በሳይንስ ሙዚየም ሲካሄድ የቆየው የስታርትአፕ ኢትዮጵያ አውደ ርዕይ ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ተካሄደ

166

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2016(ኢዜአ)፦ ለሦስት ሳምንታት በሳይንስ ሙዚየም ሲካሄድ የቆየው የስታርትአፕ ኢትዮጵያ አውደ ርዕይ ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡

በማጠቃለያ መርሃ-ግብሩ ላይ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ (ዶ/ር) ባይሳ በዳዳ እና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። 

በአውደ ርዕዩ በቴክኖሎጂ የታገዙ አዳዲስ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ወጣቶች ተሞክሯቸውን በስፋት ለሌሎች ያጋሩበት፣ ጀማሪ ስታርትአፖችን በማስተዋወቅ የተሻለ የፈጠራ ስራዎች እንዲዳብሩ ለማስቻል ምቹ ምህደር የተፈጠረበት መርሃ ግብር እንደነበር በመድረኩ ተገልጿል።

በአውደ ርዕዩ ስራዎቻቸውን ለውድድር ያቀረቡ እና ከአንድ እስከ ሦስት የወጡ ስታርትአፖችን እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በአውደ ርዕዩ 300 የሚደርሱ ስታርታአፖች ለእይታ የበቁበት፤ የተለያዩ የውይይት መድረኮች የተካሄዱበት፤ ዘጠኝ  የሚደርሱ የፖሊሲ የሪፎርም አቅጣጫዎች የተቀመጡበት  መሆኑ ተገልጿል።

በአውደ ርእዩ በግብርና፣ በጤና፣ በኢንዳስትሪ፣ በኢነርጂና ሌሎች ዘርፎች ችግር ፈቺ የሆኑ የፈጠራ ሃሳቦችና ምርቶች ለእይታ የበቁበት ሲሆን ይህም ውጤታማ የስራ ፈጣሪነትን ለመተግበር ምቹ ምህዳር የፈጠረ መሆኑ ተገልጿል።




የስራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፍሪያት ከሚል በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፣ ዛሬ ተሸላሚ የሆኑት የስታርትአፖች የተፈጠረላቸውን ምቹ እድል ተጠቅመው የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግቡ አስገንዝበዋል፡፡

በአውደ ርዕይው የተሳተፉ የስታርትአፕ ስራዎችን ከ16 ሺህ በላይ ሰዎች ጎብኝተውታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም