ባህር ዳር ከተማ ከአምስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመለሰ - ኢዜአ አማርኛ
ባህር ዳር ከተማ ከአምስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመለሰ
አዲስ አበባ፤ ጥር 2/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ባህር ዳር ከተማ መቻልን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፍቅረሚካኤል ዓለሙ በ57ኛው እና ግርማ ዲሳሳ በ68ኛው ደቂቃ ላይ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ተጠባቂው የፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ
ኢትዮጵያ የምትሳተፍበት 46ኛው የዓለም አትሌቲክስ የሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ዛሬ ይካሄዳል
መሐመድ አበራ በ94ኛው ደቂቃ ለመቻል ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ከአምስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ባህር ዳር ከተማ በ19 ነጥብ ከነበረበት 12ኛ ደረጃ ወደ 9ኛ ከፍ ብሏል። በሊጉ አራተኛ ድሉን አስመዝግቧል።
በሊጉ ሶስተኛ ተከታታይ ሽንፈቱን ያስተናገደው መቻል በ20 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።
በውድድሩ ዓመቱ የተሸነፈው ጨዋታ ብዛት አራት ደርሷል።