የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

139

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2016 (ኢዜአ)፡- የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

መስተዳድር ምክር ቤቱ በዋናነትም ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ለኢንቨስትመንት የተዘጋጁ መሬቶችን እንዲሁም በመልሶ ማልማት ከጁገል ዙሪያ ለተነሱ የገበያ ቦታዎች የተዘጋጁ መሬቶችን እና በሸዋበር ታይዋን ተብሎ በሚጠራው የገበያ ስፍራ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ አግባብነት ላላቸው አካላት የተዘጋጁ የመሬት ጥያቄ ላይ በስፋት ተወያይቶ አጽድቋል።

ለኢንቨስተሮች የመሬት ምደባ የተደረገላቸው በሚሰማሩበት የልማት መስክም ፋይዳ ያላቸውና ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስለመሆናቸው ተጠቁሟል።


 

መስተዳድር ምክር ቤቱም የተሰጠው መሬት ለተፈለገው ልማት እንዲውል በአፋጣኝ ወደ ስራ እንዲገቡ አቅጣጫ ማስቀመጡን ከሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

መስተዳድር ምክር ቤቱ ከዚህ በተጨማሪም በሌሎች አጀንዳዎች ዙሪያ ውይይት በማካሄድ ውሳኔ አሳልፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም