በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ ተዘጋጅተናል - ኢዜአ አማርኛ
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ ተዘጋጅተናል
ሚዛን አማን፤ የካቲት 14/2018 (ኢዜአ)፡- በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን በቤንች ሸኮ ዞን ኢዜአ ያነጋገራቸው ሴቶች ተናገሩ።
የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሻለ ሀሳብ ማቅረብ ላይ በማተኮር የሀገሪቱን የዴሞክራሲ ልምምድ ማጠናከር እንደሚገባቸውም ተገልጿል።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የትግራይ ክልል ሕዝብ ይበጁኛል የሚላቸውን ወኪሎቹ በነፃነት ለመምረጥ የሚያስችለው ወሳኝ መድረክ ነው
ምርጫ ቦርድ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመወዳደር የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመወዳደሪያ ምልክት ይፋ አደረገ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ግንቦት ወር ለሚካሔደው 7ኛ ጠቅላላ ምርጫ የተለያዩ ዝግጅቶችን በማድረግ ላይ መሆኑ ይታወቃል።
የምርጫው ሂደት ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ሚና ካላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች መካከል ሴቶች ዋነኞቹ ናቸው።
በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ነዋሪ የሆኑት መምህርት ትዕግሥት ኡኩሞ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ምርጫ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ይበጀናል ያልነውን የምንወክልበት በመሆኑ የነቃ ተሳትፎ ለማድረግ ተዘጋጅተናል ብለዋል።
ለዚህም ለሀገር ልማት፣ ለሴቶች ሁለተናዊ ተጠቃሚነት የሚሰራ ተፎካካሪ ፓርቲን በነፃነት ለመምረጥ የሚያስችላቸውን ካርድ ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ነው የሚገልጹት።
ዘንድሮ ኢትዮጵያ የምታካሂደው 7ኛ ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅም ሴቶች ከቤተሰብ ጀምሮ ያለንን ሚና ማጠናከር ይጠበቅብናል ነው ያሉት።
የመራጮች የምዝገባ ቀንን በጉጉት እየጠበቁ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የከተማዋ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ዘሪቱ በቀለ ናቸው።
ምርጫ የዲሞክራሲ ልምድን የሚያጎለብት በመሆኑ እኔም ሆንኩ ቤተሰቤ ሀገርን ወደ ተሻለ እድገት የሚወስድ ፓርቲን ለመምረጥ የነቃ ተሳትፎ እናደርጋለን ነው ያሉት።
ከምንም ነገር በፊት ቀዳሚ መሆን ያለበት የሀገር ሰላም በመሆኑ ሴቶች በየአካባቢያችን የተረጋጋ የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዲኖር እንሰራለን ነው ያሉት።
ፍትሐዊና ነጻ ምርጫ ማካሔድ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት መከበርና ገጽታ ግንባታ ትልቅ ሚና እንዳለው በመረዳት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሀገርን እያሰቡ ሊሰሩ እንደሚገባም አመልክተዋል።
የከተማዋ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ መሰለች ፍቃዱ፤ ሴቶች መንግስት በፖለቲካ ዘርፍ እኩል ተሳታፊ እንዲሆኑ የፈጠረላቸውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በምርጫው ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።