አርእስተ ዜና
በደብረብርሃን ከተማ ለተፈናቃይ ወገኖች ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ምግብ ድጋፍ ተደረገ
Apr 19, 2024 0
ደብረ ብርሀን ፤ ሚያዚያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ በደብረ ብርሀን ከተማ አስተዳደር በመጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የምግብ እህል ድጋፍ መደረጉን የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የጽህፈት ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ወይዘሮ ቀለሟ ኃብቴ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያና በዘመድ ቤት ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ ሲደረግ ቆይቷል። ዛሬ በደብረ ብርሀን ከተማ አስተዳደር በጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ 19ሺህ 210 ወገኖችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የምግብ እህል ድጋፍ ከፌደራል መንግስት መደረጉን ገልፀዋል። ድጋፉ 26 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው 2ሺህ 882 ኩንታል ስንዴ እና 210 ኩንታል አልሚ ምግብ መሆኑን ጠቁመው፣ በቀጣይም በእንሳሮና በምንጃር ሸንኮራ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፉ ይቀጥላል ብለዋል። የድጋፉን ፍታሃዊነት ለማረጋገጥም ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፣ ሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።   የድጋፉ ተጠቃሚ አቶ መሐመድ ይመር እንዳሉት፤ እስካሁን በመንግስት፣ መንግስታዊ ባልሆኑ አካላት እና በአካባቢው ነዋሪዎች በተደረገላቸው ድጋፍ ህይወታቸውን ማቆየታቸውን ገልጸዋል። የዛሬው ድጋፍ ወቅታዊ ችግራቸውን እንደሚያቃልል ጠቁመው፣ በቀጣይም መሰል ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል። ወይዘሮ ሀዋ አበባው በበኩላቸው ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው፤ በቀጣይ መንግስት ሰላምን በማረጋገጥ ወደ መጡበት ቄዬ እንዲመልሳቸው ጠይቀዋል። በሰሜን ሸዋ ዞን ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች እና በዘመድ ቤት የሚኖሩ 89 ሺህ 215 ወገኖች እንዳሉ መረጃዎች ያሳያሉ።  
ባለመላዎቹ ታዳጊዎች
Apr 19, 2024 13
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ ችግርን ወደ እድል የቀየሩ ባለመላዎቹ ታዳጊዎች ከመጋቢት 30 እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆየው የኢትዮጵያ "ስታርት አፕ" አውደ-ርዕይ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሳይንስ ሙዚየም ለጎብኚዎች ክፍት ተደርጓል። በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በኢንዱስትሪ፣ በፋይናንስና በሌሎች ዘርፍ የተሰማሩ ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች ''ስታርት አፖች'' በአውደ-ርዕዩ በመሳተፍ ላይ ናቸው። አውደ-ርዕዩ የተዘጋጀው በአገሪቱ የሚገኙ ስታርት አፖች ያላቸውን ምርትና አገልግሎት እንዲሁም ፈጠራዎች ተደራሽ ለማድረግ ነው። የአቤም ዩዝ አካዳሚ የሰባተኛ ክፍል ተማሪ የሆኑት ጎዶሊያስ ሙሉጌታና ሰላዲን መራዊ የግለሰብ መረጃን ወይንም ሲቪ የሚያደራጅ ድረ-ገፅ ሰርተው በስታርት አፕ አውደ-ርዕይ አቅርበዋል።   የታዳጊ ጎዶሊያስ ወንድም ስራ ለማመልከት ሲወጣ ''ሲቪ'' ረስቶ ወደቤት በመመለስ ለተጨማሪ ወጪና እንግልት መዳረጉ የዚህ ድረ-ገፅ መልማት መነሻ የሆነ ምክንያት ነው። ሰዎች ስራን ለመቀጠር የሚያስገቡት የራስ መግለጫ ''ሲቪ'' በእጅ ስልካቸው ኖሮ በማንኛውም ሰዓት ለሚፈልጉት ቀጣሪ ማስገባት የሚያስችል ድረ-ገፅ የሰሩት ታዳጊዎች የአይ ሲ ቲ መምህራቸው ለዚህ ስራቸው እገዛ እንዳደረገላቸው ተናግረዋል። ድረ-ገፁ ስለግለሰቡ የትምህርት ደረጃን ጨምሮ፣ አድራሻ፣ ክህሎቶችና የሰዎችን ምስክርነትን ማካተት የሚቻልበት መሆኑን ተናግረዋል። ድረ-ገፁ የሰዎችን ብቻ ሳይሆን የድርጅቶችን መረጃ እንዲያስቀምጥ ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑንም ታዳጊዎቹ ያስረዳሉ። በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀው አውደርዕይ ላይ መሳተፋቸው ከሌሎች ስታርት አፖች ልምድ እንዲቀስሙና እውቀታቸውን እንዲያዳብሩ እድል የሚፈጥርላቸው መሆኑንም ገልፀዋል። ስራቸውን እንዲያሳዩ እድል ስለተፈጠረላቸውና እዚህ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ እገዛ ላደረጉላቸው አካላትም ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይም ችግር ፈቺ የምርመር ስራዎችን በመስራት አገራቸውን ለመጥቀም እንደሚሰሩ ገልጸዋል።  
20ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ በዋሽንግተን ዲሲ ተካሔደ
Apr 19, 2024 27
  አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2016(ኢዜአ)፦ 20ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ በወቅቱ የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ ሊቀመንበር የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ መሪነት በዋሽንግተን ዲሲ ተካሒዷል። ሚኒስትሩ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) እና ዓለም ባንክ ስብሰባ ጎን ለጎን 20ኛውን የምስራቅ አፍሪካ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ መርተዋል።   በውይይቱም የአፍሪካ ቀንድ ሃገራት የገንዘብ ሚኒስትሮች፣ የልማት አጋሮች የአፍሪካ ልማት ባንክ፣ የአውሮፓ ህብረት የጀርመን እና የእንግሊዝ ተወካዮች መሳተፋቸው ተገልጿል። ሚኒስትሩ በውይይቱ ላይ እንደ አረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት ፣የሳኡዲ ልማት ፈንድ፣ ጃፓንና የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ያሉ አጋሮችን ተሳትፎ አመስግነዋል። አቶ አህመድ አያይዘውም ሌሎችም በአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ ማዕቀፍ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ኢኒሼቲቩ ባለፉት አምስት አመታት ሀብት በማሰባሰብ ረገድ ስኬታማ እንደነበር አስታውሰው፤ ይህ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አፅንኦት ሰጥተዋል። የምስራቅ አፍሪካ ኢንሼቲቭ ሰባት የአፍሪካ ቀንድ ሀገራትን በአባልነት አካትቶ በፈረንጆቹ 2019 የተመሰረተ ሲሆን በቀጠናው ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ለማጠናከር እየሰራ እንደሚገኝ ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።            
መንግስት ለሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ተግባራዊነት በቁርጠኝነት ይሰራል-- ተስፋዬ በልጅጌ
Apr 19, 2024 31
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ መንግስት ለሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ተግባራዊነትና ውጤታማነት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ ገለጹ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤን ጨምሮ የዴሞክራሲ ተቋማት አመራሮችና ሌሎች በተገኙበት በሽግግር ፍትህ ፖሊሲና የፌደራል የአስተዳደር ስነ-ስርአት አዋጅ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ በዚሁ ጊዜ የተለያዩ የዓለም አገራት ከተወሳሰበ ችግርና ቀውስ ለመውጣት የሽግግር ፍትህን መፍትሄ አድርገው መጠቀማቸውን አንስተዋል፡፡ በኢትዮጵያም በቀደሙ ስርዓቶች የተፈጸሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ በታሪክ ምክንያት የሚነሱ አለመግባባቶች፣ የዴሞክራሲ ስርዓት አለመጎልበት፣ ለዘመናት የተከማቹ የፖለቲካ ቀውሶች መኖራቸውን ጠቅሰው፤ ለእነዚህ ችግሮች እልባት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡ ከዚህ አኳያ ከአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር የሚመጋገብና ሂደቱን የሚያሳልጥ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። መንግስት ፖሊሲው እንዲዘጋጅ ከማድረግ ጀምሮ ቁርጠኛ የፖለቲካ አቋም መውሰዱን ገልጸው፤ይህም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አብራርተዋል፡፡ የአሁኑ ትውልድ ችግሮችን ቀርፎ ኢትዮጵያን ወደ አዲስ ምእራፍ የማሸጋገር ኃላፊነት እንዳለበትም ነው የተናገሩት፡፡ ፖሊሲ ለረዥም ጊዜ ስር የሰደዱ ችግሮችን በመፍታት ከችግር መውጫ አንዱ መሳሪያ መሆኑንም አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል። የትናንት ቁርሾዎችን በእርቀ ሰላምና ይቅርታ በመዝጋት ለነገ ትውልድ የተረጋጋችና ዘላቂ ሰላም የሰፈነባት አገር ማስተላለፍ እንደሚገባም አንስተዋል፡፡ በዚህ ረገድ መንግስት የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ለፖሊሲው ተፈጻሚነት በጋራ መስራት እንደሚገባ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ የፖሊሲው ወቅታዊነትን በሚመለከትም ከተሳታፊዎች ጥያቄ ቀርቧል፡፡ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በምላሻቸው አገራዊ የሆኑ ችግሮች በይደር የሚታለፉ አለመሆናቸውን ጠቅሰው፤ ችግሮቹን በአንድነት ለመፍታት ጊዜው አሁን መሆኑን አስረድተዋል። በኢትዮጵያ ገለልተኛ ተቋማትን በማደራጀት ነጻና ገለልተኛ ሆነው እንዲሰሩ ለማድረግ የተጀመረው ስራ ለፖሊሲው ተፈጻሚነትም አስቻይ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥርም አንስተዋል። በሌላ በኩል የፌደራል የአስተዳደር ስነ-ስርአት አዋጅ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠትና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ሚናው የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ አዋጁ አጠቃላይ የተጀመረው ለውጥ ስራ አካል መሆኑን በመጥቀስ ይህም የአሰራር ማነቆዎችን በመፍታት፣ አደረጃጀትን በማስተካከል፣ አገልግሎትን በማሻሻል ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ነው ያሉት። አዋጁ የታለመለትን ዓላማ እንዲያሳካ የተቋማት ኃላፊዎችና ሙያተኞች ተግባራዊነቱ ላይ በልዩ ትኩረት መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።    
የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ሁሉም በትብብር ሊሰራ ይገባል-አቶ ኡሞድ ኡጁሉ
Apr 19, 2024 37
ጋምቤላ ፤ ሚያዚያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል የትምህርት ቤቶችን ደረጃና ግብዓት በማሻሻል የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ገለጹ። የክልሉ የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ዛሬ በጋምቤላ ከተማ ተካሄዷል ።   ርዕሰ መስተዳድሩ በግምገማ መድረኩ ላይ እንደተናገሩት፤ የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማትና ግብዓት በማሻሻል የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ሊጠናከር ይገባል። ''የትምህርት ቤቶችን ደረጃና ግብዓት በማሻሻል የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ "ትምህርት ለትውልድ " በሚል አገር አቀፍ ንቅናቄ ወደ ስራ የተገባ ቢሆንም እንደ ክልል የተከናወኑት ተግባራት በቂ አይደሉም'' ብለዋል። በክልሉ ትምህርት ቤቶችን ተደራሽ በማድረግ ረገድ የተሻለ አፈፃፀም ቢኖርም ትምህርት ቤቶቹ የደረጃና የግብዓት ችግር ያለባቸው መሆኑን ገልጸዋል ። በመሆኑም በዘርፉ የተጀመሩ የንቅናቄ ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል የታለመውን ግብ ለማሳካት የአመራሩ፣ የዘርፉ ባለሙያዎችና የመላው ማህበረሰብ ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል ። የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ላክደር ላክባክ በበኩላቸው ባለፉት ዘጠኝ ወራት የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻልና በግብዓት ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል። በክልሉ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተጀመረው የምገባ መርሃግብር የተማሪዎችን መጠነ ማቋረጥ በመቀነስ ረገድ ፋይዳዉ የጎላ መሆኑን ገልፀዋል። ይሁን እንጂ የምገባ መርሃ ግብሩን ሳይቆራረጥ ለማስቀጠል እንዲቻል የመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እገዛ ሊጠናከር እንደሚገባም ተናግረዋል። የግምገማ መድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሻሻል ጎን ለጎን የመምህራንን አቅም ማጎልበት እንደሚገባም ሃሳብ ሰንዝረዋል። በግምገማ መድረኩ ላይ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮችን ጨምሮ የዘርፉ ባለሙያዎችና የወላጅ መምህራን ህብረት ኮሚቴዎች ተሳትፈዋል።
የሚታይ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለ1 ሺህ 460 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ
Apr 19, 2024 42
ባህር ዳር ፤ ሚያዝያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የይቅርታ አዋጁን ያሟሉ 1 ሺህ 460 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ማድረጉን የክልሉ ፍትህ ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሽም ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ የክልሉ መንግስት በበጀት ዓመቱ ለ2ኛ ጊዜ በሰጠው ይቅርታ ከሚያዚያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ይቅርታ የተደረገላቸው 1ሺህ 460 የህግ ታራሚዎች ከእስር እንዲፈቱ ወስኗል። የይቅርታ ተጠቃሚ ከሆኑት የህግ ታራሚዎች መካከል 29ኙ ሴቶች ሲሆኑ 1ሺህ 431ዱ ደግሞ ወንዶች መሆናቸውን አመልክተዋል። የህግ ታራሚዎቹ የይቅርታ ተጠቃሚ የሆኑት ይቅርታ በማያስከለክሉ ወንጀሎች ተሳትፈው በማረሚያ ቤት የቆዩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ተጠቃሚዎቹ ከግል ተበዳይ ጋር የታረቁና የካሱ፣ በጤና ችግርና በዕድሜያቸው የገፉ፣ አብዛኛውን የእስር ጊዜ ያጠናቀቁ እንዲሁም በቆይታቸው የባህሪ ለውጥ ማምጣታቸው የተረጋገጠላቸው መሆኑንም አስረድተዋል። ይሁን እንጂ በዘር ማጥፋት፣ በአስገድዶ መድፈር፣ ሰውን አስገድዶ በመሰወር፣ ከ10 ዓመትና ከዛ በላይ በሚያስቀጣ የሙስና ወንጀል በፈፀሙ፣ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል የተሳተፉ እንዲሁም በሽብርተኝነትና በመሰረተ ልማት ማውደም ወንጀል የተሳተፉ ታራሚዎች የይቅርታው ተጠቃሚ እንዳልሆኑ ገልጸዋል። በፈፀሙት ወንጀል ታርመው የይቅርታው ተጠቃሚ የሆኑ የህግ ታራሚዎችም ወደ አካባቢያቸው ሲመለሱ የበደሉትን ህብረተሰብ በልማት ሊክሱ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ህብረተሰቡም የህግ ታራሚዎቹ በፈጸሙት ጥፋት የተፀፀቱና በአግባቡ ታርመው የወጡ መሆኑን በመረዳት ከእስር የተለቀቁ ታራሚዎች ኑሯቸውን በተረጋጋ ሁኔታ እንዲመሩ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል። የክልሉ ምክር ቤት ቀደም ሲል የይቅርታ ተጠቃሚ ሆነው ከማረሚያ ቤት ከወጡ በኋላ ሦስት ዓመት ሳይሞላቸው ሌላ ወንጀል ፈፅመው የተገኙ አምስት የህግ ታራሚዎች ቀደም ሲል የተሰጣቸው ይቅርታ እንዲሰረዝ መወሰኑንም አቶ ብርሃኑ ገልጸዋል።  
ኢትዮጵያ ለስታርት አፕ የሰጠችው ትኩረት የዲጅታል ኢኮኖሚ ግንባታ ርዕይና ተስፋዋን የሚያሳካ ነው- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Apr 19, 2024 59
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ለስታርት አፕ የሰጠችው ትኩረት የዲጅታል ኢኮኖሚ ግንባታ ርዕይና ተስፋዋን የሚያሳካ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተውን የስታርት አፕ ኢትዮጵያ አውደ ርዕይ ጎብኝተዋል።   በጉብኝታቸውም ኢትዮጵያን በብዙ መልኩ የሚጠቅሙ ችግር ፈቺ የፈጠራ ሀሳቦችን መመልከታቸውን ተናግረዋል። ሀገርን ሊያሳድጉ የሚችሉ የፈጠራ ሀሳቦች ያሏቸው ወጣቶችና ታዳጊዎችን የኢትዮጵያ እድገት ተስፋዎች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ መንግስት ይህንን በመገንዘብ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት መስጠቱን አንስተዋል።   10 ዓመቱ የልማት እቅድ የገቢና ወጪ ምርቶችን ለማመጣጠንና የቴክኖሎጂ ፈጠራን ለማሳደግ የተያዘውን ሀገራዊ ግብ ለማሳካት ስታርት አፖች ሚናቸው ትልቅ ነው ብለዋል። መንግስት ስታርት አፖችን ለማጠናከር እየሰራ ስለመሆኑ አንስተው፤ ለአብነትም ምርቶቻቸውን ገዝቶ መጠቀምን የሚያበረታታ እንዲሁም የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያገኙ የሚያደርጉ የፖሊሲ አቅጣጫዎችንና የህግ ማዕቀፎችን ወደ ስራ ማስገባቱን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂና በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ብዙ ተስፋ እንዳላት ገልጸው፥ ኢትዮ ቴሌኮም አካታች የዲጅታል ኢኮኖሚ ስርዓትን በማሳለጥ ትላልቅ ስራዎችን እያከናወነ ነው ብለዋል። በተለይ በቴሌ ብር አገልግሎት አነስተኛ ብድሮችን በማቅረብ እና አርሶና አርብቶ አደሩን ጭምር የሚያሳትፉ ማዕቀፎችን በመተግበር ትልቅ እምርታ እያስመዘገበ እንደሆነ ጠቅሰዋል። በሰው ሰራሽ አስተውሎትና በቴክኖሎጂ ፈጠራ ያሉ ጅምሮች ኢትዮጵያ ያላትን ግዙፍ ራዕይ ማሳካት እንደሚቻል የሚያሳዩ መሆናቸውን አስረድተዋል። የመንግስት አገልግሎትን ለማዘመን ትልቅ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸው፤ በተለይም ቴክኖሎጅን ያወቀና የአገልጋይነት መንፈስ ያለው የሰው ኃይል ለመገንባት በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል ኢትዮጵያ በቀጣናው ብሎም በአፍሪካ የዲጅታል ኢኮኖሚ ማዕከል ለመሆን እየሰራች መሆኑንም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ ሀገራዊ የብልፅግና ጉዞን ለማሳካት በየክልሎች ያሉ ስታርት አፖችን ሁሉም ሊያበረታታ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡            
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ላሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚውሉ 150 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን አስረከበ
Apr 19, 2024 254
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2016(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስሩ ለሚገኙና ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ላሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚውሉ 150 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን አስረከበ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተሽከርካሪዎቹን ቁልፍ ለተቋማቱ አስረክበዋል። ከንቲባዋ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልእክት ከተማ አስተዳደሩ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ማዘመን ላይ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ በዚህም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ከዚህ አኳያ ተሽከርካሪዎቹ የከተማዋን ገጽታ የሚመጥኑና አገልግሎት አሰጣጡን የሚያቀላጥፉ ስለመሆናቸውም አንስተዋል። ተሽከርካሪዎቹ በከተማዋ ለሚገኙ ሁሉም ክፍለ ከተሞችና በስራቸው ላሉ ወረዳዎች እንደሚውሉም ጠቁመዋል፡፡    
የተሳታፊ ልየታ በተከናወነባቸው አካባቢዎች የአጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረኮችን ለመጀመር የሚያስችሉ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል-- የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን
Apr 19, 2024 143
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ ለአገራዊ ምክክሩ የተሳታፊ ልየታ በተከናወነባቸው አካባቢዎች የአጀንዳ ማሰባሰቢያ ህዝባዊ መድረኮች ለመጀመር የሚያስችሉ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እንደ ሀገር በሚስተዋሉ ችግሮች ላይ በመወያየት በዘላቂነት ለመፍታት፣ ብሔራዊ መግባባትና ሀገራዊ አንድነት ለመፍጠር በአዋጅ የተቋቋመ ገለልተኛ ተቋም ነው፡፡ ኮሚሽኑ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 1265/2014 ፀድቆ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቃል አቀባይ ጥበቡ ታደሰ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ከሚሽኑ ኃላፊነቱን ተረክቦ ወደ ሥራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ለምክክሩ ስኬት የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ሲያሰባስብ ቆይቷል፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ለምክክሩ ውጤታማነት አስፈላጊ በሆኑ የተሳታፊ ልየታ መድረኮች መካሄዳቸውን ገልጸዋል፡፡ በዚህም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና የህዝብ አደረጃጀቶች ጋር ሰፊ የውይይት መድረኮች በማዘጋጀት ተጨባጭ ውጤት ተገኝቷል ብለዋል፡፡ በተሳታፊ ልየታው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማህበራት፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ የዳያስፖራና የተለያዩ ትምህርት ተቋማት፣ በዕድሜና ጾታ ጭምር ተካተዋል ብለዋል። የተሳታፊ ልየታ ባልተከናወነባቸው አካባቢዎች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ስራዎችን ለማጠናቀቅ እንደሚሰራም ጠቁመዋል፡፡ በተጨማሪም ኮሚሽኑ ምክክር የሚደረግባቸው የአጀንዳ ሀሳቦችን ከጥናቶች፣ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ከህዝባዊ መድረኮች የማሰባሰብ ስልጣን እንደተሰጠው ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም የተሳታፊ ልየታ በተደረገባቸው ክልሎች የአጀንዳ ሀሳብ ለማሰባሰብ የሚያስችሉ ህዝባዊ መድረኮችን ለመጀመር የሚያስችሉ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን አብራርተዋል፡፡ ምክክር ኮሚሽኑ በሀገሪቱ ከሚገኙ ከአንድ ሺህ 300 ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚሳተፉ ተሳታፊዎች ጋር የአጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረኮችን ያዘጋጃል ብለዋል፡፡  
ማስታወቂያ
ኢዜአ
Feb 7, 2023 17723
ኢዜአ
ፖለቲካ
መንግስት ለሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ተግባራዊነት በቁርጠኝነት ይሰራል-- ተስፋዬ በልጅጌ
Apr 19, 2024 31
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ መንግስት ለሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ተግባራዊነትና ውጤታማነት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ ገለጹ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤን ጨምሮ የዴሞክራሲ ተቋማት አመራሮችና ሌሎች በተገኙበት በሽግግር ፍትህ ፖሊሲና የፌደራል የአስተዳደር ስነ-ስርአት አዋጅ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ በዚሁ ጊዜ የተለያዩ የዓለም አገራት ከተወሳሰበ ችግርና ቀውስ ለመውጣት የሽግግር ፍትህን መፍትሄ አድርገው መጠቀማቸውን አንስተዋል፡፡ በኢትዮጵያም በቀደሙ ስርዓቶች የተፈጸሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ በታሪክ ምክንያት የሚነሱ አለመግባባቶች፣ የዴሞክራሲ ስርዓት አለመጎልበት፣ ለዘመናት የተከማቹ የፖለቲካ ቀውሶች መኖራቸውን ጠቅሰው፤ ለእነዚህ ችግሮች እልባት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡ ከዚህ አኳያ ከአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር የሚመጋገብና ሂደቱን የሚያሳልጥ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። መንግስት ፖሊሲው እንዲዘጋጅ ከማድረግ ጀምሮ ቁርጠኛ የፖለቲካ አቋም መውሰዱን ገልጸው፤ይህም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አብራርተዋል፡፡ የአሁኑ ትውልድ ችግሮችን ቀርፎ ኢትዮጵያን ወደ አዲስ ምእራፍ የማሸጋገር ኃላፊነት እንዳለበትም ነው የተናገሩት፡፡ ፖሊሲ ለረዥም ጊዜ ስር የሰደዱ ችግሮችን በመፍታት ከችግር መውጫ አንዱ መሳሪያ መሆኑንም አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል። የትናንት ቁርሾዎችን በእርቀ ሰላምና ይቅርታ በመዝጋት ለነገ ትውልድ የተረጋጋችና ዘላቂ ሰላም የሰፈነባት አገር ማስተላለፍ እንደሚገባም አንስተዋል፡፡ በዚህ ረገድ መንግስት የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ለፖሊሲው ተፈጻሚነት በጋራ መስራት እንደሚገባ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ የፖሊሲው ወቅታዊነትን በሚመለከትም ከተሳታፊዎች ጥያቄ ቀርቧል፡፡ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በምላሻቸው አገራዊ የሆኑ ችግሮች በይደር የሚታለፉ አለመሆናቸውን ጠቅሰው፤ ችግሮቹን በአንድነት ለመፍታት ጊዜው አሁን መሆኑን አስረድተዋል። በኢትዮጵያ ገለልተኛ ተቋማትን በማደራጀት ነጻና ገለልተኛ ሆነው እንዲሰሩ ለማድረግ የተጀመረው ስራ ለፖሊሲው ተፈጻሚነትም አስቻይ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥርም አንስተዋል። በሌላ በኩል የፌደራል የአስተዳደር ስነ-ስርአት አዋጅ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠትና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ሚናው የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ አዋጁ አጠቃላይ የተጀመረው ለውጥ ስራ አካል መሆኑን በመጥቀስ ይህም የአሰራር ማነቆዎችን በመፍታት፣ አደረጃጀትን በማስተካከል፣ አገልግሎትን በማሻሻል ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ነው ያሉት። አዋጁ የታለመለትን ዓላማ እንዲያሳካ የተቋማት ኃላፊዎችና ሙያተኞች ተግባራዊነቱ ላይ በልዩ ትኩረት መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።    
አቶ አደም ፋራህ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ጋር ተወያዩ
Apr 19, 2024 214
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣዎ ዢዋን ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸው የጋራ ተጠቃሚነትን ለማስፋት፣ የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር እንዲሁም የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስፋት ዙሪያ መክረዋል፡፡ አቶ አደም ፋራህ የኢትዮ-ቻይና ዘመናትን የተሻገረ ወዳጅነት ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠሉንና የቻይናው ኮሙኒስት ፓርቲ አጋርነትም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ጠቅሰዋል። ከዚህ በፊት በሁለቱ ፓርቲዎች ስምምነት መሰረት በትምህርት፣ በስልጠና እንዲሁም በተሞክሮና ልምድ ልውውጥ አብሮ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ስምምነት መደረጉን አንስተዋል፡፡ በቅርቡ የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ተሳታፊ የሆኑበት የልዑካን ቡድን ውጤታማ ቆይታ አድርጎ መመለሱም የዚህ ስምምነት አካል መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ ለልዑካን ቡድኑ ለተደረገው አቀባበልና ስኬታማ የቆይታ ጊዜ ያላቸውን ምስጋና ገልጸዋል። በቀጣይም የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነቶች በመሰል የስልጠናና የልምድ ልውውጥ መርሐ ግብሮች ተጠናክሮ እንዲቀጥል ብልፅግና ፓርቲ ፍላጎቱ እንደሆነ ማብራራታቸውን ከፓርቲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡ አምባሳደር ዣዎ ዢዋን በበኩላቸው የብልፅግና ፓርቲ በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ እየሰራቸው ያሉ ውጤታማ ስራዎችን አድንቀዋል፡፡ ኢትዮጵያ የቻይና ጠንካራ ስትራቴጂክ አጋር መሆኗን ጠቅሰው ይህ ግንኙነት በፓርቲ ለፓርቲም ሆነ በመንግስታዊ ወዳጅነት ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲያድግ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
ዜጎች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባትና የተቀራረበ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የምሁራን ሚና ከፍተኛ ነው-ዶክተር ከይረዲን ተዘራ
Apr 19, 2024 123
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ ዜጎች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባትና የተቀራረበ ግንዛቤ እንዲይዙ ምሁራን የላቀ ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ከይረዲን ተዘራ ገለጹ። የሰላም ሚኒስቴር "ዘመኑን የዋጀ አርበኝነት ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ ሀገር አቀፍ የንቅናቄ መድረክ ያስጀመረ ሲሆን በእለቱ ከዩኒቨርሲቲ ምሁራን ተወካዮች ጋር ውይይት ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ከይረዲን ተዘራ ከዚህ ቀደም "አድዋን ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ" በሚል መሪ ሃሳብ ከ 40 በላይ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር ውይይት መካሔዱን አስታውሰዋል። በመድረኮቹ የጋራ ማንነት ፣ እሴት እና ሀገራዊ ጥቅም ላይ ያተኮሩ ስኬታማ ውይይቶች መደረጋቸውን በማስታወስ ኩነቱ በቀጣይ ለሚካሔዱ የንቅናቄ መድረኮች ትልቅ ግብአት የተገኘበት መሆኑን ተናግረዋል። ምሁራን መሰል ሀሳቦችን በማውረድ፣ በማወያየት እና በማዳበር በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባትና የተቀራረበ ግንዛቤ እንዲኖር ለማስቻል የላቀ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል። "ዘመኑን የዋጀ አርበኝነት ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ ይፋ የተደረገው ንቅናቄም በተመሳሳይ መልኩ የሚተገበር መሆኑን ተናግረዋል። በሁሉም ዘርፍ ለሀገር ልማትና ብሄራዊ ጥቅም ታማኝ ሆኖ መስራት ከዜጎች የሚጠበቅ ተግባር በመሆኑ በተለይም ምሁራን በዚህ ረገድ ብዙ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። በዩኒቨርሲቲዎች የተቋቋሙ ፎረሞች በዚህ ረገድ ከፍ ያሉ ሀሳቦችን በማንሳት ውይይት በማድረግ ለንቅናቄው ስኬት የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። የውይይቱ ተሳታፊ ምሁራን በበኩላቸው ለውይይቱ የሚረዱ አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል። በሀገሪቱ ያለው የውይይት ባህል እንዲዳብርና በመነጋገር የሚያምን ትውልድ እንዲፈጠር የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት እንደሚወጡ አረጋግጠዋል። በዚህ ረገድ ምሁራን ግንባር ቀደም ሚና መጫወት እንዳለባቸው ገልጸው ውይይቶቹ እንደ ከዚህ ቀደሞቹ የተሳኩ እንዲሆኑ በትኩረት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
የሽግግር  ፍትህ ፖሊሲ እና የፌዴራል አስተዳደር ሥነ ስርአት አዋጅ የዜጎች ሰብዓዊና ፍትሕ የማግኘት መብቶች እንዲከበሩ የሚያስችሉ ናቸው- አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ
Apr 19, 2024 104
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ እና የፌዴራል አስተዳደር ሥነ ስርአት አዋጅ የዜጎችን ሰብዓዊና ፍትሕ የማግኘት መብት የሚያስከብሩ መሆናቸውን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ተናገሩ። በፌደራል አስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ እና በሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ትግበራ ላይ ያተኮረ ውይይት መድረክ ተካሂዷል። የሕዝብ ተወካየች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የዴሞክራሲ ተቋማት የስራ ሃላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በውውይቱ ተሳትፈዋል። አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ በዚህ ወቅት እንዳሉት በኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አግባብ ባለው፣ በተቀናጀና አሳታፊ በሆነ መልኩ መፍትሄ ሳይሰጣቸው ቆይተዋል። በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሽግግር እና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሽግግር ፍትህ ሂደት መተግበር "ጠቃሚ ብቻ ሳይሆን እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ሀገራዊ አውዱ ያመላክታል" ብለዋል። የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው ተጎጂዎችን ማዕከል ያደረገ፣ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መርሆችና ድንጋጌዎችን ያከበረ፣ የሀገሪቱን ፖለቲካና ማህበራዊ ዐውዶችን ባገናዘበ መልኩ መዘጋጀቱን አንስተዋል። ፖሊሲው በገለልተኛ ባለሙያዎች ቡድን የተዘጋጀ፣ በባለድርሻ አካላትና ምሁራን ውይይት ተደርጎበት የጸደቀ መሆኑን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የነበሩ ቁስሎችን ሊያሽር፣ ቁርሾዎችን ሊያስቀር የሚያስችል የመፍትሔ ሀሳቦችን ይዞ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። መንግስት የዜጎችን ፍትህ የማግኘት መብት እንዲሁም የህግ የበላይነት እንደረጋገጥና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የሚያስችል የፌዴራል አስተዳድር ሥነ ስርዓት አዋጅ ተግባራዊ ማድረጉንም ተናግረዋል። ሁለቱ የሕግ ማዕቀፎች የዜጎች ሰብዓዊ መብት እና ፍትህ የማግኘት መብት እንዲረጋገጥ ካመቻቸው ጉልህ ፋይዳ አኳያ ፍትህ ሚኒስቴርን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት ለተፈጻሚነቱ እንዲሰሩ አሳስበዋል። የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በበኩላቸው ዘመናዊ የመንግስት ስርዓት ከተጀመረ ረጅም ጊዜ ቢሆነውም የህግ ማዕቀፍ ባለመኖሩ የተለያዩ ጉድለቶችና የዘፈቀደ ውሳኔዎች ይስተዋሉ ነበር ብለዋል። በዚህም የመልካም አስተዳደር ችግር መስተዋሉን ገልጸው፤ እንደዚህ አይነት የህግ ማዕቀፎች ለብዙ ችግሮች መፍትሄ እንደሚሆኑ ተናግረዋል። የህግ ማዕቀፎችን ማዘጋጀት ወሳኝ እርምጃ ቢሆንም ለተግበራዊነታቸው ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል። የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ በጥንቃቄና አሳታፊነቱን ተጠበቆ የተዘጋጀ፣ የላቀ ሀገራዊ ጠቀሜታ ያለው ፖሊሲ በመሆኑ ለትግበራው የባለድርሻ አካላትን ትብብርና ክትትል እንደሚጠይቅ ገልጸዋል። በዚህም በቀጣይ የማስፈጸሚያ የሕግ ማዕቀፍ በማውጣት የሽግግፍ ፍትሕ ፖሊሲውን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።    

ወጣቶች ሰላማቸውን በማስጠበቅ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የጀመሩትን ጥረት ማጠናከር አለባቸው - አቶ እንዳሻው ጣሰው
Apr 19, 2024 97
ወልቂጤ ፤ ሚያዝያ 11/ 2016(ኢዜአ)፦ወጣቶች የአካባቢያቸውን ሰላም በማስጠበቅ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የጀመሩትን ጥረት ማጠናከር እንዳለባቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ እንዳሻው ጣሰው ገለጹ። ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ከጉራጌ ዞን የተለያዩ መዋቅሮች ከተወጣጡ ወጣቶች ጋር በወጣቶች የልማትና የመልካም አስተዳደር ተሳትፎና ተጠቃሚነት ላይ እየተወያዩ ነው። ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት የክልሉ ወጣቶች የአካባቢያቸውን ሰላም በማስጠበቅ የልማትና መልካም አስተዳደር ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የጀመሯቸውን አበረታች ሥራዎች ማጠናከር አለባቸው። ሰላም ለሁሉም መሠረት በመሆኑ ሰላማቸውን በቅንጅት ከማጠናከር ባለፈ በአካባቢያቸው የልማት ሥራዎች ተሳታፊና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። ወጣቱ ትውልድ በመደመር ዕሳቤ ለውይይትና ለውስጥ ሰላሙ ትኩረት ሰጥቶ መንቀሳቀስና ገዥ ትርክቶችን አጉልቶ ማውጣት እንዳለበትም ተናግረዋል። አቶ እንዳሻው እንዳሉት ወጣቱ አዳዲስ እሳቤዎችን እያፈለቀና ባለው ላይ እየጨመረ የብልጽግና ጉዞን ለማፍጠን የሚደረገውን ጥረት ማገዝ አለበት። በተለይ የሚያግባቡ እና የሚያስተሳስሩ ጉዳዮች አጉልቶ በማውጣትና የወል ትርክቶችን በማጠናከር የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ለማፋጠን መረባረብ ይኖርበታል። ልማትን ለማጠናከር ዘላቂ ሰላምና የህዝቦች አንድነት ወሳኝ መሆኑን የገለጹት አቶ እንደሻው፣ በክልሉ ሁለንተናዊ ልማትን ለማፋጠን እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ወጣቶች የበኩላቸውን እገዛ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።      
ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ እና ማምረቻ ኢንዱስትሪ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጡ
Apr 19, 2024 130
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/ 2016(ኢዜአ)፦የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ እና ማምረቻ ኢንዱስትሪ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጡ። የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ከተመሰረተ በርካታ ዓመታትን ያሳለፈው የመከላከያ ኢንዱስትሪ ዘመኑ ከደረሰበት የዕድገት ደረጃ ለማድረስ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ገልፀው፣ የፋብሪካው ግንባታ ለሀገርና ለተቋሙ የሚሰጠው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።   ኢንዱስትሪው በአዲስ መልኩ ከተደራጀ በኋላ በተሰሩት ስራዎች ከኪሳራ ወደ ትርፋማነት መሸጋገሩን የገለፁት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ የኮርፖሬሽኑ አመራርና አባላቶች ለነበራቸው ቁርጠኝነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ተቋሙ የራሱን ገቢ በማመንጨት ለሰራዊቱ መሰረታዊ ጥቅም ለማሟላት አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ የሰራዊቱን የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለማድረግና ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ በኢንዱስትሪ ፤ በግብርና ፣ በማዕድንና በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ከተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር ለመስራት የተቀመጠው አቅጣጫ ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል።   የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ሀይለማርያም የመከላከያ የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ እና ማምረቻ ኢንዱስትሪ ከሽርሽር ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር በመሆን የሚገነባው መሆኑን ተናግረዋል። ኢንዱስትሪው በሰላሳ ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍና በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ መታቀዱንም ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል። አለም አቀፍ ስታንዳርዳቸውን ያሟሉ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ከመገጣጠምና ከማምረት ባለፈ በቀጣይ ፕሮጀክቱን የማስፋፋት ዕቅድ እንዳላቸው የገለፁት ዳይሬክተሩ ለፕሮጀክቱ ስኬት ያልተቋረጠ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግም ጠቁመዋል። በዝግጅቱ ላይ የመከላከያ ሚንስቴር ዲኤታ አቶ ቶማስ ቶት ፣የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ ና ወታደራዊ አታሼዎች እንዲሁም ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮች መገኘታቸውን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመለክታል።
ኮሚሽኑ በመሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሀገራዊ መግባባት እንዲፈጠር ሀላፊነቱን እየተወጣ ነው---ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ
Apr 19, 2024 103
ሻሸመኔ፤ ሚያዚያ 11/2016 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በመሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሀገራዊ መግባባት እንዲፈጠር ሀላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ገለጹ። በኦሮሚያ ክልል በዞን፣ በወረዳና በከተማ አስተዳደር ደረጃ በምክክር ሂደቱ የሚሳተፉ የህብረተሰብ ተወካዮች ልየታ የማጠቃለያ መድረክ በሻሸመኔ ከተማ እየተካሄደ ነው። በመርሀ ግብሩ ላይ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ እና ምክትል ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ሒሩት ገብረስላሴ ተገኝተዋል። ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን በመድረኩ እንደገለጹት ኮሚሽኑ እጅግ መሰረታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሀገራዊ መግባባት እንዲፈጠር የተጣለበትን ሀላፊነት በአግባቡ ለመወጣት እየሰራ ነው። የተጣለበትን ተልዕኮ ለመወጣት ገለልተኛ ተቋማትና ተባባሪ አካላትን ጭምር በማሳተፍ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ገልጸዋል። በእዚህም ኮሚሽኑ የምክክር አጀንዳዎችን ከህብረተሰቡ ጋር የመቅረፅ፣ አጀንዳዎቹ ምክክር እንዲደረግባቸው የማመቻቸት እና ምክክሮችና ውይይቶችን የማሳለጥ ሃላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ነው ፕሮፌሰር መስፍን ያስታወቁት በኦሮሚያ ክልል የተሳታፊ ልየታ ሂደቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ የክልሉ መንግስት፣ የሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር፣ ተባባሪ አካላትና ተሳታፊዎች ላደረጉት አስተዋጾም በኮሚሽኑ ሥም ምስጋና አቅርበዋል በሻሸመኔ ከተማ እየተካሄደ ባለው የማጠቃለያ የማህበረሰብ ተወካዮች ልየታ መድረክ ከምስራቅ ቦረና ዞን የነገሌ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ ከዋጭሌ፣ ዳሳ፣ አሬሮ፣ መደወላቡ፣ ጉሮዶላ እና ሊበን ወረዳዎች የተውጣጡ 500 የሚጠጉ የህብረተሰብ ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ። በመድረኩ የሀገራዊ ምክክር ምንነትና አስፈላጊነት እንዲሁም የአመራረጥ ሂደቱን በማስመልከት ለተሳታፊዎች ገለጻ ተደርጓል። የኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን ወደስራ ከገባ ጀምሮ በክልሎችና በከተማ መስተዳደሮች በርካታ የቅድመ ዝግጅት እና የተሳታፊ ልየታ ሥራዎችን አከናውኗል። በቀጣይም ኮሚሽኑ የተሳታፊዎች ልየታ ባልተከናወነባቸው ክልሎች ልየታ በማድረግ አጀንዳዎችን በህዝባዊ ውይይቶች በማሰባሰብ ምክክሮች እንዲካሄዱ ያድርጋል። በእዚህም አለመግባባቶችን ለመፍታት የሚያግዙ የሀገር ሽማግሌዎችንና በማህበሩሰቡ መካከል ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑትን የመለየትና ተቀራርቦ የመወያየት ስራዎችን እንደሚያከናወኑ ታውቋል። በምክክር ሂደቱ ውጤታማና በሃገሪቱ የተሻለ የሰላምና የፖለቲካ መደላድል እንዲፈጠር ሁሉም የበኩሉን አስተዋጾ ማበርከት እንዳለበት ኮሚሽኑ በተለያዩ ጊዜያት ጥሪ ማቅረቡም የሚታወስ ነው።        

ማህበራዊ
በደብረብርሃን ከተማ ለተፈናቃይ ወገኖች ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ምግብ ድጋፍ ተደረገ
Apr 19, 2024 0
ደብረ ብርሀን ፤ ሚያዚያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ በደብረ ብርሀን ከተማ አስተዳደር በመጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የምግብ እህል ድጋፍ መደረጉን የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የጽህፈት ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ወይዘሮ ቀለሟ ኃብቴ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያና በዘመድ ቤት ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ ሲደረግ ቆይቷል። ዛሬ በደብረ ብርሀን ከተማ አስተዳደር በጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ 19ሺህ 210 ወገኖችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የምግብ እህል ድጋፍ ከፌደራል መንግስት መደረጉን ገልፀዋል። ድጋፉ 26 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው 2ሺህ 882 ኩንታል ስንዴ እና 210 ኩንታል አልሚ ምግብ መሆኑን ጠቁመው፣ በቀጣይም በእንሳሮና በምንጃር ሸንኮራ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፉ ይቀጥላል ብለዋል። የድጋፉን ፍታሃዊነት ለማረጋገጥም ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፣ ሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።   የድጋፉ ተጠቃሚ አቶ መሐመድ ይመር እንዳሉት፤ እስካሁን በመንግስት፣ መንግስታዊ ባልሆኑ አካላት እና በአካባቢው ነዋሪዎች በተደረገላቸው ድጋፍ ህይወታቸውን ማቆየታቸውን ገልጸዋል። የዛሬው ድጋፍ ወቅታዊ ችግራቸውን እንደሚያቃልል ጠቁመው፣ በቀጣይም መሰል ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል። ወይዘሮ ሀዋ አበባው በበኩላቸው ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው፤ በቀጣይ መንግስት ሰላምን በማረጋገጥ ወደ መጡበት ቄዬ እንዲመልሳቸው ጠይቀዋል። በሰሜን ሸዋ ዞን ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች እና በዘመድ ቤት የሚኖሩ 89 ሺህ 215 ወገኖች እንዳሉ መረጃዎች ያሳያሉ።  
የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ሁሉም በትብብር ሊሰራ ይገባል-አቶ ኡሞድ ኡጁሉ
Apr 19, 2024 37
ጋምቤላ ፤ ሚያዚያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል የትምህርት ቤቶችን ደረጃና ግብዓት በማሻሻል የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ገለጹ። የክልሉ የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ዛሬ በጋምቤላ ከተማ ተካሄዷል ።   ርዕሰ መስተዳድሩ በግምገማ መድረኩ ላይ እንደተናገሩት፤ የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማትና ግብዓት በማሻሻል የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ሊጠናከር ይገባል። ''የትምህርት ቤቶችን ደረጃና ግብዓት በማሻሻል የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ "ትምህርት ለትውልድ " በሚል አገር አቀፍ ንቅናቄ ወደ ስራ የተገባ ቢሆንም እንደ ክልል የተከናወኑት ተግባራት በቂ አይደሉም'' ብለዋል። በክልሉ ትምህርት ቤቶችን ተደራሽ በማድረግ ረገድ የተሻለ አፈፃፀም ቢኖርም ትምህርት ቤቶቹ የደረጃና የግብዓት ችግር ያለባቸው መሆኑን ገልጸዋል ። በመሆኑም በዘርፉ የተጀመሩ የንቅናቄ ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል የታለመውን ግብ ለማሳካት የአመራሩ፣ የዘርፉ ባለሙያዎችና የመላው ማህበረሰብ ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል ። የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ላክደር ላክባክ በበኩላቸው ባለፉት ዘጠኝ ወራት የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻልና በግብዓት ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል። በክልሉ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተጀመረው የምገባ መርሃግብር የተማሪዎችን መጠነ ማቋረጥ በመቀነስ ረገድ ፋይዳዉ የጎላ መሆኑን ገልፀዋል። ይሁን እንጂ የምገባ መርሃ ግብሩን ሳይቆራረጥ ለማስቀጠል እንዲቻል የመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እገዛ ሊጠናከር እንደሚገባም ተናግረዋል። የግምገማ መድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሻሻል ጎን ለጎን የመምህራንን አቅም ማጎልበት እንደሚገባም ሃሳብ ሰንዝረዋል። በግምገማ መድረኩ ላይ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮችን ጨምሮ የዘርፉ ባለሙያዎችና የወላጅ መምህራን ህብረት ኮሚቴዎች ተሳትፈዋል።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለ1 ሺህ 460 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ
Apr 19, 2024 42
ባህር ዳር ፤ ሚያዝያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የይቅርታ አዋጁን ያሟሉ 1 ሺህ 460 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ማድረጉን የክልሉ ፍትህ ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሽም ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ የክልሉ መንግስት በበጀት ዓመቱ ለ2ኛ ጊዜ በሰጠው ይቅርታ ከሚያዚያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ይቅርታ የተደረገላቸው 1ሺህ 460 የህግ ታራሚዎች ከእስር እንዲፈቱ ወስኗል። የይቅርታ ተጠቃሚ ከሆኑት የህግ ታራሚዎች መካከል 29ኙ ሴቶች ሲሆኑ 1ሺህ 431ዱ ደግሞ ወንዶች መሆናቸውን አመልክተዋል። የህግ ታራሚዎቹ የይቅርታ ተጠቃሚ የሆኑት ይቅርታ በማያስከለክሉ ወንጀሎች ተሳትፈው በማረሚያ ቤት የቆዩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ተጠቃሚዎቹ ከግል ተበዳይ ጋር የታረቁና የካሱ፣ በጤና ችግርና በዕድሜያቸው የገፉ፣ አብዛኛውን የእስር ጊዜ ያጠናቀቁ እንዲሁም በቆይታቸው የባህሪ ለውጥ ማምጣታቸው የተረጋገጠላቸው መሆኑንም አስረድተዋል። ይሁን እንጂ በዘር ማጥፋት፣ በአስገድዶ መድፈር፣ ሰውን አስገድዶ በመሰወር፣ ከ10 ዓመትና ከዛ በላይ በሚያስቀጣ የሙስና ወንጀል በፈፀሙ፣ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል የተሳተፉ እንዲሁም በሽብርተኝነትና በመሰረተ ልማት ማውደም ወንጀል የተሳተፉ ታራሚዎች የይቅርታው ተጠቃሚ እንዳልሆኑ ገልጸዋል። በፈፀሙት ወንጀል ታርመው የይቅርታው ተጠቃሚ የሆኑ የህግ ታራሚዎችም ወደ አካባቢያቸው ሲመለሱ የበደሉትን ህብረተሰብ በልማት ሊክሱ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ህብረተሰቡም የህግ ታራሚዎቹ በፈጸሙት ጥፋት የተፀፀቱና በአግባቡ ታርመው የወጡ መሆኑን በመረዳት ከእስር የተለቀቁ ታራሚዎች ኑሯቸውን በተረጋጋ ሁኔታ እንዲመሩ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል። የክልሉ ምክር ቤት ቀደም ሲል የይቅርታ ተጠቃሚ ሆነው ከማረሚያ ቤት ከወጡ በኋላ ሦስት ዓመት ሳይሞላቸው ሌላ ወንጀል ፈፅመው የተገኙ አምስት የህግ ታራሚዎች ቀደም ሲል የተሰጣቸው ይቅርታ እንዲሰረዝ መወሰኑንም አቶ ብርሃኑ ገልጸዋል።  
የረጅም ዘመን የሃይማኖት ታሪክ ባላት ኢትዮጵያ የሚገኙ ሃይማኖት አባቶች ለቀጣናው ሰላም መስራት ይጠበቅባቸዋል አብድረህማን እስማዔል
Apr 19, 2024 44
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2016 (ኢዜአ)፦"የረጅም ዘመን የሃይማኖት ታሪክ ባላት ኢትዮጵያ የሚገኙ ሃይማኖት አባቶች ከአገር ውስጥ ባለፈ ለቀጣናው ሰላም መስራት ይጠበቅባቸዋል'' ሲሉ የኬንያ የሃይማኖት ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር አብድረህማን እስማዔል ተናገሩ፡፡ በየትኛውም የአለም ክፍል የህዝቦችን አብሮነት፣ መቻቻል፣ ፍቅርና ሰላም በማረጋገጥ ረገድ የሃይማኖት አባቶች ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው። የአንድን አገር ሰላም የማረጋገጥ ሃላፊነት በዋናነት የመንግስት ቢሆንም ዜጎች ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን በአግባቡና ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲወጡ ከሚያግዙ አካላት መካከል የሃይማኖት አባቶች ግንባር ቀደም ናቸው፡፡ የሃይማኖት አባቶች በተለያዩ ቦታዎች የሚታዩ የፀጥታ መደፍረስና አለመረጋጋቶችን በሰላም ለመፍታት ሚናቸው የጎላ ነው፡፡ በተለይ በምስራቅ አፍሪካ የሚከሰቱ የእርስ በእርስ ግጭቶች ለሰዎች ህይወት መጥፋት እና ለንብረት መውደም ምክንያት እንዳይሆኑ በቀጣናው አገራት ያሉ የሃይማኖት አባቶች ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው። በአካባቢው የሚታዩ ግጭቶች ተወግደው በቀጣናው ሰላም እንዲሰፍን የእምነት አባቶች ሚና ምን ሊሆን ይገባል ሲል ኢዜአ ከኬንያ የሃይማኖት ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር አብዱራህማን እስማዔል ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ እንዳሉት "የሃይማኖት አባቶች ሰዎች እንዴት እርስ በእርስ ተዋደውና ተፋቅረው መኖር እንዳለባቸው የማስተማር ኃላፊነት አለባቸው"፡፡ በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የእምነት አባቶች ጥላቻን በማስወገድ ሰዎች እርስ በእርስ ተዋደው እና ተፋቅረው እንዲኖሩ፣ እንዲሁም ልማት እንዲረጋገጥ በጋራ እያደረጉት ያለው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ስኬት ለአፍሪካ አገራት በተለይ ደግሞ የምስራቅ አፍሪካ ስኬት ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ሃይማኖት አባቶች ለቀጣናው ሰላም መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። በሰዎች መካከል የሚታየውን ጥላቻ በማስወገድ ፍቅር እንዲጎለብት እያደረጉት ያለውን ጥረት አድንቀው፤ በቀጣይም ይኽው ጥረታቸው ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉም ተናግረዋል ፡፡ በርካታ አማኞች ባሉባት ኢትዮጵያ የሃይማኖት አባቶች ስለሰላም አብዝተው በመስበክ ለአለም ምሳሌ ሊሆኑ እንደሚገባም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ፣ የክርስትና እና የእስልምና ሃይማኖቶች ለረጅም ዘመናት በሰላምና በፍቅር የሚኖሩባትና እየኖሩባት ያለች ታላቅ አገር መሆኗን ጠቅሰዋል፡፡ ነብዩ መሐመድ ተከታዮቻቸው ችግር ውስጥ በወደቁበት ወቅት ወደ ኢትዮጵያ ሂዱ ማለታቸው የሁለቱን ሃይማኖቶች የረዥም ጊዜ ቁርኝት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ ህብረ ብሔራዊነትን የተላበሰችው ታላቋ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን ታስፈልጋለች ይህችን ታላቅ ሀገር ለመገንባት ተባብሮ መስራት ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡ ይህን ማድረግም ከኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ባለፈ ጠቀሜታው ለቀጣናው አገራት ጭምር መሆኑን ተናግረዋል።  
ኢኮኖሚ
20ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ በዋሽንግተን ዲሲ ተካሔደ
Apr 19, 2024 27
  አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2016(ኢዜአ)፦ 20ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ በወቅቱ የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ ሊቀመንበር የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ መሪነት በዋሽንግተን ዲሲ ተካሒዷል። ሚኒስትሩ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) እና ዓለም ባንክ ስብሰባ ጎን ለጎን 20ኛውን የምስራቅ አፍሪካ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ መርተዋል።   በውይይቱም የአፍሪካ ቀንድ ሃገራት የገንዘብ ሚኒስትሮች፣ የልማት አጋሮች የአፍሪካ ልማት ባንክ፣ የአውሮፓ ህብረት የጀርመን እና የእንግሊዝ ተወካዮች መሳተፋቸው ተገልጿል። ሚኒስትሩ በውይይቱ ላይ እንደ አረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት ፣የሳኡዲ ልማት ፈንድ፣ ጃፓንና የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ያሉ አጋሮችን ተሳትፎ አመስግነዋል። አቶ አህመድ አያይዘውም ሌሎችም በአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ ማዕቀፍ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ኢኒሼቲቩ ባለፉት አምስት አመታት ሀብት በማሰባሰብ ረገድ ስኬታማ እንደነበር አስታውሰው፤ ይህ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አፅንኦት ሰጥተዋል። የምስራቅ አፍሪካ ኢንሼቲቭ ሰባት የአፍሪካ ቀንድ ሀገራትን በአባልነት አካትቶ በፈረንጆቹ 2019 የተመሰረተ ሲሆን በቀጠናው ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ለማጠናከር እየሰራ እንደሚገኝ ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።            
መንግስት ለግንባታ ዘርፍ የሰጠው ትኩረት በመንገድና ቤቶች ልማት ያለን ተሳትፎ እንዲጎለብት እድል ፈጥሮልናል - የሰንሻይን ኢንቨስትመንት ግሩፕ 
Apr 19, 2024 46
አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ መንግስት ለግንባታ ዘርፍ የሰጠው ትኩረት በመንገድና ቤቶች ልማት ያለን ተሳትፎ እንዲጎለብት እድል ፈጥሮልናል ሲሉ የሰንሻይን ኢንቨስትመንት ግሩፕ መስራችና ፕሬዝደንት ሳሙኤል ታፈሰ ተናገሩ። አገራዊ ለውጡን ተከትሎ መንግስት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች መካከል የመሰረተ ልማት ግንባታ ዋነኛው ነው። መንግስት በራሱ ከሚያከናውናቸው ስራዎች ባሻገር የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ እንዲጎለብትም ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ይገለጻል። የሰንሻይን ኢንቨስትመንት ግሩፕ መስራችና ፕሬዝደንት ሳሙኤል ታፈሰ፤ መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለግንባታው ዘርፍ የሰጠው ትኩረት ዘርፉ ይበልጥ እንዲነቃቃ ማድረጉን ነው ለኢዜአ የተናገሩት። ከዚህ ቀደም የመንገድ ግንባታዎች በስፋት በመንግስት ሲከናወኑ እንደነበር አስታውሰው፤ አሁን ላይ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ማድረጉን ተናግረዋል። በተጨማሪም በመንግስት የተጀመረው የ70/30 የቤቶች መርሃ ግብር በከተሞች የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመቅረፍ ካለው ሚና ባሻገር ለግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ትኩረት የሰጠ መሆኑን አንስተዋል። ይህም የግንባታውን ዘርፍ ይበልጥ እንዲነቃቃ የሚያደርግ ነው ብለዋል። የሰንሻይን ኢንቨስትመንት ግሩፕ ይህን እድል በመጠቀም በመንገድ ግንባታ እና በቤቶች ልማት ላይ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል። ለአብነትም በቅርቡ የደብረ ብርሃን አንኮበር መንገድ ሥራ ፕሮጀክትን አጠናቀው ማስረከባቸውን ጠቅሰዋል። እንዲሁም በ70/30 የቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመንግስት የተጀመረው የ70/30 የቤቶች መርሃ ግብር ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች የቤት ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው።  
አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚና ውጤታማ ለማድረግ እየተሰራ ነው
Apr 19, 2024 51
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ እና ውጤታማ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ። የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፋይናንስ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ለአምራች ኢንተርፕራይዞች የንግድ ልማት አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ ይገኛል። በዚህ መነሻነት ትግበራውን ለማከናወን ከተቋሙ ውል የወሰዱት ኮንሶልና አይ ከርቭ ኮንሠልት የትግበራ ዕቅዳቸውን ለባለድርሻ አካላት አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።   የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አለባቸው ንጉሴ በዚህ ወቅት እንደገለጹት የንግድ ልማት አገልግሎት ለአምራች ኢንተርፕራይዞች ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ዘርፉ ለአምራች ኢንተርፕራይዞች ካለው ጠቀሜታ አንፃር በልዩ ትኩረት እየተደገፈ መሆኑን በማንሳት የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ስትራቴጂ እንዲኖረው ለማስቻል ተቋማቸው ከአማካሪ ድርጅቶቹ ጋር በመተባበር እየሠራ መሆኑን ገልፀዋል። ፕሮጀክቱ የአምራች ኢንተርፕራይዝ ዘርፉን ለመደገፍ የተቀረጸ መሆኑን ተከትሎ የንግድ ልማት አገልግሎትን በስፋት ለማስተዋወቅና ተደራሽ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን አስረድተዋል። ይህ የንግድ ልማት አገልግሎት የልዩ ልዩ ሠነዶች ዝግጅት፣ ስልጠና፣ የማማከር ስራዎች፣ ጥናትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ጨምሮ 11 ያህል ተግባራት የሚከናወኑበት እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ዕቅዱ ስልጠናዎች ምን አይነት መሆን አለባቸው፤በምን መልኩ መሰጠት አለባቸው፤ የሚለውን የሚያመላክት ስለሆነ ፤ ውጤታማ እንዲሆን ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አብራርተዋል፡፡ ስልጠናው በአለም ባንክ የሚደገፍ ሲሆን የአምራች ኢንተርፕራይዞችን አቅም በመገንባትና አሰራራቸውን በማሻሻል ውጤታማ እንዲሆኑ ለማገዝ ያስችላል ብለዋል ፡፡ የንግድ ልማት አገልግሎት ቡድን መሪ ዶክተር ሃብታሙ ደመራ በበኩላቸው፤ የአምራች ኢንተርፕራይዞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ስልጠና በመስጠት አቅማቸውን እንዲያሳድጉ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ስልጠናው የኢንተርፕራይዞችን የውጭ ገበያ ድርሻ ለማሳደግ ፤ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካትና የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን ድርሻ ለማሳደግ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚህም ለ500 ኢንተርፕራይዞች እና ለ50 ባለሙያዎች ተገቢውን ስልጠናና ቴክኒካል ድጋፍ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡  
በአማራ ክልል የሌማት ትሩፋት መረሃ ግብር የዜጎችን ምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እያገዘ ነው
Apr 19, 2024 56
ደሴ፤ ሚያዚያ 11/2016(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በንቅናቄ የተጀመረው የሌማት ትሩፋት መረሃ ግብር የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እያገዘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ፓኬጅ የአሰልጣኞች ስልጠና የማጠቃለያ መድረክ በኮምቦልቻ ከተማ ተካሂዷል፡፡ የክልሉ እንስሳት ዓሳ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ነጋ ይስማው በወቅቱ እንዳሉት፤ በዘርፉ የተሻሻለ አሰራርና ቴክኖሎጂ በመጠቀም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ ነው፡፡ ለዚህም በንቅናቄ የተጀመረው የሌማት ትሩፋት መረሃ ግብር በክልሉ የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። በገጠርና በከተሞች ህብረተሰቡ በአነስተኛ ስፍራና በቀላሉ በእንስሳት ማድለብ፣ ዶሮ እርባታ፣ ንብ ማነብ፣ በወተት ልማትና ዓሳ እርባታ ላይ በመሰማራት የአቅርቦት እጥረት እንዳይኖር እያገዘ ነው ብለዋል። በዚህም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን አስረድተዋል። መረሃ ግብሩን ለማስፋትም የአዲስ አሰራር ፓኬጅ ስልጠና መሰጠቱን ጠቁመው፤ ዜጎች በአዋጭ ዘርፍ ተሰማርተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ የባለሙያ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡   በደቡብ ወሎ ዞን እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት የእንስሳት እርባታ ባለሙያ ወይዘሮ ሽብሬ መርሻ በበኩላቸው፤ህብረተሰቡ በሌማት ትሩፋት መረሃ ግብር ላይ በመሳተፍ ራሱን ከመቻል ባለፈ ለገበያ እያቀረበ ተጠቃሚ እየሆነ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ በተለይም እንቁላል፣ ወተት፣ አትክልትና መሰል ምርቶችን ህብረተሰቡ በቀላሉ በማምረት እንዲጠቀም እድል መፍጠሩን ተናግረዋል።   'የሌማት ትሩፋት በቀላሉ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የገለጹት ደግሞ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን እንስሳትና ዓሳ ሀብት ጽህፈት ቤት እንስሳት እርባታ ቡድን መሪ አቶ በሪሁን ተፈራ ናቸው፡፡ በዚህም ህብረተሰቡ በአካባቢው የማር፣ የወተት፣ የእንቁላል፣ የስጋና የሌሎችንም ምርቶች በቀላሉ እያገኘ የኑሮ ውድነቱን ለመቋቋም እያገዘ ነው ብለዋል፡፡ ለአራት ቀናት በተሰጠው የፓኬጅ ስልጠና የምስራቅ አማራ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የዘርፉ የአመራር አባላትና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ባለመላዎቹ ታዳጊዎች
Apr 19, 2024 13
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ ችግርን ወደ እድል የቀየሩ ባለመላዎቹ ታዳጊዎች ከመጋቢት 30 እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆየው የኢትዮጵያ "ስታርት አፕ" አውደ-ርዕይ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሳይንስ ሙዚየም ለጎብኚዎች ክፍት ተደርጓል። በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በኢንዱስትሪ፣ በፋይናንስና በሌሎች ዘርፍ የተሰማሩ ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች ''ስታርት አፖች'' በአውደ-ርዕዩ በመሳተፍ ላይ ናቸው። አውደ-ርዕዩ የተዘጋጀው በአገሪቱ የሚገኙ ስታርት አፖች ያላቸውን ምርትና አገልግሎት እንዲሁም ፈጠራዎች ተደራሽ ለማድረግ ነው። የአቤም ዩዝ አካዳሚ የሰባተኛ ክፍል ተማሪ የሆኑት ጎዶሊያስ ሙሉጌታና ሰላዲን መራዊ የግለሰብ መረጃን ወይንም ሲቪ የሚያደራጅ ድረ-ገፅ ሰርተው በስታርት አፕ አውደ-ርዕይ አቅርበዋል።   የታዳጊ ጎዶሊያስ ወንድም ስራ ለማመልከት ሲወጣ ''ሲቪ'' ረስቶ ወደቤት በመመለስ ለተጨማሪ ወጪና እንግልት መዳረጉ የዚህ ድረ-ገፅ መልማት መነሻ የሆነ ምክንያት ነው። ሰዎች ስራን ለመቀጠር የሚያስገቡት የራስ መግለጫ ''ሲቪ'' በእጅ ስልካቸው ኖሮ በማንኛውም ሰዓት ለሚፈልጉት ቀጣሪ ማስገባት የሚያስችል ድረ-ገፅ የሰሩት ታዳጊዎች የአይ ሲ ቲ መምህራቸው ለዚህ ስራቸው እገዛ እንዳደረገላቸው ተናግረዋል። ድረ-ገፁ ስለግለሰቡ የትምህርት ደረጃን ጨምሮ፣ አድራሻ፣ ክህሎቶችና የሰዎችን ምስክርነትን ማካተት የሚቻልበት መሆኑን ተናግረዋል። ድረ-ገፁ የሰዎችን ብቻ ሳይሆን የድርጅቶችን መረጃ እንዲያስቀምጥ ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑንም ታዳጊዎቹ ያስረዳሉ። በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀው አውደርዕይ ላይ መሳተፋቸው ከሌሎች ስታርት አፖች ልምድ እንዲቀስሙና እውቀታቸውን እንዲያዳብሩ እድል የሚፈጥርላቸው መሆኑንም ገልፀዋል። ስራቸውን እንዲያሳዩ እድል ስለተፈጠረላቸውና እዚህ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ እገዛ ላደረጉላቸው አካላትም ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይም ችግር ፈቺ የምርመር ስራዎችን በመስራት አገራቸውን ለመጥቀም እንደሚሰሩ ገልጸዋል።  
ኢትዮጵያ ለስታርት አፕ የሰጠችው ትኩረት የዲጅታል ኢኮኖሚ ግንባታ ርዕይና ተስፋዋን የሚያሳካ ነው- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Apr 19, 2024 59
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ለስታርት አፕ የሰጠችው ትኩረት የዲጅታል ኢኮኖሚ ግንባታ ርዕይና ተስፋዋን የሚያሳካ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተውን የስታርት አፕ ኢትዮጵያ አውደ ርዕይ ጎብኝተዋል።   በጉብኝታቸውም ኢትዮጵያን በብዙ መልኩ የሚጠቅሙ ችግር ፈቺ የፈጠራ ሀሳቦችን መመልከታቸውን ተናግረዋል። ሀገርን ሊያሳድጉ የሚችሉ የፈጠራ ሀሳቦች ያሏቸው ወጣቶችና ታዳጊዎችን የኢትዮጵያ እድገት ተስፋዎች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ መንግስት ይህንን በመገንዘብ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት መስጠቱን አንስተዋል።   10 ዓመቱ የልማት እቅድ የገቢና ወጪ ምርቶችን ለማመጣጠንና የቴክኖሎጂ ፈጠራን ለማሳደግ የተያዘውን ሀገራዊ ግብ ለማሳካት ስታርት አፖች ሚናቸው ትልቅ ነው ብለዋል። መንግስት ስታርት አፖችን ለማጠናከር እየሰራ ስለመሆኑ አንስተው፤ ለአብነትም ምርቶቻቸውን ገዝቶ መጠቀምን የሚያበረታታ እንዲሁም የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያገኙ የሚያደርጉ የፖሊሲ አቅጣጫዎችንና የህግ ማዕቀፎችን ወደ ስራ ማስገባቱን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂና በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ብዙ ተስፋ እንዳላት ገልጸው፥ ኢትዮ ቴሌኮም አካታች የዲጅታል ኢኮኖሚ ስርዓትን በማሳለጥ ትላልቅ ስራዎችን እያከናወነ ነው ብለዋል። በተለይ በቴሌ ብር አገልግሎት አነስተኛ ብድሮችን በማቅረብ እና አርሶና አርብቶ አደሩን ጭምር የሚያሳትፉ ማዕቀፎችን በመተግበር ትልቅ እምርታ እያስመዘገበ እንደሆነ ጠቅሰዋል። በሰው ሰራሽ አስተውሎትና በቴክኖሎጂ ፈጠራ ያሉ ጅምሮች ኢትዮጵያ ያላትን ግዙፍ ራዕይ ማሳካት እንደሚቻል የሚያሳዩ መሆናቸውን አስረድተዋል። የመንግስት አገልግሎትን ለማዘመን ትልቅ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸው፤ በተለይም ቴክኖሎጅን ያወቀና የአገልጋይነት መንፈስ ያለው የሰው ኃይል ለመገንባት በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል ኢትዮጵያ በቀጣናው ብሎም በአፍሪካ የዲጅታል ኢኮኖሚ ማዕከል ለመሆን እየሰራች መሆኑንም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ ሀገራዊ የብልፅግና ጉዞን ለማሳካት በየክልሎች ያሉ ስታርት አፖችን ሁሉም ሊያበረታታ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡            
የግሉ ዘርፍ በዲጂታል ምህዳሩ ላይ ያለውን ተሳትፎ በማጎልበት ቀልጣፋና ዘመናዊ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው- የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
Apr 19, 2024 50
አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 11/2016 (ኢዜአ)፦የግሉ ሴክተር በዲጂታል ምህዳሩ ላይ ያለውን ተሳትፎ በማጎልበት ቀልጣፋና ዘመናዊ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ይሽሩን ዓለማየሁ ገለፁ። ራይድ ትራንስፖርት እና ታዋቂው ዓለም አቀፍ የዲጂታል ክፍያ ተቋም ቪዛ በኢትዮጵያ የትራንስፖርት ክፍያን ለማቀላጠፍ የሚያስችል ጥምረት መፍጠራቸውን አስታወቀዋል። ጥምረቱ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጭ አገር ዜጎች እና ዳያስፖራዎች የቪዛ ካርዳቸውን ብቻ በመጠቀም የትራንስፖርት ክፍያቸውን እንዲያከናውኑ የሚያስችል ነው፡፡ ይህም ጎብኚዎች አስተማማኝና ቀልጣፋ ትራንስፖርት በማግኘት በኢትዮጵያ አስደሳች ቆይታ እንዲኖራቸው የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡ በመድረኩ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ይሽሩን አለማየሁ “ዲጂታል ኢትዮጵያ”ን እውን ለማድረግ ከሚከናወኑ ስራዎች መካከል ዲጂታል ክፍያ አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የዲጂታል ክፍያ ስርዓትም የተቀላጠፈና ዘመናዊ አሰራር ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያግዝ ነው ያብራሩት፡፡ ለዲጂታል ኢትዮጵያ ግንባታ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከዚህ አኳያ መንግስት የዲጂታል ምህዳሩን ምቹ ማድረግ ጨምሮ የሚጠበቅበትን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡ የሃይብሪድ ዲዛይንስ እና ራይድ መስራች ሳምራዊት ፍቅሩ፤ ጥምረቱ "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" እውን ለማድረግ እየተከናወነ ካለው ስራ ጋር የሚጣጣም መሆኑን ጠቁመዋል፡፡   ጥምረቱ ኢትዮጵያን የሚጎበኙ ቱሪስቶች ጥሬ ገንዘብ ሳይጠቀሙ በቪዛ ካርዳቸው ብቻ አገልግሎት እንዲያገኙ እንደሚያደርግም ነው የተናገሩት፡፡ በኢትዮጵያ የቪዛ ዳይሬክተር ያሬድ እንዳለ በበኩላቸው፤ ቪዛ የተቀላጠፈ እና አስተማማኝ የዲጂታል ክፍያን ለሁሉም እና በሁሉም ቦታ ለማዳረስ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።   በመሆኑም ከራይድ ጋር የተጀመረው ጥምረት የኢትዮጵያን የጉዞ እና ቱሪዝም ዘርፍ ለማዘመን ሚናው የጎላ ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይም የቪዛ ክፍያ ስርዓትን በሌሎች አገልግሎቶችም ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራም ነው የገለጹት፡፡  
በአዲስ አበባ ያሉ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጣቸውን የማዘመንና ተደራሽነታቸውን ማስፋት ላይ ትኩረት ተሰጥቷል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Apr 19, 2024 40
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ያሉ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጣቸውን የማዘመንና ተደራሽነታቸውን የማስፋት ስራ እንዲያጎለብቱ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስሩ ለሚገኙና ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ላሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚውሉ 150 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን አስረክቧል፡፡   የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተሽከርካሪዎቹን ቁልፍ ለተቋማቱ ባስረከቡበት ወቅት እንደገለጹት ተቋማት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል። በተለይም ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን መፍታት የሚያስችሉ ግብዓቶችን ማቅረብ ላይ ትኩረት ተሰጥቶታል ብለዋል። ዛሬ በከተማ አስተዳደሩ ስር ለሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተከፋፈሉትና በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት አሰጣጡን በማቀላጠፍ ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ። በተለይም ተቋማቱ ያሉባቸውን ክፍተቶች በመሙላት አቅማቸውን ለማሳደግና ለማብቃት ያለመ ስለመሆኑም ከንቲባዋ አብራርተዋል። ተሽከርካሪዎቹ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ባሻገር በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ጉልሀ ሚና እንደሚኖራቸውም አንስተዋል። በተለይም ከተማ አስተዳደሩ አዲስ አበባን ጽዱ፣ አረንጓዴና ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግ እያከናወነ ላለው የልማት ስራ በእጅጉ የሚያግዙ ናቸውም ብለዋል። በመሆኑም በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ያሉ አገልጋዮች ስራቸውን በአግባቡና በኃላፊነት በመወጣት የተጣለባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል። ለህዝብ አገልግሎት እንዲውሉ ታልመው በግዢ የተላለፉት እነዚህን ተሽከርካሪዎችንም በአግባቡ ሊጠቀሙ እንደሚገባም ከንቲባዋ አጽንኦት ሰጥተዋል። መኪኖቹ ከበላይነህ ክንዴ ግሩፕ በአገር ውስጥ የተገጣጠሙና በግዥ የቀረቡ መሆኑን ተገልጿል።  
ስፖርት
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ22ኛ ሳምንት መርኃ ግብር ዛሬ ይጀመራል
Apr 18, 2024 232
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 10/2016(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ22ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ። በ22ኛው ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ ከኢትዮጵያ መድን ከቀኑ 10 ሰዓት በድሬዳዋ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። በአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት የሚመራው ወልቂጤ ከተማ በሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው። አንድ ጊዜ ሲሸነፍ ሶስት ጊዜ አቻ ወጥቷል። ወልቂጤ በ16 ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ተጋጣሚው ኢትዮጵያ መድን በበኩሉ ካለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች አንድ ጊዜ ሲያሸንፍ በተመሳሳይ አንድ ጊዜ ተሸንፏል። በቀሪዎቹ ሶስት ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርቷል። በገብረመድህን ኃይሌ የሚሰለጥነው ኢትዮጵያ መድን በ19 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ምሽት 1 ሰዓት በሚደረገው የ22ኛ ሳምንት መርኃ ግብር ሁለተኛ ጨዋታ ባህር ዳር ከተማና ሀዲያ ሆሳዕና ይጫወታሉ። ባህር ዳር ከተማ ባለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች አልተሸነፈም። በሶስቱ ሲያሸንፍ በሁለቱ አቻ ተለያይቷል። በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው የሚመራው ባህር ዳር ከተማ በ33 ነጥብ 5ኛ ደረጃን ይዟል ። ሀዲያ ሆሳዕና በሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች በሁለቱ ድል ሲቀናው በአንዱ ተሸንፎ በሁለቱ ነጥብ ተጋርቷል። በአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ የሚመራው ሀዲያ ሆሳዕና በ30 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የ22ኛ ሳምንት መርኃ ግብር ነገ ቀጥሎ ሲውል ሀምበሪቾ ዱራሜ ከሃዋሳ ከተማ ከቀኑ 10 ሰዓት፤ ፋሲል ከነማ ከአዳማ ከተማ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። የ22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች እስከ ሚያዚያ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ይቆያሉ። ፕሪሚየር ሊጉን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ43 ነጥብ እየመራ ይገኛል። የሃዋሳ ከተማው አጥቂ አሊ ሱሌይማን 12 ጎሎች በማስቆጠር የፕሪሚየር ሊጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት እየመራ ነው። ዩጋንዳዊው የድሬዳዋ ከተማ ተጫዋች ቻርልስ ሙሲጌ፣ የቅዱስ ጊዮርጊሱ አማኑኤል ኦርቦ፣ የባህር ዳር ከተማው ቸርነት ጉግሳ እና የአዳማ ከተማው ዮሴፍ ታረቀኝ በተመሳሳይ በ9ኝ ግቦች ይከተላሉ። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ23ኛ እስከ 27ኛ ሳምንት ያሉ ጨዋታዎች በሃዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም እንደሚካሄዱ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።  
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከ23ኛ ሳምንት ጀምሮ በሃዋሳ ይካሄዳሉ
Apr 16, 2024 550
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 8/2016(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከ23ኛ ሳምንት ጀምሮ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንደሚካሄድ የፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታወቀ። የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ደግሞ ሚያዚያ 19 እና 20 ቀን 2016 ዓ.ም ይደረጋሉ። የፕሪሚየር ሊጉ መርሐ ግብር ከ16ኛ ሳምንት አንስቶ በድሬዳዋ ስታዲየም እየተከናወነ ሲሆን፥ የ22ኛ ሳምንት ጨዋታዎችም ከሚያዚያ 10 እስከ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በድሬዳዋ ይካሄዳሉ። የሊጉ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ዋንጫ ምክንያት ከተቋረጠ በኋላ ወደ ውድድር ሲመለስ የ23ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ከሚያዚያ 24 እስከ 27 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄዱ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አመልክቷል። እስከ 27ኛ ሳምንት ያሉ ጨዋታዎች በሃዋሳ እንደሚደረጉም ተገልጿል። ከ28ኛ እስከ 30ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚከናወን ማህበሩ ከዚህ ቀደም መግለጹ ይታወቃል። የሊጉ ውድድር ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ተጠቁሟል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር መርሐ ግብር በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም መካሄዱ የሚታወስ ነው።    
26ኛው መላው የኦሮሚያ የስፖርት ውድድር በጅማ ከተማ መካሄድ ጀመረ
Apr 14, 2024 951
ጅማ፣ ሚያዚያ 6/2016(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ የተለያዩ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የሚሳተፉበት 26ኛው መላው የኦሮሚያ የስፖርት ውድድር ዛሬ በጅማ ከተማ መካሄድ ጀመረ። ውድድሩ በ21 ዘመናዊ የስፖርት አይነቶች የሚካሄድ ሲሆን በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ዞኖች እና ከተማ አስተዳደሮች እንደሚሳተፉበት ታውቋል። በውድድሩ መክፈቻ መርሃግብር ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ማቴዎስ ሰቦቃ እንዳሉት ስፖርት ወዳጅነትና አንድነትን ያጎለብታል።   ስፖርት ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቅሰው ዛሬ በጅማ ከተማ የተጀመረው ውድድር ለ15 ቀናት እንደሚቆይ ገልጸዋል። ስፖርት አብሮነትን ከማጠናከር ባለፈ ለአካልና ለአዕምሮ ብቃት ወሳኝ ነው ያሉት ሃላፊው፣ በክልሉ ብቁ ታዳጊ ስፖርተኞችን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ኦሮሚያ የአትሌቶች መፍለቂያ መሆኗን አስታውሰው፣ ከክልሉ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያስጠሩ ስፖርተኞችን የማፍራት ስራው ይጠናከራል ብለዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ በበኩላቸው ታዳጊ ሕጻናት እና ወጣቶችን በዚህ መሰል የስፖርት መድረክ ማሳተፍ የሚበረታታ ነው ብለዋል።   ሀገራችን በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ብቁና ተወዳዳሪ ወጣት ስፖርተኞችን ማፍራት እንድትችል በየአካባቢው ወጣቶችን ያሳተፈ ሥራ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል ። ይህም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የስፖርት ተሳትፎ ለማሳደግ ያግዛል ያሉት አቶ ኢሳያስ፣ በየደረጃው ለታዳጊ ወጣቶች ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል። የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጣሃ ቀመር በበኩላቸው የጅማ ከተማና የጅማ ዞን ህዝብ ለውድድሩ የመጡ እንግዶችን በእንግዳ አክባሪነት ተቀብሎ እንዲያስተናግድ አስገንዝበዋል።   ስፖርት በባህሪው አዝናኝና አንድነትን የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸው፣ እንግዶች በጅማ ቆይታቸው የከተማዋን የተለያዩ አካባቢዎች እንዲጎበኙ ጠይቀዋል። ዛሬ በጅማ ከተማ በተጀመረው የመላው ኦሮሚያ ስፖርት ውድድር 21 ዞኖች እና 23 የከተማ አስተዳደሮች እንደሚሳተፉ ለማወቅ ተችሏል።    
አካባቢ ጥበቃ
በመዲናዋ እየተተገበረ የሚገኘው የወንዞች ዳርቻ ልማት የመዲናዋን ወንዞች ትንሳኤ አብስሯል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Apr 19, 2024 153
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2016(ኢዜአ)፦ ካለፉት አምስት አመታት ጀምሮ በመዲናዋ እየተተገበረ የሚገኘው የወንዞች ዳርቻ ልማት የመዲናዋን ወንዞች ትንሳኤ ያበሰረ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ "ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ" በሚል መሪ ሃሳብ ለቀጣዮቹ ስድስት ወራት ንቅናቄ አስጀምረዋል።   ንቅናቄው የአካባቢ ብክለትን በመከላከል ጽዱ አዲስ አበባን እውን ለማድረግ አላማ የያዘ ነው፡፡ በመርኃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር፣ የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ስራአስኪያጅ ድዳ ድሪባ፣ የካቢኔ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። በዚሁ ወቅት የመዲናዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዳሉት፤ አዲስ አበባ እንድትመሰረት ምክንያት የሆናት የተፈጥሮ ሀብቷና መልከ ብዙ የአየር ንብረቷ ነው። ይሁን እንጂ እነዚህን የተፈጥሮ ሀብቶች በአግባቡ መጠበቅ ባለመቻሉ መዲናዋ ለከፍተኛ ብክለት ተዳርጋለች ሲሉ የችግሩን አሳሳቢነት ጠቁመዋል፡፡ እነዚህ ጉልህ ችግሮች በከተማዋና በዙሪያዋ ባሉ አካባቢዎች ጤናን የሚያውኩ ጉዳቶችን እያስከተሉ ነው ብለዋል። ይህን ተከትሎ ባለፉት አምስት ዓመታት ችግሮቹን ለማቃለልና የከተማዋን ስነ-ምሕዳር ለማሻሻል የሚረዱ ሜጋ ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት ተደርጎ መሰራቱን አብራርተዋል። በዋናነትም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት እየተተገበረ የሚገኘው የወንዝ ዳርቻ ልማት የመዲናዋን ወንዞች ትንሳኤ ያበሰረ መሆኑን ጠቁመዋል። በተጨማሪም የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ የነበረውን የመዲናዋን የደን ሽፋን መታደግ እንዳስቻለ አስታውቀዋል። እነዚህ ስራዎች ዘላቂ ልማትን ከማረጋገጥ አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን አመላክተዋል። በከተማዋ ያለው የፍሳሽ ማስወገጃ ስርአት በአብዛኛው ከወንዞች ጋር የተገናኘ በመሆኑ በቅርቡ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ችግሩን ለመፍታት እንደሚያስችል ተናግረዋል። ረጅም ጊዜ ያገለገሉ ተሽከሪዎች በአየር ንብረት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደሩ መሆኑን በመጠቆም በታዳሽ ሀይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ጥቅም ላይ ለማዋል የወጣው ፖሊሲ የአየር ንብረት ብክለትን ለመከላከል ትልቅ ግብአት መሆኑንም አንስተዋል። የድምጽ ብክለት የከተማዋ ተጨማሪ ችግር እየሆነ መምጣቱን አንስተው ችግሩ ከተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት የሚመነጭ መሆኑን አስረድተዋል። የብክለት ችግሮቹን ከመሰረቱ ለመፍታት የተጀመሩ ጥረቶችን ለማጠናከር ግንዛቤን ማሳደግ እና የተቀመጡ ህጎችና መመሪያዎችን መተግበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ድዳ ድሪባ በበኩላቸው ንቅናቄው የአካባቢ ብክለትን በመከላከል ጽዱና የበለጸገች አገር ለትውልድ የማስተላለፍ አላማ መያዙን ገልጸዋል። የአካባቢ ብክለት በአካባቢ እና በሰው ልጅ ላይ ወቅታዊና ዘላቂ ችግር እንደሚያስከትል ገልጸው አሁን የተጀመረው ንቅናቄ ቋሚ አሰራር ሆኖ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።  
አካባቢን ለኑሮና ለስራ ምቹ ለማድረግ ከደረቅ ቆሻሻና ፕላስቲክ ብክለት የመከላከል ንቅናቄ ይካሄዳል
Apr 19, 2024 82
ሐረር/ድሬዳዋ ፤ሚያዝያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ አካባቢን ለኑሮና ለስራ ምቹ ለማድረግ ከደረቅ ቆሻሻና ፕላስቲክ ብክለት የመከላከል ንቅናቄ እንደሚያካሄድ የሐረሪ ክልል አካባቢ ጥበቃ እና የድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣናት አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከሰሞኑ ከተሞቻችን እና አካባቢያችንን ጽዱ ለማድረግ እንተባበር ባሉት መልዕክታቸው እንደገለጹት፤ የፕላስቲክ እና የቆሻሻ ብክለት ሥነ ምህዳራችንን እና ጤናችንን አደጋ ላይ ይጥላል። ''በሃላፊነት ስሜት ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ እና ዘላቂ አማራጮችን በመምረጥ ተፈጥሮን ለትውልድ ማቆየት እንችላለን'' ማለታቸው ይታወሳል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የሐረሪ ክልላዊ መንግስት እና ድሬዳዋ አስተዳደር ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሃላፊዎች ችግሩን ለመግታት በትኩረት እንደሚንቀሳቀሱ አረጋግጠዋል። በሐረሪ ክልል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ሃላፊ አቶ ሰሚር በክሪ እንደተናገሩት፤ ባለስልጣኑ በአካባቢ ብክለት፣ ቁጥጥርና ህግን ከማስፈፀም አኳያ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። አካባቢው ስነ ምህዳርና ተፈጥሯዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን የማጎልበት ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን በማከል። በተለይ በክልሉ ከተማና ገጠር አካባቢዎች በከባቢ አየር፣ ውሃ፣ በአፈርና በድምፅ ብክለት ደረጃዎች ላይ የተቀናጀ የክትትልና ቁጥጥር ስራ እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። በሐረር ከተማም ከተቋማትና ከሌሎች የሚወጡ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ጋር በተያያዘ ውስንነት እንደሚታይ የተናገሩት አቶ ሰሚር፤ ችግሩን ለመፍታት በተቀናጀ መልኩ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን አመልክተዋል። በተለይም ደረቅ ቆሻሻን ከምንጩ ጀምሮ የማስወገድ ሂደቱ ስርዓቱን ጠብቆ እንዲከናወን እየተከታተለና በትክክል በማይፈጽሙት ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑንም ገልጸዋል። እንደ አቶ ሰሚር ገለጻ፤ በተለይ ከአካባቢ ብክለት ጋር በተያያዘ በደረቅ ቆሻሻና ፍሳሽ አወጋገድ ጋር ተግባራዊ ያላደረጉ ሁለት ተቋማትን በህግ አግባብነት የመጠየቅ ስራዎች መከናወናቸውን አስረድተዋል። በክልሉ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ እስከ መስከረም ድረስ ተግባራዊ የሚሆን የአካባቢ ጥበቃ ንቅናቄ እንደሚካሄድም ገልጸዋል። “ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ” በሚል መሪ ሃሳብ የሚከናወነው ይኸው ንቅናቄ የአካባቢ ጥበቃ ውጤታማነትን ለማሳደግ፣ የወጡ ሕጎችና ደንቦች ተግባራዊ እንዲሆኑ፣ በዘርፉ የባለድርሻ አካላትንና የማኅበረሰቡን ሚና ለማጠናከር ያለመ መሆኑን አቶ ሰሚር ተናግረዋል።   በተመሳሳይ የድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱ መሐመድ በበኩላቸው፤ አካባቢን ውብና ፅዱ የስራና የመኖሪያ ስፍራ ለማድረግ የተጀመረውን አገር አቀፍ ዘመቻ ከግብ ለማድረስ በአስተዳደሩ የተቀናጀ ርብርብ እንደሚደረግ ገልጸዋል። አቶ አብዱ እንደሚናገሩት፤ አሁን የምንኖርባት አካባቢ ያለፈው ትውልድ ያወረሰን ብቻ ሳይሆን ከመጪው ትውልድ የተበደርን መሆኑን በመገንዘብ አካባቢን መንከባከብ ያስፈልጋል። ደረቅ ቆሻሻ በተለይም የፕላስቲክ ውጤቶች በመቅበርም ሆነ በማቃጠል አካባቢን ጽዱ ማድረግ እንደማይቻል የገለጹት አቶ አብዱ፤ ፕላስቲኮቹን በጥንቃቄ በመሰብሰብና በመፍጨት ሌሎች ቁሶችን በማምረት እንደሆነ ተናግረዋል። በዚህም በድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ ብክለትን ለመከላከልና የተፈጥሮ ሀብትን ለመጠበቅ የሚያግዝ የስድስት ወራት ዘመቻ መካሄድ መጀመሩን ገልጸዋል። እስከ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በሚካሄደው በዚሁ ዘመቻ የሚያዝያ በሙሉ የፕላስቲክ ብክለትን በመከላከልና የፕላስቲክ አጠቃቀምን በማዘመን የስነ ምህዳርን ለመጠበቅ የሚያግዙ ህዝባዊ ንቅናቄዎች እንደሚካሄዱ አመልክተዋል። ዘመቻው በተለይ በትምህርት ቤቶች የአካባቢ ጥበቃ ክበቦችንና ሚዲያን በመጠቀም እና በየደረጃው የሚገኘውን ህብረተሰብ ግንዛቤ በማስፋት ድሬዳዋ ለስራና ለኑሮ የምትመች ፅዱና ውብ ለማድረግ የተጀመሩ ጥረቶችን ለማሳካት እንደሚሰራ ነው የተናገሩት ። በተጨማሪም ከከፍተኛ አመራሩ እስከ ህፃናት ተማሪዎች ድረስ የሚሳተፉበት የፕላስቲክ ኮዳዎችን የመሰብሰብ ና ፕላስቲኮችን ወደ ሌላ ምርቶች ለሚለወጡ ድርጅቶች የማስረከብ ስራ ይካሄዳል ብለዋል።  
በአማራ ክልል የፕላስቲክ  አወጋገድን በማዘመን ከብክለት ነፃ  የሆኑ ከተሞችን ለመገንባት ጥረት እየተደረገ ነው
Apr 19, 2024 79
ባህር ዳር ፤ ሚያዚያ 11 / 2016 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል የፕላስቲክና የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትን በማዘመን ከብክለት ነፃ የሆኑ ከተሞችን ለመገንባት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ የአካባቢና ደን ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የፕላስቲክ እና የቆሻሻ ብክለት ሥነ ምኅዳራችንን እና ጤናችንን አደጋ ላይ እንደሚጥል መግለጻቸው ይታወሳል። እርሳቸው "በኃላፊነት ስሜት ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ እና ዘላቂ አማራጮችን በመምረጥ ተፈጥሮን ለትውልድ ማቆየት እንችላለን" በማለት ከተሞችን እና አካባቢያን ጽዱ ለማድረግ የመተባበር አስፈላጊነትን አጽንኦት ሰጥተውታል። የፕላስቲክ ቆሻሻ ለዓመታት ከምድር ላይ የማይጠፋ ለአካባቢ ብክለት ዋነኛ መንስኤ እየሆነ መምጣቱን መረጃዎች ያሳያሉ። በተለይ ከተሞች ለዚህ ችግር ሰለባ ናቸው። በገጠር አካባቢ ለግብርና ስራ ችግር ፈጣሪ እየሆነ መምጣቱና ፕላስቲክ የበሉ ላሞች እንደሚሞቱ ይገለጻል። ይህን እንዴት እየተከላከሉ እንደሆኑ ኢዜአ የጠየቃቸው በአማራ ክልል የአካባቢና ደን ጥበቃ ባለስልጣን የአካባቢና የአየር ንብረት ለውጥ ዳይሬክተር አቶ አወቀ ይቴ በሰጡት ምላሽ "ከፕላስቲክና ከደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ጋር ተያይዞ ሊያጋጥም የሚችለውን ብክለት ለማስቀረት በትኩረት እየተሰራ ነው" ብለዋል። ለዚህም የፕላስቲክና የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትን በማዘመን ከተቋማትና ከሌሎች አካላት ጋር አስተሳስሮ ለመምራት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። የተለያዩ ማህበራትን በባህር ዳር፣ ደሴ፣ ጎንደርና ሌሎች ትላልቅ ከተሞች በማቋቋም ፕላስቲክን ለይተው በማሰባሰብ የማስወገድ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። በዚህም በወር ከ30 እስከ 40 ቶን የወዳደቁ ፕላስቲኮች እንደሚሰበሰቡ አመልከተው፤ ከእነዚህም የፕላስቲክ ወንበሮች፣ ለገመድና ሌሎች ምርቶችን በማምረት ጥቅም ላይ እንዲውል እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል። የቀረውንም በመጨፍለቅና በመፍጨት አዲስ አበባን ጨምሮ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሚጓጓዝበት ሁኔታ እንዳለም ጠቁመዋል። የፕላስቲክ ምርቶች ቀደም ሲል በዘፈቀደ በየቦታው የሚጣልበት ሁኔታ እንደነበረ አስታውሰው፤ "አሁን ላይ የሚጣሉ የፕላስቲክ ቆሻሻዎችን በመሰብሰብና በማስረከብ በርካታ ወጣቶች የገቢ ምንጭ እያደረጉት ይገኛሉ" ብለዋል። ፕላስቲኮች በወንዞንች፣ በውሃ ማፋሰሻ ቦዮችና አካባቢ ስነ-ምህዳር ላይ ጉዳትና ብክለት እንዳያስከትሉ በአሰባሰብና አወጋገዱ ላይ ያተኮረ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
የአካባቢ ብክለትን መከላከል የሁላችንም ኃላፊነት ሊሆን ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሁመድ
Apr 19, 2024 95
ጅግጅጋ፤ ሚያዚያ 11/2016(ኢዜአ)፡- የአካባቢ ብክለትን በመከላከል ፅዱና ለኑሮ የሚመች አካባቢ መፍጠር የሁላችንም ኃላፊነት ሊሆን ይገባል ሲሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሁመድ ገለጹ። ርዕስ መስተዳድሩ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል በሚቀጥሉት ስድስት ወራት የሚተገበር የህዝብ ንቅናቄ ዛሬ በክልል ደረጃ አስጀምረዋል። በርዕሰ መስተዳድሩ ጽህፈት ቤት በተጀመረው የንቅናቄ መድረክ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ እንደተናገሩት በክልሉ የአካባቢ ብክለት ችግር ለመፍታት አንዱ የፕላስቲክ አጠቃቀምና አወጋገድን ማዘመን ያስፈልጋል። በክልሉ እየተስፋፉ ያሉ ከተሞች ላይ በመመስረት አካባቢ ከብክለት ነፃ እንዲሆን ሴክተር መስሪያ ቤቶች በዕቅዳቸው ውስጥ በማካተት እንዲሰሩ ትኩረት እንደሚደረግ ገልጸዋል።   በአርብቶ አደር አካባቢ የቤት እንስሳት በፕላስቲክ አወጋገድ ችግር ጉዳት ይደርስባቸዋል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የፕላስቲክ ምርቶችን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋልና በዚህም የስራ እድል ለመፍጠር ሊሰራ እንደሚገባ አሳሰበዋል። የንቅናቄ መድረኩ ህብረተሰቡ በጉዳዮ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ ኖሮት የድርሻውን እንዲወጣ ለማነሳሳት መሆኑን አመልክተዋል። የክልሉ የአካባቢ ጥበቃና ገጠር መሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ኢንጀነር ሙህየዲን አብዲ ፤ የአካባቢ ብክለት በአካባቢ ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል መሆኑን ተናግረዋል። ችግሩን ለመፍታት የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማስፋት ትኩረት ተስጥቶ እንደሚሰራ ገልጸዋል። በንቅናቄው መድረክ የተገኙት የፌደራል የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሴ ለማ በበኩላቸው፤ በአገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው ንቅናቄ የአካባቢ ብክለት በሰው እና በእንስሳት ላይ ሊያደረስ የሚችለውን ጉዳት ለማስቀረት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል። ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የፕላስቲክ አጠቃቀም ገደብ ላይ ህግ በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል ማቅረቡንም ጠቅሰዋል። "ብክለት ይብቃ! ውበት ይንቃ" በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረው ንቅናቄ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት የሚተገበር ስራ እንደሚከናወን ተመልከቷል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል- አንቶኒዮ ጉተሬዝ
Apr 15, 2024 889
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- አለም ተጨማሪ ጦርነት እንድታስተናግድ እድል ባለመፍጠር በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አሳሰቡ። ኢራን እስራኤል ከሳምንታት በፊት ሶርያ በሚገኘው ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ጥቃት አድርሳብኛለች በሚል ባሳላፍነው ቅዳሜ ሌሊት መጠነ ሰፊ ጥቃት መሰንዘሯ በተለያዩ የዓለም መገናኛ ብዙሃን መዘገቡ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ በቀጣናውና በአለም ሀገራት የተፈጠረውን ከፍተኛ ውጥረት ለማርገብ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የጸጥታ ምክር ቤቱን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል። በስብሰባውም አለም ተጨማሪ ጦርነት የምታስተናግድበት ምንም አይነት አቅም ስለሌለ ሀገራት በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። ችግሩ በቸልታ የሚታይ ከሆነ አስከፊ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል መናገራቸውን ያስነበበው ፍራንስ 24 የጸጥታው ምክር ቤት አባላት ሁኔታውን በአስቸኳይና ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ሊያስቆሙት እንደሚገባ ማሳሰባቸውንም ዘግቧል።
በሞዛምቢክ በደረሰ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ
Apr 8, 2024 1860
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2016(ኢዜአ)፦በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል የባህር ዳርቻ በተከሰተ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ። በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው ናምፑላ ግዛት 130 የሚሆኑ ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ መስጠሟን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ነዋሪዎቹ በግዛቷ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ በመሸሽ ወደ ሌላ አካበቢ ለመሄድ በጀልባ በተሳፈሩበት ወቅት አደጋው እንደተከሰተ የገለጹት ባለስልጣናቱ ጀልባዋ መሸከም ከምትችለው የሰው መጠን በላይ በመጫኗ አደጋው እንደደረሰ አመልክተዋል። በዚህም ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይታቸው እንዳለፈ ማረጋገጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። በአሁኑ ወቅት አምስት ሰዎችን ከአደጋው በሕይወት ማትረፍ እንደተቻለ ያመለከተው ዘገባው ተጨማሪ ሰዎችን ለማዳን ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስነብቧል። የናምፑላ ግዛት ባለፈው አመት በሞዛምቢክ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ ክፉኛ ከተጎዱ አካባቢዎች መካከል አንዷ መሆኗም በዘገባው ተመላክቷል።
የአየር ንብረት ለውጥና መዘዙ
Apr 5, 2024 1150
በዓለማችን ላይ እየተስተዋለ ያለው የአየር ንብረት ለውጥ የተወሳሰበ ችግር እያስከተለ ከመሆኑ በተጨማሪ በስነምህዳር ላይ እያደረሰ ያለው አደጋ ሊቀለበስ ወደ ማይችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑን ሞደርን ዲፕሎማሲ ድረገጽ አስነበበ። ድረ ገጹ በዓለማችን በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የአየር ንብረት ለውጥ በሚያስከትለው ድርቅ፣ ጎርፍ እና ተዛማጅ በሆኑ ክስተቶች ምክንያት ቀያቸውን ጥለው ለመሰደድ እንደሚገደዱ አስነብቧል። የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በይነመንግስታት ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው አሁን ላይ ያለው የዓለማችን የሙቀት መጠን ወደ 1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴሊሺየስ እየተጠጋ በመምጣቱ በስነምህዳር፣ በከባቢ አየር እና በአካባቢ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እየተስተዋለ መሆኑን ገልጿል። የአየር ንብረት ለውጥ ለዘላቂ ልማት እንቅፋት በመሆን ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ክስተቶች የሚፈጥራቸውን ችግሮች በማባባስ ለሰዎች መፈናቀልና የህይወት መጎሳቆል እያደረሰ ይገኛል። እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 በማዕከላዊ አሜሪካ እና ደቡባዊ ሜክሲኮ የተከሰተው ሃሪኬን ኤታ የተባለው የአየር ንብረት ለውጥ ክስተት ያስከተለው የሰብል ውድመትና የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ የደረሰው አደጋ ከባለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ውስጥ እጅግ የከፋ አደጋ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። በዚህም በጎርፍ፣ በመሬት መንሸራተትና በሰብል ውድመት ምክንያት ከ1 መቶ 20 ሺህ በላይ ሰዎችን ከሞቀ መኖሪያቸው ተፈናቅለው እርዳታ ጠባቂ እንዳደረጋቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽንን መረጃ ዋቢ አድርጎ አትቷል። የአየር ንብረት ለውጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን የጠቆመው ድረ ገጹ በቀጣይ ተመሳሳይ ችግሮች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉም አመልክቷል። በአውሮፓውያኑ 2022 ወደ 32 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተፈናቀሉ ሲሆን፤ ይህ አሃዝ በ2008 ከተከሰተው በ41 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ዘገባው አመልክቷል። ይህም የዓለማችን የሙቀት መጠን እየጨመረ መምጣቱን እንጂ ምንም ዓይነት የመቀነስ አዝማሚያ ያላሳየ መሆኑን ያመለከተው ዘገባው በቺሊ፣ ካናዳ፣ ዛምቢያ፣ ሞዛምቢክ፣ ሜክሲኮ፣ ኢክዋዶር፣ ሊቢያ እና በሌሎችም አገራት ሃሪኬን በተሰኘው የአየር ለውጥ፣ በሰደድ እሳት፣ በጎርፍ እና በድርቅ ምክንያት ለባለፉት በርካታ ወራት መፈናቀልን እንዳስከተለ ተገልጻል። የአለም ባንክን የትንበያ መረጃ ዋቢ ያደረገው ድረ ገጹ በአውሮፓውያኑ 2050 ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ 216 ሚሊዮን ሰዎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ተመላክቷል። ድረገጹ ይሄ ክስተት የሚያስከትላቸው ችግሮች እንዳይቀጥሉ መቆጣጠር ካስፈለገ ዘላቂ ልማት ላይ ያተኮሩ ግንዛቤን የሚያሳድጉ ትምህርቶች፣ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ እውነተኛ ውይይቶች እና ተፈጥሮን መሰረት ያደረጉ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ በማሳሰብ መሪዎች የሚጠበቅባቸውን ሊተገብሩ ይገባል ሲል ምክሩን አስቀምጧል።  
በአባቱ የሎተሪ ስጦታ 4 ሚሊዮን ዶላር ያሸነፈው እድለኛ 
Apr 4, 2024 1198
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2016(ኢዜአ)፦ በአሜሪካ ኤሊኖይ ግዛት ነዋሪ የሆነው ግለሰብ አባቱ ያበረከቱለት የሎተሪ ትኬት የ4 ሚሊዮን ዶላር እድለኛ አድርጎታል። ስቴቨን ሪቻርድስ ይባላል በኤሊኖይ የባሪንግተን ከተማ ነዋሪ ሲሆን ከቀናት በፊት ከአባቱ ጋር ቁርስ ለመመገብ ባቀኑበት ምግብ ቤት ከአባቱ ስጦታ ይበረከትለታል። ስጦታውም የ10 ዶላር የሎተሪ ትኬት ነበር። አዛውንቱ ያበረከቱለት የሎተሪ ትኬት ወዲያውኑ ተፍቆ ውጤቱን የሚያሳይ ሲሆን ስቴቨንም ትኬቱን በፋቀበት ቅጽበት ከፍተኛ ድንጋጤ እንደተሰማው ለማሳቹሴት የሎተሪ አስተዳደር ተናግሯል። የሎተሪ ትኬቱ የ4 ሚሊዮን ዶላር እድለኛ እንዳደረገኝ ሳውቅ በድንጋጤ ማመን አልቻልኩም በዚህም ውጤቱን ከመናገሬ በፊት በስልኬ ስካን አደረኩት ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል። በመቀጠለም የአባቱ ስጦታ እድለኛ እንዳደረገው ለባለቤቱ እንዲሁም ለአባቱ መናገሩን ዩፒአይ ዘግቧል። ስቴቨን በሎተሪ ከደረሰው 4 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ በተወሰነው ገንዘብ ከባለቤቱ ጋር የተለያዩ አካባቢዎችን ለመጎብኘት ማቀዱን ዘገባው አመልክቷል።
ሐተታዎች
ብሩህ ነገን የሰነቁ እንስቶች
Apr 19, 2024 118
የሰው ልጆች ከፍጥረት እስከ ዕለተ ሞት ባሉት የሕይወት ዑደቶች ውስጥ በሚገጥሟቸው መልከ ብዙ ፈተናዎች ሳቢያ ራሳቸውን ለቀቢጸ ተስፋ ይዳርጋሉ፤ ተገደውም ወደ ማይፈልጉት ሕይወት ይገባሉ። በተለይም ሴቶች በሚገጥሟቸው አይነተ ብዙ ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ጫናዎች ሳቢያ በበርካታ የህይወት ውጣ ውረድ ወስጥ ያልፋሉ፤ በሂደቱም ለአካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት የተዳረጉ በርካቶች ናቸው፡፡ ለአብነትም በአዲስ አበባ ተወልዳ ያደገችው ቃልኪዳን በላይነህ (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) በወጣትነቷ ትዳር መስርታ፣ልጆችን ወልዳ ለመሳም በቅታለች፡፡ ዳሩ ግን ባለቤቷ በድንገተኛ አደጋ በመሞቱ ምክንያት ህጻን ልጆቿን ይዛ ለአስከፊ የኢኮኖሚ ችግር መዳረጓን ትናገራለች። በዚህም ራሷንና ልጆቿን ህይወት ለማቆየት ወደ ማትፈልገው የወሲብ ንግድ ሕይወት ውስጥ ለመግባት መገደዷን ነው የገለጸችው፡፡ በህፃንነት ዕድሜ ለአካል ጉዳተኝነት የተዳረገችው ሳምራዊት (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) በበኩሏ በአካል ጉዳተኝነቷ ምክንያት ተንቀሳቀሳ መስራት ባለመቻሏ ከተወለደችበት ገጠራማ ስፍራ ወደ አዲስ አበባ መምጣቷን ትናገራለች፡፡ በአዲስ አበባም ህይወቷን በልመና ስትመራ ቆይታለች፡፡ ሌላኛዋ ባለታሪካችን ሔዋን (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) ወደ ማትፈልገው ህይወት ውስጥ ስትገባ የሚያጋጥማት ማህበራዊ ፣ አካላዊ ጥቃት እና ስነልቦናዊ ጫና ቀላል አይደለም ትላለች። እሷም ኑሮን ለማሸነፍ የገባችበት የህይወት መስመር ወደ አላስፈላጊ ሱስ ውስጥ እንድትገባና ለስነ ልቦናዊ ቀውስ እንድትጋለጥ እንዳደረጋት ገልጻለች። መንግስት በመሰል ችግር ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ለመደገፍ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከዚህም ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ለመታደግ የሚያስችልና “ለነገዋ” የተሰኘ የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል አንዱ ነው፡፡ ማዕከሉ ለተለያዩ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ችግሮች የተጋለጡ ሴቶችን በስነ ልቦና የምክር አገልግሎት እና በተለያዩ ሙያዊ ስልጠናዎች በመስጠት ብሩህ ነገን ለማቀዳጀት ስራ ጀምሯል። እነ ቃልኪዳን፣ ሳምራዊት፣ ሔዋንና ሌሎች በችግር ውስጥ የነበሩ ሴቶችም ‘የነገዋ’ የተሰኘውን የተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከልን ተቀላቅለው የተሻለ ነገን ለመኖር ተስፋ ሰንቀዋል፡፡ በማዕከሉ በሚሰጣቸው ሙያዊ ስልጠናና የምክር አገልግሎትም ወደ ተረጋጋ መንፈስ እንዲመለሱ፣ የሕይወት ተሞክሮ እንዲቀስሙ፣ ነጋቸውን ለማሳመር እንዲነሳሱ ስለማድረጉም ይናገራሉ። ማዕከሉ በአዲስ አበባ መከፈቱ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ሴቶች ትልቅ ብስራት መሆኑን ገልጸው፤ መሰል ማዕከላትም በአገር አቀፍ ደረጃ ሊስፋፋ እንደሚገባ ጠቁመዋል።   “የነገዋ” የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሄርጳሳ ጫላ ማዕከሉ ወደ ስራ ከገባ አንድ ወር በላይ ማስቆጠሩን አስታውሰው፤ 500 ሴቶችን ተቀብሎ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ሰልጣኞች ከማዕከሉ ሲወጡ ራሳቸውን በኢኮኖሚ እንዲችሉ የሚያደርግ በልዩ የክህሎት፣ የስነ ልቦና እና የሙያ በአጠቃላይ በ18 አይነት የስልጠና ዘርፎች እያሰለጠነ መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ስፌት፣ ስነ ውበት፣ የምግብ ዝግጅት፣ የከተማ ግብርና፣ የሕጻናት እንክብካቤና ሌሎች ዘርፎች ከሶስት ወር እስከ ስድስት ወር እንደሚያሰለጥን ነው የገለጹት። ከስልጠናው በኋላ ለሰልጣኞች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠርም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር ማዕከሉ በትብበር እየሰራ መሆኑም ተናግረዋል፡፡ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማእከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር) መጋቢት 05 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ለአገልግሎት ከፍት መሆኑ ይታወሳል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ''እራትም... መብራትም'' የመሆን ጅማሬ
Apr 14, 2024 1282
ሲሳይ ማሞ (ከአሶሳ) ያኔ! 2003 ዓ.ም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ የተነገሩ ተስፋዎች የማየፈቱ ህልሞች ብለን ስንቶቻችን አስበናቸው ይሆን? በአካባቢው ሊኖር ስለሚችለው ታላላቅ ክስተቶች፣ ስለሚፈጠሩት መልካም ነገሮች በሰማንበት ቅጽበት በህልም ዓለም ውስጥ እንዳለን ስንቶቻችን አስበን ይሆን? "አዬ ህልም!?" በሚል ሲደርስ እናየዋለን በሚል ቀናት ቆጥረናል። ያኔ! ነገሮች ሲነሱና ሲተረኩ ስንቶቻችን እንሆን እዚህ ቀን ላይ ደርሰን እናይ ይሆን!? የሚል ሃሳብ በእዝነ ህሊናችን የተመላለሰው? ያኔ! የታላቁ ህዳሴ ግድቡ ሲጠናቀቅ ወደ ኋላ ከ240 በላይ ኪሎ ሜትሮችን የሸፈነ ውሃ ሐይቅ ሰርቶ ተንጣሎ እንደሚተኛ እያለምን መጩውን ዘመን በጉጉት የጠበቅን ስንቶቻችን ነን? ግድቡ ግንባታው ሲገባደድ አገር የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨት በዘለለ "ከሰው ሰራሽ ሐይቁ በሚወጣ ዓሳ ሌላ የገቢ ምንጭ ይፈጠርላታል፤ በሚፈጠረው ሰው ሰራሽ ሃይቅ ላይ የጀልባ ትራንስፖርትና የመዋኛ አገልግሎቶች ይጀመራል" የሚሉት መረጃዎችንና ትንታኔዎችን ከመገናኛ ብዙሃኑ ስንሰማ እንደርስ ይሆን? የሚል ጥያቄ ወደ አእምሯቸው ያልመጣ ቢኖሩ ጥቂቶች ሳይሆኑ አየቀሩም። ያኔ! እንደትንቢት የተነገረው ዛሬ ጊዜው ሲደርስ "ይሆናል" የተባለው ከጊዜ ወደ ጊዜ "እየሆነ" መጣ። ስለታላቁ ግድብ በህልም ደረጃ ሲገለፁ የነበሩ በዕውን ወደማሳየቱ እየተንደረደረ ይገኛል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር የተያያዘ ገጠመኜን ጀባ ልበላችሁ! ዕለቱ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ከማለዳው 12 ሰዓት ነው፡፡ አፍንጫዋ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የሰካች አንድ የሞተር ጀልባ ከደቡብ ወደ ሰሜን የተንጣለለውን ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ ለሁለት እየከፈለች ትጓዛለች ከማለት ትበራለች ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ሰው ሰራሽ ሐይቁ ውሃውን እንደልቧ እየቀዘፈች ለመጓዝ አስችሏታልና! ከምዕራብ በኩል የኮርቻ ግድብ (Saddle dam) ተጠማዞ እና በኩራት ደረቱን ገልብጦ ይታያል፡፡ በስተምስራቅ አቅጣጫ ላይ የሚገኘው የግድቡ ሃይቅ ደግሞ ለስለስ ያለ ሃምራዊ ቀለም ለተመላካቹ ያሳያል። የማለዳዋ የፀሐይ ጨረር ያረፈበት የውሃው ክፍል ለእይታ ባያስቸግርም ገና ከማለዳው ከአካባቢው ሞቃታማ አየር ጋር ተዳምሮ ወላፈን የሚመስል ሙቀቱን መርጨት ጀምሯል፡፡ ከፊት ለፊታችን ደግሞ በረጅም ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያቆረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ ፊት ለፊት ተንጣሎ ይታያል፡፡ የተሳፈርንባት የሞተር ጀልባ ስምንት ያህል መንገደኞችን ይዛለች፡፡ በሰው ሰራሽ ሐይቁ ላይ የሚደረግ ጉዞ ለተጓዡ ሐሴትን ጀልባዋን ለሚዘውራት ከዕለት ገቢ የዘለለ ተድላን እንደሚለግስ አያጠራጥርም። የአካባቢውን ድባብ እየተመለከትን ጉዟችንን ቀጠልን። በጉዞው ቅፅበትም ዓይኖቻችን በአንድ ወጣት አሳ አስጋሪ ላይ አረፉ። ወጣቱ በጀልባዋ ላይ ሆኖ በአንደኛው አቅጣጫ በኩል አጎንብሶ በመንጠቆ ያጠመዳቸውን ግዙፍ አሳዎችን አጥብቆ እየያዘ ወደ ጀልባዋ ይጨምራል። ከአቅሙ በላይ ሆነው ሊያመልጡት የሚታገሉ አሳዎችን ደግሞ በብረት አንካሴ ወገባቸውን እየወጋ ለመያዝ ይታገላል፡፡ ተጠግተን ለመርዳትና አሳዎቹን በመያዝ ለማገዝም ሆነ ሌላ ድጋፍ ለማድረግ አልደፈርንም፡፡ ወጣቱ ግዙፍ አሳዎቹ ጋር የገጠመውን ግብግብ በካሜራ ለማስቀረት ጥረት ማድረጉን ግን አልዘነጋሁትም። ወጣቱ ኢትማን መሃመድ ይባላል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የጉባ ወረዳ ነዋሪ ነው፡፡ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ሐይቅ ላይ አሳ የማስገር ስራ ከጀመረ ወራት አስቆጥሯል፡፡ “ቤተሰቦቼ እንደነገሩኝ ከ13 ዓመት በፊት ግድቡን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ አሁን በሞተር ጀልባ የምንጓዝበት ሃይቅ ይፈጠራል የሚል እምነት በአካባቢው ነዋሪዎች እሳቤ ውስጥ ፈጽሞ አልነበረም።” ሲል ይናገራል ወጣቱ፡፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሃይቅ ለእርሱ እና ለሌሎች ከእርሱ ጋር ለተደራጁ 25 ወጣቶች የሥራ እድል በር መክፈቱን አጫወተኝ፡፡ ከታላቁ ግድብ ያገኙት ትሩፋት እርሱ እና የማህበሩ አባላት በአገራቸው ላይ ሰርተው የመለወጥ ተስፋቸውን በእጅጉ እንዳለመለመላቸው አጫውቶኛል፡፡ ከዚህ ቀደም በአካባቢው ከሚገኙ ወንዞች አሳ ቢያመርቱም በህዳሴው ግድብ አማካኝነት ከተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ የሚያገኙት ግን በዓይነትም በመጠንም የተለየ እንደሆነ ይናገራል። ከሐይቁ እስከ 50 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ነጫጭና ሌሎች ዓሳዎችን እያሰገረ መሆኑን በአድናቆት ጭምር ይገልፃል። ማህበሩ በቀን እስከ ሁለት ኩንታል ወይም ሁለት መቶ ኪሎ ግራም ገደማ ዓሳ ያመርታል፡፡ “የህዳሴው ግድብ የምግብ ዋስትናም ፤ የገቢ ምንጭም ሆኖናል” ሲልም ወጣቱ ሃሳቡን ቋጭቷል። ለሰዓታት በቆየሁበት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ የአሳ ማስገር እንቅስቃሴ ላይ ኢትዮጵያውያን በአንድነት መንፈስ ከገነቡት ግድብ የስራ ዕድል ተጠቃሚ የመሆን ጅማሬን ይስተዋላል። ነገሩ እንዲህ ነው! በባህር ዳር ጣና ሃይቅ ላይ ያካበተውን የአሳ መረብ አሰራር እና የሞተር ጀልባ አጠቃቀም ልምድ ለማካፈል ወደ ስፍራው ያቀናው ወጣት የሻምበል ወርቁ በማህበር ተደራጅተው አሳ ለሚያሰግሩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ወጣቶች ስልጠና ሲሰጥ ማግኘቴ ቀደም ብዬ የጠቀስኩትን መረጃ እውነታነት ያሳያል። “አንዱ ወንድሜ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ይሄም ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እኔም ከአማራ ክልል ነኝ፡፡ ሁላችንም እኩል የግድቡ ትሩፋት ተጠቃሚ ነን፡፡ ከዚህ ቀደም በአካል የማንተዋወቀውን ኢትዮጵያውያንን ግድቡ አስተዋውቆናል” ብሎኛል የሻምበል። ሌላው የመንጠቆ አጣጣል ስልጠና ለመስጠት ከአርባምንጭ ተጉዞ ወደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ መጥቶ ያገኘሁት ደግሞ ወጣት አልማው ደሳለኝ ነው። ''ለአካባቢው ወጣቶች ልምዴን እና ያለኝን ዕውቀት በማካፈሌ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ'' የሚለው ወጣቱ፤ በሃይቁ ላይ የተመለከተው ከፍተኛ የአሳ ሃብት እንደ እርሱ ያሉ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በመጥቀም ለአገሪቷም የተሻለ ገቢን ሊያመጣ እንደሚችል ያምናል። “ተባብረን በመስራት አገራችንን እንለውጣለን” በማለት ህብረትና አንድነት ከድህነት ለመውጣት የሚያስችል ዘመኑ የሚፈልገው ታላቅ መሳሪያ መሆኑን ያምናል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ...ተብለው ሲነገሩ የነበሩ የወደፊት ትልሞች አሁን እውን ሆነው 'ስራን ለሰሪው....ፍፁማዊ የገፅታ ለውጥን ለአካባቢው መልክዓ ምድር እንዲሁም ሰፊ የቱሪዝምና ሌሎች የስራ መስኮችን ለሚመለከተው አካል ለመስጠት የተግባር ጅማሬ እየታየ ነው። በግድብ ግንባታው የመሰረት ድንጋይ ማኖር ወቅት "በይሆናል" ሲባሉ የነበሩ ዕቅዶች እውን ወደ መሆን...ወደ መጨበጥ እየመጡ መሆናቸው ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው። ለኢትዮጵያውያን የ”ይቻላል” ተምሳሌት የሆነው ግድብ ዋነኛ በይበልጥ ሲጠቀስ ከነበረው የኃይል አቅርቦት ባሻገር ለዜጎች ሌላ የስራ መስክ በመፍጠር ' እራትም መብራትም' ሆኖ እስከመጨረሻው ሊዘልቅ እነሆ ውጤቱን እያሳየ ነው። እንግዲህ የነገ ሰው ብሎን ትሩፋቱን በይበልጥ ያሳየን !!  
በህብር የተገነባ ገድል
Mar 25, 2024 2181
  "የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም የትውልድ አሻራ ደምቆ የተፃፈበት የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። ይህ ቀን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት የረባ ጥቅም ሳይሰጥ ወደ ጎረቤት አገራት ሲፈስ የኖረውን የአባይ ወንዝ ወደ ብርሃን ለመቀየር በቁርጠኝነት በመነሳት የማይቻልን ነገር በይቻላል ወኔ በመቀየር ለዓለም ያሳዩበት፤ ዓለም የተደመመበት ቀን ነው። የግድቡ ግንባታ በተጀመረበት ወቅት በርካታ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያ ይህን ግዙፍ ፕሮጀክት ታሳካው ይሆን? የሚል ጥርጣሬ አዘል ርእስ የያዘ ተከታታይ ዘገባ አስነብበዋል። ኢንተርናሽናል ሪቨርስ የተሰኘው ድረ ገጽ በፈረንጆቹ 2011 ‘Can Ethiopia Afford the Grand Renaissance Dam?’ በሚል ርእስ ባወጣው ሰፋ ያለ ዘገባ ግድቡን ለመገንባት ከሚያስፈልገው ጠቅላላ ገንዘብ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ሊያዋጡ የሚችሉት በጣም ጥቂቱን ብቻ በመሆኑ ግንባታው ሊሳካ አይችልም በሚል ትንበያውን አስቀምጦ ነበር። የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገው ግሪን ፕሮፊት የተሰኘ ድረ ገጽ የግድቡን ግንባታ አስመልክቶ ‘Defiant Ethiopia is proceeding with its plan to build the Grand Millennium Dam on the Nile River, but what kind of dam can they build without cash flow? ..... there’s one important problem: Ethiopia lacks the necessary funds to see the project to completion. In fact, they can barely get it off the ground.’ በማለት ኢትዮጵያ ግድብ መገንባት የሚያስችል ገንዘብ ስለሌላት ፕሮጀክቱ ሊተገበር አይችልም ሲል ደምድሟል፤ ተሳልቋልም። በወቅቱ የዚህ ዓይነት ግምት የብዙዎቹ ተንታኞች መንደርደሪያ ነበር። “ኢትዮጵያ ደሃ አገር ስለሆነች ከዓለም አቀፍ ተቋማት ብድር ካልተገኘ በስተቀር ፕሮጀክቱ ወደ ፍፃሜ መድረስ አይችልም” የሚል ድምዳሜ ለመስጠት ተንታኞቹ ብዙም አይቸገሩም ነበር። ‘ግድቡ የጥራት ችግር ስላለበት ይደረመሳል’ ከሚለው ዘመቻ ጀምሮ በግድቡ ላይ ጥቃት እንደሚፈጸምበት ተደጋጋሚ የዛቻና የማስፈራሪያ መልእክቶች ተስተጋብተዋል። በጥቅምት ወር 2013 ዓ. ም የቀድሞ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በህዳሴ ግድብ ግንባታ ግብጽ ተጎጂ እንደሆነች አቋም በመያዝ "ግብፅ በዚህ መንገድ መቀጠል ስለማትችል ሁኔታው አደገኛ ነው፤ ግብፅ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳለች፤ አሁንም በግልፅ እናገረዋለሁ ግብፅ በድጋሚ ታፈነዳዋለች" የሚል ጠንከር ያለ የዛቻ መልእክት አስተላልፈዋል። ኢትዮጵያውያን ውኃ ወደ ናይል እንዳይፈስ የሚያቆም ግድብ ገንብተዋል ሲሉ የገለጹት ትራምፕ ግብጽ ትንሽ በመበሳጨቷ ልትወቅሷት አትችሉም ሲሉም አክለዋል። "ግብፅ የህዳሴ ግድብ እንዲገነባ መፍቀድ አልነበረባትም፤ የስምምነት ሀሳብ ለአገራቱ ባቀርብም ኢትዮጵያ ስምምነቱን ሳትቀበል ቀርታለች። እንደዚያ ማድረግ አልነበረባቸውም ይህ ትልቅ ስህተት ነው። በዚህም ምክንያት የምንሰጣቸውን ብድር አቁመናል። ስምምነቱን ካልተቀበለች በስተቀር ኢትዮጵያ ገንዘብ አታገኝም " ብለዋል። አትዮጵያ የህዳሴ ግድብን ለመገንባትና ዳር ለማድረስ ብድርና ዕርዳታ እንዳታገኝ የተለያዩ ኃይሎች ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። በዚህም ምክንያት የፕሮጀክቱን ወጪ ለመሸፈን የሚተባበር አገር ወይም ተቋም ማግኘት አልተቻለም፡፡ ስለሆነም የነበረው አማራጭ አንድም ግድቡን አለመሥራት፣ አለበለዚያ ወጪውን በራስ አቅም መሸፈን ነበር፡፡ ከእነዚህ ከባድ ሁለት አማራጮች መካከል የኢትዮጵያ ሕዝብ ምርጫ ወጪውን በራሱ አቅም በመሸፈን መስዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን በተግባር አረጋገጠ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነበር ኢትዮጵያውያን ገጠር ከተማ ሳይሉ፤ በአገር ውስጥና በውጭ ከጫፍ እስከ ጫፍ በእልህና በቁጭት በመነሳሳት ግድቡን በራሳቸው አቅም ገንብተው ዳር ለማድረስ ቃል ኪዳን ያደረጉት። ለግንባታው የሚውል ድጋፍ በገንዘብና በዓይነት በተለይም የቦንድ ሽያጭ፣ በ8100 አጭር መልእክት እና በእጣ አገልግሎት ህዝቡ ተረባረበ፤ የማይቻለውን እንደሚቻል ለዓለም አሳየ። በበርካታ ፈተናዎችና ጫናዎችን ሳይበገር ግንባታው የቀጠለው የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት የሲቪል ስራው 99 በመቶ መድረሱንና የኤሌክትሮ ሜካኒካል በተለይም የተርባይንና ጄኔሬተር ተከላ ሥራው 78 በመቶ መጠናቀቁን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባት ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት በቅርብ ያወጣቸው መረጃዎች ያመለክታሉ። ከለውጡ ማግስት ጀምሮ መንግስት ልዩ ትኩረት ከሰጣቸው ፕሮጀክቶች መካከል የህዳሴው ግድብ ቀዳሚው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ "የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" በማለት አረጋግጠዋል። በዚህም ኢትዮጵያ ከግድቡ ግንባታ ጋር የተያያዙ ውስጣዊና ውጫዊ ጫናዎች ቢኖሩባትም የግድቡን ሥራ ለአፍታም አላቋረጠችም። በአሁኑ ወቅት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አፈፃፀም ከ95 በመቶ በላይ መድረሱን የሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል። ዘንድሮ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መሠረት ድንጋይ የተጣለበትን 13ኛ ዓመት ይከበራል፤ መሪ ሀሳቡም "በኅብረት ችለናል!" የሚል ሲሆን ኢትዮጰያውያን ችለው ያሳዩበት ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። እዚህ ድል ላይ የተደረሰው በመንግሥት ቁርጠኛ አቋምና የዲፕሎማሲ ጥረት እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ነው። ባለፉት 13 ዓመታት ኢትዮጵያውያን ለግድቡ ግንባታ 18 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል። በኢትዮጵያውያን ያልተቋረጠ ተሳትፎ ተጀምሮ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ሊጠናቀቅ ወራቶች የቀሩት ይህ ታላቅ አገራዊ ፕሮጀክት የአገሪቱን የኃይል ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ ከማሻሻሉም ባሻገር ለጎረቤት አገራት ተደራሽ በማድረግ ቀጣናውን በማስተሳሰር በኩል ሚናው ከፍተኛ ነው።  
በከፍታ የታጀበ ስኬት
Mar 15, 2024 1804
ለህጻናትና ታዳጊዎች መልካም ስብእና የሚያግዙ ጽሁፎችን ያዘጋጀችው ኤሪን ሶዴርበርግ ዶውኒንግ 'JUST KEEP WALKING' በሚለው መጽሃፏ ባደራጀችው ገጸባህሪ አማካይነት “አንተ መልካምና ስኬታማ ሆነህ ሳለ ጥቂት ሰዎች ስለአንተ መጥፎነት አብዝተው መጨነቅና ማውራት ከጀመሩ የምትሄድበት መንገድም ሆነ አካሄድህ ትክክል ነውና መራመድህን አታቁም። ብዙሃኑ የስኬትህ ተካፋይና የስኬትህ አጋር ስለሆኑ የጥቂቶቹን ጫጫታ ከምንም ካለመቁጠር ተራመድ ብዙ አፍራሽ ወሬዎች ያንተን ስኬት የመመስከር አቅማቸው ከፍተኛ መሆኑን አትዘንጋ። መቆም የሽንፈት ምልክት ነውና” ትለናለች። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላለፉት 78 ዓመታት በከፍታ የዘለቀ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስምና ዝናው የገነነ ተቋም ነው። አየር መንገዱ ታህሳስ 21 ቀን 1938 ዓ.ም ተመስርቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ በረራውን መጋቢት 30 ቀን 1938 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ካይሮ አድርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየዘመኑ በአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎችን በመታጠቅና አሰራሮችን በማዘመን ራሱን እያደራጀ የኢትዮጵያ ኩራት ከመሆን አልፎ የአፍሪካ ምልክት ሆኖ ዘልቋል። ዛሬ ላይ የ152 ዘመናዊ አውሮፕላኖች ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በምስረታው ወቅት ከአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል የተገዙና በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ያገለገሉ አምስት አውሮፕላኖች ብቻ እንደነበሩት መረጃዎች ያመለክታሉ። በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በዓመት ከ22 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን እንደሚያስተናግድ የሚነገርለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞችን ፍላጎትና ምቾት ለመጠበቅ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ጨምሮ 31 አውሮፕላኖች ለመግዛት ከአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ጋር ስምምነት ላይ ደርሷል። እነዚህን ተጨማሪ አዳዲስ አውሮፕላኖችን ቁጥር ጨምሮ የሚገነባቸው ዘመናዊ አየር መንገዶች ሲደመሩ በአፍሪካ ግዙፍ ተቋምነቱን ይበልጥ የሚያረጋግጥ ያደርገዋል። የበረራ አድማሱን በየጊዜው እያሰፋ የሚገኘው አየር መንገዱ አሁን ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ 134 መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን በሀገር ውስጥ ወደ 22 መዳረሻዎች ይበራል። ከዚህ ውስጥ 60 የበረራ መዳረሻዎቹ አፍሪካ ውስጥ ነው። አየር መንገዱ ከ55 ሚሊየን ዶላር በላይ አስገንብቶ ወደ ስራ ያስገባው ዘመናዊ የካርጎ ማእከል ከምስራቅ አፍሪካ ብሎም ከአፍሪካ ከፍተኛ ተብሎ ተመዝግቦለታል። በ15 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ግንባታው ያረፈው የካርጎ ማዕከል ለኤሌክትሮኒክስ ግብይት (ኢ ኮሜርስ) አገልግሎት የሚውል ሲሆን የካርጎ አገልግሎት እየሰፋ መምጣት አየር መንገዱ የሚሰራቸው ተያያዝ በርካታ ተግባራት መስፋት፣እንዲሁም የዲጂታል ግብይት ተመራጭ መሆን ለማእከሉ ግንባታ ምክንያት ተብለው ተጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በማህበራዊ መስክ ከሚታወቅባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ሴቶችን በማብቃትና የጾታ እኩልነትን በማስተግበር ረገድ አርአያነት ያለው ተግባር መፈጸሙ ነው። በየዓመቱ የሚታሰበው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በአውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጠር ማርች 8 በሚከበርበት ዕለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላለፉት በርካታ አመታት ወደ ተለያዩ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ሙሉ ለሙሉ በሴቶች ብቻ የተመራ በረራን በማደረግ ዓለም አቀፍ ዝናን አትርፏል። አየር መንገዱ ዘንድሮ ለ9ኛ ጊዜ "ሴቶችን በማብቃት አፍሪካን ማስተሳሰር" በሚል መሪ ቃል ከአዲስ አበባ ወደ ለንደን በሴቶች ብቻ የተመራ የተሳካ በረራ አድርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመንገደኞች በሚሰጠው ዘመኑን የዋጀና ቀልጣፋ አገልግሎት በየጊዜው የተለያዩ ሽልማቶች ባለቤት መሆን የቻለ ተቋም ነው። ለአብነት የቅርብ ጊዜያቶችን ለማንሳት ያህል ባሳለፍነው ዓመት በአየርላንዷ ደብሊን በተዘጋጀ መርሐ-ግብር ላይ በዓመታዊው የ“አፔክስ” የመንገደኞች ምርጫ “ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ” ሽልማትን አሸንፏል፡፡ በተመሳሳይ ዓለም አቀፍ የአየር ጭነት ኢንዱስትሪ ጉባኤ "ኤር ካርጎ ኤሮፕ" እ.አ.አ በ2021 ባካሄደው የበይነ መረብ የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የካርጎና የሎጅስቲክ አገልግሎት የ2021 የአየር ጭነት ኢንዱስትሪ የደንበኞች እንክብካቤ ዘርፍ ሽልማት አግኝቷል። በአውሮፓውያኑ 2024 ዓመታዊውን የብሪክስ አባል ሀገራት የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የ2024 ሽልማት ላይ “የኮርፖሬት የዘላቂነት ስኬት ሽልማት” አሸናፊ ሆኗል። አየር መንገዱ በትላልቅ ስኬቶች የማለፉን ያህል ከባድ ፈተናዎችንም ተጋፍጦ በጽናትና በስኬት አልፏል። መላውን ዓለም ያዳረሰው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ አንዱ ማሳያ ነው። በዚያን ጊዜ የመንገደኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነሱ ምክንያት በዓለም ደረጃ በርካታ አየር መንገዶች በረራ በማቋረጥ ችግር ውስጥ ወድቀዋል። በዚህ ፈታኝ ወቅት አየር መንገዱ የስትራቴጂ ለውጥ በማድረግ አንዳንድ የመንገደኞች አውሮፕላኖቹን ወደ ዕቃ ጫኝ በመቀየር ጭምር ትኩረቱን ጭነት ማጓጓዝ ላይ አድርጓል። በዚያን ፈታኝ ወቅት አየር መንገዱ የቀየሰውን ስትራቴጂ በመቃወም ከውስጥም ከውጭም ከተለያዩ አቅጣጫዎች ትችትን አስተናግዷል። ይሁን እንጂ አየር መንገዱ ፈተናውን በመቋቋም እንደሌሎቹ ሀገራት አውሮፕላኖች በረራ የማቋረጥ እጣ ሳይገጥመው በታላቅ ብልሃት ማለፍ የቻለ ተቋም መሆኑ ተመስክሮለታል። በዚህም በካርጎ አገልግሎት ገቢ ከማገኘቱም ባሻገር ክትባትን ለዓለም በማዳረስ ወረርሽኙ ለመግታት በተደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት ውስጥ የራሱን አሻራ አኑሯል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የራሱ የአውሮፕላን አብራሪዎች ማሰልጠኛ ትምሕርት ቤት ሲኖረው የግል አብራሪ እና የንግድ አውሮፕላን አብራሪ ፈቃድ በመስጠት የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ዜጎችን በማሰልጠን ከአራት አስርተ ዓመታ በላይ ልምድ አካብቷል። አየር መንገዱ በሚያስተዳድረው ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የበረራ ባለሙያዎችን በቅርቡ ያስመረቀ ሲሆን ምሩቃኑ ከታንዛንያ ከደቡብ ሱዳን ከኒጀር ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከቶጎ እና ከማዳጋስካር መሆናቸው ደግሞ የአየር መንገዱን የፓንአፍሪካኒስት መንፈስ አጉልቶ ያሳየ አድርጎታል። ስኬቶቹ በዚህ ያላበቁት አየር መንገዱ የእድገት ግስጋሴውን እንደቀጠለ ይገኛል። ከሰሞኑ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደ ደማቅ ስነ-ስርዓት ላይ ለአምስት ተቋማት ‘የኢትዮጵያ ተቋማት ስኬት ሽልማትን’ አበርክተዋል። በዚህ ወቅት ከተሸለሙት ተቋማት መካከል አንዱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲሆን ሽልማቱ ለወደፊትም ለላቀ ስኬት የሚያዘጋጀው እንደሆነ ይታመናል።  
ትንታኔዎች
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች
Mar 2, 2024 3496
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች (ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ)   የአድዋ አድማስ ዘለል ገድል ሲወሳ የድሉ መገኘት የጦር አበጋዞች ከፊት ይመጣሉ። ከንጉሠ ነገሥቱ ጀምሮ ራስ፣ ደጃዝማች፣ ፊታውራሪ፣ ቀኛዝማች፣ ግራዝማች፣ ባላምባራስ እና ሌሎች ባለማዕረግ አዋጊዎች የድሉ የጀርባ አጥንት መሆናቸው እሙን ነው። ከመላ ሀገሪቷ ጠረፍ ተነቃንቆ ስንቅና ትጥቁን ታጥቆ፣ ድል ሰንቆ እስከ ግማሽ ዓመት ድረስ በባዶ እግሩ የተመመውን የሀገሬው ሰራዊት በቅጡ መርተው አዋግተዋል። ከመነሻ ሰፈር እስከ አድዋ ተረተር፣ ከአምባላጌ ኮረብቶች እስከ መቀሌ ጋራና ቁልቁለቶች፣ ከእንደአባ ገሪማ እስከ ማሪያም ሸዊቶ ሸለቋማ ቋጥኞች፣ ከምንድብድብ መስክ እስከ በገሠሦ አቆበቶች፣ .... ድልና ገድል በደምና በላብ ሲጻፍ የጠላትን የ'ክዱ' ማባባያ የጠሉ፣ ለሀገር ለመሰዋት የቆረጡ ጀግና አዋጊዎች፣ የሀገር ባለውለታዎች ነበሩ። በአድዋ ድል መታሰቢያ 12 የአድዋ ጦር አበጋዞች (ጀኔራሎች) ሀውልት ቆሞላቸዋል። እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ (አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ (አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። ከነዚህ የአገር ባለውለታዎች መካከል ሁለት ስመ ሞክሼ ጀግኖችን እንዘክራለን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከዳግማዊ አፄ ምኒልክ ቀዳሚዎች ስምንት ራሶች መካከል ብቸኛው የራስ ቢትወደድ (ከንጉሥነት በታች) ባለማዕረግ ናቸው። በፈረስ ስማቸው አባ-ገድብ ይሰኛሉ። በልጅነታቸው የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ባለሟል ሳሉ ከእስረኛው ምኒልክ ጋር ተዋወቁ። ምኒልክ ከአፄ ቴዎድሮስ አምልጠው ሸዋ ከገቡ በኋላ ከእቴጌ ጣይቱ ብጡል ወንድሞች ራስ ወሌ እና ፊታውራሪ አሉላ ብጡልን ይዘው ከመቅደላ ወደ ሸዋ ተሻገሩ፤ የምኒልክ ሁነኛ ሰው ሆኑ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም በሞት እስኪለዩ ድረስ በክፉም በደጉም ዘመን የአጼ ምኒልክ ከፍተኛ አማካሪና ተወዳጅ መስፍን እንደነበሩ፣ ከጦር ሜዳ እስከ ሽምግልናም ሁነኛ ሰው ሆነው ስለማገልገላችው በታሪክ ድርሳናት ተጠቅሷል። በሸዋ፣ ወሎ፣ ጎንደር፣ ዳሞት(ጎጃም) ተዘዋውረው በተለያዩ ግዛቶች በአስተዳዳሪነት ሰርተዋል። ድሕረ መተማ ጦርነት ምርኮኞች እንዲመለሱ፣ ድንበር እንዲካለል በመስራትም የዲፕሎማሲ ስራቸው ይጠቅሳል። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከተሳተፉባቸው ደማቅ ታሪኮች መካከል የአድዋ ድል ይጠቅሳል። ጦርነቱ አሀዱ ብሎ የጀመረው ሕዳር 28 ቀን 1888 አምባላጌ ነው። ለሁለት ሰዓታት በዘለቀው በዚህ ጦርነት ጀኔራል ቶዚሊ የተባለው የጠላት ጦር መሪ የተገደለበት ነው። በዚህ ዐውደ ውጊያ አባ ገድብ አንዱ ወሳኝ የጦር አበጋዝ ነበሩ። በተለያዩ የታሪክ ድርሳናት እንደተመዘገበው ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከግዛታቸው ከዳሞትና አገው ምድር የተውጣጣ ስድስት ሺህ እግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር ይዘው አድዋ ዘምተዋል። “አባ ገደብ መንጌ እያለ ኧረ ጐራው አምባ ላጌን ሰብሮ ቶዘሊን አስጐራው” የተባለው ለዚህ ይመስላል። አባ ገድብ ጥቅምት 11 ቀን 1903 ምሸት ከራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው ጋር እየተጫወቱ ካለምንም ህመም ድንገት አርፈው ቅድስት ሥላሴ ተቀበሩ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ ልጆቻቸውን ከተለያዩ መኳንንት ጋር በጋብቻ በማጣመር በኢትዮጰያ ታሪክ ተጠቃሽ መሆን ችለዋል። ለአብነትም ዘውዲቱ መንገሻ ጠቅላይ ሚኒስትር መኮንን እንዳልካቸውን፣ አስካለማርያም መንገሻ ልዑል ራስ ኅይሉን አግብተው የልጅ ኢያሱን ባለቤት ሠብለወንጌል ኅይሉን ወልደዋል። ደጃዝማች ጀኔራል አበበ ዳምጠውን ያገቡት ወሰንየለሽ መንገሻ ደግሞ የአልጋወራሽ አስፋወሰን ባለቤት ልዕልት መድፈሪያሽ ወርቅ አበበን ወልደዋል። ሌላው የአድዋ ጀግና የጦር መሪ ራስ መንገሻ ዮሐንስ (አባ ግጠም) ናችው። ትውልዳቸው ትግራይ፣ ዘመኑም 1857 ዓ.ም ነው። የአድዋ ጦር ውሎ ቁልፍ ሰው ራስ መንገሻ የአጼ ዮሐንስ (አባ በዝብዝ) ልጅ ናቸው። አጼ ዮሐንስ በተሰዉበት በመተማው ጦርነት ተሳትፈዋል። አባታቸው ከሞቱ በኋላም የትግራይ አገረ ገዥ ሆነዋል። በአድዋ ዘመቻ 12 ሺህ ጦር አሰልፈው በብርቱ ተዋግተዋል። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከአድዋ ጦርነት ቀደም ብሎ በአጼ ምኒልክ ላይ እንዲያምጹ ኢጣሊያኖች ሲገፋፋቸውና ሲያባብላቸው ቢቆዩም ከስልጣን ሽኩቻ ይልቅ የኢትዮጵያን ነጻነት መርጠዋል። ከአጼ ምኒልክ ጋር ቢኳረፉም በሀገር ሉዓላዊነት ግን አልተደራደሩም። የኢጣሊያ ወራሪ ጦር ትግራይ ሲገባም ራስ መንገሻ የወገን ደጀን ጦር እስኪደርስ ወደራያ አፈግፍገው፣ በአምባላጌ ጦር ሜዳ አንዱ ተሳታፊ የጦር ጀግና ነበሩ። ራስ መንገሻ የትግራይ ሀገረ ገዥ በመሆናቸውም የእርሳቸው እና በስራቸው የነበሩት የራስ አሉላ እንግዳ ጦር በጄኔራል አልቤርቶኔ ከሚመራው ጠላት ሃይል ቀዳሚው ተፋላሚ እንዲሆኑ አድርጎታል። “አይከፈት በሩ መግቢያ መውጫችን በል ተነስ መንገሻ ግጠም በር በሩን ይህን ጎሽ ጠላ ማን አይቀምሰው መንገሻ ዮሐነስ አንተን ገፍተው...” ተብሎ የተገጠመላቸውም ለዚህ ነው። የጠላት መግቢያ በር ዘብ በመሆናቸው። አባ ግጠም በአድዋው ታሪካዊ ጦርነት አሰላለፋቸው ማርያም ሸዊቶ በተሰኘው ተራራ በኩል ሲሆን ከራስ አሉላ፣ ከዋግሹም ጓንጉል ብሩና ከደጃዝማች ሀጎስ ጋር በመሆን ነበር። የጠላትን የመጀመሪያ ጥቃትን ያስተናገዱትም ራስ መንገሻ ዮሐንስ ናቸው። የአድዋ ድል ከተበሰረ በኋላ አጼ ምኒልክ ራስ መንገሻን ሹመውና ሸልመው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል። አጼ ምኒልክ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ማህበረሰቡ በጦርነት ስፍራ በመሆኑ ለደረሰበት ጉዳት 30 ሺህ ብር ድጋፍ ማድራገቸውን የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል የጻፉት ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደአረጋይ ተርከዋል። ከአድዋ ድል ከጥቂት ዓመታት በኋላ ራስ መንገሻ በአጼ ምኒልክ ላይ በማመጻቸው ተይዘው በቁጥጥር ስር ዋሉ። ሕዳር 6 ቀን 1899 ዓ.ም አንኮበር ግዞት ላይ አንዳሉ ማረፋቸውን የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከራስ መንገሻ አቲከም ግዛት ከአገው ምድር እመይቴ ተዋበች ጋር ትዳር መስርተው ዕውቁን የትግራይ መስፍን ራስ ሥዩም መንገሻን እንዲሁም ከእቴጌ ጣይቱ የወንድም ልጅ ወይዘሮ ከፈይ ወሌ ብጡል አግብተው አስቴር መንገሻን፣ አልማዝ መንገሻንና ብርሃኔ መንገሻን ወልደዋል፡፡ ለአብነት ያክል የሞክሼዎቹን ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ አነሳን እንጂ የዛሬ የ128 ዓመት በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ የጻፉ ጀግኖች ቁጥር ስፍር የላቸውም። ጀግኖቹን የመሩ የጦር መሪዎችም ብዙና ተጋድሏቸው የገዘፈ ነው። ከ11 ሺህ በላይ የጣሊያንን ሠራዊት ሙትና ቁስለኛ ያደረጉ፣ 4ሺህ የሚሆኑትን እጅ ያሰጡና የማረኩ እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር እንዲያስረክብ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሁል ጊዜም ክብር ይገባቸዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። (በአየለ ያረጋል)      
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች 
Mar 2, 2024 2331
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች ለመነሻ እኤአ በ1885 ጀርመን በተካሄደው የበርሊን ኮንፈረንስ አውሮፓውያን መላ አፍሪካን በካርታ ላይ የተከፋፈሉትን በተግባር መሬት ላይ ለመቀራመት ጦራቸውን ሰብቀው፣ ስንቃቸውን ጭነውና ትጥቃቸውን አጥብቀው ያካሄዱት ዘመቻና የወረራ ጉዞ የተገታባት አድዋ እና እለቷ ዛሬ ድረስ በተገፉ ህዝቦች ልብ ታትማ በአዕምሮ ውስጥ ተቀርጻ ትኖራለች። ጣሊያን የኢትዮጵያን መሬት፣ የአየር ንብረትና መልክዓ ምድር ተቆጣጥሮ ሀብቷን ለሮምና ለመላው አውሮፓ ለማቅረብ የቋመጠበት የዘመናት ህልሙ የተኮላሸበት ቦታ ጭምር ናት - አድዋ። ይህ ወራሪ ኃይል ሊቢያን በእጁ ካስገባ በኋላ ጉዞውን በቀይ ባሕር አስመራ አድርጎ መላ ኢትዮጵያን የመቆጣጠር ግብ ነበረው። ጄነራል ባራቴሪ የመደባቸው ጄነራል አልበርቶኒ፣ ጄኔራል አሪሞንዲ እና ጄነራል ቦርሜዳ በግንባር የተሰለፈውን ጦር ሲመሩ የኋላ ደጀንም እንደነበራቸው የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ከ17 ሺህ በላይ የጣሊያን ሠራዊት 66 የሚሆኑ መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና አውቶማቲክ መሳሪያዎችን ታጥቆ የግንባር ሜዳው ላይ ስለመድረሱ "የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው እስካሁኑ ዘመን" በሚል በአንድርዜይ ባርይትኒስኪ እና ዮዓና ማንቴል-ኒየችኮ ተጽፎ በዓለማየሁ አበበ የተተረጎመው መጽሐፍ ያስረዳል። የዛሬ የ128 ዓመት፤ ዕለቱም የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ በጀግኖች አባቶች ተሰራ። በጦርነቱ የጣሊያን መንግስት የጎመጀውን የኢትዮጵያን መሬት ሊያገኝ ይቅርና ከ11 ሺህ በላይ ሠራዊቱ ሙትና ቁስለኛ ሆኑ። 4ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ለጀግኖች አባቶቻችን እጃቸውን ሰጥተው ተማረኩ። እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር አስረከበ። የቀረው የፋሽስት ሠራዊትም ተንጠባጥቦ እግሬ አውጪኝ ብሎ ፈረጠጠ። ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ክብር፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት በአውደ ግንባሩ በፈጸሙት የጀግንነት ተጋድሎ ዓለምን ያስደመመና መላውን ጥቁር ሕዝብ ያኮራ ድል ተጎናጽፈዋል። በወቅቱ ነጭን ታግሎ ማሸነፍ አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ በይቻላል ተክቶ ሌሎችም ለነፃነታቸው እንዲታገሉ ያነሳሳ ደማቅ የታሪክ አሻራ አኑረዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። ኢትዮጵያውያን በብሔር፣ በሃይማኖት፣ በአካባቢና በሌሎች ልዩነቶች ሳይነጣጠሉ ለአገራቸው ክብርና ነጻነት በአንድነት ቆመውና መስዋት ከፍለው ያስመዘገቡት የጀግንነት ታሪክ ነው። በዓድዋ ድል ኢትዮጵያ ለአፍሪካና ለመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራትና የነፃነት ምልክት ሆናለች፡፡ የሰው ልጆችን እኩልነት በደም ዋጋ አረጋግጣለች።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋ ድል ደማቅና ታላቅ ቢሆንም በሚመጥነው ልክ መታሰቢያ አልነበረውም። ዛሬ ግን እነዚያ ዋጋ የከፈሉ ጀግኖችን በሚመጥን ሁኔታ በአዲስ አበባ ፒያሳ “የዓድዋ ድል መታሰቢያ” ተገንብቷል። ከአድዋ ድል 128 ዓመታት በኋላ፣ የተሰራው የአድዋ ድል መታሰቢያ በጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ተከፍቷል። የአድዋ ድል መታሰቢያ በአምስት ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን በአንድነት የተከፈለውን መስዋትነት፣ የአርሶ አደሮችን ተሳትፎ፣ የሴቶችን ተጋድሎ በሚያሳይ መልኩ፣ በአስገራሚ የኪነ-ህንጻ ጥበብ የታነጸ ነው።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የተገነባበት ስፍራ አገር በውጭ ወራሪ ኃይሎች እጅ እንዳትወድቅ የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ የዓድዋ ጅግኖች የዘመቻቸው መነሻ እንዲሁም ከድል በኋላ ተሰባስበው ደስታቸውን የተጋሩበት ታሪካዊ ስፍራ ነው። የአድዋ ድል በዓል 7ኛ ዓመት ዳግማዊ ምኒልክ፣ ከአርበኞች፣ ከየአካባቢው ገዢዎች፣ ከውጭ አገር ዲፕሎማቶችና ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር በደማቅ ሁኔታ በዚሁ ስፍራ አክብረውታል። ስፍራው ዛሬ የታላቁ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሳይገነባበት በፊት በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ የልማት ስራዎች ቢታጭም ውጤታማ ስራ ሳይሰራበት ቆይቷል። አካባቢው ለረጅም ዘመናት ታጥሮ ሳይለማ በመቆየቱ እጅግ የቆሸሸ፣ ሰዎች ለዝርፊያ የሚዳረጉበት ስፍራ ሆኖ ቆይቷል። ዘመናትን ተሻግሮ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በከተማዋ ከሚገነቡ ትላልቅ ፕሮጀክቶች በዓይነቱ ልዩ የሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እንዲሰራበት ተደረገ። የዓድዋ ድል መታሰቢያ እጅግ በሚስብ ኪነ ህንፃ፤ የኢትዮጵያውያንን ህያው የድል ታሪክ የሚዘክር ሆኖ ተሰርቷል።   የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የኢትዮጵያውያን የድል ብስራት፣ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ኩራት የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የራሳቸው የሆነ ስያሜ ተሰጥቷቸዋል። የምሥራቅ ጀግኖች በር፣ የምዕራብ ጀግኖች በር፣ የሰሜን ጀግኖች በር፣ የደቡብ ጀግኖች በር፣ የፈረሰኞች በር፣ የአርበኞች በር፣ የፓን አፍሪካኒዝም በር ተብለው የተሰየሙ ናቸው። በአራቱም አቅጣጫዎች የተሰየሙ በሮች ተምሳሌትነት በዓድዋ ድል ከአራቱም አቅጣጫ ኢትዮጵያውያን በጋራ የተሳተፉበት የጋራ ድላቸው መሆኑን ያመለክታል፡፡   መታሰቢያው በውስጡ ምን ይዟል? በዋናው መግቢያ:- የኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን ነጻነት ድል መገለጫ የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ ሃውልትና የሁሉም ከተሞች ርቀት ልኬት መነሻ የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ምልክት ይገኛል። የዓድዋ ጦርነት ዘመቻን ያስተባበሩትና የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት የዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና የባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሀውልትም በዚሁ መግቢያ በኩል ይገኛል። ሃውልት የቆመላቸው 12 የጦር መሪዎች:- በመታሰቢያው የአድዋን ጦርነት በታላቅ ጀግንነት በመምራት ለጥቁር ህዝቦች ድል ያበሰሩ 12 ዋና ዋና የጦር መሪዎች ሃውልት ተቀምጧል፣ እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ ( አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ ( አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። በስተቀኝ በኩል፤- እስከ 3 ሺ እንግዶችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት የስብሰባ አዳራሽ የሚገኝ ሲሆን በመጀመሪያው ኮሪደር ላይ ደግሞ ህዝቡ የጦርነት ክተት አዋጅ ጥሪ ሲሰማ ሁሉም ልዩነቱን ወደ ጎን በመተው አገሩን ከወራሪ ለመታደግ በመወኔ መነሳቱን፣ ወደ ጦር ግንባር መትመሙን እንዲሁም በጀግንነት መፋለሙን የሚሳየዩ ትዕይንቶች በእስክሪኖች ይታያሉ። በክፍሉ መሐል ላይ፤- ጦርነቱ የተጎሰመበት ግዙፍ ነጋሪት የተቀመጠ ሲሆን በነጋሪቱ ግራና ቀኝ ለጦርነቱ መንስኤ የሆነው የውጫሌው ውል አንቀጽ 17፣ የአድዋ ታሪክ እንዲሁም ከድል ወደ ሰላም የሚለው የአዲስ አበባ ስምምነት ሰነድ ተዘርግቶ ይገኛል። ከድል መልስ ግልጋሎት ላይ የዋሉ ጋሻዎች፣ መሳሪያዎች፣ አልባሳት፣ መመገቢያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ በርካታ ቅርሶች፣ ስዕሎች፣ ፎቶዎች ይገኛሉ። ወደ ውስጥ መግቢያ በሆነው በምዕራብ በር ላይ የወቅቱ የኢትዮጵያ መሪ የነበሩት አጼ ሚኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሃውልት በክብር ተቀምጦ ይገኛል። በአድዋ ጦርነት ወቅት ጠላት ለመጠጥነት ይጠቀምበት የነበረውን የምንጭ ውሃ እቴጌ ጣይቱ ብልሃት በተሞላበት መልኩ በኢትዮጵያ ሰራዊት እንዲከበብና ጠላት በውሃ ጥም እንዲዳከም በማድረግ ማሸነፍ የተቻለበት የጦር እስትራቴጂ የሚዘክር ገንዳ ከእቴጌ ጣይቱ ሃውልት ፊት ለፊት ተቀምጦ ይገኛል። የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፤- ጦርነቱ የተካሄደበትን ቦታ የሚያሳየው የአሸዋ ገበታ ሌላው የአድዋ ድል መታሰቢያ ውበትም ታሪክም ነው፡፡ የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፣ መልከዓ-ምድር የሚሳየው የመሬት ላይ ንድፍ ስራ በዚሁ መታሰቢያ መቀመጡ ኢትዮጵያውያን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለነጻነት የከፈሉትን መስዋትነት ያመላክታል። ከተራሮች አጠገብ በጦርነት ወቅት ጥቅም ላይ ከዋሉ ጣሊያናዊ ስሪት የሆነ "ቶሪኖ 1883" የሚል ጽሁፍ ያለበት መድፍ ይገኛል። በጦርነቱ ተዋጊዎችን ያጓጓዙ 45 ሺህ ፈረሰኞች የሰሩትን ጀብድ ሊወክልና ሊዘክራቸው የሚችል ‘የአድዋ ፈረሰኞች የድል ሀውልት’ ቆሞላቸዋል፡፡ የአድዋ ጀግኖች ኢትዮጵያን ከወራሪው ጣሊያን ለማዳን ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት ሳይለዩ በአንድነት ተሰባስበው የተመሙበትን የሚወክል ‘የአንድነት ድልድይ’ በሚል ተሰርቷል፡፡ የሁሉንም ተሳትፎ የሚያሳዩ የተለያዩ ሁነቶች በጦርነቱ ወቅት ህዝብና አገርን በታማኝነት ሲያስተዳድሩ የነበሩ እንደራሴዎች የሚያሳይ ስዕላዊ በመታሰቢያ የተቀመጠ ሲሆን በጦርነቱ ወቅት የነበረውን የህዝቡን እንቅስቃሴ የሚገልጹ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና የመገልገያ ቁሳቁሶች፣ ስዕሎችና ቅርጾችም ይገኛሉ።   የገበሬዎችና ሴቶች ተሳትፎ የሚያሳዩ ስራዎች በአድዋ ጦርነት ከ120 ሺህ በላይ ገበሬዎች የግብርና ስራቸውን አቋርጠው "አገራችን ተነካች" በማለት ታጥቀው ድል ያጎናጸፉ፣ ለጥቁር ህዝቦች ትልቅ ታሪክ ያስቀመጡ ጀግኖች ናቸው። በዚህ መታሰቢያ የአንድነት ማዕከል፣ የአፍሪካ ነጻነት ማስታወሻ የኢትዮጵያ ጀግኖችን ጉዞ የሚያሳዩ ምስሎች ይገኛሉ። በጦርነት ወቅት ሴቶች የቤት ሃላፊነትን ከመወጣት በተጨማሪ በአዋጊነት፣ በመረጃ ሰጪነት ቁስለኞችን በመንከባከብ ለሰሩት ስራ የተሰየመ ማስታወሻም በአድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀምጦ ይገኛል። የአሁኑ ትውልድ አሻራ፣- የኢትዮጵያ ልጆች በአንድነት ተባብረው አፍሪካ በራሷ አቅም መልማት እንደምትችል ያሳዩበት፣ አፍሪካዊ ተምሳሌት የሆነው የህዳሴ ግድብ ፏፏቴ በመታሰቢያው ይገኛል። ኢትዮጵያውያን ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት ላደረጉት ተጋድሎ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የፓን-አፍሪካ ሃውልትም ተካቷል።   ሌሎችም የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋን ጦርነት ሁነቶች ብቻ ሳይሆን ለተለያያዩ ዝግጅቶች የሚሆኑ አዳራሾችን፣ ካፍቴሪያዎችን፣ ሲኒማ ቤቶችንና ሌሎች ለበርካታ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎችንን አካቶ የተሰራ ነው። ከ2500 በላይ እንግዶችን መያዝ የሚችል ፓን አፍሪካን አዳራሽ፣ 300 ሰዎች የሚይዝ የአድዋ አዳራሽ፣ 160 ሰዎች የሚይዝ መካከለኛ አዳራሽ፣ 300 ሰው በአንድ የሚያስተናግዱ ሬስቶራንቶች፣ ሁለት ካፍቴሪያዎችና የህጻናት ሙዚየም በውስጡ አካቷል። በሌላ በኩል በአንድ ጊዜ 1000 ተሽከርካሪ መያዝ የሚችሉ ፓርኪንግ፣ ዘመናዊ ጂምና ሌሎችም ተካተዋል። የአድዋ ድል መታሰቢያ አድዋ ጊዜ የማይሽረው፣ ዘመን የማይለውጠው የጀግንነትና የአንድነት ምልክት መሆኑን ማሳያ፣ ለነጻነት የታገሉና የተሰዉ ጀግኖች የሚታሰቡበት የታሪክ ማስታወሻ ነው። የአድዋ ድል ትሩፋቶችን ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝብ በየትውልዱ ለማስተማር የሚያግዝ የዘመናት የነጻነት መንፈስን የሚያስተጋባ፣ ለመጪው ትውልድ የሚሻገር እውነት ነው። እናም የአድዋ ድል መታሰቢያ የወል ታሪካችንን የምንገነባበት የማዕዘን ድንጋይ ነው።  
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች
Mar 1, 2024 2211
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች በአየለ ያረጋል "... መጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል..." ይህን ያሉት ታላቁ ምሁር እና የአድዋ ዘማች ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማርያም ናቸው። በርግጥ በአድዋ ዘመቻ ያልዘመተ የለም። የሀይማኖት መሪዎች፣ ንጉሱ፣ ንግስቲቱ፣ ገበሬው፣ አገሬው ከነማንነቱ… ገድል ፈጽሟል። በጦር ሜዳ ገድሎች የሴቶች አበርከቶ እምብዛም አይታወስም። ሴቶች የዋሉበት ግንባር አይዘከርም። ቅሉ ሴቶች በኪነ-አድዋ ያልተዘመረላቸው ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው። እቴጌ ጣይቱን መሰል የአድዋ ሴት የጦር ፊታውራሪዎች አሉ። አዝማሪ ጣዲቄና መሰል አዝማሪዎች የሰራዊቱ ስነ ልቦና ገንቢዎች ናችው። ሴቶች የሎጂስቲክስ አሳላጮች፣ የቁስለኛ ሀኪሞች፣ የጀግና አበርቺዎች፣ የስንቅ ሰናቂዎች፣….በጥቅሉ ሴቶች የአድዋ ድል ሁለንተናዎች ነበሩ። ለዚህ ደግሞ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ቀዳሚ ምስክር ናቸው። እቴጌ ጣይቱ ከውጫሌ እስከ መቀሌ፣ ከእንጦጦ እስከ ማርያም ሸዊቶ መላ መቺም፣ ጦር አዝማችም ነበሩ። የዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዜና መዕዋል ከታቢ ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ ወልደአረጋይ ‘ታሪከ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ’ በተሰኘው መጽሐፋቸው የሴቶችን ሚና በተመለከተ እንዲህ ይላሉ። “እንዲህም እየሆነ፣ አጤ ምኒልክ ባዳራሹ እቴጌ ጣይቱ በእልፍኝ ባለሟሎችን ወይዛዝርቱን ይዘው ግብሩ አንድ ቀን ሳይጎድል፣ ይዘምታሉ። ከዘመቻ ላይ ጠጁ ማሩ አለመጉደሉ፣ ስለምንድነው ያልህ እንደሆነ ይህን ታሪክ መመልከት ነው። በስድስት ድንኳን እንጀራው ሲጋገር ሲያድር፣ በአራት ድንኳን ወጡ ሲሠራ ሲያድር፣ ጠጁ በቀንድ በኮዳ ደግሞ ሦስት መቶ ስድስት መቶ የሚሆን ገንቦኛ ሲጓዝ ግብሩ ይጎድል ይመስልሀል” (ገጽ-241) ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ይቀጥላሉ። “… ጥቂቱን ጻፍን እንጅ በአድዋ ጦርነት ዐይናቸን እንዳየው ጆሯችን እንደሰማው መጻፍ አይቻለንም። እቴጌ በዚያን ጊዜ በግምባርዎ ተደፍተው በጉልበትም ተንበርክከው ድንጋይ ተሸክመው እግዚአብሄር እያመለከቱ ሲያዝኑ ሲጨነቁ ነበር። … ሴት ወይዛዝርቱም የንጉሠ ነገሥቱ ልጅ ወይዘሮ ዘውዲቱም ደንገጡሮችንም ተከትለው ነበር። የኋላው ሰልፈኛ እንደመወዝወዝ ሲል ባዩ ጊዜ ቃልዎን አፈፍ አድርገው ተናገሩ። አይዞህ አንተ ምን ሆነሃል! ድሉ የኛ ነው በለው! አሉት… ጣሊያ ድል ከሆነ በኋላ ወንዱ በርኮር፣ ሴቱ በገንቦ ውሃ ያዙ ብለው አዘው ለተጠማውና ለቆሰለው ውሃ ሲያጠቱት ዋሉ። እንኳን ኢትዮጵያ ሰው የኢጣሊያው ስንኳ ቁስለኛ ከዚያ ስፍራ የተገኘ ከዚህ ከእቴጌ ካዘዙት ውሃ አልቀረበትም“ይላሉ። ከጽሁፉ መረዳት እንደሚቻለው እቴጌ ጣይቱና መሰሎቻቸው አንድም በጸሎታቸው፣ አንድም ተዋጊዎችን በማደፋፈር ወኔያቸው፣ አንድም በጦር መሪነት ሚናቸውን ተወጥተዋል። ዋናው ደግሞ ቁስለኞችን የማከምና ሰብዓዊነት ሙያቸው ነው። ፀሃፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ “… ሙሉ ግብር እየበላ የተጓዘ እንጂ ወታደር የስንቅ አቁማዳዉን አልፈታም“ ሲሉ የአድዋ ሴቶች ገድል ምንኛ ገናና እንደሆነ መገመት እንደሚቻል ይጠቅሳሉ። እንደ ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ስለዘመቻው አጓኳን በማስታወሻቸው እንደገለጡት ድንኳን ተካይ፤ ዕንጨት አቅራቢው፣ ወጥ ሰሪው፣ እንጀራ ጋጋሪው፣ እህል ውሃ ተሸካሚው፣ መልከኛው (አራጁ)፣ በቅሎ ጫኙ፤ ተዋጊው ሁሉም በየፊናው እንስሳቱም ሳይቀር ተደራጅቶ ዘምቷል። በርካታ የታሪክ ምንጮች የአድዋ ጦርነት ተሳታፊዎች ገሚሶቹ ሴቶች እንደሆኑ ይገልጻሉ። የታሪክ ምሁሩ ዶክተር አልማው ክፍሌ ደግሞ በአንድ ወቅት ሚዲያ ላይ ቀርበው “በአድዋ ጦርነት ዘማቾች 75 በመቶ ሴቶች ነበሩ” ብለው ነበር። በአድዋ ጦርነት ሴቶች በተለያዩ ሙያዎች ተመድበው ከካምፕ እስከ ጦር ሜዳ ከመመገብ እስከ ማጀገን፣ ከማከም እስከ መዋጋት ድንቅ ሚና ተወጥተዋል። ድርብ ድርብርብ ኃላፊነት ይዘው የዘመቱ፣ ለወንዶችም ልብ፣ ሞራልና ወኔ አቀባዮች ነበሩ። ደራሲ በዕውቀቱ ሥዩም ‘ከአሜን ባሻገር’ በተሰኘ መጽሐፉ ‘ሴቶች በዋሉበት’ በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሴቶች ተጋድሎና ሚና “ከቁስ ባሻገር ከልብ ያቀርባሉ” ይላቸዋል። “ሴቶች ባዋላጅነት ከነበራቸው የማይተናነስ ሚና በጦር ሜዳ ተጫውተዋል። እናቶቻችን በጦር ወቅት፣ መሳሪያ ያቀርቡ ነበር። ምግብ ያቀርቡ ነበር። ሃሳብ ያቀርቡ ነበር። ልብ ያቀርቡ ነበር። ደስታ ያቀርቡ ነበር። ኧረ ምኑ ቅጡ። ሴቶች ባንድ በሙቀጫ ዙሪያ፣ ማኅበረሰቡን ኬሚስት፣ ገጣሚና የፖለቲካ ተንታኝ ሆነው ማገልገላቸውን ልብ እንበል” ይላል። (ገጽ-138) የራስ መኮንን ባለሟል የነበሩት ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማሪያም ገና በ15 ዓመት ዕድሜያቸው አድዋ ዘማች ነበሩ። "የሕይወቴ ታሪክ’ (ኦውቶባዮግራፊ) በተሰኘው ግለ ታሪካቸው ከሐረር እስከ አድዋ በዘለቀው ጉዟቸው ሴቷ (አገልጋያቸው) የነበራትን ሚና ለማብራራት ቃላት ያጥርባቸውና እንዲህ ብለው የአንባቢን ህሊና ይነካሉ። “… ከቶ እሷ ባትኖር ኖሮ እንዴት እሆን ኖሯል! እያልኩ ዘወትር ሳስበው ያደንቀኛል። ዕቃ ተሸክማ ስትሄድ ትውላለች። ከሰፈርን በኋል ውሃ ቀድታ፣ እንጨት ለቅማ፣ ቂጣ ጋግራ፣ ወጥ ሰርታ፣ ታበላናለች። ወዲያውኑ እንዲዚህ ለማታ ታሰናዳለች። እንደዚህ የወለተ አማኑኤልን አገልግሎት እያሰብኩ ስደነቅ ደግሞ በየሰፈሩ እንደርሷ ስንት ሴቶች እንደሚያገለግሉ ይታሰበኛል። የሴቶቹን አገልግሎት ስገምት ደግሞ የበቅሎዎች አገልግሎት ይታወሰኛል። በመጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል። ሁሉንም አያይዥ በደምሳሳው ስመለከተው የኢትዮጵያን መንግስት ነጻነቱን ጠብቀው፤ እዚህ አሁን የደረስንበት ኑሮ ያደረሱት እነዚህ የዘመቻ ሃይሎች መሆናቸውን አልስተውም። የኢትዮጰያ መንግስት የተባለው ተቋም፣ ላገልጋዮቹ ውለታ ምላሽ ሆኗል ወይ? የዚህን ምላሽ ለመስጠት ሳስበው እልቅ የሌለው መንገድ ይገጥመኛል። ሲሄዱ መኖር ይሆንብኛል። የማልዘልቀው እየሆነብኝ፣ እየተከዝኩ እተወዋለሁ” በማለት በቁጭት ጽፈዋል። በርግጥም ሴቶች በኪነ-አድዋ በልካቸው ያልተዘመረላቸው፣ ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው።  
በአጭር ጊዜ ትልቅ እመርታ በሌማት ትሩፋት
Feb 6, 2024 3062
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል የምግብ ዋስትናን ለማረጋጥ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን የተመለከቱ ጥያቄዎች ይጠቀሳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ በግብርና ልማት በተለይም በስንዴ ላይ እየተሰራ ያለው ስራ በምግብ እራስን ለመቻል ለሚደረገው ጥረት ውጤታማነት ትልቅ ድርሻ እንዳለው አብራርተዋል። በግብርና ልማት እየተከናወኑ ባሉ ውጤታማ ስራዎች ላይ የሌማት ትሩፋት ተግባራት ሲታከሉ ከምግብ ዋስትና ባለፈ ስርአተ ምግብን በማስተካከል ረገድ አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል። ለመሆኑ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ስርአተ ምግብን ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሚኖረው ፋይዳ እንዴት ይታያል? በእስካሁኑ አካሄድስ ምን ውጤቶች ተገኙ? ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማ ‘የሌማት ትሩፋት’ መርሃ ግብርን ካስጀመሩ በኋላ በመህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ሌማት አርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደሩን እና ሸማቹን የሚያገናኝ ድልድይ መሆኑን ገልጸው ነበር። በወቅቱ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በቂ እና አመርቂ ምግብ ማግኘት መሆኑን ገልጸው በቂ የመጠን፣ አመርቂ የይዘት ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል። አክለውም በምግብ ራስን መቻል ከሀገር ሉዓላዊነትና ክብር ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንዳለው ገልጸዋል። የሌማት ትሩፋት መርኃ-ግብር ዓላማ የምግብ ሉዓላዊነት ማረጋገጥና ክብርን ማስጠበቅ ሲሆን በተለይም ስጋ፣ እንቁላል፣ ማር እና ወተት ትርፍ ምርት ሆነው እንዲገኙ ማልማትና መጠቀምን መሰረት ያደረገ ነው። መርኃ-ግብሩ የኢትዮጵያን ደካማ የአምራችነት ታሪክ በመቀየር የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና የኢኮኖሚ እድገትን የማፋጠን ግብ የሰነቀ መሆኑ ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሌማት ትሩፋት ዘመቻው በቤተሰብ፣ ብሎም በሀገር ደረጃ በምግብ ራሳችንን ለመቻል የምናደርገውን ጥረት የሚያፋጥን ነው ብለዋል። የወተት፣ የዶሮ፣ የዕንቁላል፣ የማር፣ የዓሣ እና የሥጋ ምርቶችን ለማሻሻል ሀገራዊ የመንግሥት ፕሮግራም ሆኖ ከጥቅምት 2015 ዓ.ም ጀምሮ እየተተገበረ የሚገኘው የሌማት ትሩፋት በብዙ መልኩ ውጤት እያስገኘ ነው። በእርግጥም የሌማት ትሩፋት በአንድ ዓመት ጉዞው በተለይ በወተት፣ በእንቁላል፣ በዶሮና ስጋ ምርት መጠን አርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደሩን እና ሸማቹን የሚያገናኝ ድልድይ መሆኑ የተረጋገጠበት ውጤት ተመዝግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በ2015 ዓ.ም፣ የወተት፣ የዶሮ እና የሥጋ ምርት መጠን በዕቅዱ መሠረት ጥሩ ውጤት ማምጣቱንና በተያዘው ዓመትም በበለጠ ለማሳካት የሁሉም ጥረት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና አሣ ሃብት ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ጽጌረዳ ፍቃዱ በሌማት ትሩፋት መርኃ-ግብር በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች በማር፣ በወተትና በዶሮ ልማት ከ20 ሺህ በላይ መንደሮችን በመለየት ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ለኢዜአ ገልጸዋል። ለአብነትም በወተት ልማት በተሰሩ ስራዎች 6 ነጥብ 9 ቢሊዮን ሊትር የነበረውን የማምረት አቅም ወደ 8 ነጥብ 6 በሊዮን ሊትር ከፍ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። በመጪዎቹ ዓመታትም ወደ 11 ነጥብ 7 ቢሊዮን ሊትር ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። በእንቁላል ምርት ውጤታማ ስራ መሰራቱን ጠቅሰው የጫጩቶች ስርጭት ከነበረበት 26 ሚሊዮን ወደ 42 ሚሊዮን ማደጉን ተናግረዋል። የሌማት ትሩፋት መርኃ- ግብር የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑን የሚናገሩት የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና አሣ ሃብት ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ጽጌረዳ ፍቃዱ በእንስሳት ሃብት ልማት ብቻ በዓመት ለ259 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩን ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም ለዘርፉ ትኩረት ባለመሰጠቱ ምክንያት አመርቂ ውጤት ሳያገኝ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፤ ዘርፉ በቅንጅት ከተመራ፣ በቴክኖሎጂ ከታገዘ የምግብ አማራጭን ማብዛት ይቻላል። ወተት፣ ማር፣ ስጋ እና እንቁላል መሰል የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን በገበያ ላይ ማትረፍረፍ፣ የሌማቱ በረከት ማብዛት የሚለው የብዙሃኑ እምነት ነው። የምግብ ዋስትና ጉዳይ ከተመጣጠነ ምግብ ጋር ያለው ቁርኝት የማይነጣጠል በመሆኑ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ፋይዳው ብዙ ነው። በሌማት ትሩፋት ገበታን በተመጣጠነ ምግብ መሙላት ከተቻለ የእናቶችንና የህጻናትን ፍላጎት በማሟላት በአካል የዳበረና በአዕምሮ የበለጸገ ትውልድ መገንባት ይቻላል። በተቃራኒው ያልተመጣጠነ አመጋገብ ጤና ላይ ከሚፈጥረው ችግር ባለፈ በሰዎች መካከል ያለውን የኑሮ አለመመጣጠን በማስፋት፣ ማህበራዊ ቀውስን በመፈልፈልና ኢኮኖሚውን በመጉዳት ምርትና ምርታማነትን ወደ ኋላ የሚጎትት ይሆናል። ይህ ደግሞ እንደ ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣት በከባድ ትግል ላይ የሚገኙ ሀገራትን የልማት ግስጋሴ በመግታት ቀድሞ ወደነበሩበት የድህነት አረንቋ እንዲመለሱ ያደርጋቸዋል። በኢትዮጵያ ከሚገኙና እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ከሆኑ ህፃናት ከ30 በመቶ በላይ የሚሆኑት በዕድሜያቸው ልክ ዕድገት የማያስመዘግቡ ወይም የመቀንጨር ችግር ያለባቸው መሆናቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ። ለዚህ ነው በምግብ ራስን ከመቻል ጎን ለጎን የተመጣጠነ ምግብን ተደራሽ ማድረግ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ የሚሆነው። በዚህ ረገድ የሌማት ትሩፋት እየተጫወተ ያለው ሚና ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም። የተለያዩ ምግቦችን በገበታ ላይ ማካተት የሚያስችል ስልጠናን ከተግባራዊ የልማት ስራዎች ጋር ያካተተ ሲሆን አዲስ የአመጋገብ ባህልን የሚያለማምድ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ ለተሰሩ ስራዎችና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ላሳዩት የአመራር ቁርጠኝነት በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ ተሸልመዋል። ሽልማቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምግብ ዋስትና እና በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ላሳዩት ርዕይ፣ አመራር እና ቁርጠኝነት፣ ብሎም ፈጣን፣ ተለዋዋጭ እና ፈታኝ በሆነው ከባቢያዊ ሁኔታ በስንዴ ምርት ራስን ለመቻል በተከተሉት ፈጠራዊ መፍትሔ ዕውቅና ለመስጠት የተበረከተ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመርሃ-ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ረሀብን ዜሮ ለማድረስ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ብቻ ሳይሆን የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ሀገራዊ ብልጽግናን እውን እንደምታደርግ ገልጸዋል። ባለፉት አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ የተሰሩት ስራዎች ለመጪው ትውልድ ጥሩ መሰረት የሚጥሉ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያን ለአብነት አንስተዋል። የምግብ ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ጉዟችንን በፅናት እናስቀጥላለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግብርና ስራችን የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ የተመጣጠነ ምግብን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል። የሌማት ትሩፋት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር የኢኮኖሚ ሉዓላዊነቷን ያስከበረች ነጻ አገር እውን ማድረግን ያለመ መሆኑን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አመራሩ ይህንን ተገንዝቦ እንዲሰራ አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ ህልም የሚመስሉ በርካታ አገራዊ ፕሮጀክቶችን እውን ማድረግ የቻለችው በዜጎቿ የተባበረ ክንድ መሆኑ እሙን ነው። ከዚህ አኳያ በምግብ ራስን ከመቻል በላይ የኢትዮጵያን የአምራችነት ታሪክ የመቀየር ግብ ለሰነቀው የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር ስኬታማነት ከመቼውም ጊዜ በላይ በትብብር መስራት ይጠበቃል።  
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 11434
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 15846
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 8123
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል።   “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል።   ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 9130
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 25153
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 21307
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 15846
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 12049
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 11434
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 10940
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 10698
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
ተመድ በሶሪያ በርዕደ መሬት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረበ
Feb 15, 2023 10271
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 8/2015 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በሶሪያና ቱርክ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ ሶሪያውያንን ለማገዝ የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረቡ። ዋና ጸሓፊው ጥሪውን ያቀረቡት ባሳለፍነው ሳምንት በቱርክና በሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሶሪያውያንን ለማገዝ ነው። በኒውዮርክ በሰጡት መግለጫ ሶሪያውያኑን ለማገዝ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ለሶስት ወራት ጊዜ ብቻ የሚበቃ መሆኑን ጠቅሰው የሚመለከታቸው ሁሉ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። ከአደጋው በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አስቸኳይ ድጋፍ ማቅረቡን ገልጸው ተጨማሪ እገዛዎች አሁንም እንደሚያስፈልጉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በድርጅቱ ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትና አጋር አካላት በጋራ በሚያቀርቡት ገንዘብ፤ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሶሪያውያን የመጠለያ፣ የጤና፣ የምግብ እንዲሁም ሌሎች አስቸኳይ ድጋፎች እንደሚደረጉ አብራርተዋል። ተመሳሳይ የድጋፍ ማዕቀፍ በቱርክ ድንበር ለሚገኙ ዜጎች እየተጠናቀቀ እንደሚገኝም ዋና ጸሓፊው ተናግረዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 25153
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 21307
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 15846
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 12049
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
መጣጥፍ
በድላችን ሐውልት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት የተቀረጸላቸው የካራማራው ዘማች አቶ በቀለ ገመቹ 
Mar 5, 2024 3407
አቶ በቀለ ገመቹ ወይም በቅፅል ስማቸው አሚኮ ይባላሉ፤ በሙያቸው ኤሌክትሪሺያን ናቸው። በ1969 ዓ.ም በዚያድባሬ የሚመራው የሶማሊያ አገዛዝ ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ሀገር ስትደፈር ቁጭት ተሰምቷቸው ወደ ጦር ሜዳ መዝመታቸውን ይናገራሉ። ጦር ሜዳ ከመዝመታቸው ባሻገር የኤሌክትሪክ ባለሙያ በመሆናቸው "በራ በራ የድል ጮራ" የተሰኘውን ዓርማ በመቅረጽ በ14ቱ ክፍላተ ሀገር እንዲበራ ማድረጋቸውንም ያነሳሉ። በዚህም ከወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እና ከኩባው ፕሬዝዳንት ፊደል ካስትሮ መሸለማችውን ያወሳሉ። ታንክ ማራኪው አሊ በርኬ ጓደኛቸው እንደሆኑ የሚናገሩት አቶ በቀለ፤ በተለያዩ ዐውደ ግንባሮች መሳተፋቸውን አስታውሰዋል። አቶ በቀለ ጥቁር አንበሳ በሚገኘው የኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ፓርክ በሚገኘው የድላችን ሐውልት ላይ ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት ተቀርጾላቸዋል። ሐውልት እንዲቀረጽ የተደረገበት ፎቶግራፍ በያኔው ሶስተኛው አንበሳው ክፍለ ጦር በኋለኛው ምሰራቅ ዕዝ በር ላይ በቀኝ እጃቸው መሳሪያ ከፍ አድርገው ይዘው የተነሱት ፎቶ ግራፍ እንደሆነ ገልጸው፤ በዚህም ደስተኛ እንደሆኑ ይናገራሉ። ከእርሳቸው ጎንም መንበረ የምትባል ሌላ ኢትዮጵያዊ ዘማችና መትረጊስ ተኳሽ ሴት ባደረገችው አስተዋፅኦና በደረሰባት አካል ጉዳት ሐውልት እንደተቀረጸላት ያነሳሉ። የካራማራ ድል ታላቅ ድል ነው የሚሉት አቶ በቀለ ገመቹ፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት ከፍለውበት የተገኘና ሀገርን ያስከበረ መሆኑንም ይገልጻሉ። የካራማራ ዘማቹ አቶ በቀለ ገመቹ አሁናዊ ኑሯቸው ችግር ላይ እንደሚገኙና ድጋፍ እንደሚሹም ተናግረዋል። ሶማሊያን ለ21 ዓመታት ያስተዳደሩት ዚያድባሬ 'ታላቋን የሶማሊያ ሪፐብሊክ ለመመስረት' በሚል "ድንበራችን እስከ አዋሽ ይደርሳል" እያሉ በመዛት የጦርነት ነጋሪት መጎሰማቸው የሚታወስ ነው። ይሄን እውን ለማድረግ በ1969 በኢትዮጵያ ላይ ግልጽ ወረራ ፈጸሙ። የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጦር የእብሪተኛውን የዚያድባሬ ጦር ካራ ማራ ላይ ድል አደረገ፤ የኢትዮጵያ አሸናፊነትም በአደባባይ ታወጀ። ድሉ በየዓመቱ የካቲት 26 ቀን የሚታሰብ ሲሆን ዘንድሮም 46ኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል።    
የአፍሪካ ዋንጫን በመሀል ዳኝነት  የመራችው ብቸኛዋ ሴት ዳኛ
Jan 28, 2024 3261
  በይስሐቅ ቀለመወርቅ እንደ መነሻ፡- በእግር ኳስ ውድድሮች የመሃል ዳኝነቱን ቦታ በብዛት የሚይዙት ወንዶች ሲሆኑ፤ አሁን ላይ አልፎ አልፎ ሴቶች ትልልቅ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ሲዳኙ አስተውለናል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 በኳታር አስተናጋጅነት በተከናወነው 22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ፤ ፈረንሳዊቷ ስቴፋኒ ፍራፓርት፤ ኮስታሪካ እና ጀርመን ያደረጉትን ጨዋታ በመሀል ዳኛነት መርታለች። በዚህም በወንዶች ዓለም ዋንጫ ታሪክ በመሀል ዳኝነት የእግር ኳስ ጨዋታን የመራች የመጀመሪያዋ ሴት በመሆን ታሪክ ሰርታለች ። ዘንድሮ ደግሞ በኮትዲቯር አስተናጋጅነት እየተከናወነ በሚገኘው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ሞሮኳዊቷ ቦችራ ካርቡቢ፤ ውድድሩን እንዲመሩ ከተመረጡት 32 የመሀል ዳኞች መካከል ብቸኛዋ ሴት ናት። በዚህም በውድድሩ በጊኒ ቢሳውና በናይጄሪያ መካከል የተከናወነውን ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ፤ በመሀል ዳኝት በመምራት፤ ታሪክ ጽፋለች። የሞሮኮ ዓለም አቀፍ ማኅበር የእግር ኳስ ዳኛ የሆነችው ቦችራ ካርቡቢ፤ በወንዶችም ሆነ በሴቶች አህጉራዊ የእግር ኳስ ውድድሮች ላይ በርካታ የመጨረሻ ምዕራፍ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ዳኝታለች። 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫን ብቸኛ የሴት ዳኛ ሆና የመራችው ቦችራ ካርቡቢ ማናት? ቦችራ ካርቡቢ በሞሮኮ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው "ታዛ" ከተማ፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1987 ተወለደች። የዘር ግንዷ በሰሜን ምሥራቅ ሞሮኮ ከሚገኙት ሪፊያን ከሚባሉት የበርበር ጎሳ ዝርያ ካላቸው ሕዝቦች የሚመዘዝ ሲሆን፤ ለቤተሰቦቿ አምስተኛና የመጨረሻ ልጅ ነች። ገና በልጅነቷ ለእግር ኳስ ፍቅር ያደረባት ቦችራ ካርቡቢ፤ ኳስ መጫወት የጀመረችው በአንድ ትንሽ የወጣቶች ቡድን ውስጥ ነበር። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2001 በተወለደችበት ከተማ "ታዛ"፤ ለወንዶችና ለሴቶች የእግር ኳስ ዳኝነት ሥልጠና የሚሰጥበት ትምህርት ቤት ተከፈተ ። ይኼ ትምህርት ቤት ቀልቧን የሳበው ቦችራ፤ ሥልጠናውን መውሰድ ጀመረች። "እግር ኳስን እወዳለሁ፤ ራሴንም ላስተምር ፈለኩ።ለምን አላደርገውም ብዬ ፍላጎቴን በመከተል የእግር ኳስ ጨዋታን ደንብ መማር ጀመርኩ" ስትል የእግር ኳስ ዳኝነት ትምህርት የጀመረችበትን ጊዜ ታስታውሳለች። ይኼ ድርጊቷ ካልተዋጠላቸውና፤ በበጎ ጎኑ ካልተመለከቱት ውስጥ ደግሞ፤ ወንድሞቿ ቀዳሚዎች ነበሩ። "በምኖርበት ከተማ አንድ ሴት አጭር ቁምጣ ለብሳ ከወንዶች ጋር ሥልጠና ስትወስድ መታየቷ፤ እንደ አሳፋሪ ድርጊት ስለሚታይ መነጋገሪያ ሆኜ ነበር" ትላለች። የቦችራ ካርቡቢ የዳኝነት ጉዞ እንደ አውሮፓውያን ቆጣጠር በ2007፤ ሞሮኮ ብሔራዊ የሴቶች እግር ኳስ ሻምፒዮናን ጀመረች። ይህ መሆኑ ቡችራ ካርቡቢ ብሔራዊ ዳኛ እንድትሆን ዕድል የፈጠረላት ሲሆን፤ መኖሪያዋንም ከትውልድ ሥፍራዋ "ታዛ" ወደ ሞሮኮ ሌላኛዋ ከተማ "ሚከንስ" እንድትቀይር አደረጋት። "ይህን ዕድል ማግኘቴ ቤተሰቦቼ እንዲረዱኝና ሙያዊ ለሆነ ጉዳይ እንደምሄድ እንዲያምኑ አድርጓቸዋል" በማለት የዳኝነት ሙያዋን በመጨረሻ እንደተቀበሉት ታስረዳለች። በሚከንስ ከተማ በእግር ኳስ ዳኝነት ሥልጠና ላይ እያለች፤ አንድ ቀን አባቷ መጥቶ እንደተመለከታትና፤ ወንድሞቿ ምርጫዋን ሊያከብሩላት እንደሚገባ እንደነገራቸውም ገልፃለች። የ19 ዓመት ወጣት እያለችም፤ በሞሮኮ የሴቶች አንደኛ እና ሁለተኛ የሊግ ውድድር በመዳኘት፤ የዳኝነት ሥራዋን አንድ ብላ ጀመረች። ይህ ከሆነ ከ10 ዓመት በኋላ፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2016 ደግሞ፤ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ዳኛ በመሆን ራሷን ወደ ሌላ ምዕራፍ አሸጋገረች። ከሁለት ዓመት በኋላም በ2018 በጋና አስተናጋጅነት በተከናወነው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ፤ በዛምቢያና በኢኳቶሪያል ጊኒ መካከል የተደረገውን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት አጫወተች። ይህም በአህጉራዊ የውድድር መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመሀል ዳኝነት ያጫወተችው ጨዋታ ሆኖ ተመዘገበላት። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2020፤ "ቦቶላ" እየተባለ በሚጠራው በሞሮኮ የወንዶች ከፍተኛ የሊግ ውድድር ላይ በመሀል ዳኝነት በመዳኘት፤ የመጀመሪያዋ ሴት ሆነች ። ከአንድ ዓመት በኋላም በካሜሮን አስተናጋጅነት በተከናወነው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ፤ ሴኔጋልና ግብፅ ባደረጉት የፍፃሜ ጨዋታ የቫር ዳኛ (video assistant referee) በመሆን ሰርታለች። ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊትም የሞሮኮ የንጉሱ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታን በመዳኘትም ቀዳሚዋ ሴት ናት። አሁን ላይ እየተከናወነ ባለው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ወድድርም፤ በጊኒ ቢሳውና በናይጄሪያ መካከል የተከናወነውን ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ በመሀል ዳኝት በመምራት፤ የመጀመሪያዋ ሰሜን አፍሪካዊት የአረብ ሴት ሆናለች። ቡችራ ካርቡቢ ከእግር ኳስ ዳኝነት ሥራዋ በተጨማሪ፤ የፖሊስ ኦፊሰር በመሆን ሀገሯን እያገለገለች ትገኛለች።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም