ነጌሌ አርሲ ተከታታይ አራተኛ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ነጌሌ አርሲ ተከታታይ አራተኛ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 30/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ14ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ነጌሌ አርሲ ምድረ ገነት ሽሬን 1 ለ 0 አሸንፏል።
የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ይጫወታል
አሁናዊ ቁጥራዊ መረጃዎች ስለ 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ከቤ ብዙነህ በ12ኛው ደቂቃ ላይ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
በሊጉ አራተኛ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ነጌሌ አርሲ በ25 ነጥብ ደረጃውን ከሶስተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል።
በሊጉ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ምድረ ገነት ሽሬ በ17 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።