ቀጥታ፡

ቼልሲ ዌስትሃም ዩናይትድን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ አራተኛ ከፍ አደረገ

አዲስ አበባ፤ ጥር 23/2018 (ኢዜአ)፦‎ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት  ቼልሲ ከመመራት ተነስቶ ዌስትሃም ዩናይትድን 3 ለ 2 አሸንፏል።
አርሰናል ሊድስ ዩናይትድን በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናከረ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከባህርዳር ከተማ ጋር አቻ ተለያየ

ማምሻውን በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጃሮድ ቦውን በ7ኛው እና ክሪሴንሲዮ ሳመርቪል በ36ኛው ደቂቃ ባስቋጠሯቸው ግቦች ዌስትሃም ዩናይትድ 2 ለ 0 መምራት ችሎ ነበር።



ጆአኦ ፔድሮ በ57ኛው፣ ማርክ ኩኩሬላ በ70ኛው እና ኢንዞ ፈርናንዴዝ በ92ኛው ደቂቃ ያስቆጠሯቸው ግቦች ቼልሲን አሸናፊ አድርጓል።

የዌስትሃም ዩናይትዱ ተከላካይ ጂን-ክሌር ቶዲቦ በ101ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።



በሊጉ 11ኛ ድሉን ያስመዘገበው ቼልሲ በ40 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል።

የሁለት ግብ መሪነቱን አሳልፎ የሰጠው ዌስትሃም ዩናይትድ በ20 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

በውድድር ዓመቱም 14ኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም