የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታውን ለማቀላጠፍ በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ሴቶች በንቃት ሊሳተፉ ይገባል - ኢዜአ አማርኛ
የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታውን ለማቀላጠፍ በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ሴቶች በንቃት ሊሳተፉ ይገባል
ሰመራ፤ መጋቢት 4/2018(ኢዜአ)፦የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታውን ለማቀላጠፍ በዘንድሮው ምርጫ ሴቶች በንቃት ሊሳተፉ እንደሚገባ የአፋር ክልል ሴት አመራሮች ተናገሩ።
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ካርዳችንን በመጠቀም የተሻለ ሃሳብ ያለውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል - ነዋሪዎች
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በምርጫ ጣቢያዎችና በበይነ መረብ የመራጮች ምዝገባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የአፋር ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኀላፊ ነስሮ ኡዳ እንዳሉት፤ የክልሉ ሴቶች በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት ሊሳተፉ ይገባል።
በተለይም የዴሞክራሲ ሰርዓት ግንባታውን ለማቀላጠፍና ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን በተሟላ ሁኔታ መለማመድ የሚቻለው ሴቶች በምርጫ ሂደት ላይ የሚያደርጉት ተሳትፎ ሲያሳድጉ መሆኑን ተናግረዋል።
በምርጫው ለመሳተፍ ከወዲሁ ካርድ ሊወስዱ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የአፋር ክልል ሴቶች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ፋጡማ ሃንፈሬ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ በዘንድሮው ምርጫ ሴቶች ተጠቃሚነታቸውንና ተሳታፊነታቸውን ያሳድጋል ብለው ያመኑትን ፓርቲ በንቃት መምረጥ ይጠበቅባቸዋል።
ለዚህም የመራጮች ካርድን በጊዜ በእጃቸው መያዝ እንደሚገባቸው ተናግረዋል።