ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ተወያዩ 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 14/2018 (ኢዜአ)፦   ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ውይይት አድርገዋል። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ የኬንያ ፕሬዝደንት ዊልያም ሳሞይ ሩቶን ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት መቀበላቸውን ገልጸዋል። 


 

ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጥልቅ፣ ታሪካዊ እና ወንድማዊ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው ብለዋል። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼኽ ሞሃሙድ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ይፋዊ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት አድርገዋል

በውይይቱ የሁለትዮሽ ግንኙነቱ በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ መለዋወጣቸውን አመልክተዋል። 


 

ይኽም በሰላም እና መረጋጋት፣ ብሎም በአፍሪካ መር መፍትሔዎች ላይ ያለንን የወል ጽኑ አቋም የሚያሳይ ነበር ሲሉ ገልጸዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም