ቀጥታ፡

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2018 (ኢዜአ)፦‎ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሐ-ግብር ዛሬ በዎልቭስ እና አስቶንቪላ መካከል ይካሄዳል። 


 

ጨዋታው ምሽት አምስት ሰዓት ላይ በሞልኒው ስታዲየም ይደረጋል። 

ዎልቭስ በ10 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃ ይዟል። አስቶንቪላ በ51 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። 

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲዳማ ቡና ይጫወታል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት የሶስተኛ ቀን ውሎ

ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ ሲገናኙ የአሁኑ ለ22ኛ ጊዜ ነው።

ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 21 ጨዋታዎች ዎልቭስ ሰባት ጊዜ ሲያሸንፍ አስቶንቪላ በስምንቱ አሸንፏል። በስድስቱ ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።


 

በጨዋታዎቹ ላይ ዎልቭስ 33 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ፣ አስቶንቪላ 41 ጎሎችን አስቆጥሯል።

ክለቦቹ ዘንድሮ በሊጉ የመጀመሪያ ዙር ባደረጉት ጨዋታ አስቶንቪላ 1 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

ዎልቭስ በሊጉ ሁለተኛ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታል። አስቶንቪላ ካሸነፈ በሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ፉክክሩ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ያገኛል።

የ46 ዓመቱ ክሬግ ፖውሰን ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት እስከ የካቲት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም