊልሙ ያስረዳል። በጤና፣ በማሕበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም፣ በመረጃ ፍለጋ፣ በፖለቲካ፣ በትምህርት፣ በኢኮኖሚ፣ በግብርና፣ በማዕድን ፍለጋና፣ በአገልግሎት አሰጣጥ የዚህ ቴክኖሎጂ ቁልፍ ሚና ተንጸባርቋል። ዘርፉ ከቅንጦት ይልቅ አስፈላጊነቱ ጨምሯል። ለበሽታ መከላከል፣ ለጤና እንክብካቤ፣ ለትምህርት መሻሻልና ድህነት ቅነሳ ይውላል። ለዚህም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ የተመሰረቱ መተግበሪያዎች ፈጠራና አቅም እያደገ መምጣቱ በፊልሙ ተገልጿል። ፊልሙ የኢትዮጵያ የቡና ዛፎችን የበሽታ ስርጭት ለይቶ ለማከም ያለውን ውጤታማነት ያወሳል። ሰው ሠራሽ አስተውሎት የአገራችንን ሉዓላዊነት በማስከበር ረገድ የሳይበር ደህንነትን ለመጠበቅ፣ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ፣ ምርታማነትን ለመጨመር፣ ገበያን ለማስፋት እና ለመሳሰሉት ሥራዎች በእጅጉ አስፈላጊ ነው። በአሁኑ ወቅት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ እየተስፋፉ ከሚገኙ አገልግሎቶች መካከል ማሽን ትራንስሌት ወይም የቋንቋ ትርጉም አንዱ ሲሆን በኢትዮጵያም አንዱን ቋንቋ ወደ ሌላ በመተርጎም አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። በዚህም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትም በአንድ መተግበሪያ የተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን መማር እንዲሁም ከድምጽ ወደ ጽሁፍ መቀየር የሚያስችል ሥርዓትን አበልጽጎ ለተጠቃሚዎች አቅርቧል። መተግበሪያው አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሶማሊኛ እና ትግርኛ ቋንቋዎችን በድምጽ እና በጽሁፍ ለመማር የሚያስችል ሲሆን ድምጽን ወደ ጽሁፍ መቀየር የሚያስችለው የመተግበሪያው አካል ድምጽን በመቅዳት ወይም ከመዛግብት (አርካይቭ) የድምጽ ፋይሎችን ወደ መተግበሪያው በማስገባት የጽሁፍ ቅጂውን ለማግኘት የሚያስችል መሆኑን ከፊልሙ መገንዘብ ተችሏል። በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የደረሰበትን ልህቀት ያማከሉና ከዘርፉ ውጤት ለማግኘት በአጭር ጊዜ ውስጥ የተኬደው ርቀት ይበል የሚያሰኝ ነው። ነገር ግን በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ የመጣውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ልህቀት በመመልከት ሀገራችንን የሚመስሉ የዘርፉን ውጤቶች የበለጠ ማላቅ ያስፈልጋል። በዓለም የዕለት ተለት እንቅስቃሴ ውስጥ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እያሳደረ የሚገኘውን ተጽዕኖ በመረዳት ለዘርፉ ምርምሮች የሚደረገውን ድጋፍ የበለጠ ማጠናከር ያሻል። ዓለም የሚሄድበትን ፍጥነት በመመልከት ሀገራችንን የሚመስሉ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ውጤቶችን ለመተግበር በትኩረት መሥራት ያስፈልጋል። (በሰለሞን ተሰራ)      
ብሩህ ነገን የሰነቁ እንስቶች
Apr 19, 2024 404
የሰው ልጆች ከፍጥረት እስከ ዕለተ ሞት ባሉት የሕይወት ዑደቶች ውስጥ በሚገጥሟቸው መልከ ብዙ ፈተናዎች ሳቢያ ራሳቸውን ለቀቢጸ ተስፋ ይዳርጋሉ፤ ተገደውም ወደ ማይፈልጉት ሕይወት ይገባሉ። በተለይም ሴቶች በሚገጥሟቸው አይነተ ብዙ ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ጫናዎች ሳቢያ በበርካታ የህይወት ውጣ ውረድ ወስጥ ያልፋሉ፤ በሂደቱም ለአካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት የተዳረጉ በርካቶች ናቸው፡፡ ለአብነትም በአዲስ አበባ ተወልዳ ያደገችው ቃልኪዳን በላይነህ (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) በወጣትነቷ ትዳር መስርታ፣ልጆችን ወልዳ ለመሳም በቅታለች፡፡ ዳሩ ግን ባለቤቷ በድንገተኛ አደጋ በመሞቱ ምክንያት ህጻን ልጆቿን ይዛ ለአስከፊ የኢኮኖሚ ችግር መዳረጓን ትናገራለች። በዚህም ራሷንና ልጆቿን ህይወት ለማቆየት ወደ ማትፈልገው የወሲብ ንግድ ሕይወት ውስጥ ለመግባት መገደዷን ነው የገለጸችው፡፡ በህፃንነት ዕድሜ ለአካል ጉዳተኝነት የተዳረገችው ሳምራዊት (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) በበኩሏ በአካል ጉዳተኝነቷ ምክንያት ተንቀሳቀሳ መስራት ባለመቻሏ ከተወለደችበት ገጠራማ ስፍራ ወደ አዲስ አበባ መምጣቷን ትናገራለች፡፡ በአዲስ አበባም ህይወቷን በልመና ስትመራ ቆይታለች፡፡ ሌላኛዋ ባለታሪካችን ሔዋን (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) ወደ ማትፈልገው ህይወት ውስጥ ስትገባ የሚያጋጥማት ማህበራዊ ፣ አካላዊ ጥቃት እና ስነልቦናዊ ጫና ቀላል አይደለም ትላለች። እሷም ኑሮን ለማሸነፍ የገባችበት የህይወት መስመር ወደ አላስፈላጊ ሱስ ውስጥ እንድትገባና ለስነ ልቦናዊ ቀውስ እንድትጋለጥ እንዳደረጋት ገልጻለች። መንግስት በመሰል ችግር ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ለመደገፍ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከዚህም ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ለመታደግ የሚያስችልና “ለነገዋ” የተሰኘ የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል አንዱ ነው፡፡ ማዕከሉ ለተለያዩ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ችግሮች የተጋለጡ ሴቶችን በስነ ልቦና የምክር አገልግሎት እና በተለያዩ ሙያዊ ስልጠናዎች በመስጠት ብሩህ ነገን ለማቀዳጀት ስራ ጀምሯል። እነ ቃልኪዳን፣ ሳምራዊት፣ ሔዋንና ሌሎች በችግር ውስጥ የነበሩ ሴቶችም ‘የነገዋ’ የተሰኘውን የተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከልን ተቀላቅለው የተሻለ ነገን ለመኖር ተስፋ ሰንቀዋል፡፡ በማዕከሉ በሚሰጣቸው ሙያዊ ስልጠናና የምክር አገልግሎትም ወደ ተረጋጋ መንፈስ እንዲመለሱ፣ የሕይወት ተሞክሮ እንዲቀስሙ፣ ነጋቸውን ለማሳመር እንዲነሳሱ ስለማድረጉም ይናገራሉ። ማዕከሉ በአዲስ አበባ መከፈቱ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ሴቶች ትልቅ ብስራት መሆኑን ገልጸው፤ መሰል ማዕከላትም በአገር አቀፍ ደረጃ ሊስፋፋ እንደሚገባ ጠቁመዋል።   “የነገዋ” የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሄርጳሳ ጫላ ማዕከሉ ወደ ስራ ከገባ አንድ ወር በላይ ማስቆጠሩን አስታውሰው፤ 500 ሴቶችን ተቀብሎ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ሰልጣኞች ከማዕከሉ ሲወጡ ራሳቸውን በኢኮኖሚ እንዲችሉ የሚያደርግ በልዩ የክህሎት፣ የስነ ልቦና እና የሙያ በአጠቃላይ በ18 አይነት የስልጠና ዘርፎች እያሰለጠነ መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ስፌት፣ ስነ ውበት፣ የምግብ ዝግጅት፣ የከተማ ግብርና፣ የሕጻናት እንክብካቤና ሌሎች ዘርፎች ከሶስት ወር እስከ ስድስት ወር እንደሚያሰለጥን ነው የገለጹት። ከስልጠናው በኋላ ለሰልጣኞች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠርም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር ማዕከሉ በትብበር እየሰራ መሆኑም ተናግረዋል፡፡ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማእከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር) መጋቢት 05 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ለአገልግሎት ከፍት መሆኑ ይታወሳል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ''እራትም... መብራትም'' የመሆን ጅማሬ
Apr 14, 2024 1523
ሲሳይ ማሞ (ከአሶሳ) ያኔ! 2003 ዓ.ም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ የተነገሩ ተስፋዎች የማየፈቱ ህልሞች ብለን ስንቶቻችን አስበናቸው ይሆን? በአካባቢው ሊኖር ስለሚችለው ታላላቅ ክስተቶች፣ ስለሚፈጠሩት መልካም ነገሮች በሰማንበት ቅጽበት በህልም ዓለም ውስጥ እንዳለን ስንቶቻችን አስበን ይሆን? "አዬ ህልም!?" በሚል ሲደርስ እናየዋለን በሚል ቀናት ቆጥረናል። ያኔ! ነገሮች ሲነሱና ሲተረኩ ስንቶቻችን እንሆን እዚህ ቀን ላይ ደርሰን እናይ ይሆን!? የሚል ሃሳብ በእዝነ ህሊናችን የተመላለሰው? ያኔ! የታላቁ ህዳሴ ግድቡ ሲጠናቀቅ ወደ ኋላ ከ240 በላይ ኪሎ ሜትሮችን የሸፈነ ውሃ ሐይቅ ሰርቶ ተንጣሎ እንደሚተኛ እያለምን መጩውን ዘመን በጉጉት የጠበቅን ስንቶቻችን ነን? ግድቡ ግንባታው ሲገባደድ አገር የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨት በዘለለ "ከሰው ሰራሽ ሐይቁ በሚወጣ ዓሳ ሌላ የገቢ ምንጭ ይፈጠርላታል፤ በሚፈጠረው ሰው ሰራሽ ሃይቅ ላይ የጀልባ ትራንስፖርትና የመዋኛ አገልግሎቶች ይጀመራል" የሚሉት መረጃዎችንና ትንታኔዎችን ከመገናኛ ብዙሃኑ ስንሰማ እንደርስ ይሆን? የሚል ጥያቄ ወደ አእምሯቸው ያልመጣ ቢኖሩ ጥቂቶች ሳይሆኑ አየቀሩም። ያኔ! እንደትንቢት የተነገረው ዛሬ ጊዜው ሲደርስ "ይሆናል" የተባለው ከጊዜ ወደ ጊዜ "እየሆነ" መጣ። ስለታላቁ ግድብ በህልም ደረጃ ሲገለፁ የነበሩ በዕውን ወደማሳየቱ እየተንደረደረ ይገኛል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር የተያያዘ ገጠመኜን ጀባ ልበላችሁ! ዕለቱ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ከማለዳው 12 ሰዓት ነው፡፡ አፍንጫዋ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የሰካች አንድ የሞተር ጀልባ ከደቡብ ወደ ሰሜን የተንጣለለውን ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ ለሁለት እየከፈለች ትጓዛለች ከማለት ትበራለች ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ሰው ሰራሽ ሐይቁ ውሃውን እንደልቧ እየቀዘፈች ለመጓዝ አስችሏታልና! ከምዕራብ በኩል የኮርቻ ግድብ (Saddle dam) ተጠማዞ እና በኩራት ደረቱን ገልብጦ ይታያል፡፡ በስተምስራቅ አቅጣጫ ላይ የሚገኘው የግድቡ ሃይቅ ደግሞ ለስለስ ያለ ሃምራዊ ቀለም ለተመላካቹ ያሳያል። የማለዳዋ የፀሐይ ጨረር ያረፈበት የውሃው ክፍል ለእይታ ባያስቸግርም ገና ከማለዳው ከአካባቢው ሞቃታማ አየር ጋር ተዳምሮ ወላፈን የሚመስል ሙቀቱን መርጨት ጀምሯል፡፡ ከፊት ለፊታችን ደግሞ በረጅም ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያቆረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ ፊት ለፊት ተንጣሎ ይታያል፡፡ የተሳፈርንባት የሞተር ጀልባ ስምንት ያህል መንገደኞችን ይዛለች፡፡ በሰው ሰራሽ ሐይቁ ላይ የሚደረግ ጉዞ ለተጓዡ ሐሴትን ጀልባዋን ለሚዘውራት ከዕለት ገቢ የዘለለ ተድላን እንደሚለግስ አያጠራጥርም። የአካባቢውን ድባብ እየተመለከትን ጉዟችንን ቀጠልን። በጉዞው ቅፅበትም ዓይኖቻችን በአንድ ወጣት አሳ አስጋሪ ላይ አረፉ። ወጣቱ በጀልባዋ ላይ ሆኖ በአንደኛው አቅጣጫ በኩል አጎንብሶ በመንጠቆ ያጠመዳቸውን ግዙፍ አሳዎችን አጥብቆ እየያዘ ወደ ጀልባዋ ይጨምራል። ከአቅሙ በላይ ሆነው ሊያመልጡት የሚታገሉ አሳዎችን ደግሞ በብረት አንካሴ ወገባቸውን እየወጋ ለመያዝ ይታገላል፡፡ ተጠግተን ለመርዳትና አሳዎቹን በመያዝ ለማገዝም ሆነ ሌላ ድጋፍ ለማድረግ አልደፈርንም፡፡ ወጣቱ ግዙፍ አሳዎቹ ጋር የገጠመውን ግብግብ በካሜራ ለማስቀረት ጥረት ማድረጉን ግን አልዘነጋሁትም። ወጣቱ ኢትማን መሃመድ ይባላል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የጉባ ወረዳ ነዋሪ ነው፡፡ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ሐይቅ ላይ አሳ የማስገር ስራ ከጀመረ ወራት አስቆጥሯል፡፡ “ቤተሰቦቼ እንደነገሩኝ ከ13 ዓመት በፊት ግድቡን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ አሁን በሞተር ጀልባ የምንጓዝበት ሃይቅ ይፈጠራል የሚል እምነት በአካባቢው ነዋሪዎች እሳቤ ውስጥ ፈጽሞ አልነበረም።” ሲል ይናገራል ወጣቱ፡፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሃይቅ ለእርሱ እና ለሌሎች ከእርሱ ጋር ለተደራጁ 25 ወጣቶች የሥራ እድል በር መክፈቱን አጫወተኝ፡፡ ከታላቁ ግድብ ያገኙት ትሩፋት እርሱ እና የማህበሩ አባላት በአገራቸው ላይ ሰርተው የመለወጥ ተስፋቸውን በእጅጉ እንዳለመለመላቸው አጫውቶኛል፡፡ ከዚህ ቀደም በአካባቢው ከሚገኙ ወንዞች አሳ ቢያመርቱም በህዳሴው ግድብ አማካኝነት ከተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ የሚያገኙት ግን በዓይነትም በመጠንም የተለየ እንደሆነ ይናገራል። ከሐይቁ እስከ 50 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ነጫጭና ሌሎች ዓሳዎችን እያሰገረ መሆኑን በአድናቆት ጭምር ይገልፃል። ማህበሩ በቀን እስከ ሁለት ኩንታል ወይም ሁለት መቶ ኪሎ ግራም ገደማ ዓሳ ያመርታል፡፡ “የህዳሴው ግድብ የምግብ ዋስትናም ፤ የገቢ ምንጭም ሆኖናል” ሲልም ወጣቱ ሃሳቡን ቋጭቷል። ለሰዓታት በቆየሁበት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ የአሳ ማስገር እንቅስቃሴ ላይ ኢትዮጵያውያን በአንድነት መንፈስ ከገነቡት ግድብ የስራ ዕድል ተጠቃሚ የመሆን ጅማሬን ይስተዋላል። ነገሩ እንዲህ ነው! በባህር ዳር ጣና ሃይቅ ላይ ያካበተውን የአሳ መረብ አሰራር እና የሞተር ጀልባ አጠቃቀም ልምድ ለማካፈል ወደ ስፍራው ያቀናው ወጣት የሻምበል ወርቁ በማህበር ተደራጅተው አሳ ለሚያሰግሩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ወጣቶች ስልጠና ሲሰጥ ማግኘቴ ቀደም ብዬ የጠቀስኩትን መረጃ እውነታነት ያሳያል። “አንዱ ወንድሜ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ይሄም ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እኔም ከአማራ ክልል ነኝ፡፡ ሁላችንም እኩል የግድቡ ትሩፋት ተጠቃሚ ነን፡፡ ከዚህ ቀደም በአካል የማንተዋወቀውን ኢትዮጵያውያንን ግድቡ አስተዋውቆናል” ብሎኛል የሻምበል። ሌላው የመንጠቆ አጣጣል ስልጠና ለመስጠት ከአርባምንጭ ተጉዞ ወደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ መጥቶ ያገኘሁት ደግሞ ወጣት አልማው ደሳለኝ ነው። ''ለአካባቢው ወጣቶች ልምዴን እና ያለኝን ዕውቀት በማካፈሌ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ'' የሚለው ወጣቱ፤ በሃይቁ ላይ የተመለከተው ከፍተኛ የአሳ ሃብት እንደ እርሱ ያሉ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በመጥቀም ለአገሪቷም የተሻለ ገቢን ሊያመጣ እንደሚችል ያምናል። “ተባብረን በመስራት አገራችንን እንለውጣለን” በማለት ህብረትና አንድነት ከድህነት ለመውጣት የሚያስችል ዘመኑ የሚፈልገው ታላቅ መሳሪያ መሆኑን ያምናል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ...ተብለው ሲነገሩ የነበሩ የወደፊት ትልሞች አሁን እውን ሆነው 'ስራን ለሰሪው....ፍፁማዊ የገፅታ ለውጥን ለአካባቢው መልክዓ ምድር እንዲሁም ሰፊ የቱሪዝምና ሌሎች የስራ መስኮችን ለሚመለከተው አካል ለመስጠት የተግባር ጅማሬ እየታየ ነው። በግድብ ግንባታው የመሰረት ድንጋይ ማኖር ወቅት "በይሆናል" ሲባሉ የነበሩ ዕቅዶች እውን ወደ መሆን...ወደ መጨበጥ እየመጡ መሆናቸው ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው። ለኢትዮጵያውያን የ”ይቻላል” ተምሳሌት የሆነው ግድብ ዋነኛ በይበልጥ ሲጠቀስ ከነበረው የኃይል አቅርቦት ባሻገር ለዜጎች ሌላ የስራ መስክ በመፍጠር ' እራትም መብራትም' ሆኖ እስከመጨረሻው ሊዘልቅ እነሆ ውጤቱን እያሳየ ነው። እንግዲህ የነገ ሰው ብሎን ትሩፋቱን በይበልጥ ያሳየን !!  
በህብር የተገነባ ገድል
Mar 25, 2024 2430
  "የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም የትውልድ አሻራ ደምቆ የተፃፈበት የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። ይህ ቀን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት የረባ ጥቅም ሳይሰጥ ወደ ጎረቤት አገራት ሲፈስ የኖረውን የአባይ ወንዝ ወደ ብርሃን ለመቀየር በቁርጠኝነት በመነሳት የማይቻልን ነገር በይቻላል ወኔ በመቀየር ለዓለም ያሳዩበት፤ ዓለም የተደመመበት ቀን ነው። የግድቡ ግንባታ በተጀመረበት ወቅት በርካታ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያ ይህን ግዙፍ ፕሮጀክት ታሳካው ይሆን? የሚል ጥርጣሬ አዘል ርእስ የያዘ ተከታታይ ዘገባ አስነብበዋል። ኢንተርናሽናል ሪቨርስ የተሰኘው ድረ ገጽ በፈረንጆቹ 2011 ‘Can Ethiopia Afford the Grand Renaissance Dam?’ በሚል ርእስ ባወጣው ሰፋ ያለ ዘገባ ግድቡን ለመገንባት ከሚያስፈልገው ጠቅላላ ገንዘብ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ሊያዋጡ የሚችሉት በጣም ጥቂቱን ብቻ በመሆኑ ግንባታው ሊሳካ አይችልም በሚል ትንበያውን አስቀምጦ ነበር። የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገው ግሪን ፕሮፊት የተሰኘ ድረ ገጽ የግድቡን ግንባታ አስመልክቶ ‘Defiant Ethiopia is proceeding with its plan to build the Grand Millennium Dam on the Nile River, but what kind of dam can they build without cash flow? ..... there’s one important problem: Ethiopia lacks the necessary funds to see the project to completion. In fact, they can barely get it off the ground.’ በማለት ኢትዮጵያ ግድብ መገንባት የሚያስችል ገንዘብ ስለሌላት ፕሮጀክቱ ሊተገበር አይችልም ሲል ደምድሟል፤ ተሳልቋልም። በወቅቱ የዚህ ዓይነት ግምት የብዙዎቹ ተንታኞች መንደርደሪያ ነበር። “ኢትዮጵያ ደሃ አገር ስለሆነች ከዓለም አቀፍ ተቋማት ብድር ካልተገኘ በስተቀር ፕሮጀክቱ ወደ ፍፃሜ መድረስ አይችልም” የሚል ድምዳሜ ለመስጠት ተንታኞቹ ብዙም አይቸገሩም ነበር። ‘ግድቡ የጥራት ችግር ስላለበት ይደረመሳል’ ከሚለው ዘመቻ ጀምሮ በግድቡ ላይ ጥቃት እንደሚፈጸምበት ተደጋጋሚ የዛቻና የማስፈራሪያ መልእክቶች ተስተጋብተዋል። በጥቅምት ወር 2013 ዓ. ም የቀድሞ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በህዳሴ ግድብ ግንባታ ግብጽ ተጎጂ እንደሆነች አቋም በመያዝ "ግብፅ በዚህ መንገድ መቀጠል ስለማትችል ሁኔታው አደገኛ ነው፤ ግብፅ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳለች፤ አሁንም በግልፅ እናገረዋለሁ ግብፅ በድጋሚ ታፈነዳዋለች" የሚል ጠንከር ያለ የዛቻ መልእክት አስተላልፈዋል። ኢትዮጵያውያን ውኃ ወደ ናይል እንዳይፈስ የሚያቆም ግድብ ገንብተዋል ሲሉ የገለጹት ትራምፕ ግብጽ ትንሽ በመበሳጨቷ ልትወቅሷት አትችሉም ሲሉም አክለዋል። "ግብፅ የህዳሴ ግድብ እንዲገነባ መፍቀድ አልነበረባትም፤ የስምምነት ሀሳብ ለአገራቱ ባቀርብም ኢትዮጵያ ስምምነቱን ሳትቀበል ቀርታለች። እንደዚያ ማድረግ አልነበረባቸውም ይህ ትልቅ ስህተት ነው። በዚህም ምክንያት የምንሰጣቸውን ብድር አቁመናል። ስምምነቱን ካልተቀበለች በስተቀር ኢትዮጵያ ገንዘብ አታገኝም " ብለዋል። አትዮጵያ የህዳሴ ግድብን ለመገንባትና ዳር ለማድረስ ብድርና ዕርዳታ እንዳታገኝ የተለያዩ ኃይሎች ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። በዚህም ምክንያት የፕሮጀክቱን ወጪ ለመሸፈን የሚተባበር አገር ወይም ተቋም ማግኘት አልተቻለም፡፡ ስለሆነም የነበረው አማራጭ አንድም ግድቡን አለመሥራት፣ አለበለዚያ ወጪውን በራስ አቅም መሸፈን ነበር፡፡ ከእነዚህ ከባድ ሁለት አማራጮች መካከል የኢትዮጵያ ሕዝብ ምርጫ ወጪውን በራሱ አቅም በመሸፈን መስዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን በተግባር አረጋገጠ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነበር ኢትዮጵያውያን ገጠር ከተማ ሳይሉ፤ በአገር ውስጥና በውጭ ከጫፍ እስከ ጫፍ በእልህና በቁጭት በመነሳሳት ግድቡን በራሳቸው አቅም ገንብተው ዳር ለማድረስ ቃል ኪዳን ያደረጉት። ለግንባታው የሚውል ድጋፍ በገንዘብና በዓይነት በተለይም የቦንድ ሽያጭ፣ በ8100 አጭር መልእክት እና በእጣ አገልግሎት ህዝቡ ተረባረበ፤ የማይቻለውን እንደሚቻል ለዓለም አሳየ። በበርካታ ፈተናዎችና ጫናዎችን ሳይበገር ግንባታው የቀጠለው የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት የሲቪል ስራው 99 በመቶ መድረሱንና የኤሌክትሮ ሜካኒካል በተለይም የተርባይንና ጄኔሬተር ተከላ ሥራው 78 በመቶ መጠናቀቁን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባት ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት በቅርብ ያወጣቸው መረጃዎች ያመለክታሉ። ከለውጡ ማግስት ጀምሮ መንግስት ልዩ ትኩረት ከሰጣቸው ፕሮጀክቶች መካከል የህዳሴው ግድብ ቀዳሚው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ "የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" በማለት አረጋግጠዋል። በዚህም ኢትዮጵያ ከግድቡ ግንባታ ጋር የተያያዙ ውስጣዊና ውጫዊ ጫናዎች ቢኖሩባትም የግድቡን ሥራ ለአፍታም አላቋረጠችም። በአሁኑ ወቅት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አፈፃፀም ከ95 በመቶ በላይ መድረሱን የሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል። ዘንድሮ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መሠረት ድንጋይ የተጣለበትን 13ኛ ዓመት ይከበራል፤ መሪ ሀሳቡም "በኅብረት ችለናል!" የሚል ሲሆን ኢትዮጰያውያን ችለው ያሳዩበት ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። እዚህ ድል ላይ የተደረሰው በመንግሥት ቁርጠኛ አቋምና የዲፕሎማሲ ጥረት እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ነው። ባለፉት 13 ዓመታት ኢትዮጵያውያን ለግድቡ ግንባታ 18 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል። በኢትዮጵያውያን ያልተቋረጠ ተሳትፎ ተጀምሮ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ሊጠናቀቅ ወራቶች የቀሩት ይህ ታላቅ አገራዊ ፕሮጀክት የአገሪቱን የኃይል ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ ከማሻሻሉም ባሻገር ለጎረቤት አገራት ተደራሽ በማድረግ ቀጣናውን በማስተሳሰር በኩል ሚናው ከፍተኛ ነው።  
ትንታኔዎች
መልከ ብዙው የ"ዳሞታ ተራራ"
Apr 23, 2024 209
የዳሞታ ተራራ ወላይታዎች የሚታወቁበት የራሳቸው የሆነ ባህል፣ ቅርስ እንዲሁም መለያ ምልክት ነው። ዳሞታ የወላይታ የልምላሜ መገለጫና የተፈጥሮ መስህብ ነው። ተራራው በወላይታ ሶዶ ከተማ ዙሪያ በሚገኝ 12 ሺህ 500 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በ32 ምንጮችና በ12 ጅረቶች ታጅቦ በኩራት ተንሰራፍቶ የሚገኝ የአካባቢው ማህበረሰብ መጠሪያ ነው። ከዚህ የተነሳ የወላይታ ሶዶ ከተማን ተፈጥሮ ካደላት የዳሞታ ተራራ ሞገሷ የተነሳም ተራራው ፀዳሏ ነው ብለው የሚጠሩትም አልጠፉም። የዳሞታ ተራራ ለአካባቢው ነዋሪም ሆነ አካባቢውን ሊጎበኙ ለሚመጡ እንግዳ ተቀባይነቱን በአረንጓዴ የተፈጥሮ መስህቦቹ በማሸብረቅ ውበቱን በመግለፅ የሚያሳይ ተራራ ነው። ተራራውን ወደ ላይ ለሚመለከተው ዳሞታ ብዙ የሚያሳየውና የሚነግረው ታሪክ እንዳለው ያሳብቃል። የታሪክ ድርሳናት እንደሚያስረዱት የዳሞታ ተራራ ለ800 ዓመታት ገደማ የቆየ ታሪካዊ የመስህብ ስፍራ ነው። በጥቅጥቅ ደኖች፣ በወራጅ ወንዞችና ጅረቶች፣ ለመድኃኒትነት በሚያገለግሉ ቁጥር ስፍር በሌላቸው የእፅዋት ዘሮችም የተሸፈነ ነው። በወላይታ ዞን እምብርት በወላይታ ሶዶ ከተማ ሰሜናዊ አቅጣጫ ከፍታ ላይ የሚገኘው የዳሞታ ተራራ ከፍታው ከባህር ጠለል በላይ 3000 ሜትር እንዲሁም የዙሪያ ልኬቱ ከ68 ኪሎ ሜትር በላይ እንደሆነም ይነገራል። በአንድ ወቅት ተራራው በአካባቢ መራቆት፣ በአየር ሚዛን መዛባትና በሌሎች ምክንያቶች ግርማውንና ልምላሜውን እያጣ መጣ። ይህም የወላይታን ህዝብ በማሳሰቡ ሁሉም የአካባቢው ማህበረሰብ ልጅ አዋቂ ሳይል ርብርብ በማድረግ ወደ ቀደመ አቋሙና ሙላቱ ለመመለስ ብርቱ ተፈጥሮን የመከላከል ፍልሚያ አደረገ። ፍልሚያውም በአካባቢው ማህበረሰብ አሸናፊነት በመጠናቀቁ ተራራው ልምላሜውን ጠብቆ አሁን የተላበሰውን ግርማ እንዲይዝ በማድረግ ሊያጣው የነበረውን ጥቅጥቅ ደን በመመለስ የመሬት መሸርሸርን ከመከላከልና የመንገድና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ከመጠበቅ አልፎ ትልቅ የአይበገሬነት ታሪክ እንደፃፈም ይወሳል። ለዚህም ነው ዳሞታን ከወላይታዎች ማህበረሰቡን ከተራራው ለመለየት እንደማይቻልና ጠንካራ ተዛምዶን የመሰረቱ መሆናቸው የሚገለፀው። የወላይታ ዞን የሀገር ሽማግሌ አቶ አብርሃም ባቾሬ እንደሚሉትም ዳሞታ በርካታ የቱሪስት መስህቦች፣ ታሪካዊ ቅርሶች፣ የሀገር በቀል እፅዋት፣ የዱር እንስሳትና ጥንታዊ የወላይታ ነገስታት መናገሻ ስፍራዎች ባለቤት ነው። የዳሞታ ተራራ ከወላይታ ህዝብ ታሪክና ጀግንነት እንዲሁም ከአሸናፊነት ወኔው ጋር የተቆራኘ ስለመሆኑም ያነሳሉ። በዙሪያው ዘመናትን ያስቆጠረ የጥቅጥቅ ደንና የነገስታት መኖሪያ እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናትና አድባራት የሚገኙበት መሆኑን አንስተው ለወላይታ ሶዶ ከተማም የተለየ ግርማ ሞገስን እንዳላበሳት ተናግረዋል። በዳሞታ ተራራ ዙሪያ የተኮለኮሉት ወንዞችም መነሻቸውን ከተራራው በማድረግ ወደ ታች እየተገማሸሩ ይነጉዳሉ። ወይቦ፣ ቁሊያ፣ ካልቴ ቶቦቤ፣ ሀመሳ፣ ሊንታላ፣ አይከሬ፣ ዋላጫ፣ ጫራቄ፣ ቦልዖ፣ ካዎ ሻፋ፣ ጋዜና ሻፋና ሌሎች ወንዞች ከዚሁ ተራራ ተጎራብተው፣ ከተራራው ያገኙትን መዳኛ ፀበል ለሌሎች ለማቋደስ አየተንደረደሩ ይወርዳሉ። ለአካባቢው ማህበረሰብም ልምላሜያቸውን ያጋባሉ፤ ብርቱውን መሬቱን ምሶ ገበታውን እንዲያበለፅግ ያተጋሉ። ሁሉም ግን የዳሞታ መልዕክተኞች፣ የዳሞታ ተጧሪዎች ናቸው። እንደ አቶ አብርሃም ገለፃ በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ገደማ የክርስትና ሀይማኖትን በአካባቢው በማስፋፋት ስመ ገናና የሆኑት አቡነ ተክለሃይማኖት ክርስትናን ለመስበክና መንፈሳዊ ክዋኔዎች ለመፈጸም ዳሞታ ተራራን ይወጡ እንደነበረ ከልጅነታቸው ይነገራቸው እንደነበር ያስታውሳሉ። ይህ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የመንፈሳዊ አገልግሎቶችን ሲያከናውኑ ድካም ሲሰማቸው እረፍት የሚያደርጉበት ለመንፈስ ሃሴትን የሚያጎናፅፍ ስፍራ ነው የዳሞታ ተራራ። በዚህ ምክንያት "ጦሳ ፔንጊያ" የእግዜር መተላለፊያ የተሰኘ ስያሜ የተሰጠውና "ጣዛ ጋሯ" የንጉስ ሞቶሎሚ ቤተ-መንግስት፣ የንጉስ ሞቶሎሚ የጥምቀት ሥፍራ፣ ቆሊ ቦርኮታ፣ ዳጌቾ፣ ቦቄና ሶዶ፣ ጦማ ገሬራና ሌራቶ ጎዳ የተሰኙ ታሪካዊና የሚጎበኙ ስፍራዎች ይጎበኙበታል በዳሞታ ተራራ። ካዎ ሞቶሎሚ፣ ካዎ ዳሞቴ፣ ካዎ ጎቤና ካዎ ጦና የሚባሉ የወላይታ ነገስታት ቤተ-መንግስታቸውን በተራራው አናትና ግርጌ ላይ ይገነቡ እንደነበር አቶ አብርሃም ይናገራሉ። የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ፣ የዳሞታ ተራራ በወላይታ ህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ታሪክ ውስጥ ደማቅ አሻራ ያለው መሆኑን ይገልፃሉ። ከተራራው አናት መነሻቸውን የሚያደርጉ ወንዞች የወላይታን ምድር አጥግበው ሰዎችና እንስሳቱን አጠጥተው ወደ ብላቴ እና ኦሞ ወንዝ ይፈሳሉ። የዳሞታ ተራራ ሌላው ጠቀሜታው መሬት እንዳይሸረሸር ቀጥ አድርጎ በዛ ግዝፈቱ ይዟል ይሄም ለመንገድ ደህንነትና የአካባቢውን አየር ተስማሚ ከማድረግ አኳያ አይተኬ ሚና አለው። በጥቅጥቅ ደን የተሸፈነው የዳሞታ ተራራ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ከዘመናት በፊት ተጀምሮበታል ይላሉ አስተዳዳሪው። ንፁህ የመጠጥ ውሃን በከፊል ለሶዶ ከተማ የሚያጠጣውን የዳሞታ ተራራ የቱሪስት ማዕከል ለማድረግ ከዩኒቨርስቲና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ ነውም ብለዋል። የዳሞታ ተራራ ታሪካዊ ይዘቱን ስንመለከት አካባቢው ቀደም ሲል የነገስታት መናገሻ ቦታ ነበር የሚሉት ደግሞ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል ተመራማሪ ዶክተር አበሻ ሽርኮ ናቸው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከወላይታ ሥርወ-መንግስት መካከል ካዎ ሳቴ ሞቶሎሚና የሌሎች ነገሥታት መናገሻ ስፍራ ስለነበር በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ ያለው ታሪካዊ ስፍራ ነው። የዳሞታ ተራራ ለአብዛኞቹ በወላይታ ዞን ለሚገኙ ወረዳዎች የስያሜያቸው መነሻ ነው። ዳሞት ጋሌ፣ ዳሞት ሶሬ፣ ዳሞታ ወይዴ፣ ዳሞት ፑላሳ ወረዳዎችና ሌሎች ቀበሌያት የተራራውን ስም መነሻ ያደረጉ መሆኑ ተራራውን ታሪካዊ ያደርገዋል። እዚሁ ተራራ ላይ ካሉ የተለያዩ መስህቦች መካከል የጥንታዊ ዋሻ "ሞቼና ቦራጎ" ዋሻ አንዱ ነው። ይህ ዋሻ በወላይታ ሶዶ ከተማ በሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ የሚገኝ የጥንት ሰው መኖሪያ ዋሻ ነበር። ዋሻው በዳሞታ ተራራ ከሚገኙ ከአምስት በላይ ዋሻዎች አንዱ ሲሆን በተራራው በስተምዕራብ አቅጣጫ በኩል የሚገኝና ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት ሰዎች በዚሁ ዋሻ ይኖሩ እንደነበረም ታሪክ ያስረዳል። ሞቼና ቦራጎ ዋሻ ስፋቱ 38 ሜትር፣ የጣሪያው ከፍታ 33 ሜትር፣ የዋሻው ዙሪያ ልኬት ደግሞ 58 ሜትር፣ እንዲሁም በውስጡ ከአምስት መቶ በላይ ሰዎች የመያዝ አቅም ያለው እንደሆነም መረጃዎች ያመላክታሉ። ሌላው ከዳሞታ ተራራ መስህቦች መካከል አንዱ የሆነውን ደብረ-መንክራት አቡነ ተክለኃይማኖት ገዳም ላስተዋውቃችሁ። ይህ ገዳም ለአቡነ ተክለኃይማኖት መታሰቢያነት በ1887 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ ከመመስረቱ ጋር በተያያዘ የተገነባና በዳሞታ ተራራ ምዕራባዊ ራስጌ የሚገኝ የቱሪስት መስህብ ሥፍራ እንደሆነ ነው ዶክተር አበሻ የሚናገሩት። ገዳሙ የአምልኮና የፀበል አገልግሎት እየሰጠ ከአንድ ክፈለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ በወላይታ ዞን ካሉ መንፈሳዊ ስፍራዎች አንዱ ሲሆን በውስጡ በርካታ ሐይማኖታዊና ታሪካዊ ቅርሶች ያሉት በመሆኑ በኢትዮጵያ ሐይማኖታዊ ጉዞ ከሚደረግባቸው መዳረሻዎች አንዱ ነው። በመሆኑም አካባቢው ለቱሪስት መዳረሻነት፣ ለአካባቢው ልማት ብሎም ለአየር ንብረት ሚዛንን መጠበቅ ጉልህ ሚና ያለው በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲያደርጉም አሳስበዋል።            
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች
Mar 2, 2024 3779
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች (ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ)   የአድዋ አድማስ ዘለል ገድል ሲወሳ የድሉ መገኘት የጦር አበጋዞች ከፊት ይመጣሉ። ከንጉሠ ነገሥቱ ጀምሮ ራስ፣ ደጃዝማች፣ ፊታውራሪ፣ ቀኛዝማች፣ ግራዝማች፣ ባላምባራስ እና ሌሎች ባለማዕረግ አዋጊዎች የድሉ የጀርባ አጥንት መሆናቸው እሙን ነው። ከመላ ሀገሪቷ ጠረፍ ተነቃንቆ ስንቅና ትጥቁን ታጥቆ፣ ድል ሰንቆ እስከ ግማሽ ዓመት ድረስ በባዶ እግሩ የተመመውን የሀገሬው ሰራዊት በቅጡ መርተው አዋግተዋል። ከመነሻ ሰፈር እስከ አድዋ ተረተር፣ ከአምባላጌ ኮረብቶች እስከ መቀሌ ጋራና ቁልቁለቶች፣ ከእንደአባ ገሪማ እስከ ማሪያም ሸዊቶ ሸለቋማ ቋጥኞች፣ ከምንድብድብ መስክ እስከ በገሠሦ አቆበቶች፣ .... ድልና ገድል በደምና በላብ ሲጻፍ የጠላትን የ'ክዱ' ማባባያ የጠሉ፣ ለሀገር ለመሰዋት የቆረጡ ጀግና አዋጊዎች፣ የሀገር ባለውለታዎች ነበሩ። በአድዋ ድል መታሰቢያ 12 የአድዋ ጦር አበጋዞች (ጀኔራሎች) ሀውልት ቆሞላቸዋል። እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ (አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ (አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። ከነዚህ የአገር ባለውለታዎች መካከል ሁለት ስመ ሞክሼ ጀግኖችን እንዘክራለን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከዳግማዊ አፄ ምኒልክ ቀዳሚዎች ስምንት ራሶች መካከል ብቸኛው የራስ ቢትወደድ (ከንጉሥነት በታች) ባለማዕረግ ናቸው። በፈረስ ስማቸው አባ-ገድብ ይሰኛሉ። በልጅነታቸው የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ባለሟል ሳሉ ከእስረኛው ምኒልክ ጋር ተዋወቁ። ምኒልክ ከአፄ ቴዎድሮስ አምልጠው ሸዋ ከገቡ በኋላ ከእቴጌ ጣይቱ ብጡል ወንድሞች ራስ ወሌ እና ፊታውራሪ አሉላ ብጡልን ይዘው ከመቅደላ ወደ ሸዋ ተሻገሩ፤ የምኒልክ ሁነኛ ሰው ሆኑ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም በሞት እስኪለዩ ድረስ በክፉም በደጉም ዘመን የአጼ ምኒልክ ከፍተኛ አማካሪና ተወዳጅ መስፍን እንደነበሩ፣ ከጦር ሜዳ እስከ ሽምግልናም ሁነኛ ሰው ሆነው ስለማገልገላችው በታሪክ ድርሳናት ተጠቅሷል። በሸዋ፣ ወሎ፣ ጎንደር፣ ዳሞት(ጎጃም) ተዘዋውረው በተለያዩ ግዛቶች በአስተዳዳሪነት ሰርተዋል። ድሕረ መተማ ጦርነት ምርኮኞች እንዲመለሱ፣ ድንበር እንዲካለል በመስራትም የዲፕሎማሲ ስራቸው ይጠቅሳል። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከተሳተፉባቸው ደማቅ ታሪኮች መካከል የአድዋ ድል ይጠቅሳል። ጦርነቱ አሀዱ ብሎ የጀመረው ሕዳር 28 ቀን 1888 አምባላጌ ነው። ለሁለት ሰዓታት በዘለቀው በዚህ ጦርነት ጀኔራል ቶዚሊ የተባለው የጠላት ጦር መሪ የተገደለበት ነው። በዚህ ዐውደ ውጊያ አባ ገድብ አንዱ ወሳኝ የጦር አበጋዝ ነበሩ። በተለያዩ የታሪክ ድርሳናት እንደተመዘገበው ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከግዛታቸው ከዳሞትና አገው ምድር የተውጣጣ ስድስት ሺህ እግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር ይዘው አድዋ ዘምተዋል። “አባ ገደብ መንጌ እያለ ኧረ ጐራው አምባ ላጌን ሰብሮ ቶዘሊን አስጐራው” የተባለው ለዚህ ይመስላል። አባ ገድብ ጥቅምት 11 ቀን 1903 ምሸት ከራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው ጋር እየተጫወቱ ካለምንም ህመም ድንገት አርፈው ቅድስት ሥላሴ ተቀበሩ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ ልጆቻቸውን ከተለያዩ መኳንንት ጋር በጋብቻ በማጣመር በኢትዮጰያ ታሪክ ተጠቃሽ መሆን ችለዋል። ለአብነትም ዘውዲቱ መንገሻ ጠቅላይ ሚኒስትር መኮንን እንዳልካቸውን፣ አስካለማርያም መንገሻ ልዑል ራስ ኅይሉን አግብተው የልጅ ኢያሱን ባለቤት ሠብለወንጌል ኅይሉን ወልደዋል። ደጃዝማች ጀኔራል አበበ ዳምጠውን ያገቡት ወሰንየለሽ መንገሻ ደግሞ የአልጋወራሽ አስፋወሰን ባለቤት ልዕልት መድፈሪያሽ ወርቅ አበበን ወልደዋል። ሌላው የአድዋ ጀግና የጦር መሪ ራስ መንገሻ ዮሐንስ (አባ ግጠም) ናችው። ትውልዳቸው ትግራይ፣ ዘመኑም 1857 ዓ.ም ነው። የአድዋ ጦር ውሎ ቁልፍ ሰው ራስ መንገሻ የአጼ ዮሐንስ (አባ በዝብዝ) ልጅ ናቸው። አጼ ዮሐንስ በተሰዉበት በመተማው ጦርነት ተሳትፈዋል። አባታቸው ከሞቱ በኋላም የትግራይ አገረ ገዥ ሆነዋል። በአድዋ ዘመቻ 12 ሺህ ጦር አሰልፈው በብርቱ ተዋግተዋል። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከአድዋ ጦርነት ቀደም ብሎ በአጼ ምኒልክ ላይ እንዲያምጹ ኢጣሊያኖች ሲገፋፋቸውና ሲያባብላቸው ቢቆዩም ከስልጣን ሽኩቻ ይልቅ የኢትዮጵያን ነጻነት መርጠዋል። ከአጼ ምኒልክ ጋር ቢኳረፉም በሀገር ሉዓላዊነት ግን አልተደራደሩም። የኢጣሊያ ወራሪ ጦር ትግራይ ሲገባም ራስ መንገሻ የወገን ደጀን ጦር እስኪደርስ ወደራያ አፈግፍገው፣ በአምባላጌ ጦር ሜዳ አንዱ ተሳታፊ የጦር ጀግና ነበሩ። ራስ መንገሻ የትግራይ ሀገረ ገዥ በመሆናቸውም የእርሳቸው እና በስራቸው የነበሩት የራስ አሉላ እንግዳ ጦር በጄኔራል አልቤርቶኔ ከሚመራው ጠላት ሃይል ቀዳሚው ተፋላሚ እንዲሆኑ አድርጎታል። “አይከፈት በሩ መግቢያ መውጫችን በል ተነስ መንገሻ ግጠም በር በሩን ይህን ጎሽ ጠላ ማን አይቀምሰው መንገሻ ዮሐነስ አንተን ገፍተው...” ተብሎ የተገጠመላቸውም ለዚህ ነው። የጠላት መግቢያ በር ዘብ በመሆናቸው። አባ ግጠም በአድዋው ታሪካዊ ጦርነት አሰላለፋቸው ማርያም ሸዊቶ በተሰኘው ተራራ በኩል ሲሆን ከራስ አሉላ፣ ከዋግሹም ጓንጉል ብሩና ከደጃዝማች ሀጎስ ጋር በመሆን ነበር። የጠላትን የመጀመሪያ ጥቃትን ያስተናገዱትም ራስ መንገሻ ዮሐንስ ናቸው። የአድዋ ድል ከተበሰረ በኋላ አጼ ምኒልክ ራስ መንገሻን ሹመውና ሸልመው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል። አጼ ምኒልክ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ማህበረሰቡ በጦርነት ስፍራ በመሆኑ ለደረሰበት ጉዳት 30 ሺህ ብር ድጋፍ ማድራገቸውን የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል የጻፉት ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደአረጋይ ተርከዋል። ከአድዋ ድል ከጥቂት ዓመታት በኋላ ራስ መንገሻ በአጼ ምኒልክ ላይ በማመጻቸው ተይዘው በቁጥጥር ስር ዋሉ። ሕዳር 6 ቀን 1899 ዓ.ም አንኮበር ግዞት ላይ አንዳሉ ማረፋቸውን የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከራስ መንገሻ አቲከም ግዛት ከአገው ምድር እመይቴ ተዋበች ጋር ትዳር መስርተው ዕውቁን የትግራይ መስፍን ራስ ሥዩም መንገሻን እንዲሁም ከእቴጌ ጣይቱ የወንድም ልጅ ወይዘሮ ከፈይ ወሌ ብጡል አግብተው አስቴር መንገሻን፣ አልማዝ መንገሻንና ብርሃኔ መንገሻን ወልደዋል፡፡ ለአብነት ያክል የሞክሼዎቹን ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ አነሳን እንጂ የዛሬ የ128 ዓመት በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ የጻፉ ጀግኖች ቁጥር ስፍር የላቸውም። ጀግኖቹን የመሩ የጦር መሪዎችም ብዙና ተጋድሏቸው የገዘፈ ነው። ከ11 ሺህ በላይ የጣሊያንን ሠራዊት ሙትና ቁስለኛ ያደረጉ፣ 4ሺህ የሚሆኑትን እጅ ያሰጡና የማረኩ እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር እንዲያስረክብ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሁል ጊዜም ክብር ይገባቸዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። (በአየለ ያረጋል)      
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች 
Mar 2, 2024 2562
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች ለመነሻ እኤአ በ1885 ጀርመን በተካሄደው የበርሊን ኮንፈረንስ አውሮፓውያን መላ አፍሪካን በካርታ ላይ የተከፋፈሉትን በተግባር መሬት ላይ ለመቀራመት ጦራቸውን ሰብቀው፣ ስንቃቸውን ጭነውና ትጥቃቸውን አጥብቀው ያካሄዱት ዘመቻና የወረራ ጉዞ የተገታባት አድዋ እና እለቷ ዛሬ ድረስ በተገፉ ህዝቦች ልብ ታትማ በአዕምሮ ውስጥ ተቀርጻ ትኖራለች። ጣሊያን የኢትዮጵያን መሬት፣ የአየር ንብረትና መልክዓ ምድር ተቆጣጥሮ ሀብቷን ለሮምና ለመላው አውሮፓ ለማቅረብ የቋመጠበት የዘመናት ህልሙ የተኮላሸበት ቦታ ጭምር ናት - አድዋ። ይህ ወራሪ ኃይል ሊቢያን በእጁ ካስገባ በኋላ ጉዞውን በቀይ ባሕር አስመራ አድርጎ መላ ኢትዮጵያን የመቆጣጠር ግብ ነበረው። ጄነራል ባራቴሪ የመደባቸው ጄነራል አልበርቶኒ፣ ጄኔራል አሪሞንዲ እና ጄነራል ቦርሜዳ በግንባር የተሰለፈውን ጦር ሲመሩ የኋላ ደጀንም እንደነበራቸው የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ከ17 ሺህ በላይ የጣሊያን ሠራዊት 66 የሚሆኑ መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና አውቶማቲክ መሳሪያዎችን ታጥቆ የግንባር ሜዳው ላይ ስለመድረሱ "የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው እስካሁኑ ዘመን" በሚል በአንድርዜይ ባርይትኒስኪ እና ዮዓና ማንቴል-ኒየችኮ ተጽፎ በዓለማየሁ አበበ የተተረጎመው መጽሐፍ ያስረዳል። የዛሬ የ128 ዓመት፤ ዕለቱም የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ በጀግኖች አባቶች ተሰራ። በጦርነቱ የጣሊያን መንግስት የጎመጀውን የኢትዮጵያን መሬት ሊያገኝ ይቅርና ከ11 ሺህ በላይ ሠራዊቱ ሙትና ቁስለኛ ሆኑ። 4ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ለጀግኖች አባቶቻችን እጃቸውን ሰጥተው ተማረኩ። እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር አስረከበ። የቀረው የፋሽስት ሠራዊትም ተንጠባጥቦ እግሬ አውጪኝ ብሎ ፈረጠጠ። ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ክብር፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት በአውደ ግንባሩ በፈጸሙት የጀግንነት ተጋድሎ ዓለምን ያስደመመና መላውን ጥቁር ሕዝብ ያኮራ ድል ተጎናጽፈዋል። በወቅቱ ነጭን ታግሎ ማሸነፍ አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ በይቻላል ተክቶ ሌሎችም ለነፃነታቸው እንዲታገሉ ያነሳሳ ደማቅ የታሪክ አሻራ አኑረዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። ኢትዮጵያውያን በብሔር፣ በሃይማኖት፣ በአካባቢና በሌሎች ልዩነቶች ሳይነጣጠሉ ለአገራቸው ክብርና ነጻነት በአንድነት ቆመውና መስዋት ከፍለው ያስመዘገቡት የጀግንነት ታሪክ ነው። በዓድዋ ድል ኢትዮጵያ ለአፍሪካና ለመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራትና የነፃነት ምልክት ሆናለች፡፡ የሰው ልጆችን እኩልነት በደም ዋጋ አረጋግጣለች።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋ ድል ደማቅና ታላቅ ቢሆንም በሚመጥነው ልክ መታሰቢያ አልነበረውም። ዛሬ ግን እነዚያ ዋጋ የከፈሉ ጀግኖችን በሚመጥን ሁኔታ በአዲስ አበባ ፒያሳ “የዓድዋ ድል መታሰቢያ” ተገንብቷል። ከአድዋ ድል 128 ዓመታት በኋላ፣ የተሰራው የአድዋ ድል መታሰቢያ በጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ተከፍቷል። የአድዋ ድል መታሰቢያ በአምስት ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን በአንድነት የተከፈለውን መስዋትነት፣ የአርሶ አደሮችን ተሳትፎ፣ የሴቶችን ተጋድሎ በሚያሳይ መልኩ፣ በአስገራሚ የኪነ-ህንጻ ጥበብ የታነጸ ነው።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የተገነባበት ስፍራ አገር በውጭ ወራሪ ኃይሎች እጅ እንዳትወድቅ የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ የዓድዋ ጅግኖች የዘመቻቸው መነሻ እንዲሁም ከድል በኋላ ተሰባስበው ደስታቸውን የተጋሩበት ታሪካዊ ስፍራ ነው። የአድዋ ድል በዓል 7ኛ ዓመት ዳግማዊ ምኒልክ፣ ከአርበኞች፣ ከየአካባቢው ገዢዎች፣ ከውጭ አገር ዲፕሎማቶችና ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር በደማቅ ሁኔታ በዚሁ ስፍራ አክብረውታል። ስፍራው ዛሬ የታላቁ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሳይገነባበት በፊት በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ የልማት ስራዎች ቢታጭም ውጤታማ ስራ ሳይሰራበት ቆይቷል። አካባቢው ለረጅም ዘመናት ታጥሮ ሳይለማ በመቆየቱ እጅግ የቆሸሸ፣ ሰዎች ለዝርፊያ የሚዳረጉበት ስፍራ ሆኖ ቆይቷል። ዘመናትን ተሻግሮ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በከተማዋ ከሚገነቡ ትላልቅ ፕሮጀክቶች በዓይነቱ ልዩ የሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እንዲሰራበት ተደረገ። የዓድዋ ድል መታሰቢያ እጅግ በሚስብ ኪነ ህንፃ፤ የኢትዮጵያውያንን ህያው የድል ታሪክ የሚዘክር ሆኖ ተሰርቷል።   የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የኢትዮጵያውያን የድል ብስራት፣ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ኩራት የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የራሳቸው የሆነ ስያሜ ተሰጥቷቸዋል። የምሥራቅ ጀግኖች በር፣ የምዕራብ ጀግኖች በር፣ የሰሜን ጀግኖች በር፣ የደቡብ ጀግኖች በር፣ የፈረሰኞች በር፣ የአርበኞች በር፣ የፓን አፍሪካኒዝም በር ተብለው የተሰየሙ ናቸው። በአራቱም አቅጣጫዎች የተሰየሙ በሮች ተምሳሌትነት በዓድዋ ድል ከአራቱም አቅጣጫ ኢትዮጵያውያን በጋራ የተሳተፉበት የጋራ ድላቸው መሆኑን ያመለክታል፡፡   መታሰቢያው በውስጡ ምን ይዟል? በዋናው መግቢያ:- የኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን ነጻነት ድል መገለጫ የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ ሃውልትና የሁሉም ከተሞች ርቀት ልኬት መነሻ የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ምልክት ይገኛል። የዓድዋ ጦርነት ዘመቻን ያስተባበሩትና የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት የዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና የባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሀውልትም በዚሁ መግቢያ በኩል ይገኛል። ሃውልት የቆመላቸው 12 የጦር መሪዎች:- በመታሰቢያው የአድዋን ጦርነት በታላቅ ጀግንነት በመምራት ለጥቁር ህዝቦች ድል ያበሰሩ 12 ዋና ዋና የጦር መሪዎች ሃውልት ተቀምጧል፣ እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ ( አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ ( አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። በስተቀኝ በኩል፤- እስከ 3 ሺ እንግዶችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት የስብሰባ አዳራሽ የሚገኝ ሲሆን በመጀመሪያው ኮሪደር ላይ ደግሞ ህዝቡ የጦርነት ክተት አዋጅ ጥሪ ሲሰማ ሁሉም ልዩነቱን ወደ ጎን በመተው አገሩን ከወራሪ ለመታደግ በመወኔ መነሳቱን፣ ወደ ጦር ግንባር መትመሙን እንዲሁም በጀግንነት መፋለሙን የሚሳየዩ ትዕይንቶች በእስክሪኖች ይታያሉ። በክፍሉ መሐል ላይ፤- ጦርነቱ የተጎሰመበት ግዙፍ ነጋሪት የተቀመጠ ሲሆን በነጋሪቱ ግራና ቀኝ ለጦርነቱ መንስኤ የሆነው የውጫሌው ውል አንቀጽ 17፣ የአድዋ ታሪክ እንዲሁም ከድል ወደ ሰላም የሚለው የአዲስ አበባ ስምምነት ሰነድ ተዘርግቶ ይገኛል። ከድል መልስ ግልጋሎት ላይ የዋሉ ጋሻዎች፣ መሳሪያዎች፣ አልባሳት፣ መመገቢያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ በርካታ ቅርሶች፣ ስዕሎች፣ ፎቶዎች ይገኛሉ። ወደ ውስጥ መግቢያ በሆነው በምዕራብ በር ላይ የወቅቱ የኢትዮጵያ መሪ የነበሩት አጼ ሚኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሃውልት በክብር ተቀምጦ ይገኛል። በአድዋ ጦርነት ወቅት ጠላት ለመጠጥነት ይጠቀምበት የነበረውን የምንጭ ውሃ እቴጌ ጣይቱ ብልሃት በተሞላበት መልኩ በኢትዮጵያ ሰራዊት እንዲከበብና ጠላት በውሃ ጥም እንዲዳከም በማድረግ ማሸነፍ የተቻለበት የጦር እስትራቴጂ የሚዘክር ገንዳ ከእቴጌ ጣይቱ ሃውልት ፊት ለፊት ተቀምጦ ይገኛል። የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፤- ጦርነቱ የተካሄደበትን ቦታ የሚያሳየው የአሸዋ ገበታ ሌላው የአድዋ ድል መታሰቢያ ውበትም ታሪክም ነው፡፡ የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፣ መልከዓ-ምድር የሚሳየው የመሬት ላይ ንድፍ ስራ በዚሁ መታሰቢያ መቀመጡ ኢትዮጵያውያን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለነጻነት የከፈሉትን መስዋትነት ያመላክታል። ከተራሮች አጠገብ በጦርነት ወቅት ጥቅም ላይ ከዋሉ ጣሊያናዊ ስሪት የሆነ "ቶሪኖ 1883" የሚል ጽሁፍ ያለበት መድፍ ይገኛል። በጦርነቱ ተዋጊዎችን ያጓጓዙ 45 ሺህ ፈረሰኞች የሰሩትን ጀብድ ሊወክልና ሊዘክራቸው የሚችል ‘የአድዋ ፈረሰኞች የድል ሀውልት’ ቆሞላቸዋል፡፡ የአድዋ ጀግኖች ኢትዮጵያን ከወራሪው ጣሊያን ለማዳን ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት ሳይለዩ በአንድነት ተሰባስበው የተመሙበትን የሚወክል ‘የአንድነት ድልድይ’ በሚል ተሰርቷል፡፡ የሁሉንም ተሳትፎ የሚያሳዩ የተለያዩ ሁነቶች በጦርነቱ ወቅት ህዝብና አገርን በታማኝነት ሲያስተዳድሩ የነበሩ እንደራሴዎች የሚያሳይ ስዕላዊ በመታሰቢያ የተቀመጠ ሲሆን በጦርነቱ ወቅት የነበረውን የህዝቡን እንቅስቃሴ የሚገልጹ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና የመገልገያ ቁሳቁሶች፣ ስዕሎችና ቅርጾችም ይገኛሉ።   የገበሬዎችና ሴቶች ተሳትፎ የሚያሳዩ ስራዎች በአድዋ ጦርነት ከ120 ሺህ በላይ ገበሬዎች የግብርና ስራቸውን አቋርጠው "አገራችን ተነካች" በማለት ታጥቀው ድል ያጎናጸፉ፣ ለጥቁር ህዝቦች ትልቅ ታሪክ ያስቀመጡ ጀግኖች ናቸው። በዚህ መታሰቢያ የአንድነት ማዕከል፣ የአፍሪካ ነጻነት ማስታወሻ የኢትዮጵያ ጀግኖችን ጉዞ የሚያሳዩ ምስሎች ይገኛሉ። በጦርነት ወቅት ሴቶች የቤት ሃላፊነትን ከመወጣት በተጨማሪ በአዋጊነት፣ በመረጃ ሰጪነት ቁስለኞችን በመንከባከብ ለሰሩት ስራ የተሰየመ ማስታወሻም በአድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀምጦ ይገኛል። የአሁኑ ትውልድ አሻራ፣- የኢትዮጵያ ልጆች በአንድነት ተባብረው አፍሪካ በራሷ አቅም መልማት እንደምትችል ያሳዩበት፣ አፍሪካዊ ተምሳሌት የሆነው የህዳሴ ግድብ ፏፏቴ በመታሰቢያው ይገኛል። ኢትዮጵያውያን ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት ላደረጉት ተጋድሎ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የፓን-አፍሪካ ሃውልትም ተካቷል።   ሌሎችም የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋን ጦርነት ሁነቶች ብቻ ሳይሆን ለተለያያዩ ዝግጅቶች የሚሆኑ አዳራሾችን፣ ካፍቴሪያዎችን፣ ሲኒማ ቤቶችንና ሌሎች ለበርካታ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎችንን አካቶ የተሰራ ነው። ከ2500 በላይ እንግዶችን መያዝ የሚችል ፓን አፍሪካን አዳራሽ፣ 300 ሰዎች የሚይዝ የአድዋ አዳራሽ፣ 160 ሰዎች የሚይዝ መካከለኛ አዳራሽ፣ 300 ሰው በአንድ የሚያስተናግዱ ሬስቶራንቶች፣ ሁለት ካፍቴሪያዎችና የህጻናት ሙዚየም በውስጡ አካቷል። በሌላ በኩል በአንድ ጊዜ 1000 ተሽከርካሪ መያዝ የሚችሉ ፓርኪንግ፣ ዘመናዊ ጂምና ሌሎችም ተካተዋል። የአድዋ ድል መታሰቢያ አድዋ ጊዜ የማይሽረው፣ ዘመን የማይለውጠው የጀግንነትና የአንድነት ምልክት መሆኑን ማሳያ፣ ለነጻነት የታገሉና የተሰዉ ጀግኖች የሚታሰቡበት የታሪክ ማስታወሻ ነው። የአድዋ ድል ትሩፋቶችን ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝብ በየትውልዱ ለማስተማር የሚያግዝ የዘመናት የነጻነት መንፈስን የሚያስተጋባ፣ ለመጪው ትውልድ የሚሻገር እውነት ነው። እናም የአድዋ ድል መታሰቢያ የወል ታሪካችንን የምንገነባበት የማዕዘን ድንጋይ ነው።  
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች
Mar 1, 2024 2439
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች በአየለ ያረጋል "... መጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል..." ይህን ያሉት ታላቁ ምሁር እና የአድዋ ዘማች ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማርያም ናቸው። በርግጥ በአድዋ ዘመቻ ያልዘመተ የለም። የሀይማኖት መሪዎች፣ ንጉሱ፣ ንግስቲቱ፣ ገበሬው፣ አገሬው ከነማንነቱ… ገድል ፈጽሟል። በጦር ሜዳ ገድሎች የሴቶች አበርከቶ እምብዛም አይታወስም። ሴቶች የዋሉበት ግንባር አይዘከርም። ቅሉ ሴቶች በኪነ-አድዋ ያልተዘመረላቸው ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው። እቴጌ ጣይቱን መሰል የአድዋ ሴት የጦር ፊታውራሪዎች አሉ። አዝማሪ ጣዲቄና መሰል አዝማሪዎች የሰራዊቱ ስነ ልቦና ገንቢዎች ናችው። ሴቶች የሎጂስቲክስ አሳላጮች፣ የቁስለኛ ሀኪሞች፣ የጀግና አበርቺዎች፣ የስንቅ ሰናቂዎች፣….በጥቅሉ ሴቶች የአድዋ ድል ሁለንተናዎች ነበሩ። ለዚህ ደግሞ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ቀዳሚ ምስክር ናቸው። እቴጌ ጣይቱ ከውጫሌ እስከ መቀሌ፣ ከእንጦጦ እስከ ማርያም ሸዊቶ መላ መቺም፣ ጦር አዝማችም ነበሩ። የዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዜና መዕዋል ከታቢ ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ ወልደአረጋይ ‘ታሪከ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ’ በተሰኘው መጽሐፋቸው የሴቶችን ሚና በተመለከተ እንዲህ ይላሉ። “እንዲህም እየሆነ፣ አጤ ምኒልክ ባዳራሹ እቴጌ ጣይቱ በእልፍኝ ባለሟሎችን ወይዛዝርቱን ይዘው ግብሩ አንድ ቀን ሳይጎድል፣ ይዘምታሉ። ከዘመቻ ላይ ጠጁ ማሩ አለመጉደሉ፣ ስለምንድነው ያልህ እንደሆነ ይህን ታሪክ መመልከት ነው። በስድስት ድንኳን እንጀራው ሲጋገር ሲያድር፣ በአራት ድንኳን ወጡ ሲሠራ ሲያድር፣ ጠጁ በቀንድ በኮዳ ደግሞ ሦስት መቶ ስድስት መቶ የሚሆን ገንቦኛ ሲጓዝ ግብሩ ይጎድል ይመስልሀል” (ገጽ-241) ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ይቀጥላሉ። “… ጥቂቱን ጻፍን እንጅ በአድዋ ጦርነት ዐይናቸን እንዳየው ጆሯችን እንደሰማው መጻፍ አይቻለንም። እቴጌ በዚያን ጊዜ በግምባርዎ ተደፍተው በጉልበትም ተንበርክከው ድንጋይ ተሸክመው እግዚአብሄር እያመለከቱ ሲያዝኑ ሲጨነቁ ነበር። … ሴት ወይዛዝርቱም የንጉሠ ነገሥቱ ልጅ ወይዘሮ ዘውዲቱም ደንገጡሮችንም ተከትለው ነበር። የኋላው ሰልፈኛ እንደመወዝወዝ ሲል ባዩ ጊዜ ቃልዎን አፈፍ አድርገው ተናገሩ። አይዞህ አንተ ምን ሆነሃል! ድሉ የኛ ነው በለው! አሉት… ጣሊያ ድል ከሆነ በኋላ ወንዱ በርኮር፣ ሴቱ በገንቦ ውሃ ያዙ ብለው አዘው ለተጠማውና ለቆሰለው ውሃ ሲያጠቱት ዋሉ። እንኳን ኢትዮጵያ ሰው የኢጣሊያው ስንኳ ቁስለኛ ከዚያ ስፍራ የተገኘ ከዚህ ከእቴጌ ካዘዙት ውሃ አልቀረበትም“ይላሉ። ከጽሁፉ መረዳት እንደሚቻለው እቴጌ ጣይቱና መሰሎቻቸው አንድም በጸሎታቸው፣ አንድም ተዋጊዎችን በማደፋፈር ወኔያቸው፣ አንድም በጦር መሪነት ሚናቸውን ተወጥተዋል። ዋናው ደግሞ ቁስለኞችን የማከምና ሰብዓዊነት ሙያቸው ነው። ፀሃፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ “… ሙሉ ግብር እየበላ የተጓዘ እንጂ ወታደር የስንቅ አቁማዳዉን አልፈታም“ ሲሉ የአድዋ ሴቶች ገድል ምንኛ ገናና እንደሆነ መገመት እንደሚቻል ይጠቅሳሉ። እንደ ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ስለዘመቻው አጓኳን በማስታወሻቸው እንደገለጡት ድንኳን ተካይ፤ ዕንጨት አቅራቢው፣ ወጥ ሰሪው፣ እንጀራ ጋጋሪው፣ እህል ውሃ ተሸካሚው፣ መልከኛው (አራጁ)፣ በቅሎ ጫኙ፤ ተዋጊው ሁሉም በየፊናው እንስሳቱም ሳይቀር ተደራጅቶ ዘምቷል። በርካታ የታሪክ ምንጮች የአድዋ ጦርነት ተሳታፊዎች ገሚሶቹ ሴቶች እንደሆኑ ይገልጻሉ። የታሪክ ምሁሩ ዶክተር አልማው ክፍሌ ደግሞ በአንድ ወቅት ሚዲያ ላይ ቀርበው “በአድዋ ጦርነት ዘማቾች 75 በመቶ ሴቶች ነበሩ” ብለው ነበር። በአድዋ ጦርነት ሴቶች በተለያዩ ሙያዎች ተመድበው ከካምፕ እስከ ጦር ሜዳ ከመመገብ እስከ ማጀገን፣ ከማከም እስከ መዋጋት ድንቅ ሚና ተወጥተዋል። ድርብ ድርብርብ ኃላፊነት ይዘው የዘመቱ፣ ለወንዶችም ልብ፣ ሞራልና ወኔ አቀባዮች ነበሩ። ደራሲ በዕውቀቱ ሥዩም ‘ከአሜን ባሻገር’ በተሰኘ መጽሐፉ ‘ሴቶች በዋሉበት’ በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሴቶች ተጋድሎና ሚና “ከቁስ ባሻገር ከልብ ያቀርባሉ” ይላቸዋል። “ሴቶች ባዋላጅነት ከነበራቸው የማይተናነስ ሚና በጦር ሜዳ ተጫውተዋል። እናቶቻችን በጦር ወቅት፣ መሳሪያ ያቀርቡ ነበር። ምግብ ያቀርቡ ነበር። ሃሳብ ያቀርቡ ነበር። ልብ ያቀርቡ ነበር። ደስታ ያቀርቡ ነበር። ኧረ ምኑ ቅጡ። ሴቶች ባንድ በሙቀጫ ዙሪያ፣ ማኅበረሰቡን ኬሚስት፣ ገጣሚና የፖለቲካ ተንታኝ ሆነው ማገልገላቸውን ልብ እንበል” ይላል። (ገጽ-138) የራስ መኮንን ባለሟል የነበሩት ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማሪያም ገና በ15 ዓመት ዕድሜያቸው አድዋ ዘማች ነበሩ። "የሕይወቴ ታሪክ’ (ኦውቶባዮግራፊ) በተሰኘው ግለ ታሪካቸው ከሐረር እስከ አድዋ በዘለቀው ጉዟቸው ሴቷ (አገልጋያቸው) የነበራትን ሚና ለማብራራት ቃላት ያጥርባቸውና እንዲህ ብለው የአንባቢን ህሊና ይነካሉ። “… ከቶ እሷ ባትኖር ኖሮ እንዴት እሆን ኖሯል! እያልኩ ዘወትር ሳስበው ያደንቀኛል። ዕቃ ተሸክማ ስትሄድ ትውላለች። ከሰፈርን በኋል ውሃ ቀድታ፣ እንጨት ለቅማ፣ ቂጣ ጋግራ፣ ወጥ ሰርታ፣ ታበላናለች። ወዲያውኑ እንዲዚህ ለማታ ታሰናዳለች። እንደዚህ የወለተ አማኑኤልን አገልግሎት እያሰብኩ ስደነቅ ደግሞ በየሰፈሩ እንደርሷ ስንት ሴቶች እንደሚያገለግሉ ይታሰበኛል። የሴቶቹን አገልግሎት ስገምት ደግሞ የበቅሎዎች አገልግሎት ይታወሰኛል። በመጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል። ሁሉንም አያይዥ በደምሳሳው ስመለከተው የኢትዮጵያን መንግስት ነጻነቱን ጠብቀው፤ እዚህ አሁን የደረስንበት ኑሮ ያደረሱት እነዚህ የዘመቻ ሃይሎች መሆናቸውን አልስተውም። የኢትዮጰያ መንግስት የተባለው ተቋም፣ ላገልጋዮቹ ውለታ ምላሽ ሆኗል ወይ? የዚህን ምላሽ ለመስጠት ሳስበው እልቅ የሌለው መንገድ ይገጥመኛል። ሲሄዱ መኖር ይሆንብኛል። የማልዘልቀው እየሆነብኝ፣ እየተከዝኩ እተወዋለሁ” በማለት በቁጭት ጽፈዋል። በርግጥም ሴቶች በኪነ-አድዋ በልካቸው ያልተዘመረላቸው፣ ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው።  
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 11735
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16124
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 8314
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል።   “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል።   ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 9337
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 25989
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 21751
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16124
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 12274
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 11735
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 11156
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 10919
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
ተመድ በሶሪያ በርዕደ መሬት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረበ
Feb 15, 2023 10465
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 8/2015 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በሶሪያና ቱርክ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ ሶሪያውያንን ለማገዝ የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረቡ። ዋና ጸሓፊው ጥሪውን ያቀረቡት ባሳለፍነው ሳምንት በቱርክና በሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሶሪያውያንን ለማገዝ ነው። በኒውዮርክ በሰጡት መግለጫ ሶሪያውያኑን ለማገዝ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ለሶስት ወራት ጊዜ ብቻ የሚበቃ መሆኑን ጠቅሰው የሚመለከታቸው ሁሉ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። ከአደጋው በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አስቸኳይ ድጋፍ ማቅረቡን ገልጸው ተጨማሪ እገዛዎች አሁንም እንደሚያስፈልጉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በድርጅቱ ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትና አጋር አካላት በጋራ በሚያቀርቡት ገንዘብ፤ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሶሪያውያን የመጠለያ፣ የጤና፣ የምግብ እንዲሁም ሌሎች አስቸኳይ ድጋፎች እንደሚደረጉ አብራርተዋል። ተመሳሳይ የድጋፍ ማዕቀፍ በቱርክ ድንበር ለሚገኙ ዜጎች እየተጠናቀቀ እንደሚገኝም ዋና ጸሓፊው ተናግረዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 25989
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 21751
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16124
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 12274
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
መጣጥፍ
በድላችን ሐውልት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት የተቀረጸላቸው የካራማራው ዘማች አቶ በቀለ ገመቹ 
Mar 5, 2024 3682
አቶ በቀለ ገመቹ ወይም በቅፅል ስማቸው አሚኮ ይባላሉ፤ በሙያቸው ኤሌክትሪሺያን ናቸው። በ1969 ዓ.ም በዚያድባሬ የሚመራው የሶማሊያ አገዛዝ ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ሀገር ስትደፈር ቁጭት ተሰምቷቸው ወደ ጦር ሜዳ መዝመታቸውን ይናገራሉ። ጦር ሜዳ ከመዝመታቸው ባሻገር የኤሌክትሪክ ባለሙያ በመሆናቸው "በራ በራ የድል ጮራ" የተሰኘውን ዓርማ በመቅረጽ በ14ቱ ክፍላተ ሀገር እንዲበራ ማድረጋቸውንም ያነሳሉ። በዚህም ከወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እና ከኩባው ፕሬዝዳንት ፊደል ካስትሮ መሸለማችውን ያወሳሉ። ታንክ ማራኪው አሊ በርኬ ጓደኛቸው እንደሆኑ የሚናገሩት አቶ በቀለ፤ በተለያዩ ዐውደ ግንባሮች መሳተፋቸውን አስታውሰዋል። አቶ በቀለ ጥቁር አንበሳ በሚገኘው የኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ፓርክ በሚገኘው የድላችን ሐውልት ላይ ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት ተቀርጾላቸዋል። ሐውልት እንዲቀረጽ የተደረገበት ፎቶግራፍ በያኔው ሶስተኛው አንበሳው ክፍለ ጦር በኋለኛው ምሰራቅ ዕዝ በር ላይ በቀኝ እጃቸው መሳሪያ ከፍ አድርገው ይዘው የተነሱት ፎቶ ግራፍ እንደሆነ ገልጸው፤ በዚህም ደስተኛ እንደሆኑ ይናገራሉ። ከእርሳቸው ጎንም መንበረ የምትባል ሌላ ኢትዮጵያዊ ዘማችና መትረጊስ ተኳሽ ሴት ባደረገችው አስተዋፅኦና በደረሰባት አካል ጉዳት ሐውልት እንደተቀረጸላት ያነሳሉ። የካራማራ ድል ታላቅ ድል ነው የሚሉት አቶ በቀለ ገመቹ፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት ከፍለውበት የተገኘና ሀገርን ያስከበረ መሆኑንም ይገልጻሉ። የካራማራ ዘማቹ አቶ በቀለ ገመቹ አሁናዊ ኑሯቸው ችግር ላይ እንደሚገኙና ድጋፍ እንደሚሹም ተናግረዋል። ሶማሊያን ለ21 ዓመታት ያስተዳደሩት ዚያድባሬ 'ታላቋን የሶማሊያ ሪፐብሊክ ለመመስረት' በሚል "ድንበራችን እስከ አዋሽ ይደርሳል" እያሉ በመዛት የጦርነት ነጋሪት መጎሰማቸው የሚታወስ ነው። ይሄን እውን ለማድረግ በ1969 በኢትዮጵያ ላይ ግልጽ ወረራ ፈጸሙ። የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጦር የእብሪተኛውን የዚያድባሬ ጦር ካራ ማራ ላይ ድል አደረገ፤ የኢትዮጵያ አሸናፊነትም በአደባባይ ታወጀ። ድሉ በየዓመቱ የካቲት 26 ቀን የሚታሰብ ሲሆን ዘንድሮም 46ኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል።    
የአፍሪካ ዋንጫን በመሀል ዳኝነት  የመራችው ብቸኛዋ ሴት ዳኛ
Jan 28, 2024 3502
  በይስሐቅ ቀለመወርቅ እንደ መነሻ፡- በእግር ኳስ ውድድሮች የመሃል ዳኝነቱን ቦታ በብዛት የሚይዙት ወንዶች ሲሆኑ፤ አሁን ላይ አልፎ አልፎ ሴቶች ትልልቅ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ሲዳኙ አስተውለናል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 በኳታር አስተናጋጅነት በተከናወነው 22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ፤ ፈረንሳዊቷ ስቴፋኒ ፍራፓርት፤ ኮስታሪካ እና ጀርመን ያደረጉትን ጨዋታ በመሀል ዳኛነት መርታለች። በዚህም በወንዶች ዓለም ዋንጫ ታሪክ በመሀል ዳኝነት የእግር ኳስ ጨዋታን የመራች የመጀመሪያዋ ሴት በመሆን ታሪክ ሰርታለች ። ዘንድሮ ደግሞ በኮትዲቯር አስተናጋጅነት እየተከናወነ በሚገኘው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ሞሮኳዊቷ ቦችራ ካርቡቢ፤ ውድድሩን እንዲመሩ ከተመረጡት 32 የመሀል ዳኞች መካከል ብቸኛዋ ሴት ናት። በዚህም በውድድሩ በጊኒ ቢሳውና በናይጄሪያ መካከል የተከናወነውን ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ፤ በመሀል ዳኝት በመምራት፤ ታሪክ ጽፋለች። የሞሮኮ ዓለም አቀፍ ማኅበር የእግር ኳስ ዳኛ የሆነችው ቦችራ ካርቡቢ፤ በወንዶችም ሆነ በሴቶች አህጉራዊ የእግር ኳስ ውድድሮች ላይ በርካታ የመጨረሻ ምዕራፍ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ዳኝታለች። 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫን ብቸኛ የሴት ዳኛ ሆና የመራችው ቦችራ ካርቡቢ ማናት? ቦችራ ካርቡቢ በሞሮኮ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው "ታዛ" ከተማ፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1987 ተወለደች። የዘር ግንዷ በሰሜን ምሥራቅ ሞሮኮ ከሚገኙት ሪፊያን ከሚባሉት የበርበር ጎሳ ዝርያ ካላቸው ሕዝቦች የሚመዘዝ ሲሆን፤ ለቤተሰቦቿ አምስተኛና የመጨረሻ ልጅ ነች። ገና በልጅነቷ ለእግር ኳስ ፍቅር ያደረባት ቦችራ ካርቡቢ፤ ኳስ መጫወት የጀመረችው በአንድ ትንሽ የወጣቶች ቡድን ውስጥ ነበር። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2001 በተወለደችበት ከተማ "ታዛ"፤ ለወንዶችና ለሴቶች የእግር ኳስ ዳኝነት ሥልጠና የሚሰጥበት ትምህርት ቤት ተከፈተ ። ይኼ ትምህርት ቤት ቀልቧን የሳበው ቦችራ፤ ሥልጠናውን መውሰድ ጀመረች። "እግር ኳስን እወዳለሁ፤ ራሴንም ላስተምር ፈለኩ።ለምን አላደርገውም ብዬ ፍላጎቴን በመከተል የእግር ኳስ ጨዋታን ደንብ መማር ጀመርኩ" ስትል የእግር ኳስ ዳኝነት ትምህርት የጀመረችበትን ጊዜ ታስታውሳለች። ይኼ ድርጊቷ ካልተዋጠላቸውና፤ በበጎ ጎኑ ካልተመለከቱት ውስጥ ደግሞ፤ ወንድሞቿ ቀዳሚዎች ነበሩ። "በምኖርበት ከተማ አንድ ሴት አጭር ቁምጣ ለብሳ ከወንዶች ጋር ሥልጠና ስትወስድ መታየቷ፤ እንደ አሳፋሪ ድርጊት ስለሚታይ መነጋገሪያ ሆኜ ነበር" ትላለች። የቦችራ ካርቡቢ የዳኝነት ጉዞ እንደ አውሮፓውያን ቆጣጠር በ2007፤ ሞሮኮ ብሔራዊ የሴቶች እግር ኳስ ሻምፒዮናን ጀመረች። ይህ መሆኑ ቡችራ ካርቡቢ ብሔራዊ ዳኛ እንድትሆን ዕድል የፈጠረላት ሲሆን፤ መኖሪያዋንም ከትውልድ ሥፍራዋ "ታዛ" ወደ ሞሮኮ ሌላኛዋ ከተማ "ሚከንስ" እንድትቀይር አደረጋት። "ይህን ዕድል ማግኘቴ ቤተሰቦቼ እንዲረዱኝና ሙያዊ ለሆነ ጉዳይ እንደምሄድ እንዲያምኑ አድርጓቸዋል" በማለት የዳኝነት ሙያዋን በመጨረሻ እንደተቀበሉት ታስረዳለች። በሚከንስ ከተማ በእግር ኳስ ዳኝነት ሥልጠና ላይ እያለች፤ አንድ ቀን አባቷ መጥቶ እንደተመለከታትና፤ ወንድሞቿ ምርጫዋን ሊያከብሩላት እንደሚገባ እንደነገራቸውም ገልፃለች። የ19 ዓመት ወጣት እያለችም፤ በሞሮኮ የሴቶች አንደኛ እና ሁለተኛ የሊግ ውድድር በመዳኘት፤ የዳኝነት ሥራዋን አንድ ብላ ጀመረች። ይህ ከሆነ ከ10 ዓመት በኋላ፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2016 ደግሞ፤ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ዳኛ በመሆን ራሷን ወደ ሌላ ምዕራፍ አሸጋገረች። ከሁለት ዓመት በኋላም በ2018 በጋና አስተናጋጅነት በተከናወነው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ፤ በዛምቢያና በኢኳቶሪያል ጊኒ መካከል የተደረገውን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት አጫወተች። ይህም በአህጉራዊ የውድድር መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመሀል ዳኝነት ያጫወተችው ጨዋታ ሆኖ ተመዘገበላት። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2020፤ "ቦቶላ" እየተባለ በሚጠራው በሞሮኮ የወንዶች ከፍተኛ የሊግ ውድድር ላይ በመሀል ዳኝነት በመዳኘት፤ የመጀመሪያዋ ሴት ሆነች ። ከአንድ ዓመት በኋላም በካሜሮን አስተናጋጅነት በተከናወነው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ፤ ሴኔጋልና ግብፅ ባደረጉት የፍፃሜ ጨዋታ የቫር ዳኛ (video assistant referee) በመሆን ሰርታለች። ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊትም የሞሮኮ የንጉሱ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታን በመዳኘትም ቀዳሚዋ ሴት ናት። አሁን ላይ እየተከናወነ ባለው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ወድድርም፤ በጊኒ ቢሳውና በናይጄሪያ መካከል የተከናወነውን ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ በመሀል ዳኝት በመምራት፤ የመጀመሪያዋ ሰሜን አፍሪካዊት የአረብ ሴት ሆናለች። ቡችራ ካርቡቢ ከእግር ኳስ ዳኝነት ሥራዋ በተጨማሪ፤ የፖሊስ ኦፊሰር በመሆን ሀገሯን እያገለገለች ትገኛለች።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም