በሴኡል ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ አሸነፉ - ኢዜአ አማርኛ
በሴኡል ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ አሸነፉ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 6/2018 (ኢዜአ)፦ 96ኛው የሴኡል ማራቶን ዛሬ ማለዳ ተካሄዷል።
በወንዶች አትሌት ሀፍቱ ተከሉ 2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ከ23 ሴኮንድ አንደኛ ወጥቷል።
አትሌት ሀፍቱ ውድድሩን በአራት ዓመት ውስጥም ለሁለተኛ ጊዜ አሸንፏል።
ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ጌታነህ ሞላ ሁለተኛ ወጥቷል።
አትሌት ፀጋዬ ታደሰ አራተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል።
በሴቶቹ ውድድር ደግሞ አትሌት ሔቨን ኃይሉ 2 ሰዓት ከ19 ደቂቃ ከ10 ሴኮንድ በርቀቱ የግል ምርጥ ሰዓቷን አስመዝግባ አሸንፋለች።
አትሌት በቀለች ጉደታ 2ሰዓት ከ19 ደቂቃ ከ40 ሴኮንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀች ሲሆን የግል ምርጥ ሰዓቷን አሻሽላለች።
አትሌት ቦሰና ሙላቴ ሦስተኛ ወጥታለች።
እ.አ.አ በ1931 የተጀመረው የሴኡል ማራቶን በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ የተሰጠው የጎዳና ላይ ውድድር ነው።