የሊጉ መሪ አርሰናል ከብራይተን ጋር ይጫወታል - ኢዜአ አማርኛ
የሊጉ መሪ አርሰናል ከብራይተን ጋር ይጫወታል
አዲስ አበባ፤ታህሳስ 18/2018(ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ ሰባት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
በ"ቦክሲንግ ደይ" መርሃ ግብ ማንችስተር ዩናይትድ ኒውካስትል ዩናይትድን አሸነፈ
በአፍሪካ ዋንጫ ናይጄሪያ ከቱኒዚያ ሴኔጋል ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ
ምሽት 12 ሰዓት ላይ አርሰናል ብራይተንን በኤምሬትስ ስታዲየም ያስተናግዳል።
አርሰናል ሊጉን በ39 ነጥብ እየመራ ነው። ብራይተን በ24 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 ላይ ኖቲንግሃም ፎረስት ከማንችስተር ሲቲ በሲቲ ግራውንድ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ኖቲንግሃም ፎረስት በ18 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዟል። ማንችስተር ሲቲ በ37 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች በተመልካቾች ትኩረትን አግኝተዋል።
ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ላይ ቼልሲ ከአስቶንቪላ በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታም ይጠበቃል።
ቼልሲ በ29 ነጥብ አራተኛ እና አስቶንቪላ በ36 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
በሌሎች መርሃ ግብሮች ሊቨርፑል ከዎልቭስ፣ ዌስትሃም ዩናይትድ ከፉልሃም፣ ብሬንትፎርድ ከቦርንማውዝ እና በርንሌይ ከኤቨርተን በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።