ቀጥታ፡

በክልሉ የሰብል ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን ለመቻል የተያዘውን ግብ ለማሳካት የተጀመሩ ተግባራት ይጠናከራሉ

ባህርዳር ፤ መጋቢት 6 /2018 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የሰብል ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን ለመቻል የተያዘውን ግብ ለማሳካት የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

ለ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የላቀ ሀገራዊ ራዕይን በሚያሳካ መልኩ ዝግጅት እየተደረገ ነው

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አጀበ ስንሻው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የክልሉን የሰብል ምርታማነት በማሳደግ በምግብ ራስን ለመቻል የተያዘውን ግብ ለማሳካት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ይጠናከራሉ።

በዚህም ለመጪው የምርት ዘመን ከ8 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ግዢ በመፈጸም ከ3 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የሚሆነው ወደ ወደብ መድረሱን ገልጸዋል።


 

ወደብ ከደረሰው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥም እስካሁን ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የሚሆነውን ወደ ክልሉ በማስገባት የማሰራጨት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

እየቀረበ ያለው የአፈር ማዳበሪያም የሰብል ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተያዘውን ግብ ለማሳካት የሚያስችል መሆኑንም አመልክተዋል።

በክልሉ ህብረት ስራ ኮሚሽን የግብዓትና ግብይት ዳይሬክተር አቶ ዓለምዘውድ ስሜነህ በበኩላቸው፤ ወደ መጋዝኖች የደረሰውን ማዳበሪያ በወቅቱ ለአርሶ አደሩ ተደራሽ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።


 

ወደ ዩኒየኖች መጋዝኖች የደረሰውን ማዳበሪያ ወደ መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበራት በማጓጓዝ ፈጥኖ ለአርሶ አደሩ የማሰራጨት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

ለመጪው መኸር 841 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማሰራጨት ግብ ይዞ እየሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የአድማስ ዩኒየን ስራ አስኪያጅ አቶ መሰረት ወርቄ ናቸው።


 

‎በመጋዘን ያለውን ጨምሮ እስካሁን በዞኑ 526 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ቀድመው ለሚዘሩ ሰብሎች ለማሰራጨት እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

‎ባለፈው ዓመት ወደ ክልሉ ከገባው 7 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ከ7 ሚሊዮን ኩንታል የሚልቀው ጥቅም ላይ እንደዋለም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም