አርሰናል ሊድስ ዩናይትድን በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናከረ - ኢዜአ አማርኛ
አርሰናል ሊድስ ዩናይትድን በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናከረ
አዲስ አበባ፤ ጥር 23/2018 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ24ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር አርሰናል ሊድስ ዩናይትድን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።
ማምሻውን በኢላንድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማርቲን ዙቢሜንዲ፣ ቪክቶር ዮኮሬስ፣ ጋብርኤል ጄሱስ እና የሊድስ ዩናይትዱ ግብ ጠባቂ ካርል ዳርሎው በራሱ ላይ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው አርሰናል በ53 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል። ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት በጊዜያዊነት ወደ ሰባት ከፍ አድርጓል።
መድፈኞቹ በሊጉ 16ኛ ድላቸውን አስመዝግበዋል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሊድስ ዩናይትድ በ26 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል።
በሌሎች መርሐ-ግብሮች ቦርንማውዝ ዎልቭስን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ፣ ብራይተን እና ኤቨርተን አንድ አቻ ተለያይተዋል።