ቀጥታ፡

የሲዳማ ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል መከበር ጀምሯል

 ሀዋሳ ፤ መጋቢት 6 /2018 (ኢዜአ)፦ የሲዳማ ዘመን መለወጫ  ፊቼ ጫምባላላ በዓል በሀዋሳ "ሶሬሳ ጉዱማሌ" መከበር  ጀምሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለ"ፊቼ ጫምባላላ" በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

በዓሉ በሚከበርበት ሃዋሳ "ሶሬሳ ጉዱማሌ" የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ከክልሉ ወረዳዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል ። 


 

የበዓሉ ተሳታፊ የሆኑ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ሁሉቃን ተሻግረው በመግባት ባህላዊውን የ"ቄጣላ" ስርዓት እያከናወኑ የአዲሱን አመት መግባት እያበሰሩ ነው።

"ቄጣላ" ሲዳማዎች ጥልቅ ስሜታቸውን ፣ ተስፋና ምኞታቸውን የሚገልጹበት የፊቼ ጫምባላላ ልዩ ኹነት ነው።

በአደባባይ የሚከበረው የሲዳማ  ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ አብሮነትን፣ ሰላምን፣ መረዳዳትንና ይቅርታን የሚያጠናክሩ እሴቶችን በውስጡ የያዘ የዓለም ቅርስ ነው።

ፊቼ ጫምባላላ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣  የሳይንስና ባህል ተቋም “ዩኔስኮ” በማይዳሰስ የሰው ልጅ ቅርስነት መመዝገቡ ይታወቃል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም