ወላይታ ድቻ በኢትዮጵያ ዋንጫ ወደ ፍጻሜ አለፈ

217

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዋንጫ ዛሬ በተደረገ የመጀመሪያ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ኢትዮጵያ መድንን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለፍጻሜው አለፈ።

በአበበ በቂላ በተካሄደው ጨዋታ የመስመር አጥቂው ብስራት በቀለ በ86ኛው ደቂቃ ላይ ግብ በማስቆጠሩ ወላይታ ድቻን አሸናፊ አድርጓል።

ውጤቱን ተከትሎ ወላይታ ድቻ ለኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ ያለፈ ሲሆን ከሀዋሳ ከተማና ኢትዮጵያ ቡና አሸናፊ ጋር በፍጻሜው ይገናኛል።

ሃዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ነገ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከቀኑ 9 ሰዓት ሁለተኛውን የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም