ቀጥታ፡

የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ ጋር የሚያደርጋቸውን የትብብር ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋገጠ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 23/2016 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ ጋር የሚያደርጋቸውን የትብብር ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ከአውሮፓ ሕብረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን ጋር ተወያይተዋል። 

የአውሮፓ ሕብረት ለኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ የልማት አጋር ነው

በውይይታቸውም የአውሮፓ ሕብረት ለኢትዮጵያ ቁልፍ ስትራቴጂካዊ አጋር መሆኑን የተናገሩት ዶክተር ፍጹም ሕብረቱ እስከ አሁን ላደረጋቸው የትብብር ተግባራት ምስጋና አቅርበዋል።

የእዚሁ ትብብር አካል የሆነው የ650 ሚሊዮን ዩሮ የድጋፍ ማዕቀፍ ይፋ በመሆኑም ሚኒስትሯ ምስጋና ችረዋል።

የመካከለኛ ዘመን የሶስት ዓመቱን የኢንቨስትመንት እቅድ እንዲሁም የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ሁለት ይዘቶችን በተመለከተ ሚኒስትሯ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ሕብረቱም ትብብሮችን እንዲያደርግ እንደሚያስችለው አብራርተዋል።

አገራት በአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ ኢትዮጵያ በትኩረት እየሰራች ነው

የአውሮፓ ሕብረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን በበኩላቸው  ህብረቱ በአየር ንብረት ለውጥ መከላከልና ግብርና ስራዎች፣ ብዝሃ ሕይወት ጥበቃ፣ አረንጓዴ ልማት ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም በአካባቢ ጥበቃና ታዳሽ ኃይል ልማት፣ ለሰው ኃይል ልማት ፣ በጤና ፣ በመልካም አስተዳደር፣ ሰላም ግንባታና የዴሞክራሲ ልማት ስራዎች ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር የሚያጠናክርባቸው ዘርፎች መሆናቸውን ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም