የቅድሚያ ለሴቶች የጎዳና ላይ ሩጫ በልዩ ድምቀት ተከናውኗል - ኢዜአ አማርኛ
የቅድሚያ ለሴቶች የጎዳና ላይ ሩጫ በልዩ ድምቀት ተከናውኗል
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 13/2018 (ኢዜአ)፦በመዲናዋ የቅድሚያ ለሴቶች የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በልዩ ድምቀት መከናወኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ብርቅነሽ ደሴ የቅድሚያ ለሴቶች የአምስት ኪሎ ሜትር ውድድርን አሸነፈች
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ ሴቶች በጥበብ ይኖራሉ፤ በራስ መተማመን ይሠራሉ፤በራስ መተማመን ይሮጣሉ፤ ይችላሉም! ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን የአገራችንን ብልፅግና እናረጋግጣለን ብለዋል።
ከንቲባዋ ዛሬ ማለዳ 16 ሺህ ሴቶች የተሳተፉበትን የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ማስጀመራቸውን ገልጸዋል።
በታላቁ ሩጫ አዘጋጅነት በየዓመቱ የሚካሄደው ይህ ውድድር፤ ዘንድሮ በኮሪደር ልማት አማካኝነት እጅግ ውብ፣ ምቹ እና ለከተማችን አዲስ ዘመናዊ መልክ ባላበሰው በቦሌ - አትላስ - ኡራኤል መንገድ ላይ በልዩ ድምቀት መከናወኑን አመልክተዋል።