ቀጥታ፡

የድሬ የኮሪደር ልማት የተሻሻለ የአካባቢ ውበት እውን እንዲሆን አስችሏል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2018 (ኢዜአ)፡- የድሬ የኮሪደር ልማት ምቹ የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች እና የተሻሻለ የአካባቢ ውበት እውን እንዲሆኑ ማስቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተቀላጠፈ የዲጅታል አገልግሎትን ይበልጥ ለማስፋት አቅዶ እየሠራ ነው

‎በድሬዳዋ አዲስ የፍተሻ ላቦራቶሪ በማደራጀት አገልግሎቱ ተደራሽ ተደርጓል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በድሬዳዋ ከተማ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።


 

ከጉብኝታቸው በኋላም በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የድሬ የኮሪደር ልማት ምቹ የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች እና የተሻሻለ የአካባቢ ውበት በድሬ እውን እንዲሆኑ አስችሏል ብለዋል። 


 

በተጨማሪም ጥራታቸውን የጠበቁ የማኅበረሰብ መሰብሰቢያ ስፍራዎች እውን እንዲሆኑ ማስቻሉን ጠቅሰዋል።

በኮሪደሩ ለከተማዋ ነዋሪዎች ገቢ ለማስገኘት የሚያስችሉ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጂንግ ስቴሽንን ጨምሮ ሱቆች መካተታቸውንውንም አመላክተዋል።


 

እንዲሁም ካፍቴሪያዎች እና ደረጃቸውን የጠበቁ የፓርኪንግ ቦታዎች በኮሪደር ልማቱ እንዲካተቱ መደረጉንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የገለጹት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም