ቀጥታ፡

በሻምፒዮንስ ሊጉ ማንችስተር ሲቲ በቦዶ ግሊምት ያልተጠበቀ ሽንፈት አስተናገደ

አዲስ አበባ፤ ጥር 12/2018 (ኢዜአ)፦‎ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መርሐ ግብር የኖርዌዩ ቦዶ ግሊምት ማንችስተር ሲቲን 3 ለ 1 አሸንፏል።

ማምሻውን በአስፕማይራ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ካስፐር ዋርትስ ሆግ ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር ጄንስ ፒተር ሃውግ ቀሪዋን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ራያን ቸርኪ ለሲቲ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል።


 

የማንችስተር ሲቲው አማካይ ሮድሪ በ62ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።

በጨዋታው ማንችስተር ሲቲ ከፍተኛ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ቢወስድም ቦዶ ግሊምት ግልጽ የግብ እድሎችን በመፍጠር የተሻለ ነበር።

በውድድሩ ሁለተኛ ድሉን ያስመዘገበው ቦዶ ግሊምት በስድስት ነጥብ ደረጃውን ከ32ኛ ወደ 26ኛ ከፍ አድርጓል።

በአንጻሩ በሻምፒዮንስ ሊጉ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ማንችስተር ሲቲ በ13 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል።

ሲቲ በሁሉም ውድድሮች ባለፉት አምስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

በተያያዘም ማምሻውን በተደረገ ሌላኛው መርሐ-ግብር ክለብ ብሩዥን ካይራት አልማቲን 4 ለ 1 ረቷል።

ምሽት አምስት ላይ በሳን ሲሮ ስታዲየም ኢንተር ሚላን ከአርሰናል የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም