ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼኽ ሞሃሙድ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼኽ ሞሃሙድ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 10/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሀሰን ሼኽ ሞሃሙድ ጋር ዛሬ ውይይት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የሶማሊያ ፕሬዝዳንትን ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት መቀበላቸውን ገልጸዋል።
ባለፈው አንድ አመት እየሰራንባቸው የቆየነውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ውይይቶች በመቀጠል ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው እንደገለጹት የሃሳብ ልውውጣችን የወል የቅድሚያ ጉዳዮቻችንን ለመከወን ብሎም ለጠንካራ ግንኙነት፣ ቀጣናዊ መረጋጋት እና ለልማት ያለንን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያፀና ነበር።