በሰሜን ለንደን ደርቢ አርሰናል ቶተንሃም ሆትስፐርስን በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናከረ - ኢዜአ አማርኛ
በሰሜን ለንደን ደርቢ አርሰናል ቶተንሃም ሆትስፐርስን በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናከረ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሐ-ግብር አርሰናል ቶተንሃም ሆትስፐርስን 4 ለ 1 ረትቷል።
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መሪው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ነጥብ ጣለ
የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር አቻ ተለያየ
ማምሻውን በቶተንሃም ሆትስፐርስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኤበረቺ ኢዜ እና ቪክቶር ዩኮሬሽ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን አስቆጥረዋል።
ራንዳል ኮሎ ሙዋኒ ለስፐርስ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በጨዋታው አርሰናል በተጋጣሚው ላይ ብልጫ ወስዶ ተጫውቷል።
ቶተንሃም ሆትስፐርስ በሁለተኛው አጋማሽ ግብ ለማስቆጠር ያደረጋቸው ጥረቶች አልተሳኩም።
ከሁለት ተከታታይ የአቻ ውጤቶች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው አርሰናል ነጥቡን ወደ 61 ከፍ በማድረግ መሪነቱን አጠናክሯል። በሊጉ 18ኛ ድሉን አስመዝግቧል።
ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 12ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ29 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል።
የፈረንጆች 2026 ከገባ በኋላ ምንም ድል ያላስመዘገበው ስፐርስ ባለፉት ዘጠኝ የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።
በጨዋታው ላይ ሁለት ግቦችን ያስቆጠረው ኤበረቺ ኢዜ ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ ሀትሪክ መስራቱ የሚታወስ ነው።
ዛሬ በተደረጉ በሌሎች ጨዋታዎች ሊቨርፑል ኖቲንግሃም ፎረስትን፣ ክሪስታል ፓላስ ዎልቭስን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል።
ፉልሃም ሰንደርላንድን 3 ለ 1 ረቷል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ነገ ኤቨርተን እና ማንችስተር ዩናይትድ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጠናቀቃል።