የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር አቻ ተለያየ - ኢዜአ አማርኛ
የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር አቻ ተለያየ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ጨዋታው ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂዷል።
ውጤቱን ተከትሎ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ነጥቡን ወደ 36 ከፍ አድርጓል። ቡድኑ ባለፉት አራት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ18 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
በሌላኛው መርሐ-ግብር ሃዋሳ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ሽመልስ በቀለ ለሃዋሳ ከተማ፣ ድልአዲስ ገብሬ ለድሬዳዋ ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ሃዋሳ ከተማ በ36 ነጥብ ሁለተኛ፣ ድሬዳዋ ከተማ በ25 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዘዋል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው ጨዋታ ሸገር ከተማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ሸገር ከተማ በ22 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዟል። ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ28 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
አርባምንጭ ከተማ እና ነገሌ አርሲ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቋል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተደረገው ጨዋታ በፍቅር ግዛቸው ለአርባምንጭ ከተማ፣ ዳዊት ተፈራ ለነገሌ አርሲ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
አርባምንጭ ከተማ በ13 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል።
አዲስ አዳጊው ነገሌ አርሲ በ36 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።