ቀጥታ፡

በሀረሪ ክልል ወጣቶች በቅድመ ምርጫው የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ ነው

ሀረር፤ መጋቢት 15/2018(ኢዜአ)፦ በሀረሪ ክልል ወጣቶች በቅድመ ምርጫው የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን የክልሉ ወጣቶች ፌዴሬሽን ገለጸ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው ሰሌዳ መሠረት ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በመጪው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለማከናወን የመራጮች ምዝገባና ሌሎች የቅድመ ምርጫ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ 

የሐረሪ ክልል ወጣቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ወጣት ረስተም ዑመር ከኢዜአ ጋር በነበረው ቆይታ እንደገለፀው፤ ፌዴሬሽኑ በተለያዩ ዘርፎች የወጣቶችን ክህሎትና ግንዛቤ ከማጎልበት አኳያ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ነው። 

ወጣቱ በተለይ በትምህርትና በጤና ተሳትፎ፣ የአካባቢ ሰላምን በማስጠበቅና በሌሎች የበጎ ፈቃድ ተግባራት ግንዛቤ ከመፍጠር ባለፈ ንቁ ተሳታፊ እየሆነ እንደሚገኝ ጠቁሟል። 

በአሁኑ ወቅትም ወጣቶች በምርጫው በንቃት እንዲሳተፉ ከማድረግ ባለፈ ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጿል። 

በቀጣይ በግንቦት ወር በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ከማስገንዘብ ባለፈ በታዛቢነት እንዲሳተፉ ወጣቶችን የመለየት ሥራ መከናወኑን ገልጸዋል። 

በዚህም ወጣቶች በክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች ምርጫው ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ነጻ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የታዛቢነት ሚናቸውን ይወጣሉ ነው ያሉት። 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም