ብርነሽ ደሴ የቅድሚያ ለሴቶች የአምስት ኪሎ ሜትር ውድድርን አሸነፈች - ኢዜአ አማርኛ
ብርነሽ ደሴ የቅድሚያ ለሴቶች የአምስት ኪሎ ሜትር ውድድርን አሸነፈች
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 13/2018 (ኢዜአ)፦ አትሌት ብርነሽ ደሴ የ23ኛው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የቅድሚያ ለሴቶች የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር አሸናፊ ሆናለች።
ውድድሩ ዛሬ ረፋድ ላይ መነሻውን መድረሻውን ቦሌ አትላስ ሆቴል በማድረግ ተካሂዷል።
በሁነቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣የውድድሩ አምባሳደር አትሌት መሰረት ደፋር እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
ብርነሽ ደሴ ለተከታታይ ሁለተኛ ዓመት የውድድሩ አሸናፊ ሆናለች።
ሮቤ ዲዳ በሁለተኛነት ስታጠናቅቅ ሰናይት ጌታቸው ሶስተኛ ወጥታለች።
በውድድሩ ላይ 16 ሺህ ሴቶች፣ ከ150 በላይ አትሌቶች እና 25 ተምሳሌት ተብለው የተሰየሙ ሴቶች ተሳትፈዋል።
23ኛው ቅድሚያ ለሴቶች የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ "በመላ ኑሪ በኮንፊደንስ ሩጪ" በሚል መሪ ሀሳብ ተደርጓል።
ውድድሩ የዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን በማስመልከት ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።