የ ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ለአካባቢው ማህበረሰብ ሰፊ የስራ ዕድልን የፈጠረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የ ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ለአካባቢው ማህበረሰብ ሰፊ የስራ ዕድልን የፈጠረ ነው
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 13/2018 (ኢዜአ)፦ የ ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ለአካባቢው ማህበረሰብ ሰፊ የስራ ዕድልን የፈጠረ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ሁሉን አቀፍ ምድራዊ ገነት!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት በፍራፍሬ እና በደን ዛፎች የተከበበውን የ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ መርቀው ስራ አስጀምረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፤ የ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ለአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ያለው ቅርበት የጎብኝዎችን ምቾት ከመጨመሩም በላይ ለአካባቢው ማህበረሰብ ሰፊ የስራ ዕድልን የፈጠረ ነው ብለዋል።