ቀጥታ፡

ዌስትሃም ዩናይትድ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል

አዲስ አበባ፤ ጥር 16 /2018 (ኢዜአ)፦‎ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ዌስትሃም ዩናይትድ ሰንደርላንድን 3 ለ 1 አሸንፏል። 

በለንደን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ክሪሴንሲዮ ሳመርቪል እና  ማቲውስ ፈርናንዴዝ በጨዋታ ጃሮድ ቦወን በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። 


 

ብሪያን ብሮቤይ ለሰንደርላንድ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። 

በሊጉ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ዌስትሃም ዩናይትድ በ20 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ድሉን አስመዝግቧል።

ዌስትሃም ዩናይትድ ከዋርጅ ቀጣና ለመውጣት እያደረገ ባለው ትግል ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል። 17ኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ኖቲንግሃም ፎረስት ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ዝቅ አድርጓል።


 

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሰንደርላንድ በ33 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም