የ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ለአፋር ህዝብ የተሰጠ ትልቅ ክብር ነው - ኢዜአ አማርኛ
የ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ለአፋር ህዝብ የተሰጠ ትልቅ ክብር ነው
አዲስ አበባ፤መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ)፦የ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ለአፋር ህዝብ የተሰጠ ትልቅ ክብር ነው ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገለጹ።
የ ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ለአካባቢው ማህበረሰብ ሰፊ የስራ ዕድልን የፈጠረ ነው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ትናንት በፍራፍሬ እና በደን ዛፎች የተከበበውን የ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ መርቀው ስራ አስጀምረዋል።
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በምርቃቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር አፋር የሰው ዘር መነሻ፣በተፈጥሮ ሀብት የታደለች እና በርካታ ቱሪስቶችን በመሳብ የሚታወቅ ክልል መሆኑን አመልክተዋል።
የ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ለአፋር የተሰጠ ትልቅ ክብር መሆኑን ገልጸው፥ህዝቡም ትርፍ እና ጥቅም የሚያገኝበት ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለፕሮጀክቱ እውን መሆን ላደረጉት ድጋፍ እና ጥረት ርዕሰ መስተዳድሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
እንግዳ ተቀባዩ የአፋር ህዝብ የ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ለመጠበቅ፣ለማቆየት እና ቱሪስት ለመሳብ ይሰራል ነው ያሉት።
የአፋር ክልል ሰመራ አቅራቢያ የሚገኝ በውሃ ሀብት የታደለ ስፍራን ጨምሮ የተለያዩ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለማልማት እንደሚሰራ አመልክተዋል።
ሁሉም አካላት የሰው ዘር ቅሪተ አካል ሉሲ የተገኘባትን አፋር ክልል በማልማት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።