በተጠባቂው ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በተጠባቂው ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ጥር 1/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሃዋሳ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ሃዋሳ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው
አማድ ዲያሎ - የአፍሪካ እግር ኳስ ብሩህ ተስፋ
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሽመልስ በቀለ በ46ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
ከሁለት የሊጉ ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ሃዋሳ ከተማ በ24 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉ ሰባተኛ ድሉንም አስመዝግቧል።
በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ19 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።ቡድኑ ባለፉት ስድስት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሃ ግብር ድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ምሽት 12 ሰዓት ላይ መቀሌ 70 እንደርታ ከሸገር ከተማ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።