ቀጥታ፡

ማንችስተር ሲቲ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል

አዲስ አበባ፤ ጥር 16 /2018 (ኢዜአ)፦‎ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ማንችስተር ሲቲ ዎልቭስን 2 ለ 0 አሸንፏል። 

ማንችስተር ሲቲ ከዎልቭስ ጋር ይጫወታል

ዌስትሃም ዩናይትድ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል

ማምሻውን በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኦማር ማርሙሽ እና አንቶዋን ሴሜኒዮ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።


 

አዲስ ፈራሚው ሴሜኒዮ በሲቲ ማልያ በአራተኛ ጨዋታው ሶስተኛ ግቡን አስቆጥሯል። ተጫዋቹ በሲቲ መልካም ጅማሮ አድርጓል።

ከክሪስታል ፓላስ ለማንችስተር ሲቲ የፈረመው ማርክ ጌሂ የመጀመሪያ ጨዋታውን አከናውኗል።

ከአራት ጨዋታዎች የድል አልባ ጉዞ በኋላ ማንችስተር ሲቲ ወደ ድል የተመለሰ ሲሆን በ46 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። በውድድር ዓመቱ 14ኛ ድሉን አስመዝግቧል።

ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት በጊዜያዊነት ወደ አራት ዝቅ አድርጓል።

በአንጻሩ በሊጉ 17ኛ ሽንፈትን ያስተናገደው ዎልቭስ በስምንት ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።


 

በሌሎች ጨዋታዎች ፉልሃም ብራይተንን 2 ለ 1 ሲያሸንፍ በርንሌይ እና ቶተንሃም ሆትስፐርስ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም