ቀጥታ፡

አልጄሪያ አፍሪካ ዋንጫን በድል ጀምራለች

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 15/2018(ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ አምስት ሁለተኛ ጨዋታ አልጄሪያ ሱዳንን 3 ለ 0 አሸንፋለች።
 
ማምሻውን በፕሪንስ ሙላይ አብደላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሪያድ ማህሬዝ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ኢብራሂም ማዛ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።  

የአፍሪካ ዋንጫ እውነታዎች

በአፍሪካ ዋንጫ ልንመለከታቸው የሚገቡ አምስት ተጫዋቾች

የሱዳኑ ሳላህ አዲል በ39ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። 

ውጤቱን ተከትሎ አልጄሪያ ምድብ አምስትን በሶስት ነጥብ መምራት ጀምራለች። 

በትውልድ አልጄሪያዊ በዜግነት ፈረንሳዊ የቀድሞ ተጫዋች ከልጁ ሉካ ጋር በመሆን ጨዋታውን በስታዲየም በመገኘት ተከታትሏል። 

የአልጄሪያው ሪያድ ማህሬዝ በሁለተኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል የዘንድሮው ውድድር ፈጣን ጎል ሆኗል።

የ34 ዓመቱ ተጫዋች በአፍሪካ ዋንጫው ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ ሰባት ከፍ አድርጓል። 

በአጠቃላይ ለአልጄሪያ ያስቆጠራቸው ግቦች ብዛት 36 ደርሰዋል። 

በምድብ አምስት ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ቡርኪናፋሶ ኢኳቶሪያል ጊኒን 2 ለ 1 አሸንፋለች።

#Ethiopian_News_Agency 
#ኢዜአ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም