አርእስተ ዜና
ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሃገራት ኢኮኖሚያዊ ትስስር ከፍተኛ ሚና ትጫወታለች - አቶ አሕመድ ሽዴ
May 1, 2024 41
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 23/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በቀጣናው ሃገራት ደህንነትና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ዙሪያ ቁልፍ ሚና ትጫወታለች ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ገለጹ። አቶ አሕመድ በሳኡዲ አረቢያ ሪያድ በተደረገ የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም መድረክ ላይ በነበራቸው ተሳትፎ እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ እያደገ የመጣውን ፈተና ለመቋቋም የደቡብ ደቡብ ትብብር ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። ኢትዮጵያ የቀጣናውን ሃገራት በማስተሳሰር ቁልፍ ሚና እንዳላት የገለጹት ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ከቀረው ዓለም ጋር በማገናኘት ረገድ የአንበሳውን ድርሻ እንደሚይዝም አስረድተዋል። እኛ ለቀጣናው ሃገራት ኢኮኖሚያዊ ትስስርና መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረግን ነው ያሉት ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እና በአረቡ ዓለም ግንኙተን ላይም ጉልህ ሚና እንዳላት ገልጸዋል። ዓለም እየገጠሟት ያሉትን የተለያዩ ፈተናዎች ለመቋቋምም የደቡብ ደቡብ ትብብር ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ ከዓባል ሃገራት ጋር ያላትን ኤኮኖሚያዊ ትስስር እንደሚያጠናክርላትም ነው አቶ አሕመድ ሽዴ የተናገሩት። ኢትዮጵያ የአፍሪከ ህብረትን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ማዕከል መሆኗን በውይይቱ ላይ ያነሱት አቶ አሕመድ ይህም በቀጣናው እና በአህጉሩ ያላት ሚና ከፍ ያለ እንዲሆን ማድረጉን ጠቁመዋል። የብሪክስ አባል ሃገራት በኢኮኖሚ በኢንቨስትመንት በቴክኖሎጂና በአቅም ግንባታ ረገድ በትብብር መስራት የሚችሉበት ሁኔታም ሰፊ መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ በየጊዜው ያለአግባብ የሚወገዱ የፕላስቲክ ምርቶች በሰውና እንስሳት ጤና ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት የማስቀረት ተግባር ይጠናከራል
May 1, 2024 65
ጅግጅጋ ፣ሚያዚያ 23/2016 (ኢዜአ)፡- በሶማሌ ክልል በየጊዜው ያለአግባብ የሚወገዱ የፕላስቲክ ምርቶች በሰውና እንስሳት ጤና ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት ለማስቀረት ቅንጅታዊ ስራን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተመለከተ። በሶማሌ ክልል በየጊዜው ያለ አግባብ የሚወገዱ የፕላስቲክ ምርቶች በአርብቶ አደሩ የቤት እንስሳት ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት፣ የአካባቢ መጎሳቆል እና የአፈር ለምነት ማሳጣት የሚያስከትለው ጉዳት የሚዳሰስ ፓናል ውይይት በጅግጅጋ ከተማ ዛሬ ተካሂዷል።   በክልሉ የአካባቢ ጥበቃና ገጠር መሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ሙህየዲን አብዲ፤ በክልሉ ለስድስት ወር የሚቆይ የአፈር፣ የአየር፣ የውሃ ብክለትንና የድምፅ ሁከትን ለመከላከልና ለመቀነስ የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወነ ናቸው። በክልሉ በተቀመጠው እቅድ መሰረት ፕላስቲክ የሚያደርስውን ብክለት ለመከላከል በክልሉ አምስት ከተሞች ህብረተሰብን ያሳተፈ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መካሄዳቸውን ተናግረዋል። "በጅግጅጋ የተዘጋጀው ውይይትም ፕላስቲክ ምርቶች የአርብቶ አደሩ ህብረተሰብ የኢኮኖሚ መሰረት የሆነውን የቤት እንስሳት ከጉዳት ለመታደግ ያለመ ነው" ብለዋል። የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር በየቀኑ ከሚወገደው የደረቅ ቆሻሻ መካከል አብዛኛው ያለ አግባብ የሚጣሉት ፌስታሎች እና ሌሎች የፕላስቲክ ምርቶች መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጂነር ሻፊ አህመድ ናቸው። በከተማው በየቀኑ ከሁለት ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የፕላስቲክ ውጤቶች እንደሚወገዱ ተናግረዋል ። ከመኖሪያ ቤቶችና ከንግድ ተቋማት በተለያየ መልኩ ጥቅም ላይ ውለው ያለ አግባብ የሚጣሉ የፕላስቲክ ምርቶች በከተማው የጎርፍ መውረጃ ቱቦ በመዝጋትና የአካባቢውን ውበት በማጥፋት የሚያደርሱት ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል። "በክልሉ ከተሞች ያለ አግባብ የሚወገዱና በየቦታው የሚጣሉ ፌስታሎችን የተመገቡ ከብቶች ለሞት እየተዳረጉ ነው" ያሉት ደግሞ የክልሉ አርብቶ አደር ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር መሀመድ ገዓል ናቸው።   በቅርቡም በጅግጅጋ እንስሳት በሽታዎች ላብራቶሪ ባለሙያዎች በአንድ ከብት የሆድ እቃ ከፍተኛ መጠን ያለው ፌስታል በቀዶ ህክምና መውጣቱን ለአብነት አንስተዋል። የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መሀመድ አያንሌ በበኩላቸው፤ የፕላስቲክ ውጤቶች በእንስሳትና በሰው ጤና ላይ የሚያስከትሉትን ችግር ለማስወገድ ተቀናጅቶ መስራት ተገቢ መሆኑን አመልክተዋል ።   በመድረኩ ላይ የተገኙት አገር ሽማግሌዎቹ መካከል አቶ አብዲናስር መሀመድ፤ "ከከተሞች የሚወገዱ ቆሻሻዎች የአርብቶ አደሩን እንስሳት በመጎዳት በህብረተሰቡ የጤናና ኢኮኖሚ አደጋ እፈጠሩ ነው" ብለዋል። የችግሩን ስፋት ለአርብቶ አደሩ ለሌላው ህብረተሰብ ለማስገንዘብ እንደሚሰሩም ተናግረዋል ። መድረኩ ላይ የሀይማኖት አባቶች፣ አገር ሽማግሌዎች ፣ የመንግስት ሰራተኞችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።  
ጽዱ አካባቢ የመፍጠርና ብክለትን የመከላከል ሥራ ስኬታማ እንዲሆን ሁሉም ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ
May 1, 2024 46
ሆሳዕና ፣ሚያዚያ 23/2016 (ኢዜአ)፡- ጽዱ አካባቢ የመፍጠርና ብክለትን የመከላከል ሥራ ስኬታማ እንዲሆን የሁሉም ርብርብ አስፈላጊ መሆኑን የኢፌዴሪ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ደንና አካባቢ ጥበቃ ልማት ቢሮ "ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የፅዳት ዘመቻ ዛሬ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል።   የኢፌዴሪ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ለማ በወቅቱ እንዳሉት ጽዱ አካባቢ የመፍጠርና ብክለትን የመከላከል ሥራ የሁሉንም ዜጋ ርብርብ ይጠይቃል። በተለይ በቆሻሻ አወጋገድና አያያዝ ችግር የተነሳ የሚከሰት የአካባቢ ብክለት ምርታማነትን ከመቀነስ ባለፈ በጤና ላይ የሚፈጥረው አሉታዊ ጫና ከባድ መሆኑን አስረድተዋል። በመሆኑም እንደሀገር ችግሩን ለማስቀረት መላውን ህዝብ ያሳተፈ ንቅናቄ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው ንቅናቄው ስኬታማ እንዲሆን ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ብለዋል። ባለስልጣኑ የአካባቢ ብክለት የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ከማስገንዘብ ጀምሮ የተዘጋጁ አዋጆች እንዲተገበሩ እየተጋ መሆኑንም አመልክተዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ኃላፊና የርዕሰ መስተዳድር ተወካይ አቶ ሰማን ሽፋ በበኩላቸው የአካባቢ ብክለት ምርትና ምርታማነትን መቀነስን ጨምሮ የተለያዩ ችግሮችን እንደሚያስከትል ተናግረዋል። በተለይ የምግብ ዋስትናና ጤና አጠባበቅ ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ጫና ከባድ መሆኑን ጠቅሰው ችግሩን በተቀናጀ መንገድ ለመከላከል እንሰራለን ብለዋል። የክልሉ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ከብክለት በመታደግ ጽዱና ለኑሮ ምቹ አካባቢን ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዙም አሳስበዋል። "አካባቢን በአግባቡ ባለመያዝ ምክንያት በሚከሰቱ ችግሮች የተነሳ የሰው ልጆች ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ተግዳሮት ውስጥ ወድቋል" ያሉት ደግሞ የክልሉ ደን አካባቢ ጥበቃ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሃም መጫ ናቸው። ኃላፊው እንዳሉት በክልሉ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል ማህበረሰቡን ያሳተፉ የጽዳት ዘመቻዎችና ከማድረግ ባለፈ ተሳትፎን የሚያጠናክሩ አስገዳጅ መመሪያዎች እየተዘጋጁ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ሁሉም የክልሉ ነዋሪ የፕላስቲክ ውጤቶችና ለአካባቢ ብክለት አስተዋጾ ያላቸውን ቁሶችንና ቆሻሻዎችን በአግባቡ በማስወገድ እንዲሁም የመኖሪያና የሥራ አካባቢዎችን ንጹህ የማድረግ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል። በፅዳት ዘመቻው ከተሳተፉት ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ የሺ አበበ፣ ጽዱ አካባቢን ለመፍጠር በተጀመረው ንቅናቄ ደስተኛ መሆናቸውንና ለስኬቱም የበኩላቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል። የጽዳት ሥራ ከራስ ቤትና አካባቢ ይጀምራል ያሉት ነዋሪዋ፣ ከብክለት የፀዳ አካባቢን መፍጠር ጤናማ ትውልድን ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል። በተለይ ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻዎችን በመለየትና አወጋገዱን በማዘመን ለአካባቢያችን ጽዳት የሚጠበቅብንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል። በጽዳት ዘመቻው ላይ የክልልና የሆሳዕና ከተማ አመራሮች እና ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።  
በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት በጠንካራ መሰረት ላይ ለማኖር አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለጸ
May 1, 2024 48
መቀሌ ፣ሚያዚያ 23/2016 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት በጠንካራ መሰረት ላይ ለማጽናት ሚና እንዳለው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ተወካይ ዶክተር ሄኖክ ስዩም ገለጹ። በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ላይ ያተኮረ ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እና የውይይት መድረክ በመቀሌ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ ዛሬ በተከፈተውና ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ተወካይ ዶክተር ሄኖክ ስዩም እንደገለጹት፤ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ተግባራዊ በማድረግ የአፍሪካን የንግድና የኢኮኖሚ ትብብርን ለማሳደግ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት እና በኢጋድ ስር ሆና የበኩሏን ድርሻ እየተወጣች ነው፡፡ “ስምምነቱ የአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርም እና የ10 ዓመት የስትራቴጂ እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ያግዛል” ያሉት ዶክተር ሄኖከ፤ በተለይም የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት በጠንካራ መሰረት ላይ ለማጽናት ትልቅ ሚና እንዳለው አብራርተዋል። የኢትዮጵያን የወጪ ንግድ ለማሳደግ፣ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና ተወዳዳሪ ምርቶችን ለማቅረብ እንደሚረዳ ጠቁመው፤ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሰምምነቱ የላቀ ድርሻ እንዳለው ነው የተናገሩት፡፡ የአፍሪካ አገሮች የንግድና ኢኮኖሚ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ጠቀሜታ እንዳለው ያመለከቱት ዶክተር ሄኖክ፤ የአህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግ ኢትዮጵያ ጥቅሟን ባስጠበቀ መልኩ እየሰራች መሆኗን ተናግረዋል፡፡ እንደ ዶክተር ሄኖክ ገለጻ፤ የአህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግ በተለያዩ ክልሎችና ከተሞች ብሔራዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እና የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የንግድና ኤክስፖርት ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ገብረመስቀል ታረቀ በበኩላቸው፤ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የትሬድ ማርክ አፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር አቶ አብነት በቀለ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ አፍሪካ ለምታልመው አህጉራዊ ልማትና እድገት ስምምነቱ ቁልፍ ነው። ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሲሆን በአህጉር ደረጃ 30 ሚሊዮን ዜጎችን ከድህነት እንደሚያላቅቅ አመልክተዋል። ትሬድ ማርክ አፍሪካ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በስምምነቱ ዙሪያ ከዚህ በፊት በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በድሬዳዋ፣ በሀዋሳና ጅማ ከተሞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች መስጠቱን ጠቁመዋል። አሁን በመቀሌ ከተማ እየተካሄደ ያለው ስድስተኛው ዙር መሆኑንና በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተዋል፡፡ በመድረኩ በንግድ ዘርፍ የተሰማሩ አካላት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን የመርሃ ግብሩ አስፈጻሚ አካላት እና የንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡  
የሚታይ

የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገቡ ነው - አቶ አደም ፋራህ
May 1, 2024 75
አዲስ አበባ ፤ ሚያዝያ 23/2016(ኢዜአ)፦ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡ የብልጽግና ፓርቲ የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሂዷል፡፡   በዛሬው ዕለትም የኑሮ ውድነትን ከማረጋጋት፣ ከስራ ዕድል ፈጠራ እና የተረጂነት አመለካከትን ከመለወጥ አኳያ በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱም ፓርቲው በሱፐርቪዢን ምልከታ እና በሌሎችም ጊዜያት በተደረጉ የውይይት መድረኮች ከህዝቡ የተነሱ ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ለመመለስ እየሰራ መሆኑ ተጠቁሟል። ለአብነትም የምርት አቅርቦትን ከማሻሻል፣ የኑሮ ውድነትን ከማረጋጋትና የዋጋ ንረትን ከመቆጣጠር አንጻር የተሰሩ ስራዎች አመርቂ ውጤቶች እያስገኙ መሆኑ ተመላክቷል። የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ በዚሁ ወቅት፤ ህዝቡን እየጎዳ የሚገኘውን የኑሮ ውድነት ለመቆጣጠር በመንግሥት እና በፓርቲ በኩል ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። በሀገር ደረጃ በርካታ ኢንሼቲቮች ተቀርጸው ወደ ስራ በመገባቱ ምርትና ምርታማነት እየጨመረ መምጣቱን ጠቁመው የንግድ ሰንሰለቱን በማሳጠር አምራችን ከሸማቹ ለማገናኘት የተሰሩ ስራዎችም ውጤታማ እየሆኑ መምጣታቸውን ገልጸዋል። የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ እየተሰሩ ያሉ ተግባራት ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገቡ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ የተረጂነት አመለካከትን ከመለወጥ አኳያ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የጠቆሙት የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳነት የመስራት አቅም ያላቸው ዜጎች ሰርተው መለወጥ እንዲችሉ ማድረግ ይገባልም ብለዋል። የምግብ ዋስትናን እና የኢኮኖሚ ነጻነትን ማረጋገጥ መቻል የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር ትልቅ አቅም መሆኑንም ጠቁመዋል። የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ባቀረቡት የመወያያ ጽሑፍ ከስራ ዕድል ፈጠራ አንጻር በበጀት ዓመቱ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።   በሀገር ደረጃ እየተተገበሩ የሚገኙ ኢኒሼቲቮች የስራ ዕድል መፍጠሪያ በማድረግ አበረታች ስራዎች መከናወናቸውንም ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ ከስራ ዕድል ፈላጊዎች ቁጥር አንጻር በቀጣይ ጊዜያት ሰፊ ስራዎችን መሰራት እንደሚገባ ጠቁመው ከስራ ዕድል ፈጠራ አንጻር የአመለካከት፣ የክህሎት፣ የግብዓት እና ሌሎች ችግሮችን መፍታት እንደሚገባም ነው የተናገሩት። የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ በበኩላቸው የተረጂነት አመለካከቶችን ማስወገድ እንደሚገባ ተናግረዋል።   ዜጎች በአካባቢያቸው ስርተው እንዲለወጡ የሚያግዙ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመው ይህም በተለያዩ አካባቢዎች እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ፤ አምራቾችን ከሸማቾች ጋር ለማገናኘት በተሰሩ ስራዎች በርካታ የገበያ ማዕከላት ተቋቁመው አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።   በሀገር ደረጃ አሁን ላይ 970 የእሁድ ገበያዎች መቋቋማቸውን ጠቁመው የኑሮ ውድነቱን ከማረጋጋት አንጻር ትልቅ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በውይይቱ ሃሳባቸውን የሰጡት የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ የዋጋ ግሸበትን በመቀነስ የተረጋጋ የኑሮ ሁኔታ እንዲፈጠር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡   ምርታማነትን ማሳደግ እንዲሁም የተመረተውን ምርት በአግባቡ ለገበያ ማቅረብ ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ በመሆኑ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም ተናግረዋል። ሌላው የውይይቱ ተሳታፊ አቶ በላይ ተሰማ በበኩላቸው ከስራ ዕድል ፈጠራ አንጻር የተጀመሩ ውጤታማ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡  
ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ትኩረት በመስጠት ለመጪው ትውልድ የምትመች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ መረባረብ ይገባናል -የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም
May 1, 2024 59
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 23/2016(ኢዜአ)፡- ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ትኩረት በመስጠት ለመጪው ትውልድ የምትመች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በመረባረብ ይገባናል ሲሉ የሰላም ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዷለም ገለጹ። ''ምክር ቤቶቻችን ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ አገር ግንባታ ስኬታችን'' በሚል መሪ ሀሳብ የፌዴራልና የክልል ምክር ቤቶች የስልጠና እና የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።   በሰላም ሚኒስቴር በተዘጋጀው በዚሁ መድረክ ላይ የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላት እንዲሁም የክልልና የከተማ መስተዳደር ምክር ቤቶች አፈ-ጉባኤዎች ታድመዋል። የሰላም ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዷለም በዚሁ ጊዜ እንዳሉት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ብሄራዊ መግባባት በሚፈለገው ልክ መፍጠር ያልተቻለው ሁሉን ነገር ከትላንት ጋር ብቻ በማያያዝ ዛሬና ነገን በአግባቡ መመልከት ባለመቻሉ ነው። ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ አገረ መንግስት ግንባታ ብሄራዊ መግባባት ወሳኝ ጉዳይ ቢሆንም ብሄራዊ መግባባትን ለመፍጠር የተኬደባቸው መንገዶች ትክክለኛ አቅጣጫን የተከተሉ እንዳልነበሩ ገልጸዋል። ይህም የምንመኘውንና የምንፈልገውን ብሄራዊ መግባባት መፍጠር እንዳንችል አድርጓል ነው ያሉት። ኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የመንግስት ምስረታ ታሪክ ያላትና ቀደምት የስልጣኔ ባለቤት መሆኗን አስታውሰው የቅርብ ጊዜ የምስረታ ታሪክ ያላቸውና በሁለንተናዊ ዕድገት ከኢትዮጵያ የቀደሙ አገሮች ዋነኛ ምስጢር ከትናንት ታሪካቸው ተምረው ነጋቸውን የሚያሳምር ስራ መስራት መሆኑን ገልጸዋል። ሁሉን ነገር ከትላንት ጋር ብቻ በማያያዝና ትላንት ላይ ተቸክሎ በመቆየት ለውጥ እንደማይመጣ ገልጸው ዛሬና ነገን በማሰብ በጋራ መትጋት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። ዘላቂ ሰላምና ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር ነገን መናፈቅና ለነገ የተሻለ መመኘት ወሳኝ መሆኑንም ነው ያብራሩት። ዛሬ ላይ በወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች መግባባት በመፍጠር ነገ የምንመኛትን አገር እውን ማድረግ እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል። ለዚህም ዋልታ ረገጥ እሳቤዎችን በመተው የጋራ ትርክቶች ላይ በማተኮር ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር ሁላችንም በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል። ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ትኩረት በመስጠት ለመጪው ትውልድ የምትመች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ መረባረብ እንደሚገባም ነው የተናገሩት። አገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመነጋገር መግባባት ላይ ለመድረስ ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ለኮሚሽኑ ውጤታማነት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች ኢትዮጵያዊያን በአብሮነትና በመከባበር ለትውልድ የሚሻገር መልካም ስራ መስራት ይገባናል ብለዋል። ኢትዮጵያ የብዝሃ ብሄሮች አገር እንደመሆኗ የሁሉንም ማንነት በእኩል ደረጃ መቀበል ለዘላቂ ሰላም ወሳኝ ነው ብለዋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ፀሀይ ወራሳ እንደ አገር ያለውን ብዝሃነት ተቀብሎ የጋራ እሴቶች ላይ መስራትና የህዝቦችን አንድነት ማጠናከር ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር ቁልፍ መንገድ መሆኑን አንስተዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ፋጤ ስርሞሎ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ማስፈን የሁሉም ሃላፊነት ቢሆንም በተለይ አስፈጻሚ አካላት የሰላም ጉዳይ ላይ በትኩረት እንዲሰሩ የምክር ቤት አባላት የሚያደርጉትን ክትትልና ቁጥጥር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም ነው ያነሱት።
ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ወጣት ምሁራን ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል
May 1, 2024 58
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 23/2016(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ወጣት ምሁራን ባላቸው እውቀት ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሃመድ ገለጹ። የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ”የምሁራን ወጣቶች ሚና ለሀገረ መንግስት ግንባታ” በሚል መሪ ሃሳብ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ሁለተኛ ዙር የፓናል ውይይት አካሂዷል።   በመድረኩ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሀመድ፣ ከሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የተወጣጡ ወጣት ምሁራን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሀመድ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት በኢትዮጵያ ምላሽ የሚሹ በርካታ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች አሉ፡፡ ለነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተጀመረው ጥረት የወጣቶችን የላቀ ተሳትፎና ስራ የሚጠይቅ መሆኑን ተናግረዋል። መንግስት ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ ቢገኝም አሁንም የወጣቶችን ተሳትፎ የሚጠይቁ ተግባራት መኖራቸውን አንስተዋል። ወጣቱ ትውልድ የነገ ሀገር ተረካቢ ብቻ ሳይሆን በሀገሪቱ ሁለንተናዊ የእድገት ጉዞ ውስጥ ቀዳሚ ባለቤት መሆኑን ገልጸዋል። በሀገሪቱ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና በሌሎች የልማት ዘርፎች የተገኙ አወንታዊ ለውጦች የወጣቶች አሻራ ያረፈባቸው እንደሆኑ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በርካታ አምራች ወጣት ሃይል ያላት መሆኗን በመጥቀስ አንዳንድ ልማቷንና ሰላሟን የማይፈልጉ አካላት ከጀርባ ሴራ ለመፈጸም እንደሚሰሩ ጠቁመዋል። ወጣቶች የዚህች ሀገር ባለቤት መሆናቸውን አውቀው በሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ያላቸውን ሚና በተገቢው መልኩ ሊወጡ ይገባል ሲሉ ሚኒስትሯ ተናግረዋል። በሀገሪቱ ጠንከራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት የሚሰሩ ስራዎች ፍሬያማ እንዲሆኑ በምክንያታዊነት የሚያምን እና አለመግባባቶችን በንግግር መፍታት የሚችል ህብረተሰብ ማፍራት ወሳኝ መሆኑን ሚኒስትሯ ጠቅሰዋል። ለዚህም ደግሞ ምሁራን ወጣቶች ያላቸውን እውቀት እና ክህሎት በመጠቀም ለሀገረ መንግስት ግንባታው የሚረዱ ጥናታዊ ምርምሮችን በመስራት እና ህብረተሰቡን በማንቃት ትልቅ ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ፈትሂ ማህዲ በበኩላቸው ወጣቶች በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ ትልቅ ሚና በመጫወት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።   ለበርካታ ዘመናት ትውልዱ ስለ ሀገረ መንግስት ግንባታ ያለውን ግንዛቤ ለማጎልበት የሚያስችሉ በቂ ስራዎች አለመስራታቸው ሀገሪቷ ላይ ጫና ማሳደሩን ጠቁመዋል። ይህንንም ችግር ለመፍታት ወጣቱ ትውልድ በጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ የራሱን ሚና እንዲወጣ ማስቻል ይገባል ብለዋል። የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ምክትል ፕሬዝዳንት ወጣት ፈዲላ ቢያ በበኩሏ ሊጉ ከሁለት ወራት በፊት በጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት የወጣት ምሁራንን ተሳትፎ ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የፓናል ምክክር ማካሄዱን አስታውሳለች።   ይህን ተከትሎ የተካሄደው ሁለተኛው መድረክ በሀገሪቱ የሚገኙ ወጣቶች በሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ውስጥ እያደረጉት ያለውን ሚና በመፈተሽ በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። በውይይቱ ላይ ከተሳተፉ ወጣት ምሁራን አንዱ የሆነው ወንድሙ ወዳጆ ወጣቶች ሀገሪቷ ከሚያጋጥሟት ፈተናዎች በመሻገር ጠንካራ ሀገረ መንግስት እንዲኖር የሚጠበቅብንን ሀገራዊ ግዴታ መወጣት አለብን ሲል ተናግሯል። ወጣት ጫልችሳ ምልኬቻ በበኩሉ ምሁራን ወጣቶች የሀገራችንን ችግሮች ለመፍታት የሚረዱና በእውቀትና ክህሎት ላይ የተመሰረቱ የመፍትሄ ሃሳቦች ማፍለቅ መቻል አለብን ብሏል፡፡
ማስታወቂያ
ኢዜአ
Feb 7, 2023 18094
ኢዜአ
ፖለቲካ

የማዕድን ዘርፍን በስትራቴጂ ለመምራት እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት - የፌዴራል ሱፐርቪዥን ቡድን
May 1, 2024 76
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 23 /2016(ኢዜአ)፦ የማዕድን ሚኒስቴር ዘርፍን በስትራቴጂ ለመምራት እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የፌዴራል ሱፐርቪዥን ቡድን አስታወቀ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የበጀት ዓመቱን የመንግሥት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሲገመግሙ የፌዴራል ሱፐርቪዥን ቡድን ተቋቁሞ ትኩረት በተሰጣቸው ዘርፎች ላይ የመስክ ምልከታ እንዲያደርግ አቅጣጫ ማስቀመጣቸው ይታወሳል። በዚህም የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የሚያስተባብረው የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን የማዕድን ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት ላብራቶሪን ጎብኝቷል። እንዲሁም በከበሩ ማዕድናት ላይ እሴት በመጨመር ለውጭ ገበያ የሚያቀርበውን ኦርቢት ኢትዮጵያ ፣ በከበሩ ማዕድናት ልየታ እና ደረጃ አወጣጥ ላይ ስልጠና የሚሰጠውን ዓለም አቀፍ የከበሩ ማዕድናት ፋውንዴሽን እና በደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ፋብሪካ የመስክ ምልከታ አድርጓል። በዚሁ ወቅት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በማዕድን ዘርፍ በተለይም በኦፓልና በከበሩ ማዕድናት የተከናወኑ ስራዎች፣ በግንባታ ላይ ያሉ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች እና የነባር ፋብሪካዎች የምርት ሁኔታና የማዕድን ኢንዱስትሪ ግብዓት አቅርቦትን በሀገር ውስጥ ለመተካት የተሰሩ ስራዎች ቀርበዋል።   የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን አስተባባሪ ዶክተር ካሳሁን ተስፋዬ በዚሁ ወቅት ሚኒስቴሩ የዘርፉን ውጤታማነት ለማረጋገጥ የማዕድን ሴክተር ስትራቴጂ አዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባቱ የሚበረታታ ነው ብለዋል። ወርቅ ፣ የከሰል ድንጋይና የከበሩ ማዕድናትን በተገቢው መንገድ ለመጠቀም በውስጥ አቅም የ5 አመት ስትራቴጂ ቀርፆ ወደ ስራ መግባቱን በጥንካሬ አንስተዋል። እንዲሁም ከስትራቴጂው የተቀዱ አምስት ኢንሼቲቮችን በፕሮጀክት ደረጃ በማዘጋጀት ወደ ስራ መገባቱ አበረታች ተግባር መሆኑን ጠቅሰዋል። የወርቅ የወጭ ንግድን ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ለውጦችን በማስገኘት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል። በአንፃሩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከያዘው ዓመታዊ እቅድ አንፃር አፈጻጸሙ አጥጋቢ እንዳልሆነ አንስተው የጎደለውን ለመሙላት በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል። ባህላዊ የወርቅ አምራቾችን ወደ መካከለኛ አምራችነት ለማሳደግ እና የወርቅ አምራች ኩባንያዎችን ቁጥር ለመጨመር እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። በወርቅ ላይ የሚታየውን የኮንትሮባንድ ንግድ ከፀጥታ አካላትና ከክልል አመራሮች ጋር በመቀናጀት መከላከል እንደሚገባ አመላክተዋል። ከውጭ የሚገባውን የድንጋይ ከሰል በሀገር ውስጥ ለመተካት እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል። የከበሩ ማዕድናት ላይ እሴት ጨምሮ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የተጀመሩ ስራዎች መጠናከር እንዳለባቸው ነው የተናገሩት ። በዘርፉ የተሰማሩ ኩባንያዎችን በፋይናንስ፣ በስልጠና እና አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች መደገፍ ተገቢ መሆኑን ጠቅሰዋል። በግንባታ ላይ ያሉ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ በትኩረት መስራት እንደሚገባ በማሳሰብ በስራ ላይ ያሉ ፋብሪዎችን በመደገፍ በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ ማድረግ ይገባል ሲሉ አክለዋል። በተቋሙ ስር ያለውን ቤተ ሙከራ ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ ማደራጀት እንደሚገባ ዶክተር ካሳሁን ተናግረዋል። ተቋማዊ አደረጃጀት እና የስራ አካባቢን ምቹ በማድረግ ረገድ የተሰሩ ስራዎች ለሌሎች ተቋማት ተሞክሮ መሆን እንደሚችሉ ተናግረዋል።   የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት በማዕድን ዘርፍ ያሉትን ማነቆዎች ለማስወገድ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል። የማዕድን ሃብት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገትና ለህብረተሰቡ ኑሮ መሻሻል ያለው አቅም ከፍተኛ ቢሆንም እያበረከተ ያለው ድርሻ ግን አነስተኛ መሆኑን ጠቁመዋል። ለዘርፉ በሚገባ አለማደግ በርካታ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች እንዳሉ ያመለከቱት ሚኒስትሩ በተለይም ከዚህ ቀደም ዘርፉ የሚመራበት ስትራቴጂ አለመኖሩ ቀዳሚው ተግዳሮት እንደሆነ ተናግረዋል። መንግስት ሀገሪቱ ከማዕድን ተገቢውን ሃብት እንድታገኝ በሰጠው ልዩ ትኩረት በአስር አመት መሪ የልማት እቅድ ቅድሚያ ከተሰጠባቸው ጉዳዮች አንዱ መሆኑን አንስተዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአምስት አመት የማዕድን ዘርፍ ስትራቴጂ በማዘጋጀት ወደ ስራ መግባቱን ተናግረዋል። እንዲሁም የማዕድን ምክር ቤት ተቋቁሙ ዘርፉን በተገቢውን መንገድ ለመምራት እየተሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
በፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ሀላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ ከፍትሕ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኤርሚያስ የማነ ብርሃን ጋር ተወያዩ
Apr 30, 2024 85
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 22 /2016 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ሀላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ ከፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታ እና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኤርሚያስ የማነ ብርሃን ጋር ተወያዩ። በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ዙሪያ እና የወንጀል ምርመራን በቴክኖሎጂ ከማዘመን አንፃር የተሰሩ ስራዎችን ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ ገለጻ ማድረጋቸው ተመላክቷል። ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ ለፍትህ ሚኒስትር ዴኤታው እና በዘርፉ ለሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች ገለፃ አድርገዋል፡፡ ከገለፃው ጎን ለጎን የፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታ እና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኤርሚያስ የማነ ብርሃን ከልዑክ ቡድናቸው ጋር በቢሮው የተሰሩ የሪፎርም ስራዎችን እና የወንጀል ምርመራን በቴክኖሎጂ ከማዘመን አንፃር የተሰሩ ስራዎችን ምልከታ አድርገዋል፡፡ አባላቱ በተመለከቷቸው የሪፎርም ስራዎች መደሰታቸውንና ለፍትህ ስርአቱ ተስፋ የሰነቀ ስራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም ሁለቱም ተቋማት በሪፎርም ስራዎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን በፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ መረጃ ያመለክታል፡፡
በአፍሪካ ዘላቂ ሰላም ልማትና ዴሞክራሲ ለማረጋገጥና ብቁ አመራር ለማፍራት በሚደረገው ጥረት የኢትዮጵያ ሚና ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው
Apr 30, 2024 89
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 22/2016(ኢዜአ)፦ በአፍሪካ ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲን ለማረጋገጥና ብቁ አመራር ለማፍራት በሚደረገው ጥረት የኢትዮጵያ ሚና ተጠናክሮ መቀጠሉን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ዛዲግ አብርሃ ገለጹ። በአካዳሚው በሁለት ወራት ብቻ ከ120 በላይ የአፍሪካ አገራት አመራሮች ሥልጠና መውሰዳቸውንም ተናግረዋል። የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ካደረጉ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ጋር ውይይት አድርጓል። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ዛዲግ አብርሃ፤ አካዳሚው ከኢትዮጵያም ባለፈ በመላ አፍሪካ ብቁ መሪዎችን ለማፍራት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።   በአፍሪካ ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ ለማረጋገጥና ብቁ አመራር ለማፍራት በሚደረገው ጥረት የኢትዮጵያ ሚና ከጥንት እስካሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የቀድሞውን የኬንያ መሪ ጆሞ ኬንያታ እና የነፃነት ታጋዩን ኔልሰን ማንዴላ ማሰልጠኗን አስታውሰው፤ በዘመናዊ የአመራር ማሰልጠኛ በርካቶች እየሰለጠኑ መሆኑን ተናግረዋል። አካዳሚው የአፍሪካን ችግር የሚፈታ ብቁ አመራር ለማፍራት በሚያስችል መልኩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት በዘመናዊ መልኩ የተደራጀ መሆኑንም ጠቅሰዋል። አሁን ላይ ሥልጠና ለመውሰድ ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን ገልጸው፤ ይህንን ፍላጎት ተግባራዊ ለማድረግም በትኩረት ይሰራል ብለዋል። አካዳሚው በአህጉሪቱ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት የሚያስችሉ ሥራዎችን በስፋት እያከናወነ መሆኑን ተናግረው፤ ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ ከ120 በላይ የአፍሪካ አገራት አመራሮች ሥልጠና መውሰዳቸውን ጠቅሰዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎችም በተሟላና ዘመናዊ በሆነ መልኩ የተገነባው አካዳሚው ዓላማውም የሚደነቅ በመሆኑ የሁላችንም ድጋፍና እገዛ ያስፈልገዋል ብለዋል። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ እያደረገች ላለው የላቀ አስተዋጽዖ ምስጋናቸውን በማቅረብ ሌሎች አገራትም ይህንን መልካም አርዓያ ሊከተሉ ይገባል ብለዋል።    
ዘመናዊ ሰራዊት የመገንባት ሒደት በተከታታይ ስልጠና ተጠናክሮ ይቀጥላል- ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ
Apr 30, 2024 113
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 22/2016(ኢዜአ)፦ ዘመናዊ ሰራዊት የመገንባት ሒደቱ በተከታታይ ስልጠና ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የመከላከያ መሐንዲስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ ገልፀዋል። የውጊያ ምህንድስና ክፍለጦር ያሰለጠናቸውን የውጊያ ምህንድስና ሙያተኞች በዛሬው ዕለት አስመርቋል። በምረቃ መርሀ- ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የመከላከያ መሐንዲስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ ዘመናዊ ሰራዊት የመገንባት ሒደቱ በተከታታይ ስልጠና ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ተናግረዋል።   የውጊያ ምህንድስና ክፍለጦር የውጊያ ድጋፍ የመስጠት ግዳጁን በአስተማማኝ እየተወጣ መሆኑን የተናገሩት ጄኔራል መኮንኑ በተለይም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማደናቀፍ መዳረሻ መንገዶች ላይ ፀረ-ሰላም ኃይሎች የሚቀብሯቸውን ፈንጂና ተተኳሾች በማክሸፍ የውጊያ ምህንድስና ሙያተኞች ለሀገር ልማት በፅናት እየሰሩ ነው ብለዋል።   የውጊያ ምህንድስና ክፍለጦር አባላት አልሸባብ በሶማሌያ ድንበር አካባቢዎች የጥፋት ተልዕኮውን እንዳያሳካም ከሌሎች የሰራዊቱ ክፍሎች ጋር በመሆን በአስቸጋሪ የአየር ፀባይና የመሬት ገፆች ላይ የህይወት መስዋዕትነትም ጭምር በመክፈል ግዳጅ የተወጡ ጀግኖች መሆናቸውንም ገልፀዋል። ተመራቂዎቹ በመሰናክል አስቀማጭና አስወጋጅ መሠረታዊ ሙያ የተዋጊ መሐንዲስ እንዲሁም የተገጣጣሚ የተንቀሳቃሽና የተንሳፋፊ ድልድዮች የግዳጅ አፈፃፀም ሙሉ ዕውቀትና ብቃት እንዲይዙ የሚያስችል ሥልጠና የተሰጣቸው መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የውጊያ ምህንድስና ክፍለጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል ተስፋዬ ኩምሳ ናቸው።   በተቀመጠው የስልጠና መርሀ ግብር መሠረት በጠላት የሚጠመዱ የመስክ ወጥመዶችን ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ መሰናክሎችን ማስወገድ ለወገን ጦር ግዳጅ አፈፃፀም ምቹ ሁኔታን መፍጠር የጠላትን ግስጋሴ የመግታትና የወገንን እንቅስቃሴ የሚያቀላጥፉ ሥልጠናዎችን የወሰዱና ብቃታቸው በፈተና የተረጋገጠ መሆኑንም ኮሎኔል ተስፋዬ መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘ ውመረጃ ያመለክታል። ተመራቂዎቹም በሠለጠኑት ሙያ ሀገራቸውን በታማኝነት ለማገልገል መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ አሰባሳቢ የወል ትርክቶችን በመገንባት ረገድ የበኩላችንን ለመወጣት ተዘጋጅተናል
Apr 30, 2024 102
አዲስ አበባ ፤ ሚያዝያ 22/2016 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያን የቆዩ ስብራቶች በመጠገን አሰባሳቢና የወል ትርክቶችን በመገንባት ረገድ የበኩላችንን ለመወጣት ተዘጋጅተናል ሲሉ የኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች ገለጹ። በኢትዮጵያ ከስድስት አመታት በፊት የመጣውን ለውጥ ተከትሎ በመደመር እሳቤ ሁሉንም አሳታፊ ያደረገ የኢኮኖሚ፣ የማልማትና የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሂደት ተጠናክሮ ቀጥሏል። በዋልታ ረገጥ እሳቤዎች ሲንከባለሉ የመጡትን የጥላቻና የመገፋፋት ትርክቶች በመቀየር የጋራና አሰባሳቢ ትርክቶችን የመገንባት ስራም በስፋት እየተከናወነ ይገኛል። በመሆኑም ሀገራዊ መግባባት በመፍጠር ለሁሉም የምትመችና የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ከምንም በላይ የጋራ ጥረትና ትብብር ማድረግ እንደሚገባ ይታመናል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች፤ የኢትዮጵያን የቆዩ ስብራቶች በመጠገን አሰባሳቢና የወል ትርክቶችን በመገንባት ረገድ የበኩላችንን ድርሻ ለመወጣት ተዘጋጅተናል ሲሉ ተናግረዋል። የሀዋሳ ከተማ ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ ምርጫዬ ደመቀ፤ በኢትዮጵያ አሰባሳቢ ትርክትን የመገንባት ተግባር የሚዲያና ኮሙንኬሽን ተቀዳሚ ተግባር መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም በዋልታ ረገጥ እሳቤዎች ጥላቻና ቁርሾ የሚፈጥሩ ትርክቶችን በማረም የሚያቀራርቡ አሰባሳቢ ትርክቶችን ለማጉላት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል። ለዚህም የኮሙንኬሽን አመራርና ባለሙያዎች ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ በመሆን ወደ ስራ ገብተናል ሲሉ ተናግረዋል።   የስልጤ ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ሳሊያ ሐሰን፤ በሀገር ጉዳይ ከሚያለያዩና ተቃርኖ ከሚያባብሱ ጉዳዮች በመራቅ ከምንም በላይ ለአብሮነትና አንድነት ለመስራት ተዘጋጅተናል ብለዋል። የሀገር አንድነትና ብሄራዊ መግባባት የሁሉም ነገር መሰረት መሆኑን ጠቅሰው ልዩነቶችን በመስበክ አብሮነትን መሸርሸር ለማንም የማይጠቅምና ሀገርንም የሚጎዳ መሆኑን ጠቅሰዋል።   የኮንታ ዞን የኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አበበ ጎበና፤ በመደመር እሳቤ ሀገራዊ አንድነትን በማጎልበት ልማትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ መስራት የሁላችንም ሃላፊነት ሊሆን ይገባል ብለዋል።    
ለሀገራዊ የምክክር ስኬት የድርሻችንን እንወጣለን ሲሉ  የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተናገሩ
Apr 30, 2024 108
አሶሳ/ሐረር ሚያዚያ 22/2016 (ኢዜአ)፡- ለሀገራዊ ምክክር ስኬት የድርሻችንን እንወጣለን ሲሉ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የአሶሳና ሐረር ከተሞች የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተናገሩ። አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ ሃሰንያ ሱሊማን እንዳሉት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልም ሆነ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች በርካታ ፈተናዎች ሲያጋጥሙን ቆይተዋል፡፡ እነዚህ ፈተናዎች ለግጭት እንዲዳርጉን ባለመፍቀድ በሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አማካኝነት በሚካሄድ ንግግር አጃንዳዎች ሆነው እንደሚመጡ መፍትሄም ያገኛሉ ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። "የምክክር ውጤት ሠላም ነው" የሚሉት ወይዘሮ ሃሰንያ፤ የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ዓላማ ደግሞ ሠላምን ከማስፈን ባሻገር ወንድማማችነትን የበለጠ ስለሚያጠናክር የድርሻዬን ለመወጣት ዝግጁ ነኝ ብለዋል።   አቶ ሰለሞን ካሳ የተባሉ የከተማው ነዋሪ በበኩላቸው ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሚሠራው ለሀገር ሰላም እንደሆነ ይገልጻሉ። በውይይት የሚነሱ ሃሳቦች ችግሮቻችንን በመፍታት አንድነታችንን ያጠናክራሉ የሚሉት ነዋሪው ኮሚሽኑ ሀገራዊ ምክክር እንዲካሄድ እያደረገ የሚገኘው ጥረት ላይ የድርሻቸውን ለመወጣት እንደሚተጉ ተናግረዋል፡፡   ወይዘሮ አሙና አብዱልዋሂድ የተባሉ የአሶሳ ከተማ ነዋሪም የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ያልተግባባንባቸውን የሀገራችንን የውስጥ ጉዳዮች ሶስተኛ ወገን ሳይገባ በራሳችን መፍታት ያስችለናል ብለዋል። ይህ ደግሞ በሐሳብ የበላይነት በማመን እና ችግሮችን ተነጋግሮ በመፍታት ሀገራችንን በሠላማዊ እና በተረጋጋ መንገድ መምራት ያስችለናል ሲሉ አመልክተዋል፡፡ እንደ አንድ የሀገር ዜጋ እኛ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ነዋሪዎች የኮሚሽኑ ጥረት እንዲሳካ የድርሻችንን እንወጣለን ሲሉ ገልጸዋል። ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ስኬታማ እንዲሆን ሁሉም የበኩሉን ድጋፍ ማድረግ ይገባዋል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።   ሀገራዊ ምክክሩ የሚታዩ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ተስፋ የሚሰጥና የሚበረታታ ነው ያሉት ደግሞ የሐረር ከተማ ነዋሪ መምህር ቶማስ ዱባለ ናቸው።   በምክክር ኮምሽኑ በሐረሪ ክልል የህብረተሰብ ተወካይ ሆነው ከተመረጡት መካከል አቶ መስፍን አክሊሉ ሀገራዊ ምክክሩ ጦርነትና ግጭቶችን የማስወገድና እንደ ሀገር የታሰበው ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲያመጣ የሚያስችል ነው ብለዋል። በመሆኑም እንደ ማህበረሰብ ተወካይ ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬት የሚጠበቅብኝን ለመወጣት ተዘጋጅቻለሁ ብለዋል። እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ የምክክሩ ሂደት ውጤታማነት የሚረጋገጠው ሁሉም በባለቤትነት ሲሳተፍ በመሆኑ ለዚህም የሚጠበቅብንን መወጣት ይገባል ብለዋል።              

ማህበራዊ
በህገወጥ መንገድ 46 በርሜል ናፍጣና ቤንዚን ሲያዘዋውሩ የተገኙ ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
May 1, 2024 54
ሚዛን አማን ፣ሚያዚያ 23/2016 (ኢዜአ)፡- በሚዛን አማን ከተማ በህገወጥ መንገድ 46 በርሜል ናፍጣና ቤንዚን ሲያዘዋውሩ የተገኙ ሦስት ተጠርጣሪ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአስተዳደሩ ፖሊስ አስታወቀ። ሕገወጥ የነዳጅ አቅርቦትና ሽያጭ በከተማዋ በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ላይ እጥረት እንዲያጋጥም በማድረግ ተደጋጋሚ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ እያስነሳ መሆኑንም ጠቁመዋል። የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር አዳነ አለማየሁ በከተማዋ ምሽትን ተገን በማድረግ 35 በርሜል ናፍጣና 11 በርሜል ቤንዚን በህገ ወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የተገኙ ሦስት ተጠርጣሪ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ተናግረዋል።   በህገ ወጥ መንገድ ቤንዚንና ናፍጣ የሚያሸሹና እጥረት እንዲከሰት የሚያደርጉ አካላት መኖራቸውን ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው፤ በዚህም ተጠርጣሪ ግለሰቦቹ ሊያዙ መቻላቸውን አስረድተዋል። በዚህ መሰረት ትናንት ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ገደማ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-A38706 AA የሆነ አይሱዙ መኪና 11 ቤርሜል ቤንዝል ጭኖ ሊወጣ ሲል በተደረገው ክትትል ከነአሽከርካሪው መያዙን ተናግረዋል። በተጨማሪም ከምሽቱ ስምንት ሰዓት ገደማ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-B52395 AA የሆነ የአይሱዙ መኪና 35 ቤርሜል ናፍጣ በህገወጥ መንገድ ጭኖ ሊወጣ ሲል አሽከርካሪው ከነረዳቱ መያዙን ነው የገለጹት። በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሶስቱም ተጠርጣሪ ግለሰቦች ላይ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝም አስረድተዋል። የቁጥጥርና ክትትል ተግባርን በማጠናከር በህገወጥ መንገድ ከማደያ የሚያወጡ፣ በበርሜልና በሌሎችም ቁሶች ነዳጅ የሚቸረችሩ አካላት ላይ የተጠናከረ እርምጃ እንደሚወሰድም ተናግረዋል። ህገወጥ የነዳጅ ግብይት በመበራከቱ የግብይት ስርአቱ እንዳይረጋጋ እያደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ ኅብረተሰቡ ጥቆማ በመስጠት እና ከፖሊስ ጎን በመቆም እያሳየ ያለውን ትብብር እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።  
በደብረ ብርሃን ከተማ 69 መኖሪያ ቤቶች ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች ተላለፉ
May 1, 2024 44
ደብረ ብርሀን ፤ ሚያዝያ 23/2016(ኢዜአ)፡- የደብር ብርሃን ከተማ አስተዳደር የተለያዩ አካላትን በማስተባበር ያስገነባቸውን 69 መኖሪያ ቤቶችን ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች ማስተላለፉን አስታወቀ። የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት እንደገለጹት፤ አስተዳደሩ የተለያዩ አካላትን በማስተባበር ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ወገኖች የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ ነው።   በዚህም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን፣ ባለሃብቶች እና ወጣቶችን በመስተባበር ከ10 ሚሊዮን ብር ወጪ 12 ብሎክ ያላቸው 98 መኖሪያ ቤቶችን ግንባታ እያከናወነ መሆኑን ገልፀዋል። እየተገነቡ ካሉ መኖሪያ ቤቶች መካከል ግንባታቸው የተጠናቀቁ 69 መኖሪያ ቤቶችን በዛሬው እለት ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ መቻሉን ተናግረው፣ ቀሪ ቤቶችም በቅርቡ ተጠናቀው ለተጠቃሚዎች ይተላለፋሉ ብለዋል። ተጠቃሚዎቹ የፋሲካ በዓልን በደስታ እንዲያሳልፉ ታሳቢ ተደርጎ ቤቶቹ መተላለፋቸውን ጠቁመው፣ ለቤቶቹ ግንባታ ህብረተሰቡ በገንዘብ፣ በጉልበትና በቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል መኖሪያ ቤቶችን በመገንባት የህብረተሰቡን ችግር ለመፍታት የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አቶ በድሉ አስታውቀዋል። በተጨማሪም በከተማው የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለማቃለል በዚህ ዓመት በ196 ማህበራት ለተደራጁ 5 ሺህ 500 አባወራዎች የግንባታ ቦታ እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል። በከተማው ጠባሴ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ዮርዳኖስ ዓለሙ እንዳሉት፤ ከጎናቸው ደጋፊ በማጣት ከሁለት ልጆቻቸው ጋር በቤት እጦት ምክንያት ሲቸገሩ መቆየታቸውን አስታውሰዋል። ከተማ አስተዳደሩ በትንሳኤ በዓል ዋዜማ የዘመናት የመኖሪያ ቤት ችግራቸው በመፍታቱ መደሰታቸውንና ለተደረገላቸው እገዛም ምስጋና አቅርበዋል። ሌላዋ ተጠቃሚ ወይዘሮ ብዙአየሁ ዓለማየሁ በበኩላቸው፤ ባላቸው አነስተኛ ገቢ የቤት ኪራይ ከፍለው ለመኖር ተቸግረው እንደነበር አስታውሰው፤ በአሁኑ ወቅት ችግራቸው በመፈታቱ አስተዳደሩን አመስግነዋል። በመኖሪያ ቤት ርክክቡ ላይ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችና የሚመለከታቸው አካላት እንዲሁም የእድሉ ተጠቃሚዎች ተገኝተዋል።        
በክልሉ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን ለማሳደግ የፕሮጀክቶች ግንባታ እየተከናወነ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሰታ ሌዳሞ
May 1, 2024 80
ሀዋሳ ፤ ሚያዝያ 23/2016(ኢዜአ)፡- በሲዳማ ክልል የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን ለማሳደግ የሚረዱ ፕሮጀክቶች በመገንባት ላይ መሆናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ አስታወቁ ። በሀዋሳ ከተማ 80 ሺህ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርገው የፋራ-ሂጣታ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ሥራ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በተገኙበት ተጀምሯል።   ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ ሲዳማ በክልል ከተደራጀ በኋላ የክልሉ መንግስት ለመጠጥ ውሃ ተደራሽነት ትኩረት ሰጥቷል። በወቅቱ የክልሉ የንፁህ መጠጥ ውሀ ተደራሽነት 38 በመቶ እንደነበር ያወሱት አቶ ደስታ፤ በአሁን ወቅት 66 በመቶ ማድረስ የሚችሉ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ መሆኑን ተናግረዋል። የፋራ-ሂጣታ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክትም የዚሁ አካል እንደሆነ ጠቅሰዋል። "ለኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝምና ኢንቨስትመንት ተመራጭ በሆነችው ሀዋሳ እየጨመረ የመጣውን የነዋሪ ቁጥር ፍላጎት ጋር የሚመጣጠንና ደረጃውን የጠበቀ የውሃ አቅርቦት ተደራሽ ይደረጋል" ብለዋል። የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ መኩሪያ መርሻዬ በበኩላቸው፤ "ፕሮጀክቱ የፋራና ሂጣታ ቀበሌ ነዋሪዎችን የዓመታት የመጠጥ ውሃ ጥያቄ የሚመልስ ነው" ብለዋል።   አስተዳደሩ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ተጀምረው በወቅቱ ስራቸው ባለመከናወኑ የተጓቱ ፕሮጀክቶችን ገምግሞ ለህዝቡ ከሚሰጡት ጠቀሚታ አኳያ 790 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ለአገልግሎት እንዲበቁ ማድረጉንም ተናግረዋል። "ፕሮጀክቱ ከስድስት እስከ ዘጠኝ ወራት ባለው ጊዜ ግንባታው ተጠናቅቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ጥረት እናደርጋለን" ብለዋል። "በከተማዋ የአላሙራ ተራራን ተንተርሰው የተመሰረቱት የፋራና ሂጣታ ቀበሌዎች ካሉበት ከፍታ ቦታ አኳያ ለከተማዋ ሚሰራጨው የመጠጥ ውሃ ሳይደርሳቸው ለዓመታት ቆይተዋል" ያሉት ደግሞ የሀዋሳ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ሌላሞ ናቸው።   ፕሮጀክቱ በቀበሌዎቹ የሚኖሩ 80 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመው፤ ከተማው ያለውን የመጠጥ ውሀ ሽፋን ከ80 በመቶ ወደ 84 በመቶ የሚያሳድግ እንደሆነ አብራርተዋል። ፕሮጀክቱ የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራን ጨምሮ በ232 ሚሊዮን ብር እንደሚገነባ አስታውቀዋል ። የፋራ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ማርቆስ ቡኡሻ "በአካባቢያችን የመጠጥ ውሀ ባለመኖሩ ከሌላ አካባቢ አንድ ጀሪካን ውሃ በሁለት ብር ገዝተን በማምጣት አልያም በጋሪ አዙረው ከሚሸጡ ሰዎች አንዱን ጀሪካን በ20 ብር በመግዛት እየተጠቀምን እንገኛለን" ብለዋል።   የመጠጥ ውሃ ችግራቸው የከፋ በመሆኑ ለዓመታት ቅሬታ ሲያሰሙ መቆያታቸውን አንስተው፤ ዛሬ ባገኙት ምላሽ መደሰታቸውን ገልጸዋል ። የሂጣታ ቀበሌ ነዋሪ አቶ አማረ ብሩ በበኩላቸው፤ በውሃ እጦት ከሚያገኛቸው ድካምና እንግልት ባለፈ ለውሃ ወለድ በሽታዎች እንደሚጋለጡ ገልፀዋል።   ይህንን ችግራችንን የሚፈታልን የመጠጥ ውሃ ግንባታ ሊካሄድ በመሆኑ እጅግ ደስ ብሎናል " ብለዋል ። በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዐቱ ላይ የክልልና የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የባህል አባቶችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በአማራ ክልል የዳኝነትና ፍትህ ሥርዓቱን በማሻሻል ለህብረተሰቡ ፈጣንና ፍትሃዊ አገልግሎት ይሰጣል--አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ
May 1, 2024 69
ደሴ ፤ ሚያዝያ 23/2016(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል የፍትህና የዳኝነት ስርዓቱን በማሻሻል ለህብረተሰቡ ፈጣንና ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ ገለጹ። የአማራ ክልል የፍትህ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ስትሪንግ ኮሚቴ በደሴ ከተማ ከህብረተሰብ ተወካዮች ጋር መክሯል።   ዋና አፈ ጉባኤዋ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ በየደረጃው ከህዝብ ጋር በተደረጉ ምክክሮችና የዳሰሳ ጥናቶች በዘርፉ የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተትና የስነ ምግባር ግድፈቶች እንዳሉ ተረጋግጧል። እንዲሁም የቅንጅት ክፍተት፣ የአሳሪ ደንብና መምሪያዎች መኖራቸውን ገልፀዋል። ለዚህም ዋነኛው ችግር የዳኝነትና ፍትህ ስርዓቱ መሆኑን ጠቁመው፣ ሥርዐቱን ከባለድርሻ አካላት ጋር በማሻሻል ለህብረተሰቡ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህም ከህዝብ ጋር በመሆን ክፍተቱን ለይቶ ዘርፉን የሚያሻሽል ኮሚቴ በማቋቋም ወደሥራ እንዲገባ መደረጉን የገለጹት ወይዘሮ ፋንቱ፣ "በየደረጃው በመምከርና ፍትህን በማስፈን ለክልሉ ዘላቂ ሰላም በትኩረት ይሰራል" ብለዋል። ህብረተሰቡ በፍትህ ስርዓቱ እምነት እንዲኖረው፣ መንግስትና ህዝብ እንዲቀራረብ፣ የህግ የበላይነት እንዲከበርና በእርቅና ሽምግልና ችግሮች መፈታት እንዲችሉ ኮሚቴው እየሰራ መሆኑንም ወይዘሮ ፋንቱ አስታውቀዋል። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አብዬ ካሳሁን በበኩላቸው እንዳሉት፤ በፍትህ ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን በማስተካከል ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት በየደረጃው ውይይት እየተደረገ ነው።   እስካሁን በተደረጉ ውይይቶች በዘርፉ ላይ የፍርድ መጓደል፣ የቅንጅት ክፍተት፣ የአቅም ውስንነት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እና ሌሎች ችግሮች እንደተስተዋሉ መለየታቸውንም ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ደንብና መመሪያዎችን ጭምር በማስተካከል የዳኝነት አገልግሎቱ ቀልጣፋና ፍትሃዊ እንዲሆን ጥረት እየተደረገ መሆኑን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፤ ለውጤታማነቱ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል። አቶ አብዬ እንዳሉት ለችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ሽምግልናና አበጋርን ጨምሮ ሌሎች ባህላዊ የእርቅ አሰራሮችም በህግ እንዲደገፉና ሚናቸውን ከፍ እንዲል ይደረጋል። የውይይቱ ተሳታፊ አቶ ሀብታሙ አሊ በበኩላቸው እንደገለጹት የተጀመረው ውይይት ችግሩን ለማስተካከል ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፣ "ችግሩን ለመፍታት ለሚከናወኑ ሥራዎች ስኬታማነት የድርሻዬን ለመወጣት ዝግጁ ነኝ" ብለዋል።   ሌላዋ የውይይቱ ተሳታፊ ወይዘሮ ፋጡማ መሃመድ በበኩላቸው፤ ችግሮች በዘላቂነት መፍትሄ እንዲያገኙ ባህላዊ የእርቅ ስነ ስርዓቶች በህግ ጭምር ተደግፈው ወደ ተግባር ሊቀየሩ ይገባል ብለዋል።   በመድረኩ የክልል፣ የደቡብ ወሎ ዞን እና የደሴ ከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም የከተማዋ ምክር ቤት አባላት፣ የፍትህ አካላትና ሌሎችም ተሳትፈዋል።  
ኢኮኖሚ
ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሃገራት ኢኮኖሚያዊ ትስስር ከፍተኛ ሚና ትጫወታለች - አቶ አሕመድ ሽዴ
May 1, 2024 41
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 23/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በቀጣናው ሃገራት ደህንነትና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ዙሪያ ቁልፍ ሚና ትጫወታለች ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ገለጹ። አቶ አሕመድ በሳኡዲ አረቢያ ሪያድ በተደረገ የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም መድረክ ላይ በነበራቸው ተሳትፎ እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ እያደገ የመጣውን ፈተና ለመቋቋም የደቡብ ደቡብ ትብብር ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። ኢትዮጵያ የቀጣናውን ሃገራት በማስተሳሰር ቁልፍ ሚና እንዳላት የገለጹት ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ከቀረው ዓለም ጋር በማገናኘት ረገድ የአንበሳውን ድርሻ እንደሚይዝም አስረድተዋል። እኛ ለቀጣናው ሃገራት ኢኮኖሚያዊ ትስስርና መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረግን ነው ያሉት ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እና በአረቡ ዓለም ግንኙተን ላይም ጉልህ ሚና እንዳላት ገልጸዋል። ዓለም እየገጠሟት ያሉትን የተለያዩ ፈተናዎች ለመቋቋምም የደቡብ ደቡብ ትብብር ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ ከዓባል ሃገራት ጋር ያላትን ኤኮኖሚያዊ ትስስር እንደሚያጠናክርላትም ነው አቶ አሕመድ ሽዴ የተናገሩት። ኢትዮጵያ የአፍሪከ ህብረትን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ማዕከል መሆኗን በውይይቱ ላይ ያነሱት አቶ አሕመድ ይህም በቀጣናው እና በአህጉሩ ያላት ሚና ከፍ ያለ እንዲሆን ማድረጉን ጠቁመዋል። የብሪክስ አባል ሃገራት በኢኮኖሚ በኢንቨስትመንት በቴክኖሎጂና በአቅም ግንባታ ረገድ በትብብር መስራት የሚችሉበት ሁኔታም ሰፊ መሆኑን ገልጸዋል።
በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት በጠንካራ መሰረት ላይ ለማኖር አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለጸ
May 1, 2024 48
መቀሌ ፣ሚያዚያ 23/2016 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት በጠንካራ መሰረት ላይ ለማጽናት ሚና እንዳለው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ተወካይ ዶክተር ሄኖክ ስዩም ገለጹ። በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ላይ ያተኮረ ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እና የውይይት መድረክ በመቀሌ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ ዛሬ በተከፈተውና ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ተወካይ ዶክተር ሄኖክ ስዩም እንደገለጹት፤ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ተግባራዊ በማድረግ የአፍሪካን የንግድና የኢኮኖሚ ትብብርን ለማሳደግ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት እና በኢጋድ ስር ሆና የበኩሏን ድርሻ እየተወጣች ነው፡፡ “ስምምነቱ የአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርም እና የ10 ዓመት የስትራቴጂ እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ያግዛል” ያሉት ዶክተር ሄኖከ፤ በተለይም የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት በጠንካራ መሰረት ላይ ለማጽናት ትልቅ ሚና እንዳለው አብራርተዋል። የኢትዮጵያን የወጪ ንግድ ለማሳደግ፣ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና ተወዳዳሪ ምርቶችን ለማቅረብ እንደሚረዳ ጠቁመው፤ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሰምምነቱ የላቀ ድርሻ እንዳለው ነው የተናገሩት፡፡ የአፍሪካ አገሮች የንግድና ኢኮኖሚ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ጠቀሜታ እንዳለው ያመለከቱት ዶክተር ሄኖክ፤ የአህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግ ኢትዮጵያ ጥቅሟን ባስጠበቀ መልኩ እየሰራች መሆኗን ተናግረዋል፡፡ እንደ ዶክተር ሄኖክ ገለጻ፤ የአህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግ በተለያዩ ክልሎችና ከተሞች ብሔራዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እና የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የንግድና ኤክስፖርት ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ገብረመስቀል ታረቀ በበኩላቸው፤ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የትሬድ ማርክ አፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር አቶ አብነት በቀለ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ አፍሪካ ለምታልመው አህጉራዊ ልማትና እድገት ስምምነቱ ቁልፍ ነው። ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሲሆን በአህጉር ደረጃ 30 ሚሊዮን ዜጎችን ከድህነት እንደሚያላቅቅ አመልክተዋል። ትሬድ ማርክ አፍሪካ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በስምምነቱ ዙሪያ ከዚህ በፊት በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በድሬዳዋ፣ በሀዋሳና ጅማ ከተሞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች መስጠቱን ጠቁመዋል። አሁን በመቀሌ ከተማ እየተካሄደ ያለው ስድስተኛው ዙር መሆኑንና በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተዋል፡፡ በመድረኩ በንግድ ዘርፍ የተሰማሩ አካላት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን የመርሃ ግብሩ አስፈጻሚ አካላት እና የንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡  
በማዕከላዊ ጎንደር ለውጭ ገበያና ለአግሮ ኢንዱስትሪዎች በግብዓትነት የሚቀርብ ሰብል ለማምረት ዝግጅት ተጀምሯል
May 1, 2024 49
ጎንደር ፤ ሚያዝያ 23/2016(ኢዜአ)፡- በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በመኽር ወቅት ለውጭ ገበያና ለአግሮ ኢንዱስትሪዎች በግብዓትነት የሚቀርብ ከአራት ሚሊዮን ኩንታል በላይ የሰብል ምርት ለማምረት ዝግጅት መጀመሩን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ፡፡ በዞኑ የ2016/17 ምርት ዘመን መኽር ወቅት የሰብል ልማት የንቅናቄ መድረክ ዛሬ በጎንደር ከተማ ተካሂዷል፡፡ የመምሪያው ሃላፊ አቶ ንጉሴ ማለደ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ በመኸር ወቅት ለውጪና ለአገር ውስጥ ገበያ የሚቀርቡ የቅባት እህሎችና ለአግሮ ኢንዱስትሪዎች በግብዓትነት የሚውል ሰብል በ185 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ይመረታል፡፡ በዚህም በምርት ዘመኑ በ93 ሺህ ሄክታር መሬት ለውጪ ገበያ የሚቀርብ አንድ ሚሊዮን ኩንታል አኩሪ አተር፣ ማሾና ሰሊጥ ለማምረት የሚያስችል የእርሻ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም በ92 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ደግሞ ለአገር ውስጥ አግሮ ኢንዱስትሪዎች በግብዓትነት የሚውል ሦስት ሚሊዮን ኩንታል የቢራ ገብስ፣ ስንዴ፣ ሽንብራና በቆሎ እንደሚመረት አመልክተዋል፡፡ ምርታማነት ለመጨመር የሚያግዙ ኩታ ገጠም እርሻ፣ በመስመር መዝራትና የጥቁር አፈር ማንጣፈፍ የግብርና አስራሮችና ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ጠቁመዋል፡፡ አርሶ አደሩ በአካባቢው እየሰፈነ ያለውን ሰላም በመጠቀም እስካሁን ከ400 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት አርሶ በማለስለስ ለዘር ስራ ዝግጁ ማድረጉንም አብራርተዋል፡፡ የምርት ማሳደጊያ ግብዓቶች እንዲቀርቡ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ "እስካሁንም ከ267 ሺህ ኩንታል በላይ ማዳበሪያና 9 ሺህ 400 ኩንታል ምርጥ ዘር ቀርቦ ለአርሶ አደሩ እተሰራጨ ይገኛል" ብለዋል፡፡ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አላምረው አበራ በበኩላቸው፤ የመኽር እርሻ ዝግጅቱ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲያከናውን ሰላምን የማረጋገጥ ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡   በዞኑ በ2016/17 የምርት ዘመን 529 ሺህ ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች በማልማት 17 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት ግብ ተጥሎ እየተሰራ መሆኑም ታውቋል፡፡
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የግል ባለሃብቶች የተሽከርካሪዎች ቻርጅ ስቴሽን ግንባታ ላይ እንዲሰማሩ ጥሪ ቀረበ
Apr 30, 2024 76
የግል ባለሃብቶች የተሽከርካሪዎች ቻርጅ ስቴሽን ግንባታ ላይ እንዲሰማሩ ጥሪ ቀረበ አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 22/2016(ኢዜአ)፡- የግል ባለሃብቶች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ከማስገባት ባለፈ የቻርጅ ስቴሽን ግንባታ ላይ እንዲሰማሩ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ጥሪ አቀረበ። የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ምትኩ አስማረ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በከተማዋ በቀን ውስጥ ከሚደረገው 3 ነጥብ 4 ሚሊየን የትራንስፖርት ምልልስ ውስጥ 31 በመቶው በብዙኃን ትራንስፖርት የሚሸፈን ነው። የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን መጠቀም አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት እንደ አገር እየተከናወነ ያለውን ሥራ ለመደገፍ ትልቅ አስተዋጽዖ አለው።   በተለይም ኢትዮጵያ ነዳጅ ከውጭ ለማስገባት የምታወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንዲቀር በማድረግ ለኢኮኖሚው አበርክቶ ይኖረዋል ነው ያሉት። መንግሥትም ለብዙኃን ትራንስፖርት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል። በከተማ አስተዳደሩ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ተሽከርካሪዎች አብዛኞቹ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በከተማው ያለው የተሽከርካሪዎች ቻርጅ ስቴሽን በቂ ስላልሆነ ባለሃብቱ በዚህ ላይ ቢሳተፍ እራሱንና አገሩን ይጠቅማል ብለዋል። ቢሮው በዘርፉ ለተሰማራው የግል ትራንስፖርት ሰጪ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ የግል ባለሃብቶች በኤሌክትሪክ ቻርጅ ስቴሽኖች ላይ እንዲሰማሩም ጥሪ አቅርበዋል።   መንግሥት 100 በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የከተማ አውቶቡሶች ግዥ በመፈፀም በአጭር ጊዜ ለማስገባት ሥራ መጀመሩንም ነው የገለፁት። በተጨማሪም አገልግሎት እየሰጡ ያሉ የከተማ አውቶቡሶችን በቴክኖሎጂ የተደገፉ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል። ሕብረተሰቡ አውቶቡሶች በስንት ሰዓት እንደሚደርሱ መረጃ የሚያገኙበት የመረጃ ሥርዓት በመርካቶ ተርሚናል ሥራ መጀመሩንና በሌሎች ለማስፋት እንደሚሰራም ተናግረዋል። የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የሕዝብ ትራንስፖርት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች እየገጣጠመ እንደሚገኝና በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የመጀመሪያዎቹ 216 ተሽከርካሪዎች መገጣጠማቸውን የገለፁት ደግሞ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ ሰጠኝ እንግዳው ናቸው።   በቬሎሲቲ ኤክስፕረስ ድርጅት አማካኝነት 20 የኤሌክትሪክ ሚኒባሶችና ሁለት ኤሌክትሪክ ከተማ አውቶቡሶች በሙከራ ደረጃ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል። አውቶቡሶቹ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ከመሆናቸው ባሻገር ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ሆነው መዘጋጀታቸውንም ነው የገለፁት።    
በኢትዮጵያ ስታርት አፖችን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የኮሪያ ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ ድጋፍ ይቀጥላል
Apr 30, 2024 94
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 22/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ስታርት አፖችን ለማሳደግ የሚደረጉ ጥረቶችን ለማገዝ የኮሪያ ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በድርጅቱ የኢትዮጵያ ተወካይ ሃንዳክ ጆ ገለጹ። በኢትዮጵያ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ወጣቶች በመደገፍና በማበረታታት ስታርት አፖች በስፋት እየተዋወቁ ይገኛሉ። በዘርፉ የተሻለ የፈጠራ ስራ እንዲኖር ምቹ ምህዳር እየተፈጠረ መሆኑ ይታወቃል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የኮሪያ ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) የኢትዮጵያ ተወካይ ሃንዳክ ጆ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ አሁን ላይ የፈጠራና ቴክኖሎጂ ትግበራ ልዩ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ጠቅሰዋል። በመሆኑም በኢትዮጵያ በተለይም በቅርብ አመታት በስታርት አፖች ለተሻለ የፈጠራ ስራ ምቹ ምህዳር መኖሩን አድንቀዋል። ኮይካ የ10 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት በመያዝ ለስታርት አፖች የተቋማት ኢንኪዩቤሽን ማዕከላት ግንባታ ምቹ ምህዳር ለመፍጠር ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል። በመሆኑም በኢትዮጵያ በዘርፉ የሚደረጉ ጥረቶችን በማገዝ ረገድ የኮይካ ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ፣ በስታር አፖች እንዲሁም በአርቴፊሻል ኢንተሌጀንስ ዘርፍ በኢትዮጵያ የተጀመሩ ጥረቶች የሚደነቁ ናቸው ብለዋል። በኢትዮጵያ ከለውጡ በፊት 50 ብቻ የነበሩት ስታርት አፖች አሁን ላይ ከ900 በላይ ጀማሪ፣ መካከለኛ ደረጃ ላይ ያሉ እና ወደ ገበያ የገቡ ስታርት አፖች እንዳሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በሳይንስ ሙዚየም ተከፍቶ በነበረው አውደ ርዕይ 300 የሚደርሱ ስታርት አፖች ለእይታ ቀርበው የተሻሉ የስራ ሃሳብ የነበራቸው ስታርት አፖች መሸለማቸው ይታወሳል።
በአማራ ክልል ከተሞችን በማዘመን አገልግሎት አሰጣጣቸውን ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቷል- የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን 
Apr 29, 2024 90
ደሴ ፤ ሚያዚያ 21/2016(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ከተሞችን በቴክኖሎጂ በማበልጸግና በማዘመን አገልግሎት አሰጣጣቸውን ለማሻሻል ትኩረት መሰጠቱን የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በደሴ ከተማ አስተዳደር በአምስቱም ክፍለ ከተሞች የ"ስማር ሲቲ" ፕሮጀክት ዛሬ ተጀምሯል፡፡ የአማራ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የቻለ ይግዛው በማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት ላይ እንዳሉት፤ በክልሉ ከተሞችን በማዘመንና አሰራራቸውን በቴክኖሎጅ በማገዝ ፈጣንና ፍትሃዊ አገልግሎት እንዲሰጡ እየተሰራ ነው፡፡ ለዚህም የ"ስማር ሲቲ" ፕሮጀክት ዛሬ በደሴ ከተማ መጀመሩን አብስረዋል። ባህር ዳርን ጨምሮ በክልሉ ስምንት ከተሞችም በቅርቡ እንደሚጀመር አመላክተዋል፡፡ “አሰራሩ ከተለመደ አሰራርና ከወረቀት መረጃ አያያዝ በመውጣት በቴክኖሎጂ ወደ ዲጅታል የሚቀይር እንዲሁም የከተሞችን ደህንነት፣ እድገት፣ መሬት አያያዝ፣ አገልግሎት አሰጣጥና ሌሎችም የሚያሻሻል ነው” ብለዋል፡፡ “ህብረተሰቡና ተቋማት መንግስት የሚጀመረውን አሰራር በመከተልና በመደገፍ የክልሉን ሁለተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል” ሲሉም አክለዋል። የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው፤ በከተማው ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል፣ የከተማውን ሁለተናዊ እድገት ለማፋጠን፣ አገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ ለማስደገፍና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዛሬ የ"ስማር ሲቲ" አዲስ የቴክኖሎጂ አሰራር መጀመሩን ገልጸዋል፡፡ አሰራሩ አስፈላጊው ዝግጅትና ግብዓት ተሟልቶ መጀመሩን ጠቁመው፤ ቀደም ብሎ በአንድ ክፍለ ከተማ የተካሄደው ሙከራ ውጤታማ መሆኑን መረጋገጡን አብራርተዋል። በዚህም መሰረት ዛሬ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የ"ስማር ሲቲ" ፕሮጀክት እንዲጀመር መደረጉን ተናግረዋል። “ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመቀናጀት የከተማውን ሁለተናዊ እድገትና የቴክኖሎጂ አሰራር ውጤታማ ለማድረግ የድርሻችንን እንወጣለን” ያሉት ደግሞ የኢትዮ-ቴሌኮም ሰሜን ምስራቅ ሪጅን ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ ማስረሻ ገበየሁ ናቸው፡፡ አሰራሩ መሰረተ ልማቶችን ለማፋጠን፣ አሰራሩን ለማዘመንና ለዜጎች ፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችል ጠቁመው፤ “ በተሻለ በኢንተርኔት ዳታና ቴክኖሎጂ ለማስደገፍ ሪጅኑ የራሱን ዝግጅት አድርጓል” ብለዋል፡፡ በማስጀመሪያ ስነ ስርአት ላይ የክልልና የከተማ አመራር አባላት፣ የተለያዩ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡
ባለፉት ዘጠኝ ወራት 3 ሺህ 400 የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች ምዝገባ ተካሂዷል
Apr 29, 2024 112
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 21/2016(ኢዜአ)፡- ባለፉት ዘጠኝ ወራት 3 ሺህ 400 የአዕምሯዊ ንብረት ምዝገባ ማካሄዱን የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን አስታወቀ። ባለሥልጣኑ በ2018 በጀት ዓመት የ11 ሺህ 500 የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች ምዝገባ በማካሄድ መብቶች እንዲጠበቁ ለማድረግ እየሰራ መሆኑንም አስታውቋል። የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወልዱ ይመስል ለኢዜአ እንዳሉት፤ ባለሥልጣኑ የአዕምሯዊ ንብረት የፓተንት፣ የመገልገያ ሞዴል፣ ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ፣ የንግድ ምልክት እንዲሁም የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ ላይ እየሰራ ይገኛል። ባለፈው በጀት ዓመት 3 ሺህ መብቶች የመጠበቅ ሥራ መሠራቱን ጠቅሰው፤ ዘንድሮ ለ4 ሺህ 500 መብቶች ለመጠበቅ መታቀዱን ተናግረዋል። በዘንድሮ በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት የ3 ሺህ 400 የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች ምዝገባ መካሄዱንም ተናግረዋል። በቀጣይ አመታት መብቶች የማስጠበቅ አቅምን በማሳደግ በ2018 በጀት ዓመት ለ11 ሺህ 500 የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች ጥበቃ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል። ባለሥልጣኑ የፓተንት፣ የንግድ ምልክት እና የቅጂና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ የሚመሩበት ሦስት አዋጆች አፈጻጸም ደካማ እንደሆነም ተናግረዋል። የኅብረተሰብ ግንዛቤ ማነስና ፈጠራን ለማበረታታት የሚወሰዱ የፖሊሲ አቅጣጫዎች ውጤታማ ያለመሆን ለአፈጻጸሙ ማነስ ምክንያት መሆናቸውን አብራርተዋል። አዋጆቹ ዘመኑን በሚመጥን አግባብ እየተሻሻሉ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ግብርናን መሠረት ያደረጉ የፈጠራና የባህል መብቶች የሚጠበቁበት ሕግ እየተረቀቀ መሆኑንም ገልፀዋል። በኢትዮጵያ ከ30 ሺህ በላይ የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች ተመዝግበው ጥበቃ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ።
ስፖርት
የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ይካሄዳል
Apr 28, 2024 126
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20 /2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ይካሄዳል:: የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና መካከል ዛሬ ይደረጋል። የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ከቀኑ 9 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይከናወናል። ሀዋሳ ከተማ በሩብ ፍጻሜው አርባ ምንጭ ከተማን 2 ለ 0 እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና ፋሲል ከነማን 4 ለ 1 በማሸነፍ ለግማሽ ፍጻሜው ማለፋቸው ይታወቃል።   በአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ የሚመራው ሀዋሳ ከተማ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎች ቤንች ማጂ ቡና እና መቻልን አሸንፏል። ክለቡ በኢትዮጵያ ዋንጫ እስከ አሁን ባደረጋቸው 3 ጨዋታዎች 7 ግቦችን ከመረብ ሲያሳርፍ 1 ጎል አስተናግዷል። ተጋጣሚው ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ በዚህ ውድድር አስቀድሞ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ወልዲያ እና ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማን ማሸነፉ ይታወቃል።   በአሰልጣኝ ነጻነት ክብሬ የሚመሩት ቡናማዎቹ በውድድሩ ባደረጓቸው 3 ጨዋታዎች 10 ጎሎችን ሲያስቆጥሩ የተቆጠረባቸው 1 ግብ ብቻ ነው። የሁለቱ ክለቦች አሸናፊ ከወላይታ ድቻ በፍጻሜው የሚገናኝ ይሆናል። በኢትዮጵያ ዋንጫ ትናንት በተደረገው የመጀመሪያ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ኢትዮጵያ መድንን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለፍጻሜ ማለፉ ይታወቃል።   የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ በቀጣዩ ዓመት በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን ወክሎ ይሳተፋል።  
የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ ይካሄዳሉ 
Apr 27, 2024 154
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 19/2016(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋሉ። የመጀመሪያው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በወላይታ ድቻ እና ኢትዮጵያ መድን መካከል ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ይከናወናል። በሩብ ፍጻሜው ወላይታ ድቻ ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 1 እንዲሁም ኢትዮጵያ መድን አዳማ ከተማን 3 ለ 1 በማሸነፍ ለግማሽ ፍጻሜ ጨዋታው ቀርበዋል። ወላይታ ድቻ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር ደሴ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕናን ማሸነፉ ይታወቃል። ክለቡ በኢትዮጵያ ዋንጫ ባደረጋቸው 3 ጨዋታዎች 10 ግቦችን ሲያስቆጥር 4 ግቦችን አስተናግዷል። ተጋጣሚው ኢትዮጵያ መድን በበኩሉ በውድድሩ የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎች ድሬዳዋ ከተማ እና አርሲ ነገሌን አሸንፏል። ኢትዮጵያ መድን እስከ አሁን በኢትዮጵያ ዋንጫ ባደረጋቸው 3 ጨዋታዎች 7 ጎሎችን ከመረብ ጋር ሲያገናኝ 3 ግቦችን አስተናግዷል። በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ወላይታ ድቻ በ28 ነጥብ 11ኛ፤ ኢትዮጵያ መድን በ22 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በሌላኛው የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ መርሐ ግብር ነገ ሀዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም እንደሚደረግ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የፍጻሜው ጨዋታ የሚደረግበት ቀንና ቦታ በቀጣይ ይፋ እንደሚሆንም ፌዴሬሽኑ ገልጿል። የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ በቀጣዩ ዓመት በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን ወክሎ ይሳተፋል። የኢትዮጵያ ዋንጫ በኮቪድ-19 ወረርሽኝና በተለያዩ ምክንያቶች ላለፉት አራት ዓመታት ሳይካሄድ የቆየ ሲሆን በዚህም ምክንያት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ የሚያጠናቅቀው ቡድን ኢትዮጵያን ወክሎ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሲሳተፍ ቆይቷል።        
አካባቢ ጥበቃ
በክልሉ በየጊዜው ያለአግባብ የሚወገዱ የፕላስቲክ ምርቶች በሰውና እንስሳት ጤና ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት የማስቀረት ተግባር ይጠናከራል
May 1, 2024 65
ጅግጅጋ ፣ሚያዚያ 23/2016 (ኢዜአ)፡- በሶማሌ ክልል በየጊዜው ያለአግባብ የሚወገዱ የፕላስቲክ ምርቶች በሰውና እንስሳት ጤና ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት ለማስቀረት ቅንጅታዊ ስራን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተመለከተ። በሶማሌ ክልል በየጊዜው ያለ አግባብ የሚወገዱ የፕላስቲክ ምርቶች በአርብቶ አደሩ የቤት እንስሳት ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት፣ የአካባቢ መጎሳቆል እና የአፈር ለምነት ማሳጣት የሚያስከትለው ጉዳት የሚዳሰስ ፓናል ውይይት በጅግጅጋ ከተማ ዛሬ ተካሂዷል።   በክልሉ የአካባቢ ጥበቃና ገጠር መሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ሙህየዲን አብዲ፤ በክልሉ ለስድስት ወር የሚቆይ የአፈር፣ የአየር፣ የውሃ ብክለትንና የድምፅ ሁከትን ለመከላከልና ለመቀነስ የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወነ ናቸው። በክልሉ በተቀመጠው እቅድ መሰረት ፕላስቲክ የሚያደርስውን ብክለት ለመከላከል በክልሉ አምስት ከተሞች ህብረተሰብን ያሳተፈ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መካሄዳቸውን ተናግረዋል። "በጅግጅጋ የተዘጋጀው ውይይትም ፕላስቲክ ምርቶች የአርብቶ አደሩ ህብረተሰብ የኢኮኖሚ መሰረት የሆነውን የቤት እንስሳት ከጉዳት ለመታደግ ያለመ ነው" ብለዋል። የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር በየቀኑ ከሚወገደው የደረቅ ቆሻሻ መካከል አብዛኛው ያለ አግባብ የሚጣሉት ፌስታሎች እና ሌሎች የፕላስቲክ ምርቶች መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጂነር ሻፊ አህመድ ናቸው። በከተማው በየቀኑ ከሁለት ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የፕላስቲክ ውጤቶች እንደሚወገዱ ተናግረዋል ። ከመኖሪያ ቤቶችና ከንግድ ተቋማት በተለያየ መልኩ ጥቅም ላይ ውለው ያለ አግባብ የሚጣሉ የፕላስቲክ ምርቶች በከተማው የጎርፍ መውረጃ ቱቦ በመዝጋትና የአካባቢውን ውበት በማጥፋት የሚያደርሱት ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል። "በክልሉ ከተሞች ያለ አግባብ የሚወገዱና በየቦታው የሚጣሉ ፌስታሎችን የተመገቡ ከብቶች ለሞት እየተዳረጉ ነው" ያሉት ደግሞ የክልሉ አርብቶ አደር ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር መሀመድ ገዓል ናቸው።   በቅርቡም በጅግጅጋ እንስሳት በሽታዎች ላብራቶሪ ባለሙያዎች በአንድ ከብት የሆድ እቃ ከፍተኛ መጠን ያለው ፌስታል በቀዶ ህክምና መውጣቱን ለአብነት አንስተዋል። የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መሀመድ አያንሌ በበኩላቸው፤ የፕላስቲክ ውጤቶች በእንስሳትና በሰው ጤና ላይ የሚያስከትሉትን ችግር ለማስወገድ ተቀናጅቶ መስራት ተገቢ መሆኑን አመልክተዋል ።   በመድረኩ ላይ የተገኙት አገር ሽማግሌዎቹ መካከል አቶ አብዲናስር መሀመድ፤ "ከከተሞች የሚወገዱ ቆሻሻዎች የአርብቶ አደሩን እንስሳት በመጎዳት በህብረተሰቡ የጤናና ኢኮኖሚ አደጋ እፈጠሩ ነው" ብለዋል። የችግሩን ስፋት ለአርብቶ አደሩ ለሌላው ህብረተሰብ ለማስገንዘብ እንደሚሰሩም ተናግረዋል ። መድረኩ ላይ የሀይማኖት አባቶች፣ አገር ሽማግሌዎች ፣ የመንግስት ሰራተኞችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።  
ጽዱ አካባቢ የመፍጠርና ብክለትን የመከላከል ሥራ ስኬታማ እንዲሆን ሁሉም ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ
May 1, 2024 46
ሆሳዕና ፣ሚያዚያ 23/2016 (ኢዜአ)፡- ጽዱ አካባቢ የመፍጠርና ብክለትን የመከላከል ሥራ ስኬታማ እንዲሆን የሁሉም ርብርብ አስፈላጊ መሆኑን የኢፌዴሪ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ደንና አካባቢ ጥበቃ ልማት ቢሮ "ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የፅዳት ዘመቻ ዛሬ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል።   የኢፌዴሪ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ለማ በወቅቱ እንዳሉት ጽዱ አካባቢ የመፍጠርና ብክለትን የመከላከል ሥራ የሁሉንም ዜጋ ርብርብ ይጠይቃል። በተለይ በቆሻሻ አወጋገድና አያያዝ ችግር የተነሳ የሚከሰት የአካባቢ ብክለት ምርታማነትን ከመቀነስ ባለፈ በጤና ላይ የሚፈጥረው አሉታዊ ጫና ከባድ መሆኑን አስረድተዋል። በመሆኑም እንደሀገር ችግሩን ለማስቀረት መላውን ህዝብ ያሳተፈ ንቅናቄ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው ንቅናቄው ስኬታማ እንዲሆን ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ብለዋል። ባለስልጣኑ የአካባቢ ብክለት የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ከማስገንዘብ ጀምሮ የተዘጋጁ አዋጆች እንዲተገበሩ እየተጋ መሆኑንም አመልክተዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ኃላፊና የርዕሰ መስተዳድር ተወካይ አቶ ሰማን ሽፋ በበኩላቸው የአካባቢ ብክለት ምርትና ምርታማነትን መቀነስን ጨምሮ የተለያዩ ችግሮችን እንደሚያስከትል ተናግረዋል። በተለይ የምግብ ዋስትናና ጤና አጠባበቅ ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ጫና ከባድ መሆኑን ጠቅሰው ችግሩን በተቀናጀ መንገድ ለመከላከል እንሰራለን ብለዋል። የክልሉ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ከብክለት በመታደግ ጽዱና ለኑሮ ምቹ አካባቢን ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዙም አሳስበዋል። "አካባቢን በአግባቡ ባለመያዝ ምክንያት በሚከሰቱ ችግሮች የተነሳ የሰው ልጆች ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ተግዳሮት ውስጥ ወድቋል" ያሉት ደግሞ የክልሉ ደን አካባቢ ጥበቃ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሃም መጫ ናቸው። ኃላፊው እንዳሉት በክልሉ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል ማህበረሰቡን ያሳተፉ የጽዳት ዘመቻዎችና ከማድረግ ባለፈ ተሳትፎን የሚያጠናክሩ አስገዳጅ መመሪያዎች እየተዘጋጁ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ሁሉም የክልሉ ነዋሪ የፕላስቲክ ውጤቶችና ለአካባቢ ብክለት አስተዋጾ ያላቸውን ቁሶችንና ቆሻሻዎችን በአግባቡ በማስወገድ እንዲሁም የመኖሪያና የሥራ አካባቢዎችን ንጹህ የማድረግ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል። በፅዳት ዘመቻው ከተሳተፉት ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ የሺ አበበ፣ ጽዱ አካባቢን ለመፍጠር በተጀመረው ንቅናቄ ደስተኛ መሆናቸውንና ለስኬቱም የበኩላቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል። የጽዳት ሥራ ከራስ ቤትና አካባቢ ይጀምራል ያሉት ነዋሪዋ፣ ከብክለት የፀዳ አካባቢን መፍጠር ጤናማ ትውልድን ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል። በተለይ ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻዎችን በመለየትና አወጋገዱን በማዘመን ለአካባቢያችን ጽዳት የሚጠበቅብንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል። በጽዳት ዘመቻው ላይ የክልልና የሆሳዕና ከተማ አመራሮች እና ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።  
በምሥራቅ ወለጋ ዞን የአትክልትና ፍራፍሬ፣ የደን ሽፋንና የእንሰሳት መኖ ችግኞች ተዘጋጁ
May 1, 2024 70
ነቀምቴ፤ ሚያዝያ 23/2016 (ኢዜአ)፦ በምሥራቅ ወለጋ ዞን በመጪው ክረምት አርንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የሚተከሉ የአትክልትና ፍራፍሬ፣ የደን ሽፋንና የእንሰሳት መኖ ችግኞች መዘጋጀታቸውን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ። የፅህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ አስፋው ሀምቢሳ እንደገለጹት፣ በዞኑ ባሉ ሁሉም ወረዳዎች የችግኝ ዝግጅት በስፋት እየተካሄደ ነው። እየተዘጋጁ ከሚገኙ ችግኞች መካከል ከሌላው ጊዜ በተለየ ለምግብነት ለሚውሉ የችግኝ አይነቶች ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል። ከችግኞቹ መካከል በአብዛኛው አትክልትና ፍራፍሬ፣ ለደን ሽፋን፣ ለእንሰሳት መኖና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ዛፎች መሆኑን ተናግረዋል። የተዘጋጁት ችግኞች ለህብረተሰቡ የዕለት ፍጆታ እንዲውሉና የገበያ መረጋጋትን እንዲፈጥሩ ጭምር ታስቦ መሆኑን ተናግረዋል። ችግኞቹ እየተዘጋጁ ያሉት በሁለት ሺህ ችግኝ ማፊያ ጣቢያዎች ሲሆን ከዚህ ውስጥ 64 የመንግስት ችግኝ ማፍያ ጣቢያ ሲሆን የተቀረው የግለሰቦች ችግኝ ጣቢያዎች መሆኑን ገልጸዋል። እስካሁን በአጠቃላይ ለመጪው ክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ562 ሚሊዮን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል። ከዚህ በፊት የተተከሉትን የመንከባከብ ስራም ጎን ለጎን እየተሰራ ሲሆን ይኸም የአካባቢን የአየር ንብረት ከመለወጥ ጀምሮ ብዙ ጠቀሜታ እያስገኘ ነው ብለዋል። ከአረንጓዴ አሻራ ተጠቃሚ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችም ከራሳችን አልፈን ለልጆቻችን የሚተርፍ ስራ በመስራታችን ለቀጣዩ ሥራ መነሳሳት ፈጥሮልናል ብለዋል። ከነዋሪዎቹ መካከል አቶ ሁንዴ ዳበና እንዳሉት እንደ ሀገር በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ምክንያት ችግኝ ሲተልኩ መቆየታቸውን ተናግረዋል። አቶ መልካሙ ገመዳ፣ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ችግኞችን መትከል ከጀመሩ በኋላ ብዙ ጥቅም እና ለውጥ ማየታቸውን ተናግረው ከዚህ በፊት የተተከለውን ከአካባቢው ነዋሪ ጋር ሆነው እየተንከባከቡ ይገኛሉ። የከብት መኖን ጨምሮም የአየር ንብረቱ ተስተካክሎ ለእርሻ ምቹ ሁኔታ መፍጠር መቻሉን አክለው ''ለወደፊቱም ይበልጥ እንድንሰራ አነሳስቶናል'' ብለዋል።
ቆሻሻና የፕላስቲክ ውጤቶች በአግባቡ በማስወገድ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የበኩላችንን እንወጣለን
Apr 30, 2024 86
ሀዋሳ ፤ ሚያዝያ 22/2016 (ኢዜአ)፡- ከየቤቱ የሚወጣውን ቆሻሻና የፕላስቲክ ውጤቶች በአግባቡ በማስወገድ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የበኩላቸውን እንደሚወጡ በሀዋሳ ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ገለጹ። በሀገር አቀፍ ደረጃ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የተጀመረው ንቅናቄ በክልሎች፣ በከተማ አስተዳደሮችና በተለያዩ የዞን መዋቅሮችም እየተካሄደ ነው። በሀዋሳ ከተማም ንቅናቄው የተጀመረ ሲሆን አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች እንዳሉት ከየቤቱ የሚወጣውን ቆሻሻና የፕላስቲክ ውጤቶች በአግባቡ በማስወገድ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የድርሻቸውን ይወጣሉ። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል የመሃል ክፍለ ከተማ ነዋሪው አቶ ዲላ አሻንጎ የአካባቢ ብክለት ጤናን ከማወክ ጀምሮ የከተማ ገጽታ ስለሚያበላሽ ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ሃላፊነት መወጣት አለብን ብለዋል፡፡ ለዚህም ከየቤት የሚወጣው ቆሻሻና የፕላስቲክ ውጤቶችን በአግባቡ ከማስወገድ በተጨማሪ ለይቶ በማስቀመጥ የጽዳት ስራ ማገዝ ይገባናል ብለዋል። ለዚህም ግንዛቤ ከማስጨበጥ ጀምሮ ለአካባቢ ብክለት የሚያጋልጡ ተግባራትን የሚፈጽሙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ በማድረግ ጭምር ለአካባቢያቸው ንጽህና እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። የኩል ፕላስቲክ ሪሳይክሊንግ ኢንተርፕራይዝ ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሰላማዊት ቶማስ በበኩላቸው ከስድስት ዓመት በፊት ተደራጅተው የጀመሩት ስራ የአካባቢ ብክለትን በመከላከል የበኩሉን ድርሻ እያበረከተ ነው ። በተለይም ከኢንዱስትሪዎች፣ ከተቋማትና ከየቤቱ የሚወገዱ የፕላስቲክ ውጤቶችን መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውሉ በማድረግ የአካባቢ ብክለትን ከመቀነስ ባሻገር የስራ እድል መፍጠራቸውን ገልጸዋል። ፕላስቲኮችን መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውሉ በማድረግ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት ስራንም እያከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም ከተማዋን ከብክለት ለመከላከል የሚሰራውን ስራ በማገዝ የድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑን ገልጸው ህብረተሰቡ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓቱን እንዲያዘመን የተጀመረው የንቅናቄ ስራ መጠናከር አለበት ብለዋል። ሀዋሳ ከተማን ጽዱ፣ውብና ምቹ ለማድረግ የሚከናወነው የጽዳት ስራ ውጤታማ እንዲሆን የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓቱን ማስተካከል ይገባል ያለው ደግሞ የባህል አዳራሽ ክፍለ ከተማው ወጣት እስራኤል ሸከካ ነው።   በሚኖርበት ክፍለ ከተማ እስከ ቀበሌ በቆሻሻ አወጋገድ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ስራ እንደሚሰሩ ገልጾ ንቅናቄው ውጤታማ እንዲሆን አጠናክረን እንቀጥላለን ብሏል። ማህበረሰቡ ከቤቱ ከሚያወጣው ቆሻሻ ጀምሮ የፕላስቲክ አጠቃቀሙን ቢያስተካክል ችግሩን መቀነስ እንደሚቻልም ተናግሯል። የጤና ባለሙያዋ ሲስተር ሲሳይ ፈለቀ በበኩሏ የአካባቢ ብክለት በአየር ንብረት ለውጡ ላይ የሚያስከትለው ተጽእኖ ከፍተኛ በመሆኑ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እየተበራከተ መምጣቱን ገልጸዋል። ችግሩ ዓለም አቀፍ ትኩረት የሚጠይቅ ቢሆንም ለመፍትሔው የእያንዳንዱ ግለሰብ አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይ የፕላስቲክ አወጋገዳችንን በማስተካከል ጤናችንን መጠበቅ ይገባናል ነው ያሉት። የተጀመረው የንቅናቄ መድረክም የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጅ ውስጥ የሚተገበረውን የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት የሚያግዝና ለውጥ የሚያመጣ በመሆኑ በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል። የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር "ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ" በሚል በመሪ ሐሳብ ለቀጣይ ስድስት ወራት በተቀናጀ መንገድ የሚተገበር ንቅናቄ መጀመሩ ይታወሳል።  
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል- አንቶኒዮ ጉተሬዝ
Apr 15, 2024 1259
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- አለም ተጨማሪ ጦርነት እንድታስተናግድ እድል ባለመፍጠር በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አሳሰቡ። ኢራን እስራኤል ከሳምንታት በፊት ሶርያ በሚገኘው ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ጥቃት አድርሳብኛለች በሚል ባሳላፍነው ቅዳሜ ሌሊት መጠነ ሰፊ ጥቃት መሰንዘሯ በተለያዩ የዓለም መገናኛ ብዙሃን መዘገቡ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ በቀጣናውና በአለም ሀገራት የተፈጠረውን ከፍተኛ ውጥረት ለማርገብ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የጸጥታ ምክር ቤቱን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል። በስብሰባውም አለም ተጨማሪ ጦርነት የምታስተናግድበት ምንም አይነት አቅም ስለሌለ ሀገራት በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። ችግሩ በቸልታ የሚታይ ከሆነ አስከፊ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል መናገራቸውን ያስነበበው ፍራንስ 24 የጸጥታው ምክር ቤት አባላት ሁኔታውን በአስቸኳይና ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ሊያስቆሙት እንደሚገባ ማሳሰባቸውንም ዘግቧል።
በሞዛምቢክ በደረሰ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ
Apr 8, 2024 2155
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2016(ኢዜአ)፦በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል የባህር ዳርቻ በተከሰተ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ። በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው ናምፑላ ግዛት 130 የሚሆኑ ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ መስጠሟን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ነዋሪዎቹ በግዛቷ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ በመሸሽ ወደ ሌላ አካበቢ ለመሄድ በጀልባ በተሳፈሩበት ወቅት አደጋው እንደተከሰተ የገለጹት ባለስልጣናቱ ጀልባዋ መሸከም ከምትችለው የሰው መጠን በላይ በመጫኗ አደጋው እንደደረሰ አመልክተዋል። በዚህም ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይታቸው እንዳለፈ ማረጋገጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። በአሁኑ ወቅት አምስት ሰዎችን ከአደጋው በሕይወት ማትረፍ እንደተቻለ ያመለከተው ዘገባው ተጨማሪ ሰዎችን ለማዳን ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስነብቧል። የናምፑላ ግዛት ባለፈው አመት በሞዛምቢክ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ ክፉኛ ከተጎዱ አካባቢዎች መካከል አንዷ መሆኗም በዘገባው ተመላክቷል።
የአየር ንብረት ለውጥና መዘዙ
Apr 5, 2024 1467
በዓለማችን ላይ እየተስተዋለ ያለው የአየር ንብረት ለውጥ የተወሳሰበ ችግር እያስከተለ ከመሆኑ በተጨማሪ በስነምህዳር ላይ እያደረሰ ያለው አደጋ ሊቀለበስ ወደ ማይችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑን ሞደርን ዲፕሎማሲ ድረገጽ አስነበበ። ድረ ገጹ በዓለማችን በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የአየር ንብረት ለውጥ በሚያስከትለው ድርቅ፣ ጎርፍ እና ተዛማጅ በሆኑ ክስተቶች ምክንያት ቀያቸውን ጥለው ለመሰደድ እንደሚገደዱ አስነብቧል። የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በይነመንግስታት ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው አሁን ላይ ያለው የዓለማችን የሙቀት መጠን ወደ 1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴሊሺየስ እየተጠጋ በመምጣቱ በስነምህዳር፣ በከባቢ አየር እና በአካባቢ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እየተስተዋለ መሆኑን ገልጿል። የአየር ንብረት ለውጥ ለዘላቂ ልማት እንቅፋት በመሆን ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ክስተቶች የሚፈጥራቸውን ችግሮች በማባባስ ለሰዎች መፈናቀልና የህይወት መጎሳቆል እያደረሰ ይገኛል። እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 በማዕከላዊ አሜሪካ እና ደቡባዊ ሜክሲኮ የተከሰተው ሃሪኬን ኤታ የተባለው የአየር ንብረት ለውጥ ክስተት ያስከተለው የሰብል ውድመትና የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ የደረሰው አደጋ ከባለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ውስጥ እጅግ የከፋ አደጋ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። በዚህም በጎርፍ፣ በመሬት መንሸራተትና በሰብል ውድመት ምክንያት ከ1 መቶ 20 ሺህ በላይ ሰዎችን ከሞቀ መኖሪያቸው ተፈናቅለው እርዳታ ጠባቂ እንዳደረጋቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽንን መረጃ ዋቢ አድርጎ አትቷል። የአየር ንብረት ለውጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን የጠቆመው ድረ ገጹ በቀጣይ ተመሳሳይ ችግሮች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉም አመልክቷል። በአውሮፓውያኑ 2022 ወደ 32 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተፈናቀሉ ሲሆን፤ ይህ አሃዝ በ2008 ከተከሰተው በ41 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ዘገባው አመልክቷል። ይህም የዓለማችን የሙቀት መጠን እየጨመረ መምጣቱን እንጂ ምንም ዓይነት የመቀነስ አዝማሚያ ያላሳየ መሆኑን ያመለከተው ዘገባው በቺሊ፣ ካናዳ፣ ዛምቢያ፣ ሞዛምቢክ፣ ሜክሲኮ፣ ኢክዋዶር፣ ሊቢያ እና በሌሎችም አገራት ሃሪኬን በተሰኘው የአየር ለውጥ፣ በሰደድ እሳት፣ በጎርፍ እና በድርቅ ምክንያት ለባለፉት በርካታ ወራት መፈናቀልን እንዳስከተለ ተገልጻል። የአለም ባንክን የትንበያ መረጃ ዋቢ ያደረገው ድረ ገጹ በአውሮፓውያኑ 2050 ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ 216 ሚሊዮን ሰዎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ተመላክቷል። ድረገጹ ይሄ ክስተት የሚያስከትላቸው ችግሮች እንዳይቀጥሉ መቆጣጠር ካስፈለገ ዘላቂ ልማት ላይ ያተኮሩ ግንዛቤን የሚያሳድጉ ትምህርቶች፣ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ እውነተኛ ውይይቶች እና ተፈጥሮን መሰረት ያደረጉ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ በማሳሰብ መሪዎች የሚጠበቅባቸውን ሊተገብሩ ይገባል ሲል ምክሩን አስቀምጧል።  
ሐተታዎች
ነገረ - አስተውሎት
Apr 24, 2024 202
ሰው በሀሳብ ከሕይወታዊያን ፍጥረት ይለያል። ከፍጥረቱ ጀምሮ ኑሮውን ቀላል ለማድረግ አስቧል። ሀሳቡም መላ ፈጥሯል። ድንጋይ አፋጭቶ እሳትን አንድዷል። እንስሳትን አላምዶ፣ ሰብልን አባዝቶ፣ መጠለያውን ቀልሶ… ኑረቱን አሳልጧል። ዕለታዊ ተግባሩን ለማቃለል በቁስ ላይ ተመራምሮ አጋዥ ቁስ ፈጥሯል። በሂደትም የኢንዱስትሪን አብዮት አፈንድቷል። በ18ኛው ክፍለ ዘመን በባተው የኢንዱስትሪ አብዮት ዓለም አዲስ ክስተት አስተናግዳለች። ፋብሪካዎች፣ መኪናና አውሮፕላን፣ የእንፋሎትና የኤሌክትሪክ ኃይልና የኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂዎች ተፈብርከው ምርትና ምርታማነት ጨምሯል። ከተሜነት አብቧል። የዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ አውቶሜሽን፣ ሮቦቲክስና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች በሰው ተፈጥረዋል። ሳይንስን ለመፍትሔ-እንከን አውሏል። ቴክኖሎጂን ለሁለንተናዊ ሕይወት ማቃለያ ተጠቅሟል። ጊዜ፣ ጉልበትና ሀሳብን ከፈጠራ ጋር አዋዶ ኑሮና ሕይወት አቅልሏል። ኮምፒዩተር ፈበረከ፤ ኢንተርኔትን ፈጠረ፣ ዓለምን አስተሳሰረ። የተዓምር ዘመን ሆነ። ሰው እያስተዋለ... እያስተዋለ… በረቀቀ ጥበብና ግኝት ዛሬ ከዘመነ-አስተውሎት ደረሰ። ሰው ሰራሽ አስተውሎት!! የዘመኑ ቴክኖሎጂ ልህቀት ደረጃ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ) እንደሆነ ይጠቀሳል። ዳሩ የቴክኖሎጂው እምርታ የዘመን ክስተት ሳይሆን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በፊት ጀምሮ እርሾ ሲያቦካ እንደነበር የዘርፉ ምሁራን ይጠቅሳሉ። ዋረን ማክኩሎች እና ዋልተር ፒትስ ለዛሬው ሰው ሰራሽ አስተውሎት እርሾ የሆነ በነርቭ አውታረ መረብ የሚታገዝ ሒሳባዊ ሞዴል የፈጠሩት በ1943 ዓ.ም ነበር። በ1950 ዓ.ም ደግሞ አለን ተርኒግ እንደ ሰው ማሰብ የሚችል ማሽን ፈለሰፈ። በተመሳሳይ በ1960ዎቹ አጠቃላይ ችግር ፈቺ፣ ሎጂክ ቴዎሪስትና መሰል የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፕሮግራሞች በልፅገዋል። በ1950 ዓ.ም ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ራሱን ችሎ እንዲጠና ተወሰነ። ለውስብስብ ችግሮች አይነተኛ መፍትሄ መሆኑ ታመነበት። በ1970 እና 80ዎቹ የዘርፉ ሊቃውንት የሰውን ልጅ የመወሰን አቅም የሚተካ የኮምፒውተር ፕሮግራም ለማበልጸግ ጥረት አድርገዋል። በ1990ዎቹ ምርምሮቹ መቀዛቀዝ ጀምረው ነበር። በ21ኛው ክፍለ ዘመን ዳግም አንሰራርቷል። ስልተ ቀመርን (algorithm) የሚረዱ ማሽኖች ስራ ላይ ውለዋል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት የጥናት ዘርፍ የሰውን ስራና ሃሳብ በኮምፒዩተር መራሽ ቁሶች መተካት ነው። የሰው ልጅ ፍጥረት የሆኑ ማሽኖች መገንዘብ፣ መማርና ችግሮችን እንዲቀርፉ ማስቻልም ነው። ማሽኖች በሰው ልጅ ምትክ አካባቢን ማመዛዘን፣ መማር፣ ማቀድና መፍጠር፣ መተንተንና እንከኖችን ማምከን እንዲችሉ ማድረግ ነው። የሰውን የማሰብ ኅይል በኮምፒዩተር አዳብሮ በሰውኛ ጥበብ ሕይወትን ማቅለል ነው። አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሰው ልጅ ያሉትን የስሜት ህዋሳት ክህሎቶች ለማሽኖች በማስተማር ሰዎች ነገሮችን በቀላሉ እንዲያገኙና እንዲተገብሩ ማስቻል ነው። በዚህም የኮምፒውተር ሊቃውንት ስልተ ቀመር ወይም አልጎሪዝምና አስበው የሚሰሩ ማሽኖች ወደ ስራ እያስገቡ ነው። ለአብነትም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ጥበብ ቤት የሚያጸዱ ሮቦቶች፣ አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪዎች፣ ሰው አልባ ጦር መሳሪያዎች፣ የደህነንት ጥበቃ ካሜራዎች፣… በልጽገው ስራ ላይ ውለዋል። በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ የተጀመረው ይህ ቴክኖሎጂ ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተስፋም ስጋትም ይዞ መምጣቱ ይነገራል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት ዛሬ ላይ በሁሉም መስክ ገቢራዊ እየተደረገ ነው። በትምህርት፣ በኢንዱስትሪ፣ በጤና፣ በደህንነት፣ በግብርና ዘርፎች ምርትና አገልግሎትን ለማቀላጠፍና ለመጨመር ቁልፍ አማራጭ ተደርጓል። ቴክኖሎጂው ከዓለም ገበያ ከ350 ቢሊዮን ዶላር በላይ ድርሻ አለው። አፍሪካም እያደገ የመጣውን ዓለም አቀፍ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ገበያ 10 በመቶ ድርሻ መያዝ ከቻለች እኤአ 2030 አሁን ያለው አህጉራዊ ጥቅል ምርቷ (ጂዲፒ) 50 በመቶ ይጨምራል። ኢትዮጵያ ከአራት ዓመታት በፊት ዘርፉን የሚመራ ተቋም መስርታለች፤ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን። ኢንስቲትዩቱ ኢትዮጵያን በአፍሪካ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ምህዳር ተጠቃሽ ሀገር ለማድረግ አበክሮ እየሰራ ነው። በቅርቡ የተመረቀው “አስተውሎት” የተሰኘ ፊልም ደግሞ ለዚህ ሁነኛ ማሳያ ነው። ሰው ሰራሽ አስተውሎት በሰው ልጅ የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ የማይገባበት ሕይወት እንደሌለ ፊልሙ ያስረዳል። በጤና፣ በማሕበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም፣ በመረጃ ፍለጋ፣ በፖለቲካ፣ በትምህርት፣ በኢኮኖሚ፣ በግብርና፣ በማዕድን ፍለጋና፣ በአገልግሎት አሰጣጥ የዚህ ቴክኖሎጂ ቁልፍ ሚና ተንጸባርቋል። ዘርፉ ከቅንጦት ይልቅ አስፈላጊነቱ ጨምሯል። ለበሽታ መከላከል፣ ለጤና እንክብካቤ፣ ለትምህርት መሻሻልና ድህነት ቅነሳ ይውላል። ለዚህም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ የተመሰረቱ መተግበሪያዎች ፈጠራና አቅም እያደገ መምጣቱ በፊልሙ ተገልጿል። ፊልሙ የኢትዮጵያ የቡና ዛፎችን የበሽታ ስርጭት ለይቶ ለማከም ያለውን ውጤታማነት ያወሳል። ሰው ሠራሽ አስተውሎት የአገራችንን ሉዓላዊነት በማስከበር ረገድ የሳይበር ደህንነትን ለመጠበቅ፣ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ፣ ምርታማነትን ለመጨመር፣ ገበያን ለማስፋት እና ለመሳሰሉት ሥራዎች በእጅጉ አስፈላጊ ነው። በአሁኑ ወቅት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ እየተስፋፉ ከሚገኙ አገልግሎቶች መካከል ማሽን ትራንስሌት ወይም የቋንቋ ትርጉም አንዱ ሲሆን በኢትዮጵያም አንዱን ቋንቋ ወደ ሌላ በመተርጎም አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። በዚህም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትም በአንድ መተግበሪያ የተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን መማር እንዲሁም ከድምጽ ወደ ጽሁፍ መቀየር የሚያስችል ሥርዓትን አበልጽጎ ለተጠቃሚዎች አቅርቧል። መተግበሪያው አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሶማሊኛ እና ትግርኛ ቋንቋዎችን በድምጽ እና በጽሁፍ ለመማር የሚያስችል ሲሆን ድምጽን ወደ ጽሁፍ መቀየር የሚያስችለው የመተግበሪያው አካል ድምጽን በመቅዳት ወይም ከመዛግብት (አርካይቭ) የድምጽ ፋይሎችን ወደ መተግበሪያው በማስገባት የጽሁፍ ቅጂውን ለማግኘት የሚያስችል መሆኑን ከፊልሙ መገንዘብ ተችሏል። በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የደረሰበትን ልህቀት ያማከሉና ከዘርፉ ውጤት ለማግኘት በአጭር ጊዜ ውስጥ የተኬደው ርቀት ይበል የሚያሰኝ ነው። ነገር ግን በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ የመጣውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ልህቀት በመመልከት ሀገራችንን የሚመስሉ የዘርፉን ውጤቶች የበለጠ ማላቅ ያስፈልጋል። በዓለም የዕለት ተለት እንቅስቃሴ ውስጥ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እያሳደረ የሚገኘውን ተጽዕኖ በመረዳት ለዘርፉ ምርምሮች የሚደረገውን ድጋፍ የበለጠ ማጠናከር ያሻል። ዓለም የሚሄድበትን ፍጥነት በመመልከት ሀገራችንን የሚመስሉ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ውጤቶችን ለመተግበር በትኩረት መሥራት ያስፈልጋል። (በሰለሞን ተሰራ)      
ብሩህ ነገን የሰነቁ እንስቶች
Apr 19, 2024 466
የሰው ልጆች ከፍጥረት እስከ ዕለተ ሞት ባሉት የሕይወት ዑደቶች ውስጥ በሚገጥሟቸው መልከ ብዙ ፈተናዎች ሳቢያ ራሳቸውን ለቀቢጸ ተስፋ ይዳርጋሉ፤ ተገደውም ወደ ማይፈልጉት ሕይወት ይገባሉ። በተለይም ሴቶች በሚገጥሟቸው አይነተ ብዙ ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ጫናዎች ሳቢያ በበርካታ የህይወት ውጣ ውረድ ወስጥ ያልፋሉ፤ በሂደቱም ለአካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት የተዳረጉ በርካቶች ናቸው፡፡ ለአብነትም በአዲስ አበባ ተወልዳ ያደገችው ቃልኪዳን በላይነህ (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) በወጣትነቷ ትዳር መስርታ፣ልጆችን ወልዳ ለመሳም በቅታለች፡፡ ዳሩ ግን ባለቤቷ በድንገተኛ አደጋ በመሞቱ ምክንያት ህጻን ልጆቿን ይዛ ለአስከፊ የኢኮኖሚ ችግር መዳረጓን ትናገራለች። በዚህም ራሷንና ልጆቿን ህይወት ለማቆየት ወደ ማትፈልገው የወሲብ ንግድ ሕይወት ውስጥ ለመግባት መገደዷን ነው የገለጸችው፡፡ በህፃንነት ዕድሜ ለአካል ጉዳተኝነት የተዳረገችው ሳምራዊት (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) በበኩሏ በአካል ጉዳተኝነቷ ምክንያት ተንቀሳቀሳ መስራት ባለመቻሏ ከተወለደችበት ገጠራማ ስፍራ ወደ አዲስ አበባ መምጣቷን ትናገራለች፡፡ በአዲስ አበባም ህይወቷን በልመና ስትመራ ቆይታለች፡፡ ሌላኛዋ ባለታሪካችን ሔዋን (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) ወደ ማትፈልገው ህይወት ውስጥ ስትገባ የሚያጋጥማት ማህበራዊ ፣ አካላዊ ጥቃት እና ስነልቦናዊ ጫና ቀላል አይደለም ትላለች። እሷም ኑሮን ለማሸነፍ የገባችበት የህይወት መስመር ወደ አላስፈላጊ ሱስ ውስጥ እንድትገባና ለስነ ልቦናዊ ቀውስ እንድትጋለጥ እንዳደረጋት ገልጻለች። መንግስት በመሰል ችግር ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ለመደገፍ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከዚህም ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ለመታደግ የሚያስችልና “ለነገዋ” የተሰኘ የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል አንዱ ነው፡፡ ማዕከሉ ለተለያዩ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ችግሮች የተጋለጡ ሴቶችን በስነ ልቦና የምክር አገልግሎት እና በተለያዩ ሙያዊ ስልጠናዎች በመስጠት ብሩህ ነገን ለማቀዳጀት ስራ ጀምሯል። እነ ቃልኪዳን፣ ሳምራዊት፣ ሔዋንና ሌሎች በችግር ውስጥ የነበሩ ሴቶችም ‘የነገዋ’ የተሰኘውን የተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከልን ተቀላቅለው የተሻለ ነገን ለመኖር ተስፋ ሰንቀዋል፡፡ በማዕከሉ በሚሰጣቸው ሙያዊ ስልጠናና የምክር አገልግሎትም ወደ ተረጋጋ መንፈስ እንዲመለሱ፣ የሕይወት ተሞክሮ እንዲቀስሙ፣ ነጋቸውን ለማሳመር እንዲነሳሱ ስለማድረጉም ይናገራሉ። ማዕከሉ በአዲስ አበባ መከፈቱ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ሴቶች ትልቅ ብስራት መሆኑን ገልጸው፤ መሰል ማዕከላትም በአገር አቀፍ ደረጃ ሊስፋፋ እንደሚገባ ጠቁመዋል።   “የነገዋ” የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሄርጳሳ ጫላ ማዕከሉ ወደ ስራ ከገባ አንድ ወር በላይ ማስቆጠሩን አስታውሰው፤ 500 ሴቶችን ተቀብሎ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ሰልጣኞች ከማዕከሉ ሲወጡ ራሳቸውን በኢኮኖሚ እንዲችሉ የሚያደርግ በልዩ የክህሎት፣ የስነ ልቦና እና የሙያ በአጠቃላይ በ18 አይነት የስልጠና ዘርፎች እያሰለጠነ መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ስፌት፣ ስነ ውበት፣ የምግብ ዝግጅት፣ የከተማ ግብርና፣ የሕጻናት እንክብካቤና ሌሎች ዘርፎች ከሶስት ወር እስከ ስድስት ወር እንደሚያሰለጥን ነው የገለጹት። ከስልጠናው በኋላ ለሰልጣኞች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠርም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር ማዕከሉ በትብበር እየሰራ መሆኑም ተናግረዋል፡፡ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማእከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር) መጋቢት 05 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ለአገልግሎት ከፍት መሆኑ ይታወሳል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ''እራትም... መብራትም'' የመሆን ጅማሬ
Apr 14, 2024 1603
ሲሳይ ማሞ (ከአሶሳ) ያኔ! 2003 ዓ.ም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ የተነገሩ ተስፋዎች የማየፈቱ ህልሞች ብለን ስንቶቻችን አስበናቸው ይሆን? በአካባቢው ሊኖር ስለሚችለው ታላላቅ ክስተቶች፣ ስለሚፈጠሩት መልካም ነገሮች በሰማንበት ቅጽበት በህልም ዓለም ውስጥ እንዳለን ስንቶቻችን አስበን ይሆን? "አዬ ህልም!?" በሚል ሲደርስ እናየዋለን በሚል ቀናት ቆጥረናል። ያኔ! ነገሮች ሲነሱና ሲተረኩ ስንቶቻችን እንሆን እዚህ ቀን ላይ ደርሰን እናይ ይሆን!? የሚል ሃሳብ በእዝነ ህሊናችን የተመላለሰው? ያኔ! የታላቁ ህዳሴ ግድቡ ሲጠናቀቅ ወደ ኋላ ከ240 በላይ ኪሎ ሜትሮችን የሸፈነ ውሃ ሐይቅ ሰርቶ ተንጣሎ እንደሚተኛ እያለምን መጩውን ዘመን በጉጉት የጠበቅን ስንቶቻችን ነን? ግድቡ ግንባታው ሲገባደድ አገር የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨት በዘለለ "ከሰው ሰራሽ ሐይቁ በሚወጣ ዓሳ ሌላ የገቢ ምንጭ ይፈጠርላታል፤ በሚፈጠረው ሰው ሰራሽ ሃይቅ ላይ የጀልባ ትራንስፖርትና የመዋኛ አገልግሎቶች ይጀመራል" የሚሉት መረጃዎችንና ትንታኔዎችን ከመገናኛ ብዙሃኑ ስንሰማ እንደርስ ይሆን? የሚል ጥያቄ ወደ አእምሯቸው ያልመጣ ቢኖሩ ጥቂቶች ሳይሆኑ አየቀሩም። ያኔ! እንደትንቢት የተነገረው ዛሬ ጊዜው ሲደርስ "ይሆናል" የተባለው ከጊዜ ወደ ጊዜ "እየሆነ" መጣ። ስለታላቁ ግድብ በህልም ደረጃ ሲገለፁ የነበሩ በዕውን ወደማሳየቱ እየተንደረደረ ይገኛል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር የተያያዘ ገጠመኜን ጀባ ልበላችሁ! ዕለቱ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ከማለዳው 12 ሰዓት ነው፡፡ አፍንጫዋ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የሰካች አንድ የሞተር ጀልባ ከደቡብ ወደ ሰሜን የተንጣለለውን ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ ለሁለት እየከፈለች ትጓዛለች ከማለት ትበራለች ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ሰው ሰራሽ ሐይቁ ውሃውን እንደልቧ እየቀዘፈች ለመጓዝ አስችሏታልና! ከምዕራብ በኩል የኮርቻ ግድብ (Saddle dam) ተጠማዞ እና በኩራት ደረቱን ገልብጦ ይታያል፡፡ በስተምስራቅ አቅጣጫ ላይ የሚገኘው የግድቡ ሃይቅ ደግሞ ለስለስ ያለ ሃምራዊ ቀለም ለተመላካቹ ያሳያል። የማለዳዋ የፀሐይ ጨረር ያረፈበት የውሃው ክፍል ለእይታ ባያስቸግርም ገና ከማለዳው ከአካባቢው ሞቃታማ አየር ጋር ተዳምሮ ወላፈን የሚመስል ሙቀቱን መርጨት ጀምሯል፡፡ ከፊት ለፊታችን ደግሞ በረጅም ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያቆረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ ፊት ለፊት ተንጣሎ ይታያል፡፡ የተሳፈርንባት የሞተር ጀልባ ስምንት ያህል መንገደኞችን ይዛለች፡፡ በሰው ሰራሽ ሐይቁ ላይ የሚደረግ ጉዞ ለተጓዡ ሐሴትን ጀልባዋን ለሚዘውራት ከዕለት ገቢ የዘለለ ተድላን እንደሚለግስ አያጠራጥርም። የአካባቢውን ድባብ እየተመለከትን ጉዟችንን ቀጠልን። በጉዞው ቅፅበትም ዓይኖቻችን በአንድ ወጣት አሳ አስጋሪ ላይ አረፉ። ወጣቱ በጀልባዋ ላይ ሆኖ በአንደኛው አቅጣጫ በኩል አጎንብሶ በመንጠቆ ያጠመዳቸውን ግዙፍ አሳዎችን አጥብቆ እየያዘ ወደ ጀልባዋ ይጨምራል። ከአቅሙ በላይ ሆነው ሊያመልጡት የሚታገሉ አሳዎችን ደግሞ በብረት አንካሴ ወገባቸውን እየወጋ ለመያዝ ይታገላል፡፡ ተጠግተን ለመርዳትና አሳዎቹን በመያዝ ለማገዝም ሆነ ሌላ ድጋፍ ለማድረግ አልደፈርንም፡፡ ወጣቱ ግዙፍ አሳዎቹ ጋር የገጠመውን ግብግብ በካሜራ ለማስቀረት ጥረት ማድረጉን ግን አልዘነጋሁትም። ወጣቱ ኢትማን መሃመድ ይባላል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የጉባ ወረዳ ነዋሪ ነው፡፡ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ሐይቅ ላይ አሳ የማስገር ስራ ከጀመረ ወራት አስቆጥሯል፡፡ “ቤተሰቦቼ እንደነገሩኝ ከ13 ዓመት በፊት ግድቡን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ አሁን በሞተር ጀልባ የምንጓዝበት ሃይቅ ይፈጠራል የሚል እምነት በአካባቢው ነዋሪዎች እሳቤ ውስጥ ፈጽሞ አልነበረም።” ሲል ይናገራል ወጣቱ፡፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሃይቅ ለእርሱ እና ለሌሎች ከእርሱ ጋር ለተደራጁ 25 ወጣቶች የሥራ እድል በር መክፈቱን አጫወተኝ፡፡ ከታላቁ ግድብ ያገኙት ትሩፋት እርሱ እና የማህበሩ አባላት በአገራቸው ላይ ሰርተው የመለወጥ ተስፋቸውን በእጅጉ እንዳለመለመላቸው አጫውቶኛል፡፡ ከዚህ ቀደም በአካባቢው ከሚገኙ ወንዞች አሳ ቢያመርቱም በህዳሴው ግድብ አማካኝነት ከተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ የሚያገኙት ግን በዓይነትም በመጠንም የተለየ እንደሆነ ይናገራል። ከሐይቁ እስከ 50 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ነጫጭና ሌሎች ዓሳዎችን እያሰገረ መሆኑን በአድናቆት ጭምር ይገልፃል። ማህበሩ በቀን እስከ ሁለት ኩንታል ወይም ሁለት መቶ ኪሎ ግራም ገደማ ዓሳ ያመርታል፡፡ “የህዳሴው ግድብ የምግብ ዋስትናም ፤ የገቢ ምንጭም ሆኖናል” ሲልም ወጣቱ ሃሳቡን ቋጭቷል። ለሰዓታት በቆየሁበት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ የአሳ ማስገር እንቅስቃሴ ላይ ኢትዮጵያውያን በአንድነት መንፈስ ከገነቡት ግድብ የስራ ዕድል ተጠቃሚ የመሆን ጅማሬን ይስተዋላል። ነገሩ እንዲህ ነው! በባህር ዳር ጣና ሃይቅ ላይ ያካበተውን የአሳ መረብ አሰራር እና የሞተር ጀልባ አጠቃቀም ልምድ ለማካፈል ወደ ስፍራው ያቀናው ወጣት የሻምበል ወርቁ በማህበር ተደራጅተው አሳ ለሚያሰግሩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ወጣቶች ስልጠና ሲሰጥ ማግኘቴ ቀደም ብዬ የጠቀስኩትን መረጃ እውነታነት ያሳያል። “አንዱ ወንድሜ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ይሄም ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እኔም ከአማራ ክልል ነኝ፡፡ ሁላችንም እኩል የግድቡ ትሩፋት ተጠቃሚ ነን፡፡ ከዚህ ቀደም በአካል የማንተዋወቀውን ኢትዮጵያውያንን ግድቡ አስተዋውቆናል” ብሎኛል የሻምበል። ሌላው የመንጠቆ አጣጣል ስልጠና ለመስጠት ከአርባምንጭ ተጉዞ ወደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ መጥቶ ያገኘሁት ደግሞ ወጣት አልማው ደሳለኝ ነው። ''ለአካባቢው ወጣቶች ልምዴን እና ያለኝን ዕውቀት በማካፈሌ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ'' የሚለው ወጣቱ፤ በሃይቁ ላይ የተመለከተው ከፍተኛ የአሳ ሃብት እንደ እርሱ ያሉ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በመጥቀም ለአገሪቷም የተሻለ ገቢን ሊያመጣ እንደሚችል ያምናል። “ተባብረን በመስራት አገራችንን እንለውጣለን” በማለት ህብረትና አንድነት ከድህነት ለመውጣት የሚያስችል ዘመኑ የሚፈልገው ታላቅ መሳሪያ መሆኑን ያምናል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ...ተብለው ሲነገሩ የነበሩ የወደፊት ትልሞች አሁን እውን ሆነው 'ስራን ለሰሪው....ፍፁማዊ የገፅታ ለውጥን ለአካባቢው መልክዓ ምድር እንዲሁም ሰፊ የቱሪዝምና ሌሎች የስራ መስኮችን ለሚመለከተው አካል ለመስጠት የተግባር ጅማሬ እየታየ ነው። በግድብ ግንባታው የመሰረት ድንጋይ ማኖር ወቅት "በይሆናል" ሲባሉ የነበሩ ዕቅዶች እውን ወደ መሆን...ወደ መጨበጥ እየመጡ መሆናቸው ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው። ለኢትዮጵያውያን የ”ይቻላል” ተምሳሌት የሆነው ግድብ ዋነኛ በይበልጥ ሲጠቀስ ከነበረው የኃይል አቅርቦት ባሻገር ለዜጎች ሌላ የስራ መስክ በመፍጠር ' እራትም መብራትም' ሆኖ እስከመጨረሻው ሊዘልቅ እነሆ ውጤቱን እያሳየ ነው። እንግዲህ የነገ ሰው ብሎን ትሩፋቱን በይበልጥ ያሳየን !!  
በህብር የተገነባ ገድል
Mar 25, 2024 2504
  "የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም የትውልድ አሻራ ደምቆ የተፃፈበት የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። ይህ ቀን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት የረባ ጥቅም ሳይሰጥ ወደ ጎረቤት አገራት ሲፈስ የኖረውን የአባይ ወንዝ ወደ ብርሃን ለመቀየር በቁርጠኝነት በመነሳት የማይቻልን ነገር በይቻላል ወኔ በመቀየር ለዓለም ያሳዩበት፤ ዓለም የተደመመበት ቀን ነው። የግድቡ ግንባታ በተጀመረበት ወቅት በርካታ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያ ይህን ግዙፍ ፕሮጀክት ታሳካው ይሆን? የሚል ጥርጣሬ አዘል ርእስ የያዘ ተከታታይ ዘገባ አስነብበዋል። ኢንተርናሽናል ሪቨርስ የተሰኘው ድረ ገጽ በፈረንጆቹ 2011 ‘Can Ethiopia Afford the Grand Renaissance Dam?’ በሚል ርእስ ባወጣው ሰፋ ያለ ዘገባ ግድቡን ለመገንባት ከሚያስፈልገው ጠቅላላ ገንዘብ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ሊያዋጡ የሚችሉት በጣም ጥቂቱን ብቻ በመሆኑ ግንባታው ሊሳካ አይችልም በሚል ትንበያውን አስቀምጦ ነበር። የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገው ግሪን ፕሮፊት የተሰኘ ድረ ገጽ የግድቡን ግንባታ አስመልክቶ ‘Defiant Ethiopia is proceeding with its plan to build the Grand Millennium Dam on the Nile River, but what kind of dam can they build without cash flow? ..... there’s one important problem: Ethiopia lacks the necessary funds to see the project to completion. In fact, they can barely get it off the ground.’ በማለት ኢትዮጵያ ግድብ መገንባት የሚያስችል ገንዘብ ስለሌላት ፕሮጀክቱ ሊተገበር አይችልም ሲል ደምድሟል፤ ተሳልቋልም። በወቅቱ የዚህ ዓይነት ግምት የብዙዎቹ ተንታኞች መንደርደሪያ ነበር። “ኢትዮጵያ ደሃ አገር ስለሆነች ከዓለም አቀፍ ተቋማት ብድር ካልተገኘ በስተቀር ፕሮጀክቱ ወደ ፍፃሜ መድረስ አይችልም” የሚል ድምዳሜ ለመስጠት ተንታኞቹ ብዙም አይቸገሩም ነበር። ‘ግድቡ የጥራት ችግር ስላለበት ይደረመሳል’ ከሚለው ዘመቻ ጀምሮ በግድቡ ላይ ጥቃት እንደሚፈጸምበት ተደጋጋሚ የዛቻና የማስፈራሪያ መልእክቶች ተስተጋብተዋል። በጥቅምት ወር 2013 ዓ. ም የቀድሞ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በህዳሴ ግድብ ግንባታ ግብጽ ተጎጂ እንደሆነች አቋም በመያዝ "ግብፅ በዚህ መንገድ መቀጠል ስለማትችል ሁኔታው አደገኛ ነው፤ ግብፅ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳለች፤ አሁንም በግልፅ እናገረዋለሁ ግብፅ በድጋሚ ታፈነዳዋለች" የሚል ጠንከር ያለ የዛቻ መልእክት አስተላልፈዋል። ኢትዮጵያውያን ውኃ ወደ ናይል እንዳይፈስ የሚያቆም ግድብ ገንብተዋል ሲሉ የገለጹት ትራምፕ ግብጽ ትንሽ በመበሳጨቷ ልትወቅሷት አትችሉም ሲሉም አክለዋል። "ግብፅ የህዳሴ ግድብ እንዲገነባ መፍቀድ አልነበረባትም፤ የስምምነት ሀሳብ ለአገራቱ ባቀርብም ኢትዮጵያ ስምምነቱን ሳትቀበል ቀርታለች። እንደዚያ ማድረግ አልነበረባቸውም ይህ ትልቅ ስህተት ነው። በዚህም ምክንያት የምንሰጣቸውን ብድር አቁመናል። ስምምነቱን ካልተቀበለች በስተቀር ኢትዮጵያ ገንዘብ አታገኝም " ብለዋል። አትዮጵያ የህዳሴ ግድብን ለመገንባትና ዳር ለማድረስ ብድርና ዕርዳታ እንዳታገኝ የተለያዩ ኃይሎች ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። በዚህም ምክንያት የፕሮጀክቱን ወጪ ለመሸፈን የሚተባበር አገር ወይም ተቋም ማግኘት አልተቻለም፡፡ ስለሆነም የነበረው አማራጭ አንድም ግድቡን አለመሥራት፣ አለበለዚያ ወጪውን በራስ አቅም መሸፈን ነበር፡፡ ከእነዚህ ከባድ ሁለት አማራጮች መካከል የኢትዮጵያ ሕዝብ ምርጫ ወጪውን በራሱ አቅም በመሸፈን መስዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን በተግባር አረጋገጠ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነበር ኢትዮጵያውያን ገጠር ከተማ ሳይሉ፤ በአገር ውስጥና በውጭ ከጫፍ እስከ ጫፍ በእልህና በቁጭት በመነሳሳት ግድቡን በራሳቸው አቅም ገንብተው ዳር ለማድረስ ቃል ኪዳን ያደረጉት። ለግንባታው የሚውል ድጋፍ በገንዘብና በዓይነት በተለይም የቦንድ ሽያጭ፣ በ8100 አጭር መልእክት እና በእጣ አገልግሎት ህዝቡ ተረባረበ፤ የማይቻለውን እንደሚቻል ለዓለም አሳየ። በበርካታ ፈተናዎችና ጫናዎችን ሳይበገር ግንባታው የቀጠለው የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት የሲቪል ስራው 99 በመቶ መድረሱንና የኤሌክትሮ ሜካኒካል በተለይም የተርባይንና ጄኔሬተር ተከላ ሥራው 78 በመቶ መጠናቀቁን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባት ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት በቅርብ ያወጣቸው መረጃዎች ያመለክታሉ። ከለውጡ ማግስት ጀምሮ መንግስት ልዩ ትኩረት ከሰጣቸው ፕሮጀክቶች መካከል የህዳሴው ግድብ ቀዳሚው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ "የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" በማለት አረጋግጠዋል። በዚህም ኢትዮጵያ ከግድቡ ግንባታ ጋር የተያያዙ ውስጣዊና ውጫዊ ጫናዎች ቢኖሩባትም የግድቡን ሥራ ለአፍታም አላቋረጠችም። በአሁኑ ወቅት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አፈፃፀም ከ95 በመቶ በላይ መድረሱን የሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል። ዘንድሮ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መሠረት ድንጋይ የተጣለበትን 13ኛ ዓመት ይከበራል፤ መሪ ሀሳቡም "በኅብረት ችለናል!" የሚል ሲሆን ኢትዮጰያውያን ችለው ያሳዩበት ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። እዚህ ድል ላይ የተደረሰው በመንግሥት ቁርጠኛ አቋምና የዲፕሎማሲ ጥረት እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ነው። ባለፉት 13 ዓመታት ኢትዮጵያውያን ለግድቡ ግንባታ 18 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል። በኢትዮጵያውያን ያልተቋረጠ ተሳትፎ ተጀምሮ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ሊጠናቀቅ ወራቶች የቀሩት ይህ ታላቅ አገራዊ ፕሮጀክት የአገሪቱን የኃይል ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ ከማሻሻሉም ባሻገር ለጎረቤት አገራት ተደራሽ በማድረግ ቀጣናውን በማስተሳሰር በኩል ሚናው ከፍተኛ ነው።  
ትንታኔዎች
መልከ ብዙው የ"ዳሞታ ተራራ"
Apr 23, 2024 273
የዳሞታ ተራራ ወላይታዎች የሚታወቁበት የራሳቸው የሆነ ባህል፣ ቅርስ እንዲሁም መለያ ምልክት ነው። ዳሞታ የወላይታ የልምላሜ መገለጫና የተፈጥሮ መስህብ ነው። ተራራው በወላይታ ሶዶ ከተማ ዙሪያ በሚገኝ 12 ሺህ 500 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በ32 ምንጮችና በ12 ጅረቶች ታጅቦ በኩራት ተንሰራፍቶ የሚገኝ የአካባቢው ማህበረሰብ መጠሪያ ነው። ከዚህ የተነሳ የወላይታ ሶዶ ከተማን ተፈጥሮ ካደላት የዳሞታ ተራራ ሞገሷ የተነሳም ተራራው ፀዳሏ ነው ብለው የሚጠሩትም አልጠፉም። የዳሞታ ተራራ ለአካባቢው ነዋሪም ሆነ አካባቢውን ሊጎበኙ ለሚመጡ እንግዳ ተቀባይነቱን በአረንጓዴ የተፈጥሮ መስህቦቹ በማሸብረቅ ውበቱን በመግለፅ የሚያሳይ ተራራ ነው። ተራራውን ወደ ላይ ለሚመለከተው ዳሞታ ብዙ የሚያሳየውና የሚነግረው ታሪክ እንዳለው ያሳብቃል። የታሪክ ድርሳናት እንደሚያስረዱት የዳሞታ ተራራ ለ800 ዓመታት ገደማ የቆየ ታሪካዊ የመስህብ ስፍራ ነው። በጥቅጥቅ ደኖች፣ በወራጅ ወንዞችና ጅረቶች፣ ለመድኃኒትነት በሚያገለግሉ ቁጥር ስፍር በሌላቸው የእፅዋት ዘሮችም የተሸፈነ ነው። በወላይታ ዞን እምብርት በወላይታ ሶዶ ከተማ ሰሜናዊ አቅጣጫ ከፍታ ላይ የሚገኘው የዳሞታ ተራራ ከፍታው ከባህር ጠለል በላይ 3000 ሜትር እንዲሁም የዙሪያ ልኬቱ ከ68 ኪሎ ሜትር በላይ እንደሆነም ይነገራል። በአንድ ወቅት ተራራው በአካባቢ መራቆት፣ በአየር ሚዛን መዛባትና በሌሎች ምክንያቶች ግርማውንና ልምላሜውን እያጣ መጣ። ይህም የወላይታን ህዝብ በማሳሰቡ ሁሉም የአካባቢው ማህበረሰብ ልጅ አዋቂ ሳይል ርብርብ በማድረግ ወደ ቀደመ አቋሙና ሙላቱ ለመመለስ ብርቱ ተፈጥሮን የመከላከል ፍልሚያ አደረገ። ፍልሚያውም በአካባቢው ማህበረሰብ አሸናፊነት በመጠናቀቁ ተራራው ልምላሜውን ጠብቆ አሁን የተላበሰውን ግርማ እንዲይዝ በማድረግ ሊያጣው የነበረውን ጥቅጥቅ ደን በመመለስ የመሬት መሸርሸርን ከመከላከልና የመንገድና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ከመጠበቅ አልፎ ትልቅ የአይበገሬነት ታሪክ እንደፃፈም ይወሳል። ለዚህም ነው ዳሞታን ከወላይታዎች ማህበረሰቡን ከተራራው ለመለየት እንደማይቻልና ጠንካራ ተዛምዶን የመሰረቱ መሆናቸው የሚገለፀው። የወላይታ ዞን የሀገር ሽማግሌ አቶ አብርሃም ባቾሬ እንደሚሉትም ዳሞታ በርካታ የቱሪስት መስህቦች፣ ታሪካዊ ቅርሶች፣ የሀገር በቀል እፅዋት፣ የዱር እንስሳትና ጥንታዊ የወላይታ ነገስታት መናገሻ ስፍራዎች ባለቤት ነው። የዳሞታ ተራራ ከወላይታ ህዝብ ታሪክና ጀግንነት እንዲሁም ከአሸናፊነት ወኔው ጋር የተቆራኘ ስለመሆኑም ያነሳሉ። በዙሪያው ዘመናትን ያስቆጠረ የጥቅጥቅ ደንና የነገስታት መኖሪያ እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናትና አድባራት የሚገኙበት መሆኑን አንስተው ለወላይታ ሶዶ ከተማም የተለየ ግርማ ሞገስን እንዳላበሳት ተናግረዋል። በዳሞታ ተራራ ዙሪያ የተኮለኮሉት ወንዞችም መነሻቸውን ከተራራው በማድረግ ወደ ታች እየተገማሸሩ ይነጉዳሉ። ወይቦ፣ ቁሊያ፣ ካልቴ ቶቦቤ፣ ሀመሳ፣ ሊንታላ፣ አይከሬ፣ ዋላጫ፣ ጫራቄ፣ ቦልዖ፣ ካዎ ሻፋ፣ ጋዜና ሻፋና ሌሎች ወንዞች ከዚሁ ተራራ ተጎራብተው፣ ከተራራው ያገኙትን መዳኛ ፀበል ለሌሎች ለማቋደስ አየተንደረደሩ ይወርዳሉ። ለአካባቢው ማህበረሰብም ልምላሜያቸውን ያጋባሉ፤ ብርቱውን መሬቱን ምሶ ገበታውን እንዲያበለፅግ ያተጋሉ። ሁሉም ግን የዳሞታ መልዕክተኞች፣ የዳሞታ ተጧሪዎች ናቸው። እንደ አቶ አብርሃም ገለፃ በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ገደማ የክርስትና ሀይማኖትን በአካባቢው በማስፋፋት ስመ ገናና የሆኑት አቡነ ተክለሃይማኖት ክርስትናን ለመስበክና መንፈሳዊ ክዋኔዎች ለመፈጸም ዳሞታ ተራራን ይወጡ እንደነበረ ከልጅነታቸው ይነገራቸው እንደነበር ያስታውሳሉ። ይህ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የመንፈሳዊ አገልግሎቶችን ሲያከናውኑ ድካም ሲሰማቸው እረፍት የሚያደርጉበት ለመንፈስ ሃሴትን የሚያጎናፅፍ ስፍራ ነው የዳሞታ ተራራ። በዚህ ምክንያት "ጦሳ ፔንጊያ" የእግዜር መተላለፊያ የተሰኘ ስያሜ የተሰጠውና "ጣዛ ጋሯ" የንጉስ ሞቶሎሚ ቤተ-መንግስት፣ የንጉስ ሞቶሎሚ የጥምቀት ሥፍራ፣ ቆሊ ቦርኮታ፣ ዳጌቾ፣ ቦቄና ሶዶ፣ ጦማ ገሬራና ሌራቶ ጎዳ የተሰኙ ታሪካዊና የሚጎበኙ ስፍራዎች ይጎበኙበታል በዳሞታ ተራራ። ካዎ ሞቶሎሚ፣ ካዎ ዳሞቴ፣ ካዎ ጎቤና ካዎ ጦና የሚባሉ የወላይታ ነገስታት ቤተ-መንግስታቸውን በተራራው አናትና ግርጌ ላይ ይገነቡ እንደነበር አቶ አብርሃም ይናገራሉ። የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ፣ የዳሞታ ተራራ በወላይታ ህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ታሪክ ውስጥ ደማቅ አሻራ ያለው መሆኑን ይገልፃሉ። ከተራራው አናት መነሻቸውን የሚያደርጉ ወንዞች የወላይታን ምድር አጥግበው ሰዎችና እንስሳቱን አጠጥተው ወደ ብላቴ እና ኦሞ ወንዝ ይፈሳሉ። የዳሞታ ተራራ ሌላው ጠቀሜታው መሬት እንዳይሸረሸር ቀጥ አድርጎ በዛ ግዝፈቱ ይዟል ይሄም ለመንገድ ደህንነትና የአካባቢውን አየር ተስማሚ ከማድረግ አኳያ አይተኬ ሚና አለው። በጥቅጥቅ ደን የተሸፈነው የዳሞታ ተራራ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ከዘመናት በፊት ተጀምሮበታል ይላሉ አስተዳዳሪው። ንፁህ የመጠጥ ውሃን በከፊል ለሶዶ ከተማ የሚያጠጣውን የዳሞታ ተራራ የቱሪስት ማዕከል ለማድረግ ከዩኒቨርስቲና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ ነውም ብለዋል። የዳሞታ ተራራ ታሪካዊ ይዘቱን ስንመለከት አካባቢው ቀደም ሲል የነገስታት መናገሻ ቦታ ነበር የሚሉት ደግሞ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል ተመራማሪ ዶክተር አበሻ ሽርኮ ናቸው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከወላይታ ሥርወ-መንግስት መካከል ካዎ ሳቴ ሞቶሎሚና የሌሎች ነገሥታት መናገሻ ስፍራ ስለነበር በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ ያለው ታሪካዊ ስፍራ ነው። የዳሞታ ተራራ ለአብዛኞቹ በወላይታ ዞን ለሚገኙ ወረዳዎች የስያሜያቸው መነሻ ነው። ዳሞት ጋሌ፣ ዳሞት ሶሬ፣ ዳሞታ ወይዴ፣ ዳሞት ፑላሳ ወረዳዎችና ሌሎች ቀበሌያት የተራራውን ስም መነሻ ያደረጉ መሆኑ ተራራውን ታሪካዊ ያደርገዋል። እዚሁ ተራራ ላይ ካሉ የተለያዩ መስህቦች መካከል የጥንታዊ ዋሻ "ሞቼና ቦራጎ" ዋሻ አንዱ ነው። ይህ ዋሻ በወላይታ ሶዶ ከተማ በሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ የሚገኝ የጥንት ሰው መኖሪያ ዋሻ ነበር። ዋሻው በዳሞታ ተራራ ከሚገኙ ከአምስት በላይ ዋሻዎች አንዱ ሲሆን በተራራው በስተምዕራብ አቅጣጫ በኩል የሚገኝና ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት ሰዎች በዚሁ ዋሻ ይኖሩ እንደነበረም ታሪክ ያስረዳል። ሞቼና ቦራጎ ዋሻ ስፋቱ 38 ሜትር፣ የጣሪያው ከፍታ 33 ሜትር፣ የዋሻው ዙሪያ ልኬት ደግሞ 58 ሜትር፣ እንዲሁም በውስጡ ከአምስት መቶ በላይ ሰዎች የመያዝ አቅም ያለው እንደሆነም መረጃዎች ያመላክታሉ። ሌላው ከዳሞታ ተራራ መስህቦች መካከል አንዱ የሆነውን ደብረ-መንክራት አቡነ ተክለኃይማኖት ገዳም ላስተዋውቃችሁ። ይህ ገዳም ለአቡነ ተክለኃይማኖት መታሰቢያነት በ1887 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ ከመመስረቱ ጋር በተያያዘ የተገነባና በዳሞታ ተራራ ምዕራባዊ ራስጌ የሚገኝ የቱሪስት መስህብ ሥፍራ እንደሆነ ነው ዶክተር አበሻ የሚናገሩት። ገዳሙ የአምልኮና የፀበል አገልግሎት እየሰጠ ከአንድ ክፈለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ በወላይታ ዞን ካሉ መንፈሳዊ ስፍራዎች አንዱ ሲሆን በውስጡ በርካታ ሐይማኖታዊና ታሪካዊ ቅርሶች ያሉት በመሆኑ በኢትዮጵያ ሐይማኖታዊ ጉዞ ከሚደረግባቸው መዳረሻዎች አንዱ ነው። በመሆኑም አካባቢው ለቱሪስት መዳረሻነት፣ ለአካባቢው ልማት ብሎም ለአየር ንብረት ሚዛንን መጠበቅ ጉልህ ሚና ያለው በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲያደርጉም አሳስበዋል።            
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች
Mar 2, 2024 3873
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች (ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ)   የአድዋ አድማስ ዘለል ገድል ሲወሳ የድሉ መገኘት የጦር አበጋዞች ከፊት ይመጣሉ። ከንጉሠ ነገሥቱ ጀምሮ ራስ፣ ደጃዝማች፣ ፊታውራሪ፣ ቀኛዝማች፣ ግራዝማች፣ ባላምባራስ እና ሌሎች ባለማዕረግ አዋጊዎች የድሉ የጀርባ አጥንት መሆናቸው እሙን ነው። ከመላ ሀገሪቷ ጠረፍ ተነቃንቆ ስንቅና ትጥቁን ታጥቆ፣ ድል ሰንቆ እስከ ግማሽ ዓመት ድረስ በባዶ እግሩ የተመመውን የሀገሬው ሰራዊት በቅጡ መርተው አዋግተዋል። ከመነሻ ሰፈር እስከ አድዋ ተረተር፣ ከአምባላጌ ኮረብቶች እስከ መቀሌ ጋራና ቁልቁለቶች፣ ከእንደአባ ገሪማ እስከ ማሪያም ሸዊቶ ሸለቋማ ቋጥኞች፣ ከምንድብድብ መስክ እስከ በገሠሦ አቆበቶች፣ .... ድልና ገድል በደምና በላብ ሲጻፍ የጠላትን የ'ክዱ' ማባባያ የጠሉ፣ ለሀገር ለመሰዋት የቆረጡ ጀግና አዋጊዎች፣ የሀገር ባለውለታዎች ነበሩ። በአድዋ ድል መታሰቢያ 12 የአድዋ ጦር አበጋዞች (ጀኔራሎች) ሀውልት ቆሞላቸዋል። እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ (አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ (አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። ከነዚህ የአገር ባለውለታዎች መካከል ሁለት ስመ ሞክሼ ጀግኖችን እንዘክራለን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከዳግማዊ አፄ ምኒልክ ቀዳሚዎች ስምንት ራሶች መካከል ብቸኛው የራስ ቢትወደድ (ከንጉሥነት በታች) ባለማዕረግ ናቸው። በፈረስ ስማቸው አባ-ገድብ ይሰኛሉ። በልጅነታቸው የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ባለሟል ሳሉ ከእስረኛው ምኒልክ ጋር ተዋወቁ። ምኒልክ ከአፄ ቴዎድሮስ አምልጠው ሸዋ ከገቡ በኋላ ከእቴጌ ጣይቱ ብጡል ወንድሞች ራስ ወሌ እና ፊታውራሪ አሉላ ብጡልን ይዘው ከመቅደላ ወደ ሸዋ ተሻገሩ፤ የምኒልክ ሁነኛ ሰው ሆኑ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም በሞት እስኪለዩ ድረስ በክፉም በደጉም ዘመን የአጼ ምኒልክ ከፍተኛ አማካሪና ተወዳጅ መስፍን እንደነበሩ፣ ከጦር ሜዳ እስከ ሽምግልናም ሁነኛ ሰው ሆነው ስለማገልገላችው በታሪክ ድርሳናት ተጠቅሷል። በሸዋ፣ ወሎ፣ ጎንደር፣ ዳሞት(ጎጃም) ተዘዋውረው በተለያዩ ግዛቶች በአስተዳዳሪነት ሰርተዋል። ድሕረ መተማ ጦርነት ምርኮኞች እንዲመለሱ፣ ድንበር እንዲካለል በመስራትም የዲፕሎማሲ ስራቸው ይጠቅሳል። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከተሳተፉባቸው ደማቅ ታሪኮች መካከል የአድዋ ድል ይጠቅሳል። ጦርነቱ አሀዱ ብሎ የጀመረው ሕዳር 28 ቀን 1888 አምባላጌ ነው። ለሁለት ሰዓታት በዘለቀው በዚህ ጦርነት ጀኔራል ቶዚሊ የተባለው የጠላት ጦር መሪ የተገደለበት ነው። በዚህ ዐውደ ውጊያ አባ ገድብ አንዱ ወሳኝ የጦር አበጋዝ ነበሩ። በተለያዩ የታሪክ ድርሳናት እንደተመዘገበው ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከግዛታቸው ከዳሞትና አገው ምድር የተውጣጣ ስድስት ሺህ እግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር ይዘው አድዋ ዘምተዋል። “አባ ገደብ መንጌ እያለ ኧረ ጐራው አምባ ላጌን ሰብሮ ቶዘሊን አስጐራው” የተባለው ለዚህ ይመስላል። አባ ገድብ ጥቅምት 11 ቀን 1903 ምሸት ከራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው ጋር እየተጫወቱ ካለምንም ህመም ድንገት አርፈው ቅድስት ሥላሴ ተቀበሩ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ ልጆቻቸውን ከተለያዩ መኳንንት ጋር በጋብቻ በማጣመር በኢትዮጰያ ታሪክ ተጠቃሽ መሆን ችለዋል። ለአብነትም ዘውዲቱ መንገሻ ጠቅላይ ሚኒስትር መኮንን እንዳልካቸውን፣ አስካለማርያም መንገሻ ልዑል ራስ ኅይሉን አግብተው የልጅ ኢያሱን ባለቤት ሠብለወንጌል ኅይሉን ወልደዋል። ደጃዝማች ጀኔራል አበበ ዳምጠውን ያገቡት ወሰንየለሽ መንገሻ ደግሞ የአልጋወራሽ አስፋወሰን ባለቤት ልዕልት መድፈሪያሽ ወርቅ አበበን ወልደዋል። ሌላው የአድዋ ጀግና የጦር መሪ ራስ መንገሻ ዮሐንስ (አባ ግጠም) ናችው። ትውልዳቸው ትግራይ፣ ዘመኑም 1857 ዓ.ም ነው። የአድዋ ጦር ውሎ ቁልፍ ሰው ራስ መንገሻ የአጼ ዮሐንስ (አባ በዝብዝ) ልጅ ናቸው። አጼ ዮሐንስ በተሰዉበት በመተማው ጦርነት ተሳትፈዋል። አባታቸው ከሞቱ በኋላም የትግራይ አገረ ገዥ ሆነዋል። በአድዋ ዘመቻ 12 ሺህ ጦር አሰልፈው በብርቱ ተዋግተዋል። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከአድዋ ጦርነት ቀደም ብሎ በአጼ ምኒልክ ላይ እንዲያምጹ ኢጣሊያኖች ሲገፋፋቸውና ሲያባብላቸው ቢቆዩም ከስልጣን ሽኩቻ ይልቅ የኢትዮጵያን ነጻነት መርጠዋል። ከአጼ ምኒልክ ጋር ቢኳረፉም በሀገር ሉዓላዊነት ግን አልተደራደሩም። የኢጣሊያ ወራሪ ጦር ትግራይ ሲገባም ራስ መንገሻ የወገን ደጀን ጦር እስኪደርስ ወደራያ አፈግፍገው፣ በአምባላጌ ጦር ሜዳ አንዱ ተሳታፊ የጦር ጀግና ነበሩ። ራስ መንገሻ የትግራይ ሀገረ ገዥ በመሆናቸውም የእርሳቸው እና በስራቸው የነበሩት የራስ አሉላ እንግዳ ጦር በጄኔራል አልቤርቶኔ ከሚመራው ጠላት ሃይል ቀዳሚው ተፋላሚ እንዲሆኑ አድርጎታል። “አይከፈት በሩ መግቢያ መውጫችን በል ተነስ መንገሻ ግጠም በር በሩን ይህን ጎሽ ጠላ ማን አይቀምሰው መንገሻ ዮሐነስ አንተን ገፍተው...” ተብሎ የተገጠመላቸውም ለዚህ ነው። የጠላት መግቢያ በር ዘብ በመሆናቸው። አባ ግጠም በአድዋው ታሪካዊ ጦርነት አሰላለፋቸው ማርያም ሸዊቶ በተሰኘው ተራራ በኩል ሲሆን ከራስ አሉላ፣ ከዋግሹም ጓንጉል ብሩና ከደጃዝማች ሀጎስ ጋር በመሆን ነበር። የጠላትን የመጀመሪያ ጥቃትን ያስተናገዱትም ራስ መንገሻ ዮሐንስ ናቸው። የአድዋ ድል ከተበሰረ በኋላ አጼ ምኒልክ ራስ መንገሻን ሹመውና ሸልመው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል። አጼ ምኒልክ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ማህበረሰቡ በጦርነት ስፍራ በመሆኑ ለደረሰበት ጉዳት 30 ሺህ ብር ድጋፍ ማድራገቸውን የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል የጻፉት ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደአረጋይ ተርከዋል። ከአድዋ ድል ከጥቂት ዓመታት በኋላ ራስ መንገሻ በአጼ ምኒልክ ላይ በማመጻቸው ተይዘው በቁጥጥር ስር ዋሉ። ሕዳር 6 ቀን 1899 ዓ.ም አንኮበር ግዞት ላይ አንዳሉ ማረፋቸውን የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከራስ መንገሻ አቲከም ግዛት ከአገው ምድር እመይቴ ተዋበች ጋር ትዳር መስርተው ዕውቁን የትግራይ መስፍን ራስ ሥዩም መንገሻን እንዲሁም ከእቴጌ ጣይቱ የወንድም ልጅ ወይዘሮ ከፈይ ወሌ ብጡል አግብተው አስቴር መንገሻን፣ አልማዝ መንገሻንና ብርሃኔ መንገሻን ወልደዋል፡፡ ለአብነት ያክል የሞክሼዎቹን ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ አነሳን እንጂ የዛሬ የ128 ዓመት በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ የጻፉ ጀግኖች ቁጥር ስፍር የላቸውም። ጀግኖቹን የመሩ የጦር መሪዎችም ብዙና ተጋድሏቸው የገዘፈ ነው። ከ11 ሺህ በላይ የጣሊያንን ሠራዊት ሙትና ቁስለኛ ያደረጉ፣ 4ሺህ የሚሆኑትን እጅ ያሰጡና የማረኩ እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር እንዲያስረክብ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሁል ጊዜም ክብር ይገባቸዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። (በአየለ ያረጋል)      
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች 
Mar 2, 2024 2629
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች ለመነሻ እኤአ በ1885 ጀርመን በተካሄደው የበርሊን ኮንፈረንስ አውሮፓውያን መላ አፍሪካን በካርታ ላይ የተከፋፈሉትን በተግባር መሬት ላይ ለመቀራመት ጦራቸውን ሰብቀው፣ ስንቃቸውን ጭነውና ትጥቃቸውን አጥብቀው ያካሄዱት ዘመቻና የወረራ ጉዞ የተገታባት አድዋ እና እለቷ ዛሬ ድረስ በተገፉ ህዝቦች ልብ ታትማ በአዕምሮ ውስጥ ተቀርጻ ትኖራለች። ጣሊያን የኢትዮጵያን መሬት፣ የአየር ንብረትና መልክዓ ምድር ተቆጣጥሮ ሀብቷን ለሮምና ለመላው አውሮፓ ለማቅረብ የቋመጠበት የዘመናት ህልሙ የተኮላሸበት ቦታ ጭምር ናት - አድዋ። ይህ ወራሪ ኃይል ሊቢያን በእጁ ካስገባ በኋላ ጉዞውን በቀይ ባሕር አስመራ አድርጎ መላ ኢትዮጵያን የመቆጣጠር ግብ ነበረው። ጄነራል ባራቴሪ የመደባቸው ጄነራል አልበርቶኒ፣ ጄኔራል አሪሞንዲ እና ጄነራል ቦርሜዳ በግንባር የተሰለፈውን ጦር ሲመሩ የኋላ ደጀንም እንደነበራቸው የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ከ17 ሺህ በላይ የጣሊያን ሠራዊት 66 የሚሆኑ መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና አውቶማቲክ መሳሪያዎችን ታጥቆ የግንባር ሜዳው ላይ ስለመድረሱ "የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው እስካሁኑ ዘመን" በሚል በአንድርዜይ ባርይትኒስኪ እና ዮዓና ማንቴል-ኒየችኮ ተጽፎ በዓለማየሁ አበበ የተተረጎመው መጽሐፍ ያስረዳል። የዛሬ የ128 ዓመት፤ ዕለቱም የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ በጀግኖች አባቶች ተሰራ። በጦርነቱ የጣሊያን መንግስት የጎመጀውን የኢትዮጵያን መሬት ሊያገኝ ይቅርና ከ11 ሺህ በላይ ሠራዊቱ ሙትና ቁስለኛ ሆኑ። 4ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ለጀግኖች አባቶቻችን እጃቸውን ሰጥተው ተማረኩ። እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር አስረከበ። የቀረው የፋሽስት ሠራዊትም ተንጠባጥቦ እግሬ አውጪኝ ብሎ ፈረጠጠ። ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ክብር፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት በአውደ ግንባሩ በፈጸሙት የጀግንነት ተጋድሎ ዓለምን ያስደመመና መላውን ጥቁር ሕዝብ ያኮራ ድል ተጎናጽፈዋል። በወቅቱ ነጭን ታግሎ ማሸነፍ አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ በይቻላል ተክቶ ሌሎችም ለነፃነታቸው እንዲታገሉ ያነሳሳ ደማቅ የታሪክ አሻራ አኑረዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። ኢትዮጵያውያን በብሔር፣ በሃይማኖት፣ በአካባቢና በሌሎች ልዩነቶች ሳይነጣጠሉ ለአገራቸው ክብርና ነጻነት በአንድነት ቆመውና መስዋት ከፍለው ያስመዘገቡት የጀግንነት ታሪክ ነው። በዓድዋ ድል ኢትዮጵያ ለአፍሪካና ለመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራትና የነፃነት ምልክት ሆናለች፡፡ የሰው ልጆችን እኩልነት በደም ዋጋ አረጋግጣለች።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋ ድል ደማቅና ታላቅ ቢሆንም በሚመጥነው ልክ መታሰቢያ አልነበረውም። ዛሬ ግን እነዚያ ዋጋ የከፈሉ ጀግኖችን በሚመጥን ሁኔታ በአዲስ አበባ ፒያሳ “የዓድዋ ድል መታሰቢያ” ተገንብቷል። ከአድዋ ድል 128 ዓመታት በኋላ፣ የተሰራው የአድዋ ድል መታሰቢያ በጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ተከፍቷል። የአድዋ ድል መታሰቢያ በአምስት ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን በአንድነት የተከፈለውን መስዋትነት፣ የአርሶ አደሮችን ተሳትፎ፣ የሴቶችን ተጋድሎ በሚያሳይ መልኩ፣ በአስገራሚ የኪነ-ህንጻ ጥበብ የታነጸ ነው።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የተገነባበት ስፍራ አገር በውጭ ወራሪ ኃይሎች እጅ እንዳትወድቅ የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ የዓድዋ ጅግኖች የዘመቻቸው መነሻ እንዲሁም ከድል በኋላ ተሰባስበው ደስታቸውን የተጋሩበት ታሪካዊ ስፍራ ነው። የአድዋ ድል በዓል 7ኛ ዓመት ዳግማዊ ምኒልክ፣ ከአርበኞች፣ ከየአካባቢው ገዢዎች፣ ከውጭ አገር ዲፕሎማቶችና ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር በደማቅ ሁኔታ በዚሁ ስፍራ አክብረውታል። ስፍራው ዛሬ የታላቁ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሳይገነባበት በፊት በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ የልማት ስራዎች ቢታጭም ውጤታማ ስራ ሳይሰራበት ቆይቷል። አካባቢው ለረጅም ዘመናት ታጥሮ ሳይለማ በመቆየቱ እጅግ የቆሸሸ፣ ሰዎች ለዝርፊያ የሚዳረጉበት ስፍራ ሆኖ ቆይቷል። ዘመናትን ተሻግሮ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በከተማዋ ከሚገነቡ ትላልቅ ፕሮጀክቶች በዓይነቱ ልዩ የሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እንዲሰራበት ተደረገ። የዓድዋ ድል መታሰቢያ እጅግ በሚስብ ኪነ ህንፃ፤ የኢትዮጵያውያንን ህያው የድል ታሪክ የሚዘክር ሆኖ ተሰርቷል።   የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የኢትዮጵያውያን የድል ብስራት፣ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ኩራት የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የራሳቸው የሆነ ስያሜ ተሰጥቷቸዋል። የምሥራቅ ጀግኖች በር፣ የምዕራብ ጀግኖች በር፣ የሰሜን ጀግኖች በር፣ የደቡብ ጀግኖች በር፣ የፈረሰኞች በር፣ የአርበኞች በር፣ የፓን አፍሪካኒዝም በር ተብለው የተሰየሙ ናቸው። በአራቱም አቅጣጫዎች የተሰየሙ በሮች ተምሳሌትነት በዓድዋ ድል ከአራቱም አቅጣጫ ኢትዮጵያውያን በጋራ የተሳተፉበት የጋራ ድላቸው መሆኑን ያመለክታል፡፡   መታሰቢያው በውስጡ ምን ይዟል? በዋናው መግቢያ:- የኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን ነጻነት ድል መገለጫ የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ ሃውልትና የሁሉም ከተሞች ርቀት ልኬት መነሻ የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ምልክት ይገኛል። የዓድዋ ጦርነት ዘመቻን ያስተባበሩትና የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት የዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና የባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሀውልትም በዚሁ መግቢያ በኩል ይገኛል። ሃውልት የቆመላቸው 12 የጦር መሪዎች:- በመታሰቢያው የአድዋን ጦርነት በታላቅ ጀግንነት በመምራት ለጥቁር ህዝቦች ድል ያበሰሩ 12 ዋና ዋና የጦር መሪዎች ሃውልት ተቀምጧል፣ እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ ( አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ ( አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። በስተቀኝ በኩል፤- እስከ 3 ሺ እንግዶችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት የስብሰባ አዳራሽ የሚገኝ ሲሆን በመጀመሪያው ኮሪደር ላይ ደግሞ ህዝቡ የጦርነት ክተት አዋጅ ጥሪ ሲሰማ ሁሉም ልዩነቱን ወደ ጎን በመተው አገሩን ከወራሪ ለመታደግ በመወኔ መነሳቱን፣ ወደ ጦር ግንባር መትመሙን እንዲሁም በጀግንነት መፋለሙን የሚሳየዩ ትዕይንቶች በእስክሪኖች ይታያሉ። በክፍሉ መሐል ላይ፤- ጦርነቱ የተጎሰመበት ግዙፍ ነጋሪት የተቀመጠ ሲሆን በነጋሪቱ ግራና ቀኝ ለጦርነቱ መንስኤ የሆነው የውጫሌው ውል አንቀጽ 17፣ የአድዋ ታሪክ እንዲሁም ከድል ወደ ሰላም የሚለው የአዲስ አበባ ስምምነት ሰነድ ተዘርግቶ ይገኛል። ከድል መልስ ግልጋሎት ላይ የዋሉ ጋሻዎች፣ መሳሪያዎች፣ አልባሳት፣ መመገቢያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ በርካታ ቅርሶች፣ ስዕሎች፣ ፎቶዎች ይገኛሉ። ወደ ውስጥ መግቢያ በሆነው በምዕራብ በር ላይ የወቅቱ የኢትዮጵያ መሪ የነበሩት አጼ ሚኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሃውልት በክብር ተቀምጦ ይገኛል። በአድዋ ጦርነት ወቅት ጠላት ለመጠጥነት ይጠቀምበት የነበረውን የምንጭ ውሃ እቴጌ ጣይቱ ብልሃት በተሞላበት መልኩ በኢትዮጵያ ሰራዊት እንዲከበብና ጠላት በውሃ ጥም እንዲዳከም በማድረግ ማሸነፍ የተቻለበት የጦር እስትራቴጂ የሚዘክር ገንዳ ከእቴጌ ጣይቱ ሃውልት ፊት ለፊት ተቀምጦ ይገኛል። የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፤- ጦርነቱ የተካሄደበትን ቦታ የሚያሳየው የአሸዋ ገበታ ሌላው የአድዋ ድል መታሰቢያ ውበትም ታሪክም ነው፡፡ የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፣ መልከዓ-ምድር የሚሳየው የመሬት ላይ ንድፍ ስራ በዚሁ መታሰቢያ መቀመጡ ኢትዮጵያውያን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለነጻነት የከፈሉትን መስዋትነት ያመላክታል። ከተራሮች አጠገብ በጦርነት ወቅት ጥቅም ላይ ከዋሉ ጣሊያናዊ ስሪት የሆነ "ቶሪኖ 1883" የሚል ጽሁፍ ያለበት መድፍ ይገኛል። በጦርነቱ ተዋጊዎችን ያጓጓዙ 45 ሺህ ፈረሰኞች የሰሩትን ጀብድ ሊወክልና ሊዘክራቸው የሚችል ‘የአድዋ ፈረሰኞች የድል ሀውልት’ ቆሞላቸዋል፡፡ የአድዋ ጀግኖች ኢትዮጵያን ከወራሪው ጣሊያን ለማዳን ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት ሳይለዩ በአንድነት ተሰባስበው የተመሙበትን የሚወክል ‘የአንድነት ድልድይ’ በሚል ተሰርቷል፡፡ የሁሉንም ተሳትፎ የሚያሳዩ የተለያዩ ሁነቶች በጦርነቱ ወቅት ህዝብና አገርን በታማኝነት ሲያስተዳድሩ የነበሩ እንደራሴዎች የሚያሳይ ስዕላዊ በመታሰቢያ የተቀመጠ ሲሆን በጦርነቱ ወቅት የነበረውን የህዝቡን እንቅስቃሴ የሚገልጹ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና የመገልገያ ቁሳቁሶች፣ ስዕሎችና ቅርጾችም ይገኛሉ።   የገበሬዎችና ሴቶች ተሳትፎ የሚያሳዩ ስራዎች በአድዋ ጦርነት ከ120 ሺህ በላይ ገበሬዎች የግብርና ስራቸውን አቋርጠው "አገራችን ተነካች" በማለት ታጥቀው ድል ያጎናጸፉ፣ ለጥቁር ህዝቦች ትልቅ ታሪክ ያስቀመጡ ጀግኖች ናቸው። በዚህ መታሰቢያ የአንድነት ማዕከል፣ የአፍሪካ ነጻነት ማስታወሻ የኢትዮጵያ ጀግኖችን ጉዞ የሚያሳዩ ምስሎች ይገኛሉ። በጦርነት ወቅት ሴቶች የቤት ሃላፊነትን ከመወጣት በተጨማሪ በአዋጊነት፣ በመረጃ ሰጪነት ቁስለኞችን በመንከባከብ ለሰሩት ስራ የተሰየመ ማስታወሻም በአድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀምጦ ይገኛል። የአሁኑ ትውልድ አሻራ፣- የኢትዮጵያ ልጆች በአንድነት ተባብረው አፍሪካ በራሷ አቅም መልማት እንደምትችል ያሳዩበት፣ አፍሪካዊ ተምሳሌት የሆነው የህዳሴ ግድብ ፏፏቴ በመታሰቢያው ይገኛል። ኢትዮጵያውያን ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት ላደረጉት ተጋድሎ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የፓን-አፍሪካ ሃውልትም ተካቷል።   ሌሎችም የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋን ጦርነት ሁነቶች ብቻ ሳይሆን ለተለያያዩ ዝግጅቶች የሚሆኑ አዳራሾችን፣ ካፍቴሪያዎችን፣ ሲኒማ ቤቶችንና ሌሎች ለበርካታ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎችንን አካቶ የተሰራ ነው። ከ2500 በላይ እንግዶችን መያዝ የሚችል ፓን አፍሪካን አዳራሽ፣ 300 ሰዎች የሚይዝ የአድዋ አዳራሽ፣ 160 ሰዎች የሚይዝ መካከለኛ አዳራሽ፣ 300 ሰው በአንድ የሚያስተናግዱ ሬስቶራንቶች፣ ሁለት ካፍቴሪያዎችና የህጻናት ሙዚየም በውስጡ አካቷል። በሌላ በኩል በአንድ ጊዜ 1000 ተሽከርካሪ መያዝ የሚችሉ ፓርኪንግ፣ ዘመናዊ ጂምና ሌሎችም ተካተዋል። የአድዋ ድል መታሰቢያ አድዋ ጊዜ የማይሽረው፣ ዘመን የማይለውጠው የጀግንነትና የአንድነት ምልክት መሆኑን ማሳያ፣ ለነጻነት የታገሉና የተሰዉ ጀግኖች የሚታሰቡበት የታሪክ ማስታወሻ ነው። የአድዋ ድል ትሩፋቶችን ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝብ በየትውልዱ ለማስተማር የሚያግዝ የዘመናት የነጻነት መንፈስን የሚያስተጋባ፣ ለመጪው ትውልድ የሚሻገር እውነት ነው። እናም የአድዋ ድል መታሰቢያ የወል ታሪካችንን የምንገነባበት የማዕዘን ድንጋይ ነው።  
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች
Mar 1, 2024 2506
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች በአየለ ያረጋል "... መጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል..." ይህን ያሉት ታላቁ ምሁር እና የአድዋ ዘማች ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማርያም ናቸው። በርግጥ በአድዋ ዘመቻ ያልዘመተ የለም። የሀይማኖት መሪዎች፣ ንጉሱ፣ ንግስቲቱ፣ ገበሬው፣ አገሬው ከነማንነቱ… ገድል ፈጽሟል። በጦር ሜዳ ገድሎች የሴቶች አበርከቶ እምብዛም አይታወስም። ሴቶች የዋሉበት ግንባር አይዘከርም። ቅሉ ሴቶች በኪነ-አድዋ ያልተዘመረላቸው ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው። እቴጌ ጣይቱን መሰል የአድዋ ሴት የጦር ፊታውራሪዎች አሉ። አዝማሪ ጣዲቄና መሰል አዝማሪዎች የሰራዊቱ ስነ ልቦና ገንቢዎች ናችው። ሴቶች የሎጂስቲክስ አሳላጮች፣ የቁስለኛ ሀኪሞች፣ የጀግና አበርቺዎች፣ የስንቅ ሰናቂዎች፣….በጥቅሉ ሴቶች የአድዋ ድል ሁለንተናዎች ነበሩ። ለዚህ ደግሞ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ቀዳሚ ምስክር ናቸው። እቴጌ ጣይቱ ከውጫሌ እስከ መቀሌ፣ ከእንጦጦ እስከ ማርያም ሸዊቶ መላ መቺም፣ ጦር አዝማችም ነበሩ። የዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዜና መዕዋል ከታቢ ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ ወልደአረጋይ ‘ታሪከ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ’ በተሰኘው መጽሐፋቸው የሴቶችን ሚና በተመለከተ እንዲህ ይላሉ። “እንዲህም እየሆነ፣ አጤ ምኒልክ ባዳራሹ እቴጌ ጣይቱ በእልፍኝ ባለሟሎችን ወይዛዝርቱን ይዘው ግብሩ አንድ ቀን ሳይጎድል፣ ይዘምታሉ። ከዘመቻ ላይ ጠጁ ማሩ አለመጉደሉ፣ ስለምንድነው ያልህ እንደሆነ ይህን ታሪክ መመልከት ነው። በስድስት ድንኳን እንጀራው ሲጋገር ሲያድር፣ በአራት ድንኳን ወጡ ሲሠራ ሲያድር፣ ጠጁ በቀንድ በኮዳ ደግሞ ሦስት መቶ ስድስት መቶ የሚሆን ገንቦኛ ሲጓዝ ግብሩ ይጎድል ይመስልሀል” (ገጽ-241) ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ይቀጥላሉ። “… ጥቂቱን ጻፍን እንጅ በአድዋ ጦርነት ዐይናቸን እንዳየው ጆሯችን እንደሰማው መጻፍ አይቻለንም። እቴጌ በዚያን ጊዜ በግምባርዎ ተደፍተው በጉልበትም ተንበርክከው ድንጋይ ተሸክመው እግዚአብሄር እያመለከቱ ሲያዝኑ ሲጨነቁ ነበር። … ሴት ወይዛዝርቱም የንጉሠ ነገሥቱ ልጅ ወይዘሮ ዘውዲቱም ደንገጡሮችንም ተከትለው ነበር። የኋላው ሰልፈኛ እንደመወዝወዝ ሲል ባዩ ጊዜ ቃልዎን አፈፍ አድርገው ተናገሩ። አይዞህ አንተ ምን ሆነሃል! ድሉ የኛ ነው በለው! አሉት… ጣሊያ ድል ከሆነ በኋላ ወንዱ በርኮር፣ ሴቱ በገንቦ ውሃ ያዙ ብለው አዘው ለተጠማውና ለቆሰለው ውሃ ሲያጠቱት ዋሉ። እንኳን ኢትዮጵያ ሰው የኢጣሊያው ስንኳ ቁስለኛ ከዚያ ስፍራ የተገኘ ከዚህ ከእቴጌ ካዘዙት ውሃ አልቀረበትም“ይላሉ። ከጽሁፉ መረዳት እንደሚቻለው እቴጌ ጣይቱና መሰሎቻቸው አንድም በጸሎታቸው፣ አንድም ተዋጊዎችን በማደፋፈር ወኔያቸው፣ አንድም በጦር መሪነት ሚናቸውን ተወጥተዋል። ዋናው ደግሞ ቁስለኞችን የማከምና ሰብዓዊነት ሙያቸው ነው። ፀሃፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ “… ሙሉ ግብር እየበላ የተጓዘ እንጂ ወታደር የስንቅ አቁማዳዉን አልፈታም“ ሲሉ የአድዋ ሴቶች ገድል ምንኛ ገናና እንደሆነ መገመት እንደሚቻል ይጠቅሳሉ። እንደ ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ስለዘመቻው አጓኳን በማስታወሻቸው እንደገለጡት ድንኳን ተካይ፤ ዕንጨት አቅራቢው፣ ወጥ ሰሪው፣ እንጀራ ጋጋሪው፣ እህል ውሃ ተሸካሚው፣ መልከኛው (አራጁ)፣ በቅሎ ጫኙ፤ ተዋጊው ሁሉም በየፊናው እንስሳቱም ሳይቀር ተደራጅቶ ዘምቷል። በርካታ የታሪክ ምንጮች የአድዋ ጦርነት ተሳታፊዎች ገሚሶቹ ሴቶች እንደሆኑ ይገልጻሉ። የታሪክ ምሁሩ ዶክተር አልማው ክፍሌ ደግሞ በአንድ ወቅት ሚዲያ ላይ ቀርበው “በአድዋ ጦርነት ዘማቾች 75 በመቶ ሴቶች ነበሩ” ብለው ነበር። በአድዋ ጦርነት ሴቶች በተለያዩ ሙያዎች ተመድበው ከካምፕ እስከ ጦር ሜዳ ከመመገብ እስከ ማጀገን፣ ከማከም እስከ መዋጋት ድንቅ ሚና ተወጥተዋል። ድርብ ድርብርብ ኃላፊነት ይዘው የዘመቱ፣ ለወንዶችም ልብ፣ ሞራልና ወኔ አቀባዮች ነበሩ። ደራሲ በዕውቀቱ ሥዩም ‘ከአሜን ባሻገር’ በተሰኘ መጽሐፉ ‘ሴቶች በዋሉበት’ በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሴቶች ተጋድሎና ሚና “ከቁስ ባሻገር ከልብ ያቀርባሉ” ይላቸዋል። “ሴቶች ባዋላጅነት ከነበራቸው የማይተናነስ ሚና በጦር ሜዳ ተጫውተዋል። እናቶቻችን በጦር ወቅት፣ መሳሪያ ያቀርቡ ነበር። ምግብ ያቀርቡ ነበር። ሃሳብ ያቀርቡ ነበር። ልብ ያቀርቡ ነበር። ደስታ ያቀርቡ ነበር። ኧረ ምኑ ቅጡ። ሴቶች ባንድ በሙቀጫ ዙሪያ፣ ማኅበረሰቡን ኬሚስት፣ ገጣሚና የፖለቲካ ተንታኝ ሆነው ማገልገላቸውን ልብ እንበል” ይላል። (ገጽ-138) የራስ መኮንን ባለሟል የነበሩት ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማሪያም ገና በ15 ዓመት ዕድሜያቸው አድዋ ዘማች ነበሩ። "የሕይወቴ ታሪክ’ (ኦውቶባዮግራፊ) በተሰኘው ግለ ታሪካቸው ከሐረር እስከ አድዋ በዘለቀው ጉዟቸው ሴቷ (አገልጋያቸው) የነበራትን ሚና ለማብራራት ቃላት ያጥርባቸውና እንዲህ ብለው የአንባቢን ህሊና ይነካሉ። “… ከቶ እሷ ባትኖር ኖሮ እንዴት እሆን ኖሯል! እያልኩ ዘወትር ሳስበው ያደንቀኛል። ዕቃ ተሸክማ ስትሄድ ትውላለች። ከሰፈርን በኋል ውሃ ቀድታ፣ እንጨት ለቅማ፣ ቂጣ ጋግራ፣ ወጥ ሰርታ፣ ታበላናለች። ወዲያውኑ እንዲዚህ ለማታ ታሰናዳለች። እንደዚህ የወለተ አማኑኤልን አገልግሎት እያሰብኩ ስደነቅ ደግሞ በየሰፈሩ እንደርሷ ስንት ሴቶች እንደሚያገለግሉ ይታሰበኛል። የሴቶቹን አገልግሎት ስገምት ደግሞ የበቅሎዎች አገልግሎት ይታወሰኛል። በመጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል። ሁሉንም አያይዥ በደምሳሳው ስመለከተው የኢትዮጵያን መንግስት ነጻነቱን ጠብቀው፤ እዚህ አሁን የደረስንበት ኑሮ ያደረሱት እነዚህ የዘመቻ ሃይሎች መሆናቸውን አልስተውም። የኢትዮጰያ መንግስት የተባለው ተቋም፣ ላገልጋዮቹ ውለታ ምላሽ ሆኗል ወይ? የዚህን ምላሽ ለመስጠት ሳስበው እልቅ የሌለው መንገድ ይገጥመኛል። ሲሄዱ መኖር ይሆንብኛል። የማልዘልቀው እየሆነብኝ፣ እየተከዝኩ እተወዋለሁ” በማለት በቁጭት ጽፈዋል። በርግጥም ሴቶች በኪነ-አድዋ በልካቸው ያልተዘመረላቸው፣ ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው።  
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 11797
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16187
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 8367
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል።   “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል።   ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 9432
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 26347
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 21917
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16187
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 12328
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 11797
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 11209
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 10977
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
ተመድ በሶሪያ በርዕደ መሬት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረበ
Feb 15, 2023 10524
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 8/2015 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በሶሪያና ቱርክ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ ሶሪያውያንን ለማገዝ የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረቡ። ዋና ጸሓፊው ጥሪውን ያቀረቡት ባሳለፍነው ሳምንት በቱርክና በሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሶሪያውያንን ለማገዝ ነው። በኒውዮርክ በሰጡት መግለጫ ሶሪያውያኑን ለማገዝ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ለሶስት ወራት ጊዜ ብቻ የሚበቃ መሆኑን ጠቅሰው የሚመለከታቸው ሁሉ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። ከአደጋው በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አስቸኳይ ድጋፍ ማቅረቡን ገልጸው ተጨማሪ እገዛዎች አሁንም እንደሚያስፈልጉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በድርጅቱ ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትና አጋር አካላት በጋራ በሚያቀርቡት ገንዘብ፤ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሶሪያውያን የመጠለያ፣ የጤና፣ የምግብ እንዲሁም ሌሎች አስቸኳይ ድጋፎች እንደሚደረጉ አብራርተዋል። ተመሳሳይ የድጋፍ ማዕቀፍ በቱርክ ድንበር ለሚገኙ ዜጎች እየተጠናቀቀ እንደሚገኝም ዋና ጸሓፊው ተናግረዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 26347
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 21917
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16187
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 12328
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
መጣጥፍ
በድላችን ሐውልት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት የተቀረጸላቸው የካራማራው ዘማች አቶ በቀለ ገመቹ 
Mar 5, 2024 3804
አቶ በቀለ ገመቹ ወይም በቅፅል ስማቸው አሚኮ ይባላሉ፤ በሙያቸው ኤሌክትሪሺያን ናቸው። በ1969 ዓ.ም በዚያድባሬ የሚመራው የሶማሊያ አገዛዝ ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ሀገር ስትደፈር ቁጭት ተሰምቷቸው ወደ ጦር ሜዳ መዝመታቸውን ይናገራሉ። ጦር ሜዳ ከመዝመታቸው ባሻገር የኤሌክትሪክ ባለሙያ በመሆናቸው "በራ በራ የድል ጮራ" የተሰኘውን ዓርማ በመቅረጽ በ14ቱ ክፍላተ ሀገር እንዲበራ ማድረጋቸውንም ያነሳሉ። በዚህም ከወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እና ከኩባው ፕሬዝዳንት ፊደል ካስትሮ መሸለማችውን ያወሳሉ። ታንክ ማራኪው አሊ በርኬ ጓደኛቸው እንደሆኑ የሚናገሩት አቶ በቀለ፤ በተለያዩ ዐውደ ግንባሮች መሳተፋቸውን አስታውሰዋል። አቶ በቀለ ጥቁር አንበሳ በሚገኘው የኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ፓርክ በሚገኘው የድላችን ሐውልት ላይ ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት ተቀርጾላቸዋል። ሐውልት እንዲቀረጽ የተደረገበት ፎቶግራፍ በያኔው ሶስተኛው አንበሳው ክፍለ ጦር በኋለኛው ምሰራቅ ዕዝ በር ላይ በቀኝ እጃቸው መሳሪያ ከፍ አድርገው ይዘው የተነሱት ፎቶ ግራፍ እንደሆነ ገልጸው፤ በዚህም ደስተኛ እንደሆኑ ይናገራሉ። ከእርሳቸው ጎንም መንበረ የምትባል ሌላ ኢትዮጵያዊ ዘማችና መትረጊስ ተኳሽ ሴት ባደረገችው አስተዋፅኦና በደረሰባት አካል ጉዳት ሐውልት እንደተቀረጸላት ያነሳሉ። የካራማራ ድል ታላቅ ድል ነው የሚሉት አቶ በቀለ ገመቹ፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት ከፍለውበት የተገኘና ሀገርን ያስከበረ መሆኑንም ይገልጻሉ። የካራማራ ዘማቹ አቶ በቀለ ገመቹ አሁናዊ ኑሯቸው ችግር ላይ እንደሚገኙና ድጋፍ እንደሚሹም ተናግረዋል። ሶማሊያን ለ21 ዓመታት ያስተዳደሩት ዚያድባሬ 'ታላቋን የሶማሊያ ሪፐብሊክ ለመመስረት' በሚል "ድንበራችን እስከ አዋሽ ይደርሳል" እያሉ በመዛት የጦርነት ነጋሪት መጎሰማቸው የሚታወስ ነው። ይሄን እውን ለማድረግ በ1969 በኢትዮጵያ ላይ ግልጽ ወረራ ፈጸሙ። የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጦር የእብሪተኛውን የዚያድባሬ ጦር ካራ ማራ ላይ ድል አደረገ፤ የኢትዮጵያ አሸናፊነትም በአደባባይ ታወጀ። ድሉ በየዓመቱ የካቲት 26 ቀን የሚታሰብ ሲሆን ዘንድሮም 46ኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል።    
የአፍሪካ ዋንጫን በመሀል ዳኝነት  የመራችው ብቸኛዋ ሴት ዳኛ
Jan 28, 2024 3572
  በይስሐቅ ቀለመወርቅ እንደ መነሻ፡- በእግር ኳስ ውድድሮች የመሃል ዳኝነቱን ቦታ በብዛት የሚይዙት ወንዶች ሲሆኑ፤ አሁን ላይ አልፎ አልፎ ሴቶች ትልልቅ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ሲዳኙ አስተውለናል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 በኳታር አስተናጋጅነት በተከናወነው 22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ፤ ፈረንሳዊቷ ስቴፋኒ ፍራፓርት፤ ኮስታሪካ እና ጀርመን ያደረጉትን ጨዋታ በመሀል ዳኛነት መርታለች። በዚህም በወንዶች ዓለም ዋንጫ ታሪክ በመሀል ዳኝነት የእግር ኳስ ጨዋታን የመራች የመጀመሪያዋ ሴት በመሆን ታሪክ ሰርታለች ። ዘንድሮ ደግሞ በኮትዲቯር አስተናጋጅነት እየተከናወነ በሚገኘው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ሞሮኳዊቷ ቦችራ ካርቡቢ፤ ውድድሩን እንዲመሩ ከተመረጡት 32 የመሀል ዳኞች መካከል ብቸኛዋ ሴት ናት። በዚህም በውድድሩ በጊኒ ቢሳውና በናይጄሪያ መካከል የተከናወነውን ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ፤ በመሀል ዳኝት በመምራት፤ ታሪክ ጽፋለች። የሞሮኮ ዓለም አቀፍ ማኅበር የእግር ኳስ ዳኛ የሆነችው ቦችራ ካርቡቢ፤ በወንዶችም ሆነ በሴቶች አህጉራዊ የእግር ኳስ ውድድሮች ላይ በርካታ የመጨረሻ ምዕራፍ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ዳኝታለች። 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫን ብቸኛ የሴት ዳኛ ሆና የመራችው ቦችራ ካርቡቢ ማናት? ቦችራ ካርቡቢ በሞሮኮ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው "ታዛ" ከተማ፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1987 ተወለደች። የዘር ግንዷ በሰሜን ምሥራቅ ሞሮኮ ከሚገኙት ሪፊያን ከሚባሉት የበርበር ጎሳ ዝርያ ካላቸው ሕዝቦች የሚመዘዝ ሲሆን፤ ለቤተሰቦቿ አምስተኛና የመጨረሻ ልጅ ነች። ገና በልጅነቷ ለእግር ኳስ ፍቅር ያደረባት ቦችራ ካርቡቢ፤ ኳስ መጫወት የጀመረችው በአንድ ትንሽ የወጣቶች ቡድን ውስጥ ነበር። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2001 በተወለደችበት ከተማ "ታዛ"፤ ለወንዶችና ለሴቶች የእግር ኳስ ዳኝነት ሥልጠና የሚሰጥበት ትምህርት ቤት ተከፈተ ። ይኼ ትምህርት ቤት ቀልቧን የሳበው ቦችራ፤ ሥልጠናውን መውሰድ ጀመረች። "እግር ኳስን እወዳለሁ፤ ራሴንም ላስተምር ፈለኩ።ለምን አላደርገውም ብዬ ፍላጎቴን በመከተል የእግር ኳስ ጨዋታን ደንብ መማር ጀመርኩ" ስትል የእግር ኳስ ዳኝነት ትምህርት የጀመረችበትን ጊዜ ታስታውሳለች። ይኼ ድርጊቷ ካልተዋጠላቸውና፤ በበጎ ጎኑ ካልተመለከቱት ውስጥ ደግሞ፤ ወንድሞቿ ቀዳሚዎች ነበሩ። "በምኖርበት ከተማ አንድ ሴት አጭር ቁምጣ ለብሳ ከወንዶች ጋር ሥልጠና ስትወስድ መታየቷ፤ እንደ አሳፋሪ ድርጊት ስለሚታይ መነጋገሪያ ሆኜ ነበር" ትላለች። የቦችራ ካርቡቢ የዳኝነት ጉዞ እንደ አውሮፓውያን ቆጣጠር በ2007፤ ሞሮኮ ብሔራዊ የሴቶች እግር ኳስ ሻምፒዮናን ጀመረች። ይህ መሆኑ ቡችራ ካርቡቢ ብሔራዊ ዳኛ እንድትሆን ዕድል የፈጠረላት ሲሆን፤ መኖሪያዋንም ከትውልድ ሥፍራዋ "ታዛ" ወደ ሞሮኮ ሌላኛዋ ከተማ "ሚከንስ" እንድትቀይር አደረጋት። "ይህን ዕድል ማግኘቴ ቤተሰቦቼ እንዲረዱኝና ሙያዊ ለሆነ ጉዳይ እንደምሄድ እንዲያምኑ አድርጓቸዋል" በማለት የዳኝነት ሙያዋን በመጨረሻ እንደተቀበሉት ታስረዳለች። በሚከንስ ከተማ በእግር ኳስ ዳኝነት ሥልጠና ላይ እያለች፤ አንድ ቀን አባቷ መጥቶ እንደተመለከታትና፤ ወንድሞቿ ምርጫዋን ሊያከብሩላት እንደሚገባ እንደነገራቸውም ገልፃለች። የ19 ዓመት ወጣት እያለችም፤ በሞሮኮ የሴቶች አንደኛ እና ሁለተኛ የሊግ ውድድር በመዳኘት፤ የዳኝነት ሥራዋን አንድ ብላ ጀመረች። ይህ ከሆነ ከ10 ዓመት በኋላ፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2016 ደግሞ፤ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ዳኛ በመሆን ራሷን ወደ ሌላ ምዕራፍ አሸጋገረች። ከሁለት ዓመት በኋላም በ2018 በጋና አስተናጋጅነት በተከናወነው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ፤ በዛምቢያና በኢኳቶሪያል ጊኒ መካከል የተደረገውን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት አጫወተች። ይህም በአህጉራዊ የውድድር መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመሀል ዳኝነት ያጫወተችው ጨዋታ ሆኖ ተመዘገበላት። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2020፤ "ቦቶላ" እየተባለ በሚጠራው በሞሮኮ የወንዶች ከፍተኛ የሊግ ውድድር ላይ በመሀል ዳኝነት በመዳኘት፤ የመጀመሪያዋ ሴት ሆነች ። ከአንድ ዓመት በኋላም በካሜሮን አስተናጋጅነት በተከናወነው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ፤ ሴኔጋልና ግብፅ ባደረጉት የፍፃሜ ጨዋታ የቫር ዳኛ (video assistant referee) በመሆን ሰርታለች። ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊትም የሞሮኮ የንጉሱ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታን በመዳኘትም ቀዳሚዋ ሴት ናት። አሁን ላይ እየተከናወነ ባለው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ወድድርም፤ በጊኒ ቢሳውና በናይጄሪያ መካከል የተከናወነውን ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ በመሀል ዳኝት በመምራት፤ የመጀመሪያዋ ሰሜን አፍሪካዊት የአረብ ሴት ሆናለች። ቡችራ ካርቡቢ ከእግር ኳስ ዳኝነት ሥራዋ በተጨማሪ፤ የፖሊስ ኦፊሰር በመሆን ሀገሯን እያገለገለች ትገኛለች።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም