ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መሪው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ነጥብ ጣለ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ14ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር የሁለተኛ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተደርገዋል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና መቻል ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።



የሊጉ መሪ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ነጥቡን ወደ 37 ከፍ አድርጓል። ከተከታዩ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለውን የነጥብ ልዩነት የማስፋት እድል አልተጠቀመበትም።

መቻል በ30 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።



በሌላ መርሐ-ግብር ድሬዳዋ ከተማ ባህርዳር ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ኤልሳ መኮንን በ56ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥራለች።

ድሬዳዋ ከተማ በ16 ነጥብ ደረጃውን ከ9ኛ ወደ 8ኛ ከፍ አድርጓል።

ባህር ዳር ከተማ በ10 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም