ሀገሩን የሚወድ የተሰለፈበትን ዓላማ የተረዳና ፕሮፌሽናል የሆነ ብሄራዊ የመከላከያ ሠራዊት ተገንብቷል -ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ 

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ(ኢዜአ)፦ሀገሩን የሚወድ የተሰለፈበትን ዓላማ የተረዳና ፕሮፌሽናል የሆነ ብሄራዊ የመከላከያ ሠራዊት ተገንብቷል ሲሉየኢፌዴሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ገለጹ። 

ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ከሠራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል። 

በውይይቱም ራሱን በየጊዜው እየገመገመ በሁለንተናዊ መስኩ እያበቃ የመጣ ሀገሩን የሚወድና የተሰለፈበትን ዓላማ ጠንቅቆ የተረዳ ፕሮፌሽናል ሠራዊት መገንባቱን ገልፀዋል። 

የመከላከያ ሠራዊት በተሻለ ዝግጁነትና ቁመና ላይ ይገኛል - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

በሀገራችን የመጣውን ለውጥ ተከትሎ በተቋሙ የተሰራው ሪፎርም በርካታ ውጤቶች ለማስመዝገብ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ማስቻሉንም አንስተዋል። 

ሀገራችን በታሪኳ በዚህ ደረጃ ብዛትና ጥራት ያለው የፕሮፌሽናል ሰራዊት ገንብታ አታውቅም ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ፣ ሀገሩንና ሙያውን የሚወድ የሚሰጠውን ግዳጅ በአነስተኛ ኪሳራ የመፈፀም ብቃት ያለው ሀይል ተገንብቷል ብለዋል። 


 

ሠራዊቱ ሀገርን ከብተና ከማዳን ባለፈ የሀገራችንን ሰላም ፣ ብልፅግናና ዲሞክራሲን ለማረጋገጥ እየተደረገ ባለው ጥረት ያስመዘገባቸው ድሎች በታሪክ ሲዘከር የሚኖር መሆኑንም ገልፀዋል። 

በተገኙ ድሎች ባለመኩራራት የተመዘገቡ ሁለንተናዊ ድሎች አጠናክሮ ለማስቀጠልና የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብም በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም አረጋግጠዋል። 

በተሳሳተ ስሌት ወደጫካ ገብተው የነበሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች የሰላምን መንገድ በመከተል እጃቸውን ለሠራዊቱ መስጠታቸውን የገለፁት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣በተለያየ ቦታ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ፅንፈኞች ከመቼውም ጊዜ በላይ መዳከማቸውና የሰላምን ጥሪ ባልተቀበሉት ላይ የተጀመሩት የመለቃቀም ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል። 

የሀገራችንን እድገትና ብልፅግና ማስቀጠል የሚችል አስተማማኝ የሰላም ሀይል ማፍራት ተችሏል- ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

በጦር ሜዳ ማሸነፍ ያቃታቸው የሀገርና የህዝብ ጠላቶች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የውሸት ትርክት በመፍጠር በተቋሙ ፣ በአመራሩና በሰራዊቱ ላይ የስነልቦና ጦርነት በመክፈት ለማጠልሸት ቢሞክሩም በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት በማጣታቸው ለሠራዊታችን የሚደረገው ህዝባዊ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል። 

በምድር ፣ በባህር ፣ በአየር እና በሳይበር ሀይል የተደራጀው ሠራዊታችን ዘመኑ የደረሰበት የቴክኖሎጂና የውጊያ አቅም ላይ ለማድረስ እንደተቻለ መግለጻቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመለክታል።

ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ በተሳሳተ ስሌት ውጊያ ለመክፈት የሚሞክሩ ሀይሎችን በአነስተኛ ኪሳራና በአጭር ጊዜ ለመደምሰስ የሚያስችል ሁለንተናዊ ዝግጁነት መኖሩንም አረጋግጠዋል።
 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም