ፋሲል ከነማ የሊጉ መሪ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
ፋሲል ከነማ የሊጉ መሪ ሆነ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 20/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አንዋር ሙራድ በ62ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በሊጉ ስድስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ፋሲል ከነማ በ24 ነጥብ የሊጉን መሪነት ከሲዳማ ቡና በጊዜያዊነት ተረክቧል።
ፋሲል ከነማ በሊጉ ምንም ሽንፈት ያላስተናገደ ብቸኛው ክለብ ነው።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ20 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።