የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት የሶስተኛ ቀን ውሎ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት የሶስተኛ ቀን ውሎ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2018 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ኢትዮጵያ ቡና ደረጃውን ያሻሻለበትን ድል አስመዘገበ
ምሽት 12 ሰዓት ላይ ፋሲል ከነማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ፋሲል ከነማ በሊጉ 20 ጨዋታዎች አድርጎ ስምንት ጊዜ ድል ሲቀናው በሶስቱ ተሸንፏል። በዘጠኝ ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል። 15 ግቦችን ከመረብ ጋር ሲያገናኝ 11 ጎሎች ተቆጥረውበታል።
ቡድኑ በ33 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል።
በውድድር ዓመቱ ካከናወናቸው 20 ጨዋታዎች መካከል ሶስቱን ብቻ ያሸነፈው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በስምንቱ ሽንፈት አስተናግዷል። በቀሪ ዘጠኝ ጨዋታዎች ነጥብ ጥሏል።
በ20 ጨዋታዎች 13 ግቦችን ሲያስቆጥር 22 ጎሎችን አስተናግዷል። ወልዋሎ በ18 ነጥብ 19ኛ ደረጃን በመያዝ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
ሁለቱም ቡድኖች በተመሳሳይ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች አላሸነፉም። ቡድኖቹ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታሉ።
ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር በሁለተኛ ሳምንት ተገናኝተው ፋሲል ከነማ 2 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።
በሌላኛው መርሐ-ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሀዲያ ሆሳዕና ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ28 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሀዲያ ሆሳዕና በ24 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዟል።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ባለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም። በ20ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሀዲያ ሆሳዕና በባህርዳር ከተማ 1 ለ 0 ተሸንፏል።
ሁለቱም ቡድኖች ወደ አሸናፊነት መንገድ ለመመለስ ይጫወታሉ።
ምድረ ገነት ሽሬ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ምድረ ገነት ሽሬ በ23 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዟል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ24 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ባለፉት አራት ጨዋታዎች ከድል የራቀው ምድረ ገነት ሽሬ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ተከታታይ ድሉን ያስመዘግባል።
ምሽት 12 ሰዓት ላይ ባህርዳር ከተማ ከአርባምንጭ ከተማ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ባህርዳር ከተማ በ27 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል። አርባምንጭ ከተማ በ13 ነጥብ 20ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ባህር ዳር ከተማ በሊጉ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታል።
አርባምንጭ ከተማ በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ድሉን ለማስመዝገብ ይፋለማል።