ሸገር ከተማ እና ፋሲል ከነማ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ሸገር ከተማ እና ፋሲል ከነማ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሸገር ከተማ እና ፋሲል ከነማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የፋሲል ከነማው የአማካይ ተጫዋች አቤኔዘር ዮሐንስ በ72ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።
ውጤቱን ተከትሎ ሸገር ከተማ በ15 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ስድስት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።
ፋሲል ከነማ በ26 ነጥብ ደረጃውን ከሶስተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል።
ከሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነትም ወደ አንድ ዝቅ የማድረግ እድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል።