ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ይፋዊ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት አድርገዋል - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ይፋዊ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት አድርገዋል
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 7/2018 (ኢዜአ):- ለህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ይፋዊ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት አድርገናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ከህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ውይይት ካደረግን በኋላ ከልዑካን ቡድኖቻችን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል ብለዋል።
በውይይታችን በኢትዮጵያ እና ህንድ መካከል እያደገ የመጣውን ትብብር እና የወል ቅድሚያዎች የሚያንፀባርቁ አዳዲስ የትብብር መስኮችን ቃኝተናል ሲሉም ገልጸዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል በጉምሩክ የጋራ አስተዳደር ድጋፍ፣ በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳታ ማዕከል ምስረታ የመግባቢያ ሥምምነቶችን እንዲሁም በአለምአቀፍ የሰላም ማስከበር ላይ ያለ ቁርጠኝነትን የሚያሳይ እና የሚያጠናክረውን የተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ሥራ የመግባቢያ ሥምምነት የፊርማ ሥነሥርዓት ላይም መገኘታቸውን አስታውቀዋል።
ህንድ የኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ አጋር ስትሆን የዛሬዎቹ ውይይቶች እና ሥምምነቶችም ለጋራ ጥቅም በተለያዩ ዘርፎች ያሉንን ትብብሮች ለማስፋት ያለንን የጋራ ቁርጠኛ አቋም ያሳያሉ ሲሉም ነው የገለጹት።