ነጌሌ አርሲ እና ወላይታ ድቻ አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ነጌሌ አርሲ እና ወላይታ ድቻ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ነገሌ አርሲ እና ወላይታ ድቻ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ገ/መስቀል ዱባለ በ83ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ ነገሌ አርሲ መሪ ሆኗል።
በፕሪሚየር ሊጉ ነጌሌ አርሲ ከወላይታ ድቻ ሸገር ከተማ ከፋሲል ከነማ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ
ካርሎስ ዳምጠው በ94ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠረው ግብ ለወላይታ ድቻ አንድ ነጥብ አስገኝቷል።
ውጤቱን ተከትሎም አዲስ አዳጊው ነገሌ አርሲ በ26 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
ከሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነትም ወደ አንድ ዝቅ የማድረግ ዕድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
በሊጉ አምስተኛ ተከታታይ ድሉን የማስመዝገብ ሙከራውም አልተሳካም።
ወላይታ ድቻ በ13 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፤ ቡድኑ ባለፉት አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።