ኢትዮ ኤሌክትሪክ ምድረገነት ሽሬን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ምድረገነት ሽሬን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ አደረገ
አዲስ አበባ፤ ታኅሣስ 16/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ11ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ምድረገነት ሽሬን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አቤል ሀብታሙ በ95ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ
በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ20 ነጥብ ደረጃውን ከአራተኛ ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በሊጉ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ምድረገነት ሽሬ በ14 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።