የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ገዥ ትርክትን በመገንባት ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን የሚያጎለብት ነው - ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ - ኢዜአ አማርኛ
የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ገዥ ትርክትን በመገንባት ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን የሚያጎለብት ነው - ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 5/2017(ኢዜአ)፦ የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ገዥ ትርክትን በመገንባት ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን የሚያጎለብት መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ።
19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን "ሀገራዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ ህዳር 29/2017 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ ከተማ ይከበራል።
በሲዳማ ክልል19ኛው የብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ባህላዊ እሴቶችን በሚያጠናክር አግባብ ይከበራል
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው
በድሬደዋ ከተማ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ
ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች የበዓሉን ዝግጅት ለመመልከት ትላንት ማምሻውን አርባ ምንጭ ከተማ ገብተዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የበዓሉን የዝግጅት ስራዎች በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።
በዚህም ኮሚቴዎች ተዋቅረው ወደ ስራ መግባታቸውን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በዓሉ በሁሉም መልኩ በልዩ ድምቀት እንዲከበር ሰፊ ዝግጅት መደረጉን ጠቁመዋል።
በዓሉ ኢትዮጵያ ስብራቶችን በመጠገን ታሪካዊ እጥፋት ላይ ባለችበት ወቅት የሚከበር መሆኑ የተለየ ያደርገዋል ነው ያሉት።
በዓሉ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦችን አብሮነትና ሀገራዊ አንድነትን ይበልጥ የሚያጎለብት፣ የኢትዮጵያውያን መቀራረብ እና መተሳሰብ የሚገለጽበት መሆኑን ተናግረዋል።
ዘላቂ ሰላምን ከመገንባት እና እውነተኛ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ከማስፋት አኳያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም አመላክተዋል።
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን መከበር የፌዴራል ስርዓቱን በፅኑ መሰረት ላይ ለመገንባት ሚናው የጎላ ነው
በዓሉ ገዥ ትርክትን በመገንባት ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን የሚያጎለብት እና የሚያሰርጽ፣ ማህበራዊ ትስስርን የሚያጎላ እና ነባር እሴቶችን የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል።
የበዓሉን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፋይዳ በመገንዘብ ልዩ ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።
የክልሉ ህዝብም የበዓሉን ታዳሚዎች በድምቀት ለመቀበል ከወዲሁ በርካታ ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
በዓሉ ክልሉ ያለውን እምቅ አቅም በማስተዋወቅ ረገድ ጉልህ ሚና እንዳለው ገልጸው፥ አልሚዎች በክልሉ ባሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።