ወላይታ ድቻ እና አርባምንጭ ከተማ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ወላይታ ድቻ እና አርባምንጭ ከተማ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 20/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ወላይታ ድቻ እና አርባምንጭ ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ጨዋታው በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተደርጓል።
ውጤቱን ተከትሎ ወላይታ ድቻ በ11 ነጥብ ከ17ኛ ወደ 16ኛ ደረጃውን ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል።
አርባምንጭ ከተማ በስድስት ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል።
አርባምንጭ ከተማ በሊጉ እስከ አሁን ምንም ጨዋታ ያላሸነፈ ብቸኛው ክለብ ነው።