ቀጥታ፡

በሻምፒዮንስ ሊጉ ባየር ሙኒክ ከዩኒየን ሴይንት-ጂሎይስ ጋር ይጫወታል

አዲስ አበባ፤ ጥር 13/2018 (ኢዜአ) በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዛሬ ዘጠኝ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

በአሊያንዝ አሬና ስታዲየም ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ባየር ሙኒክ ከዩኒየን ሴይንት-ጂሎይስ ጋር ይጫወታል።

የስድስት ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ባየር ሙኒክ 15 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

በሻምፒዮንስ ሊጉ ኢንተር ሚላን ከአርሰናል የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው

አርሰናል በሻምፒዮንስ ሊጉ ጥሎ ማለፍ የገባ የመጀመሪያ ቡድን ሆኗል

በውድድሩ ላይ የመጀመሪያ ተሳትፎውን እያደረገ የሚገኘው ዩኒየን ሴይንት-ጂሎይስ በስድስት ነጥብ 30 ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ሁለቱ ክለቦች በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሲገናኙ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

ባየር ሙኒክ ጨዋታውን የማሸነፍ ሰፊ ግምት ያገኘ ሲሆን፤ ሶስት ነጥብ ማግኘት ወደ ጥሎ ማለፍ የመግባት እድሉን ያሰፋዋል።


 

በሌሎች መርሐ-ግብሮች ማርሴይ ከሊቨርፑል፣ ቼልሲ ከፓፎስ፣ ስላቪያ ፕራግ ከባርሴሎና፣ ጁቬንቱስ ከቤኔፊካ፣ ኒውካስትል ዩናይትድ ከፒኤስቪ አይንድሆቨን እና አትላንታ ከአትሌቲኮ ቢልባኦ በተመሳሳይ ምሽት አምስት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በሻምፒዮንስ ሊጉ ማንችስተር ሲቲ በቦዶ ግሊምት ያልተጠበቀ ሽንፈት አስተናገደ

ጋላታሳራይ ከአትሌቲኮ ማድሪድ እና ካራባግ ከኢንትራክት ፍራንክፈርት በተመሳሳይ ምሽት 2 ሰዓት 45 ላይ ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም