የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች በምርጫው ንቁ ተሳታፊ የሚያደርጋቸውን የምርጫ ካርድ እየወሰዱ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች በምርጫው ንቁ ተሳታፊ የሚያደርጋቸውን የምርጫ ካርድ እየወሰዱ ነው
ሆሳዕና፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ መስጠት የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ እየወሰዱ መሆኑን የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
በሀረሪ ክልል ወጣቶች በቅድመ ምርጫው የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ ነው
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በመጪው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሔደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ በዲጂታል እና በማንዋል እየተከናወነ ይገኛል፡፡
የሆሳዕና ከተማ ነዋሪው ብሩክ ታደሰ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ መስጠት የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ ወስደዋል፡፡
የምርጫ ካርድን በወቅቱ በመውሰድ ህገ መንግስታዊ መብትን መጠቀም እንደሚገባ በማመን የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት የፖለቲካ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙሃን የሚያደርጉትን ክርክር በማድመጥና የሚያቀርቡትን ሀሳብ በመገንዘብ የሀገሪቱን ቀጣይ እጣ ፈንታ የተሻለ ማድረግ ይችላል ላሉት ፓርቲ ድምጽ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
ሌላው የከተማዋ ነዋሪ ሰናክሪም ዘውገ በበኩላቸው፤ የምርጫ ካርድ በመውሰድ የሚወክላቸውን አካል ለመምረጥ የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን ነው የጠቆሙት።
በምርጫው የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የሀገሪቱን እድገትና ልማት ማስቀጠል የሚችል አካልን ወደ ስልጣን ለማምጣት ማቀዳቸውንም አስታውቀዋል።
የሴቶችን መብት ከማስጠበቅና ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አኳያ የተጀመሩ ጥረቶችን ለማጠናከር በምርጫው የነቃ ተሳትፎ ማድረግ የሚያስችለኝን የመራጭነት ካርድ አውጥቻለው የምትለው ደግሞ ወጣት ፀጋነሽ ገብረ ሚካኤል ናት፡፡